Christian ዜማ Tube @christian_zema_tube Channel on Telegram

Christian ዜማ Tube

@christian_zema_tube


ወንጌል ያሸንፋል ወንጌል ይለውጣል ወንጌል ለሁሉም!

Christian ዜማ Tube (Amharic)

በቅደም መሰከረሚያዊ ለመሆንባለን 'Christian ዜማ Tube' የቴሌግራም አካባቢ ነው ፡፡ አንዳንድ አስተያየቶችን ከዛሬ ጋር ለማግኘት ያሉ የምሁመራሽ አካባቢዎችን ይዝናኑና ልዩነት ይሰጣል፡፡ 'Christian ዜማ Tube' በቴሌግራም ከፌቶናል ስህተት እንዳትጓዝ ልጆቻቸውን ለምኞታቸው እንደደንብ እና ደንቃቸውን እናህል እዝገባለን፡፡ ዝናኑም ሴት በቆሎ ወንጌልን ይሸናፍ እና ትክፏን ለመስጠት አንዳንዶች ነበር።

Christian ዜማ Tube

28 Dec, 07:54


ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሸ መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚል ርዕስ ከዘማሪት ሀና ተክሌ ጋር አምላካችንን ለማክበር እንገናኝ  ይህን የአምልኮ ድግስ ያዘጋጀው ኤፔክስ ኢቨንትስ ሲሆን ብቸኛ አጋር ኤልሀዳር ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነዉ #መሥዋዕት #hannatekle   #apexevent  #apexventures     #worship #protestant #christian #jesus #millenniumhall #christiantiktok

Christian ዜማ Tube

25 Dec, 18:23


#የስራው_ባለቤት_እግዚአብሔር_ነው።

እግዚአብሔር በውስጤ ያስቀመጠውን ሸክም ወደ ተግባር ለማውረድ 11 የሚሆኑ ሰዎች ከእነርሱም ውስጥ ግማሾቹ ቤተሰቦቼ የሆኑ ተሰብስበን ብሔራዊ አከባቢ በሚገኝ መምህራን ማህበር ካፌ ውስጥ ለተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያን መመስረት ምክንያት የሆነውን ፕሮግራም ከጀመርን እነሆ #አያ_አምስት_ዓመት ሆነን ይህ አገልግሎት ሲጀመር በእድሜም በአገልግሎት ልምድም ታናሽ ነበርኩ ነገር ግን ለአገልግሎት ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ የቆጠረኝ እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶልኝ በምህረቱ ደግፎኝ ስደክም እያበረታኝ ስዝል እያፀናኝ በፊቴ የወጡ ተግዳሮችን በሙሉ በእርሱ ብቃት አሳለፈኝ

እርሱ የስራው ባለቤት ነውና በመንግሰቱ እርሻ ላይ አብረውኝ በትህትና እና በልብ ቅንነት የሚያገለግሉ ወንድሞችና እህቶች ሰጠኝ በአገልግሎታችን ብዙዎች በመንግስቱ ወንጌል ተማርከው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጨመሩ ዕለት ዕለት እየተማሩ ደቀመዝሙር በመሆን እግዚአብሔር በሰጣቸው ፀጋ ለአገልግሎት ተሰማሩ እርሱ እግዚአብሔር አስጀምሮናልና በእርሱ እርዳታ አንድ ሁለት እያልን #25ኛ_ዓመት_የብር_እዮቤልዩን ለማክበር ደረስን የትላንት ጉዞአችንን ስናስብ “አቤንዔዘር” የምንለው የተፃፈውን እንብበን ብቻ ሳይሆን ረዳትነቱን በተግባር አይተነው ነው።

"ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።"
1ሳሙ 7:12

በዚህ አጋጣሚ ባለፉት #ሃያ_አምስት_ዓመታት በነበረን የአገልግሎት ጉዞ በተለያየ መንገድ አብራችሁን ለቆማችሁ በቅርብ በሩቅም ያላችሁ ሁሉ በያላችሁበት የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

በሁሉም አጥቢያዎች በታማኝነት እያገለገላችሁ ያላችሁ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ የቤተክርስቲያን ራስ እና ባላቤት የሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርካችሁ! ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።

መልካም #25ኛ_ዓመት_የብር_ኢዮቤልዩ_በዓል እንዲሆንልን እየተመኘው ለዚህ ከበረ በዓል እየተዘጋጁ ያሉ ፕሮግራሞች የተቃና እንዲሆን የተለመደው ትጋታችሁና ትብብራችሁን አይለየን።
በድጋሚ ሁላችንንም እንኳን አደረሳችሁ!!

ወንድማችሁ ፓስተር ሚካኤል ወንድሙ / ሚኪ/ ከዋሽንግተን ዲሲ

Christian ዜማ Tube

25 Dec, 18:22


https://youtu.be/R2uLcgd47bg?si=FFrDaQk_hwsqbCvt

Christian ዜማ Tube

25 Dec, 11:43


የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከወንጌላውያን የሚዲያ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን “የወንጌላውያን ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና” በሚል ርዕስ የወንጌላውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጾኖ ፈጣሪዎች ጋር ምክክር በተደረገበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ም/ቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ታምራት ታሪኩ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ልጆች ለሃጋአራችን ሰላም የራሳቸውን አስተዋጾኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ታምራት በመልዕክታቸው እያንዳንዱ ሰው ለሰላም የሚያበረክተው ጥቂት አስተዋጾኦ ሲተራቀም ለሀገራችን ሰላም ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ ወጣቶች ወንጌልን እና ሰላምን እኩል በመስበክ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ግርማ በበኩላቸው ማህበሩ ከተመሰረት ጀምሮ የአባላቱን አቅም ለመገነባት እየሰራ እንደሆነ አንስተው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ክርስቲያኖች ለሀገራችን ሰላም የራሳቸውን አበርክቶ ከፍ እንዲያደርጉ ይህ ሰልጠና በጋራ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የሰላም እና አድቮኬሲ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደቻሳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በሀገራችን የሰላም እና አድቮኬሲ እየሰራ ያለውን ስራ በማንሳት የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች በሰላም ስራ ከፍተኛ ስራ እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።

አቶ ደቻሳ ሚዲያ ያለውን አቀም ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን በመልካም ከተጠቀምን እንደ አጠቃቀማችን ለማህበረሰባችን የሚንሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ይሆናል በማለት እንደ ክርስቲያን ሰላምን አበክረን ልንሰብክ እና አስተዋጽዓችንን ከፍ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

ዮቲዩብ ፤ ፋስቡክ ፤ ቲክቶክ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰሩ ክርስቲያን ባለሞያዎች በበኩላቸው
ባላቸው አቅም አበርክቶአቸውን ከፍ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ በመድረኩ የጠቀሱ ሲሆን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መሰል ስልጠናዎች በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ ሌሎች ተጨማሪ ሰራዎችን እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ምንጭ : ክርስቲያን ቲዩብ

Christian ዜማ Tube

26 Jul, 07:15


Channel photo updated

Christian ዜማ Tube

12 Jul, 08:21


ስለ ኩሪፍቱ ቃለህይወት ዝም አንልም

Christian ዜማ Tube

12 Jul, 08:21


ስለ ኩሪፍቱ ቃለህይወት ዝም አንልም

Christian ዜማ Tube

12 Jul, 08:21


ስለ ኩሪፍቱ ቃለህይወት ዝም አንልም

Christian ዜማ Tube

30 Mar, 18:35


#አታስመስሉ

የትም ስትሄድ ከእግዚአብሔር የወጣችሁትበትን ያንን መልክ በመግለጥ ተባረኩ። ክርስቲያን ከሆንክ በግልጽ ክርስቲያን ሁን አጥርና ካብ ላይ ደጅ ደጁን መልኩን እንደሚቀያይር እስስት አትሁን። ያስታውቅብህ ✍️ከሚያሽቃብጡት ጋር አታሽቃባት የወንጌሉን መልክን ሁኑ። አለማውያንና ታዋቂ ሰዎች ጴንጤ ለመምሰል እንደሚያደሩጉት ጥረት አታስመስል። አለምም ጋር ጌታም ጋር ለመጫወት አትሞክር። በአለም ከሆንክ በአለም ሁን ለጌታ ልታዝንለት ፈልገህ ክርስቲያን ለመምሰል አትጣር። ጌታ የሰው እጥረት የለበትም። በጌታም ብትሆን የምትጠቀመው አንተ ባትሆን የምትጎዳው አንተ። አታሰመስል በግልፅ አደባባይ ላይ ለተሰቀለልህ ጌታ በግልፅ አደባባይ ታይለት።
ደጋፊዎችን ለማስደሰት እንደሚጥር የእግርኳስ ቡድን ያለ አቅምሕ ያለ መረዳትህ ውስጥህ በሌለው አንተን ባልገዛህ ጉዳይ ላይ እየተጋጋጥክ ግብም ነጥብህ ለሌለው በርታ በርታ የሚሉህ ደጋፊዎችህን ለማስደሰት አትምኮር። ወዳጄ ማንንም ለማሞቅ ብለህ በማሰመሰል እሳት ላይ ራስህን አትጣድ።
ግልባጭ ለአንዳንድ አገልጋዮችና ለአርቲስቶች እንዲሁም በማስመሰል ለምትሰቃዩ
Dave khc ነኝ

Christian ዜማ Tube

27 Mar, 15:10


የመጋቢ በጋሻው ደስአለኝ በአደባባይ ኢየሱስን መስበክ ያላንፈራገጠው የለም። እስከዛሬ ዝም ያለ ሁሉ ከያለበት ዋሻ ብቅ ብቅ ማለት ጀመረ…ከፌዘኛው በእውቀቱ እስከ ሀይማት ሙቀቱ ሀሳብ ሰጠ! ዝም ያሉህ ዝም ስላልክ እንጂ የሚናገርህ ስለሌለ አይደለም። ኢየሱስ ማለት ስትጀምር በአደባባይ ስትናገር ከለበስከው ልብስ እስከ ጠቀስከው ጥቅስ ሀሳብ ሰንጣቂው ብዙ ነው!

የዳንበትን ኢየሱስ ግን እነሱ ስለኛ እየተናገሩ እኛ ስለእርሱ እንናገርለታለን!! ተነሱ ዝም አትበሉ ሊናገሯቹ ይጀምሩ ኢየሱስ እርሱ የጌቶች ጌታ ነው!!

Christian ዜማ Tube

27 Mar, 09:34


ኮከቡ ኢየሱስ ነው!!

Christian ዜማ Tube

27 Mar, 03:44


#ለኦርቶዶክስ_ቀኛተኛ_ነበረኩ
#ከተዋህዶ_የበደለኝ_ማንም_የለም_ከዛ_የወጣሁት
#ኢየሱስ_ከዛ_ውጣ_አለኝ
ልጅነቴን ፣ ወጣትነቴን ያገለግልኳት፣ ለኦርቶዶክስ ቀናተኛ ነበረኩ። ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማንም አልበደለኝም ኢየሱስ ስለጠራኝ ነው። የጠራኝ የሆነ የጦር ጀነራል ሆኖ አይደለም የጠራኝ መስቀል ላይ ሆኖ እንደተቸነገረ እንደቆሰለ ምንድን የሰቀሉት በድብደባ አይኑ ጠፍቷል ዝም ብሎ ያየኛል እሱ ፣ ና ወደ እኔ አይልም ይሄ የሆነው የዛሬ 7 ሰዓት ነው። ራዕይ ረጅም ሰዓት ነው። በዛን ጊዜ ዝም ብሎ ነው የሚያየኝ በዛው በኦርቶዶክስ ቀጥል የሚለኝ መሰሎኝ ነበረ። ገና አፌን ስከፍት የሚመጣው ያ ብርሃን ፣ ያ ችንኳር ነው። ማንም ሰብኮ ሊቀይረኝ ያልቻለውን የቀረየኝ ያ ነው። ማንም ከኦርቶዶክስ የበደለኝ የለኝም። ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እወዳችኋለሁ። ማንም ከኦርቶዶክስ ያጠቃኝ የለም። ሰይጣንም አይደለም። እኔን የጠራኝ ኢየሱስ ነው። 7 አመት በክርስቶስ የኢየሱስ ፍቅር እየነደደ አለ። በ2008 እና 2009 ድምጽን አጥፋ አለኝ። ያፈረሰው በጋሻው 7 አመት ፈጀበት።እግዚአብሔርን አፍርሶ ሰራኝ።

እውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና አስተምህሮ።

Christian ዜማ Tube

18 Mar, 08:27


አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን - 1955 ዓ.ም

Source Caption: Addis Abeba Meserete Kiristos Chapel back in 1963

Lancaster Mennonite Historical Society/Hostetter, Elizabeth Louise, 1926-2014, Papers:
https://lmhs.pastperfectonline.com

Christian ዜማ Tube

16 Mar, 17:12


የሊዲያ ጉዳይ

አንዳንዶች በውስጥ መስመር እየመጡ ፀረሙስሊም እንደሆንኩ የሚከሱኝ አሉ። ለምን ለሊዲያ ድምፅ ትሆናለህ ነው ምክንያታቸው። እኔ የህግ መምህር ነኝ። ድግምትና ጥንቆላ ብሎ ወንጀል እንደሌለ አውቃለሁ። አስተምራለሁ። አቋሜ ከሞያ አንፃር እንዲህ ላስቀምጠው 👇

አንድ ነገር ወንጀል ለመባል ሶስት መስፈርቶችን ማሟላት አለበት።

አንድ ድርጊት

ወንጀል ማለት አታድርግ የተባለን አለማድረግ አታድርግ የተባለን ማድረግ ነው። ድርጊት መኖር አለበት። ይህም ድርጊት በማስረጃነት ለፍርድቤት የሚቀርብ መሆን አለበት።

ሁለት ህግ

አንድ ድርጊት ወንጀል ነው የሚባለው በወንጀለኛ መቅጫ ህጋችን ላይ ወንጀል መሆኑን እና የሚያስቀጣውን የቅጣት አይነት መታወጅ አለበት። በህግ በግልፅ የተቀመጠ መሆን ይኖርበታል። አቃቢ ህግ ይህን የተጣሰ ህግ ጠቅሶ ነው ክስ የሚመሰርተው።

ሶስት የህሊና ክፍል

ድርጊት እንኳ ቢኖርም፣ ድርጊቱ በህግ እንደሚያስቀጣ የተጠቀሰ ቢሆንም እንኳ፣ አድራጊው ድርጊቱን ሲፈፅም የአዕምሮው ሁኔታ ሊታይ ይገባል። ህፃን (8አመት በታች)፣ አዕምሮ ህመምተኛ እና ሆነ ብሎ አለማድረጉ እና የመሳሰሉት መስፈርቶች አንድን ድርጊት ወንጀል መሆን አለመሆኑን ይወሰናሉ።

እንግዲህ ሊዲያ የተከሰሰችው በድግምት/ጥንቆላ ተማሪዎች ላይ ጉዳት አደረሰች ነው። አጠገቧ የነበረች ሙስሊም ልጅ ራሷን ስታ ወድቃ "እየሱስ ጌታ ነው" ብላ ተናገረች። ይህን ያለችው በሊዲያ ድግምት ነው በሚል ነው የወደቀችው ልጅ ቤተሰብ ለፖሊስ በመክሰስ ልጅቷ የታሰረችው።

ሊዲያ ልጅቷ አጠገብ ከመገኘት በቀር ድርጊት የሚባል ነገር አልፈፀመችም። የጥንቆላ/ድግምት ስራዎች ላይ ያልተሰማራች ተማሪ ናት። ሊዲያ ፕሮቴስታንት ናት።

በህጋችን ስለድግምትና ጥንቆላ በወንጀልነት የተጠቀሰው ድግምት/ጥንቆላን እንደ ምክንያት በመጠቀም የማጭበርበር ድርጊት መፈፀምን እና

ድግምትና ጥንቆላን እንደ ምክንያት በመጠቀም ለሰዎች ጤና አደገኛ የሆኑ በአድ ነገሮችን በመስጠት የጤና ጉዳት ማድረስ የሚል ነው።

በህጉ የተጠቀሰው ማጭበርበርና ጤና ላይ ጉዳት ማድረስ ነው እንጂ ድግምት መስራት አይደለም። ድግምት በህጋችን ቦታ የለውም። እርግማን ቦታ የሌለው ያህል ድግምትና ጥንቆላም ቦታ የላቸውም። ሊፈፀሙ የማይችሉ ወንጀሎች ብለን ነው የምናስተምረው። "በቡዳ በላቺኝ" ብሎ ክስ እንደሌለው ሁሉ ይህም በድግምት ሀይማኖት ማስቀየር የሚባል ነገር የለም።

(የክሱን ሁኔታ ዝርዝር ላጤነ የሀይማኖት ጉዳይ እንዳለበት ግልፅ ነው። ክሱን ከመጀመሪያ ጀምሮ ተከታትዬዋለሁ። ድግምት የተባለውን ጉዳይ ወደ መመረዝ እና የተለያዩ ጉዳዮች ጨማምረው አሳደጉት እንጂ ነገሩ የወደቀችው ልጅ እና የቤተሰቧ ጉዳይ ነው። )

ሊዲያ አንድና ሁለትን ስለማታሟላ ሶስተኛውን መስፈርት ማብራራት አያስፈልግም።

ይልቅ የልጅቷ እድሜ ለአቅመ ሄዋን አለመድረሷን ከግምት ስናስገባ በርካታ መታረም ያለበት ጉዳይ እንድናነሳ እንገደዳለን። በህግ መነፅር ይህች ልጅ ህፃን ናት (15 አመት) ። በህገመንግስት የህፃናት መብትና ቢከሰሱም ሊያዙበት የሚገባው መንገድ እንደ አዋቂዎች አለመሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። (ዝርዝሩ ብዙ ነው)

ፍርድቤት ዛሬ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ለቅቋታል። ፖሊስ ፍርድቤትን አክብሮ እንደሚፈታት ተስፋ አለኝ።

በተረፈ እኔ ከሀይማኖት መነፅር ሳይሆን ጉዳዩን እንደ አንድ ሚዛናዊ ሰው፣ ህግ እንደሚያውቅ ሰው ነው ተመልክቼው ለልጅቷ ድምፅ የሆንኩት። ወገንተኝነት የሚባል ነገር የለብኝም። ለተበደለ መናገር ተፈጥሮዬ ነው። ስለዚህ በውስጥ መስመር የምትሳደቡ ሰዎች ጉዳዩን ከወገንተኝነት ፀድታችሁ ለፍትህ ቁሙ። ፍትህ ሲዛባ ነገ ወደናንተም ይመጣል።

በዚህ አቋም ምስጋናም አልሻም። ማንም ጤነኛና በህዝብ ሀብት የተማረ ሰው ሁሉ ሊያደርገው የሚገባውን ነው ያደረግሁት።