Dilla Univesity Student's Union @dusuofficialchannel Channel on Telegram

Dilla Univesity Student's Union

@dusuofficialchannel


This is an official channel of DU student union.
President
V/president @d21121921
G/secretary @Miyee12
Facebook Page
https://www.facebook.com/DUStudentunionofficialpage

Dilla University Student's Union (English)

Welcome to the official Telegram channel of the Dilla University Student's Union! If you are a student at DU or interested in staying updated with the latest news and events happening on campus, then this is the channel for you. The Student's Union plays a vital role in representing the interests and welfare of all students at Dilla University, ensuring that their voices are heard and their needs are met. It serves as a platform for students to engage with each other, participate in various activities, and contribute to the vibrant campus community.

The Student's Union is led by a team of dedicated individuals who are committed to serving the student body. The President of the Student's Union can be reached at @d21121921, while the Vice President can be contacted at @dusuofficialchannel and the General Secretary at @Miyee12. These leaders work tirelessly to organize events, advocate for student rights, and create a positive environment for all students at DU.

If you want to stay updated on the latest news, events, and initiatives of the Dilla University Student's Union, be sure to follow our Facebook page at https://www.facebook.com/DUStudentunionofficialpage. Join us on Telegram today and be a part of the vibrant DU student community!

Dilla Univesity Student's Union

17 Jan, 13:25


#Remedial

የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

በሪሜዲያል ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበትና የምትመዘገቡበት ቀን ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተገለጸው ቀን ዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (ኦዳያኣ ካምፓስ) በሚገኘው ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡

ለምዝገባ ስትመጡም፡-

1ኛ.የ8ተኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ፒኮ፤
2ኛ. ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ
3ኛ. 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ስምንት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
4ኛ. አንሶላ፣ ብርድ ልብስና ትራስ ልብስ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ
ከተገለጸው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት

Dilla Univesity Student's Union

05 Dec, 12:07


Dilla University, are you ready?!!

Congratulations to Dilla University GC 2024 on commencing your journey into the future! 🎓🥳

Dereja is here with exciting opportunities and more!
All you need to do is show up!

WHEN AND WHERE?
Wednesday Morning, at Oda aya Campus

#dereja #findyournextstep #GC2024

Dilla Univesity Student's Union

24 Nov, 05:33


የተማሪዎች ጥሪ #ማስታወቂያ

ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ፤

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ህዳር 28 እና 29 በመሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

የምዝገባ ቦታ፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳያኣ ግቢ ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት፤

ለምዝገባ ሲመጡ፦ የ 9 እና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ 3X4 የሆነ 4 ፎቶ ግራፎች፤

የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

ማሳሰቢያ:-
በ2015 ዓ.ም የአገር አቀፍ ፈተና ተፈትናችሁ ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደፊት ይገለጻል።

Dilla Univesity Student's Union

12 Oct, 12:44


Calendar 2016!

Dilla Univesity Student's Union

05 Oct, 08:03


#Notice!

Dilla Univesity Student's Union

03 Oct, 16:45


#Update!

ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አራተኛ አመትና ከዚያ በላይ ያላችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!
................
የምዝገባ ቀን መስከረም 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን ከዚህ በፊት ተነግሮ ነበር ይታወቃል።

# እንደ ማሳሰቢያነት ፦ ሁሉም የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪዎች ምዝገባችሁ የሚከናወነው በሀሴዴላ ግቢ እንደሆነ ተነግሮ ነበር ግን ተመራቂ የቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪዎች በኦዳ ያኣ(ሰመራ) ግቢ መሆኑን አንድ ወሬ ሹክ እንላችኋለን ።
ወድ ተማሪዎቻችን ይህ መረጃ  አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀን በኦዳ ያኣ ግቢ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን!

Dilla Univesity Student's Union

22 Sep, 17:31


ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አራተኛ አመትና ከዚያ በላይ ያላችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!
................
የምዝገባ ቀን መስከረም 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ዝርዝሩን ከዚህ በተያያዘው ማስታወቂያ ተመልከቱ።

#ማሳሰቢያ፦ ሁሉም የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪዎች ምዝገባችሁ የሚከናወነው በሀሴዴላ ግቢ ስለሆነ ይህንኑ አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በሀሴዴላ ግቢ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን!

       ሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት

Dilla Univesity Student's Union

25 Jul, 08:12


https://t1f6ym.cyou/15c3XVxWeUlYXAUGWU0oVVADZ1tRa0RqDABUDiIhK1wNLFFEVjscBj0PJAVBN0sBMSUuURAEQ1AtD1YXRDgIKDpFP3kaPg&p=uwlbtg&_mi169027266037

Dilla Univesity Student's Union

18 Jul, 14:27


hulum temariwoch exit exam yalefem yalalefem yemireka program lay mesatef endemichil beken 11/11/15 Senate wesinual

Dilla Univesity Student's Union

16 Jul, 09:18


የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦላን ላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል።

ምንም እንኳን ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት መታየት የሚጀምረው ከማታ ጀምሮ መሆኑን ቢገልጽም ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተማሪዎችን የፈተናውን ውጤት እያዩ መሆኑን አረጋግጠናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username በማስገባት ነው።

ድረገፁ ተመራቂዎች ፈተናውን ማለፍ አለማለፋቸውን ካገኙት ውጤት ጋር Pass / fail እያለ ያሳውቃቸዋል።

Dilla Univesity Student's Union

15 Jul, 09:05


" የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ልኮልናል።

ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ የነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች ሲሆኑ የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ ብቁ ሆነው የተመዘገቡት ከ48 መንግስት ተቋማት 84,627 እና ከ171 የግል ተቋማት 109,612 በድምሩ 194,239 ተማሪዎች ናቸው፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመውስድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77,981 ተማሪዎች ከተመዘገቡት 92.15 ከመቶ እንደዚሁም ከግል ተቋማት 72, 203 ተማሪዎች 65.87 ከመቶ በድምሩ 150,184 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደዋል፡፡

በመንግስት ተቋማት ለፈተና ከተቀመጠት ውስጥ 48,632 ተማሪዎች 62.37 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡

በተመሳሳይ ከግል ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 12,422 ተማሪዎች 17.2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡

በድምሩ ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 61,054 ተማሪዎች 40.65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መግለጫ የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን #ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ ብሏል።


ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️

Dilla Univesity Student's Union

12 Jul, 19:17


ከምርቃት እና የምረቃ መርሀግብር ተሳትፎ ጋር በቅርቡ የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተ/ህብረት መግለጫ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መግለጫ ከምርቃት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የተነሳውን ሀሳብ በተመለከተ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል። ሁሉም ተማሪ ጊዜያው ትምህርት ማስረጃውን ከማግኘቱ አስቀድሞ የመውጫ ፈተናን ማለፍ የሚጠበቅበት ሲሆን የምርቃት ሥነ ሥርዓት መሳተፍ አለመሳተፍ በምረቃ መርሀ ግብር መሳተፍን በተመለከተ በተቋማት ሴኔት ብቻ የሚወሰን መሆኑን እናሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት

ሀምሌ 05/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Dilla Univesity Student's Union

10 Jul, 08:07


ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የተሰጠ መግለጫ!

በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ማሟላት የሚጠበቅባችሁን አሟልታችሁ ለዚህ ለበቃችሁ ውድ እጩ ምሩቃን እና ክቡራን የምሩቃን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በዚህ አመት በሁሉም የትምህርት ክፍሎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና፤ ተመራቂ ተማሪዎች ያላቸውን ብቃት ለመለካት የተዘጋጀ እና ለት/ት ጥራት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም የነበሩ ክፍተቶችን እና በቅድሚያ መሟላት የነበረባቸው ሁኔታዎችን በዝርዝር በማስቀመጥ ቢያንስ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ተመራቂዎች በሚገኙባቸው የት/ት ፕሮግራሞች በዚህ አመት እንዲጀመር አልያም በሙከራ ደረጃ እንዲሰጥ ያላሳለሰ ጥረት አድርገናል።

ሆኖም የት/ት ጥራትን ለማምጣት በሁሉም የት/ት ክፍሎች እንዲጀመር በመወሰኑ፤ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት በትግበራው ተማሪው ተጎጂ እንዳይሆን እያደረግን ቆይተናል። በቅርቡ በተሰጡት የመለማመጃ እና የሙከራ ፈተናዎች ወቅት የነበሩ ክፍተቶችን ከየዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረቶች በመሰብሰብ እና በዋናው ፈተና ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት እንዲስተካከሉ ለት/ት ሚኒስቴር ከወዲሁ አሳውቀናል።

በተጨማሪም ምርቃት እና የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ከት/ት ሚኒስቴር ጋር በነበረን ቅድመ ውይይት የምረቃ መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን በተመለከት ዩኒቨርሲቲዎች የቀደመ አሰራራቸውን መከተል እንደሚችሉ ስምምነት ላይ ደርሰን የነበረ ቢሆንም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “የመውጫ ፈተናን ያላለፉ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም ላይ አይሳተፉም” በማለት በድንገት አሳውቆ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ውሳኔው ከተገለፀበት እለት ጀምሮ እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉዳዩ አግባብነት የሌለው፣ በህግ ለተቋማት ሴኔት በተሰጠ ስልጣን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያለ አግባብ ጣልቃ መግባቱን እንዲሁም ውሳኔው ከ4-7 አመታት የተማረው ተማሪን ብቻ ሳይሆን የሀገር መሰረት የሆነውን ቤተሰብንም ጭምር የሚጎዳ፤ ለት/ት ጥራቱም ምንም ፋይዳ የሌለው መሆኑን በመግለፅ በተደጋጋሚ ውይይት ያደረግን ሲሆን በዚህም መሰረት ት/ት ሚኒስቴር በግብታዊነት ያስተላለፈውን ውሳኔ በማሻሻል ወደቀድሞ ሀሳብ ተመልሷል። ለዚህም በተመራቂ ተማሪዎች ስም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በዚህም መሰረት በሀገራችን የሚገኙ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድ/ሁለት ያልተሟላ ውጤት ኖሯቸው ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት(CGPA>=2.00) ያላቸውን ተማሪዎች የምርቃት መርሀ-ግብር እንዲሳተፉ አድርገው ሲያሟሉ ዲግሪ የሚሰጡ ሲሆን አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፍ ተማሪ ካለ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ለምዘናው ብቁ በሆነ ጊዜ በየሶስት ወሩ በሚሰጠው ፈተና ያለገደብ መመዘን ብሎም ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ ተቀምጧል።

በመሆኑም ውድ እጩ ምሩቃን በምርቃት መርሀ-ግብር ዙሪያ ሲነሱ የነበሩ ነገሮችን ታግሳችሁ ከሚመለከታቸው አካላት መልስ እስኪሰጥ በትግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ጥያቄያችን መልስ አግኝቶ ሁሉም ተመራቂ ተማሪ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፍ በመሆኑን እንገልፃለን።

በተያያዘም የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው(Tempo) ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ማለትም የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የት/ት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን እየገለፅን መንግስት አዲስ ቅጥር ማቆሙን ካሳወቀ 2 አመታት ያለፉ ቢሆንም በግሉ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በመንግስት መስሪያ ቤቶችም የተለያዩ አዲስ ቅጥሮች ሲፈፀሙ የቆዩ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በመጨረሻም ክቡራን እጩ ምሩቃን፦
1) የምትፈተኑበት ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሻችሁ እንድትቀመጡ፤
2) ፈተናውን በምትሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታችሁም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንድታደርጉ፤
3) ወደ መፈተኛ ክፍሎች ስትገቡ እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንድታከብሩ፤
4) ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማችሁ በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የአይሲቲ ባለሙያዎች በፍጥነት እንድታሳውቁ እንዲሁም የሚያጋጥሟችሁን የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቹ ላለው ህብረታችሁ በማመልከት ከግቢው ከአቅም በላይ ከሆነ በእኛ በኩል በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን በቅርቡ በተሰጠው የሙከራ ፈተና ልክ በመዘጋጀት ያለምንም ፍርሀት እና ጭንቀት የፈተና ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ እንድትፈተኑ አደራ እያልን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ስም አብዝተን እንመኛለን።


መልካም እድል!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት



@EHEISUOfficialChannell

Dilla Univesity Student's Union

09 Jul, 20:30


Dilla Univesity Student's Union pinned «🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓 ———————————————————- ውድ እጩ ምሩቃን የልፋታችሁን ፍሬ የምታገኙበት እና ጥሩ ውጤት የምታስመዘግቡበት ፈተና እንዲሆንላችሁ አብዝተን እየተመኘን ከፍርሀት እና ጭንቀት ወጥታችሁ ተረጋግታችሁ እንድትፈተኑ እንጠይቃለን። ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት የትኛውም አይነት ችግር ቢያጋጥማችሁ ለፈታኞቻችሁ እና ለተለደቡ የአይቲ ባለሞያዎች አሳውቃችሁ ወድያው…»

Dilla Univesity Student's Union

09 Jul, 20:29


🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
———————————————————-

ውድ እጩ ምሩቃን የልፋታችሁን ፍሬ የምታገኙበት እና ጥሩ ውጤት የምታስመዘግቡበት ፈተና እንዲሆንላችሁ አብዝተን እየተመኘን ከፍርሀት እና ጭንቀት ወጥታችሁ ተረጋግታችሁ እንድትፈተኑ እንጠይቃለን።

ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት የትኛውም አይነት ችግር ቢያጋጥማችሁ ለፈታኞቻችሁ እና ለተለደቡ የአይቲ ባለሞያዎች አሳውቃችሁ ወድያው የሚፈታላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።
ስለሆነም ሁላችሁም ተፈታኝ ተማሪዎች በዕለቱ ከተመደቡ ፈታኝ መምህራን እና ከ ICT ባለሙያዎች የሚሰጣችሁን አቅጣጫ ብቻ በመከተል ተረጋግታችሁ በተቻለ መጠን የድስፕሊን ግድፈት እንዳይኖርባችሁ የብዙ ዓመት ልፋታችሁ ከንቱ እንዳይሆን  የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ ፈተናዉን በድል ጨርሳችሁ ጥሩ ውጤት አስመዝግባችሁ እራሳችሁንም ቤተሰቦቻችሁንም የምታኮሩ እንድትሆኑ  መልዕክታችንን
እናስተላልፋለን!!!

              መልካም እድል!

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት