አዶናይ @thedayofpentecost Channel on Telegram

አዶናይ

@thedayofpentecost


በዚህ ቻናል በኩል የታረደውን የእግዚአብሔር በግ እያከብረን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በውስጥ ሰውነታችንን በሀይል እንበረታለን።

መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው 🥰

@AdonaiComments_bot

አዶናይ (Amharic)

አዶናይ ለእናንተ የሚሰራው ቻናል በኢየሱስ በመላው ተዘጋጅቶ ከፍ እንዲያመነዝሩና ለሀሳብና አስታየት ብቻ የሚሰጥ ነው። የዚህ Bot መሣሪያችን @AdonaiComments_bot ለመጠቀም እና በመክፈቱ፣ በሀሳብና ለመመከቱም የሚችሉን የቻናል አዝራሮች እንደሚለዋወጡ ጠቃሚ እና መረጃ ዝግጅትን ይበልጥ ይህን ቻናል እንደ ምሳሌ በማስመረጥ መነሻ እንዱለን። አዶናይ እናንተን እናንተን ለማዳን እና ከራስ ቻናለ᯽ን ለማረጋጋት ይህን ቻናል በመጪው ነፃ አንድ የመከላከያ ስለማድረግ ይህን ስለሚያስተማር ሊንኩሳርን መረጃ የሚሆነውን በአሰፋ እንደሚያከናውኑ ሆኖ ለእኛም በመሆን እኛ የኛ እና ለእናንተ ነን። እንዲህም ነው የእኛ ማንቸም ቻናሉ አዶናይ ።

አዶናይ

12 Jan, 17:35


እስከ ዛሬ በህይወታቹ ውስጥ ስለበዛው ታላቅ ምህረት እግዚአብሔርን አመስግኑ🙏

“በተከበበች ከተማ ውስጥ፣ የሚያስደንቅ ምሕረቱን ያሳየኝ፣ እግዚአብሔር ይባረክ።”
መዝሙር 31፥21

አዶናይ

10 Jan, 17:17


ምን እየሆንን ነው ?

ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ የክርስትናችን መልክ ባንድም በሌላም መንገድ ስርዓት የሚባል ነገር እያጣ መጥቷል፤ ትናንት ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ብዙ ልክ ያልነበሩ ነገሮች አሁን ላይ ግን ተደጋግመው ስለሚደረጉ ብቻ ትክክል መሆን ጀምረዋል፤ በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ስንፀየፋቸው የነበሩ ኃጢአቶች አሁን አሁን በቤተ-ክርስቲያን ደረጃ እንኳን እውቅና እየተሰጣቸው ነው ፤ የእግዚአብሔር ፅድቅ በዘመን አመጣሹ Democracy አሳፋሪ እየሆነ ፣ የኛ ቅጥ ያጣ ነውር ደግሞ በአደባባይ ይጨበጨብለታል 😡 የውላቹ የተወደዳቹ እኛ አገልግሎታችን ለ Media ፍጆታ፣ ጌታን እንድናሳይበት የተሰጠንን መድረክ ደግሞ ለራስ ክብርና ለታይታ እንድናደርገው አይደለም የተጠራነው፤ መቼም ቢሆን ደግሞ የኛ ስህተት በታዋቂ ሰዎች ስለተደገፈ እና ህዝብ ስላጨበጨበለት ብቻ ትክክል አይሆንም፤ሁላችንም ሀሳብ ልክ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ከተስማማ ብቻ ነው ካለዚያ ልክ ናቸው ያልናቸው እውነታዎቻችን ሁሉ ስህተት ይሆናል፤ ክርስትናችንም ቢሆን የእውነት የሚሆነው ዘመን ከሚያመጣው ስልጣኔና በየዘመኑ ከሚነሳው የሰዎች ትምህርት በላይ በእግዚአብሔር እውነት ላይ ከተመሰረተ ብቻ ነው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

07 Jan, 05:55


ስንቸገርበት ለነበረው ኃጢአትና በጣም ስንፈራው ለነበረው ሞት ሁነኛ የሆነ መድሃኒት ከወደ ቤተልሄም አግኝተናል🤗 ደስ ይበላችሁ 🥰

መልካም በዓል ለሁላቹም

አዶናይ

03 Jan, 17:26


አንድ ሰሞን 💪🔥..... 😞🙇

መፀለይ ታዞትራላቹ ፣ ውስጣቹም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይቀጣጠላል የሚደንቁ ህልሞችንና ራዕዮችንም ማየት ትጀምራላቹ ፣🔥 ነገር ግን ይሄ ከአንድ ሰሞን አያልፍም ደግሞ ወደዛ ወደማቶዱት ህይወት ትመለሳላቹ... መድከም ትጀምራላቹ🙍 ያንን ትጋታቹን ትጥሉታላቹ፣ ኃጢአት Normal ይሆንባቿል ብቻ ብዙ ነገር... አሁን በዚህ አይነት ድካም ውስጥ እያለፈ ያለ ሰው ካለ የምለው ነገር በደንብ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ ፤ " ግን ለምንድነው ምደክመው ? " የብዙዎቻቹ ጥያቄ ነው እስቲ ላንዳፍታ ይሄ ጥያቄ በውስጣቹ የሚፈጠርባቹ ልጆች ጥቂት ጊዜ ወስዳቹ ዙሪያቹን ተመልከቱ...የአባቴ ልጆች እናንተ አላስተዋላቹም እንጂ እኮ የእናንተ አድካሚዎች በዙሪያቹ ነው ያሉት ለምሳሌ ጓደኞቻቹ ፣ የ social media አጠቃቀማቹ እና ሌላም... የተወደዳቹ እንደ ወንድም የምትሰሙኝ ከሆነ አንድ ምክር ልምከራቹ፤ እንድትደክሙ ከሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ራሳቹን አርቁ በቃ ወስኑ አውቃለው ከለመዳቹት ነገር መለየቱ ያማል ነገር ግን እያመማቹም ቢሆን
ሳታውቁት ዛሬ ላይ ሀይላቹን እያደከሙባቹ ካሉ ነገሮች
ፈጥናቹ ራሳቹን አድኑ።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

01 Jan, 17:49


በዘመኔ ማንም ልቤን ሳይወስደው እንዲሁ እግሮችህ ስር እንደተንበረከኩ ዘመኔ ይለቅልኝ😭 የእኔነቴም መጨረሻ ያሳደጉኝ እጆች ላይ ይሁንልኝ...እኔ ቤት ጓደኛ ፣ ገንዘብና ዝና ካንተ እንፃር ሲታዩ ምን አይነት ዋጋ የላቸውም፤ ከፊት ቢሆን ከኃላ፣ መጨረሻም ላይም ቢሆን መጀመሪያ ላይ አንተ ካለ ብቻ ነው የኔ ህይወት ትርጉም የሚኖረው፤ የኔ አባት ዛሬ እንደ ልጅ እጠይቅሃለሁ ከእጆች መዳፍ እንዳልርቅ ጥብቅ አድርገህ በፍቅር ያዘኝና እጆችህ ላይ ዘመኔን ልጨርስ😭

አዶናይ

31 Dec, 17:40


መሰማት ይፈልጋል

ብዙ ጊዜ በጌታ ፊት ተንበርክከን ስንፀልይ አንደ ልጅ ጌታን ብዙ ነገሮችን እንጠይቀዋለን፤ አባ ይሄን ነገር አድርግልኝ ፣ ካንተ ይሄን እጠብቃለው እንለዋለን፤ ነገር ግን ብዙዎቻችን እኛ ጌታን እንደ አባት የሚያስፈልገንን እንደምንጠይቀው ሁሉ የሚሰማንም አባት እኛ ልጆቹ እንድንኖርለት የሚፈልገው ህይወት እንዳለ አናስተውልም፤ አይታቹ ከሆነ የዛ የጠፋው ልጅ ትልቁ ጥፋት ንብረት መካፈሉ ላይ ሳይሆን ንብረት ከተካፈለ በኋላ አባቱን ምን አይነት ህይወት መኖር እንዳለበት አለመጠየቁ ላይ ነው፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ፀሎታቹ የእናንተ ሀሳብ ብቻ የሚፀባረቅበት ስፍራ መሆን የለበትም፤ እኛ በፀሎት ስፍራችን ላይ ተንበርክከን አባታችን እንዲሰማን እንደምንፈልገው ሁሉ ጌታም በግሉ በልጆቹ መሰማትን ይፈልጋል፤ ይሄ አባት ምን አይነት ህይወት ልኑርልህ... እንደ ልጅ ከኔ የምትፈልገው ምንድነው እንድትሉት ይፈልጋል፤ ከጌታ ጋር የሚኖራቹ ህብረትም ፍሬያማ የሚሆነው በእናንተ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በእርሱም የልብ ፍቃድ ላይ የሚመሰረት ከሆነ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

27 Dec, 17:19


እንደ ኢየሱስ ሁኑባቸው

አንዳንድ ሰዎች እናንተ የደርሳቹበት ደረጃ ላይ መድረስ ሲከብዳቸው እናንተን ለማቆም ብለው ውጪው መልካም የሚመስል ውስጡ ግን ቅናት የሞላበት ምክር ይመክራቿል፤ "እኛም የሆነ ሰሞን እንዲህ ነበርን " ፣ "ብዙ አታካብድ/ አታካብጂ " ፣ "ትደርሳለህ ቀስ በል" የሚሉ ምክር መሳይ ቃላቶች ከቅርብ ከሚባሉ ሰዎች ትሰማላቹ...እነኚን ወደ ኃላ የሚጎትቷቹን ድምፆች አልሰማ ብላቹ ይበልጥ ከፍ ስትሉ ደግሞ እነኛው ሰዎች እናንተን በአካል ማግኘት ስለማይችሉ በጎን ለሚያውቋቹ ሰዎች በመጥፎ ተግባር ስማቹን ለማጥፍት ይሞክራሉእንደዚህ ዓይነት ሰዎች የግድ የእነርሱ ማንነት ለማተለቅ ሲሉ የሌሎችን ማንነት ማኮሰስ እንዳለባቸው የሚያምኑ ሰዎች ናቸው፤ ኢየሱስንም በዘመኑ የጠራቢው ልጅ ፣ አጋንንት ያደረበት እብድ መሪ የሚሉት ሰዎች ነበሩ ጌታ ግን ለእነርሱ ትችትና ስላቅ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በሽተኞችን እየፈወሰና ሙታኖችን እያስነሳ እርስ በርሳቸው ግራ እንዲጋቡ ማድረግን ነበር የመረጠው፤ ዛሬም በእናንተ ህይወት ውስጥ እንደዚህ አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ካሉ በእነርሱ ላይ ኢየሱስ ካደረገው የተለየ ነገር ለማድረግ አትሞክሩ፤ የእናንተ ዝምታ ብቻ ለእነርሱ ትልቅ ጥያቄ ነው፤ ዝም ብላቹ ጉዟቹን ቀጥሉ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

26 Dec, 18:49


🎙️ላይህ ናፍቃለሁ😭

መቼ ትሆን ያቺ ቀን ......

ድንቅ መዝሙር 🥰

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

24 Dec, 17:18


እኛ በማናውቀውና ገና ባልተረዳነው ፍቅር ልክ ኢየሱስ ዛሬም ይወደናል🥰

ማንም ሊወዳቹ በማይችልበት ፍቅር መጠን ኢየሱስ ወዷቿል ይሄን መቼም አትርሱ

አዶናይ

21 Dec, 17:07


የት ነው ያ ስፍራ ?

ሁላችንም በመንፈሱ ጠንካራ የሆነ፣ ከውሳኔዎቹ በፊት ቆም ብሎ የሚያስተውል፣ ህይወቱንም እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ የሚመራ ጠንካራ ማንነት ያለው ሰው መሆን እንፈልጋለን ነገር ግን መፈለግ ብቻ እንጂ ያንን የምንፈልገውን አይነት ሰው መሆን ይከብደናል 😔 ይህ የሁላችንም ችግር ነው ዛሬ ያንን የምትፈልጉት አይነት ማንነት አግኝታቹ የምቶጡበትን ስፍራ እጠቁማቿለሁ ይሄ ስፍራ በግላቹ ከጌታ ጋር ህብረት የምታደርጉበት ስፍራ ነው... አዎ ብዙዎቻቹ በቤተሰብ ወይም ከጓደኞቻቹ ጋር ትፀልዩ ይሆናል ነገር ግን ከዛ ባለፈ በየግላቹ ከጌታ ጋር ህብረት የምታደርጉበት የፀሎት ሰዓት ሊኖራቹ ይገባል፤ ብቻቹን ከጌታ ጋር ህብረት የማድረጊያ ጊዜ ሲኖራቹና ያንንም ደጋግማቹ ስታደርጉት የእናንተን ሙሉ ስብዕና የሚቀይር፤ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ አዲስ ማንነት በዛ ህብረት ውስጥ ታገኛላቹዳንኤል ትዝ ይላቹ ከሆነ በቀን ሶስት ጊዜ ከአምላኩ ጋር የግል ህብረት ነበረው በዚህም ምክንያት ዙሪያው ካሉት ጓደኞቹ ሁሉ በላይ በጥበብና በማስተዋል የጠነከረ ፣ የእግዚአብሔርም ሞገስ ያረፈበት ሰው እንደነበር መጽሐፍ ይነግረናል፤ ልክ እንዲሁ እናንተም በየቀኑ ከጌታ ጋር የግል ህብረት የሚኖራቹ ከሆነ በመንፈስ አለም ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ዘንድ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ህይወት ይኖራቿል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

19 Dec, 17:11


🎙️ ባይህ ምናለ 😭

የውስጤን ርሀብ የገለፀልኝ ድንቅ መዝሙር 🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

17 Dec, 17:52


የእውነት ያስብልናል ?

ሰው እንኳን እኛን በቀረበንና በወደደን መጠን ስለእኛ የሆነ መልካም ነገር ያስባል እግዚአብሔርስ ስለ እኛ ምን ያስባል ? እንዲህ ብላቹ ጠይቃቹ አታውቁም ? የእውነት እግዚአብሔር ምን ያስብልናል ካሰበስ ምን አይነት ሀሳብ ? መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድ የምወደው ቃል አለ እንዲህ ይላል “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” — ኤርምያስ 29፥11 በየቀኑ ጥላት በእኛ ህይወት ክፉ ነገሮችን እንደሚያስበው ሁሉ እግዚአብሔርም በኛ ህይወት የሰላምን ሀሳብ በየቀኑ ያስባል፤ ታዲያ ለምን እንዲህ አታደርጉም 🥰 ጠዋት ከእንቅልፋቹ ስትነሱ በዛች ቀን ጥላት በእናንተ ህይወት ላይ ያሰበባቹን ክፉ ሃሳብ ከምታስቡና ከምትጨነቁ ለምን የሚወዳቹ ጌታ በዛች ቀን ለእናንተ ለልጆቹ ያሰበውን መልካም ሀሳብ እያሰባቹ ቀናቹን አታሳምሩትም🥰 የዛኔ በእርግጠኝነት እግዚአብሔር በዛች ቀን ለናንተ ያሰባትን ሀሳብ ማስተዋል ትጀምራላቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

13 Dec, 17:14


ሸክላ ሠሪው

ሸክላ ሠሪ ሲሰራ አይታቹት ከሆነ ብዙ የሚያድበለብላቸው ጭቃዎች አሉት፤ ጥቂት የሸክላው ጭቃ ድብልብሎች ደግሞ እግሩ ስር ይወድቃሉ እነኚ የሸክላ ጭቃዎች ከስሩ ስለማይርቁ ዳግም ለመሰራት እድል ያገኛሉድንገትም ፀሀይ አግኝቷቸው ሊደርቁም ካሉ በውሀ አርሷቸው ዳግም ጌጥ አድርጓቸው ከሸክላው እቃ ጋር ያገኛቸዋል፤ ከምድራዊው የሸክላ ሠሪ የሚበልጠው የኛ ህይወት ሰሪ ደግሞ ለኛ ለልጆቹ ከዚህ በላይ ያስባል፤ መድከም፣ መሰበር የሸክላው ባህሪ ነው ሰሪው ግን እንደወደደ አሳምሮ ያበጀዋው ፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች በዚህ ሰዓት በብዙ ድካም ውስጥ ሊትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን ምንም ያህል ብደክሙም እዚው ዳግም ሰርቶ ሊያቆማቹ ከሚችለው ከኢየሱስ እግሮች ሥር በፍፁም አትራቁየጌታ እግሮች የብርቱዎች መሰብሰቢያዎች ሳይሆኑ የደካሞች መኖሪያዎች ናቸው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

11 Dec, 17:32


በጣም የምወደው በረከት 🥰

መዝሙር 20
¹ እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤
የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
² ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤
ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
³ ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤
የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ።
⁴ የልብህን መሻት ይስጥህ፤
ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።

እግዚአብሔር በነኚ በረከቶች ይባርካቹ 🔥

አዶናይ

07 Dec, 17:54


ለሁላቹም ይጠቅማቿል ብዬ የመረጥኳቸው ትምህርቶች ስለሆኑ ' ADONAI ' የሚለውን በመንካት የምትፈልጉትን ትምህርት ሙሉውን ማግኘት ትችላላቹ ።

ስለ መንፈሳዊ እድገት
👉 ADONAI .... Part 1
👉 ADONAI .... Part 2
👉 ADONAI .... Part 3

በህይወታቹ ጥያቄዎች ከበዙባቹ
👉 ADONAI .... Part 1
👉 ADONAI .... Part 2
👉 ADONAI .... Part 3

ስለ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም
👉ADONAI .... Part 1
👉 ADONAI .... Part 2
👉 ADONAI .... Part 3

አጉል ስሜታዊነት በፍቅር ህይወት ውስጥ
👉ADONAI .... part 1
👉ADONAI .... part 2

የእግዚአብሔር ጊዜ ስለመጠበቅ
👉 ADONAI .... Part 1
👉 ADONAI .... part 2

ለሴት እህቶች የተሰጠ ምክር
👉 ADONAI .... Part 1
👉 ADONAI .... Part 2

ከአዶናይ ቤተሰቦች የተጠየቁ ጥያቄዎች
👉 ADONAI .... Q 1
👉 ADONAI .... Q 2
👉 ADONAI .... Q 3

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

05 Dec, 17:22


ጌታ በቅርቡ ሊወስደን ይመጣል


ለመሄድ ተዘጋጁ

አዶናይ

03 Dec, 17:26


የኛ ቤት ይስሃቅ

በተፈጥሮ የመውለጃዋ እድሜ ያለፈባት እናት ነው ያለችው አባቱ ቢሆን የመቶ አመት የእድሜ ባለፀጋ ነው፤ ልጅዬው በአጭሩ የተአምር ልጅ ነው ፤ በሽምግልናም ስለተገኘ የቤቱ ደስታም ጭምር እንጂ ልጅ ብቻ አልነበረም ወላጅ እናቱ ከልቧ መሳቅ የጀመረችው ይሄን የመጀመሪያ ልጇን ካገኘች በኋላ ነው፤ ይሄ ልጅ ይስሃቅ ይባላል 🥰
ይስሃቅ በዛ ቤት ቢጠይቅ የማይሰጠው ቢፈልግ የማያገኘው ምንም ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ምንም ያህል በተአምር የተገኘ የቤቱ ብቸኛ ልጅ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ድምፅ በላይ ግን ተሰሚነት የለውም... እዚህ ቤት ከይስሃቅ ይልቅ ለእግዚአብሔር ነበር ምን ላድርግልህ የሚባለው ፤ አብርሃም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር እንኳን ልቡ የሚሳሳለትን ውዱን ይስሃቁን እንኳን ይሰጠዋል ለዛውም መስዋአት አድርጎ 💯 የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች አሁን ላይ ብዙ ሰዎች በየቤታቸው አንድ ትኩረት የሚሰጡት ጉዳይ አላቸው አንዳንዱ ጋር ቤተሰቡ፣ ሌሎቹ ጋር ደግሞ ስራቸው እና ገንዘባቸው ዋና ጉዳያቸው ነው እንደ አብርሃም ያሉ ሰዎች ጋር ግን የእግዚአብሔር ነገር በጣም ከጓጉለት ነገር በላይ ትኩረትና ተሰሚነት አለው፤ ለካስ የእኛ ቤት ይስሃቅ ፤ ነገ ላይ ህዝብ የሚሆነው ከእግዚአብሔር በታች የሚሰማ ከሆነ ብቻ ነው።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

29 Nov, 17:21


ሰሞኑንን ጌታን አምርሬ አንድ ጥያቄ እየጠየኩት ነው... ተጠቀምብኝ ብዬ 😭 እድሜ ከሰጠህኝ ላይቀር ፣ ካሰነበትከኝ ላይቀር ለክብርህ የሚሆን እቃ እድርገህ በሙሉ መልክህ ታይብኝ እያልኩት ነው ... መኖርንማ ጌታን የማያውቁትም ይኖራሉ የኛ ኑሮ ግን ከስም ባለፈ እርሱን በማሳየት ሲኖር ነው ተኖረ ሚባለው፤ ካለዚያ በእድሜያችን ላይ የሚጨመሩልን ቀናቶች ዋጋ አይኖራቸውም።

በእኛ በኩል ኢየሱስ ራሱን ለሌሎች ይግለጥ🔥

አዶናይ

18 Nov, 17:13


እንዲሁ ኢየሱስ ኢየሱስ እያላቹ ዘመናቹ ይለቅ 🔥

አዶናይ

17 Nov, 17:33


🎙️የግድ ታስፈልገኛለህ

ይሄ መዝሙር ፀሎትም ጭምር ነው

መንፈስ ቅዱስ የግድ ታስፈልገኛለህ 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

14 Nov, 09:57


🎙️Nefse _Hoy 🥰

ይሄን መዝሙር ለነፍሳቹ ንገሯት

ቃላቹን ጠብቁ !

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

11 Nov, 17:05


“እግዚአብሔር ዓለቴአምባዬመድኃኒቴአምላኬበእርሱም የምተማመንበት ረዳቴመታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።”
— መዝሙር 18፥2

አዶናይ

05 Nov, 17:39


የስልካቹ ጥሪ አድርጉት🥰

@thedayofPentecost

አዶናይ

04 Nov, 17:15


ኃጢአት አይደለም 👩‍❤️‍👨

እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሴትና ወንድን ሲፈጥር በውስጣቸው በፍቅር የታጀበ መፈላለግ እንዲኖር አድርጎ ነው የፈጠራቸው፤ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ እንዲፈልግ፣ እንዲያፈቅርና አብሯት እንዲኖር የእግዚአብሄር ሀሳብ ነው ሴትም ለወንድ ልጅ እንዲሁ ነገር ግን ብዙዎች ይሄን በወንድና በሴት መካከል ያለውን የፍቅር ስሜት እግዚአብሔር ያስቀመጠው ስጦታ ነው ብለው ከማመን ይልቅ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሌለበት የሰው ልጆች ስጋዊ ስሜት ብቻ አድርገው ይቆጥሩታል እነኚ ሰዎች ብዙ ጊዜ ይህንን እንድያስቡ የሚያደርጋቸው ትናንት ላይ በሰዎች ህይወት ወይንም በራሳቸው የፍቅር ህይወ ውስጥ በሚፈፅሟቸው ስተቶች ምክንያት ነው ለምሳሌ በዝሙት መውደቅ ሊሆን ይችላል እንደዚህ አይነት ስተቶች ደግሞ እግዚአብሔር በወንድና በሴት መካከል ያስቀመጠውን የፍቅር ግንኙነት ትክክል ባልሆነ መልኩ እንዲረዱትና ሴትን ልጅ በፍቅር አለመቅረብ እንደ ትልቅ ፅድቅ እንዲያዩት ብሎም ሴት ልጅ ሲሸሹ ከዝሙት እንደሸሹ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ፤ በርግጥ ሁላቹም እንደምታውቁት ከትዳር በፊት በዝሙት መውደቅ ትልቅ ኃጢአት ነው ነገር ግን በዝሙት ወይም እናንተ በፍቅር ህይወታች ውስጥ በምትሰሯቸው ስተቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ፍቃድ የሆነውን የፍቅር ግንኙነት እንደ ኃጢአት አድርጎ ማሰብም ሆነ ሴትን ልጅ በፍቅር አለመቅረብ እንደ ፅድቅ መቁጠሩ በፍፁም ትክክል አይደለም።

የፍቅር ህይወታቹ + በቅድስና የታጀበው ቃል ኪዳናቹ = ትዳር የሚባለውን ትልቅ ተቋም ይፈጥራል

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

02 Nov, 17:32


የርሀቧ ጥግ ኢየሱስን ጠራው

ገና በለሊት ቤት መቀመጥ አላስችል ብሏት የህይወቷን መምህር ፍለጋ ምንም በሌለበት መቃብር ስፍራ ላይ ብቻዋን እያለቀሰች 😭 አይኖቿ አስሬ የተከፈተውን መቃብር ታያለች የምትፈልገው መምህሯ ግን በቦታው የለም ፤ የኢየሱስን ከመቃብር መጥፋት ለማየት ከማርያም ጋር የመጡት ሌሎች ደቀ-መዛሙርት መቃብሩ መከፈቱንና የኢየሱስ ስጋ ከቦታው አለመኖሩን ከማየት ባለፈ እንደዚች ሴት የጌታ አለመኖር ጥያቄ አልሆነባቸውም መግደላዊት ማርያም ግን እርሱ እኮ ሞቷን ብለው የነገሯትን ረቢኒዋን ፍለጋ አይኖቿ እረፍት አጥተዋል በዚህ ሁሉ የጭንቅ ፍለጋ ውስጥ ግን አንድ ለማመን የሚከብዳትና የምታውቀውን ውብ ድምፅ ከበስተ ኃላዋ ሰማች " ማርያም " የሚል ድምጽ ፤ ይሄ ድምፅ ጥያቄዎቿን ሁሉ የሚመልስላት የምቶደው የመምህሯ ድምጽ ነበር... ማርያም በጣም በሚያስፈራ በመቃብር ስፍራ አጥብቃ የፈለገችው የህይወቷ መምህር በመጨረሻ ራሱን በትንሳኤ አካል ገለጠላት

የርሀቧ ጥግ ኢየሱስን ጠራው 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

30 Oct, 17:18


የህይወቴ ርዕስ ፣ የአገልግሎቴ ሁሉ ድምቀት የወጣትነቴ ውበት መንፈስ ቅዱስ ... በዘመኔ ካላንተ ህልውና ካላንተ መገኘት የምኖርባቸው ቀኖች አይደሉም ሰዓታት አይኑሩኝ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ... ሁሌ አንተን ብቻ
እስከ እድሜዬ መባቻ
🔥

አዶናይ

28 Oct, 17:36


እርሱ አልጨረሰም

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ አንድ የሚገርመኝ ታሪክ አለ ሉቃስ 8፡26 ላይ፤ እዚህ ሰው ላይ ተስፍ ያልቆረጠ አልነበረም፤ ቤተሰቡየጌርጌሴኖን ሀገር ሰዎች፣ በጤንነት ሳለ የሚያውቁት ጓደኞቹ ሁሉ እርሱ ላይ ያላቸውን ተስፍ ጨርሰዋል ፤ በዚህም የተነሳ ከሰው ተለይቶ በመቃብር ስፍራ ይህ ሰው ይኖር እንደነበር መጽሐፍ ይናገራል፤ እና በጣም የሚገርመው ሰውዬው ፈላጊ እንደሌለውና በማንም እንደማይፈለግ ህዝቡ ሁሉ ተረድተው ማንም በሌለበት የመቃብር ስፍራ ዋጋ እንደሌለው ሰው ጣሉት፤ነገር ግን ለዚህ ተስፍ ቢስ ሰው አንድ ወዳጅ ሊሆነው የፈለገ ሰው ነበር፤ ወዳጆቼ ይህ ሰው ለሰፈሩ ሰዎች ከአሳማ እንኳን ያነሰ ዋጋ ያለው ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው ምክንያቱም ተስፍ የሌለው ስለመሰላቸው፤ ኢየሱስ ግን ይህ ሰው ላይ የለውን አላማ አይጨርሰም፤ ፈፅሞም ተስፍ አልቆረጠበትም፤ እንደ ቤተሰቡም መቃብር ስፍራ እንዲኖር አልፈቀደለትም፤ ለዚህም ነው እርሱን ለመርዳት ሲል የውሀውን መአበሉ ፀጥ አድርጎ ወደ ነበረበት ስፍራ የመጣው።
ውድ የአባቴ ልጆች እናንተ አበቃለት ብላቹ በጨረሳቹለት ጉዳይ ላይ ኢየሱስ ሲመጣ ከአዲስ ይጀምረዋል፤ ፈላጊ የሌላቹ የመሰላቹ እናንተ ናቹ እርሱ ግን እናንተን ለመርዳት በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ይበራል በደመናትም ላይ ይራመዳል፤

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

26 Oct, 17:14


የእግዚአብሔር ጥበቃ ልክ እንዲህ ነው 🔥

“እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።”
— መዝሙር 91፥3


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

24 Oct, 17:26


ማባከን አይደለም 😭

በየቀኑ አለም የምትሰጠንን የቤት ስራ አለመስራት ሰነፍ አያስብለንም ፣ እግሩ ስር መዋልም ሞኝነት አይደለም ማርያም በይሁዳ አይን ስትታይ ምናልባት አባካኝ ፣ የገንዘብ ጥቅም ያልገባት ሴት ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ይሄ የኢየሱስ እግሮች ውበት ላልገባው ሰው እንጂ እንደ ማርያም በኢየሱስ ፍቅር ለተነካ ሰው ሶስት መቶ ዲናር ለእግሮቿ እንኳን የማይበቃ ስጦታ ነው ፤ እኛም ለዚህ ጌታ ወጣትነታችንን ስንሰጠውና ስንበረከክለት ላኑን ሰዎች ዘመኑ ያልገባን ዘመናዊነትን የማናውቅ ሞኞች ልንመስላቸው እንችላለን ነገር ግን እኛ ሰዎች እንደሚሉን ዘመኑ ሳንረዳው ቀርተን ወይ ደግሞ የሚመክረን አጥተን ሳይሆን እንደ ማርያም ሁሉን የሚያስንቅ ፍቅር ስለተካፈልን ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

23 Oct, 22:53


አልዋሽህም አባ

አልዋሽህም ደና ነኝ ብዬ 😔
አልዋሽህም ብርቱ ነኝ ብዬ
እንደገና ስራኝ እንደገና
እንደገና ዳሰኝ እንደገና 😥


እግርህ ስር ልሰንብት እንደገና 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

23 Oct, 17:36


Fake Channel

ይሄ በአዶናይ ስም የተከፈተ ከ 1.4k በላይ ተከታዮች ያሉት Channel ነው በእርግጥ ቻናሉ እስካሁን የማን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን የከፈትኩት ቻናል እንዳልሆነ እንድታውቁ ፈልጋለሁ፤ በዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁትን መልዕክቶች ለሰዎች ማጋራትና በየቻናሎቻቹ መልቀቅ ምንም ጥፋት የለውም ነገር ግን እንዲህ ስምና ሎጎውን ጨምሮ የዚኑ ቻናል ትምህርቶች ሳያስፈቅዱ መጠቀም ሰዎችን ግራ ለማጋባት ካልሆነ በቀር ሌላ አላማ የለውም።

አዶናይ

22 Oct, 17:25


ያየኽውን እንደሚያይ ለዛም ራሱን እንደሚለይ ግብ የሆነ ያንተ ክብር ከነብሱም ጋር የማይማከር ስራኝ እንደዚህ እንደ ክቡር እቃ ላየኽው ለመጨረሻው ዝናብ እንድበቃ ስራኝ እንደዚህ እንደ ክብሩ እቃ ላየኽው ለክብር ቀን እንድበቃ 😭

አዘጋጀኝ ለክብርህ 🔥

አዶናይ

20 Oct, 17:16


ጥያቄዎቹ ራሳቸው ይናገራሉ

አንዳንዴ ለችግራቹ መፍትሄ እንደሚሆኗቹ የምታስቧቸው ቤተሰቦቻቹና ጓደኞቻቹ የእናንተ ችግር ሰሚ እንጂ ባለመፍትሄ መሆን ይከብዳቸዋል፤ በገንዘባችን እና በሰዎች ጥበብ የማንፈታው እግዚአብሔር ብቻ መልስ የሆነበት የሆነ ጥያቄ በእያንዳንዳችን ቤት ውስጥ ይኖራል ፤ ይሄ ጥያቄ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ እንዳለ ይናገራል ፤ ለምሳሌ የሀና የልጅ ጥያቄ በባሏ መልስ ቢያገኝ ኖሮ እግዚአብሔር ሀናን ጎበኘ ተብሎ አይወራም ነበር ፤ አስተውላቹ ከሆነ በአንዳንድ ከባባድ ጥያቄዎች ምክንያት ለጥያቄዎች በቂ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ክብር ያገኛሉ እግዚአብሔር ለዚህ ነው በእርሱ ብቻ የሚመለስ ጥያቄ በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ ያስቀመጠው፤ ሀና ቤት ለረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው ሳሙኤል የሆነ ቀን እግዚአብሔር በዛ ቤት እንዳለ እንደተናገረ ሁሉ እናንተም ቤት መፍትሄ ያጣቹባቸው ጥያቄዎቻቹ አንድ ቀን እግዚአብሔር እንዳለ በግልፅ ይናገራሉ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

አዶናይ

19 Oct, 17:54


ወገኖች ተዉ እናምልክበት 😁

እውነት ለመናገር እኔ በአምልኮ ሰዓት ሼም የሚይዘው፣ አዩኝ አላዩኝ የሚያበዛ ሰው ጎን ባትቀመጡ ባይ ነኝ 😊 አይታቹ ከሆነ አንዳንድ ወገኖቻችን ከተንቀሳቀሱ እንኳን የሚንቀሳቀሱት "ሚልኮን ትናቀኝ እንደለመደባት ተፈቶ ማምለክ መቼም አይሆንላት " የሚለው መዝሙር ሲዘመር ነው እንጂ ንቅንቅ አይሉም እሱንም ቢሆን የመዝሙሩ ቃል እንዳይፈፀምባቸው ፈርተው ነው 😁 ብቻ ከልባቹ ተፈታቹ አምልኩ፤ ደግሞ እንኳን ለዚህ ለከበረው ጌታ ይቅርና ክብር ለሌለው ጠንቋን እንኳን ሽር ጉድ ይባልለታል።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

17 Oct, 17:15


ይሳቅን ፍለጋ...

እግዚአብሔር ለአብርሀም ልጅ እሰጥሀለው ብሎት ኪዳን ገባለት ነገር ግን የተነገረው የትንቢት ቃል ሳይፈፀም አመታቶች ይቆጠራሉ በዚህም ምክንያት አብርሃም ትኩረቱ ልጅ ላይ ብቻ ስለነበር በዚያም በዚም ብሎ ይወርስሀል ተብሎ የተነገረውን ልጅ ፍለጋ ሚስቱን ሳራን ትቶ ሞግዚቷ አጋር ጋር ገባ ነገር ግን ይሳቅን አገኛለው ብሎ አጋር ጋር የሄደው አብርሃም ከአጋር ማግኘት የቻለው የተጠበቀውን ይሳቅን ሳይሆን ያልታሰበውን እስማኤልን ነበር ....ለካስ የተስፍው ቃል ባለቤት ይስሀቅ ያለው ያረጀቺው ሳራ ጋር እንጂ ወጣቷ አጋር ጋር አልነበረም ፤ አብርሃም ተሸወደ 😊 የተወደዳቹ እግዚአብሔር የእናንተን ይሳቅ ጠብቃቹት እንጂ አቋራጭ መንገድ ተጠቅማቹ እንድታገኙት በፍፁም አይፈልግም፤ ጌታ የነገራቹን ቃል የሚፈፅምበት የራሱ ጊዜ አለው እናንተ ብቻ የተባላቹትን በተባላቹት ስፍራ ላይ ሆናቹ ጠብቁ

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

14 Oct, 17:37


🎙️ ፈራ ፍራቴ

መስማት ማቆም ከብዶኛል የእውነት ምን አይነት መዝሙር ነው 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

12 Oct, 17:21


እግዚአብሔር በእናንተ ህይወት ውስጥ ይሳካለት 🔥

አዶናይ

09 Oct, 17:09


300 ዲናር ለእግሮቹ 😭 30 ዲናር ለሰውነቱ 🤯

ይሄ እውነት በአንድም በሌላም መልኩ በእናንዳንዳችን ህይወት ውስጥ ይኖራል ብዬ አስባለሁ፤ ትናንት ይሁዳ ላላወቀው የኢየሱስ ሰውነት ሰላሳ ዲናር ዋጋ ሲሰጠው ማሪያም ግን ሰላሳ ዲናር ለተሰጠው ሰውነት እግሮች ከሶስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣውን ውድ ሽቶ አፈሰሰችበት ፤ የተወደዳቹ ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ በእናንተ ህይወት ውስጥ ለኢየሱስ ዋጋ ስጡት ብትባሉ ስንት ትሰጡት ይሆን ለእግሮቹስ ምን የሚሰበር ነገር ይሆራቿል ? ከእርሱ ጋር መዋልና እግሩቹ ስር መቆየት በፍፁም ኪሳራ አይደለም እንደ ማርያምም ውዱን አልባስጥሮስ ሽቶ እግሮቹ ላይ መስበርም ማባከን አይደለም፤ በመንፈስ ቅዱስ በኩል የጌታ ዋጋ እየገባቹ ሲመጣ እናንተ ህይወት ውስጥ ትናንት ላይ ትልቅ ቦታ የነበራቸው ነገሮች ቀስ በቀስ ዋጋ እያጡ ይመጣሉ።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

06 Oct, 17:18


የሰጠኽኝ እንዳይወስደኝ 😭

አዝኖላቸው አምስቱን እንጀራ አምስት ሺ አድርጎ ካበላቸው በኃላ በንጋታው ሰጪውን ረስተው የተአምር እንጀራ ፍለጋ ኢየሱስን ይፈልጉት ጀመር ትናንት የተሰጣቸው እንጀራ በአንድ ቀን ከሰጪው ወሰዳቸው ዛሬስ እኛን ምን ይሆን የወሰደን ተጠቀሙበት ብሎ የሰጠን ገንዘብ ወይስ አገልግሉበት ብሎ የሰጠን መድረክ ? የቱ ይሆን ? አሁን ላይ ሰይጣን ከወሰደብን ነገር ይልቅ ትናንት ከጌታ ተቀብለነው ዛሬ ላይ እኛን የወሰደን ነገር ይበልጣል። ሰለሞን ጥበብን ፣ ሳምሶን ሀይልን ፣ ይሁዳ ደግሞ ደቀ-መዝሙርነት የተቀበሉት ከጌታ ነበር ነገር ግን ሁሉም የተሰጣቸውን ነገር እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ባለማወቃቸው ምክንያት ኃላ ላይ የተሰጣቸው ስጦታ ከሰጪ እንደበለጠባቸው መጽሐፍ ይነግረናል፤ እናንተ ቤት ግን ሰጪው ንጉስ ይሁን🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

04 Oct, 17:15


ገንዘብ ወይስ ነፍስ ?

መቼም አሁን በ Airdrop ዙሪያ መጥፎ ነገር ብናገር ብዙዎቻቹ ትቀየሙኛላቹ ፤ ነገር ግን ለአሁን የ Airdrop ጉዳይ አግባብ ነው ወይስ አይደለም ማለቱን ትተን ከጀርባ በወጣቱ ልብ ላይ እየሰሩትን ያለውን ስራ በጥቂቱ እንመልከት... እንደምታውቁት ገንዘብ የሁላችንም ደካማ ጎን ነው በተለይ ለወጣቶች ታዲያ በዚህ ደካማ ጎናችን በኩል መጥተው የያዝነውን እውነት ቀስ በቀስ በገንዘባቸው እያባበሉ እየነጠቁን እንደሆነ ስንቶቻቹ አስተውላቿል ? አሁን ብዙዎቻቹ በቀላሉ ገንዘብ ብንሰራ ችግሩ ምኑ ጋር ነው ልትሉኝ ትችላላችሁ እኔም በቀላል መንገድ ገንዘብ ማግኘት ስህተት ነው እያልኳቹ አይደለም ነገር ግን እንዲህ መስቀል በሚዘቀዝቁ እና በጌታ ስራ ላይ በሚቀልዱ ድርጅቶች ስር ሆኖ ታፕ ታፕ እያደረጉ ገንዘብ መሰብሰብ ለጭለማው መንግስት ድጋፍ እንደመስጠት ነው የሚቆጠረው፤ እነኚ ድርጅቶች ለጊዜው የሆነ ገንዘብ ሊሰጧቹ ይችላሉ ነገር ግን ከገንዘቡ ባለፈ ዋናው አላማቸው እናንተ ለመጨረሻው ዘመን ያላቹን ንቃት ማጥፋትና የጌታን መምጣት እንድትረሱት ማድረግ ነው፤ ስለዚህ እንደ መንፈሳዊ ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ ቆም ብላቹ አስቡበት

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

29 Sep, 17:31


ከፍርሀቶች ሁሉ ውዱ ፍርሀት ከአባታቹ ጋር ያላቹ ህብረት ሲቀዘቅዝ እና መፀለይ ሲያቅታቹ የሚሰማቹ ፍርሃት ነው፤ ጌታ በሌለበት መዋል ስታበዙ፣ ከፍቃዱ መስመር ስትርቁ የሚሰማቹን ፍርሃት ውደዱት።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

27 Sep, 17:32


የአባትዬው ስፍራ

ትዝ ይላቿል ሉቃስ 15 ላይ ያለው የጠፋው ልጅ ታሪክ ? እዚህ ታሪክ ውስጥ የጠፋው ልጅና የአባትዬው የሀሳብ ልዩነት ይገርመኛል፤ ልጅ ከአባቱ የድርሻውን ንብረት ከወሰደ በኃላ ወደ ሩቅ ሀገር ጠፍቶ የልቡን እያደረገ ገንዘቡን ያጠፋል ታዲያ በዚህ ጊዜ ትናንት ከአባቱ ይልቅ ያመነው ገንዘቡ ቀስ በቀስ ሲከዳውና የሚበላው ሲያጣ የግድ ህይወቱን ለማስቀጠል ሲል ትናንት ልጅ በነበረበት ቤት እንደ ባሪያ ለመኖር ይወስናል፤ ተበዳይ አባት ግን ያን ሁሉ ጥፍት ረስቶ ልጄ አንድ ቀን ሊመለስ ይችላል በሚል ተስፋ ለጠፋው ልጁ የእጅ ቀለበት እና ለሰውነቱ ጥሩ ልብስ እያዘጋጀ እንዴት ሮጦ እንደሚያቅፈው ያስባል ታዲያ በመጨረሻ ልጅ የትናንቱን ጥፍት እየሰበ ከወሰነው ባርነት ይልቅ አባት ልጅነቱን እያሰበ የወሰነው ክብር በልጦ ተገኘ

የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች እናንተ ትናንት ላይ ያጠፋቹትን ጥፍት እያሰባቹ ለራሳቹ ከሰጣቹት ስፍራ በላይ ጌታ ልጅነታቹን እያሰበ ያዘጋጀላቹ ያ የክብር ስፍራ ይበልጣል።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

26 Sep, 17:12


የትውልዱ አባቶች 😍

እናንተ ተርባቹ የዘመናቹን ትውልዶች የክብር ርሀብተኛ አደረጋቹት🔥

አዶናይ

18 Sep, 17:56


እንደ ወንድም አንድ ነገር ልበላቹ ያው ብዙዎቻቹ ወጣቶች ናቹ ወጣት ደግሞ በየቀኑ ፈተና ውስጥ ነው በተለይ ደግሞ በዚህ ጊዜ .... ለምን ከጌታ ቤት Back አታደርግም፣ ለምን Porn አታይም ፣ ለምን ከአለም ጋር አትመሳሰልም፣ የሚሉ ድምጾች በየቀኑ የያዛቹትን ታላቅ እውነት ከእጃቹ ላይ ነጥቀው ተራ ሰው ሊያደርጓቹ
ይታገላሉ ... አዎ ልክ ነው በዚህ ዘመን ሁሉም መጥፊያው መረብ ውስጥ ሊያስገባቹ ይሞክራል ነገር ግን የተወደዳቹ ምን ያህል ጥላት ሊያጠፋቹ ቢሞክርም እናንተን የያዛቹ ጌታ ግን ፈፅሞ
እንደማይጥላቹ እወቁ ብዙ ልብ ሰራቂዎችብዙ በኃጢአት እንድትወድቁ የሚፈልጉ ሀሳቦች ቢኖሩም ከሁሉም በላይ ግን ፀንታቹ እንድትቆሙ የሚያደርጋቹ የምህረት እጅ እንዳለ አትርሱ በዚህ ሰዓት ደክማቹ፣ አቅም አታቹ ይሄን መልዕክቴኝ የምታነቡ የአባቴ ልጆች ካላቹ እግዚአብሔር የደከሙበትን ልጆቹን ወደ እርሱ የሚጠራበት ምህረት የሚባል የፍቅር ቋንቋ እንዳለው ልነገራቹ ፈልጋለው።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

አዶናይ

16 Sep, 17:14


የእግዚአብሔር ምህረት ይግነንላቹ 🔥

አዶናይ

14 Sep, 17:39


🎙️ባስቀመጥከኝ ስፍራ

ይሄን መዝሙር በሰማሁ ቁጥር በመንፈስ እነካለሁ🔥 ምን አይነት መንፈስ የሞላበት መልዕክት ነው 🥰

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost