👋 ሰላም ሰላም ወዳጆች እንኳን ለቅዳሚት አደረሳችሁ✨ የዛሬዋ ቅዳሜ ለየት ያለችና ጠጠር ያለ ሃሳብ የተነሳባት ነበረች ።
እንዴት አትሉም ሁላችንም የምንፈራውና የማንደፍረውን ሃሳብ "ሞት" ነበር የመወያያ ርዕሳችን ፦
ወዳጆች እናንተስ ስለሞት ምን ታስባላችሁ ?ሞት ምን ይመስላችኋል?እናንተ የየራሳችሁን መልስ እስክትመልሱ እኔ የተሰጡ ሃሳቦችን እየነገርኳችሁ ልቆይ፦
"የመጀመሪያው ሃሳብ ሞት የእድል በር ናት ወደ አምላክ መጠጊያ ናት "
"ሞት የስጋና የነብስ መለያየት ነው "
"ከፅንስ እኩል ሞት ይፀነሳል"
"ለዚኛው ህይወት ማብቂያ ለወዲያኛው መጀመሪያ ናት "
እውነት ግን ከዚህ አለም በኋላ ህይወት የለም?
አንዲት እህቴ ምን አለች መሰላችሁ" ሞት እውነት ነው ግን መጨረሻ አይደለም" ለምን መሰላችሁ " Reincarnation ስላለ We can't be sure if death is the end of our life." አለችን
አስባችሁታል ግን ከዚህ በኋላ ሌላ ህይወት ቢኖረን?
ስለ ሞት ይሄ ከተባለ ዘንዳ ሞትን አብዛኞቻችን ለምን እንፈራለን ግን ሞትን መፍራት አለብን እንዴ?መፍራት ከሌለብን እንዴት ፍርሃታችንን እንጋፈጥ ?
ምን ታስባላችሁ? እኔ እስከዛ ከተሰነዘሩ ሃሳቦች ጨረፍ ላድርግ፦
"ነብስ ሞትን አትፈራም ስጋ ብቻ ነው ሞትን የምትፈራው ለነብስ ዘላለማዊ ማረፊያ ናትና"
"እንፈራዋለን ግን የፍርሃት መጠናችን ይለያያል"
"ለእምነታችን ቅርብ ከሆንን አንፈራውም"
"በጣም ልንናፍቀው የሚገባ ነገር ነው ከሞት በኋላ ያለውን ህይወት" (ከሃይማኖት አንፃር)
"አዲስ ነገር ስለሆነ እንፈራዋለን ከለመድነው መውጣት ያስፈራል ለዛ ነው እንጂ የምንፈራው ነገር ሆኖ አይደለም "
እስኪ ግን የህይወት ትርጉም ለአንቺ/ለአንተ ምንድነው?ሞት በመኖሩ ግን ትርጉሟን አታጣም ?
እንደቀደመው እላችኋለሁ እናንተ አሰቡ እኔ ወዳጆች የሰጡትን ሃሳብ ልቀጥል፦
"ነብሳችን ይፀድቃል ብለን የምንሰራው ስራ ከሞትን በኋላ ያለውን ፍራቻ ስለሆነ ግዴለሽ አንዳንሆን ያደርገናልና እንዳውም ትርጉም ይሰጠዋል"
እኔ በግሌ ተስማምቻለሁ እናንተ ምን ይመስላችኋል ?
"መስራት ያለብንን ሰርተን ከሞትን ትርጉም አለው ካልሆነ ነው ትርጉም የሚያጣው "
"ሞት ራሱ የሆነ መዳረሻ ነው፣ አላማ፣ ግብ ነው (ምሳሌ:ሰማዕታት )"
ሞትን የምንለምደው ይመስላችኋል? ግን እኮ ሁሌም የሞት ዜና ለሰው ልጅ አዲስ ነው ምናልባት አሁናዊ ሁኔታችን ትንሽ ቢያለዝበን አንጂ …
"የህይወት ሁኔታችን ወስኖን እንለምደዋለን(ምሳሌ: ወታደር ሞትን አይፈራም )
"የሞትን ቅንጣትን በምድር እንቀምሳለን ለዛ ለምደነዋል/እንለምደዋለን "
"ሁሌም አብሮን ነው ምክንያቱም እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም ነው"
"ሁሌም አብሮን ነው ብዙ ከዚኛው ህይወታችን ጠፍተን የተመለስንበት ሁኔታዎች አሉ "
"ሁሌም አብሮን ነው ንጥሻችን መሃል እንኳን ለሰከንዶች ነብሳችንና ስጋችን ተላቆ ነው የምንመለሰው ስለዚህ የሚለመድ ነገር ነው "
የዛሬ ሃሳብ መቼም በጣም ያስገርማል አይደል 😄 መቼ ነው መሞት የምትፈልጉት ?እንዴት ነው መሞት የምትፈልጉት ? ይሄ ብቻ መሰላችሁ ከሞታችሁ በኋላ ምን ይባልላችሁም ተባልን እኮ የዚህን ሃሳብ እንኳን ለመስማት ስለጓጓሁ መልሶቻችሁን ኮመንት ላይ አስቀምጡልኝ🙄
እናንተ መልሶቻችሁን እስክታዘጋጁ እኔ ልቀጥል ፦
"በተኛሁበት ሞቼ ራሴን ማግኘት "ከሞተ በኋላ ራሱን ማየት ይፈልጋል 🙂
"በምወደው ሰው እቅፍ መሞት ነው ፍላጎቴ "
"ስጋዬን ገድዬ መታመም አቁሜ ነው መሞት የምፈልገው "
"አሻራ ጥዬ መሞት ነው የምፈልገው "
"Romantic የሆነ ሞት ነው መሞት የምፈልገው"
"እኔን እያሰበ ፈገግ የሚል ሰው ኖሮ መሞት እፈልጋለሁ እንዲሁም
100 አመት ልደቴን አክብሬ በማግስቱ መሞት ነው የምፈልገው ደግሞም
በአለም ያሉ የሚደረጉ ነገሮች ልህቀት ጥግ ከደረሱ በኋላ መሞት እፈልጋለሁ "
እንደልማዴ ግን የመጨረሻዋን መወያያ ሃሳብ ለእናንተ እተዋለሁ ሞት ብርሃናዊ ገፅታ አለው ብላችሁ ታስባላችሁ ?
እኔ በዚሁ አበቃሁ ደህና ቆዩልኝ 🙏
📝 በማክዳ ጸጋዬ ( 3ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ተማሪ)
☑️ አድራሻችን Main Campus, Radio ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው
አዳራሽ።
🔘የቴሌግራም አድራሻዎቻችንን ላልተቀላቀላችሁ በታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።
👇👇👇👇
ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ!!
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@RvcClub
@RvcClub