ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store) @yoftahiebooks Channel on Telegram

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

@yoftahiebooks


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
የፈለጉትን መጻሕፍት በፈለጉት ጊዜና ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ስልክ👉 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ
ለማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት👉 @yoftahiebot
Facebook ፔጃችን #Like ያድርጉ👇
https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store) (Amharic)

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር የሚከተለው እስከዚህ ተሳታፊ ነው። እስከዚህ ተሳታፊ መጻሕፍት ለተለያዩ ገበያ ሰጪ ማዕከል ነው። እባኮትን ወዲህ ደግሞ በፈለጉት ጊዜና ሰዓት የተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። እናመሰግናለን፣ ዎይም የጥበብ ቃልን እናስተዳደርለታለን በሚለው ቅናሽን፣ ይደውሉ። ማንም ጥያቄ ማስተዋወቅ እና ሌላ ላይ፣ አስተያየት @yoftahiebot በተፅናፍና ሙሉ በተለይም ስልክ 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ። ፈሸሽን ፈሸሽን፣ ፅሁፍ ከፅሁፍ Facebook ፔጃችን #ለገምገሙ ያድርጉ፣ ስለተቀራበ፣ ፈለጉ፡https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

15 Feb, 19:26


የመካከለኛው ክፍለዘመን ተዋስኦዎች ውስጥ ይልቁንም በእስልምና-ክርስትና ተዋስኦ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት ሊቃውንት መካከል ግንባር ቀደሙ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን እንደሆነ ይታወቃል። የዚህ ታላቅ ሊቅ ሥራ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ከፍተኛ ቦታ እንዳለው ይታወቃል። ይህን ለመረዳት የሚፈልግ በመምህር ኤፍሬም ክንዱ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ይህን ሥራ በማንበብ መገንዘብ ይችላል። የቅዱሱ በረከት ይደረብን፣ አሜን።
ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Feb, 18:55


ባሕረ ሒሳብ ( ሐሳበ ባሕር)
( የዘመን መቁጠሪያ)

      አድራሻችን
               👇
+251918004191   +251902093535
    Contact - @yoftahebooks
    t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Feb, 15:39


https://www.facebook.com/share/v/16DJ8kSpBa/

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

10 Feb, 12:08


❗️ጀምስ ብሩስ የሰረቀው መጽሐፈ ሄኖክ
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
እንሆ ለ፲፭ ተኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በቃ። መጽሐፉን የተረጎሙት እራሴላስ ጋሻ ነህ።
ይህ መጽሐፍ የተመሠረተው ሚካኤል ኒብ በጥንቃቄ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በተረጎመው በኢትዮጵያዊው መጽሐፈ ሄኖክ ላይ ነው፡፡ (የኢትዮፒክ መጽሐፈ ሄኖክ፤ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ) ይህ ትርጒም
አሁን ካሉት ከየትኞቹም ትርጒሞች የተሻለ ነውም ብዬ አምናለሁ፡፡
ስለ መጽሐፈ ሄኖክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ከጥቂት ዓመታት
በፊት ስለ መጨረሻው ዘመን ትንቢታት በማጠናበት ጊዜ ነበር፡፡
መጽሐፉን አግኝቼ ሳነበው በጣም የተለየና ያልተለመደ ዓይነት ሆነብኝ፡፡
“ማነው እንዲህ ዓይነት ግራ አጋቢ መጽሐፍ የጻፈልን? አልኩኝ፡፡ሄኖክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘፍጥረት ላይ በጥሩ ነገር እንደተጠቀሰ አውቃለሁ፡፡
በሄኖክ መጽሐፍ ውስጥም በስም ባይሆንም ስለ ሙሴና እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ያደረጉት ጉዞ በስውር ተጠቅሷል፡፡
በዚህ መሠረት መጽሐፈ ሄኖክ የተጻፈው ቶራ (ብሉይ ኪዳን) በተጻፈበት ጊዜ አካባቢ (ማለትም በ1400 ከክ.ል.በ) አካባቢ መሆን አለበት የሚል ንድፈ ሐሳብ አመጣሁ፡፡ ነገር ግን ከብዙ ምርምር በኋላ
ይህንን ማረጋገጥም ሆነ ሌላ ንድፈ ሐሳብ ማግኘት አልቻልኩም፡፡
ስለ እንስሳት ስለ መጭው ዓለም የተተነበየበት የመጽሐፉ ክፍል በርግጥም ከሙሴ በኋላ ስላለው ጊዜ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሙሴን የሚያክልን ሰው በእንስሳት አምሳል አድርጎ መጽሐፍ ለመጻፍ ማን ሊደፍር ይችላል?
መጽሐፈ፡ ሄኖክ ኢትዮጵያዊ፡፡
ይህንን መጽሐፍ ለማዋቀር የተጠቀምኩባትን ትርጒም የሠራው
ሚካኤል ኒብ ባደረገው ሰፊ ጥናት እንደተረዳው መጽሐፉ ከክርስቶስ
መምጣት በፊት በብዙ ሀገሮች ይታወቅና ይነበብ የነበረ መሆኑን ነው፡፡
በተለያዩ ቦታዎች ተጠቅሶ የሚገኘው ይህ መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን
በጥንቃቄ የጠበቁልን ይሄው መጽሐፍ እንደሆነም ተረጋግጧል፡፡
በስተመጨረሻም ይህ መጽሐፍ ከሌላ ምንጭ ልናገኛቸው ስለማንችላቸው ቀደምት ክስተቶች ለማወቅ ብቸኛ ምንጭ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡
ሄኖክ በመጽሐፉ በእርሱ ዘመን ስለነበሩ ስልጡን ባሕል ስላላቸው የእግዚአብሔር መላእክት ስለሚባሉ ሕዝቦች የጻፈልን ሲሆን መጽሐፉ ራሱ የተጻፈው በመላእክት ትእዛዝ ነው፡፡
በአካዳሚኩ ዓለም በሰፊው የሚታመነው ከ200 እስከ 300 (ከክ.ል.በ)
አንድ የናወዘ አክራሪ ሃይማኖተኛ መጽሐፉን እንደጻፈው ነው፡፡ እኔ ግን
ይህንን ለመደገፍ በቂ ምክንያት የለም ብዬ አምናለሁ፡፡
ይህንን መጽሐፍ ሊጽፈው የሚችለው ሰው ስለ ሀገራት ስምም ሆነ ስለ ሃይማኖቶች ምንም የማያውቅ መሆን አለበት፡፡በጸሐፊው ገለጻ ጠባቂዎቹ መላእክት የሚላቸው ባለ ፈዛዛ ቢጫ ቀለም ጸጉር ባለቤቶች ሲሆኑ ከምድር ሴት ልጆች ጋር ለመሴሰን ከሰማይ
ኮብልለው የመጡ መሆናቸውን ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በትክክል የተቀመጡትን ትንቢታት ጨምሮ ሌሎችም ማስረጃዎች ግን መጽሐፉን በቅዱስነት የሚያዩት ሃይማኖቶች እንኳን ያጡት ነገር ነው ብዬ
አምናለሁ፡፡
በመጨረሻም በራሴ በኩል መጽሐፉ በሚባልለት ልክ በአግባቡ የተጠበቀ ጥንታዊና እውነተኛ እንደሆነ ደምድሜያለሁ። መጽሐፈ ሄኖክ ኢትዮጵያዊ ተብሎ በኦክስፎርድ ዬንቨርስቲ ተመራማሪዎች ከኢትዮጵያ እንደመጣ ስላመኑበት "መጽሐፈ ሄኖክ ኢትዮጵያዊ" ብለው ሰየመውታል።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

10 Feb, 11:50


ጾመ ነነዌ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአጽዋማት ቀኖና መሠረት ሰባት የዐዋጅ ጾም አጽዋማት አሉ። ከሰባቱ አጽዋማት አንዷ በዕለታት ተወሳክና በዓመቱ መጥቅዕ ድምር ውጤት ወይም በመባጃ ሐመር የምትውለዋ ጾመ ነነዌ ናት።

ጾመ ሰብአ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ጾም) የምትጾመው ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ ፴፭ ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም፤ አይወጣም ማለት ነው፡፡ በዚህም ቀመር መሠረት የ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ነነዌ የካቲት ሦስት ጀምሮ በአምስት ያበቃል፡፡

ጾመ ነነዌን የጾሙት በነነዌ የሚኖሩ ሰዎች በአምላካችን እግዚአብሔር ትእዛዝ እና በነቢዩ ዮናስ ነጋሪነት ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት አምላካችም ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ እንዲሄድ አዘዘው፡፡ (ዮናስ. ፬፥፲፩)

እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” ብለው ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑም ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔርን የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ፣ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡

ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ፤ (ዮናስ ፩ እና ፪)፡፡ መጀመሪያ ከተልእኮው ቢያፈገፍግም “ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፦ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ” እንደተባለው ነቢዩ ዮናስ የኋላ ኋላ ወደ ነነዌ ሄዶ የእግዚአብሔርን መልእክት ዐውጇል። (ዮናስ ፴፫፥፬) በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎችም እንዲህ አደረጉ፤ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ” (ቁጥ.፭) እንዲል፡፡

መጽሐፉ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር እንደማራቸው ይገልጻል፡፡ (ዮናስ ፫) ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አምላካችን ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ (ዮናስ ፬) ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም ለቅጣት የመጣው እሳት እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቅ ዛፎች ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ የእሳቱ ወላፈን ነክቷቸው ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ በንስሐ በጾምና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው ከጥፋትና መዓት ድነዋል።

እኛንም ካለንበት መከራ፣ ችግርና ሥቃይ እንዲያወጣን፣ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲያኖረን እንደ ነነዌ ሰዎች ንስሐ እንግባ፤ በጸሎት፣ በጾምና በበጎ ምግባር ተወስነን በሃይማኖት እንጽና!

አምላካችን እግዚአብሔር ቸርነቱን ያብዛልን፤ አሜን!
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

10 Feb, 11:14


           ናዋዥ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
          6
      አድራሻችን
               👇
+251918004191   +251902093535
    Contact - @yoftahebooks
    t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

07 Feb, 14:58


" ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት፤ ትልቅም ለመባል በርግጡ የሚገባት ነው፤ ይህች አገር አንድ ትልቅ መሪ ያገኘች እንደሆነ የመላው አፍሪካ ገዥ ለመሆን ትችላለች። ይህ ቃል ሲነበብ ምናልባት አንድ አገሪቱን አፍቃሪ የሆነ ሰው እንደስሜቱ የተናገረው ይመስላል። እንደ እውነቱ ከሆነ አገሪቱን የግዛታቸው ጥገኛ ለማድረግ ከሚከጅሉ ከአንዳንድ የአውሮፓ መንግሥታት በስተቀር በትክክለኛ አስተያየት ለሚመለከቱ ሁሉ ሊያምኑ የሚችሉበት አያሌ ምክንያቶች አሉ። . . . "
ዐድዋ እና ምኒልክ
#በጸሐፊ ትእዛዝ ገብረሥላሴ
እና
በግራዝማች ዮሴፍ
#አሰናኝ ናምሩድ ዘርዐ ያዕቆብ
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

06 Feb, 09:11


ሰው ሳይኮን በቅጡ መልአክነት መ^ቀላወጡ
================================
ሳተናው!

አንድ ወንድምህ በፈተና ተንጦ፣ በንባብ ረግቶ፣ በልምድም በስሎ ያገኛቸውን መራር ሐቆች በምክር መልክ አቅርቦልሃል፤ አንተ ግን በወደድከው ኑር!

የዘመኔን ትውልድ በተለይም መንፈሳዊ መኾን፦ በመንፈሳዊነቱ አባቱንና አምላኩን ማወቅ፣ ባወቀውና በገባው ልክም መኖር ፈልጎ ብዙ ከሚያባክኑት ርቆ የመጣውን ወንድሜን ምን አጠፋው አትሉኝም?

በሉኛ?

በቅጡ ሰው ሳይኾን መልአክነትን እንዲቀላወጥ መማሩ!

ከሰውነት ልክ፣ በሰውነት ቅጥ፣ በተለይም በወንድነት ቁና በአባወራነት ግርማ በመከራ ተጠቅጥቆ፣ ተሰፍሮ፤ በዋናነት ለመጣበት ዓላማ ሲቀጥል ግን ለራሱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጆቹ፣ ለቤተሰቡ፣ ለማኅበረሰቡ፣ ለቤተክርስትያንና ለሀገር ይተረፈረፍ የነበረው ወንድሜ፤ መልአክነትን የመንፈሳዊነት ግብ አድርገው በጋቱት መምህራን ከሰውነት ራቀ፣ ወደቀ፣ ደቀቀ፣ ....።

ይህ ሰው ኾኖ ተፈጥሮ ራስን እንደ መላእክት መቁጠር በተለይ ካቶሊካውያን ዘንድ የተለመደ መጀመሪያ ካህናቱን ሲቀጥልም ማኅበረ ምዕመኑን አልጫ ያደረጉበት መንገድ ሸፍጥም ነው!

በተለይ ከደርግ መውደቅ በኋላ የመጡ፣ ቀድመው የነበሩና ያንሰራሩ(እንደ ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ዓይነት) ትውልዱ ሰው ሳይኾን በቅጡ መልአክነትን እንዲናፍቅ፣ እንዲስል፣ እንዲመኝ፣ እንዲለማመድ አድርገውታል።

ስለኾነም ወገኔ በሰውነቱ የተሰጠውን ጸጋ ቀብሮ፣ ከሰውነት ግብርና ምግባር ርቆ፣ ከሰው ጋር እየኖረ ሰውነት ባሕርዩን ክዶ ከመላእክት ወገን ለመደመር፣ ለመቆጠር፣ ይናፍቃል! ሲያምረውም ይቀራል እንጂ መቼም አይኾንም!

ሲጀመር መልአክነት የሚያስመኝ ምንም ነገር የለም!

የማይኾን፣ የማይቻል፣ የማይጠበቅ፣ የማይደረግ ነገር ይቻላል ብለውት፤ ራስ ማንነቱን አስኮንነውና አስጥለው መልአክነትን አጽድቀው አስናፍቀው ግተውት፤ ከሰውነት ተርታ፣ አባቱ ሊያድነው ወዶና ፈቅዶ ከለበሰው ስጋ፣ በሚመለክበት እሪና ካስቀመጠውም ሰውነቱ ለይተውት ሲያበቁ፦ ሰው ኹን ይሉታል!

እንዴት ይኾናል?

ወንድሜን! እኔን!

የሚደንቀው ነገር ሰውነቱን በሰውነቱም ያለ ጸጋ ሰጦታውን፣ በተለይም በወንድነቱ ተለይቶ የተለገሰውን ወንድነት መክሊቱን፦ እንዲንቅ፣ እንዲጠየፍ፣ እንዲለይ፣ እንዲጥል፣ እንዲቀብር ካደረጉት በኋላ በእነርሱ ሊፈጽማቸው የነበሩትን ጽድቅና ፍትሕ ከእርሱ ይጠብቃሉ።

እነርሱ በጽሑፍና በመጻፍ በመድረክም ማላዘናቸው አይቀርም እኮ! ነገር ግን የሚጮኋትን መሬት ላይ አውርደው አይሠሯትም፤ በጣታቸውም አይነኳትም!

ግራ ተጋብቶ፣ ግራ ገብቶትም ወንድሜ ዝም ቢል! "ትውልዱ ፈዛዛ ነው! ደንዛዛ ነው! ይሄ ትውልድ እንኳን ተነገሮት እንዲህና እንዲያ ቢደረግም አይገባውም! ይበለው!" ይላሉ።

ታናሼ! ወንድሞቼን ስለ ሰውነት ከምንም በላይ ግን ስለ ወንድነት ማን ነገራቸው? ሌላውን ቅጥያ ተውትና "ሰው" የመኾንን ኩነት፣ በተለይ ደግሞ "ወንድ" የመኾንን ልዩነትንስ ማን ዐሳያቸው!

ወንድነታቸው በዚያም ያሉ ባሕርያት የኃጢያት ምክንያት እንጂ ጽድቅ መፈጸሚያ መሣሪያ መኾናቸውን ምን ያክሎቹ ተማሩ! እንዲያ መኾኑንስ ካወቁት ምን ያክሎቹ በእነርሱ ላይ ሠለጠኑ አበለጸጓቸውም!
ብዙዎቹ መልአክነትን የሚናፍቁ አይደለምን!

ግን ለምን?

በቅጡ ሰው ሳንኾን? ውጤቱስ ምን ሊኾን?
ቅዳሜ የካቲት 8 2017 ዓ.ም. ኑና ራሳችንን እንፈትሽ!

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

05 Feb, 07:19


እስኪ ተጠየቁ
ዮሐንስ አድማሱ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
         
      አድራሻችን
               👇
+251918004191   +251902093535
    Contact - @yoftahebooks
    t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

04 Feb, 15:58


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
         
      አድራሻችን
               👇
+251918004191   +251902093535
    Contact - @yoftahebooks
    t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

04 Feb, 06:19


" - - - #ፓና የግእዝ ቃል ሲሆን መብራት ማለት ነው። መብራት ሲበራ ጨለማ ይርቃል። ይህ #መጽሐፍ ቢነበብም የዕውቀት ጨለማ ይርቃልና፤ መጽሐፉ ፓና ግእዝ ወቅኔ ተብሎ ተሰይሟል። - - -"
ፓና ግእዝ ወቅኔ
ዲያቆን ይኸነው አንዱዓለም (ኢ/ር)

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
         
አድራሻችን
👇
+251918004191   +251902093535
    Contact - @yoftahebooks
    t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

17 Jan, 13:37


የፕሮፌሰር ኤመረተስ ሽብሩ ተድላ 85ኛ ዓመታቸውን በአክብሮትና በምስጋና ፕሮግራም በድምቀት ተከበረ!

(ይትባረክ ዋለልኝ)

#Ethiopia | የፕሮፌሰር ኤመረተስ ሽብሩ ተድላ 85ኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋሊያ መፅሐፍት አዳራሽ በድምቀት ተካሄደ::

የእኚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር 85ኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም ላይ የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ጓደኞች የሆኑት ፕሮፌሰር ዘሪሁን ወልዱና የፕሮፌሰር በላይ ስማኒ እንኳን ለ85ኛ ዓመት የልደት ቀንህ አደረሰህ ብለው የክብር ካባ አልብሰዋቸዋል::

እንዲሁም ሠዓሊ ወንደሰን ከበደ ለፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ያለውን ከፍተኛ ክብርና ምስጋና ለመግለፅ ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን የ7500 ዓመት ታሪክ የሚተርከውን በነሐስ ተቀርፃ እና ከሴንትራል አፍሪካ በሚገኝ "ማሆጋኒ " በተሰኝ ልዩ እንጨት የሰራውን የጥበብ ስራ ሰጥተዋቸዋል::

በተጨማሪም ሠዓሊ መስፍን መብራቱ በእንጨትና በወርቅ ቅብ መደብ የሰራልኝን ልዩ ሥጦታ እነኚህ ሁለት ምሁራን አበርክተውላቸዋል::

በዚህ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የቀድሞ ተማሪና ጓደኛ ፕሮፌሰር ዘሪሁን ወልዱ እንደተናገሩት " ጋሽ ሽብሩ እድሜውን ሙሉ በማስተማር በመመራመር ለሐገሩ ብዙ የሰራ አሁንም እየሰራ ያለ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው::

ለሐገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ምሁር የ85ኛ ዓመት የልደት ቀኑን በማስመልከት ይህንን ፕሮግራም ያዘጋጃችሁትንም ከልብ አመሰግናለሁ:: ጋሽ ሽብር እንኳን ለ 85 ኛ ዓመትህ አደረሰህ!" በማለት ተናግረዋል::

ፕሮፌሰር በላይ ወልዱም በበኩላቸው ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በሙያቸው ለሐገራቸው የሰሯቸውን ስራዎች በማንሳት አድናቆታቸንና አክብሮታቸውን ገልፀው 85 ኛ ዓመትህ አደረሰህ! አሁንም ረጅም እድሜ እመኝልሃለው ብለዋቸዋል::

ሌላው በፕሮግራሙ ላይ ተገኝቶ የነበረው ደራሲ ዘነበ ወላ የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን ለሐገር ያበረከቱትን አስተዋፅኦ እና የንባብ ባህል በማድነቅ ወጣቶች ከእርሳቸው የንባብ ባህል ብዙ ሊማር እንደሚገባ ተናግሯል:: ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉም የ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን የሕይወት ታሪክ ለታዳሚው አንብቧል::

በመጨረሻም ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ለታዳሚው ባሰሙት ንግግር " በጓደኞቼ አማካኝነት ከብዙ ንግግር በኃላ ወደ እዚህ እንድመጣ የተነገረኝ በመፅሐፍህ ላይ ውይይት አለ ተብዬ ነው:: እዚህ ስደርስ ግን የሆነው ሌላ ነው::ዛሬ 85ኛ ዓመት የልደት ቀኔን በማስመልከት ይህን አይነት ፕሮግራም ስለተዘጋጀልኝ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ" በማለት ተናግረዋል:: በመጨረሻም ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ከታዳሚው ጋር የመፅሐፍ ፊርማና የፎቶግራፍ ፕሮግራም አካሂደዋል::

የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የ85 ኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን ይህ የአክብሮትና የለምስጋና ዝግጅት እንዲሳካ በማድረግ ከፍተኛውን አስተዋፅዖ ያደረገችውን ወ/ሮ ሐና ይገዙ (ቡክ ኮርነር) ከልብ እናመሰግናለን:: እንዲሁም ሲቲ ሐሰን ( ዋሊያ መፅሐፍት)፣ ሠዓሊ ወንደሰን ከበደ፣ ሠዓሊ መስፍን መብራቱ፣ ደራሲ በሁሉም አለበልና የማስታወቂያ ባለሙያ ቢንያም ዩሐንስን ከልብ እናመሰግናለን::

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

16 Jan, 05:06


" የትምህርት ሥርዓታችን ባለ ጥሩ ስብዕናም፥ ጥሩ ባለሙያም አያደርግም። " ዓለማየሁ ዋሴ (ዶክተር)

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

13 Jan, 04:03


መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
   አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

13 Jan, 04:02


መጽሐፈ ቀለሚንጦስ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
   አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
  ➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Jan, 07:54


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Jan, 07:52


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን!!


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን👇
🇪🇹 ባሕር ዳር ቀበሌ 04
➠ ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

26 Dec, 05:27


#እነሆ_አዲስ_ነገር
እርገተ ኢሳይያስ
በመምህር ማዕበል ፈጠነ የሽዋስ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

07 Dec, 12:47


ላምባ በአስኳትራ
በአማኑኤል ደርበው

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                         
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

06 Dec, 07:40


ቅኔ ቊንቍኔ
የቅኔ መማሪያ እና ማስተማሪያ መጽሐፍ
በመምህር ዓብይ ለቤዛ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                         
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

04 Dec, 06:33


የኢትዮጵያ ሠራዊት
ከድል ወደ ውድቀት (1967-1983)
ደራሲ- ዶ/ር ፋንታሁን አየለ
የታተመበት ጊዜ- 2010 ዓ.ም.
#በ ውብሸት ሙላት
⨳⨳⨳⨳⨳
መጽሐፉ ታትሞ ለገበያ ከቀረበ ሰነባብቷል። በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ቋንቋም ጭምር ታትሟል። መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ ከዚያ ወደ አማርኛ ተመልሶ ነው የቀረበው። በተለያዩ መድረኮችም የምረቃ ሥርዓት ተደርጎለታል፤ውይይትም ተደርጎበታል።

የመጽሐፉ ይዘትና ጭብጥ ማጠንጠኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ታሪክ ከ1967 ጀምሮ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ ማቅረብ ነው። በሌላ አገላለጽ በደርግ ዘመን የነበረውን የሠራዊቱን ታሪክ መመርመር ነው።

መጽሐፉ በመንደርደሪያነት ከ1933 ጀምሮ እስከ 1966 ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ሠራዊት አደረጃጀት፣ ሥልጠናውን፣ ትጥቁን ወዘተ ምን ይመስል እንደነበር በወፍ በረር አቅርቧል።

ከዚያም የዐጼ ኃይለሥላሴ መንግሥት ወድቆ ደርግ ሥልጣን ከያዘበት እስከ ወደቀበት ባሉት ጊዜያት መካከል በመሐል አገርም፣በምሥራቅ ከሶማሊያ ጋር ፣በሰሜን ከሻዕቢያና ከወያኔ ጋር በተካሔዱት ውጊያዎች የሠራዊቱን ድልም ውድቀትም የታሪክ የምርምር ውጤት አቅርቦልናል።


በእነዚህ ጊዜያት መካከል ሠራዊቱ በምሥራቅም በሰሜንም በነበሩት ጦርነቶች የነበሩትን ኹነቶች መቼ፣ የት፣ ምን፣በማን፣ እንዴትና ለምን እንደሆኑ በጥልቀት መርምሯል።

በምሥራቁ የአገራችን ክፍል ከሶማሊያ ጋር የነበረው ጦርነት ሠራዊቱ በስምንት ወራት ውስጥ በድል አጠናቆታል። በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ የሶማሊያ ሠራዊት በቁጥርም፣ በመሣሪያም ከኢትዮጵያ ይበልጥ ነበር። ይሁን እንጂ በአጭር ጊዜ ተደራጅቶ፣ ተዘጋጅቶ፣ ታጥቆና ዘምቶ በድል አጠናቆታል። የኢትዮጵያን ሠራዊት ለድል ያበቁት ምክንያቶችም በመጽሐፉ ተገልጸዋል።

የሰሜኑ ጦርነት የጀመረው ከምሥራቁ አስቀድሞ ቢሆንም የሰሜኑ የሽምቅ ውጊያ (Guerrilla)፣ የምሥራቁ መደበኛና (Conventional) በመጠኑም ቢሆን ግዙፍ ነበር። መደበኛና ግዙፉን የሶማሊያ ጦርነት በአጭር ጊዜ ያሸነፈ ሠራዊት፤ ከሽምቅ ውጊያ የጀመሩትን ሻዕቢያና ጀብሐ፣ ወያኔና ኢሕዴንን ወደ ግማሽ ሚሊዮን የተጠጋው ግዙፉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንዴት ማሸነፍ ተሳነው? ለሚለው ጥያቄ መጽሐፉ በዝርዝር ምላሽ አለው።

የመጽሐፉ ትኩረት የኢትዮጵያ ሠራዊት ድልና ውድቀት ስለሆነ የሌሎቹን ጥንካሬና የድል ምክንያቶች እምብዛም አይዳስስም።

በመሆኑም መጽሐፉ ሠራዊቱ በየዐውደ ውጊያዎቹ የተቀዳጃቸውን ድሎችና ሽንፈቶች፣ በአጠቃላይ በጦርነቱም ለምን እንደተሸነፈ በዝርዝርም በጥቅልም ምክንያቶቹን አቅርቧል። የምልመላ ኹኔታውና የሕዝብ ድጋፍ መቀነስ፣ የሠራዊቱ አደረጃጀት፣ ዕዝና ቁጥጥር ጋር የተገናኙ ችግሮች፣ በሎጅስቲክስ ዘርፉ የነበረው ሻጥርና ችግር፣ የካድሬዎችና የወታደራዊ መሪዎች ግንኙነት የፈጠረው ቅያሜ፣ የሠራዊቱ የወታደራዊ መረጃ ስለላ፣ የአፀፋ ስለላና ደኅንነት ዘርፍ የነበረው ድክመትና ሴራ፣ የተሳሳተ የፀረ አመፅ (Counterinsurgency) ስትራቴጂ እና የሠራዊቱ መሰላቸት ለውድቀቱ በጥቅል በምክንያትነት ቀርበዋል።

መጽሐፉ አሁንም ከትሕነግና ከሸኔ ጋር እየተደረገ ላለው ውጊያና መከላከል የሚጠቅሙ በርካታ ትምሕርቶች አሉት። በተለይ የኢትዮጵያ ሠራዊት ኃላፊዎችና አመራሮች ቢያነቡት በእያንዳንዱ ውጊያም በጥቅል በጦርነቱም ሠራዊቱ የተሸነፈበትን ምክንያቶች በጥልቀት ስለተጠና አኹን የገጠመንን ጦርነት (ከሸኔም ከትሕነግም ጋር) በድል ለማጠናቀቅ ምን ማድረግ እንደሚገባ ትምሕርቶቹ ብዙ ናቸው።

ከሠራዊቱ አመራሮች ባለፈ የክልል የፀጥታ ኃይሎችን የሚመሩ አካላትና ኃላፊዎች ከሠራዊቱ ጋር (Horizontally) የሚኖራቸውን ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት በደርግ ዘመን በአየር ወለዱ፣ በኮማንዶው፣ በስፓርታኪያዱ፣ በእግረኛው፣ በሚኒሻው ወዘተ መካከል የነበረው የጎንዮሽ ያልሰመረ ግንኙት ያስከተለው ዳፋ ምን እንደነበር በመረዳት ለአኹኑም ወሳኝ መልእክት ነው።

በመደበኛ ይሁን በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሳተፈው፣ አስተያየት የሚሰጠው፣ የሚጽፈው፣ የሚተነትነው ወዘተ ቢያነበው መልካም ነው። ወደ ሠራዊቱ የሚደርስ አሉባልታ፣ ፕሮፓጋንዳ፣ ሐሜት ወዘተ ለሠራዊት ውድቀት የሚኖረውን ድርሻ መረዳት ያስችላል።

እናም ያነበባችሁትም ድጋሜ ብትከልሱት፣ ያላነበባችሁትም ብታነቡት ታተርፉበታላችሁ። እኔም ስለመጽሐፉ መጻፌ ለዚህ ነው።

∞∞∞∞∞∞∞∞
[ማስታወሻ፦ ዶ/ር ፉንታሁን የወታደራዊ ታሪክ (Military History) ተመራማሪና መምሕር ናቸው። መጽሐፉ ለዶክትሬት ድግሪ ማሟያ ያካሔዱት የጥናት ውጤት ነው። ውጊያ የተካሔደባቸውን ቦታዎች በአካል ጎብኝተው፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መዛግብትን ለረጅም ጊዜያት አጥንተው፣ በርካታ የጦር መኮንኖችን ቃለመጠይቅ አድርገው ያቀረቡት ሥራ ነው።]

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

03 Dec, 10:01


እንኳን ለሃያ አራቱ (፳ወ፬ቱ) ካህናተ ሰማይ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

02 Dec, 09:54


ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                         
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

02 Dec, 08:23


የሁለት ከተሞች ወግ
በቻርልስ ዲክንስ
ተርጓሚ ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                         
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

29 Nov, 08:26


የጎጃም ትውልድ በሙሉ ከአባይ እስከ አባይ
በአለቃ ተክለ-ኢየሱስ ዋቅጀራ የጻፉት ግርማ ጌታሁን እንዳዘጋጀው
#እና
ጥንታዊ የጎጃም ታሪክ ከ5500 ዓ.ዓ-350 ዓ.ም
በአበረ አረፈዓይኔ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

28 Nov, 13:50


ገበያ ላይ በብዛት ከማይገኙት መጻሕፍት መካከል
እነዚህ በመደብራችን ያገኛሉ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                         
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

22 Nov, 11:26


ገድለ ፮ቱ ቅዱሳን ዘገዳመ ጎረጎር
ዘውእቶሙ
ብፁዕ አቡነ መርዓዊ
ብፁዕ አቡነ ምሰሶ
ብፁዕ አቡነ ደንቆሮ
ብፁዕ አቡነ ሞአብራ
ብፁዕ አቡነ ሙሴ
ብፁዕ አቡነ አላሽኝ

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

20 Nov, 12:06


በገበያ ላይ የጠፋው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት
' አራቱ ኃያላን ' መጽሐፍ አንድ ኮፒ በመደብራችን ይገኛል። ይፍጠኑና የግልዎ ያድርጉ

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

20 Nov, 11:13


ታሪክ ነገሥት
በ መምህር ደሴ ቀለብ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

19 Nov, 11:33


"ኦርቶጵያ"
በቄስ ዶክተር ጆን ቢንስ ተፅፎ በራሴላስ ጋሻነህ የተተረጎመ።
መሰረት መብራቴ
ክርስትናና ኢትዮጵያ እንደምን ተዋወቁ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ለኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ ባህል፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ምን አበረከተች? ምንዳዋስ ምን ሆነ?
ቤተ ክርስቲታኒቱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? ጥርስ ውስጥ ያስገባት የ 2000 ዓመት ጉዞና መጪው ፈታኝ ጊዜ፣ እንዲሁም ተስፋዋስ ምንድነው? የሚሉትና መሰል ሀገራዊ እና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች በስፋት የተዳሰሱበት መፅሐፍ ነው።
ፀሀፊው ዶክተር ጆን ቢንሰን በካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ጥናት ማዕከል ተጋባዥ ፕሮፌሰር እንዲሁም በካምብሪጅ የምትገኘው የታላቋ ቅድስት ድንግል ማርያም ቄሰ ገበዝ ናቸው።
ብዙ ጊዜ በውጭ ሀገራት ፀሀፊዎች ስለኢትዮጵያ እና ስለ ቤተክርስቲያን የተፃፉ መፃህፍት አንዳንዶቹ ላይ የማስተውለውን የታሪክ ክፍተት አላየሁበትም። እንዲያውም ግሩም በሆነ አተራረክ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክትስቲያን ታሪክ፣ ሥነ-መለኮት፣ ጥነተ ታሪክ፣ አሁናዊ ተግዳሮት፣ መፃኢ ተስፋ እና ለቤተ ክትስቲያኗ ያላቸውንም ልባዊ ፍቅር ያየሁበት ነው።
የእንግሊዘኛውን ቅጂ PDF ከአሳታሚው ለማግኘት ችያለሁ፤ “The Orthodox Church of Ethiopia History” by John Binns
አመሰግናለሁ።
ተርጓሚው በጥሩ ሁኔታ አቅርቦታል።
ነፃ ምልከታዬ ነው።
ሰሞኑን ቦሌ አካባቢ የሚገኝ ጋዝ ስቴሽን ነዳጅ ለመቅዳት ወረፋ ይዤ መፅሀፍ ከሚሸጥ ወንድም ነው የገዛሁት።
አንብቤው ስለወደድኩት በንባብ ክረምታችሁን ዘና እንድትሉበት ለመጋበዝ ነው።
መልካም ቀን!
#እናንብብ #እናብብ
#readingislife
#history
#ethiopiaorthodoxtewahidochurch⛪️

መጽሐፉን ዳጎስ ባለ ቅናሽ #በሽያጭ_ላይ_ነን!!!

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks
ለጥያቄዎ
t.me/@yoftahiebot
fb : https://www.facebook.com/yoftahiebooks/

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

19 Nov, 11:02


መጅኑኑ ለይላ
(እብዱ የፍቅር ሰማዕት)
በሷሊት አስታጥቄ

                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

19 Nov, 10:48


ማን ይናገር የነበረ
የታኅሣሡ ግርግርና መዘዙ
በ ብርሃኑ አስረስ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

16 Nov, 09:51


7DAYS
BY DEON MEYER

' One of the best crime writers on the planet '
Daily Mail
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                          
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

15 Nov, 05:59


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

13 Nov, 10:51


ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                          
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

12 Nov, 15:16


የኤፌሶን ወንዝ
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

01 Nov, 06:15


3 ቀናት #በጣና_ገዳማት_እና_አድባራት ስንቆይ

ራስን ከዓለም ጫጫታና ጫና፣ ከየብስ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ፣ የትራፊክ መጨናነቅ የተሽከርካሪ ድምጽ ወደ ማይሰማበት፣ የሰው ወከባ ወደ ማይታይበት፣ ንጋት ብቻዋን እንደ ሰማይ በተዘረጋው ጣና ላይ ወደ ምትፈነጭበት፣ የሰማይ አድማስ ከምድር ጋር ገጥሞ መንገድ መስመር መሄጃ የሌለ በሚመስልበት መሐል ላይ ተሁኖ የብስ ለዓይን ጥቅሻ ያህል በሚናፈቅበት የገዳማቱ መልክዓ ምድር ህሊናን ወደ ሚሰርቅበት አረንጓዴዎቹ አጸዶች አይን ወደሚስቡበት ከነሱ በሚወጣ ነፋስ በሹክሹክታ በጆሯችን በሚነጋገሩበት የተለያዩ የዓለም ሀያላን ሀገራት ምሥጥሩን ለማወቅ ብዙ የደከሙለት ግን መርምረው ያልደረሰበት ድንቅ ሀይቅ።

በየገዳማቱ ደርሰን ከድካማችን ታግሰን የአባቶቻችን የትህትና ጥግ ተመልክተን ከስጋ ድካም አርፈን የምድርን በረከት ቀምሰን የእመቤታችን ተሰዳ ያረፈችበትን እያየን ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ጋር እየተነጋገርን የጌታን ነገር የምናደንቅበት ፀሀይ ወደ አድማሷ ስትገባ ያለምንም ከልካይ ጽዮን ላይ ቁጭ ብለን በስስት የምንሰነባበትበት በመዝሙራት ከቅዱሱ ከያሬድ ጋር የምናመሰግንበት በአባቶች የቀን እና የማታ ጉባኤያት ለነፍሳችን ተጨማሪ ምግብ የምንመገብበት ብዙ ስንቅ የምንይዝበት ጣናን ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ ተጉዘን የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራእየተመለከትን የምናደንቅበት ሀይቅ

ከቦታዎቹ እና ለቅዱሳን ከተገባላቸው ቃል ኪዳን በረከት አግኝተን ወደ መነሻችን ተመልሰን በዓይናችን ያየነውን ግን ለዘመናት በኅሊናችን ቀርጸን የምናስቀምጥበት አምላክ እድሜ ለንሰኃ ጊዜ ለፍስኃ ሰጥቶ መልሶ እንዲያገናኘን ለበረከትም እንዲያበቃን እየሰብን በናፍቆት የምንሰነባበትበት ድንቅ ጉዞ🥰 ካየሁት ነው የጻፍኩት ከሰማሁት ሳይሆን 
እና  ምን ለማለት ነው ይሄ ሁሉ ነገር 🥰መጥታችሁ እዩ ለማለት ነው 🤩🤩

ጉዞዉ ከጥቅምት 29- ህዳር 1 ለሦስት ቀን ሲሆን ምግብ እና መጠጥን ጨምሮ 1600 ብር ሲሆን

ትኬት_የምናገኝባቸው_ቦታዎች

➥አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቱ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ
➥ታዬ ሞላ ስቴሽነሪ
➥ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር
➥ቤተ ጊዮርጊስ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ
➥ማኅደር መጻሕፍት መሸጫ ሱቅ
➥አባይ ማዶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቱ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ

ለተጨማሪ መረጃወች
0940908594//0920114370//0902092705
ይደዉሉ

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

28 Oct, 12:56


የሁሉ
በዶ/ር ዳዊት አሰፋ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                          
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

19 Oct, 13:44


#አዲስ መጽሐፍ በሽያጭ ላይ ነን።
ላምባ በአስኳትራ
በአማኑኤል ደርበው
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

14 Oct, 09:06


የከበደ ሚካኤል ሥራዎች ውስጥ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
                          
                         አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191   +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

12 Oct, 08:21


➤ ሜሎሪና ስውር ጥበብ
➤ ሜሎሪና ቴሎስ
➤ ሜሎሪና ሕይወቴ
የናሁሰናይ ፀዳሉን መጻሕፍት #እየሸጥን ነው።
"ሕይወት ድራማ ነች፤ ነዋሪዎቿም የሚተውኑትን ገጸባህሪ ይመርጣሉ። በዚህ ተውኔት ውስጥ አንዳንድ ሰዎች በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ ዋና ገጸባህሪ መኾን ይፈልጋሉ። የሚበጅህን እኔ አውቅልሃለው፣ እኔ እወስንልሃለው በማለት የራሳቸውን ገፀባህሪ ትተው የሌሎች ገፀባህሪን ለመተወን ይባዝናሉ።... "
ሜሎሪና -ሕይወቴ ገጽ 73
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

12 Oct, 04:41


እነዚህ የሕይወት ተፈራ መጻሕፍት ይሸጣሉ።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Oct, 07:12


ድጋሜ እትም
ከመዝ ነአም
እንዲህ እናምናለን
መምህር ገብረ መድኀን እንየው

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

11 Oct, 05:23


#የመጽሐፍ_ትዝታ
የመጽሐፉ ርእስ፦ ሀኖስ
ደራሲ፦ ንጉሴ አየለ ተካ
የታተመበት ዓ.ም፦ 1990
ዘውግ፦ ልብወለድ
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
#በሽያጭ ላይ ነን
አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
+251918004191 +251902093535
Contact - @yoftahebooks
https://t.me/yoftahiebooks

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)

10 Oct, 15:24


ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን -እንዴት ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ፈለጉ?

-ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮነን የተወለዱት 1942 ዓ.ም. ደብረ መዊእ ማርያም ነበር፡፡ የድጓ ሊቅ ናቸው፡፡ ድጓ በጉንጩ ማለት ትችላላችሁ፡፡ ጎንደር ቤተልሔም አስመስክረዋል፡፡ ደቡብ ጎንደር ጽርሐ አርያም ዙር አባ አረጋዊ ዘልቀው ዝማሬ መዋሥዕት ተመረቁ፡፡ ወንበር ዘርግተው ማስተማር ጀመሩ፡፡ እናም በመርዓዊ ማርያም ቤተክርስቲያን በድጓ መምህርነት ሲያገለግሉ በነበረበት ዘመን በአንድ አጋጣሚ ምክንያት ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ተነሳሱ፡፡ ለድጓ መምህሩ ደመወዝ የሚከፈለው ከአርሶ አደሩ እህል፣ ከሴቱ እና አባወራው ብርና ሳንቲም በመሰብሰብ ነበር፡፡ በዘመነ ደርግ 1968 ዓ.ም. አንድ ቀን ክፍያ ከሚያስፈጽሙት ጋር ሳንቲም ለመጠየቅ ሻይ ከምትሸጥ ሴት አዳሪ ቤት ዘለቁ፡፡ ክፍያ አስፈጻሚዎቹ “ለድጓ መምህሩ 50 ሳንቲም ክፈይ” አሉ፡፡ ያች ምስኪን ሴት “ምንም ነገር የለኝም አልክፍልም” አለች፡፡ ወዲህ ቢሉ ወዲያ እጅግ ቢለምኗት አልከፍልም በማለት በአቋሟ ጸናች፡፡ አስፈጻሚዎቹ ለእግድ በማለት ከቤቷ የሻይ በራድ ይዘውባት ወጡ፡፡ “እባካችሁ በራዴን መልሱልኝ” እያለች ለመነች፡፡ ፈጽሞ ሊመልሱላት አልፈለጉም፡፡ ከዛም ክፍያ አስፈጻሚዎቹ ከቤት ውጭ ሁነው “ክፍያ ክፈይ የድጓው መምህር እሳቸው ናቸው” አሏት፡፡ ያች ሴት የድጓ መምህሩን በላይ መኮንን ትኩር ብላ ዐየችና "ይህማ ወጣት አይደል ለምን ሠርቶ አይበላም?" አለች፡፡ ያኔ ሊቁ በላይ እድሜያቸው 27 ዓመት ነበር፡፡ ክፍያ አስፈጻሚዎቹ በንግግሯ በጣም ሳቁ፡፡ ነገር ግን ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮነን አልሳቁም፡፡ ንግግሯ ልባቸውን ነክቶት ነበርና፡፡ "እውነቷን ነው:: ስማር ለምኜ መምህር ሁኜ ለምኜ" በማለት ለምን ሠርቸ አልበላም? አሉና ሠርቶ ለመብላት ዘመናዊ ትምህርት መግባት አለብኝ በማለት ቆርጠው ተነሱ፡፡ ሁል ጊዜ ሲያስታውሱ ያች ሴት ያን ንግግር ባትናገርና ልቦናየ ባይነካ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ገብቸ አልማርም ነበር ይላሉ፡፡ ለሊቅ አንድ ቃል ትበቃዋለች የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ በብዙ ውጣ ውረድ እንዳይማሩ ግፊት በሚያደርግ የማኅበረሰብ ሽሙጥና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተቋቁመው ዘመናዊ ትምህርቱን በ27 ዓመታቸው ከሕጻናት ጋር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየዋሉ በመማር ጀምረው በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ዘልቀው ተምረዋል፡፡ ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን ከዘጠኝ(9) በላይ መጻሕፍት ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡ በተለይ “ዕሴተ ትሩፋት ዘቅዱስ ያሬድ” በተሰኘ መጽሐፍ ይታወቃሉ፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት መጽሔት ላይ በቅዱስ ያሬድ ታሪክ ጉዳይ ጥናት አሳትመዋል፡፡ “ሕያው ልሳን ግዕዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት” የተሰኘ መጽሐፍን ለማሳተም አዲስ አበባ የነበራቸውን ቤት ለመሥራት መሠረት የጣሉበትን መሬት ሽጠው አሳትመዋል፡፡ ሊቁ እጅግ በብዙ ውጣ ውረድ ተምረው ያገኙትን እውቀት ለትውልድ ለማስተላለፍ በቃልና የጽሑፍ ሥራ የደከሙ ትልቅ ሰው ናቸው፡፡ ስለ ሊቁ ዝርዝር ታሪክ ማንበብ ለሚፈልግ በ2011 ዓ.ም. በታተመ “ማኅደረ ደራሲያን” በተሰኘ መጽሐፍ ከገጽ 43-57 እንድታነቡ ይመከራል፡፡

-አይደክሜው ሊቅ አዲስ መጽሐፍ "ሐመር ዘዮናስ" የተሰኘ በቅርቡ አሳትመዋል። ስለ መጽሐፋ የሚከተለውን ብለዋል "ሐመር ዘዮናስ" በሚል ርእስ ያዘጋጀሁት ይህ የታሪክ መጽሐፍ ከይዘት አንጻር ጠቅለል ብሎ ሲታይ ቤተ ክርስቲያኒቱ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን እምነቶችን ከተቀበለችባቸው ዘመናት ጀምሮ ለ3000 ዓመታት ያህል ‹‹የአብነት ትምህርት ቤት››ን ማእከል አድርጋ ለሥነ ጥበብ፣ ኪነ ጥበብና ለሀገር-በቀል ዕውቀቶች፥ እንዲሁም ለሀገር መንግሥት ግንባታ፣ ለሀገሪቱ አንድነትና ለሕዝቦችዋ አብሮነት ያበረከተችው ኹለንተናዊ አስተዋጽዖ የተቃኘ ሲኾን፤ አሁን የገባችበት ፈተናም እንዳለ ኾኖ ያሉዋትን መልካም ዕድሎችና ተስፋዎችን ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡"

-የሊቃውንትን መጽሐፍ በመግዛት እያነበብን እናበረታታ እንደግፍ፡፡
Yosef Fiseha Sewunet

3,022

subscribers

4,254

photos

43

videos