ጥቅምት 13
Oct 23
ፊልጶስ እና ናትናኤል
ዮሐንስ 1:43-46ን ያንብቡ። የፊልጶስ መልእክት በኢየሱስ ላይ ስላለው እምነት ምን አሳይቷል?
Save Notes
ልክ እንደ እንድርያስና እንደ ጴጥሮስ ሁሉ፣ ፊሊጶስም የቤተሳይዳ ሰው ነበር። ወዳጁ ናትናኤልን አግኝቶ ስለ ኢየሱስ ነገረው። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን “የእግዚአብሔር በግ” ብሎ ጠርቶታል። እንድርያስ ለጴጥሮስ “መሲሑን” እንዳገኘ ነግሮት ነበር። ፊልጶስ ግን ሙሴና ነቢያት የጻፉለትን ኢየሱስን “የናዝሬቱ ኢየሱስ” ሲል ጨምሮ ጠርቷል። ናዝሬት የሚለውን ሥም መጥቀሱ ከጓደኛው የሰላ ምላሽን አስከትሏል። ናትናኤል ለትንሿ ናዝሬት ከተማ ጭፍን ጥላቻ የነበረው ይመስላል። በእርግጥ ንጉሥ ከእንዲህ ዓይነቱ መንገድ ዳር ላይ ከለ ሥፍራ እንደማይመጣ የታወቀ ነው። ጭፍን ጥላቻ በእውነት ዋጋ ያለውን ነገር እንዳያዩ ሰዎችን በቀላሉ አይናቸውን ያሳውራል። ፊልጶስ ቀደም ሲል ከናትናኤል ጋር ካደረገው ውይይት ምናልባትም ጭፍን ጥላቻን ለመቋቋም ትክክለኛው መንገድ ከፍ ያለ ፍልስፍናዊ ወይም ሥነ-መለኮታዊ ክርክር ሳይሆን ግለሰቡ እውነቱን ለራሱ እንዲያውቅ መጋበዝ እንደሆነ የተገነዘበ ይመስላል። ዝም ብሎ “መጥተህ እይ” አለው። ያደረገውም ይህንኑ ነው። ሄዶ አየ። ዮሐንስ 1:47-51ን ያንብቡ። ኢየሱስ ናትናኤልን ማንነቱን ያሳመነው እንዴት ነበር? የናትናኤልስ ምላሽ ምን ነበር?
Save Notes
በቁጥር 46 እና 47 መካከል የሌለው ነገር ናትናኤል ለፊልጶስ ግብዣ የሰጠው ምላሽ ወሳኝ ዝርዝር ጉዳይ ነው። ምንም ቢሆን ግን ተነሥቶ ለማየት ሄደ። ከፊልጶስ ጋር የነበረው ወዳጅነት ከጭፍን ጥላቻ ይልቅ የበረታ ነበር፤ እናም ሕይወቱ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተለወጠ። ኢየሱስ ስለ ናትናኤል ጥሩ ቃላት ተናግሯል፣ “ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው” ብሎ ጠራው (ዮሐ. 1:47); ይህ ናትናኤል (በዮሐ. 1:46) ስለ ኢየሱስ ከተናገረው በጣም የተለየ ነው። ናትናኤል ኢየሱስን ከዚህ በፊት አግኝቶት ስለማያውቅ በመገረም መለሰ። ከዚያም ኢየሱስ ከበለስ ዛፍ ሥር እንዳየው የተናገረ ሲሆን፣ ይህ ጥቂት ንግግር ናትናኤልን አሳምኖታል። ናትናኤል እውነትን በመሻት በዚያ ዛፍ ሥር ሲጸልይ ኢየሱስ በመለኮታዊ መገለጥ ተመልክቶታል። ናትናኤልም መልሶ፦ “መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” ሲል ከፍ ያለ ኑዛዜን ተናገረ። ትንሽ የሚመስለው መገለጥ ወደ ትልቁ የእምነት ኑዛዜ እንዴት እንደሚመራ አስተውሉ።
@SabbathSchool @TekalignSorato