ቪርጎ
(ከነሀሴ 17 እስከ መስከረም 12)
- ቪርጎዎች ጣፋጭና ዝምታኛ ናቸዉ፣ ግን እያንዳንዷ ትናንሽ ነገር አታመልጣቸዉም፣ በዉል ይከታታሏታል። ጎበዝ አድማጭና ተንታኝም ስለሆኑ፣ ቁም ነገር ያለዉ ምክር መስጠት ላይ የተካኑ ናቸዉ። በአብዛኛዉ ደስተኞች፣ ነገር ግን በቅርባቸዉ ካለዉ ሰዉ ጋ ከተቀያየሙ፣ ደስታ ይርቃቸዋል፣ ይከፋሉ።
- ማንንም ለማስደሰት መጣር የለባቹም፣ ራሳቹ ላይ ትኩረት አድርጉ። ብቁና ምክንያታዊ በራስ መተማማን እንዲኖራቹ ያደርጋቹዋል። እንዲሁም ሚሰማቹንም በግልጽነት መናገር፣ ከለአላስፈላጊ ጭንቀትና ደስታ ማጣት ይከላከላቹዋል። ዘና ማለትና መዝናናትን አካላቹ በደንብ እንዲፍታታ፣ ዐእምሯቹ በደንብ እንዲያስብና የፈጠራ ክህሎቱንም እንዲያሳድግ ያግዘዋል። አንድ አንዴ ፍልስፍናቹንና ስለውደፊት ማሰብ ትታቹ አሁንን ብቻ አስቡ። ምግብ መስራት፣የጓሮ አትክልት መንከባከብ፣ ሲኒማ ማየት፣ ለየት ያሉ ምግቦችን መሞከርና በፊት የረሳቹትን አርት ለመስራት ሞክሩ።
- ሁሉንም ጥፋታቹን ወደ ራሳቹ በመዉሰድ ራሳቹን እንደ ጥፋተኛ አትዩ፣ ምክንያታዊነት ለናንተም ሆነ ለአጋራቹ ጠቀሜታ አለው፣ ሚሰማቹን ያለምንም መወዛገብ ጨዋ በሆነ መንገድ ግለጹ። ቪርጎዎች መስራት ሚትፈልጉትንና የተሰሩ ስራዎችን ሊስት ማየት ደስ ይላቸዋል፣ ብዙ ግዜም ቼክ ያደርጋሉ፣ ይሄም ስለሚሰሩት ስራ ጥንቅቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ይረዳቸዋል።
- ቪርጎዎች መጀመሪያ ላይ ሲታዩ ምንም ከሰዉ ሚግባቡ አይመስሉም፣ ትንሽ ግዜ ብቻ ስጧቸው፣ በደንብ ይግባባሉ፣ ሀሳባቸዉንም በነጻነት ይገልጻሉም ያወያያሉም። አእምሯቸዉን በደንብ ማለማመድና ማስሞከርን ይወዳሉ፣ ጫዎታዎችና ካልኩሌሽኖች ሊሆኑም ይችላል። ቪርጎዎች በራሳቸው ዛቢያ ፈታ ማለትን ይወዳሉ፣ ደስታ ከራቃቸዉ ግን ማንም አጠገባቸዉ ድርሽ እንዲል አይፈልጉም፣ ድንበራቸዉ ጠንከር፣ ፊታቸዉም ፈካ አይልም፣ ሰዉንም ለማስከፋት ቅርብ ይሆናሉ። ለራሳቸው ያላቸዉ ግምትም ይወርዳል።
.
.
.
.
.
.
.
.
.
ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ
ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን
ለመጋበዝ 👉🏼@zodiac_channels