ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚 @noahtoaels_idea Channel on Telegram

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

@noahtoaels_idea


ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። የምትስማሙባቸውን ለወዳጆ ሼር ያድርጉላቸው።🙏

@Noahtoael

በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ!

በዚህም ቻናል.!

፦አጫጭር አዝናኝ እና አስተማሪ ታሪኮች
፦ተከታታይ ታሪኮች
፦ትረካዎች
፦ግጥም እና ስነፅሁፎች
.......ያገኛሉ!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚 (Amharic)

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚 እንዴት አለባቸው? ኖህቶኤል ታሪካዊ ሀሳቦችን ለመጻሕፍትና ለትክክል የተጻፈ እና ማህበረሰብ ቀላል ነው። የአዲስ ትምህርት ልብስ በቀላሉ ከሚክክለው ኢሜላውያዳት ወይም የኢሜላውያዊ ልምድ ከመመርመር ብሎ ከተመለከተ ለሆነ የሚናገሩትን ሼር ያድርጉ። የትምህርት በዚህ ቻናል ጥናትንና ተመንፅና መንገድ ይጠቀሙ፡፡ ማጊስትያችሁን እናስታዋስ።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

28 Dec, 19:05


በህይወታችን የሚገጥሙን ፈተናዎች የመዳኛ ምክንያቶች ስለሚሆኑ ፈጣሪን አትፈትነኝ ከማለት ይልቅ ፈተናዎችን ተምሬ እንዳልፋቸው እርዳኝ ማለት ይበልጣል!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

28 Dec, 16:19


-አስፓልት እየተሻገረ ቶሎ በል እንጂ መኪና እንዳይገጭ ሲባል "ዜብራ ላይ ነኝ ከገጨኝ ጥፋቱ የእሱ ነው!" ከሚል ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል?

-እንቅልፌን ተኝቼ ጠርቶ ካስነሳኝ በኋላ "ቀሰቀስኩህ እንዴ?" ከሚል ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል?

-ምግብ እየበላው እንብላ ስለው "የተባረከ ይሁን" ብሎ ምራቁን እየዋጠ ምግቡ ላይ ከሚያፈጥ ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል?

-በፍቅር አውርቶኝ እኔ በሌለው ጊዜ በጥላቻ ከሚዘልፈኝ ሰው ጋር እንዴት መግባባት እችላለው?

መፅሃፍ እያነበብኩ መጥቶ እስከሚበቃው ካወራ በኋላ ሲጨርስ "እረበሽኩ እንዴ?" ከሚል ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል?

ዶይስቶቭስኪ የመዳኒት ስም ከሚመስለው ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል?


  እኮ እንዴት  መግባባት ይቻላል!¿ 🤔

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

28 Dec, 14:59


ሰዎችን የእውነት እንደምንወዳቸው ያለነሱ እንደማይሆንልን ውስጣችን እንዳሉ የምናሳያቸው በይቅርታችን ብቻ ነው ።ይቅር ስትላቸው ወይን ይቅርታ ስትጠይቃቸው ያኔ የእውነት ለነሱ ምንክል ቦታ እንዳለህና ምንያክል ውስጥህ እንዳሉ ትገልጥላቸዋለህ። እኔ አንተ ጋር ቦታ ቢኖረኝ ይቅር ትይኛለህ። አንተ ውስጥ ካለሑ ይቅር ትለኛለህ። ከልብህ ፈልገኸኝ ከልብህ ቀርበኸኝ ከነበረ ይቅር ትለኛለህ።ይቅርታ አንዳችን ባንዳችን ውስጥ ስለመኖራችን ብቸኛ ማሳያ ነው። እኔ ባንተ ውስጥ አንተም በእኔ ውስጥ መኖራችንን የምናሳየው በይቅርታ ነው ።በሌላ በምን እናሳያለን? ጓደኛህ በድሎህ ይቅር ካላልከው ምኑን አንተና እሱ ተሳሰራችሁ? ምኑን ከምንም በላይ ተፈላለጋችሁ?እንዲያ ከሆነማ ቀድሞውንም ያ ሳቃቹና ፍቃራቹ የሽንገላና የማስመሰል ነበር ማለት ነው ። ከበደሉ እሱ የሚበልጥብህ ከሆነ ይቅር ትለዋለህ ።እሱ ይቅርታ ካላለ ወይ አንተ ይቅር ካላልክ ቀድሞሞ ግንኙነታቹ ለግዜ ማሳለፊያ  መፈላለግ ነበር።ይቅርታ አድርጌልሀለሑ ስትለው ምን ያሕል እንደምትወደው ምን ያሕል እንደምትፈልገው ምን ያሕል አንተ ጋር ቦታ እንዳለው ታሳየዋለህ እንደገና እንድትረዳዱ እንደገና እንድትስቁ ትፈልጋለህ(ይቅር ስትል ብቻ ሳይሆን ይቅርታ ስትልም)ታድያ  ከዚ በላይ በምን ትገልጥላቸዋለህ?

ይቅርታ የማይንደው የተራራ አይነት የማይሽረው የቁስል አይነት የለም

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 19:57


በሂደት ግን የተረዳሁት ለካ ህይወት በጊዜ መጠን ሲርቁት የሚለዩት ነዉ። ብልጭ ሲል መከራና ስቃይ ይታየኛል:ብልጭ ሲል ስኬት ና አስተምሮ:ደሞ ብልጭ ሲል ፍርሀትና ወድቀት....
✍️ፍቅረ ማርቆስ ደስታ
የሚሳም ተራራ🖤🖇.......

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 19:53


ማናት?
.
.
ከፍጡራን በላይ ፣
        ከፀሐይ የበራች፣
ደምቃ የምትታይ፣
           በቀኙ የቆመች፣
ወርቅን ተጎናጽፋ፣
          ምሕረት የምትለምን፣
በኵሯን ታቅፋ፣
            አለም የምታድን፣
ቃላቶች ደርድረን፣
       ፅፈን የማንገልፃት፣
የጣፈጠ ስሟን፣
     ጠርተን የማንጠግባት፣
እዉን ይህቺ ማናት?
..................................
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 19:50


አሌክስ አብርሃም
.
.
.
.
አልተዘዋወረችም

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 19:46


ኦሾ ይህን ይለናል

<<እኔነትን ጥላቹ የሁለንተናው አካል መሆናቹሁን ከተረዳቹ ሞት የሚባል ነገር የለም።  ሞት ልክ አሮጌ ልብሳቹህን አውልቃቹ አዲስ አዲስ ልብም እንደ መልበስ ይመስላል 
     በቀላል ምሳሌ ላስረዳቹ
በእናታቹ ማህፀን ለ 9 ወራት ቆይታቹ ትወለዳላቹ ለዚህ ምድር ውልደት ሲሆን በእናታቹ ማእፅን  ለነበረው ይህወታቹ ግን መወለድ መሞት ነው ።   >>

ይህን አባባል እንዴት ተረዳችሁት!¿

    

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 16:42


አራቱ ስህተቶቻችን

•  አጥብቀን መያዝ ያለብንን ነገር በቀላሉ መልቀቃችን፣ በቶሎ መልቀቅ የሚገባንን ነገር ደግሞ አጥብቀን መያዛችን!!!

•  ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ነገር በነጻ መጠበቃችን፣ በነጻ የተሰጠንን ነገር ሰርተን አለማሳደጋችን!!!

•  የማይፈልጉንንና የማይጠቅሙንን ሰዎች መከታተላችን፣ የሚፈልጉንንና የሚጠቅሙንን ሰዎች ችላ ማለታችን!!!

•  መናገር በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ ዝም ማለታችን፣ ዝም ማለት በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ መናገራችን!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Dec, 16:34


ምን አጠፋሑና ታዝንብኛለሕ?ምን ወንጀል ሰራሁና ዳኛ በሌለበት ትከሰኛለሕ?ምን አጠፋሁና በፊትህ ፈገግታ ታለቅስብኛለሕ?ወጣትነትህን አባከንኩብሕ?
ወጣትነቴ እንደምስጥ ውስጥ ውስጤን ይበላኛል።ያለፈው ጊዜ ጥሎኝ የሔደው ጊዜ የማይመለሰው ጊዜ ይናፍቀኛል።
ወጣትነቱን እንደ አቧራ ንፋስ ውስጥ ለበተነ ሰው ምን ይቅርታ ይደረግለታል?ማንስ ደፍሮ"አይዞሕ ግድ የለም ባይሖን ትማርበታለሕ" ይለዋል?
ውብ ወጣትነቴ
ገነት ልጅነቴ
ከሩቅ እያየችኝ
እየናፈቀችኝ...

ምን ሰራሕበት አንተስ?
ተናገር በወጣትነትሕ ምን ሰራሕበት?ወይስ ምን ልትሰራበት ነው?

📜 ሌቱም አይነጋልኝ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Dec, 17:33


ህይወት አዙሪት ናት። ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።ራቁትክን ትወለዳለክ እርቃንክን ወደ መቃብር ትወርዳለሕ። በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለሕ፤ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለሕ።የህይወትን ትግል እየዳህህ ትጀምራለሕ፤አጎንብሰህ ትጨርሳለሕ።ዘመንም ተምኔታዊ ነው። መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሀል። ሰኞ ማክሰኞ ብለሕ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለሕ።ህይወት አዙሪት ናት፤መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው።የጀመርክበትን አትርሳ መጨረሻህ ነውና።የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለሕና።ልብ በል!ባለማወቅ ትጀምራለሕ፤በመዘንጋት ትጨርሳለሕ።እውቀት አላመጣህምና እውቀትም ይዘሕ አትሄደም።በለቅሶ ትጀምራለሕ በጭንቅ ትጨርሳለሕ።በሰው እቅፍ ትጀምራለሕ በሰው ሸክም ትጨርሳለሕ።ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው ከጸሐይ በታች አዲስ ነገር የለም።አለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በጸጸተን።ልብ በል!የአለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው፤ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን።
ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ ትመጣለህ።

📜 ዶ/ር አለማየው ዋሴ
        (መርበብት)

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Dec, 17:02


ሰው ለዝምታ ራቅ ያለ ገጠራማ ስፍራ ምርጫው ነው።

ለእንደኔ ላለ ከተምኛ ዝምታ የማይቻል ነው። ይልቅ ለነገሬ ሁሉ ለሊትን እመርጣለሁ። ሰማያዊ ሰማይ ብርሃን፤ብልጭ ድርግም የሚሉ የመንገድ መብራቶች፤ የግርግዳ ላይ ስዕሎች፤ በንፋስ የሚገፉ ስስ ፌስታሎች፤ በየጣርያው የሚዘሉ ድመቶች፤ ውሃ ያቆሩ ግርድፍ መሬቶች፤ የገደል ማሚቱ የዋጠው ጭር..ረጭ! ያለ ከተማ ውስጥ ዝም ማለት ባልችል እ'ኳ ከራሴ ጋር አወራለሁ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Dec, 05:45


እርግጥ መልፋትና መድከማችን ከጸጸት ያድነን ይሆናል ነገር ግን የስራው ውጤት የሚያመጣውን ጥቅም አይተካልንም ወይም በመሰራቱ ሊቀር የሚችለውን ችግር አያቀልልንም እናም ልናሳካው ያሰብነው ግብ እሩቅ ሆኖ አእምሯችንን እረፍት መንሳቱ፥ቋሚ ህመም ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም።በእርግጥም ግድግዳ የሚገፋ ሰው ስራ ሰራ የሚባለው ግድግዳው ሲንቀሳቀስ እንጂ የሰውዬው ልፋትና ድካም ታስቦ አይደለም።የሰው ልጅ ድካምና ጥረት ዋና ግቡ ከ ጸጸት መዳን አይደለም፤እርሱ የህመሙ ማስታገሻ ኪኒን ነው። ግቡ የታሰበውን ማሳካት ነው የተጀመረውን መጨረስ የተፈለገውን ማግኘት ነው።


             "ሚተራሊዮን"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Dec, 05:45


በእድሜ ዘመናችን መጀመርያ ወደ መጠንከርና መበርታት ቀጥሎ ኋላ ላይ ደግሞ ወደ መጠውለግና መጨማደድ መቀየራችንን እንረሳዋለን።ይህ የተፈጥሮ ህግ የማይቀየርና የማይቀር በመሆኑ ዋናው ነገር ለሁሉም ነገር በተገቢው መዘጋጀት እንጂ ለመርሳት መሞከር ግብዝነት ይሆናል።
መድከምና መዛል ወይም መጠውለግና መጨማደድ ብቻ ሳይሆን ካልተዘጋጀን መጠንከርና መጎልመስ፥መጎምራትና ማማርም አስቸጋሪ ይሆናሉ።ጉልበትና ውበት የሞት ወጥመድ ሆኖ ሊመጣ ይችላል።ወጣትነትም ጉልምስናም እርጅናም የራሱ የስነ ልቦና ዝግጅት ይፈልጋል።አእምሯችንን ከአካላችን ለውጥ ጋር ካላገናኘነው ከስጋ አካላችን ቀድሞ መገርጀፍ ወይም ከፈዘዘ አካላችን ጋር ያልተቀናጀ አስተሳሰብ ይዘን ሽማግሌ ሕጻን ወይም ህጻን ሽማግሌ ልንሆን እንችላለን።


            📜ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ
              ከ   "ሚተራሊዮን"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Dec, 17:03


ይህ ስእል "የማዕበል ትእይንት" ይባላል

ስእሉ የተሳለው ጆሴፍ ደዚሬ በሚባል ፈረንሳዊ እውቅ  ሰአሊ ሲሆን ወቅቱም እ.ኤ.አ 1927 ነው!!

ስእሉ ላይ እንደሚታየው አንድ ሰውዬ ከአንድ ጥልቅ ጉድጏድ ውስጥ አባቱን ለማውጣት ሲታገል ይታያል - ለማውጣት የሚቀሉት እና የሚቀርቡት ግን ሚስቱ እና ልጁ ናቸው::

ይህ ስእል በተለያዩ ባለሙያዎች የተለያዩ ትርጉሞች ተሰጥቶታል

በብዛት ከተሰጡት አንዱ እነሆ:

"ሚስቱ የሰውዬውን የአሁን ነባራዊ ህይወት ትወክላለች ልጁ ደግሞ የሰውዬውን ቀጣይ የነገ ህይወቱን ይወክላል:: በተቃራኒው ደግሞ አባየትየው ያለፈ ህይወቱን ነው የሚያሳየው:: ያለፈ ህይወቱን መልቀቅ ያቃተው ይህ ሰው የዛሬ እና የነገ ህይወቱ ሲያመልጠው ስእሉ ያሳያል"

"ከመቶ አመት በኃላም ይህ ስእል የብዙዎችን ህይወት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው" ይላሉ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Dec, 06:26


አንድ አመት ምን ያህል እንደሆነ ይገባሐል? አስበው።የዘጠኝ የአስር አመት ልጆች ሳለን ክፍል በመድገም አንድ አመት ብናጠፋ  ምንም አይደለም።በሀያ ስድስት፣በሀያ ሰባት አመታችን አንድ አመት ማጥፋት ግን ሌላ ነገር ነው።ምክንያቱም እነዚህ አመታት ከሀያ አምስት እስከ ሰላሳ አምስት ሰፈር ያሉት አመታት የሌሎቹን አመታት ሶስት አራት እጥፍ ዋጋ አላቸው።አሑን ነው ህይወታችንን ለመጨረሻ የምንቀርጸው።አሑን ነው ያለ የሌለንን ለሐገራችን ልናበረክትላት የሚገባን።አሁን ነው የኑሮ ስራችንን የምንመርጥበት የምንጀምርበት ጊዜ።አሑን ነው የኑሮ ጓደኛችንን የምንመርጥበት፣ትዳራችንን የምንቆረቁርበት ጊዜ።አሁን ነው።አሁን! አሁን! አሁን ነው ልጅነትም የማያታልለን፤እርጅናም የማይጫጫነን።አሁን ነው ፍሬ ለመስጠት ዋጋ ለማስገኘት የምንችለው።


📜 "ትኩሳት"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

23 Dec, 16:31


አንድ ቀን የአንድ ገበሬ አህያ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች። እና እንስሳዉ ለሰዓታት ጮክ ብላ እያለቀሰች ነበር። ገበሬዉ አህያዋን ለማውጣት ቢጥርም አልቻለም።

በመጨረሻም ገበሬው አህያው አርጅታለች እናም ጉድጓዱ ደርቋል ስለዚህ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት ጉድጓዱ መሸፈን ያስፈልገዋል ብሎ ወሰነ።

አህያውን ከጉድጓዱ ውስጥ ለማውጣት ሳያስብ ጎረቤቶቹን በጠቅላላ ኑና እርዱኝ ብሎ ጠራቸው። እያንዳንዳቸውም አካፋ ያዙና ቆሻሻ ወደ ጕድጓዱ ይጥሉ ጀመር።

አህያው እየሆነ ያለውን አውቃ በአሰቃቂ ሁኔታ አለቀሰች። ከዚያም ሁሉም ሰው የተወሰኑ ቆሻሻዎች ከጣሉ በኋላ ገበሬው በስተመጨረሻ ወደ ጉድጓዱ ተመለከተና ባየው ነገር ተገረመ። በእያንዳንዱ የቆሻሻ ክምር አህያዋ የሚገርም ነገር እየሰራች ነው። በአካፋው የሚጣልባትን በጠቅላላ እየረገጠች ከቆሻሻው አናት ላይ እየቆመች ነበር። በዚህም ወደላይ ከፍ እያለች ነበር። ይህን የተመለከቱት ሁሉም ሰዎች አህያዋ ከጉድጓዱ አፋፍ ላይ እንዴት እንደደረሰች በማየት ተደነቁ።

ህይወት ቆሻሻ ልትደፋባችሁ ነው። እና ሁሉም አይነት ቆሻሻ ከጉድጓዱ የመውጣት ዘዴ ነው። እያንዳንዳችን ችግሮቻችን መወጣጫ ደረጃዎች ይሆኑናል። ተስፋ ካልቆረጥን ብቻ ከጥልቁ ጉድጓድ መውጣት እንችላለን። እናም ህይወትም ሆነ ሌሎች ሰዎች የሚጥሉባችሁን እያንዳንዱን ቆሻሻ እናንተን ከመቅበሩ በፊት ቀድማችሁ ቅበሩት እላችኋለሁ!።


ይህን 5ት ህጎች ሁሌም አስታውሱ፦

1.ልባችሁን ከጥላቻ ነፃ አርጉ

2.አእምሮአችሁን ከሚያዘናጋና ከሚረብሽ ነገር ነጻ ይሁን

3.የሚያጋጥማችሁን ነገሮች ቀለል አድርጋችሁ ተመልከቱት

4.ብዙ ስጡ ትንሽ ጠብቁ

5.አብዝታችሁ ውደዱና ቆሻሻውን አራግፉ። ምክንያቱም በዚህ ህይወት ውስጥ "ችግር" መቀበርያ ሳይሆን መወጣጫ መፍትሔ ነው!።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

23 Dec, 07:43


እናም በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው።ህይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብ እና ተስፋን የተሞላች ናት!በዚህ አለም ሁሉ ነገር አበቃ አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል የምናውቀው እና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር ዙርያችን ጭው ያለ በረሀ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሪያለሁ።እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም ትጋት የተስፋ ልጅ ናት ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ሰለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና።


            📜  ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ
                         ከ"ሰበዝ"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

07 Dec, 17:22


ወንድሜ ለብር ብለህ ሕሊናህን አትሽጥ

My generation is saying :-
የት ነው የሚሸጠው? ብዙ አለኝ::እንደውም ላንተ እቀንስልሃለሁ:: ጓደኞቼም የሚሸጥ ብዙ ሕሊና አላቸው::

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

06 Dec, 16:18


ወተት ከተበላሸ እርጎ ይሆናል!... እርጎ ከወተት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው። በጣም የከፋ ከሆነ ወደ አይብ ይቀየራል...አይብ ከሁለቱም እርጎ እና ወተት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው... እና የወይን ጭማቂ ወደ ጎምዛዛነት ከተለወጠ ወደ ወይን ጠጅ ይለወጣል...ይህም ከወይኑ ጭማቂ የበለጠ ውድ ነው። ስህተት ስለሰራህ መጥፎ አይደለህም!...

ክሪስቶፈር ኮሎምበስ አሜሪካን እንዲያገኝ ያደረገው የአሰሳ ስህተት ሰርቷል። የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ ስህተት ፔኒሲሊን እንዲፈጥር አድርጎታል። ስህተቶችህ እንዲያሳዝኑህ አትፍቀድ። ፍጹም የሚያደርገው ልምምድ አይደለም። ፍፁም የሚያደርገው ከስህተታችን የተማርናቸው ስህተቶች ናቸው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

05 Dec, 16:43


🦋


መጨረሻውን ማስተካከል የምትችለው
መጀመሪያው ላይ ነው። መጀመሪያው
ደግሞ ሁሌ አሁን ነው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

04 Dec, 16:03


#ጠያቂ - መርዝ ምንድነው?

#ሩሚ- ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣ ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉጉት፣ ወይንም ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል።
.
#ጠያቂ - ፍርሃት ምንድነው?

#ሩሚ- እርግጠኛ አለመሆንን አለመቀበል ነው። እርግጠኛ አለመሆናችንን ብንቀበል ፣ ፍርሃትገድል ይሆናል።
.
#ጠያቂ - ቅናት ምንድነው?

#ሩሚ- የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል።
.
#ጠያቂ - ንዴት ምንድነው?

#ሩሚ - ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል።
.
#ጠያቂ - ጥላቻ ምንድነው?

#ሩሚ - ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል።

"አንድን ነገር በጥሞና እና በጥልቅ ከተረዳህ፣ በዛ ውስጥ ሁሉንም ነገር ትረዳለህ
"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

02 Dec, 12:51


ካታርሲስ (Catharsis)

የአሪስቶትል የፍልስፍና ሃሳብ ካታርሲስ /ስሜትን ማጥለል / ይባላል ። የካታሪስ ቲዎሪ ባጭሩ ሲቀመጥ ይህንን ይመስላል...

" አንድ ሰው የቅርብ የሆነ ዘመዱ ወይም ወዳጁ ሲሞት የሚያለቅሰው ለሟቹ ሰው በማዘን ሳይሆን በማዘኑና በማልቀሱ ግን ራሱ የሚያገኘው እፎይታ(relief) ስላለ ነው። በለቅሶውም የራሱ ሃጢያትና ክፋት ካሳ እንደሚያገኝለት ያምናል። "

በሌላ አገላለጽ አሪስቶትል ይህንኑ ሲያስረዳን...

"አንድ ንፁህ ሰው በሞት ሲቀጣ ብትመለከትና ብታለቅስ፤ ንፁህ ሰው ያለጥፋቱ በመሞቱ ሳይሆን ያለቀስከው ራስህን በሰውዬው ቦታ በማስቀመጥ 'እኔ በዚህ ሰው ቦታ ብሆንስ?' በሚል ስሜት ስለምትንገላታ ነው። እንግዲህ በሰው ሞት ውስጥ የራስህን ሞት ማየት ካታርሲስ ይባላል" ይለናል ።

ምንጭ ፦ "ጥበብ ከጲላጦስ"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

01 Dec, 15:03


አንዳንዴ እኮ ምንም ሳይጎድለን ትዕግስት ማጣት ብቻ ባለንበት ያስቀረናል። ይቺ አለም ትንፋሹን ዋጥ አርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሚያሸንፍባት መድረክ ናት።

ለምሳሌ መዝናናት ፈታ ማለት እያማረህ ግን ቆይ እስኪ ዛሬ ይለፈኝ ማለት ከጀመርክና ያን ጊዜ ለሚጠቅምህ ነገር ከተጠቀምከው አትጠራጠር ትክክለኛው መንገድ ላይ ነህ። ያ series movie ዛሬ ይለፈኝና ትንሽ ላንብብ ማለት ከጀመርክ ለውጡን በቅርቡ ታየዋለክ። ትዕግስት ማለት ገንዘብ አውጥቶ ፈታ ማለት ያምርህና ግን ለምን አንደኛዬን ጥሩ ጊዜ ሲኖረኝ አልዝናናም ብሎ ወጥሮ መስራት ነው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

01 Dec, 06:08


ለመኖር ሰው ሳይሆን ፈጣሪ ነው የሚያስፈልግህ!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

30 Nov, 16:16


በነገራችን ላይ ሁሌም ከእራሴ ጋር የምንነጋገርበት ብቸኛ ምክንያት፤ ሳወራው ስለሚያዳምጠኝ ነው 🤝🏼🤗

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

30 Nov, 07:39


ኤልያስ መልካ ፍቅር የያዘው ገና በአፍላነቱ ዘመን ነበር፡፡ የልጅነት መልኳ እንደ ማለዳ ጀንበር ቀስ እያለ ልቡን አሞቀው፡፡ ወደዳት፡፡ ግን አልነገራትም፡፡

ቤተሰቦቿ የቤተሰቦቹ ወዳጆች ስለነበሩ ፈራ፡፡ ወንድሞቿ ጓደኞቹ ስለሆኑ ተጨነቀ ቤታቸው ስትመጣ ደስ ይለዋል፡፡ ከእህቶቹ ጋር ስታወራ አተኩሮ ያያታል፡፡ ድንጋጤ የነገሰበት ሕይወት አልባ ሳቁን ባወራች ቁጥር ይለግሳታል፡፡

ፍቅሩ የአንድ ሰሞን አልሆነም፡፡ ወራት መጥተው ወራት ቢሄድም  ሊቀንስ አልቻለም፡፡

በዚህ መኸል ወሬ ሰማ፡፡ ሌላው የሰፈሩ ልጅ እንደሱው እንደሚወዳት አወቀ፡፡ ምን ማድረግ ይችላል መፍትሄው ሁለቱንም በዓይነ ቁራኛ መከታተል ነበር፡፡ ለጥቂት ጊዜያት በአሰበው መንገድ ቀጠለ፡፡

በኃላ ላይ ግን የልጅነት ፍቅሩ ቤታቸው መምጣት አቆመች፡፡ ዕድሜው ከፍ እያለ ሲሄድ ውሎዋ መርካቶ በሚገኘው የቤተሰቦቿ ሱቅ ውስጥ ሆነ፡፡

ኤልያስ አልሰነፈም፡፡ ጓደኞቹን እየያዘ መርካቶ ይሄዳል፡፡ ምክንያቱን ባይናገራቸውም በቅመማቅመም  ተራ በኩል እንለፍ ይላቸዋል፡፡ ይከተሉታል፡፡ ቆም ብሎ በዓይኑ ይፈልጋታል፡፡ ካለች ደስ ይለዋል፡፡ ከሌለች የት ሄዳ ይሆን እያለ ፈዝዞ ወደ ሰፈሩ ያመራል፡፡

አብሮ አደጎቹ ነገሩን ያወቁት ዘግይተው ነበር፡፡ ኤልያስ ባቅላባ ለመብላት ፒያሳ ድረስ በእግራቸው ሲወስዳቸው ኑሯል፡፡ ከአብነት ተነስቶም ኳስ ለመጫወት ጃንሜዳ ድረስ አስከትሏቸው ያወቃል፡፡

የመርካቶው  እንቆቅልሽ ግን ግራ ያጋባል፡፡ ያለምክንያት እናቶች በሚበዙበት ቅመማ ቅመም ተራ በኩል እንለፍ እያለ ሲጨቀጭቃቸው
የቅርብ ጓደኞቹ እኛ እንንገርልህ አሉት፡፡

ቤተሰቦቿ ከቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ወንድሞቿም ለእሱ ቅርቦቹ መሆናቸውን ስለሚያውቅ አይደረግም ብሎ ተከራከራቸው፡፡ መፍትሄው በቤት ስልካቸው እየደወለ፤ ለማውራት መሞከር ነበር፡፡ ዓይን አፋሩ ኤልያስ እየተርበተበተ ስልኩን ይመታል፡፡

ወደ ሕዝብ ስልኩ የሚከታቸው ሳንቲሞች ግን ትርፋቸው ኪሳራ ነበር፡፡ ገና ድምጿን ሲሰማ ሀሳቡ ይበተናል፡፡ እራሱን ለመሰብሰብ ሲጥር የከተተው ሳንቲም አልቆ ስልኩ ይዘጋል፡፡...... ቀሪውን ከመፅሐፉ ታነቡ ዘንድ ጋበዝኩኝ

ምንጭ፦ የከተማው መናኝ
  ➧በይነገር ጌታቸው

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

29 Nov, 17:07


ሰው ከ1 እስከ 20 አመቱ ንፋስ ነው። ይሮጣል ይከንፋል አንዱን ይዞ ሌላኛውን ለመያዝ። ከአንዱ አምሮት ወደሌላኛው አምሮት። እድሜው እራሱ 20 ላይ እንዴት እንደደረሰ አይታወቀውም። ከ20 እስከ 40 ደግሞ እሳት ነው። ጀብደኝነት ጉልበተኝነት ሁሉንም እችላለው ባይነት ይወርሰዋል። ከእሱ ውጭ ማንም የለም የትኛውም ሰው አይታየውም።

ከ40 እስከ 60 ውሃ ነው። ቅዝቅዝ ይላል ይረጋጋል። ንግግሩ ዘለግ ያለህ ዝምታ የሚያበዛ ሰው ይሆናል። ከ60 እስከ 80 መሬት ነው። ያጎነብሳል የእርጅና ግዜ ነው። አስታራቂ፣ ትዳር አስጀማሪ እና ለቅሶ አስለቃሽ ቀድሞ ተሰሚ የሚኮንበት ግዜ ነው። እዛ እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች "አሄ አፈር ለምንሆነው" "ምንድነው ይሄ ሁሉ ይኸው ትናንት እንተናን ቀብረን መጥተን ኸረ ተሁ" ማለት ያዘወትራል። ምን መሰላችሁ ሰው እድሜ ይመክረዋል!

    
  -አባ ገ/ኪዳን

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

28 Nov, 15:39


የአንድ አባት ምክር ፦

ሃብታም ነው ብለህ ፣ስልጣን አለው ብለህ ፣ ያሳልፍልኛል ብለህ ፣ ያግዘኛል ብለህ፣ ባለሃብት ነው ብለህ ቀልቡን ለመግዛት የምትሆነውን መሆን በፊቱ  ሞገስ ለማግኘት ብለህ  የምትሄደውን እርቀት ለአምላክ ብታደርገው
   
ታሪክህ ይቀየራል
!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

27 Nov, 17:24


💭
.
.
🤌በመጨረሻም የተረዳውት ነገር ቢኖር ብዙ ሚያውቁ እና የተሻሉ የሚመስሉ ሰዎች እንዳሰብናቸው አይደሉም በተቃራኒው ናቸው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

25 Nov, 12:44


እንደ ጨው

ጨው እንደ ሌሎች ቅመሞች መምሰል አያስፈልገውም። እንደ ሌሎች ቅመሞች ምንም አይነት መዓዛም የለውም። ነገር ግን ምግብ ያለሱ ጣዕም የለውም።

ጨው ንጹሕ አቋሙን ይጠብቃል
ጨው ገዢው ከመግዛቱ በፊት እንዲቀምሰው አይጠበቅበትም ምክንያቱም ጨው ከዘመናት በፊት ታማኝነቱን ስላረጋገጠ።

የእውነተኛ ሰዎች ለቦታ፣ ለታይነት ወይም ለመታየት አይታገሉም።
ውጤታቸው ለእነርሱ  በቂያቸው ነው።

ለመስማት መጮህ አያስፈልግም ሰዎች አስተዋይ ሰዎችን ለመስማት ዝም ይላሉ።

ሰዎች አንተን ከማመናቸው በፊት መሳደብ ከጀመሩ ታማኝነት ይጎድልሃል ማለት ነው።

ጨው ጣዕሙን ሊያጣ የሚችለው ከማንኛውም ነገር ጋር ሲቀላቀል ነው። ስለዚህ እራስህን መልካም እሴት ከሌላቸው ሰዎች ጠብቅ።

አንድ ቀን ሁላችንም ችግሮቻችንን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠን እንድንለዋወጥ ከተፈቀደልን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሁሉም በጸጥታ ራሱን ይዞ እንደሚወጣ እርግጥ ነው። ፍጹም የሆነ ሕይወት የሚባል ነገር የለም፣ ማንም አንድ ላይ ያለው  የለም። ፊታችን እንደሚለያይ ችግሮቻችንም እንዲሁ።

አንዳንድ ጊዜ የምትቀናባቸው ሰዎች፣ አንተ የምትኖረውን ህይወት እንዲኖራቸው ይመኙ ይሆናል ከአቅም በላይ አታስብ፣ በእርካታ ኑር፣ ያለህን ነገር ተንከባከብ አመስጋኝ
ሁን።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Nov, 16:25


ሞትን ለዘነጋው ልቤ፣ ደረቴን ደቃሁ አምርሬ ፥
ነጠላዬን አዘቅዝቄ፣ ሙሾ አወረድኩ ለራሴ ፥
አበባ ፈልጌ አኖርኩ፣ ከልብህ ስር ከመቃብሬ፤

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Nov, 15:48


ይጠቀይቁታል፦

"ወደዚህ የጥበብ እና የግንዛቤ ደረጃ እንዴት ደረስክ? የትኞቹን መጻሕፍት ብታነብ ነው?"

እሱም መለሰላቸው፡- ስለ ሰማውት አምሳ ወግ በጥልቀት አሰብኩ እና ሰባ ጦርነቶችን ተመልክቻለሁ፤ ብዙ መቃብሮችን ጎብኝቻለሁ፤ እጀግ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቀውሶች ውስጥ ኖሬያለሁ፤ እናም በጣም የምወዳቸውን ሰዎችን ቀብሪያለሁ።

፨ ቅናትን በዘመድ አይን አየሁትና መጠንቀቅን ተማርኩ።

፨ ጭካኔን ባፈቀርኩት ሰው አይን ውስጥ ሲተራመስ አየሁ በዚህም ዝምታን ተማርኩ።

፨ ከቅርብ ወዳጆቼ መከዳትን አየሁና መለየትን ተማርኩ።

፨ እጀግም የምወዳት እናቴን ቀብሪያለሁ ስለዚህ ናፍቆት ምን እንደሆነ ተምሪያለሁ።


ለመማር ከፈለጋችሁ አለምን አንብቡ ምክንያቱም ተወዳዳሪ የሌለው ብቸኛው መፅሃፍ ነው። እና በህይወት ትምህርት ውስጥ ምንም ነገር ነፃ እንዳልሆነ አውቃለሁ።


Written by፦

-Ahmed Imad El-Din Shakuhi

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Nov, 14:22


የሰውን ልጅ በትክክል መረዳት ማለት ልብ ውስጥ የሚገኘውን፣
.
ሰው ትክክለኛ እይታውን፣ ሁኔታውን እና ማንነቱን እንዲገለጥ ልብ ውስጥ ቦታ መተው ማለት ነው፣
.
ቀድሞ ፈራጅ አለመሆን ፣ ቀድሞ እሱ እኮ እንደዚህ ነው፣ እሷ እኮ እንደዚህ ነች ፣
ብሎ በር አለመዝጋት ነው ፣
.
ሰውን እንዳመጣጡ መቀበል ነው፣ ቀድሞ አለመወሰን ነው!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Nov, 13:21


ወደ አሜሪካን ጎት ታለንት ( American Got Talent) ከሚመጡ ተወዳዳሪዎች መሃል Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) የምትባለውን ብዙዎች አይረሷትም፡፡ ተወዳዳሪዋ ወደ መድረክ በመጣች ጊዜ የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አለች"
ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድንው የምታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውም ባንድ አፍ እሺ ቀጥይ አሉ:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::
ከዚያም ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ፣ ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል ስትል ሳይመን በድንጋጤ ተመለከታት ፡፡ ቀጠለና ሀዋርድ "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" አላት ተገርሞ!!
Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በሗላ የዳኞች ውሳኔ የሚሰጥበት  ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት፡
"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::
ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱ ዓይኖቹ ፈሰሱ::
ከፊቱ ያለውን ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም  አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች  አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ  ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
በአንድ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "ፈጣሪ አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰደውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም  "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የፈጣሪን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትልም ነበር፡፡በመጨረሸም እንዲህ ነበር ያለቸው፦
"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

22 Nov, 15:53


ጀግና ከሆንክ ምን ይላል መሰላችሁ ቅዱስ ዩሃንስ አፈወርቅ "ጀግና ከሆንህ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት" መቆጣት ከፈለክ መጀመርያ በራስህ ላይ ተቆጣ!። ልክስክስነትህን፣ ስግብግብነትህን፣ ክፋትህን፣ ዝርክርክነትህን፣ ዘማዊነትህን ተቆጣው!። ስንፍንሃን ተቆጣው!። በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት። ከዘላለም እርስትህ ለነጠቀ፤ ከልጅነትህ ለሚያዋርድህ፤ ከፈጣሪህ ለሚያጣላህ፤ እግዚአብሔርን ያህል አባት፣ ገነትህን ያህል ቦታ፣ ልጅነትህን ያህል ተድላ ደስታ ከነጠቀህና ከክብርህ ካዋረደ በሱ ላይ መጀመርያ ተነስ!።

እውነቴን ልንገራችሁ ሰው መጀመርያ ከእራሱ እና ከዲያብሎስ ጋር ጦርነት ከገጠመ በአለም ላይ ያሉ ጦርነቶች ሁሉ ይጠፋሉ..



           ፦አባ ገ/ኪዳን

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

22 Nov, 03:59


..እርጥብ አይኖቿ ውስጥ የሚታየው ምሬት ብቻ ነው፡፡የሷ ቀን ትናንት ነበር፡፡ዛሬን አታቀውም፡፡ነገን የመኖር ጉጉት የላትም፡፡ትናንት ብቻ፡፡ቁሞ እንደመቅረት ያለ ነገር ነው፡፡የሆነ ሰው በህይወቷ ገባ፡፡ዘልዓለሟን ነጠቃት፡፡ፈቅዳ ወዳ ቀኗን ሰጠችው፡፡አልታመነላትም፡፡አላዘነላትም፡፡አጉል ቦታ ላይ ጥሏት ሄደ፡፡ይመጣል ብላ ጠበቀች፡፡ሳይመጣ ቀረ፡፡ባይመጣም ስትጠብቀው መኖር  መረጠች፡፡አይኗን አርጥቦ ልቧን ሸንቁሮ ወጣትነቷን አወይቦ በዛው ቀረ.... ...አይኖቿ ጠፈፍ ብለው አያውቁም፡፡ሁሌ እርጥብ ሆነው ሁሌ የእንባ መፍሰሻ ቦይ ሆነው ጊዜዋ አለፈ፡፡እምነቷን አላጎደለችም፡፡ተስፋ አልቆረጠችም፡፡አልሰነፈችም ቀን ትቆጥራለች፡፡ጥላውን ጥሎባት መቅረቱ አልገባትም፡፡በቦዘዙ አይኖች መምጫውን ትናፍቃለች... ...አስወልዷት ነበር፡፡ልጅ ፈጥረው ነበር፡፡ሊተዋት ሲፈልግ መጀመሪያ ባህሪውን ለወጠ፡፡ቀጠለና ልጁን አያቱ ጋር አስቀመጠ፡፡ሰለሰና ራሱን ከሷ ነጠለ፡፡በአንዴ እሱንም ልጇንም አሳጣት፡፡አበደቻ!!!ራሷን ሳተቻ!!እምነት ጎደለባታ!!መፍትሄዋ እንባ ሆነ፡፡አጨንቁሮ በመጠበቅ የሰለሉ  ጭምጭም አይኖቿ የወንዝ ዳር ይመስል ውሃ እያመነጩ ቀሩ... ...ከልጇ በላይ ከአብራኳ ክፋይ በላይ እሱ ይናፍቃታል፡፡ይናፍቋታል፡፡አመታት አልፈው ድምጹ ጆሮዋ ላይ ጥላውን እንደጣለ ነው ሳቁ ይሰማታል፡፡ያቀፋት የሳማት ይመስላታል... "ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ"ትንከተከታለች... ...በደል ሲበዛ ጫንቃ ቢያደነድንም መቋቋም ከብዷት በየእለቱ እየሰለለች እየከሰለች አመዷ ወጣ፡፡ተመልሶ ቢመጣ እንደዚህ ተጎሳቁላ ቢያያት አይጠየፋት ይመስል ተስፋ አድርጋ ትጠብቃለች፡፡ደብዳቤ ጽፋ ይዛለታለች፡፡አንዴ ብቻ ብታገኘው ልጇን ስማ ደብዳቤውን እንዲያነብ ብታደርግ አቤት ደስታዋ!!!... ..."መቼ ነው የምትመጣው?ወይም መቼ ነው ከውስጤ ጠቅለህ የምትሄደው?መቼ ነው ዳግም በእቃፎትህ የምሞቀው?መቼ ነው እንደሌለህ አምኜ ተስፋ የምቆርጠው?የምሄድበት የምሸሽበት መንገድ  አዙሮ የሚያደርሰኝ አንተ ጋር ነው፡፡መድረሻየ አንተ ነህ፡፡የማመልጥበት ቅያስ የለም፡፡ልጄን ቀምተህ አንተን ከኔ ቀምተህ እኔን ከእኔ ቀምተህ በድለኸኝ እንኳን ትውስታየ ውስጥ የቀረው ፍቅርህ ነው፡፡ያልነጠቅከኝ ያልወሰድክብኝ ነገር የለም፡፡ስጋየ የለም ሞቷል፡፡የሚጠብቅህ ሙት መንፈሴ ነው"... ...እርጥብ አይን!!ሁሌ ውሃ የሚያመነጭ፡፡የተሰበረ ልብ፡፡የተበደለ እናትነት...ፍቅር ክፋቱ በደልን አለማየቱ ነው፡፡ፍቅር ክፋቱ አይንን ማወሩ ነው፡፡አብዳለች፡፡ለራሷ አውርታ ለራሷ ቀልድ ራሷ ትስቃለች፡፡አድሎኛዋ አለም ያልነጠቀቻት ነገር የለም፡፡ነፍሷ ብቻ በአጽሟ እንደ ክራንች ተደግፋ ትንከላወሳለች...

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

21 Nov, 16:57


`` ልዩ የመሆን እብደትን አስወግዱ። በህይወታችሁ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተራ ሁኑ። ግን በንቃተ ህሊና እና በማዳመጥ ውስጥ ያለህ ተራነት ተዋሃዱ።

ተኙ፣ ብሉ፣ ስሩ፣ ውደዱ፣ ጸልዩ፣ በተመስጦ እና በመገለጥ ተቀመጡ ነገር ግን ልዩ ሰው እንደሆናችሁ ወይም የተለየ ነገር እየሰራችሁ እንደሆነ በፍጹም አታስቡ። ወደ መገንዘብ የምትደርሱት እንደዚህ ባለው ተራነት ነው። ልዩ መሆናችሁን ስታሰቡ ወደ ማይቀለበስ የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ ትገባላችሁ። ያን አንድ ሰው እንኳን እንዳያስረዳችሁና እንዳትመለሱ "ልዩ ስለሆንኩ እኮ ነው" በምትል መርዝ መመረዝ ነው። እውነቱን ለመናገር ልዩ አይደላችሁም ደደቦች ናችሁ!።
``

Osho ፦Life A song A Dance 📖
              

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

21 Nov, 15:58


`` እኛ በየቀኑ ስለራሳችን አዲስ ነገር እያገኘን ህይወትን እንኖራለን፤ ሌሎች ግን "እኔ እኮ በደንብ ነው የማውቃችሁ" እያሉ ይመጻደቁብናል!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

20 Nov, 15:11


በህይወት ውስጥ አንድ ሰው ሁሉን ነገር ያጣል ጤና ገንዘብ ጓደኝነት ቤተሰብ ምንም ነገር አይቆይም ሁሉንም ነገር እስከ መጨረሻው አይሄድም።

ማይክ ታይሰን የቦክስ ጀግና ነው ሴት ልጁን በመኪና አደጋ በሞት አጥቷል። በአንዳንድ የህግ ጥሰት ጉዳዮች እዳ ተከማችቶበት ነበር። የገንዘብ ችግር በእርጅና እድሜው ወደ ወጣትነት ስራው እንዲመለስ አደረገው።

ምን አልባት ግጥሚያውን መሸነፍ በሱ መንገድ ላይ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ህይወቱን መልሶ ለመገንባት ብዙ ገንዘብ አግኝቷል።

ወድቀን መነሳት አለብን

ማይክ ታይሰን ጊዜ የሰው ልጅ እውነተኛ ጠላት መሆኑን አረጋግጥልን!

ግዜ የሰው ልጅ ጠላት ሲሆን የምታሸንፈውን ጦርነት እንደተሸነፍክ ታልፈዋለህ። በአንድ ዝረራ
knackout የምታሶጣውን ውርጭላ ምላሱን እያወጣ ያፌዝብሃል!። ቢሆንም ራስህን ታውቀዋለህ..

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

19 Nov, 03:56


"በ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተነስቸ እሮጣለሁ ምክንያቱም ተፎካካሪዬ አሁንም እንደተኛ ስለማውቅ ጥሩ እድል ይሰጠኛል."  ይህ ማይክ ታይሰን በየቀኑ ጎህ ሲቀድ ከእንቅልፋ ተነስቶ ይሮጥ እንደሆነ ሲጠየቅ የሰጠው ምላሽ ነበር።

ታይሰን አክሎም "ከተፎካከሪዎቼ አንዱ ከሌሊቱ 10  ላይ እንደሚሮጥ ካወቅኩኝ ፣ከሌሊቱ  8 ሰአት ላይ መሮጥ እጀምራለሁ እና አንዱ ተፎካካሪየ  ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ ተነስቶ ልምምድ  ስልጠናውን የሚያከናውን መሆኑን ካወኩ  ልምምዴን ለመቀጠል ሙሉ በሙሉ መተኛትን አቆማለሁ."።

"ያለ ዲሲፒሊን፣ ምንም ያህል ተሰጥኦ ቢኖርህም ምንም አይጠቅምምህም" 
🥊 ማይክ ታይሰን

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

18 Nov, 15:48


"የውስጣዊ ዓይኖች ካልተከፈቱ በስተቀር፤ውስጣዊው አቅጣጫችሁ በብርሃን የተሞላ ካልሆነ በስተቀር ራሳችሁን ማየት ካልቻላችሁ በስተቀር፤ራሳችሁን ካላወቃችሁ በስተቀር የነቃችሁ እንደሆናችሁ አታስቡ!"

📓ርዕስ፦የመጨረሻው ህግ
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

17 Nov, 06:37


አንድ ቀን ትነቃለህ፤ ዘላለለማዊ መንቃት። ይህ መገለጥ ህይወትህን እድትወድ ምክንያት ይሆንሃል፤ ከዛ ላልፈለጉ ደርሰው አሁን ለሚፈልጉ ሰዎች..ስምህን ሲጠሩ መልስህ የሚሆነው "የማርያምን ብቅል እየፈጨው ነው"

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

16 Nov, 16:41


`` ብዙ ጊዜ መናገር  ማውራት ፈልጌ ነበር ግን የሚሰማኝን ለመግፅ ስለማልችል ዝምታን መረጥኩደስ የሚለው ነገር ዝም ማለት ነበር.. ``

`` መቃብሬን ስትጎበኝ የምትገዛቸው አበባዎች ለእኔ አይጠቅሙኝም እና በራሴ ላይ እንድታለቅስም አልፈልግምብቻ ሳንድዊች ገዝተህ ለመቃብር ጠባቂው ስጠው ``
        
`` በመቃብሬ ላይ ቆሻሻ ሲከምሩና የምግብ ፍርፋሪ ሲበትኑበት ያለምንም ጥሪ ወፎችና ውሾች በላዬ ላይ ያንዣብባሉ እናም ያን በሚያደርጉ ሰዎች ላይ አልተናደድኩም ምክንያቱም በዚህች ተራ ተግባር ብቻዬን እንደሆንኩ አይሰማኝም ነበር። ``


                   ―ዶይስቶቭስኪ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

16 Nov, 13:51


አንዳንዴ 𝚝𝚑𝚎𝚛𝚎 𝚒𝚜 𝚝𝚑𝚒𝚜 𝚏𝚎𝚎𝚕𝚒𝚗𝚐..... ይሄ ነው ብዮ ልናገረው ፤ ላስረዳው የማልችለው። .......ልቤ ግን ጭንቅ ሲለኝ ይታወቀኛል።
.
ትከሻዬን ተጭኖኛል ግን ቃላት እንኳን ሊደርሱበት አይችሉም። .
ደስታና ሰቃይ አብረው ይመጣሉ.....

.......ግን አንዳንዴ ብቻ
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

15 Nov, 18:46


`` እናም ወዳጄ መከራ በየትኛውም አቅጣጫ ስለሚነካህ በጣም ትደክማለህ ይቺ አለም ብዙ ለሚያስቡ ቶሎ ለሚሰማቸው ሰዎች ጥሩ አይደለችም!። ``

                      ―ኩዌል ግላንድ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

15 Nov, 03:57


በራስህ ላይ ሳቅ 😁

ታዉቃለህ ። እራስህን በጣም ማስተዋል ፣ መመልከት ስትጅምር  ካለምንም ፍርድ እና አስተያየት በእውነት በራስህ ትገረማለህ ። ማለትም እራስህን እንደ ሁለተኛ
ወገን ቆጥረህ ስራዎችህን ስትመለከት ስትታዘብ የስህተቱችህን ፣ የጥፋቱችህን ፣ የችግሮችህን አስቂኝነት ትረዳለህ ።

ባንተ ላይ በደረሰው ኩነት ላይ አንተ እራስህ የምትሰጠው ፍርድ እና አስተያየቱች ብቻ አንተን ደስታ ቢስ እንዳደረጉህ ትረዳለህ ።

🤌💙ውብ አሁን!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

14 Nov, 06:01


የተመረጡ 10  ጥያቄዎች ለፍልስፍና ባለቤቶች እና አማኞች!


የሚከተሉትን ሰዎች ስታገኙ ጥያቄዎችን ጠይቁልኝ

1, የአለም ተመራማሪ ወይም የጠፈር ሳይንቲስት ነን የሚሉትን ይሄን ጠይቁልኝ...

አንድ ድሀ የነበረ ሰው በየቀኑ 10,000 ብር ቢሰጣችሁ እና ከየት ነው የምታመጣው ስትሉት አንድ ባለሀብት አለ ስጠኝ ለሚሉት ምስኪኖች ሁሉ  በየቀኑ 1,000,000 ብር ይሰጣል እሱ ከሰጠኝ ላይ ነው 10,000 ብር የምሰጥህ ቢላችሁ በናንተ የአስተሳሰብ ጥግ ቀጣይ ንግግራችሁ የሚሆነው ከድሀው ወዳጃችሁ ጋር ሳይሆን ከባለፀጋው ሰው ጋር ይሆናል ምክንያቱም ሰጪ እና የበላይ እንደሆነ ስለምታውቁ ...... ነገርግን ምድርን ስለፈጠራት  ፈጣሪ ማንነት ሳይሆን ምድር ላይ ስለተፈጠሩ ነገሮች በስፋት ታጠናላችሁ ለምን ?

2, ምድር ፈጣሪ የላትም ሰውም እንደዛው  ብለው የሚያምኑትን ይሄን ጠይቁልኝ ...

ምድር ፈጣሪ ከሌላት ሰውም ከሌለው የበላይ አካል ሰው ነው ማለት ነው ያ እስከሆነ ድረስ ለምን ሰው አለመሞት እየፈለገ አለመሞት አልቻለም? አደለም ሞትን መቆጣጠር የሚሞትበትን ቀን ማወቅ ለምን ተሳነው? ሌሎች ሰዎችስ አምላክ ብለው የሚያመልኳቸውን አምላኮች ማን አስተማራቸው ? በእምነታቸውስ ለምን ተአምራት ይደረጋሉ?...

3, ሰው ከዝንጀሮ መጣ ብለው የሚያስተምሩ እና የሚያምኑን ይሄን ጠይቁልኝ..

የሰው ልጅ ከዝንጀሮ ከመጣ አሁን ላይ ያሉ ዝንጀሮዎች ለምን ወደሰውነት አልተቀየሩም?

4, ስለሰው አፈጣጠር 100% አዉቀናል ብለው ለሚናገሩ እና  ሉሲ እና መሰሎቿን  የመጀመሪያ ሰው ለሚሉ ይሄን ጠይቁልኝ...

ሉሲ ወይም መሰሏ የመጀመሪያ ሰው ከሆነች ዘር በመተካት እኛን ለዚህ ቁጥር ያበቃን ካጠገቧ የነበረው ጥንታዊ ወንድ ማነው?
ሉሲ እና መሰሎቿ ከየት ተገኙ? ከመሬት ከሆነ ሌላ ጊዜ ስንቆፍር የምናገኘው ከሷ የተሻለ ጥንታዊ አፅም ወይም የፈረሰ እና አፈር የሆነ ከሷ በፊት የሚኖር ሰው ላለመኖሩ ምን ማረጋገጫ አላችሁ? የመጀመሪያው ሰው አይታወቅም ካላችሁም አዳም የመጀመሪያው ሰው እንደሆነ  አታምኑም ወይም መላምት አትሰጡም ለምን?

5,  ፈጣሪ ከውልደት እና ከሞት ውጪ የፃፈው የህይወት ገፅ የለም ሌላውን እኛ በራሳችን መንገድ ነው ኖረን የምንፅፈው የሚሉትን ይሄን ጠይቁልኝ...

እናንተ 100% እንደምትፈልጉት የፈለጋችሁትን ሁሉ እያገኛችሁ እና እያደረጋችሁ ነው ? ያላችሁት ልክ ከሆነ የምትፈልጉትን ኖራችሁ ከመፃፍ ምን አገዳችሁ ? ለምንስ ያልጠበቃችሁት ነገር እንቅፋት ይሆንባችኋል ?

6, አለም ከተፈጠረች ከሚልዮን በላይ አመታት ተቆጥረዋል የሚሉትን ይሄን ጠይቁልኝ...

አለም ከተፈጠረች ያን ያክል ዘመን መቆጠሩን ማን አሰላላችሁ? በራሳችሁ መንገድ  ካወቃችሁት ከ ሚልዮን አመታት በፊት አለም ምን እንደምትመስል እና በዛ ዘመን የሚኖሩ ሰዎችን ታሪክ በሰፊው መተረክ ለምን ተሳናችሁ?

7, መሬት ከፈጣሪ ስራ ውጪ በማንኛውም መንገድ ተፈጠረች ለሚሉ ይሄንን ጠይቁልኝ...

መሬት ከፈጣሪ ስራ ውጪ በማንኛውም መንገድ ብትፈጠር እነዛን የተፈጠረችባቸውንስ ነገሮች ማን ፈጠራቸው? እናንተ እንዳላችሁት ሚልዮን አመታትን ስንኖርስ ለምን እንደመሬት አይነት ተፈጥሮ ያላት  ሌላ ፕላኔት አልፈጠሩም ?

8, ሰዎች ከዝንጀሮ መጡ የሚሉትን በድጋሚ ይሄንን ጠይቁልኝ...

ሰው ከዝንጀሮ መጣ ካላችሁ ዝንጀሮስ ከምን መጣ? ማን ፈጠረው ?

9, በምድር ላይ ሰው እና ፍጥረታትን ጨምሮ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም የሚሉትን ይሄን ጠይቁልኝ...

ስለሰው ብዙ ተባብለናል  እንሰሳት እና እፀዋትን አየርን እና ሌሎችን ማን ሰራቸው? መቼም ምድር ራሷ ወይም ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ ሊሆን አይችልም እና ምንድነው ?...

በፍልስፍናቸው ልክ ብዙ የማይመልሷቸው እልፍ ጥያቄዎች አሉ...

የመጨረሻ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ከሰዉ ልጅ በላይ የሆነ ፈጣሪ ከሌለ የሰው ልጅ እንዴት በእጁ ያልሰራዉን ልጅ ይወልዳል ? መልሳችሁ አንድና አንድ ተፈጥሮ ነው ግን ...
ተፈጥሮ ቃሉ ራሱ ትርጉሙ ምንድነዉ ? ... ተፈጥሮ ማለት የተፈጠረ ማለት ነው ተፈጠረ የሚለዉ ቃል ደግሞ ፈጣሪ እና ተፈጣሪን የሚያማክል ነው ተፈጣሪ እስካለ ድረስ ደግሞ የፈጣሪ መኖር ግድ ይላል!  ይህ ለሁሉም ጥያቄም መልስም መሆን ይችላል
ሁሉም በራሱ አለም እውነት ፈላስፋ ቢባልም ለብዙሀኑ ይፋ የሚደረገው ፍልስፍና እዉነታን አረጋግጦ የያዘ ቢሆን ባይ ነኝ.... እንደኔ እውነታ የሁሉም ጥያቄዎች መልስ ሁሌም የማምነዉ... የሰራኝ[የፈጠረኝ] ነው ! እናንተስ?.....
                  
               ከኤልሳ[FB]

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

14 Nov, 04:48


ካፌ ውስጥ ተቀምጫለሁ። ማኪያቶዬን እያጣጣምኩ አንዳንዴም ስልኬን እየነካካሁ አለሁ። ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ልጁን ከትምህርት ቤት ይዟት እየመጣ የሚመስል አባት ገባ።የሰውነቱ መዛል የደከመው ነገር ይመስላል። ከአባትና ልጅ ሁኔታ እንደተረዳሁት ከሆነ ግን የኑሯቸው ደረጃ በጣም የወረደ ነው ። እሱም የቀን ስራ ላይ ያለ እንደሆነ እገምታለሁ ።

ጥግ ላይ ተቀመጡ። ልጂቱ ምናልባት የስድስት አልያም የሰባት ዓመት ልጅ ብትሆን ነው። በጣም ትረብሸዋለች ። እዚህም ካፌ አስገድዳው አልያም እሷን ለማስደሰት እንደገባ ያስታውቃል ።

አስተናጋጇ በጣም በሚያስጠላ አይነት መንገድ ታዘዘቻቸው። ቆይታ በጎድጓዳ ሳህን የተሞላ ቺፕስ ይዛላቸው መጣች። ልጂቱ ሰሀኑን ስባ በልጅ መስገብገብ አይነት ትበላለች ። በዚህ ሁሉ መሀል አባት ልጁን በስስት ያያታል። ከቺፕሱ በፍጹም አላነሳም። ልጁ ሆናበት እንጂ እየተናጠቃት ቢበላ የተመኘ ይመስላል። ባዶ አንጀቱ ፊቱ ላይ ይነበባል ። ልጂት በዓመት አንዴ የመጣላት እድል ይመስል አንድም ሳታስቀር ወደ ሆዳ ልካለች። አባት ፈገግ አለ ደስታዋን አይቶ።

ተመግባ እንደጨረሰች አሁንም ተነስታ እጁን እንውጣ እያለች ትጎትታለች። የተጠየቀውን ሂሳብ ከየኪሱ ሰብስቦ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ተነሳ።

ቁሞም ጎድጓዳው ሳህን ላይ ዓይኑን እንደዘበት ላክ አደረገ። እስከሞቴ አፋፍ እስከምደርስ ድረስ ከዓይኔ የማትጠፋውን ነገር አደረገ ...

እጁን ዘርግቶ ከሰሀኑ ውስጥ ከልጂቱ እጆች አምልጠው የተራረፉ ቺፕሶችን አንስቶ ወደ አፉ አስገባ።

ወላጆቻችን ስንት አምሮቶቻቸውን ለእኛ ሲሉ ሰዉልን!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

13 Nov, 16:10


አንድ ድሃ ኬክ ሻጭ ወደ ታዋቂው ግሪካዊ ቢሊየነር ኦናሲስ (በቅፅል ስሙ የነዳጅ ታንከሮች ንጉስ) ወደሚባለው  ባለሃብት ጋር ቀረበና ኬክ እንዲገዛው ጠየቀው። ኦናሲስ አንድ ሳንቲም አውጥቶ ሻጩን እንዲህ አለው። "ጎፈር ወይስ ሰው? ከተሸነፍኩ በኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ገንዘብና አንድ የቼክ ፊርማ እሰጥሃለው። ከተሸነፍክ ደግሞ የተሸከምከውን ኬክህን በጠቅላላ ጠረጴዛው ላይ ታስቀምጣለህ።"

ሻጩም እንዲህ ሲል መለሰ፡- -ጌታዬ እኔ ድሃ ነኝ፤ ያለኝን ሁሉንም ኬክ ከሰጠው ዛሬ ቤተሰቤን መመገብ አልችልም።

ኦናሲስ ወደ ኋላ በመዞር ጀርባውን ለነጋዴው ሰጥቶ እንዲህ አለ፡-

``ኬክ ሻጩ ተወልዷል ፥ ኬክ ሻጩ ይሞታል..`` 😎

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

11 Nov, 18:26


Take a moment to appreciate life ✨️
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

11 Nov, 16:20


በእድሜ የገፋች አንዲት አሮጊት ሴትዮ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሄደችና የባንክ ቡኳን ለገንዘብ ያዡ እየሰጠች ``10 ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ`` አለችው።

ካሸሪውም፡-
"ከ$100 በታች ገንዘብ ለማውጣት  እባክዎን ኤቲኤም ይጠቀሙ።"

አሮጊቷም
``ለምን?``

ካሸሪውም በቁጣ የባንክ ቡኩን መልሶ እየሰጣት "እነዚህ መመሪያዎች ናቸው፤ እባክዎን ከኋላ የሚጠብቁ ብዙ ደንበኞች አሉ! ሌላ ትዕዛዝ ከሌለ መንገድ ይልቀቁልኝ!"

️‍️አሮጊቷ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም ካለች በኋላ የባንክ ቡኩን ወደ ካሸሩ እየመለሰች፦
``እባክህን አካውንቴ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በሙሉ ማውጣት ብትረዳኝ!``

ካሸሪውም አሮጊቷ በአካውንቷ ያስቀመጠችውን ገንዘብ ሲመለከት በጣም በመገረም  እንዲህ አላት፦"በአካውንቱ ውስጥ 500,000 ዶላር አለ እና ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል መጠን የለውም ነገ ተመልሰው መምጣት ይችላሉ?"

ሴትየዋም በመቀጠል ምን ያህል ገንዘብ ወዲያውኑ ማውጣት እንደምትችል ጠየቀች ገንዘብ ተቀባዩ፦ "ማንኛውም መጠን ቢኖር የሚቻለው እስከ 30,000 ዶላር ብቻ ነው።"

አሮጊቷም ሴትዮ ይህንን ስትሰማ እንዲህ አለችው፦
``ይሁን መልካም አሁን 30,000 ዶላር እንድወስድ ብትፈቀድልኝ?``

ካሸሪውም በንዴት ወደ ካዝናው ተመልሶ 20 እና 10 ዶላር ቁልል አውጥቶ አስር ደቂቃውን 30,000 ዶላር በመቁጠር አሳለፈ። ከዚያም ገንዘቡን እየሰጠ እንዲህ አላት፦"ተጨማሪ የማደርግላችሁ ነገር አለ?"

አሮጊቷም በእርጋታ ከተቀበለችው ገንዘብ 10 ዶላር መዝዛ ቦርሳዋ ውስጥ እያስገባች እንዲህ አለች፡-

``አዎ ጌታዬ $20,990 ወደ አካውንቴ ማስገባት እፈልጋለሁ።``

አስተምሮቱም፡-

ከአረጋውያን እና ልምድን ከተካኑ ሰዎች ጋር እልህ አትጋባ ህይወታቸውን በመማር አሳልፈዋልና
😑

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

10 Nov, 19:08


በጊዜ ብዛት የሚያዋጣትን የለየች የሚያዘልቃትን መሰብሰብ የያዘች ከአሁን አሁን አያትና ወደፊት እንደሷ እንዳልሆን እሰጋለሁ።

እሷንስ መኖር አይደል እንደዚህ ያደረጋት፣ እድሜ አይደል ጎራ ያስለያት ፣ ጊዜ አይደል የጣላት።
.
.
ማን ያቃል እኔም እንደሷ መጠንከር ያቃታት ያቺ ሴት እሆን ይሆናል።

ጊዜ ብዙ ያስተምረናል ፣ አዙሮ አዙሮ ግን ያየነውን ፣ የታዘብነውን ያንኑ ያደርገናል፤

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

10 Nov, 17:06


ታላላቆቻችን እንዲህ ይሉ ነበር
 
"በመንገድ ላይ ሳለህ ወደ ኋላ የማየት ፍላጎት ካለህ በቅድሚያ ሰዓትህን ቃኝ እየሄድክበት ያለው ጉዳይህ ጊዜ ሚሰጥህ ከሆነ ቁም ወደኋላም ዙረህ ያለፍከዉን ተመልከት

ነገር ግን ፊትለፊትህ ያለው ጉዳይ ሚበልጥብህ ከሆነ እና ሰዓትህ ዞረህ ኋላህን ለማየት ማይበቃህ ከሆነ አትዙር

አንተ ግን ሁለቱንም በ አንድ ላይ አስኬዳለው ብለህ ኋላህን እያየህ ወደፊት የተራመድክ እንደሆን እንቅፋት አግኝቶህ እንደምቶድቅ አትርሳ "

አባቶቻችን በ እግራችን ስለምንራመድበት መንገድ አይደለም ያወሩት

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

10 Nov, 16:16


መኖራችን ላይ ያላቅማችን እንጣዳለን ፥ ካለ እድሜ እንበስላለን ፥ ያለጊዜያችን እንከስላለን በዚች ህይወት ማገዶ ከመፍጀት ውጭ ያተረፍነው የለም! እንዲያው መንደድ ብቻ ሰማይ ላንደርስ መትነን።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

09 Nov, 17:50


‘ ‘ ድድብና ከእውቀት የበለጠ በራስ መተማመንን ይፈጥራል!። ’ ’

    ፦ ቻርለስ_ዳርዊን

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

09 Nov, 16:10


🦋

ለምሳሌ ነው

አንድ ደደብ የሆነ አካል ድድብናውን ለመቀየር የሚያደርጋቸው ጥረት ሁሉ የዛው ድድብና አካል ናቸው ።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

09 Nov, 06:30


አሁን በዚ ሰአት በምጽፍበት ቅጽበታት አይኖችሽን ከድነሻል የለሽም ወደ አለመኖር ውስጥ ሰጥመሻል የኔ ሴት በእርጋታ እየተነፈስሽ ከዚህ ከሁካታው አለም ከዚህ ከረባሹ አለም እርቀሻል እኔ ግን እየተመለከትኩሽ ነው።እንዲህ ፈገግ ልትል የከጀለች ፊትሽ ትታየኛለች ደግሞ በስሱ ገርበብ ያሉት ከናፍሮችሽን ተመለከትኳቸው ህይወትን በድም ስሬ የዘሩብኝ ከአለማት ሰውረው ሁለንተናዬን ያስረሱኝ ፍቅርሽን መውደድሽን በጥብቅ ሳሞት የገለጥሽባቸው ከናፍሮችሽን አየኋቸው በደብዛዛው ቀላ ያሉ ሆነው ውበትን እና ህይወትን የተላበሱ ናቸው።ያቺ ከነጻች ነብስሽ እየደረሰች የምትመለሰው ትንፋሽሽ ደግሞ በጽሞና ስትመላለስ ተሰማችኝ አንጎሌ ተነሳበት ድርቀት ወጠረው ተጠማሽ አሰኘሽው እባክሽ አንዴ ተጠጊኝና በሀይል ሳብ አድርጌ ልላክለት ኦ!! ፍቅሬ ሀሳቤ ሁሉ ወዳንቺ ተጓዘ አንቺ ግን ይሄኔ በዚህ አለም የለሽም ትንፋሽሽ ብቻ የተከደኑ አይኖችሽ ብቻ ያቺን ክብ ጨረቃ የምትመስለው እንደርሷም ጸአዳ ብረሀን የሚነጸባረቅባት ገጽሽ ፈገግ ብላ የተኛች ህጻንን መስላ ትታየኛለች አንቺ ግን የለሽም በሚነፍሰው ንፋስ ውስጥ በእነዛ ከሰማያት በላይ በረገፉት ከዋክብቶች መሀል ነብስሽ በአርምሞ እየተንሳፈፈች ነው የለሽም እርቀሻል አካልሽን ብቻ በዚህ አለም ትተሽ ጠፍተሻል እኔም እየተከተልኩሽ ነው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

08 Nov, 16:37


ዕቃ የጠፋን ያህል እንኳን ፈጣሪን ብንፈልገው ምንኛ መልካም ነበር፤ እቃ የጠፋን ያህል ብንፈልገው.. ሰው የገዛ ሞባይሉ ቢጠፋ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገለባብጦ ነው የሚፈልገው። ፈጣሪያችንን ሳናገኝ ግን ውለን እናድራለን። ፈጣሪን በማጣታችን ነፍሳችን ደግሞ ጥያቄዋ አያርፍም። ሁልጊዜ ሰው አይረካም፤ ስለማይረካም ነው ይገላል ይቀማል፤ ተሹሞ መሾም ይፈልጋል፤ አግብቶ ማግባት ይፈልጋል፤ ይዞ መያዝ ይፈልጋል። ሰው ለምንድነው ልቡ የማያርፍለት ካላችሁኝ የልብ ማረፊያው ፈጣሪ ስለሆነ ነው።

          :- አባ ገብረ ኪዳን
         

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

08 Nov, 13:17


"እኔን..." .....ነበር ያላት ለመጀመሪያ ጊዜ። ቀና ብላ ስታየው ፈገግ ብሎ ይመለከታታል።
ፈገግ አለችለት ..ልቧ ሲሞቅ ተሰማት.... .....ወደ ስራ ለመግባት ተቻኩላ ስትደናቃፍ ተመልክቷት ነው ።
በጣም እንደ ደነገጠች የታወቃት እጇ እየተንቀጠጠ እንደሆነ ስትመለከት ነበር።
ቀኑን ሙሉ ያሳያትን ፈገግታ.....፤ ድምፁ......፤ መልኩ....... በአይምሮዋ ሲመላለስ ነበር የዋለው።
ብቻ የሆነ ነገሩ ደስ ብሏታል። እንደ ዘውትር ስተኳትን ውላ የመውጫዋ ሰአት ደርሶ ስትወጣ የተመለከተችው ግን መቼም የማትጠብቀው ነገር ነበር።
.
.
ያስደነገጣት ከዛም በላይ ግን ደስ ያሰኛት ጠዋት ካገኘችው ቦታ ቆሞ የእሷን መውጣት እየተጠባበቀ መሆኑን ስትመለከት ነው።
ፈገግ እንዳለ እርሷ ወዳለችበት እየተጠጋ እጁን ዘረጋላት። እጇን እየጨበጠ መስፍን እባላለው አላት። አፏ ሲያያዝ.... ፤ ሰውነቷ አልታዘዝ ሲላት ታውቋታል፤ አይምሮዋ እንደሌለ ሁሉ ዝምታን መርጦ ከድቷታል ።
ያንቺስ ማን ይባላል ? .........ብሎ ሲጠይቃት ነበር ከእንቅልፍ እንደነቃ ሰው ብንን ያለችው።

እእእእ.....እኔ መስፍን ....ማነው ሜሮን እባላለው ...... አለች ቃላቶቿን በግድ ገጣጥማ።
የእሱን ስም ተሳስታ መጥራቷ እንድታፍር አረጋት።
.
ወዴት ነው ምትሄጂው?...
.
እ...?
.
ወዴት ነው ምትሄጂው?
.
ወወደቤት ።
.
ልሸኝሽ?
.
እሺ.......።
እንግዲህ እንደዚህ የተጀመረ ፍቅር አድጎ ትልቅ ቤተሰብ የመሠሰረተው።
አይ ፍቅር .......ደስ ሲል ግን።
Abu
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

08 Nov, 03:46


"ምንድናት ይህቺ?" አለችኝ ። "እስኪ አትጠፋም እንዴ?" ትፈትጋታለች በጣቶቿ።

ይህቺ ምልክት እሷን ናት። ከግራ ደረቴ ላይ ያረፈች ዳና። በእዚህ መንገድ ሂጄበታለሁ .. እዚህ ደረት ላይ ተኝቼበታለሁ ..የሚል መልዕክት ይዟል ። ታዲያ ማናት ይህን ዛሬ ላይ የምታነበው ሴት?

"አታምህም ግን ? እስኪ " ወደጎን ትስባታለች ይህቺኛዋ ሴት ደግሞ ። " የሆነ ክሬም አለ የሚቀባ እሰጥሃለሁ ማታ ማታ ትቀባታለህ ከዚያ ትጠፋልሀለች" ዓይንሽ ይጥፋ እላለሁ በልቤ።

ለሶስት ዓመታት እዚህ ደረት ላይ ተንተርሳለች። የልቤን ምት ከፍ-ዝቅ አድምጣለች። በዚህም ከሺ ልቦች መሀል ልቤን አስቀምጣችሁ የሱ የታለ ብትሏት "ይኸው" ብላ ታወጣታለች። የልቤን ምት ሪትም እንደዘለሰኛ ኮምኩማለች። ለሶስት ተከታታይ ዓመታት እዚህ ደረት ላይ ነበረች። እሷ ስትሄድ ይህቺ ምልክት ከደረቴ ላይ ቀረች።

"ምንድነው ስለት ወግቶህ ነው?" ትለኛለች ይህቺኛዋ አዲስ መጤ። " ውዴ በጣም በልዛለችኮ" እያለች በጣቷ ትፈትጋታለች። ባለፈው የነበረችውም እንዲህ ሞክራለች። ምልክቷ ሳትጠፋ እነሱ ይጠፋሉ ።

እንደ ሰባሰገሎቹ እሷን ማግኘት የሚፈልግ በዚህች ምልክት ይመራ። እሷን ያገኛታል! ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የተንተራሰችው ደረት ላይ ያረፈች የ 'እዚህ ነበርኩ' ምልክት ። ይህቺ የደረቴ ክብ ብልዝ የጆሮዋ ጌጥ ፈርጥ ማህተም ናት። ተንተርሳ ያተመቻት የታሪኳ ዶሴ! ተኝታ በተነሳች ቁጥር እየደመቀች መጥታ አሁን ላይ የሶስት ዓመታትን ታሪክ ያረገዘች ብልዝ!

አንዳንድ ሰው አሻራውን በኛ ላይ ለማሳረፍ ትልቅ ገድል መፈፀም ላይኖርበት ይችላል ። እንደቀላል እንዲሁ እንደዘበት የአንዲት የጌጥ ፈርጥ ስፋት ያህል ትበቃዋለች። እሷን ሰጥቶን ያልፋል ። ህይወታችንን ...ዛሬያችንን...ተስፋችንን ...ፍቅራችንን...በፈርጧ ሳይሆን ፈርጧ ባተመችው ብልዝ ይቀይሩናል።

እንርሳ ብንል አንችልም... መጪዎቹ ብልዛችንን እናጥፋላችሁ በሚል ሰበብ ይፈትጉናል። ከብልዙ ቀድመው እነሱ ይጠፋሉ ....

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

07 Nov, 17:07


በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡
ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን።
ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ...
መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም ለመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ነበር፡፡

ራሳችንን ሁልጊዜ እንደ ንጹህ እናያለን ግን ለምን?

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

07 Nov, 06:48


ጉርሻ

የከንፈሯን ደርዞች በጣቶቼ እዳስሳቸዋለሁ። ይህ የሚሆነው ራት እየተመገብን ሳጎርሳት ነው። ላጎርሳት ስል ለመጉረስ ከንፈሮቿን ገርበብ ስታደርጋቸው። ልቤ አብሮ ይከፈታል። ያንጊዜ ምግብ የጠቀለሉ ጣቶቼ በዐየር ላይ እንዳቆምኳቸው ክብነት ዋሻ ያስመሰለው ከንፈሯ ላይ ዓይኖቼ ይላተማሉ። ንዝረት በሙሉ አካሌ ላይ ደሜን ተክቶ ይዘዋወራል። ሲነዝረኝ ጉርሻው ከአፏ ሳይደርስ ይንጠባጠባል።

"አካሌዋ! አንተኮ ጉርሻህ በባህር እንደሚያቋርጡ ስደተኞች ነው። ከአፌ ሳይደርስ መንገድ ላይ ተንጠባጥቦ ያልቃል" ብላ ትተርበኛለች። እንደገና ሌላ ጉርሻ ጣቶቼ ያሳድዳሉ። አሁንም እየተንጠባጠቡ ሄዶ አፏን ይሞላሉ።

" ጉርሻህ ይጨንቃል ሆኖም እወደዋለሁ" ትለኛለች። ጉርሻ ቃል ነው። በአጎራረሴ ውስጥ ደግሞ መልዕክት አለ። ይህን ደግሞ እሷ አትረዳም ። አጎርሳታለሁ..ታላምጣለች..ትውጣለች..እጠግባለሁ።ወደቤቷ ትገባለች። በቃ።

አንድ ቀን ታዲያ እንደሁሌው የራታችን ማዕድ ላይ ሳጎርሳት እንዲህ ጠየቀችኝ (ለመጠየቅ ምክንያቷን የጉርሻ አምላክ ይወቀው)

" አካሌዋ! ምንድነው ጉርሻ?"
ጉርሻ ማለትማ ... ፍቅር፣ ህብራዊነት፣ ደስታ አብሮነት ጋሻነት ስስት ጉጉት የሚገለፁበት የስሜት ዓውድ ነው።

" ጣዕሜዋ! አልገባኝም " አለቺኝ አየር ላይ ተንጠባጥቦ ያለቀውን ጉርሻዬን እያላመጠች።
" በአጭሩ ጉርሻ ማለት መገለጫ ያገኘ ስሜት ነው" አልኳት
ይኸው ከዚህ በኋላ ራት ከበላን አጎርሳታለሁ ታላምጣለች ትውጣለች እጠግባለሁ። ቁርስ በልተን ነው የምንለያየው።


አካሌ🫶

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

06 Nov, 15:57


በርግጥ መሳካት አለመሳካቱ ላይ እርግጠኛ አደለሁም ግን እሞክራለሁ፤ ይከብዳል፣ይደክማል አውቃለሁ ግን እሞክራለሁ የልቤን ምኞት ለፈጣሪዬ ነግሬ በቃሉ በረታለሁ በቃ ከዛ የመጣው ይምጣ ባንዱ መንገድ ባይሄድልኝ ሌላ አላጣም፤ እጄን አጣጥፌ አልተክዝም።

ስሞክር ይረዳኝም አይደል🤲🏼

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

06 Nov, 03:49


ምንም ነገር ሳይለኝ ከተለየኝ ከ 8 ወራት ብኃላ በቀደም ደወለልኝ።ስልኬን አንስቼ ስመለከተው ያልተመዘገበ ስልክ ነበር ስልክ ቁጥሩን አተኩሬ ሳጤን የማውቅው መሰለኝ ብልጭ ያለልኝን ሀሳብ እውነትነቱን ለማረጋገጥ ባለማመን ከእጅ ቦርሳዬን ውስጥ መታወቂያዬን አውጥቼ ቁጥሩን አመሳሰልኩት ልክ ነበርኩ እራሱ ነው(ድንገት መታወቂያዬ ቢጠፋ እንኳ ብዬ ከራሴ ቁጥር ተዕዩ የሱን ቁጥር ነበር ያስቀመጥኩት)።የሰው ልጅ ግን ልርሳ ካለ ግዜ ይፈጃል እንጂ ይረሳል አይደል?!የእሱን ቁጥርኮ ከራሴ ቁጥር እኩል ነበር በቃሌ የማውቀው ዛሬ ግን ለማስታወስም ተቸገርኩ  ምንድነው ግን እየተሰማኝ ያለው? ፍቅር፣ጥላቻ፣ናፍቆት፣ንዴት ወይስ ሁሉም በአንድነት? አላውቅም!...ይህን ሁሉ ሳብሰለስል ስልኩ ጥሪው አብቆቶ በድጋሚ መጥራት ጀመረ አነሳሁት "እረሳሽኝ አይደል?" በሚል ወቀሳ ተቀበለኝ እንዲህ አይነቱን ሰው ምን ይሉታል እንግዲህ? ምንም ሳይነግረኝ በማላውቀው ምክንያት እንደተለየኝ፣እርሱን ላገኝበት የምችላቸውን መንገዶች ሁሉ ሆን ብሎ በአንድ ቀን እንደዘጋጋብኝ፣ግራ ገብቶኝ ይገኛል ብዬ ያሰብኩት ቦታ ሁሉ ሂጄ እንዳጣውት፣በአጋጣሚ መንገድ ላይ አግኝቼው መገረሜ ሳይለቀኝ እንደማንኛውም የማይተዋወቅ ሰው ባላየ እንዳለፈኝና መገረሜን እጥፍ እንዳደረገው ሁሉንም በአምሮዬ በምልሰት ቃኘዋቸው....ከአፌ የወጣው ግን "ዛሬ ከየት ተገኘህ?" የሚለው ብቻ ነው። "ካለሁበት ቦታ ነዋ" ብሎ እንደዘበት መልሶልኝ ሌላ ወሬ ጀመረ።

የትም ሂዶ ሲመጣ ቁጭ ብዬ እንደምጠብቀው በጣም እርግጠኛ ነው።ከአንዴም ሁለቴ ተመሳሳዩን አድርጎ መጥቶ ስለተቀበልኩት ዛሬም ሲመጣ እጄን ዘርግቼ አሰፍስፌ እንደምቀበለው ነው የሚያስበው ንግግሩም የሚያሳብቀው ይህንኑ ነው።አንዳንድ ሰው ከትላንት ስህተቱ አይማርም ዛሬም ሌላ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት ሲሽቀዳደም እግሩን ውልፍት አይለውም...come on man! ህይወት እኮ አንዳንዴ ሁለተኛ እድል አትሰጥም!።እኔ እርሱ በሄደበት ወቅት መገፋቱን ተቋቁሜ ያለ ሰው በድል መቆም ችያለው ዛሬም ለመኖር ከእግዚያር በቀር እርሱ እንደማያስፈልገኝም እንዲሁ።ማንም ለማንም የመኖርና የመቀጠል ዋስትና ሊሆን አይችልም፡ቀድሞውኑ በእርሱ ላይ እምነት መጣሌ ስህተት ነበር ዛሬ ይህ እውነት ሲገባኝ ብቻዬን ነገሮችን ማድረግ ችያለው ዳ...ዲ እያልኩ ጀምሬም ቢሆን አሁን ላይ እሯጭ ነኝ።

ብዙ ጉዳዬችን አንስተን ካወጋን ቡሃላ "በአንቺ ከራሴወ በላይ እርግጠኛ ነበርኩ እንደምትጠብቂኝ አውቅ ነበር ይህን ህብረት ድጋሚ እንደትላንት እናድሰዋለን ያጠፋውትንም እክስሻለሁ!" አለ ሙሉነት በሚነበብት ድምፀት ሃሃሃሃሃ ይቅርታና ድጋሚ አብሮ መቀጠል ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ይቅር ብዬዋለው ግን ደግሞ ትላንት ተሸመድምጄ እንድወድቅ ደግሞ ደጋግሞ ጉድጓድ ከማሰልኝ ሰው ጋር ቁጭ ብዬ የወዳጅነት ቡና አልገባበዝም! ሁልግዜም ቀና ብለው አሻግረው ለተመለከቱ የተሻለ ነገር አለ። ዛሬ ላይ የሱ መኖር በእኔ ህይወት ውስጥ ቅንጣት ታህል ጥቅም የለውም መንገዳችን ለየቅል ሆኗል። እኔ ዛሬ ላይ እንጂ እሱ ትላንት ትቶኝ በሄደበት ቦታ ላይ አይደለሁም ስለዚህ በዙ ነገሮች ተቀይረዋል።ይህን አስረግጬ ነግሬው ተሰናበትኩት።

    Cheers🥂 ለአዲሱ መንገዳችን

ተወዳጆች ሆይ!! ቸር ዋሉ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

05 Nov, 15:12


እንዲህ ነው ነገሩ Happiness is more than just not being sad
Absence of sadness doesn't mean happiness.
Just because someone isn't sad ደስተኛ ነው ማለት አደለም maybe ያ ሰው ባዶነት, ንዴት, ጭንቀት or neutral የሆነ ስሜት ላይ ይሆናል ...which is not the same as happiness
እዉነተኛ ደስታ ከሀዘን ስሜት መራቅ አደለም
Happiness is when u feel actively engaged,connected ስትሆን positive presence ሲሰማህ ነው ደስታ ማለት so Happiness is more than just not being sad!!!
ይሄ ጥያቄ ብዙ ጊዜ እንደ አንድ issue ስለሚነሳ that's why i bring it here... ይምስለኛል ይሄ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው because we think emotions as opposites happy vs sad,angry vs calm, good vs bad
We think happiness and sadness are two side of coin, which is wrong ማለት ሁለቱም የተለያዩ ስሜቶች ናቸው coexist ሊያደርጉ ይቺላሉ , but they are actually separate emotions that can co exist in complex ways
happiness and sadness often coexist, each giving depth to the other. The experiences that cause sadness can sometimes bring wisdom, strength, or clarity, which can enrich happiness too. So, happiness isn't the absence of sadness; it's a state that can coexist with or even be heightened by our acceptance of all emotions.

So like Happiness is more about contentment, fulfillment, or moments of joy and purpose right while sadness often reflects something meaningful that’s been lost or a need that’s unmet. Recognizing sadness doesn’t cancel out happiness; in fact, it can make happy moments feel even more valuable

Instead of trying to erase sadness, embracing it as part of our experience can make us more resilient, compassionate, and capable of feeling deeply

"Yes" ያለችሁ ሰወች we can discusse it here

For me Happiness is more than just not being sad!!!

ፀዴ ምሽት ተመኘሁ

Kal(kaku)✍️

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

05 Nov, 03:28


እየሱስ ሆይ አትምጣ

አንተ የምድር ታላቁ እንግዳ ሆይ ...

(የት ታርፋለህ? ህዝቡንስ ወዴት ትሰበስበዋለህ? ገበያ መሀል? በጭራሽ አይሆንም ! ዘመኑ የይሁዳ ነውኮ። ይጫረቱሀል። ለማይጠረቃ ሆዳቸው ሲሉ ነዋይ ያሰሉብሀል። የዘመኑ ግብይት ደግሞ በገንዘብ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ሆኗል። አንተን ለመሸጥ ሲሉ የእለቱ ምንዛሬ ስለማይበቃቸው የሰውን ነፍስን ይመርቃሉ።

እየሱስ ሆይ አትምጣ። በምድር በየትኛው ክፍል ታርፋለህ?
ወይስ እንደውልደትህ በአንድ የሚስኪን ገበሬ በረት ውስጥ ትገለጣለህ? ዘንድሮ ገበሬ ያለ መስሎህ? ሞፈርና ቀንበሩን ወርውሮ ነፍጥ አንግቷል። በጅራፍ ምትክ ጠመንጃውን እየወለወለ ነው። አትፍረድበት። ኑሮው በሰቀቀን ሆኗል ። ሀገሩ ሁሉ የመንደር አለቃ ሞልቶታል። ልጄን ሊገሉብኝ ሚስቴን ሊደፍሩብኝ ብሎ ተሸብሯል። እና በዚህ ከቀልቡ ያልሆነ ሚስኪን ገበሬ በረት ውስጥ ድንገት ብትከሰት ኢየሱስ መሆንህን ለይቶ ለእግርህ ውሃ ያቀርባል ብለህ ትገምታለህ ? የጠመንጃውን ምላጭ ይስባል ።

አደባባይ ላይስ? ምድሪቱ በሙሉ ተበክላለች
ቤተመቅደስ ውስጥ ? አይሆንም ኢየሱስ ! ቤተመቅደሶቻችን የካድሬ አባቶች መናሀሪያ ከሆኑ ቆዩ። ትልቁ ቤተመቅደስ የሰው ልጅ ነበር። የልቡ መቅደስን ያፈረሰ ትውልድ እንዴት የግንብ አጥሩን ሊያስጠብቅ ይቻለዋል።

እንደአብርሀም ዳስ ትጥላለህ? ሹማምንቶቹ ደግሞ አይሰሙህም። ለልማት ይፈልጉታል። ደም ዘርተው ህንፃ ያበቅሉበታል መሬቱን ሁሉ። ዘመኑ የድንጋይ ነው እዚህ ጋር እናቆምበታለን ዳይ ዳይ ዳሱ ይነቀል !

ምድር ከርፍታለች። አንተን ለሚያህል ታላቅ እንግዳ የሚመጥን አቀባበል የላትም ።በሃጢአት ምክንያት አፈሯም ሰዋም የሚሰነፍጥ ጠረን ያፈልቃሉ። የሰዎቹ ሞገስ ከላያቸው ተገፏል። ደግሞ ርቧቸዋልኮ! ስትመጣ አሁንም ዳቦና አሳ ከሰማይ  ትለማመንላቸዋለህ? የዘመኑ ሆድ የሚጠረቃው በዳቦ አይደለም። በሰው ስጋ ሆኗል! ያውም ደሙ ጠፈፍ ያላለ የሰው ስጋ...

አትምጣ !

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

04 Nov, 16:18


ማንም ሰዉ እኛ የፃፍነውን
ሊያነብ ይችልል ...
ግን ማንም እኛ የሚሰማንን
ሊሰማዉ አይችልም ።

ተሳሳትኩ?

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

03 Nov, 19:31


"ማን ትባላለህ ልጄ?" አሉኝ። ዮሓቶኤል እባላለሁ እማማ አልኳቸው ። ቁመታቸው ከደረቴ ስለማያልፍ አናታቸው ጭስ ጭስ ይሸታል። ከነጠላቸው ሾልከው የወጡት ፀጉራቸው ከነጠላቸው ከለር ጋር ተመሳስሏል።

" የኔ ልጅ ዮሓ እባክህን ላስቸግርህ። ይቺን ፍራንክ ለልጄ ልሰድላት ነበር። ጣፍልኝ ከወረቀቱ ላይ" አሉኝ ከደረታቸው ውስጥ መዳፍ የምታክል ቦርሳ እያወጡ። እጆቻቸው ስራቸውን ሲከውኑ ጣቶቻቸው ይንቀጠቀጣሉ። ጫፎቻቸው ተሰነጣጥቀዋል። ከቦርሳዋ ብሩን ፈልፍለው አውጥተው እንደተጠቀለለ ሰጡኝ።

"እስኪ ቁጠረው ልጄ። አንድ ወር ሙሉ ሶፍት ሽጬ ያጠራቀምኩት ነው። አላውቅም ስንት መሆኑን ቁጠረው" አምነውኝ ያልቆጠሩትን ገንዘብ እንዲሁ ሲሰጡኝ ገረመኝ። እናትነታቸው ይጋባል። ዝርዝርና ድፍን ብሮችን ቆጥሬ ነገርኳቸው። 1200 ብር! ነገርኳቸው።

"ጎበዝ!" አሉ እጃቸውን እያማቱ። ደስ አላቸው። የሚጠበቅባቸውን ያህል ያሟሉ እንደሆነ ተሰምቷቸዋል። " በል እዚህ ወረቀት ላይ ጣፍልኝ። ለልጄ ብሩክታይት ጀምበሩ ብለህ አስገባልኝማ እሰይ" አሉኝ ከነበሩበት ስሜት ወጥተው እየሳቁ። ምናልባት ይህ በህይወታቸው ትልቁ ድል ይሆናል ። ዩኒቨርስቲ ለምትማር ልጃቸው 1200 ብር መላክ የሰማይ ያህል ርቋቸው የከረመ ይመስላል። አሁን ግን አደረጉት !!

"አየህ አሁን እኔ ይሄን ልኬላት በእግሬ ነው ብዙ መንገድ በእግሬ የምሄደው። ለታክሲ በሚል እንኳ አልቀንስባትም። ብዙ ጊዜ ሆነኝ ከላኩላትኮ። ቢሆንም ትጦረኛለች ብዬ ነው ልጄዋ" አሉኝ የመላኪያ ወረቀቱ ላይ እየፃፍኩላቸው። ጣታቸው ላይ ቀለም ቀብቼ አስፈረምኳቸው። ጣቶቻቸው ሟምተዋል። ወስጄ አስገባሁላቸው ገንዘቡን። ያስገባሁበትን ደረሰኝ አምጥቼ ሰጠኋቸው። ገብቷል ስላቸው የድል አድራጊነት ስሜታቸው ገንፍሎ እጄን ስበው ሳሙኝ መረቁኝ። እጄን ሳይለቁኝ ይቺን ደሞ ለታክሲ ትሆናለች ያዟት ብዬ 50 ብር አስጨበጥኳቸው። ደስ አለኝ ይህን ስላደረኩላቸው!!

ከባንኩ ወጣሁ። እጄን ወደ ኪሴ አስገባሁ። 600 መቶ ብሮችን ጨብጬ አወጣሁ። ከ1200 ብር ላይ እኩል ለእኩል የተከፈለ ገንዘብ። 600 መቶ ብርን ለብሩክታይት አስገብቼላታለሁ። ህይወት እንዲህ ፍትሀዊ መሆን አለባት። የእናቷን እርዳታ በምትፈልገው ብሩክታይት እና በሽተኛ እናቱ እርዳታ በሚያስፈልገው እኔ ዮሓቶኤል መሀል ዛሬ ፍትህ ሰፍናለች።

አስፋልት ተሻግሮ መድሀኒት መደብር ይታየኛል። ወደሱ አመራሁ....😓

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

03 Nov, 14:26


ንጉሡ ለባለሟሎቹ ከተማው መሀል ላይ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዘዛቸው። ባለሟሎቹም በታዘዙት መሠረት ከተማው መሀል ትልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ።

ንጉሱም የተቆፈረውን ጉድጓድ ካየ በኀሏ ማታ ላይ የከተማው ሰው ሁሉ አንድ ብርጭቆ ወተት አምጥቶ ጉድጓዱን እንዲሞላ አዘዘ። አንድ ሰው ግን አንድ እኩይ ሀሳብን አሰበ።ወደ ጉድጓዱ በወተት ፋንታ ውሀ መውሰድ።  ሁሉም ወተት ስለሚወስድ የኔ ውሀ መውሰድ አይታወቅም በዛ ላይ ምሽት ስለሆነ ማንም አያየኝም ብሎ አንድ ብርጭቆ ውሀ ጉድጓዱ ውስጥ ጨመረ።

በማግስቱ ንጉሱ በወተት የተሞላውን ጉድጓድ ለማየት ሲሄድ ባየው ነገር ተደናገጠ። ጉድጓዱ በወተት ሳይሆን በውሀ ነበር የተሞላው። ልክ በወተት ፋንታ ውሀ እንደወሰደው ሰው የከተማው ሰው ሁሉ "ሌላው ወተት ስለሚያመጣ እኔ ውሀ ብወስድ የሚያውቅ የለም"ብሎ ወተት ሳይሆን ውሀ ነበር የወሰደው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

02 Nov, 13:34


ተማሪው መምህሩን ይጠይቃል

👇🏾

በህይወቴ ምን አይነት ውሳኔዎችን ልወስን?

መምህሩ ይመልሳል?

👇🏾

የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውሳኔዎች አሉ

አንዳንድ ውሳኔዎች ባርኔጣ ናቸው - ባርኔጣ አንድ ጊዜ ትሞክረውና ካልተስማማህ እና ካላማረብህ አውልቀህ ሌላውን ትቀይረዋለህ: የሚያምርብህን ታደርጋለህ

አንዳንድ ውሳኔዎች የፀጉር ቁርጥ ናቸው - ፀጉርህን ትቆረጣለህ ግን አትወደውም: አዲስ ቁርጥ ልትሞክር ትችላለህ ነገር ግን ካልወደድከው እና ከአንተ ስታይል ጋር ካልሄደ እስኪበቅል የመጠበቅ ሁለተኛ እድል አለህ: ፀጉርህ ወደ ቦታው እስኪመለስ ትእግስት ማድረግ ብቻ ነው

አንዳንድ ውሳኔዎች ንቅሳት ናቸው - ንቅሳት አንድ ጊዜ ገላህ ላይ ካረፈ የሰውነትህ አካል ነው: አትቆርጠውም አትፍቀውም:: በመስታወት ስታየውም ሆነ ሰዎች ሲያስታውሱህ ያለፈውን ተቀብለህ የወደፊቱን ከመራመድ ውጪ አማራጭ የለህም

👇🏾

ሁላችንም የባርኔጣ: የፀጉር ቁርጥ እና የንቅሳት ውጤቶች ነን

❤️🙌🏼

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

02 Nov, 06:04


ተስፋ !

ተስፋ የሰው ልጅ ተረጋግቶና በሠላም ይኖር ዘንድ ከፈጣሪው የተሰጠ ዋነኛው ስጦታ ነው። ከ22ቱ ፍጥረታት መካከል በተስፋ የሚኖር የሰው ልጅ ብቻ  ነው። ሰው በተስፋ የማይኖር ከሆነ ባዶ፣ ተቅበዝባዥና በጭንቀት የሚኖር ብሎም ራሱን ወደ መጥላትና ማጥፋት የሚጓዝ ግደለሽ ይሆናል።

ተስፋ ማለት በየዕለቱ ሊገጥሙን ለሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች መፍትሔ፣ ለሃዘናችን መጽናኛ፣ ለደስታችን ፍሬ በጉጉት የምንጠብቅበት ብቻም ሳይሆን  አስቸጋሪ መስለው ለሚታዩን ነገሮች በጎ ነገርን የምናይበት ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው።

ለዚህም ነው ሰዎች በምክራቸው  "ተስፋችሁ ሕያው፣ ጠንካራ፣ ጽኑና የማይናወጥ መሆን አለበት" የሚሉት።

ተስፋ ካለን ብዙ ነገሮች አሉን፤ የምንሄድበት አቅጣጫ የምንንቀሳቀስበት ኃይል፣ ብዙ አማራጮች ሺህ መንገዶችና ሊገመቱ የማይችሉ ህልሞች አሉን ተስፋ ካለን መሄድ ወደ ምንፈልግበት ቦታ ግማሽ መንገድ ላይ ደርሰናል ማለት ሲሆን ተስፋ ከሌለን ወይም ተስፋ ከቆረጥን ግን ለዘለዓለሙ ጠፍተናል ማለት ነው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

01 Nov, 17:01


ከዚህ ትምህርትቤት ሳንወጣ። አንዲት ወፈርፈር ያለች የሳይንስ አስተማሪ ስለእንስሳት ተዋፅዖ ለማስተማር በክፍሉ ውስጥ በተመስጦ ቆማለች። ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ምንም ቅደመ ንግግር ሳታደርግ አንድ የተጠማመደችውን ተማሪ አስነስታ ትጠይቀዋለች።


አስተማሪዋ: "ዶሮ ምን ትሰጥሃለች?"

ተማሪው፡ "እንቁላል!"

አስተማሪ: "በጣም ጥሩ፤ እሺ በሬ ምን ይሰጥሃል?"

ተማሪው፡ "ስጋ"

አስተማሪዋ: "በጣም ጥሩ፤ እምም
... የሰባች ላም ምን ልትሰጥህ ትችላለች?"

ተማሪው፡ "የቤት ስራ!"
😕

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

01 Nov, 16:22


አስተማሪው በጠዋት ገብቶ ተማሪዎቹን ስለራስ ከፍ ያለ ግምት ሊያስተምራቸው ፈለገና "እስቲ ደደብ የሆነ ከመቀመጫው ይነሳ" ብሎ ጠየቀ። ሁሉም ሲቀጡ አንድ ልጅ ብቻ ተነስቶ ቆመ። አስተማሪው ማንም አይነሳም ብሎ ስላሰበ በመገረም “ለምን ተነሳህ?” ብሎ ጠየቀው። ተማሪውም “አውቃለው በሁለታችን መኃል ብዙ አለመግባባት ይኖራል፤ ነገር ግን አንተን ብቻህን ስትቆም ጨክኜ ልተውህ አልቻልኩ” 😑

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

31 Oct, 16:00


[ የህይወት መርሆዎች በተለያዩ ፈላስፎች አንደበት ]

1. የበለጠ ለማወቅ ጣር  (Platonism)

2. መልካም ሰው ሁን (Aristotelianism)

3. ራስህን ቻል (cynicism)

4. ዛሬ ተደሰት ነገ ለራሱ ይጨነቅ (hedonism)

5. ራስህን ከስቃይ አግልል (epicureanism)

6. ምክንያታዊ ሁን መቀየር ማትችለው ነገር አያስጨንቅህ (stoicism)

7. የግለሰብ ነጻነትን አክብር (classical liberalism)

8. ሌሎች እንዲያደርጉልህ ምትፍለገውን ነገር ለሌሎች አድርግ (kantianism)

9. የምትፍለገውን ነገር አድርግ ምክንያቱም ህይወት ትርጉም የለውም (nihilism)

10. ሃሳብህ ላይ ሳይሆን ተግባርህ ላይ ትኩረት አድርግ (pragmatism)

11. የፈጣሪህን አላማ ኑር  (Theism)

12. ያንተ ውስኔ ያንተን ህይወት ይመራል (Existentialism)

13.የህይወት ትርጉም ምንድነው እያልክ
አትፈላሰፍ፣ ዝም ብለህ ኑር (Absurdism)

14. ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው (humanism)

15. ህይወት ትርጉም የለውም አነተ ትርጉም ካልሰጠኸው logical (positivism)

16. ሰዎችን ሁሉ እኩል ውደድ (Mohsim)

17. ከቅንጦት የጸዳ ተራ ህይወት የበለጠ ትርጉም አለው (Confucianism)


*

              - የቱን ህግ ወደዳችሁት?

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

30 Oct, 15:41


ይህ ስዕል "ፈተናን በድጋሚ መውደቅ" ይባላል

ስዕሉ የተሳለው በእውቁ ራሺያዊ ሰአሊ ፌዶር ራሽቲንኮቭ ሲሆን የስእሉ ጭብጥ ከትምህርት ቤት ፈተና ወድቆ ወላጆቹ ፊት በሃፍረት የቆመ አንድ ታዳጊን ያሳያል

ታዳጊው ፈተናውን በድጋሚ በመውደቁ በቤተሰቡ ፊት ራሱን አቀርቅሮ ወንድሙን ጨምሮ የቤተሰቡ አባላት ሁሉ "እንዴት ድጋሚ ትወድቃለህ?" ብለው በሃፍረት አንገቱን አስደፍተውት ያሳያል

የአርቲስቱ መልእክት "እንደ ውሻው ተቀበሉት" የሚል ነው

በስእሉ ላይ እንደሚታየው ታዳጊው ፈተናውን ቢወድቅም የውሻው ፍቅር አልጎደለበትም - በውድቀቱም ሆነ በስኬቱ ከፍቅር አልጎደለበትምና



ይህ በ1952 እ.ኤ.አ የተሳለው ስእል ሰዎችን በፍቅር እና በትህትና  ከውድቀታቸው ስለማንሳት ተምሳሌት ሆኗል

በሰዎች ውድቀት  ከፍቅር አትጉደሉ❗️❗️

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Oct, 14:59


የህይወት ጣእሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤ በየእለቱ ተመሳሳይ ሕይወት የሚኖሩና በሕይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች አሉ። |
ሕይወትን በማሰብ ( በአእምሮ ) ብቻ የሚኖሯት ሰዎች ሕይወት ትርጉም አልባ ሆናባቸዋለች። ኦሾ የምዕራባውያንን ፈላስፎች የሚከሳቸው አንደኛው በዚህ ነው ፣ "ሕይወትን በአእምሮ ተግባራት ብቻ በመሙላት አሰልቺ ያደረጉ ፤ የልብ ቋንቋ የማይገባቸው ፤" ይላቸዋል።
ህይወትን በአእምሮ ሳይሆን በልብ ኑሯት ፤ ህይወታችሁን በልባችሁ ቋንቋ ስትመሯት አእምሯችሁ ታላቅ ተፈጥሮውን ያሳያችኋል፡፡ በአእምሯችሁ ስትኖሩ ፖለቲከኛ ፣ ዘረኛ ፣ አክራሪ ... ወዘተ ትሆናላችሁ ፤ በልባችሁ ስትኖሩ ግን መንፈሳዊ ትሆናላችሁ። በልባችሁ ስትኖሩ የህይወት ጣዕሙ ይገባችኋል፤ የፍቅር ሙቀቱ ይሰማችኋል፡፡
ተልእኳችሁን ስታቁና በተሰጥኦዋችሁ ስትኖሩ የሕይወታችሁ ገዢ ሀይል ከልባችሁ ይመነጫል፤ አእምሯችሁም የልባችሁ ታዛዥ ይሆናል፡፡ ሴቶች ከወንዶች የሚበልጡትና ከወንዶች ይልቅ ደስተኞች የሆኑት ለዚህ ነው፤ ወንድ ሕይወቱን የሚዘውረው በአእምሮው ሲሆን ፣ የሴቷን ሕይወት የሚዘውረው ግን ልቧ ነው፡፡
ከአእምሮ ሎጂክና ምክንያት ሲወጣ ፣ ከልብ ግን ፍቅር ይወጣል። ሎጂክና ምክንያት ብዙ ነገሮችን ትርጉም አልባ እና አሰልቺ ሲያደርጋቸው፤ ፍቅር ግን እያንዳንዱን የሕይወት ስንጣሪ በትርጉም የተሞላችና አስደሳች ያደርጋታል።

#ፍልስፍና ፩ ከተሰኘው የ ብሩህ ዓለምነህ መፅሐፍ ከመጨረሻው ገፅ ላይ የተወሰደ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

26 Oct, 10:52


ከመንጋው ጋር ካልሆኑ በስተቀር መዝናናት የማይችሉ አሉ፤ እውነተኛው ጀግና ብቻውን ይዝናናል።

            -Charles Baudelaire

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

25 Oct, 23:19


ለእነሱ ብላችሁ የራቋቻዋቸው ሰዎች አሉ አይደል? እየወደዳቹሀቸው ግን እነሱ እንዳይጎዱ እናንተ ተጎድታችሁ ትውት ያረጓችሁዋቸው ሰዎች

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

25 Oct, 04:45


የኦሾ እይታ

#ማወዳደር ታላቁ በሽታ

ማወዳደር በሽታ ነው። ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ በሽታ። እናትህ ከሌሎች ልጆቿ ጋር ታወዳድራሃለች፤ አባትህ አስተማሪህ ሁሉም ያወዳድሩሃል። እየው እሱን እንዴት እንደተሳካለት አንተ ግን ምንም ዋጋ የለህም ይሉሃል።

#ከመጀመርያ ጀምሮ እራስህን ከሌሎች ጋር እንድታወዳድር ነው የሚነግርህ። ይህ ከበሽታዎች ሁሉ የከፋ ነው። እኔ እኔ ነኝ አንተ ደግሞ ራስህ ነህ።በቃ! ማንጎና ፖምን ታወዳድራለህ?አታወዳድርም። እያንዳንዱ ሰው ፍጹም የተለየ ነው።ስለዚህ ማወዳደር የሚባል ነገር ሊታሰብ አይገባም።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Oct, 15:32


እርጋታ ዝምታ አይደለም። የቱጋ ዝም ማለት እንዳለብን ማወቅ ነው። የሁሉም መልስ ያለው ሁሉንም ጥያቄ ጠይቆ የጨረሰ ነው። የቱን መምረጥ እንዳለበት የሚያውቅ፤ ችላ ባለው  ትርምስ ውስጥ እርጋታ የልቦናው በር ይጎበኘዋል። ጠቢብ ግን ባንቀላፉት  መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይሰርቃል

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

24 Oct, 09:04


ደስታችንን ያጣነው መሞት እንዳለ ስለምንዘነጋ ነው። .....ለዚህ ሁሉ ሁካታ ....፤ ለዚህ ሁሉ የሕይወት ፍጥጫ ማብቂያ እንዳለው  ስለማናስብ ነው ።  ...የሰው ልጅ ለመኖር  ያለው ከፍተኛ ፍላጎት እውነታውን እንዳያስብ ያደርገዋል።ወይም ደግሞ መሞትን መፍራቱ ያለውን እውነታ ከመቀበል ይልቅ 𝚊𝚟𝚘𝚒𝚍𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚋𝚑𝚊𝚟𝚒𝚘𝚛𝚜 እንዲኖረው ያደርጋል። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ጆሮን ዳባ ልበስ ብሎ ሁሉም እንደሚያልፍ እና  ጊዜያዊ መሆኑን የረሳ ቀን ስስት...፤ ጊዜያዊ ደስታን ብቻ መፈለግ... ፤ መጨነቅ ....፤ ተስፍ መቁረጥ.. እና ሌሎች እልፍ የሆኑ ሀሳቦች ተግተልትለው ይመጣሉ።Arthur Schopenhauer  የተባለው የጀርመን ፈላስፍ ሞትን እንደ  መጥፎ ነገር ከማየት ይልቅ የሕይወት ዋናው እና አስፈላጊ ነገር አንደሆነ ያምናል። ሞትን 𝚝𝚑𝚎 𝚞𝚕𝚝𝚒𝚖𝚊𝚝𝚎 𝚐𝚘𝚊𝚕 𝚘𝚏 𝚕𝚒𝚏𝚎 ,ማብቂያ ከሌለው ውስጣዊ ፍላጎትና ስቃይ     ነፃ የምንወጣበት መቋጫ ነው ሲል ያትታል። .....𝚂𝚘𝚌𝚛𝚊𝚝𝚎𝚜 እንዲሁም 𝚎𝚙𝚒𝚌𝚞𝚛𝚞𝚜 ሀሳቡን ይጋሩታል። እኔም ፈላስፍ ከተባልኩ የነሱን ሀሳብ እጋራለው።
ሀሙስ ሌሊት 7:30

.
.
.
𝚘𝚟𝚎𝚛𝚝𝚑𝚒𝚗𝚔  እያረኩ ይሆን ? ብላ እራሷን ጠየቀች ። ....ሁሌም እንዲህ ናት በውስጧ የሚመላለስ ሀሳብ  ካለ ተናግራው ወይ ፅፋው ካላወጣችው  እንቅልፍ አይወስዳትም።  በዚህ ውድቅት ለሊት ከ𝙳𝚒𝚊𝚛𝚢 ጋር እንድትፍጠጥ ያደረጋት። ይህን ከትባ ሰከንድ ሳይጅባት ነበር ለሞት ታናሽ ወንድም እንቅልፍ እጇን የሰጠችው......።

https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

23 Oct, 19:09


በሕይወት አንድ ቀን.....
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

23 Oct, 16:57


የዚህ ቻናል ምርጡ ሰው 👉 tg://settings
😁

Clamp your hand👏👏👏👏

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

23 Oct, 05:35


አንዳንዱ ክለብ ለክለብ ሲንዘላዘል ስላደረ አሪፍ የሆነ ይመስለዋል😔

አንዳንዱ ፌስቡክ ላይቭ ገብቶ በድፍረት ስለተበጠረቀ የሁሉ ነገር ተንታኝ የሆነ ይመስለዋል😜

አንዳንዱ ሁለት መፅሃፍ አንብቦ የሁሉም ነገር አዋቂ የሆነ ይመስለዋል🥲

አንዳንዱ አንድ ወር ጂም ሰርቶ ትንሽ ደረቱ አበጥ ካለ ሁሉንም ደብድቦ የሚያሸንፍ ይመስለዋል🥲

አንዳንዱ እሱ ሲበጠረቅ አንተ ዝም ብለህ ስለሰማህ እሱ አዋቂ አንተ ደነዝ ይመስለዋል😌

አንዳንዱ በብዙ ሰው ሲከበርና ሲወደድ እሱ ራሱ ተራ ሰው መሆኑን ይረሳውና የተለየ ይመስለዋል😒

ብቻ ምን አለፋህ ደነዝ ምን የማይመስለው አለ😳

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

22 Oct, 15:40


አንዲት እናት ግመልና እና ሕፃን ልጇ ከለምለም ዛፍ ሥር ተኝተው ነበር። ከዚያም ሕፃኑ ግመል "እኛ ግመሎች ለምን ቶሎ ቶሎ ውሃ አይጠማንም?" ብሎ ጠየቃት። እናትም "እኛ የበረሃ እንስሳት ስለሆንን በጣም ትንሽ ውሃ ይዘን እንድንኖር ውሃ ለማከማቸት የተዘጋጀ የሰውነት አካል አለን" አለችው።

ሕፃኑ ግመልም ለትንሽ ጊዜ አሰበና ፣ “እሺ… እግሮቻችን ለምን ረጃጅም እና ጠንካሮች ሆኑ?" አላት፤ እናትም "በረሃ ውስጥ ለመራመድ ታስበው የተፈጠሩ ናቸው" ብላ መለሰች። ሕፃኑ ለአፍታ ቆመና አስቦ አስቦ "ለምን የዐይን ሽፋኖቻችን ረዘሙ?"
እናትም "እነዚህ ረዣዥምና ወፍራም የዓይን ሽፋኖች ንፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ዓይኖቻችንን ከበረሃው አሸዋ ይከላከላሉ"አለችው።

ሕፃኑ ግመል በጣም አሳብ ያዘውና እያሰበ በዛው ተኛ። በነገታውም እናቱ ጋር ሄዶ እንዲህ አላት፤ "በረሃ ውስጥ ብንሆን ኖሮ ውሃ ለማጠራቀም የሚረዳ አካል አለን አላት በአፉ እየጠቆመ፤ እግሮቻችን በበረሃ ውስጥ ለመራመድ ተብለው የተሰሩ ናቸው እና የዓይን ሽፋኖቻችን ከበረሃ አሸዋ ዐይኖቻችንን ይጠብቃሉ" እናት በልጇ የማስታወስ ችሎታ ተገርማ ሳታበቃ፤ ልጇ ይሄን ጠየቃት " ግን እኮ እማ፤ እኛ ያለነው እጅግ ለምለም በሆነ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ ነው!"
***
ሞራል፡
ተሰጥኦዎ ጠቃሚ የሚሆነው የተገቢው ቦታ ላይ ከሆነ ብቻ ነው። ያለዛ ለምን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል
?
***

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

22 Oct, 04:59


𝙻𝚎𝚜𝚜𝚘𝚗𝚜 𝚒𝚗 𝚕𝚒𝚏𝚎 𝚠𝚒𝚕𝚕 𝚋𝚎 𝚛𝚎𝚙𝚎𝚊𝚝𝚎𝚍 𝚞𝚗𝚝𝚒𝚕 𝚝𝚑𝚎𝚢 𝚊𝚛𝚎 𝚕𝚎𝚊𝚛𝚗𝚎𝚍.
-𝚞𝚗𝚔𝚗𝚘𝚠𝚗

https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

21 Oct, 16:26


አንድ ድሀ ሰው ነበረ..
ሶስት ብርቱካኖችን ይገዛል  ሊበላ አንደኛውን ብርቱካን ሲቆርጠው የተበላሸ ነው... ሁለተኛውንም ሲቆርጠው የተበላሸ ነው... ሶስተኛውን ከመቁረጡ በፊት ግን መብራቱን አጠፋና ቆርጦ በላው።....

አንዳዴ ለመኖር ሲባል አይተን👀 እንዳላየን ሰምተን👂 እንዳልሰማን መሆን አለብን !

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

20 Oct, 14:42


ምን በጣም ያስፈራሻል.....?𝚊𝚝𝚝𝚊𝚌𝚑𝚖𝚎𝚗𝚝....አለችኝ
ለምን?

ለምን ማለት ጥሩ...አለች ብልጭ ያለች ፈገግታ እያሳየችኝ
...ምክንያቱም የማጣትን መራራ ፅዋ ስጋት ስለኖርኩ ፤ ምክንያቱም ሰው በጣም  በምፈልግ ሰዐት በረሀ ላይ እንደበቀለች ግራር የብቸኝነት ነፋስ ሲወዘውዘኝ ስላደኩ ....ብቻ ለምን ካልከኝ  ሺህ ምክንያት ይኖራል ። I don't know ምናልባት 𝚙𝚊𝚛𝚊𝚍𝚘𝚡𝚒𝚊𝚕 ሆኜ ይሆናል ።ግን...
ከዚህ በላይ አልቀጠለችም ። የቀረውን ብሶት ቃል ሳታወጣ በእንባዋ ብቻ ነገረቺኝ።
.
.
.𝚙𝚊𝚛𝚊𝚍𝚘𝚡𝚒𝚊𝚕 ...እውነትም እርስዋ  ነች። በነገሮች በጣም ተስፍ ታረጋለች በዛው ልክ እራሷን ታርቃለች።  በጣም ተግባቢ በዛው ልክ በጣም ብቸኛ። በጣም ጠንካራ ግን ደካማ። 𝚜𝚑𝚎 𝚒𝚜𝚓𝚞𝚜𝚝 𝚙𝚛𝚎𝚍𝚒𝚌𝚝𝚊𝚋𝚕𝚎 𝚒𝚗 𝚑𝚎𝚛 𝚞𝚗𝚙𝚛𝚎𝚍𝚒𝚌𝚝𝚊𝚋𝚒𝚝𝚢........

𝕒𝕓𝕦
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

20 Oct, 03:35


🪐

        ^^ ሰዎችን ትጠላለህ እንዴ? ^^

አልጠላቸውም!፤ ብቻ በአቅራቢያዬ በሌሉ ጊዜ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል..።

         -ቡኮውስኪ

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

19 Oct, 11:02


....ላንቺ ያለኝን የጓደኝነት ፍቅር ጥልቀት ማወቅ ትፈልጊያለሽ?እንግዲያውስ ስሚኝ....

...በህይወት ሳለሁ ለተላለፍኩት ህግ ለሰራሁት ስራ የነፍሴ መዳረሻ ገሀነም እንደሆነ አውቃለሁ ።ምክንያቱም እኔ የማረባና መጥፎ ነኛ! ጂስሜን የሚወሰውሰው አመንዝራነት ነበር ።ይሄ ደሞ በእግዜሩ ህግ ወደ ጄሀነም የሚያስጥል ይቅር የማይባል ሀጢያት  ነው...

...አንቺ ደሞ ቅን ነሽ ።ሰው ወዳድም ነሸ ።በህይወትሽ የገነት በሮችን የሚያስከረችም በደል የለብሽምና የምትከትሚው ገነት ነው ።የሚገባሽ ቦታ እዛ ነው ።እናም አንቺ ጄነት እኔ ሲኦል ስንገባ ወዳጅነታችን እንደሚያበቃ ሳስብ ከእሳቱ በላይ አንቺን ባለማግኘት የምቃጠለው የላቀ እንደሆነ አውቃለሁ...

...በመጨረሻ እኔ ሲኦል አንቺ ገነት ገብተሽ ስንለያይ...

-ከእግዜሩ በላይ
-ጥያራ ከሚያስከነዱት መላኢካዎች በላይ
-ከነፋሻው የገነት ቀዝቃዛ አየር በላይ

....ከሁሉ በላይ የምናፍቀው...

...በገሀነም የእሳት አጥሮች ተንጠላጥየ  የአንቺን ፊት አሻግሬ ማየት ነው.....

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

19 Oct, 07:13


"Today’s goals: Coffee and kindness. Maybe two coffees, and then kindness."
— Nanea Hoffman.
https://t.me/taoriia

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

18 Oct, 16:44


አታርፍድ!

የሕይወት ትልቁ ስህተት
#ማርፈድ ነው። ሁሉም የሚያምረውና የሚበጀው በጊዜው ሲሆን ነው፡፡ ማድረግ ያለብህን ነገር ሳታመነታ ቶሎ አድርገው፤ መጀመር ያለብህን ጉዳይ ሳትዘገይ ጀምረው፤ መተው ያለብህም ነገር ካለ ሳታቅማማ በጊዜ ተወው፤ መወሰን ያለብህ ጉዳይ ካለም ዛሬውኑ ወስን፤ ማቋረጥ ያለብህን ግኑኝነት ካለ ሳይወሳሰብ ቋጨው። ህይወት ማለት እንደ አልፎ ሂያጅ ወንዝ ናት፤
ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትራመድም። ረፍዶ ኋላ እንዳይፀፅትህ ጊዜና ዕድሜህን በአግባቡ ተጠቀምበት። አስተውል! ፀፀት መጀመሪያ መጥቶ አያውቅም መጨረሻ እንጂ። ስለዚህ ነገን እንዳይቆጭህ ዛሬን
#አታርፍድ

    መልካም ምሽት ❤️

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

18 Oct, 15:59


አንዳንዴ ማንም ህያው የሆነ  ሁሉ ልብህ ውስጥ የተሸከምከውን ሸክም አይረዳልህም ።ማንም።በህይወት ስትጓዝ የሚገጥሙህን የልብህን መጋጋጥ ማንም ምንም አያውቅልህም!!  አንተው ልብ ውስጥ በቅለው አንተው ልብ ውስጥ ኖረው አንተው ልብ ውስጥ ብቻ ቀርተው  ካንተው ጋር የሚቀበሩ አንተ ብቻ ያየሀቸው አንተ ብቻ የተረዳሀቸው ስንት እውነቶች አሉ ? ማንም ሳያውቅልህ!! ማንም ሳይሰማልህ!! ማንም ሳያይልህ!! ያንተው እውነት ብቻ ሆነው ወደ ዘለአለም አለም አዘቅት የሚወርዱ ስንት ነገር አለ ልብህ ውስጥ ገና ለመናገር ስታስብ እንኳ ዳገት የሚሆንብህ!!



ብቻ ዝም ነው።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

18 Oct, 14:42


`` አእምሮ ያለው ማንኛውም ሰው የአእምሮ ህመም ሊያጋጥመው ይችላል። የሌላቸው ሰዎች ግን አያሰጋቸውም። ``

     
📷 በአንድ ወቅት አማኑኤል ሆስፒታል

     ..ያለ አእምሮ ጤና ፤ ጤና የለም!..

                   -ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

18 Oct, 03:42


እምነት ወደ እውነት የሚደረግ የህይወት ጉዞ እንጂ በቃላት የሚደረግ ጫወታ አይደለም።

ፈጣሪ የሚለው ሃሳብ በሰው ልጅ ውስጥ መፈጠሩ በራሱ የእሱ ህልውና ማረጋገጫ ነው ስለዚህም ይህ ነው እምነት።

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

17 Oct, 18:56


...ብረሳሽ አሁን አይከፋኝም ነበር፡፡አያመኝም ነበር፡፡ራስህን አጥፋ አጥፋ የሚል ድምጽ አይሰማኝም ነበር፡፡ግን አልሞትም፡፡ራሴን ካጠፋሁ ትዝታሽን ባጣውስ?ደግሜ እየወደድኩሽ ባልኖርስ?ስምሽ ቢጠፋብኝ ድምጽሽ ቢርቀኝስ?የሴጣን ጆሮ ይደፈን ሞቼስ አንቺን በመርሳት ድጋሚ አልሞትም!!!እንዲሁ ባከበብኳት መስመር ውስጥ እኖራለሁ እንጂ!!!!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

17 Oct, 16:09


ሰውዬው ስራ አጥ ነው
ከአንድ ድርጅት ዘንድ ሄዶ "ተላላኪም ቢሆን ቅጠሩኝ" ብሎ ይማፀናል

የድርጅቱ ቀጣሪ "ኢሜይልህን ስጠኝ እና ፎርም እልክልሃለሁ: እሱን ሞልተህ ይዘህ ትመጣለህ" ይለዋል

"ጌታዬ! እኔ ዘመናዊ ስልክ እና ኮምፒውተር የለኝም :ኢሜይልም አልጠቀምም:: ስራው ግን በጣም ያስፈልገኛል" ብሎ ይማፀናል

"ኢሜይል እንኳ ሳይኖርህ ነው እንዴ ስራ የምትጠይቀው!" ብሎ በግልምጫ ያሰናብተዋል

ሰውዬው ወደ መንደሩ ተመለሰ
ስራ የማግኘት ተስፋው ሲደበዝዝ እጁ ላይ በሚገኘው ብር እንቁላል ቀቅሎ አካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች ማቅረብ ጀመረ: ትንሽ ቆይቶ ትርፉን በማጠራቀም ሌሎች ምግቦችን ጨመረ

እንዲህ እንዲህ እያለ ለትላልቅ ተቋማት እና ዩኒቨርስቲዎች ምግብ የሚያቀርብ ስኬታማ ሰው ሆነ

***

ከአመታት በኃላ ላፈራው ንብረት ኢንሹራንስ ለመግባት ወደ አንድ ድርጅት ጎራ ብሎ ጉዳዩን አስረዳ

"የሚሞላ ፎርም ስላለ ኢሜይልህን ስጠኝ!" አለችው አስተናባሪዋ

"ኢሜይል የለኝም እመቤቴ"

"ኢሜይል ሳይኖርህ እንዲህ ስኬታማ የምግብ ኢንዱስትሪ ከገነባህ ኢሜይል ቢኖርህ ደግሞ ምን ልትሆን ትችል እንደነበር ታውቀዋለህ?"

ሰውዬው መለሰ

👇🏾

"አዎ አውቀዋለሁ: ተላላኪ ነበር የምሆነው"

ሰዎች በሚለጥፉባችሁ ስያሜ እና ስለ እናንተ ባላቸው አመለካከት አትገደቡ !!❤️🙌🏼

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

17 Oct, 05:59


አንድ ዕለት የሞተ ማንነቴን እየቀበርኩ ሳለ መቃብር ቆፋሪው
ወደ እኔ መጣና «ለቀብር እዚህ ከሚመጡት ሁሉ አንተን ብቻ እወድሃለሁ» አለኝ፡፡

«አንተም ደስ ትለኛለህ፣ ግን እኔን እንዴት ልትወደኝ ቻልክ?»አልኩት፡፡

«ምክንያቱም» አለኝ፡፡ «ሌሎቹ ሲመጡም ሲሄዱም ያለቅሳሉ፡፡ አንተ ግን ስትመጣም ስትሄድም ትስቃለህ፡፡»

📙ርዕስ: የጥበብ መንገድ
✍️ደራሲ: ካህሊል ጂብራን