የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation @housingdevelomentcorporation Channel on Telegram

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

@housingdevelomentcorporation


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation (Amharic)

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በበቀለበት ሕግ ለወጡን ውጤቶች በባለሙያን በትኑር ድርጅቶች የምስራቅ ስነ-መስከረም፡መልካም ማህበረሰብ፣ ደምር፡መስራትና አባልነቱ በዚህ አስተዳደር ለመጠቀም የቀናት ማህበረሰብ እና ታማኝ ማህበረሰብ እንዲሆኑ ነው። ይህንን ህብረተሰብ ለቀላሉ ከመንግስት ፈሳሽ የበለጠ በሚለው ዓለም ፍቅር የሚያደርገ ገቢ እንደሆነ ተወዳዳሪ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

03 Oct, 08:07


የተከበራችሁ የቴግራም ገፃችን ተከታዮች በሙሉ ተቋማችን አዲስ የቴለግራም ገፅ የከፈተ በመሆኑ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ(link) እንድትከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን https://t.me/aahdc_official

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

03 Oct, 06:17


እሬቻ የጋራ ሃብታችን፣ የሁላችንም ኩራት፣ የአብሮነታችን መድመቂያና ዘመናትን በህብር የተሻገረው የአብሮ መኖራችን ሚስጥር ነው"አቶ ከፍያለው ተፈራ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት አካባቢ የፅዳት መርሀ ግብር አካሄደ።

የፅዳት መርሐ ግብሩ በኦሮሞ ባህል መሰረት በአባገዳዎችና በሀደሲንቄዎች በምረቃ ስነ ሰርዓት ተጀምሯል።

ፅዳቱን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ኢሬቻ ሰላም በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ለሰላምና ለአብሮነት ያለንን ቁርጠኝነት በማሳየታችን ነው ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህልና እሴት አክብራ የምትንቀሳቀስ መሆኗን ያስታወሱት ኢንጂነሩ የዛሬው ፅዳት ቦታውን ከማፅዳት ባለፈ የጋራ አብሮነታችንን የምናሳይበት ነውም ብለዋል።

በፅዳት መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል የሰላም የአብሮነት፤ የተለያየ የሚገናኝበት፤ ከሁሉ በላይ ፈጣሪ የሚመሰገንበት በመሆኑ ሁላችንም ተቀራርበን አብሮነታችንን ከፍ እያደረግን አንድነታችንን እያፀናን ልናከብር ይገባል ብለዋል ፡፡

አቶ ከፍያለው አክለውም በዓሎቻችን የጋራ ሃብቶቻችን፣ የሁላችንም ኩራት፣ የአብሮነታችን መድመቂያና ዘመናትን በህብር የተሻገረው የአብሮ መኖራችን ሚስጥር ናቸውም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ እሴቶች ያላት ሀገር ስለሆነች ይህንን እሴት በአግባቡ ከተጠቀምን ለአንድነታችን ለእድገታችን ትልቅ አቅም ነው ያሉት አቶ ከፍያለው
እሬቻ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍትህ የሚሰጥ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት እሴቶቻችንን በአግባቡ ከተጠቀምን ለአብሮነታችን ትልቅ አቅም ነው ብለዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙባረክ ከማል በበኩላቸው እሬቻ የገዳ ስርዓት ካጎናፀፈን እሴቶች አንዱና ዋናው ነው። እሬቻ ሲከበር ጎላ ብሎ ከሚከወኑ ጉዳዮች አንዱና ዋናው ምስጋና ነው። ስለዚህ ይህ የምስጋና በዓል በክፍለ ከተማችን በመከበሩ ለእኛ ለቂርቆስ ነዋሪዎች ትልቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል

እሬቻ በከተማችን መከበር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ህዝባችን በኢኮኖሚው ዘንድ ትልቅ ጥቅም እያገኙ ነውና ይህ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

በፅዳት መርሐ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ፣የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙባረክ ከማልን ጨምሮ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባገዳዎችና ሀደሲንቄዎች፣ የተለያዩ የሀገር ሽማግሌዎች፤ ታዋቂ ሰዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

02 Oct, 19:09


https://www.facebook.com/100069185470323/posts/845774911072017/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

02 Oct, 19:08


https://www.facebook.com/100069185470323/posts/845775497738625/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

02 Oct, 19:08


https://www.facebook.com/100069185470323/posts/845776034405238/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

01 Oct, 09:02


መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከማልታ ሪፐብሊክ መንግስት እና ከቻድ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተፈረማቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን ለማጽደቅ የቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንኛውም የማልታ ከተማ እና ወደ እንጃሜና ከተማ በ3ኛና 4ኛ ትራፊክ መብት የመንገደኛ እና የጭነት የበረራ ምልልስ ለማድረግ፣ ተወካይ አየር መንገዶችን በሽርክና ለማሰራት፣ በ5ኛ ትራፊክ መብት ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በረራ ለማድረግ የሚያስችል እና አገራችን ከሁለቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት፣ ለወጪ ንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን በአባል አገራት መካከል ሕብረት በመፍጠር የኢንዱስትሪ ንብረትን ለመጠበቅ፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የግልጋሎት ሞዴሎች፣ የኢንዱስትሪ ንድፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርቶች ምንጭ አመልካች ምልክቶች ለመጠበቅ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ለመከላከል እና ለግብርና እና ሁሉንም የተመረቱ ወይም ተፈጥሯዊ ምርቶች የሚያካትት ነው፡፡ የኮንቬንሽኑ መጽደቅ ሀገራችን ለምታደርገው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድጋፍ የሚሆን ሲሆን ከአባል ሀገራቱ ለሚነሱ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን ለሚመለከቱ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ለመስጠት ያስችላል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውን ፕሮቶኮል ለማጽደቅ በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ፕሮቶኮሉ የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በአገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ምርቶች እና አገልግሎቶች ያላግባብ ለሌሎች ጥቅም እንዳይውሉ በቂ ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚፈጥር፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች እንዲኖሩና የሀብት ምንጭ እንዲሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በፕሮቶኮሉ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት ለመወጣት፤ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት እንዲሁም ከፓስፖርት የቆይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ ያሉ ጥቄዎችን መፍታት እንዲችል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

30 Sep, 20:12


https://www.facebook.com/100066583024934/videos/890280979705450/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

30 Sep, 16:11


ባለፉት ሁለት ቀናት በኮሪደር ልማት ስራችን የጀመርናቸውን የታክሲ እና ባስ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንጎች እንዲሁም የፒያሳ መልሶ ማልማት ስራዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረን ገምግመናል::

በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራችን ሰርተን ለህዝብ ክፍት ካደረግናቸው ስራዎች በተጨማሪ በከተማችን ያለውን የትራፊክ ስርዓት እንዲያሳልጡ ከጀመርናቸው 48 የመኪና ማቆሚያ እና የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች ውስጥ 11 የሚሆኑት ከ 2 እስከ 3 ወለል ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ እየተገነቡ መሆኑን መግለፃችን ይታወሳል::

በመሆኑም በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ ቸርችል መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ፣ ባሻ ወልዴ አካባቢ፣ ደጎል አደባባይ አካባቢ፣ ቦሌ ድልድይ አካባቢ፣ ቦሌ መንገድ ደንበል አካባቢ፣ ሳር ቤት፣ ቀበና አካባቢ፣ መገናኛ እና ሲኤምሲ አካባቢ ከመሬት በታች ከ 2 እስከ 3 ወለል ከመሬት በታች እና ከመሬት በላይ የሆኑ የታክሲና የባስ ተርሚናሎች የግንባታ ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን በታቀደው ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል::

በተጨማሪም በኮሪደር ልማት ስራችን የዋና መንገድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ጨምሮ ከተማችንን ለመኖር ምቹ እና አለምአቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ የጀመርናቸው ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶችንም የሚያካትት ሲሆን እነዚህ ስራዎች ለከተማችን ነዋሪዎችም ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ናቸው::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

30 Sep, 09:15


ቀን 20/01/2017
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአብሮነት ቀን ታስቦ ዋለ።
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አብሮነትን በማጠናከር የተሻለ ስኬት  በሚል መርህ መደበኛ ስራ ከመጀመሩ በፊት  ሁሉም ሰራተኛ በተገኘበት በየዘርፉ ውይይት በተደረገበት ወቅት ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን የአብሮነት ትርጉሙን በተመለከተ ማብራሪያ በሚሰጥበት ወቅት ሰራተኛው እራስ በራሱ በመተዋወቅ(በመግባባት) በአካባቢው እና በስራ ቦታው ያለውን የተሻለ አግባቦትና የስራ ባህል ለሌላው ልምዱን በማካፈል ጥሩ የሚባል የስራ አካባቢ በመፍጠር ተቋሙን ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል መድረክ መሆኑ በመጠቆም ውይይቱም በየሳምንቱ ሰኞ ከስራ ሰዓት በፊት የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።