ኒሳኡል መሻሪዕ @nisaulmesharie Channel on Telegram

ኒሳኡል መሻሪዕ

@nisaulmesharie


ሐያእ ለሴት ልጅ ዉበት ነዉ
#ሴትነት_የፆታ_መለያ_እንጂ_የድክመት_ምሽግ_እንዳልሆነ ከእውነተኛ ቂሷ ጋር የሚማሩበት #ልዩ_የሴቶች_የርቀት_መድረሳ 👇
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
you tube
https://youtube.com
https://youtube.com
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
ማንኛዉም አስተያየትና ጥያቄ ካላችሁ
https://t.me/maidaAhmed አናግሩን

ኒሳኡል መሻሪዕ (Amharic)

ኒሳኡል መሻሪዕ ላይ፣ የሴት ልጅ ምዕራፍ የሆነ በመተያየታችሁ፣ አድሂዳ፣ መለያ፣ እና መደናኛ ብቻ ደረጃ ነዉ! ወደ እውነተኛ ቂሷ ጋር በመላው #ልዩ_የሴቶች_ርቀት እና መድረስ ለመስማት ያስችላል። እባኮትንም የእናቱ ምሽግ በዓለም ነኝ። እናውቃለን ከአብቱ የተለያዩ ሊከባካ፣ የደጋ፣ እና ምሽጌ ነናል። እናገናናናለን! የሴት እና እናት መሳሪያዎችን በተመለከታችሁ አካባቢ ለመለዋዋጅ፣ መስራት እና መድረስ ለማፍጠር የጠቃሚ ነዉ። የሴት ልጅ ዉበት ነዉ፣ በእናቱ እና አብቱ መለያዎች የማዝን ነዉ። ለቅርብ ፈቃድን ለማነፃ።

ኒሳኡል መሻሪዕ

09 Jan, 10:32


ነገ ማለትም ጥር 1
ኸሚስ ምሽት 02:00 ላይ በቲክቶክ እና በቴሌግራም ላይቭ ስለ ነቢያችን የኢስራእ እና ሚዕራጅ ተዐምር የሚናገረውን
"ሙጂቡል ሙህታጅ ፊመዕሪፈቲል ኢስራኢ ወልሚዕራጅ" የተሰኘውን ኪታብ መቅራት እንጀምራለን።
በመሆኑም ይሄን ኪታብ ይዛቹህ እንድትከታተሉ እንጋብዛቹሀለን።
ኪታቡ የሌላቹህም ፒዲኤፉን ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ታገኙታላቹህ።

👇👇👇👇👇👇👇
Tiktok.com/shamilunkamil
Telegram.me//shamilunkamil

ኒሳኡል መሻሪዕ

15 Sep, 09:22


አንሷሮች የአሏህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መዲና መምጣታቸውን አስመልክተው አክበርዋል፡ ዛሬ ላይ ደግሞ ዓለም ላይ ያሉት ኢስላሚዊ ህዝቦች ወደዚች አለም መምጣታቸውን አስመልክተው እያከበሩ ይገኛሉ።

የነቢዩ መውሊድ የተባረከ እንዲሆንላቸው እየተመኘን እንኳን ደስ አላቹህ እንላለን ፡ አመት እሰከ አመት ሰላም ሁኑ።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil

ኒሳኡል መሻሪዕ

21 Aug, 14:26


❝አንድ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አሏህ እሱን በማገዝ ላይ ነው❞

- እርስ በርስ ተረዳዱ
- እርስ በርስ ተዋደዱ
- በመልካም ነገር ተጋገዙ

ሸይኽ ጂይል ሷዲቅበትርጉም

👇👇👇👇👇👇
🔸 @shamilunkamil 🔸

ኒሳኡል መሻሪዕ

20 Aug, 15:22


የተሰበረ ልቦችን መጠገን
ከደጋጎች ባህሪ ውስጥ ነው

ሸይኽ ጂይል ሷዲቅ ✍️ በትርጉም
👇👇👇👇👇👇
🔸@shamilunkamil 🔸

ኒሳኡል መሻሪዕ

29 May, 06:41


የተበደለ ሰው ዱዓእ

አንድ ንጉስ ቤተ መንግስት እንዲሰራለት አዘዘ,
ተሰርቶ ሲያበቃ እና ከለታት አንድ ቀን ሲወጣ አንድ ቤት አየ , ከዛም "የማን ነው ይሄ ቤት?" ሲል ጠየቀ, "ከቤተ መንግስትህ ጎን የምትኖር የአንዲት ሽማግሌ ሴትዮ ቤት ነው" አሉት, እሱም "አፍርሱት ምክኒያቱም ምቾት አይሰጠኝም" ብሎ አዘዛቸው, ከዛም አፈረሱት, ሴትዮዋም እዝን ብላ ከፈረሰው ቤቷ ላይ ቁጭ አለች, ንጉሱ በሷ በኩል ሲያልፍ "ምንድን ነው ምጠበቂ?" ብሎ ሲጠይቃት, "የቤተ መንግስትህን መፍረስ ነው ምጠብቅ" ስትል መለሰችለት, እሱም አሹፎባት ከወታደሮቹ ጋር አለፈ, ከዛም እሷ እጇን አንስታ "ጌታየ አምላኬ ሆይ እኔ ደካም ነኝ አንተ ደግሞ የሀይል ባለቤት ነህ ተበቀልልኝ (የስራውን ስጥልኝ)" ብላ ዱዐ አደረገች, ከዛም ወዲያውኑ አሏህ በዚህ ቤተ መንግስት ላይ መቅፀፍትን አውርዶ አወደመው, ከግድግዳዎቹ አንዱ ላይም እነዚህን የግጥም ቤቶች አገኙ
أتهزأ بالدعاء وتزدريه وما يدريك ما صنع الدعاء
سهام الليل لا تخطئ ولكن لها أمد وللأمد انقضاء
وقد شاء الإله بما تراه فما للملك عندكم بقاء
በዱዐ ታሾፋለህን ዱዐ ምን እንሚሰራ መች አውቀህ
የሌሊት ቀስት እኮ አይስትም ነገር ግን ጊዜ አለው ጊዜው ደግሞ ማለቁ አይቀርም
በርግጥ ጌታ የምታየውን ሽቷል ንግስና እኮ እናንተ ጋር ለዘላለም አይቆይም

ወዳጆቼ አደራቹህን የተበደለ ሰው ዱዐ እንዳያገኛቹህ ምክኒያቱም ዱዐውን ዳመናዎች ናቸው ሚወስዱት።

ኒሳኡል መሻሪዕ

23 Jul, 13:58


🔸ሱራቀቱ ኢብኑ ጅዕሹም ቢን ማሊክ"
             |ክፍል አምስት|
በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ
:)
የኛ ነቢይ ﷺ እድሚያቸው ዓርባ በሞላ ጊዜ የሪሳላን ኃላፊነት ተረከቡ። እዛው ከተወለዱባትና እጅግ በሚወዷት አገር "መካ"ም  ለአስራ ሦስት አመት ያክል ወደ ኢስላም ተጣሩ። መካዊያን ግን በነቢዩም ﷺ ሆነ እሳቸውን በሚከተሉ ምዕመናን ላይ አይከፉ ከፉባቸው።

አሏህም፥ መካን ለቀው ወደ "የስሪብ" እንዲጓዙ አዘዘ።
ጉዟቸውን ሊያደናቅፍ የሚመጣን ነገር ሁሉ ጠባቂው ጌታቸው በረቂቅ ጥበቡና ተቀናቃኝ በሌለው ኃይሉ ያስወግድላቸው ነበር።

ሱራቃን ምን እንኳን መንገድ አዋቂነቱና ፈረሰኛነቱ እሳቸው ጋር ቢያደርሰውም፤ ጠባቂያቸው አሏህ ነውና
የፈረሱ እግሮች በመሬት እንዲዋጡ አድርጎና የሳቸውን ሩህሩህነት አሳይቶ ሊገድል የመጣውን ሰውዬ በሳቸው ማንነት ተማርኮ እጅ እንዲሰጥ አደረገላቸው።

የመካ ሙሽሪኮችም ቢሆኑ እሳቸውን ለመግደል ከመቋመጥ፣ ታጥቀውና ተሰናድተው ዳናቸውን በማነፍነፍ ከገቡበት ዋሻ በሩ ድረስ ቢደርሱም፤ ጀሊሉ በረቀቀው ጥበቡ "በሸረሪት ድር" እና "በእርግብ ዕንቁላል" ውዱን ወዳጁን ጠብቋል።
 
/አሏህ ሲጠብቅ/ 

ምን እንኳ የአሞራ ዱካን አነፍንፎ መንገድን የማወቅ መክሊትን ቢያዳብሩም፤ የራቀን አቅርቦ የሚያይ አማታሪ ዓይን ቢኖራቸውም፤ ዳሩ፥  አሏህ ሲጠብቅ

ከቤቶች ሁሉ በጣም ደካማ የተባለው "የሸረሪት ድር (ቤት)" ከሰማይ ጠቀስ የብረት ግንቦች በላይ ከለላ እንዲሆን ያደርጋል።  ገደሉን ሜዳውን በማቆራረጥ ያልደከመን ገላ እና ያልጨለመን ተስፋ "እርግብና ዕንቁላሏ" ተስፋ ቢስ እንድታደርጋቸው ያደርጋል።

እንዲህ አይነቱ  የጀሊል ጥበቃ ሳይለያቸው
ሰይዳችን ﷺ የስሪብ በሰላም ገቡ። ከዚያም
በክፉ ወረርሽኟ፣ በአሩራማ ሙቀቷና በበረሃማነቷ የማትመቸውን "የስሪብን" ከመጠሪያ ስያሜዋ ጀምረው፥ ገፅታዋንም አየር ንብረቷንም ቀየሩላት። "መዲና" ሲሉ ሰየሟት፤ በሳቸው በርታለችናም "አብሪይቷ" (ሙነወራ) የሚል ማዕረግም ታከለላት።

ከዚያም ትልቁ ሰው ﷺ እልፍ አእላፍ ተከታዬችን አሰልፈው  እዬወደዷት የለቀቋትን፤ ሁሌም የምትናፍቃቸውን አገር "መከቱል ሙከረማህን" ፈትሕ አድርገው በድል ገቡ።

የዚህን ጊዜ ነበር "ሱራቀቱ ቢን ማሊክ" በድጋሚ ነቢያችንን ﷺ በአካል የማዬቱን ዕድል ያገኘው። ሰይዳችን ሱራቃን ገና ከማዬታቸው አስታውሰው አወቁት። እርሱም ውድ እጃቸው ላይ እጁን በማሳረፍ እስልምናውን ይፋ አጸደቀ።
   
አሁን ላይ ሱራቃ እንደ ነቢያችን ﷺ የሚወደው፤ ከሳቸው የሚያወዳድረው ሆነ በሳቸው የሚለውጠው አንዳችም ነገር የለም።

ለመቶ ግመሎች ብሎ እሳቸውን ሊገድል የወጣበትን ቅፅበት ሲያስብ ልቡ በኃፍረት ይደማል፤ በፀፀት ይዋጣል። 
    
"አሁን ላይ ለሱራቃ፥ መቶ ግመሎች ይቅርና በዱንያ ያሉ ግመሎችና ነዋያቶች ሁሉ ቢሰበሰቡለትም
ከሙሐመድ ﷺ ከአንዲቷ የፀጉር ዘለላ ወይም ከጥፍራቸው ቅንጣት ቁራጭ ጋር ፈፅሞ አይነፃፀሩም።

ሙሐመድን ﷺ ጥቂት አወቃቸው፤ እጅግ በጣም ወደዳቸው፤ አምኖባቸውም ተከታያቸው ሆነ።


"የኪስራ የእጅ አምባሮች" ጉዳይስ ምን ላይ ደረሰ


በእርግጥ የኪስራ አምባሮች ለአሁኑ ሱራቃ ምንሙም አይደሉም። ምክኒያቱም የርሱ ሃብቱም ወረቱም ቀኑም ሌቱም በጠቅላላው ሃያቱም በሙሐመዲይነት ተወርሷልና።

ታዲያ በታማኙ ነቢይ ﷺ ቃል የተገባለት የንጉሱ አምባሮች ጉዳይስ ፍፃሜው እንዴት ነበር???

ይቀጥላል•••

ኒሳኡል መሻሪዕ

23 Jul, 06:57


"ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም ቢን ማሊክ"
   |ክፍል አራት|

በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

ሱራቀቱ ኢብኑ ማሊክ፥ ነብዩን ﷺ ገድሎ አሊያ ዠደግሞ አስሮ አቡ ሱፍያን፤ አበል ሐከም (አቡ ጀህል)፤ ዑትባ ቢን ረቢዓ፤ ወሊድ ቢን አል ሙጊራ ለመሳሰሉት የመካ ሹማምንቶች ለማስረከብ እንዳልወጣ፥ በዓይኑ ያን መሰሉን ሙዕጅዛ ሲያይና ለጆሮው እንግዳ ነገሮችን ሲሰማ "ልቡ" በሙሐመድ ተሳበች፤ ተማረከች።

አሁን ላይ ሱራቃ በታማኙ ነቢይ ﷺ ለማመን የሚከብድ ቃል ተገብቶለታል፤ ፈረሱም ገርቶለት ወደ መጣበት እዬተመለሰ ነው። ሱራቃ እንዲህ ይላል፥

"ሙሐመድን እና ጓደኛቸውን ይዤ ለማስረከብ እጅጉን ጓጉቼ የወጣሁ ብሆንም፤ አሁን እነርሱን አንዳች ክፉ ነገር እንዳይነካቸው በመመኘት እየተመለስኩ ነው።"

መካ ደረሰ፤
የመካ ሹማምንት የሱራቃ ባዶ እጁን መመለስ አስከፍቷቸዋል።

በመለኮታዊ ክብከባ የሚጠበቁት ሙሐመድ ﷺ  የያዙት ታላቅ ጉዳይ አንዳች አስቋሚ ኀይል እንደሌለው የተገነዘበው ሱራቃ፣ እርሱ እጅ እንደሰጠው ሁሉ እነርሱም እጅ ይሰጡ እንደሁ በማለት ለአበል ሐከም (አቡ ጀህል)ና መሰሎቹ የምትከተለውን የግጥም ስንኝ አነበነበ

أَبَا حَكَمٍ وَاللَّهِ لَوْ كُنْتَ شَاهِدًا
لأَمْرِ جَوَادِيَ إِذْ تَسُوخُ قَوَائِمُهُ
عَلِمْتَ وَلَمْ تَشْكُكْ بِأَنَّ مُحَمَّدًا
رَسُولٌ بِبُرْهَانٍ فَمَنْ ذَا يُقَاوِمُهُ
عَلَيْكَ بِكَفِّ الْقَوْمِ عَنْهُ فَإِنَّنِي
أَرَى أَمْرُهُ يَوْمًا سَتَبْدُو مَعَالِمُهُ
بِأَمْرٍ يَوَدُّ النَّاسُ فِيهِ بِأَسْرِهِمْ
بِأَنَّ جَمِيعَ النَّاسِ طُرًّا تسَالِمُهُ

አባ ሐከም ብታይ ያየችውን ነፍሴ
መሬት ስር ሲሰምጡ እግሮቹ ፈረሴ
ያላንዳች ጥርጥር ባመንክ የርሱን መንገድ
ያሏህ መልክተኛ መሆኑን ሙሐመድ
ህዝቦችህን አስቁም! ያንን ሰው ከማገድ
ባለም ሲሆን ይፋ ታዬኝ የርሱ መንገድ
ታያለህ አይቀርም አንድ ቀን ይመጣል
ሁሉም በጠቅላላ ለርሱ እጅ ይሰጣል 
 

የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል

ኒሳኡል መሻሪዕ

22 Jul, 05:12


ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም |ክፍል ሦስት|

    በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም ( ኢብን ማሊክ)፣ እንደ ምንም ወደ ነቢያችን ﷺ ቀረበ። መሄድ ያቃተው ፈረሱን በግድ  እንዲገሰግስ ቢያስነሳውም የፈረሱ የፊት እግሮቹ ጉልበቶቹ ድረስ በመሬት ተዋጡ። ሱራቃም እዬሆነ ያለው ጉድ ተስፋ አስቆረጠው።

"ሙሐመድ" ተራ ሰው አለመሆናቸውንና የያዙት ጉዳይም የመለኮታዊ እንክብካቤና ጥበቃ እንዳለበት ተረዳ።

የሱራቃ ፍላጎትም ከመቶ ቀያይ ግመሎች ነፍስን ወደ ማዳን ተለወጠ፤ ሁሉንም ትቶ በሰላም ወደ ቤተሰቦቹ መመለስን ብቻ ፈለገ። እንዲህ ሲልም ትልቁን ሰው መማፀን ጀመረ

"እባካችሁን! ከገባሁበት ጉድ ብቻ አውጡኝ!  ምንም ጉዳት አላደርስባችሁም፤ የምትጠሉት የሆነን ነገርም አላደርግም"

የኛ ነቢይም ﷺ ዱአ አድርገው የፈረሱ እግር ከመሬት እንዲወጣና እንዲረጋጋ አደረጉ። ወደ አቡበክር በመዞርም "ምን ፈልጎ እንደመጣ ጠይቀው" አሉ። ተጠይቆ የሚከተለውን መለሰ፥

"ህዝቦችህ አንተን ገድሎ ወይም አስሮ ላመጣላቸው ሰው መቶ ግመሎችን እንደሚሸልሙት አውጀዋል። ታዲያ እኔም መንገድ አነፍንፎ የማወቅ ክሂሌን ተማምኜ የሽልማቱ ባለቤት ለመሆን የወጣሁ ነኝ።"

የኛ ፈንታም ﷺ "ሚስጥራችን ጠብቅልን" አሉት።
የሙሐመድን ታላቅነት፤ በአሏህ የሚጠበቁ ልዩ ሰው መሆናቸውን የተረዳው ሱራቃ፣ ይህ የያዙት መንገድ ወደፊት እጅግ እንደሚሰፋና አለምን እንደሚያዳርስ ታውቆታል።
  
ከዚያም ሱራቃ "የደህንነት ማረጋገጫ ውል" እንዲፅፉለት ጠየቀ፤ (ለወደፊት ካገኛቸው ውለታ መዋሉን የሚያረጋግጥለትንና ለደህንነት ዋስትና የሚሆነውን ውል)
  
የኛ ነቢይም ﷺ  የጠየቀው ይሆንለት ዘንድ አቡበክርን አዘዙ። አብሯቸው የነበረው የአቡበክር አገልጋይ "ዓሚር ቢን ፉሃይራም" ውሉን ፃፈለት።

   ሱራቃ ወደ መጣበት ለመመለስ ሲሰናዳ
የኛ ነቢይ ﷺ   "ሱራቃ ሆይ!" አሉትና፦
 
ነብይነታቸውን የሚያመላክት እና እጅጉን የሚደንቅ የሆነ ንግግር ከሰይዳችን አንደበት ወጣ

"ሱራቃ ሆይ! የኪስራውን ንጉስ የእጅ አምባሮች ብትለብስ ምን ይመስልሃል?!"

(ሚስጥራችን ከደበቅክልን በምትኩ የኪስራው ንጉስ እጁ ላይ ያጠለቃቸውን አምባሮች ታገኛለህ)

"ሱራቃ" እጅጉን በመገረምና በመደንገጥ መሃል ሆኖ "ኪስራ ቢን ሁርሙዝን" ማለታችሁ ነው? አላቸው።
የኛ ነቢይም "አዎን! የኪስራውን ንጉስ" ሲሉ አረጋገጡለት።

በጊዜው  የሩሙ "ኪስራ ቢን ሁርሙዝ" ንግስናው ላይ ነበር። ሱራቃ ዓይኑ የሚያዬው ሆነ ጆሮው የሚሰማው ሁሉ ነገር ከተለምዶው ውጭ ሆኖበታል።

"ሙሐመድ ﷺ" ያሉትን ነገር "ውሸት ነው" እንዳይል ባይኑ በብረቱ ተአምራትን አይቷል። "እውነት ነው" እንዳይል  "ንጉስ ኪስራ" ከእጁ ያጠለቃቸው አምባሮቹ ቀርቶ የግዛቱ ጫፍ እንኳ በምንም የማይደፈሩ የኀያል ኀያል ነው። 

የሱራቃ ልብ በሙሐመድ ﷺ ተጠለፈ፤ ወደዳቸው፤ ከዚያም ምንም ጉዳት እንዳይደርስባቸው እየተመኘ ወደ መጣበት ተመለሰ።

ይቀጥላል....ሼርርር

ኒሳኡል መሻሪዕ

20 Jul, 05:21


ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም  |ክፍል አንድ|

✍️በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

የኛ ነብይ ﷺ ከወዳጃቸው አቡበክር ጋር በመሆን መካን ለቀው ወደ መዲና ባቀኑ ጊዜ
ሙሽሪኮች የሚከተለውን አዋጅ አወጁ፦

"ሙሐመድንና ጓደኛውን ገድሎም ይሁን አስሮ ላመጣ በየ አንዳንዱ (መቶ ቀያይ ግመሎችን) እንሸልመዋለን!"

በወቅቱ የዐረብ ውድ ንብረት ቀያይ ግመሎች ሲሆኑ፣ የሽልማቱ ባለቤት ለመሆን ሲሉ ሙሐመድን ለመያዝ የወጡት ብዙዎች ነበሩ። ከነርሱም ውስጥ የአንደኛውና የስመ ገናናውን ግለሰብ ታሪክ በጨረፍታ ላወሳ ወደድኩ፤

ይህ ሰው  ብቁ ፈረሰኛ፤ አልሞ ማይስት ቀስተኛና ዳገት ሜዳውን፣ መግቢያ መውጫውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ዱካ አነፍናፊም ነበር።

ይህ ሰው፣ ሙሐመድን ﷺ በወጡበት ወጥቶና በገቡበት ገብቶ ሙሐመድን በመያዝ የመቶ ቀያይ ግመሎች ባለድል ለመሆን እጅጉን ቋምጧል። 

የርሱን መውጣት አውቀው ሌሎች እንዳይወጡና መቶ ግመሎች ላይ እንዳይቀናቀኑት በመስጋት በድቅድቅ ሌሊት ፈረሱን ሙሉ ትጥቅን አስታጥቆ አሰናዳው፤ እርሱም ፍላፃዎቹን ሰብስቦና ደጋኑን አነግቶ ለጉዞው ተበጃጀ፤ እንዳቀደውም ጉዞውን ለብቻው ተያያዘው፦

ታዲያ በሃሳቡ ድቅን የሚለው

መቶ ቀያይ ግመሎችን ሲሸለም፤ ህዝቡ በእልልታ አቀባበል ሲያደርግለት፤ የወደፊት ህይወቱን በተድላ ሲኖር_

ይቀጥላል...

ኒሳኡል መሻሪዕ

20 Jul, 05:21


ሱራቀቱ ኢብኑ ጁዕሹም |ክፍል ሁለት|

✍️ በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

(የነቢያችን  መካን ጥሎ መውጣት የአሏህን ትዕዛዝ መሰረት ያደረገ እንጂ፣ የኢስላምን ጥሪ በማድረስ ላይ ፈርተውና ሸሽተው ወይም አንዳች ነገር እንዳልሆን ሲሉ ለነፍሳቸው ሰግተውም አልነበረም።)

ለመካ ሹማምንት ሽንፈትንና ፍርሃትን ያወረሰው የነቢያችን ጉዞ፣ እንዲሰናከል ሲባል ብዙ እተጣረ ነው፤
ሆኖም አሏህን ብቻ የሚፈሩትና በአሏህ ብቻ የሚመኩት ነቢይ ከወዳጃቸው ጋር ጉዞው ላይ ናቸው

ዱካን አነፍንፎ የሚያውቀው "ሱራቃም" መቶ ቀያይ ግመሎችን የብቻው ሊያደርግ ፈረሱን ኮልኩሎ ወጥቷል፤

ሱራቃ እንዲህ ይላል፦

"ተከትያቸው ወጣሁ፤ ከሩቅ ቢሆንም እንኳ ጥላቸውን ግን ማዬት ቻልኩ። አገኘኋቸው ብዬም ተደሳሁ። ነገር ግን ምን እንዳገኘው አላውቀውም ፈፅሞ ለግሞ የማያውቀው ፈረሴ እንግዳ አመል አመጣ፤ መሀል መንገድ ላይ እግሮቹ መውተሽተሽና መተሳሰር ያዙ፤

ከዚያም ሱራቃ በጃሂሊያ ጊዜ እንደሚያደርጉት ዕጣ የማውጣት ስርአትን ፈፀመ።

የዕጣ ስርዐቱ እንዲህ ይከናወን ነበር፦  "አይሆንም"  እና "ይሆናል" ተብሎ ከተፃፈባቸው ሁለት ፍላፃዎች አንዱን ነቅሰው ይመዛሉ፤ የወጣው ፍላፃ  "ይሆናል" የሚለው ከሆነ፣ በለስ ይቀናናል ብለው ስለሚያምኑ ጉዳዩን ይቀጥላሉ፤ "አይሆንም" የሚለው ከወጣ ደግሞ ድል አይገጥመንም ስለሚሉ ጉዳዩንም ይተውታል። 

ሱራቃም የፈረሱን እንግዳ ባህሪ ማምጣት ሲያይ፣  ጉዞዬ የተሳሳተ ይሆን እንዴ! በማለት ይኸን የጃሂሊያ ስርዐት ፈፀመ።  ዳሩ፤ የወጣው ፍላፃ  "አይሆንም" ተብሎ የተፃፈበቱ ነው። የሱራቃ አይን ላይ የተደቀኑት መቶ ቀያይ ግመሎች ግን እስከዛሬ ድረስ ያምንበት የነበረውን ልማዳዊ ግብርም አስካዱት። ከዚያም እንዳዲስ ፈረሱን ኮለኮለና እንዳዲስ ወደ ፊት መገስገስ ያዘ።

"የሙሐመድ ድምፅ እስኪሰማኝ ድረስ ይበልጥ ቀረብኳቸው፤ እሳቸው ወደ ምንም ሳይዞሩ ወደ ፊት ብቻ ሲሄዱ አብሯቸው ያለው ሰው ግን (አቡበክር) መዟዟርን ያበዙ ነበር።
 
ድንገት ግን የፈረሴ ኮቴዎቹ መሬት ውስጥ ተቸከሉ፤
እግሮቹን ነቅሎ ለማውጣት የሚያደርገው ጥረቱ በአቧራ እንድሸፈን አደረገኝ።

እዬሆነ ያለው ነገር አስፈርቶኝ አልመለስ ነገር ቀያይ ግመሎች ፊቴ ላይ ናቸው። ይሁን ብዬ ወደ ፊት እንዳልቀጥል ጉዳዩ ከተለምዶ ውጭ ሆኖብኛል።

ከዚያም በድጋሜ ዕጣ የማውጣቱን ስርዐት ፈፀመ።
ሆኖም ግን የወጣው ፍላፃ "አይሆንም" ተብሎ የተፃፈበት ነው

ይቀጥላል...

ኒሳኡል መሻሪዕ

19 Jul, 03:57


ከዶክቶር ሸይኽ ጀሚል ሀሊም አል ሁሰይኒይ የተላለፈ መልዕክት (አሏህ ይጠብቃቸው)

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ አሏህ ይሁን አሏህ በሰይዳችን ሙሀመድ እና ንፁህ ፣ ደጋግ በሆኑ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ሶላትን ያውርድ ፦ በመቀጠል ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ በተከበረው ፣ በተላቀው እና በተባረከው የሂጅራ አመት መጀመሪያ ላይ እኔንም እናንተንም ወደ አሏህ ተውበት እንድናደርግ አስታውሳለው ፤ ሰዎችን ተውበት እንዲያደርጉ እና ወደ አሏህ ፣አሏህን ወደ መታዘዝ ፣ አሏህን ወደ መገዛት እና አሏህን ወደ ማውሳት ፣ ወደ ዲናዊ ዕውቀት እና ዲናዊ ዕውቀትን ተግባር ላይ ወደ ማዋል እንዲመጡ እንድትጠሯቸው አስታውሳቹሀለው።

ይህንን ጠቃሚ ጉዳይም አስታውሳቹሀለው ዲየሪቢይ "ሙጀረባቱ ሷሊሂን" ላይ የጠቀሱት ሲሆን ፦ ከሙሀረም የመጀመሪያው ቀን ላይ አየቱል ኩርሲይ ሶስት መቶ ስልሳ ጊዜ (360) ይቀራል ፡ መጀመሪያቸው ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል) ማለትም ሁሉንም እያንዳንዱን ሲቀራ መጀመሪያ ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል)።  እናም (ዲየሪቢይ) እንዲህ ይላሉ ፡ (ይህንን የቀራ) በዛ አመት ከተረገመው ሸይጣን መጠበቂያ ምሽግ ይሆንለታል። እንደዚሁም በውስጡ አሏህ እንጂ ሌላ የማያውቀው ብዙ ጠቃሚ ነገሮች አሉት። ከዛም (አየቱል ኩርስይን ቀርቶ) ሲያበቃ እንዲህ ይላል፡

"اللهمَ يا مُحَوِّلَ الْأَحْوَالْ حَوِّل حَالِي إِلَى أَحْسَنِ الأحوال بِحَوْلِكَ وَقُوَتِكَ يَا عَزيزُ يَا مُتَعَالْ، وَصَلَى الله على سيّدّنا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم".

❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯

ኒሳኡል መሻሪዕ

19 Jul, 03:57


መልካም የሂጅራ ዓመት 1445
አመቱን ሙሉ ሰላም ሁኑ
Happy New Hijri Year

❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯

ኒሳኡል መሻሪዕ

13 Jul, 04:37


[ተበሳሪዎች]

ነቢያችን ﷺ ፣አቡበክር፣ዑመር እና ዑስማን ሆነው በዘለቁበት ጊዜ ኡሁድ (ተራራ) ተርገፈገፈ፤ መልዕክተኛውም እንዲህ አሉ፦
«ኡሁድ ሆይ! (ባለህበት) ፅና! ላይህ ላይ ያሉት፥ ነቢይ ሲዲቅ እና ሰምዐቶች ናቸውና" ኢማሙ አሕመድ ዘገበውታል ።

**********

ኒሳኡል መሻሪዕ

08 Jul, 12:22


❝ እርሱን የሚመስለው ምንም ነገር የለም!እርሱም ሰሚና ተመልካች ነው❞
አል -ሹራ 11

ኒሳኡል መሻሪዕ

03 Jul, 13:44


🌹ወደ አሏህ ተጣሪ ሁን🌹

ከቀናቶች በኋላ የሂጅራ 1444ኛው ዓመት ያበቃል እናም አዲሱ የሂጅራ 1445ኛው ዓመት ይጀምራል።

አዲሱ አመት ግዴታ የሆኑ ነገሮችን በመፈፀም ፣ ክልክል የሆኑ ነገሮችን በመከልከል እና ሱና የሆኑ ነገሮችን በማብዛት የመልካም እና የበረከት ዓመት እንዲሆን ፣ ችግርን ፣ የኑሮ ውድነትን አሏህ እንዲያሳልን እንመኛለን።

ይሄውላችሁ ደግሞ የጀመዒየቱል መሻሪዕ አልኸይሪየቱል ኢስላሚያ በሂጅራ አቋጣጠር የ1445ኛው ዓመት የተከበረው ነቢያዊ ሂጅራ መታሰቢያ መፈክር።

❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯

ኒሳኡል መሻሪዕ

30 Jun, 17:23


👆👆#code 008 ገብታቹህ Like አድርጉልን
ባረከሏሁ ቢኩም

ኒሳኡል መሻሪዕ

30 Jun, 17:22


ወዳዳሪ ቡድን   ዙመር ስድስት

#Code 008
ወድ እና የተከበራችሁ የዙመር ኢስላሚክ ሚዲያ አዘጋጆች እና ታዳሚወች እንዴት ናችሁልን
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

እንኳን ለ 1444ተኛው የዒድ አልአድሀ በዐል በሰላም አደረሳችሁ በማለት የዙመር ስድስት (6) አባላት መልካም መኞታችን ለመግለፅ እንወዳለን🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸


عيد سعيد

🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

ኒሳኡል መሻሪዕ

23 Jun, 07:05


🕋 የሐጅ ማእዘናቶች 🕋

◈ ኢህራም ማድረግ
◈ዐረፋ ላይ መቆም
◈ጠዋፍ ማድረግ
◈በሶፋ እና መርዋህ መካከል መመላለስ
◈ፀጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር
◈አብዛኛው ማእዘናት ላይቅድመ ተከተልን መጠበቅ

👇👇👇👇👇👇👇
{t.me/shamilunkamil}
{t.me/shamilunkamil}
{t.me/shamilunkamil}

ኒሳኡል መሻሪዕ

22 Jun, 17:06


🌹የለይለቱል ጁሙዐህ ግብዣ🌹

🎙ሰይዲ🎙

🌸ምርጥ ነሺዳ🌸

🎤በአንዋር አል ቡርዳ

❮te.me/shamilunkamil❯

ኒሳኡል መሻሪዕ

18 Jun, 15:47


🌙ከዙል ሒጃ መጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት መፆም ጥብቅ ሱና ሲሆን የተቀሩት በጎና መልካም ስራዎች ደግሞ ምንዳቸው ከሌላው ጊዜ እጅጉን የበዛ ነው።
በነዚህ ቀኖች የሚደረጉ ዚክር፣ ሶደቃ (ምፅዋት)፣ ፆም እና መሰል ስራዎች ሁሉ አሏህ የሰሪዎችን ምንዳ እጥፍ ያደርገዋል።
**********
አስ - ሱናህ TV ''ሚዛናዊ መርህ ''

❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯
❮❮❮t.me/shamilunkamil❯❯❯

ኒሳኡል መሻሪዕ

16 Jun, 04:49


📿የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ:
❝ጅብሪል ወደኔ መጣና እንዲህ አለኝ፡ ሙሐመድ ሆይ! ባልደረቦችህን እዘዝ! ተልቢያ ሲያደርጉ{ጥሪን ሲቀበሉ} ድምፃቸውን ከፍ እንዲያደርጉ፣ምክንያቱም ይሄ የሐጅ ምልክት ነውና!❞
◈ሐጁን◈መብሩር◈
📿ጁሙዓ ሙባረክ