ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ @dessiefana Channel on Telegram

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

@dessiefana


Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0 (Amharic)

ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0 ለተከታታይ ከአድራሻ አለም በመደብ እና በባህርዳር ሃገር ከፍተኛ እንዲከበር ያስደሰቱ የሃገር ወርቃዊ ተማሪ ዋና ሽደን አሉ፡፡ ተከተሉት ከሩቅ በለስ ዕውቀት እየተሰቀሉ ያለባችሁ ከሬዶ በሮች በቀጣይ ትክክለኛ የሃብተኛ ምርጥ ጥቅም የሃገር ምርጥ ኡራንክ አገልግሎት ናቸው፡፡nnፊት እና የተጊዘረለትና በጣም ባተኮርደትና አንድ እንግሊዝን የመንግስት አስተዳደር ቅኝት የሆነች የሃምሌ፣ ሴለፕ አንዯለይ፡፡ በዚህ ቦርና ዝግጅት የልደቱን እያቀየረ ዜና እንዳልሆነ በ፩ ሰአት ተከሰት፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

18 Jan, 14:21


በደሴ ከተማ የከተራ በዓል

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

18 Jan, 05:26


የጥምቀት በዓል ማህበረሰቡ አንድነቱን፣ ፍቅሩን፣ መተሳሰቡን እና መረዳዳቱን የሚያሳይበት አንዱ ገፅታ ነው ተባለ።

ደሴ- ጥር 10/2017/ደሴ ፋና/ይህ የተነገረው በደሴ ከተማ ባህረ ጥምቀት የሚከወንበት የሆጤ ሜዳን የማፅዳት ስራ በተሰራበት ወቅት ነው።

በወቅቱ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እንደተናገሩት ደሴ ላይ ያሉ ሀይማኖቶች በአብሮነትና በመረዳዳት መልካም እሴትን የገነቡት ቀደም ባሉ ዘመናት በመሆኑ ዛሬም ይህንን መልካም እሴት በማስቀጠል ባህረ ጥምቀቱ የሚከበርበትን ቦታ የፅዳት ችግር እንዳይኖርበት የማፅዳት ስራን ሰርተዋል።

የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓል በመሆኑ ከፅዳቱ ባሻገር ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከወን ወጣቱ ተደረጅቶ አካባቢውን ለመጠበቅና ሰላሙን ለማስከበር ቅድመ ዝግጅት አድርጓል ያሉት አቶ ሳሙኤል ከተማዋ እስከዛሬ ድረስ ሰላሟን አስጠብቃ የቆየችው በማህበረሰቡ ጥንካሬና ሰላም ወዳድነት በመሆኑ አሁንም በዓሉ በሰላም እንዲከበር የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የተለያዬ እምነት ተካታዮች እንደገለፁት ደሴ የተለያዩ ሀይማኖቶች የሚኖሩባት የአብሮነትና የሰላም ከተማ በመሆኗ አንዱ ለአንዱ ደጋፊ እና መከታ የሚሆኑባት ናት ብለዋል።

መጪውን የትምቀት በዓል የሚከበርበት ሆጤ ሜዳ ፅዱ እንዲሆን ከሰራነው ስራ በተጨማሪ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶቻችን በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብሩ ከጎናቸው እንሆናለንም ሲሉ ተናግረዋል።

ስንታየሁ አራጌ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

11 Jan, 15:54


230 ኪሎ ቮልት ያለው የመብራት ማከፋፈያ ጣቢያ በደሴ ከተማ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ደሴ- ጥር 3/2017/ደሴ ፋና/በፌደራል መንግስት ወጭ ከ465 ሚሊየን ብር በላይ በደሴ ከተማ አስተዳደር 230/33/15 ኪሎ ቮልት የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህ ትልቅ ፕሮጀክት የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ምቹ ሁኔታ እና የመንገድ መሰረተ ልማትን በማሟላት እየተሰራ መሆኑን አቶ በድሩ አህመድ የሰሜን ምስራቅ ሪጅን አንድ ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦኘሬሽንና ጥገና ዳይሬክተር  ገልፀዋል።

ለዚሁ የኤሌክትሪክ ሀይል ግብአት ሁለት  ትራንስፎርመሮች 230/33/15ኪ.ቮ 2*63/40/23MVA ዛሬ በማከፋፈያ ጣቢያው የደረሰ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ ለስራው ስኬት ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረጉ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል።

በደሴ ከተማ በ1970ዎቹ አካባቢ ጀምሮ ከ66 ኪሎ ቮልት ኔት ወርክ የነበር በመሆኑ እና ይህ ደግሞ ለከተማው እና አካባቢው እድገት ትልቅ ችግር የነበር ነው።

ይህ ማከፋፈያ ጣቢያ እንዲሰራ የከተማው ማህበረሰብና መንግስት የረጅም ጊዜ ጥያቄ ስለነበር የፌደራል መንግስት አቅዶ መስራቱ ለደሴ ከተማ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ከተሞች ጭምር ፋይዳው ከፋተኛ ነው ተብሏል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

11 Jan, 05:04


የከተማዋን የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ማሳደጉን የመርሳ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ደሴ- ጥር 3/2017/ደሴ ፋና/ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2016 እና በ2017 በጀት አመት በከተማዋ አዳዲስ የመኖሪያ መንደሮችን ጨምሮ ከ17 ኪሎ ሜትር በላይ የማስፋፊያና የማሻሻያ መስመር ተዘርግቶ ከ1 ሽ 700 በላይ አዲስ ደምበኞች አገልግሎት እያገኙ ነው።

በከተማዋ በአጠቃላይ ከ8 ሽ 500 በላይ የውሀ ቆጣሪ ስራ ላይ ይገኛልም ተብሏል።

በአራት ጉድጓዶች ውሀ በማምረት አገልግሎት እየሰጠ ያለው ተቋሙ ከአንድ አመት በፊት አጠቃላይ ምርቱ 27 ሊትር  በአንድ ሰኮንድ የነበረውን ፓምፕ በመቀየርና ማሻሻያዎችን በመጨመር  የማምረት አቅሙን 74 ሊትር በአንድ ሴኮንድ በማሳደግ በተቀመጠው ፈረቃ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ውሀ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ መርሳ አካባቢ ፕሮግራም ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተቋሙ ፕሮጀክት ቀርጾ ባገኘው 4 ሚሊዮን ብር በተለምዶ ስሙ አምስቱ ሄክታር ከተባለ የውሀ ማምረቻ ጉድጓድ የተነሳ 2.5 ኪሎ ሜትር መስመር በመዘርጋት የማምረት አቅሙን ከ2 ወደ 18 ሊትር በሴኮንድ ማሳደጉን በምሳሌነት ጠቅሷል።

አሁን ላይ በተሟላ እውቀትና ክህሎት እየተመራ የሚገኘው ተቋሙ በቂ ውሀ ለማምረት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እጥረት ያለበት ቢሆንም ለነዳጅ ግዥ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት  በፈረቃ አገልግሎት እየሰጠ አንዲቀጥል መገደዱን ተጠቃሚው ህብረተሰብ ማወቅ እንዳለበት ተገልፅዋው።

ወደፊት የከተማዋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከተሻሻለና በቂ ሀይል ሲለቀቅ የፈረቃ ማሻሻያ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

መርሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

10 Jan, 18:13


በመጭው ጥር 15 የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም የደቡብ ወሎ ዞን የተቀናጀ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የንቅናቄ መድረክ በደሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ደሴ- ጥር 2/2017/ደሴ ፋና/የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ ለዘመኑ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አንስተው 609 ሽህ ሰሪ ኃይል የተለየ ሲሆን ፤የተፋሰስ ልየታና ጥናት እንዲሁም የቀያሽ አርሶ አደር ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

በዞኑ ከ84 ሽህ ሄክታር በላይ ሽፋን ያላቸውን 1ሽህ 433 ተፋሰሶች ለመሥራት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ተጠናቋል ያሉት አቶ አህመድ በዚህ ዓመት ሥራው በተፋሰስ ኮሚቴ መመራት ይኖርበታል ብለዋል።

የዞኑ የንቅናቄ መድረክ በወረዳ፣ በቀበሌና በተፋሰስ ደረጃ ተመሳሳይ የንቅናቄ መድረክ በማካሄድ አርሶ አደሩ ጋር መግባባት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ከጥር 15 ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ30 ቀናት በዘመቻ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

           ስንታየሁ አራጌ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

10 Jan, 17:48


በድንገተኛ ፍተሻ የሺሻ እቃዎች መያዙን ፓሊስ አስታወቀ።

ደሴ- ጥር 2/2017/ደሴ ፋና/በደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ መምሪያ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ባደረገው ድንገተኛ ኦፕሬሽን ተግባር 40 የሺሻ እቃዎች መያዛቸውን የጣቢያ ሃላፊ ም/ኮማንደር መንግስቱ አሊ ገልፀዋል።

ሃላፊው አክለው ወጣቶች ባልባሌ ቦታ እንዲውሉ እና አደንዛዥ እፅ እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር በወንጀል ድርጊት እንዲሳተፉ የሚያደርግ ስለሆነ ይህንኑ ተግባር ለመግታት ይቻል ዘንድ ጣቢያው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም በማስጠቀም ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሠቦችም በደንብ ማስከበር እንዲቀጡ ተደረጓል ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡም እንዲህ አይነት መሠል ድርጊቶችን በመከላከል ሂደት ላይ እያሳየ ያለውን መተባበር እና መረጃ በመስጠት በኩል የሚያደረገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

10 Jan, 14:43


በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ስራዎች ዞናዊ የንቅናቄ መድረክና የዕውቅና መድረክ ተካሂዷል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

10 Jan, 13:19


በአማራ ክልል ፕሮጀክቶች በጥራት በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን ገለፁ።

ደሴ- ጥር 2/2017/ደሴ ፋና/ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በኮምቦልቻ ከተማ እየተሰራ ያለውን 7.5 ኪሎ ሜትር የማሳለጫ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አብዱ ሁሴን እንደገለፁት በክልሉ  በተለያዩ አካባቢዎች የልማት ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ያሉ ሲሆን የአስፋልት መንገዶችን ጨምሮ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከመስራት ባለፈ በጥራት በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የሚያመላክት ጉብኝት መሆኑንም ገልጸዋል።

በምልከታቸውም የመንገድ ስራውን ሂደታቸውን በመገምገምና አቅጣጫ በመስጠት ክፍተቶች እንዲሞሉ ከማድረግ ባለፈ የዘገዩትን ጭምር አፈጻጸማቸው እንዲሻሻል እየተደረገ መሆኑን ገልፀው በኮምቦልቻ ከተማ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም እንዲጠናቀቁ ክልሉ ተገቢውን እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

የክልሉ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጋሻው አወቀ በበኩላቸው በክልሉ 61 የአስፋልት መንገዶች መኖራቸውን ገልፀው 27 ፕሮጀክቶች ደግሞ ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።

ቀሪዎችንም በቅርቡ ሥራ ለማስጀመር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥረት ይሰራል ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም 12 አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር በጨረታ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመው በዘንድሮው በጀት ዓመትም 97 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እስካሁን 46 ኪሎ ሜትር መንገድ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በከተማው 7.5 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድአሚን የሱፍ እንደነዚህ አይነት ፕሮጀክቶች ለከተማዋ የተሻለ እድገትን የሚያመጡ በመሆናቸው የቁጥጥር ስራውን በመስራት እስኪጠናቀቅ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

         ሰብለ አክሊሉ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

05 Jan, 12:13


በደሴ ከተማ የታክሲና የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ አገልግሎት ትርፍ መጫን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ነዎሪዎች ገለጹ።

ደሴ- ታህሳስ 27/2017/ደሴ ፋና/እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በስራ መግቢያና መውጫ ሰአት እንዲሁም በበዓላት እና ቅዳሜና እሁድ ትርፍ መጫን የተለመደ ሆኗል።

የመንገድ ትራፊክ ደንብ መተላለፍ ቅጣቱ አሽከርካሪዎችን በበቂ ሁኔታ አስተማሪ አይደለም ያሉት ነዋሪዎቹ ለተሣፋሪዎችም ቅጣት ቢጀመር ሲሉ ጠይቀዋል።

የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር አደፍርስ ታፈሰ በበኩላቸው የደንብ ማስከበር ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ነዋሪዎች ባነሷቸው ጊዜያት ያለውን ክፍተት ለመከታተልም በተጠናከረ ስምሪት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች ትርፍ በመጫን አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር መነሻ ሆኖ በጫኑት ሰው ልክ መቶ ብር ተባዝቶ በድምሩ ያለውን ያህል ይቀጣሉ ብለዋል።

እስከ አሁን የተሣፋሪዎች ቅጣት ደንብ የለም ያሉት ኢንስፔክተር አደፍርስ እግረኞች በጉዞ ላይ ደንብን ከጣሡ ግን የሚቀጡበት ህግ መኖሩን ገልጸዋል።

እግረኞች በመንገድ ላይ ህገወጥ ድርጊት ከፈጸሙ መቶ ብር ይቀጣሉም ሲሉ ተናግረዋል።

          አለባቸው አባተ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

04 Jan, 12:30


የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ500 ሚሊየን ብር ወጪ በኮምቦልቻ ከተማ ያስገነባው ዘመናዊ የቢሮ መገልገያ ሕንጻ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ደሴ- ታህሳስ 26/2017/ደሴ ፋና/በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ÷ ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ልክ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡

ለውጡ ሲጀመር በዓመት ከ200 ቢሊየን ብር በታች ገቢ ይሰበስብ የነበረው በዘንድሮው በጀት ዓመት ያለፉት አምስት ወራ ብቻ ከ380 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አመላክተዋል።

አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመንና ገቢን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የጉምሩክ ቅርንጫፎችን በማጠናከርና በመደገፍ ለኢትዮጵያ ሁለተናዊ እድገት ሚናቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን ሁለተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ኮሚሽኑ የድርሻውን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ አሰራሩን ለማዘመን በቴክኖሎጂ የተደራጀ፣ ከወረቀት ንክኪ ነፃና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀዋል።

ይህም ኮንትሮባንድና ሌሎችንም ሕገ ወጥ አሰራሮችን በመከላከል የወጭና ገቢ እቃዎች ጤናማ የንግድ ስርዓት እንዲይዙ እንደሚያግዝ ነው ያስረዱት፡፡

በአለባቸው አባተ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

04 Jan, 09:11


500 ሚሊየን ብር በሚገመት ወጭ የተገነባው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት ግንባታ ተመረቀ።

ደሴ- ታህሳስ 26/2017/ደሴ ፋና/አጠቃላይ የግቢው የቦታ ስፋት 8000 ካሬ ሜትር ሲሆን በታህሳስ 2010 ዓ.ም የቦታ ርክከብ በማድረግ በዋና መስሪያ ቤት በተያዘለት በጀት ግንባታው ተጀምሯል፡፡

በወቅቱ ተቋራጩ በገባው ውል መሰረት በ18 ወራት ውስጥ ተሰርቶ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ግንባታው ተቋርጦ በመቆየቱ በተባለው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ቀርቷል፡፡

ለህንፃው የወጣውን አጠቃላይ ወጭ በተመለከተ በብር 79.023.263.15 ውል ተወስዶ በ2010 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም በጦርነት ምክንያት ግንባታው ሲቋረጥ አፈፃፀሙ 43.95 በመቶ ደርሶ ነበር።

ግንባታው ከ3 ዓመታት ከአራት ወር ያህል ተቋርጦ ከቆየ በኋላ እንደገና እንዲቀጥል የኮሚሽኑ አመራሮች በወሰዱት ርምጃ ለሁለተኛ ጊዜ 346 ሚሊየን 227 ሽህ 862 ብር ውል ለመጀመሪያው ተቋራጭ እንዲወስድ ተደርጎ ግንባታውን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

ህንፃውን ለመጨረስ የፈጀው ጠቅላላ የግንባታው ወጭ 425 ሚሊየን 251 ሽህ 125 ብር የደረሰ ሲሆን በተጨማሪም ህንጻው የሚያስፈልገውን የውስጥ መገልገያ ቁሣቁሶች እና ግብአቶች ለማሟላት 95 ሚሊየን 151 ሽህ 111 ያህል ወጭ ተደርጎበታል።

አለባቸው አባተ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

04 Jan, 09:04


የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ በኮምቦልቻ ከተማ  ያሥገነባውን ህንጻ አስመረቀ።

ደሴ- ታህሳስ 26/2017/ደሴ ፋና/የጉምሩክ ኮሚሽን በኮምቦልቻ ከተማ ያሥመረቀው ህንጻ ባለ ስድስት ወለልና ዘመኑን የሚመጥን አደረጃጀት ጭምር ያለው ነው ተብሏል።

በምርቃ ስነ ስርአቱም የገቢዎች ሚንስቴር ሚንስትር አይናለም ንጉሴ እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተገኝተዋል።

አለባቸው አባተ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

02 Jan, 12:23


ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

ለቀናት በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሬዲዮ ስርጭታችን ተስተካክሎ ስርጭት መጀመራችንን እንገልፃለን።

ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0 ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

01 Jan, 18:53


በአማራ ክልል የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ 35 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ጤና ቢሮው ገለፀ።

ደሴ- ታህሳስ 23/2017/ደሴ ፋና/ይህ የተባለው ተደራሽነትና ጥራት ያለው እንክብካቤ በሁሉም ቦታ በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ህፃናት ቀን እና የሳንባ ምችን ለመግታት ግንባር ቀደም እንሁን በሚል አለም አቀፍ የሳንባ ምች ቀን በተከበረበት ወቅት ነው።

ቢሮው የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ እና በሳምባ ምች በሽታ የሚሞቱ ህጻናትን ሂወት ለመታደግ እንዲቻል ከአጋር አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልፅዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ እንደገለፁት በክልሉ የጤና ተቋማትን በማስፋፋትና ግብዓት በማሟላት የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ እንዲሁም ለእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ልዩ ትኩረት በመስጠትና በመንከባከብ የህጻናትን ሞት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በክልሉ ያለ እድሜያቸው በመወለድና በሳምባ ምች በሽታ የሚሞቱ ጨቅላ ህጻናት ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የሞት ምጣኔውን ለመቀነስና ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በክልሉ ከሚወለዱ አስር ህጻናት መካከል አንዱ ያለ እድሜው እየተወለደ መሆኑን ጠቁመው ከተወለዱት ደግሞ 35 በመቶ የሚሆኑት ሞት እያጋጠማቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

እንዲሁም አጠቃላይ በተለያየ ምክንያት ከሚሞቱ ጨቅላ ህጻናት መካከል 17 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በሳምባ ምች በሽታ መሆኑን ጥናቶች እንደሚያሳዩም ተገልፅዋል።

የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ልጆች ችግርን ለመግታት እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትልን ማድረግና የባለሙያን ምክር መተግበራቸው 75 በመቶ መከላከል እንደሚቻልም ተጠቁሟል።

በዚህም ለህፃናት ሞት በቀዳሚነት ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ጤና ተቋማትን በመደገፍ፣ በማጠናከር፣ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና ለህብረተሰቡም ግንዛቤን በመፍጠር ችግሩን ለመቀነስ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

       ሰብለ አክሊሉ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

28 Dec, 14:34


እዮቤል ፀጋዬ የፋና ላምሮት ምዕራፍ 18 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆነ

ደሴ- ታህሳስ 19/2017/ደሴ ፋና/ላለፉት ሶስት ወራት በአስደናቂ ተወዳዳሪዎች ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 18 ውድድር ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡

ለፍጻሜው ማዕረግ ሀይሉ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ ግሩም ነብዩ እና እዮቤል ፀጋዬ በሶስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከዛየን ባንድ ጋር አቅርበዋል፡፡

በውድድሩ እዮቤል ፀጋዬ አንደኛ በመውጣት ያሸነፈ ሲሆን÷ በዚህም የ400 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ግሩም ነብዩ ውድድሩን 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ 300 ሺህ ብር የተሸለመ ሲሆን÷ ማዕረግ ሀይሉ ደግሞ 3ኛ በመውጣት የ200 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የፍጻሜ ውድድሩን 4ኛ ሆና ያጠናቀቀችው እየሩሳሌም አሰፋ የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆን ችላለች፡፡

የፋና ላምሮት የምዕራፍ 18 ውድድር መስከረም 25 ቀን 2017 ዓ.ም በ16 ተወዳዳሪዎች የተጀመረ ሲሆን÷ተወዳዳሪዎቹም ለስምንት ሳምንታት በሁለት ምድብ ተከፍለው ሲወዳደሩ ቆይተዋል፡፡

በውድድሩ በየሳምንቱ አንድ ተወዳዳሪ የተሰናበተ ሲሆን÷ ከውድድሩ የተሰናበቱ ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዳቸው ከ5 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 35 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

ብርቱ ፉክክር በተደረገበትና በእየሳምንቱ በሁለት ዙሮች በተካሄደው በዚህ የፋና ላምሮት የምዕራፍ 18 ውድድር 10 ወንዶችና 6 ሴት ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለዚህ ውድድር በአጠቃላይ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቶ ተወዳዳሪዎችን መሸለሙን አስታውቋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

28 Dec, 07:30


በደሴ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የሰላም፣ የልማትና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ለከተማዋ እድገት እየሰራ መሆኑን የሸርፍ ተራና አካባቢው ነጋዴዎች የልማት፣ መተሳሰብና ሰላም ማህበር ገለፀ።

ደሴ- ታህሳስ 19/2017/ደሴ ፋና/ማህበሩ ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ  በነጋዴው መካከል መተሳሰብ እንዲኖር በማድረግ፣ የሚነግድበትን ቦታ ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ ያለስጋት እንዲሰራ እያደረገ ነው።

የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ኡመር  አህመድ እንደሚሉት የሸርፍ ተራ የውስጥ መንገድን ከ2.6 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ከማሰራት ጀምሮ የእሳት አደጋ ቢከሰት ችግሮች እንዳይፈጠሩ መወጣጫ መሰላሎችን እና ሲሊንደሮችን ገዝቷል።

ማህበሩ ለሸርፍ ተራ አካባቢ ጥበቃዎችን በመቅጠር በቀንም ሆነ በሌሊት ጥበቃ እንዲደረግ እያደረገ ሲሆን ስራ የሌላቸው ወጣቶችን ተያዥ እንዲያመጡ በማድረግ ባጅና ገዋን በማዘጋጀት ወደ ስራ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

ማህበሩ በዛሬው እለት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሔደ ነው።

ስንታየሁ አራጌ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

27 Dec, 10:17


ኮምቦልቻ አካባቢ የመብራት ማስታለፊያ ታወር በመዘረፉ ምክንያት የመብራት አገልግሎት በፈረቃ ሆኗል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ድስትሪክት

ደሴ-ታህሳስ 18/2017/ደሴ ፋና/የድስትሪክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብቱ አበበ ለጣቢያችኝ እንደተናገሩት ኮምቦልቻ አካባቢ የመብራት ተሸካሚ ታወር በመዘረፉና በመውደቁ ምክንያት መብራት እስኪስተካከል ድረስ በአካባቢው በፈረቃ እንደሚሰጥ አንስተዋል።

በዚህም ደሴ ከተማ፣ ወረባቦ ፣አልቡኮ ፣ኩታበር ፣ ደሴ ዙሪያና ወልዲያ የተወሰኑ አከባቢዎች ችግሩ እስኪስተካከል መብራት በፈረቃ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ማህበረሰቡ ችግሩ አስኪስተካከል በትእግስት እንዲጠብቅም ጥሪ ቀርቧል።

ከድር መሀመድ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

26 Dec, 19:01


የርስ በርስ ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር እንዲቻል ባህልን በመጠቀም እሴትን ከፍ ማድረግ ይቻላል ተባለ።

ደሴ- ታህሳስ 17/2017/ደሴ ፋና/ይህ የተባለው 16ኛው ዞን አቀፍ የባህልና የኪነጥበብ ፌስቲቫል በተጀመረበት ወቅት ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ አስያ ኢስራ እንደገለፁት ለ3 አመታት ተቋርጦ የነበረው የባህል ፌስቲቫል 16 ወረዳዎች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል መካሄዱ አንዱ ወረዳ ከሌላኛው ልምድን ከመለዋወጥ ባለፈ ማህበረሰቡ ሲጣላ፣ ሲፋቀር እንዲሁም ችግሩንና አብሮነቱን የሚገልፅበት ቱባ የሆነ ባህል ስላለው ለወጣቱ ቱውፊቱን ለማሻገር የሚረዳ ነው ብለዋል።

ማህበራዊ መስተጋብርን ለማሳለጥ ባህልን ማጠናከርና እሴትን መጠበቅ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

ደቡብ ወሎ ዞን ተፅፎ የማያልቅ ባህልና እምነት ያለበት የጥበብ ሁሉ ቁንጮ የሆነ በመሆኑ የቋንቋ ብዝሃነትንም የምናይበት ነው ብለዋል።

ባህልን ከባህል ለማወዳደር ሳይሆን ፌስቲቫሉ የተዘጋጀው ዞኑን ወክለው የሚሄዱ ፈርጦችን ለመምረጥ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በበጀት እጥረትና በወቅታዊ ጉዳይ ሁሉም ወረዳዎች ተሳታፊ ባይሆኑም አሸናፊ የሆነው ቡድን ዞኑን ወክሎ በክልል ደረጃ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ገልፀዋል።

በዚህም የተሻለ ውጤትን እንዲያመጡና የዞኑን ባህል በተሻለ አቅም እንዲያስተዋውቁ ከአጋር አካለት በመመካከር ስልጠናና ድጋፍ በማድረግ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋልም ብለዋል።

ፊስቲቫሉ እስከ ነገ የሚቀጥል ሲሆን ተወዳዳሪ ወረዳዎችም ባህላቸውን በሙዚቃ፣ በቲያትርና በተለያዩ ክዋኔዎች የሚያስተዋውቁ ሲሆን ከወሎ ዩኒቨርስቲ በመጡ ዳኞችም የሚዳኙ ይሆናል።

       ሰብለ አክሊሉ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

07 Dec, 09:47


ሰላምና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ በመሆናቸው ልንጠብቅና ልናስቀጥላቸው ይገባል ተባለ።

ደሴ- ህዳር 28/2017/ደሴ ፋና/ይህ የተባለው ሰላምና ልማትን በተመለከተ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ሰላም ከሰው አልፎ ለአራዊቱም አስፈላጊ ነውና ሁሉም በጋራ ሊጠብቀው ይገባል ብለዋል።

በተለይም ከተማችንን ወደ ላቀ ኢኮኖሚ ለማሻገር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑትን ሰላምና ልማት መጠበቅና ማሻገር ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

ነጋዴው ገቢን የሚያገኘውና በልማቱ ተሳታፊ የሚሆነው ሰላሙ ሲረጋገጥ ነውና የከተማችንን ፀጥታ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የፖለቲካ መነሻው ኢኮኖሚ በመሆኑ የሁሉም መሰረት በዋጋ የማይተመን የልማት ድጋፍ የሆነውን ሰላም ማስፈን ተገቢ ነው።

የንግዱም ማህበረሰብ ለዚህ አጋርና ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታንና ሰላምን በመፍጠር ወደ ተሻለ ኢኮኖሚ እንዲሸጋገር ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ከተማችንን ለማሳደግ በጋራ በመስታት ሃላፊነታችንን እንወጣለንም ብለዋል።

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የሚደረግበት የከተማው የኮሪደር ልማት በተያዘለት የግዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የንግዱ ማህበረሰብ በጋራ በመስራት ሰላምን ማስቀጠል እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

በመድረኩ በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል በላይ ስዩም፣ ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣ የአማራ ክልል ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ አቶ ሞላ ትዕዛዙ፣ የፓርቲ አመራሮች፣ የመምሪያ ሃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብና ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች ተገኝተዋል።

ሰብለ አክሊሉ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

07 Dec, 08:50


በክረምት በጎ ፈቃድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ12 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ ቤቶች ለነዋሪዎች ተላለፉ።

ደሴ- ህዳር 28/2017/ደሴ ፋና/በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በ12 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ ቤቶች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ለነዋሪዎች የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።

በኢኖቬሽንና ታክኖሎጂ ሚኒስቴር እና አጋር ተቋማት የተገነቡ እያንዳንዳቸው ሁለት ክፍል ያላቸው ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀምረው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ለነዋሪዎች መሠጠቱ የቤት ችግርን የፈታ ነው ተብሏል።

የቤት ቁልፍ የተረከቡ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆነ የቤት ችግር እንደነበረባቸው ገልፀው ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በቁልፍ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ለነዋሪዎች የተላለፉት ቤቶች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ገልፀው ተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ሚኒስቴሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል

አቶ መሀመድ አሚን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው አሁን ላይ ለነዋሪዎች የተላለፉት ቤቶች ከተባበርን የማንፈታው ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ያሉ ሲሆኑ የሚኒስቴሩን በጎ ተግባር በከተማ አስተዳደሩ እና በህዝቡ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በተመሳሳይ እየተሰሩ የሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶች በቅርቡ ተጠናቀው ለነዋሪዎች እንደሚተላለፉ አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከስፔስ ሳይንስና ጅኦስፖሻል ኢንስቲቱዩት እንዲሁም ባዩ ኢመርጂንግ ኢንስቲቱዩት የተገነቡት ቤቶች ለነዋሪዎች ተላልፈዋል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ደሴ ቅርንጫፍ

05 Dec, 13:36


ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የዶሮ እርባታ ክላስተር የስራ እድል መፍጠሪያ የሼድ ግንባታ በደሴ ከተማ ተጀምሯል።

ደሴ- ህዳር 26/2017/ደሴ ፋና/የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የሚገነባው ሼድ የወጣቶችን የስራ እድል ከፍ ከማድረግ ባሻገር የእንቁላልና የዶሮ ስጋ አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።

ከ4 አስከ 6 ወር ጊዜ አጠናቆ እና መሰረተ ልማቱን አሟልቶ በአጭር ጊዜ ስራ ለማስጀመር እንደሚሰራም ተገልጿል።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከተማን ለመለወጥ የኢንዱስትሪና የከተማ ልማት ስራ ወሳኝነት እንዳለው አንስተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ለስራ እድል ፈጠራ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር ኘሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት ይጠበቃል ብለዋል።

የደሴ ከተማን ልማት የተሻለ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በአመቱ ለ28 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ያያዘ ሲሆን አስከ አሁን 4 ሽ 500 ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩም ተገልጿል።

ከድር መሀመድ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

30 Nov, 12:57


በሩብ አመቱ 155 ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ መያዛቸውን የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ አስታወቀ።

ደሴ- ህዳር 21/2017/ደሴ ፋና/በመምሪያው የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ አቶ በሪሁን ካሳው እንደገለፁት በሩብ አመቱ በተደረ ምርመራ 155 ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ተገኝቷል።

በ2016 ዓ.ም በተደረገ ምርመራ ደግሞ 587 ቫይረሱ በደማቸው መገኘቱን አስታውሰዋል።

በዚህም በደሴ ከተማ የስርጭት መጠኑ 3.9 ፐርሰንት ላይ መድረሱም ተጠቁሟል።

የቫይረሱ ስርጭት የጨመረበት ምክንያት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው መዘናጋት በመሆኑ ሁሉም ቅድመ ምርመራ እና ጥንቃቄን በማድረግ ሃገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በጋራ መሰራት አለበት ሲሉም አቶ በሪሁን መልዕክትን አስተለልፈዋል።

ሰብለ አክሊሉ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

30 Nov, 10:11


"ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል የአለም የኤች አይ ቪ ቀን በደሴ ከተማ ተከብሯል።

ደሴ- ህዳር 21/2017/ደሴ ፋና/በመድረኩ የተገኙት የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው እንደተናገሩት አሁን ላይ ማህበረሰቡ ለስኳርና ለደም ግፊት የሚሰጠውን ያክል ትኩረት እየተሰጠው ባለመሆኑ ስርጭቱ እየተስፋፋ መቷል ብለዋል።

ከቤተሰብ ጀምሮ ግልፀኝነትን ልምድ በማድረግ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ሃላፊነት ያለባቸው ሁሉ ግንዛቤን በመፍጠር የምርመራ ባህላችንን በማሳደግ ስርጭቱን መግታት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ ፍስሃ ዳውድ በበኩላቸው አምራች ዜጋን ለማፍራት እንዲቻል የኤች አይ ቪ ስርጭትን መግታትና መከላከል ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በከተማዋ እየታየ ያለውን ስርጭት ለመግታት ከመዘናጋት በመውጣት እየተጠቃ ያለውን የነገ አገር ተረካቢ የሆነውን ወጣት ከዚህ ቫይረስ እራሱን እንዲጠብቅ ሁሉም ሊሰራ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ከትምህርት ቤት ጀምሮ የግንዛቤ ስራን በማስፋት መከላከል ላይ ከመስራት ባለፈ በማህበረሰቡ ዘንድ እየታየ ያለውን መዘናጋት ለመቅረፍና ማህበረሰቡን የማነቃቃት አላማን ይዞ በአሉ እየተከበረ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የኤች አይ ቪ ቀን በአለም ለ37ኛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ36ኛ ግዜ ተከብሯል።

ሰብለ አክሊሉ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

29 Nov, 13:18


https://youtu.be/bdmG_eRwQSA?si=jWLb2OWgCUcMEIm0

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

29 Nov, 11:23


በደሴ ከተማ በሚሰራው የኮሪደር ልማት አማካኝነት የተቋረጡ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስታወቁ።

ደሴ- ህዳር 20/2017/ደሴ ፋና/በደሴ ከተማ በኮሪደር ልማቱ ምክንያት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ እንዳይቆራረጥ እየተሰራ መሆኑን ተቋማቱ ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የህዝብ ግነኙነት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አሊ እንድሪስ እንደተናገሩት ከኢሚግሬሽን አስከ አቡነ ግቢ እና ከቧንቧ ውሀ አስከ እፎይታ መገንጠያ ያለውን የውሀ አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር እየተሰራ ነው።

በኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጂን የኔትወርክ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ቀለም ወርቅ ታረቀኝ በበኩላቸው የተነሱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ዲዛይን በማውጣት ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ይቀየራሉ ያሉ ሲሆን በጊዜአዊነት በተለይም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተቋማትን በመለየትም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኢብራሂም የሱፍ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ሪጂን የኮንስትራሽን ስራ አስኪያጅ ለጣቢያችን እንደተናገሩት መብራት የተቋረጠባቸው አካባቢዎችን በአፋጣኝ ለመስራት በጊዜያዊነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ክትትል እየተደረገ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ተገልጋዮችን በመለየት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

     ከድር መሀመድ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

28 Nov, 18:34


"አንድነታችን ለአብሮነት እና ለታሪካችን ምንጭ ነው" በሚል መሪ ቃል 19ኛው የብሔርብሔረሰብ ቀን በደሴ ከተማ ተከበረ።

ደሴ- ህዳር 19/2017/ደሴ ፋና/በደሴ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዘጋጅነት የተከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ፤ ብሔር ብሔረሰቦች ለነፃነት፣ ለእኩልነት እና ለፍትህ በጋራ እና በአንድነት መስራት ያለውን ሀይል በማሳየት የራስን እና የሌሎችን ማንነት አክብሮ ለሀገር ሰላምና ልማት መስራት የሚያስችል ነው ሲሉ የደሴ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሙህዬ ገልፀዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በበኩላቸው እንደ ሀገር የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲከበር ብሔራዊ ፌደራሊዝም የወል ትርክትን ማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር ለኢትዮጵያ ብሔረሰቦች መብት መከበር ዋስትና ያረጋገጠ ነው ያሉት የበአሉ ተሳታፊዎች ብሔር ብሔረሰቦች ያላቸውን ባህል፣ ቋንቋ እና እሴት ልምድ ይለዋወጡበታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊት ሀገር በመሆኗ አንዱ ያላንዱ ምንም ነው ያሉት ተሳታፊዎች በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍና በመተባበር ሀገሪቱን የማልማት ስራ ለመስራት እንደሚያስችልም ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የህዝቦችን የነፃነት፣ የእኩልነት እና ፍትህ የተረጋገጠበትም ነው ተብሏል።

ስንታየሁ አራጌ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

28 Nov, 11:17


ከዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ 9.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ተባለ።

ደሴ- ህዳር 19/2017/ደሴ ፋና/በአማራ ክልል የ2017 ዓ.ም የበጋ መስኖ የስንዴ ዘር ስራ በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ እና መቅደላ ወረዳ ተጀምሯል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ እንዳለው በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 254ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል።

በዚህም 9.5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማምረት ግብ ተጥሏል ያሉት ቀኛዝማች መስፍን በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለዚህ ምርት ስኬታማነት በቂ ግብአት እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ 36ሺህ 500 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሰራ ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት መታቀዱን አቶ አህመድ ጋሎ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴን እየዘሩ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች እንዳሉት ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት በበጋ ስንዴን በመዝራታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተያዘው የበጋ መስኖ ስንዴ አማካኝነት ምርታማነታቸውን ከፍ ለማድረግ ቴክኖሎጂ እና ግብአት በአግባቡ እየተጠቀሙ እንደሆነም ነግረውናል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

21 Nov, 10:23


https://youtu.be/nPu6PBT3g0M?si=2jU6vr60G5zU1u1-

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

21 Nov, 09:59


በደሴ ከተማ መናኻሪያ አካባቢ የሚታየውን የጽዳት ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ይሰራል ተባለ።

ደሴ- ህዳር 12/2017/ደሴ ፋና/በከተማዋ መናኻሪያ አካባቢ በተከፈተ ካናል ምክንያት በተደጋጋሚ የጽዳት ችግር መኖሩን ጣቢያችን ያረጋገጠ ሲሆን የሚመለከታቸውን አካላትንም ጠይቋል።

የሆጤ ክፍለ ከተማ ጽዳትና ውበት አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቴወድሮስ አሰፋ ለጣቢያችን እንደተናገሩት የጽዳት ችግሩ የተከሰተው የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን ካናሉን ለረጂም ጊዜ ክፍት በማድጉ ነው ያሉ ሲሆን ተቋሙ ለችግሩ መፍትሔ መስጠት አለበት ብለዋል።

የደሴ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሀላፊ አቶ አንዱአለም አሰፋ በበኩላቸው በግብአት እጥረት ምክንያት ካናሉ በወቅቱ ባለመሰራቱ የመጣ ችግር መሆኑን አምነው ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዚህ በአጭር ቀን ውስጥ ካናሉን በማስተካከል ለአካባቢው ጽዳት ምቹ የማድረግ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ማህበረሰቡ ለአካባቢው ጽዳት ሀላፊነት እንዳለበት የተነሳ ሲሆን ሀሉም ሚናውን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል።

ከድር መሀመድ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

20 Nov, 20:54


በ21 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ ሲቪክ ተሳትፎ ማጎልበት ፕሮጀክት በሲቪክ መሀበረሰብ ነፃ ሀሳብ ዙሪያ እየሰራ መሆኑን ገለፀ።

ደሴ- ህዳር 11/2017/ደሴ ፋና/ከ USAID በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ በምስራቅ አማራ፣ ሶማሌ ፣ ድሬደዋ እና ምእራብ ኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ለሲቪክ መሀበረሰብ ነፃ ሀሳብ መጎልበት እና በሰላም እሴት ግንባታ ላይ እየሰራ ነው።

በ USAID ኢትዮጵያ ሲቪክ መሀበረሰብ ተሳትፎ ፕሮጀክት ኀላፊ ሜሊሳ ብሪል እንዳሉት በሰላም እሴት ግንባታ፣ በመሀበረሰብ አብሮነት እና የሲቪክ ማህበረሰብ የሀሳብ ነፃነት ዙሪያ ለሚሰሩ ድርጅቶች እና ተቋማት የቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪክ መሀበረሰብ ተሳትፎ ፕሮጀክት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ብሌን አስራት በበኩላቸው ለአራት ዓመታት ተግባራዊ በሚደረገው ፕሮጀክት የአፈፃፀም ግምገማ ይካሄድበታል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሙህራን እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የኀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ ናቸው።

በፕሮጀክቱ ትግበራ የጋራ የሰላም እሴቶች እንዲጎለብቱ እና የመሀበረሰብ አብሮነት እንዲጠናከር የተለያዩ የውይይት መድረኮች ያመቻቻሉ።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

20 Nov, 20:49


መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ለተመደቡ ተማሪዎቹ ጥሪ አስተላልፏል።

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

20 Nov, 14:52


https://www.facebook.com/100069672641659/posts/880227844309629/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

20 Nov, 07:27


በበጀቱ ሩብ አመት ለ2 ሽ 600 ወጣቶች ስራ እድል መፍጠሩን የደሴ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ገልጿል።

ደሴ- ህዳር 11/2017/ደሴ ፋና/መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለፀውም ስራ እድል ፈጠራን በታቀደው ልክ ለመፈፀም ከስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

የስራና ስልጠና መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እንደተናገሩት ከተፈጠሩት የስራ እድሎች መካከል 92 በመቶ በላይ የሚሆነው ቋሚ ስራ እድል ነው።

ሴክተር መስሪያ ቤቶች በየዘርፉ ስራ እድል ለመፍጠር እየሰሩ ያሉት መልካም ጅምር ቢሆንም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አቶ ጥላሁን ገልፀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በዚህ አመት ለ2 ሽ 828 ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ ነው።

እለኒ ተሰማ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

20 Nov, 03:07


የማህፀን በር ካንሰርን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችለውን ክትባት በዞኑ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

ደሴ- ህዳር 11/2017/ደሴ ፋና/የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጌታቸው በለጠ እንደገለፁት ከህዳር 9 እስከ 14/2017 ዓ.ም በሚቆየው ዘመቻ በዞኑ ያሉ 146 ሺህ ልጃገረዶችን ለመከተብ ታቅዷል።

ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ በሰፈር እና ልጃገረዶቹ ባሉበት አካባቢ እየተሰጠ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ 9 እስከ 14 ዓመት ልጃገረዶችን ያጠቃልላል።

እስከ አሁን የእቅዱን 46 በመቶ መከወን መቻሉን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን በማስከተብ እና እንዲከተቡ በመገፋፋት ከማህፀን በር ካንሰር እንዲከላከሉ ማድረግ እንዲችሉም ጥሪ ተላልፏል።

በተያያዘ ዜና

የማህፀን በር ካንሰርን ቀድሞ ለመከላከል በትምህርት ተቋማት የክትባት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ገለፀ።

የመምሪያው የእናቶች ህፃናትና ወጣቶች የጤና አገልግሎት ኦፊሰር ሲስተር ሮዛ ሽፈራው በሁሉም ትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ9-14 የሆኑ ታዳጊዎች ክትባቱን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው።

እስከ ህዳር 14 በሚሰጠው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ8ሺ 400 በላይ ታዳጊዎች ተደራሽ ይሆናሉ ያሉት ሲስተር ሮዛ ከዚህ ውስጥ 1 ሽ 400 የሚሆኑት ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ናቸው ተብሏል።

የክትባት ዘመቻውን 20 ቡድን በውስጣቸው 4 ባለሙያዎች ያላቸው ተመድበው ክትባቱን እየሰጡ ሲሆን ታዳጊዎች ክትባቱን በመውሰድ በሽታውን ቀድሞ መከላከል እንዲቻል ወላጆች እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

 ዘገባው የሰብለ ሲሳይ እና የስንታየሁ አራጌ ነው

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

19 Nov, 17:07


https://www.facebook.com/100069672641659/posts/880227844309629/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

19 Nov, 10:04


በ2017 ትምህርት ዘመን ከ12ሺ በላይ ተማሪዎችን ለመመገብ ወደ ተግባር መግባቱን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ደሴ- ህዳር 10/2017/ደሴ ፋና/ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ በቁጥር አንድ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርን አስጀምሯል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መንግስቱ አበበ እንደገለፁት የተማሪዎች ምገባ በ2015 ዓ.ም በ500 ተማሪዎች በ3 ትምህርት ቤቶች የተጀመረ ሲሆን ይህንንም በማስፋት በ2016 በሁሉም ትምህርት ቤቶች 5 ሽ 302 ተማሪዎችን 20 ሚሊየን ብር በመመደብ እየመገቡ እንደነበር ገልፀዋል።

በዚህ አመት ደግሞ ከ12ሺ በላይ ተመሪዎችን ለመመገብ መርሃ ግብሩ ተጀምሯል።

ለዚህም 75 ሚሊየን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን 50 ሚሊየን ብሩን ከተማ አስተዳደሩ 25 ሚሊየን ብሩን ደግሞ ከማህበረሰቡና ባለሃብቱ መገኘቱን ተናግረዋል።

በዚህም የአቋሯጭ ተመሪ ቁጥርን ከመቀነስ ባለፈ ተማሪዎች የተሻለ ውጤትን እንዲያስመዘግቡ እያደረገ በመሆኑ አጋር አካላትና ማህበረሰቡ በጋራ በመስራት ሁሉም አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪን አቅርበዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሃመድ አሚን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ተማሪዎች ላይ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ትምህርት የሁሉም ልማት መሰረት በመሆኑ የተማሪዎች ምገባ ላይ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በክልሉ እየታየ ያለውን መቀንጨርን ከመከላከል ባለፈ ተማሪዎች በአካልም በአዕምሮም ያደጉ እንዲሆኑና የነገይቱን ኢትዮጵያን ለመግንባት ትውልድ ላይ መስራት ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ አመት ከኬጅ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ለመመገብ በቀን ለአንድ ተማሪ 35 ብር በመመደብ ወደ ተግባር ተገብቷል።

      ሰብለ አክሊሉ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

14 Nov, 12:45


በመጪዎቹ 10 ቀናት የጧቱ እና የሌሊቱ ቅዝቃዜ እንደሚጨምር የምስራቅ አማራ ሜትሮዎሎጂ ማእከል አስታወቀ።

ደሴ- ህዳር 5/2017/ደሴ ፋና/በአብዘሀኛው የምስራቅ አማራ አካባቢዎች ነፋሻማ እና ቀዝቃዛ የአየር ንብረት እንደሚኖር በመአከሉ የትንበያ እና ትንተና ዴስክ ኀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሉባባ መሃመድ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከሌሊቱ እና ጧት ላይ ከሚኖር ቅዝቃዜ በተጨማሪ በመጪዎቹ አስር ቀናት አጋማሽ ላይ ዝናብ ሰጪ የአየር ንብረት እንደሚኖር ይጠበቃል

በዚህም ምክንያት አርሶአደሩ የደረሱ ሰብሎችን በማጨድ እና በፍጥነት ከማሳ ላይ በማንሳት ሰብሉን ከብልሽት እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

የምስራቅ አማራ ሜትሮዎሎጂ አገልግሎት መአከል ወቅታዊ የአየር ትንበያ መረጃዎችን በፍጥነት ለማህበረሰቡ እንደሚያደርስ ገልጿል።

          እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

13 Nov, 08:50


ተሽከርካሪዎች ላይ የሚታየውን ህገ ወጥነት ለመከላከል አዲስ አሰራር መዘርጋቱን የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

ደሴ- ህዳር 4/2017/ደሴ ፋና/በመምሪያው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ  የሆኑት ኢንስፔክተር አደፍርስ ታፈሰ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በተለይም ባለ ሶስት አግር ተሽከርካሪዎችንና በተለምዶ ዳማስ ተብለው የሚጠሩትን መለስተኛ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር መዘርጋቱን ገለጸዋል።

ህገወጥ ተሽከርካሪዎችን ለመለየት እንዲሁም ማህበረሰቡን ከዝርፊያ ለመከላከል በተተገበረው አሰራር ተሽከርካሪዎቹ በግልጽ የሚታይ የታርጋ ታፔላና የባለቤት ስምና አድራሻ ያለበት አብረቅራቂ ልብስ ማድረግ ግዴታ  እንደሆነም ተነስቷል።

አሰራሩ ህገ ወጡን ከመለየት ባለፈ ተገልጋዮች ችግር ቢደርስባቸው ችግር አድራሹን አካል በቀላሉ ለመለየት ይረዳል የተባለ ሲሆን በተለይም ስርቆትን ለመከላከል ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተነስቷል።

ስራው ወደ ትግበራ የገባ ሲሆን ሀሉም ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሊተገብሩት እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከድር መሀመድ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

13 Nov, 07:33


ወጣቱ ከጠባቂነት ወጥቶ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዳለበት ተገለፀ።

ደሴ- ህዳር 4/2017/ደሴ ፋና/በደሴ ከተማ "የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለፈጠራ ክህሎት" በሚል መሪ ሀሳብ የአፍሪካ ወጣቶች ቀን እየተከበረ ይገኛል።

በአፍሪካ ለ18ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ በሚከበረው እለት ወጣቶች የተሻለ የስራ ባህል እንዲኖራቸው መሰራት እንደሚገባው ተገልጿል።

ያነጋገርናቸው ወጣቶችም ወጣቱ የፈጠራ ችሎታውን ሊያዳብርበት የሚችል ቦታ በሰፊው ሊኖር እንደሚገባ እና ወጣቱም ከጠባቃነት ወጤቶ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዳለበት ተነስቷል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

12 Nov, 17:40


በአማራ ክልል ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ ያለው የወባ ወረርሽኝ ስርጭት መኖሩ ተነገረ።

ደሴ- ህዳር 3/2017/ደሴ ፋና/የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አብዱልከሪም መንግስቱ እንደገለፁት በአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም ከነበረው የወባ ስርጭት አንፃር ዘንድሮ እጅጉን ከፍተኛ በተባለ መጠን ስርጭቱ ተባብሷል።

በ2016 አመቱን ሙሉ 1.5 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍል በወባ በሽታ ተይዞ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ በአንደኛው ሩብ አመት በሶስቱ ወራት ብቻ ከ530 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል በወባ መያዙን ተናግረዋል።

ይህንን ወረርሽኝ ለመግታት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ቢሮ ሀላፊው የአርብ ጠንካራ እጆች የወባ ወረርሽኝን ይገታሉ በሚል መሪ ቃል የጤና ጣቢያ መር የማህበረሰብ አቀፍ የአካባቢ ቁጥጥር በሚል ላለፉት ሶስት ሳምንታት ታውጆ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ የወባ መራቢያ ቦታዎችን የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ቤት ለቤት የወባ ህሙማንን ልየታ ምርመራና ህክምና አገልግሎቶች እየሰጡ ሲሆን በጤና ድርጅት ደግሞ አስፈላጊውን የመድሀኒት አቅርቦት በማሟላት ሁሉም አካባቢ ላይ እንዲሰጥ እየተደረገ ነው።

የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ለወባ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ህብረተሰቡ የወባ መራቢያዎችን በማጥፋትና ንፅህናውን በመጠበቅ ብሎም የህመም ስሜት ሲሰማው ወደ ህክምና ተቋም በመሔድ ራሱን የመከላከል ስራ እንዲሰራም ጥሪ ቀርቧል።

        ስንታየሁ አራጌ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

12 Nov, 17:38


በ3 አመት ውስጥ ከ17ሺ በላይ የኢትዮ ኮደርስ ሰልጣኞችን ብቁ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ የደሴ ከተማ ስራና ስልጠና መምሪያ

ደሴ- ህዳር 3/2017/ደሴ ፋና/በበይነ መረብ የሚሰጠውና አለም አቀፍ ይዘት ያለው በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ስልጠና የሚሰጥበት የኢትዮ ኮደርስ መርሀ ግብር በደሴ ከተማ መጀመሩ ተነግሯል።

የከተማዋ ስራና ስልጠና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ስለጠናው በቴክኖሎጂ ብቁ ከማድረግ ባሻገር አለም አቀፍ ተወዳዳሪም የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በከተማ አስተዳደር ደረጃ በ3 አመት ውስጥ ከ17 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ለማሳተፍ የታቀደ ሲሆን 4 ሺህ የሚደርሱት በዚህ አመት ስልጠናውን የሚወስዱ ናቸው ተብሏል።

አስከ አሁን ከ1 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎች ያሉ ሲሆን 260 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው መመረቃቸው ተነግሯል።

ሰልጣኞች በግል ስልካቸውም ስልጠናውን መውሰድ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ማእከሎችን ቢያዘጋጅም ጉዳዩን ተገንዝቦ ወደ ስልጠና የሚገባው ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ስለጠናው በርካታ ጥቅሞች ያሉት በመሆኑ ሀሉም ሊሳተፍበት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

           ከድር መሀመድ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

12 Nov, 11:46


የእናቶች ጤና አገልግሎትን በተሻለ መልኩ እየሠጠ መሆኑን የደሴ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽፈት ቤት ገለጸ።

ደሴ- ህዳር 3/2017/ደሴ ፋና/የጽፈት ቤቱ ምክትል ሀላፊ  እንደገለጹት  ለነፍሰ ጡር እናቶች የሚደረግ ምርመራና እንክብካቤ ተጠኔክሮ ቀጥሏል።

የሠለጠኑ ባለሙያዎችና ተንቀሳቃሽ አልትራ ሳውንድ በመጠቀም በሰባት ጤና ጣቢያዎች  ለ355 ነፍሰ ጡር እናቶች የምርመራ አገልግሎት ተሠጥቷል።

በተመሣሣይ የሠለጠኑ ባለሙያዎችን በማንቀሳቀስ 372 እናቶች የመሀጸን በር ካንሰር ምርመራ አድርገዋል።

ከተመረመሩት ውስጥም 16 የሚሆኑ እናቶች ቅድመ ካንሰር ህክምናን እንዲከታተሉ ወደ ህክምና ተቋማት ተልከዋል።

ለ26 እናቶች የጡት ካንሰር ምርመራ የተደረገ ሲሆን አንዲት እናት የቅድመ ካንሰር ደረጃ ተገኝታ ወደ ህክምና ጣቢያ እንድትደርስ ተደርጓል።

ወረዳው ለእናቶች በወሊድ ክትትል በማህጸን በር ካንሰርና በጡት ካንሰር ምንነትና የምርመራ ሂደትም የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ትምህርት እየሠጠ ይገኛል።

     አለባቸው አባተ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

11 Nov, 19:01


በ2017 በጀት አመት 288 ሸዶችን ለመገንባት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ አስታወቀ።

ደሴ- ህዳር 2/2017/ደሴ ፋና/በመምሪያው ተወካይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት የሚታየውን የሸድ አጠቃቀም ችግር በመፍታት የሚደራጁ ማህበራትን እጥረት ሳይኖር በፍትሃዊነት ለማዳረስ እንዲረዳ 288 ሸዶችን ለመገንባት በማቀድ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

ይህንንም እውን ለማድረግ ከወረዳዎች ጋር መግባባትን በመፍጠር 20 ሚሊየን ብር ሸድ ለመገንባት ገንዘብ መመደቡንም ገልፀዋል።

ይሁን እንጅ ወረዳዎች ይህን ገንዘብ ቢመድቡም ሁሉም ግን እኩል ተሳታፊ አይደሉም ያሉ ሲሆን በተለያየ ምክንያት ገንዘብ  ያላስገቡ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በወተት፣ በዶሮ እርባታ፣ በማር ምርትና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የማልማት አቅምን በማሳደግ አመርቂ የሆነ ምርትን ለመሰብሰብ እንዲቻል ሸዶችን በክላስተር ለመስራትም ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

ተወካይ ሃላፊው አክለውም 488 ሸዶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው የሚገኙ ሲሆን በፀጥታ ችግር ምክንያት ማስመለስ አለመቻሉን ገልፀዋል።

      ሰብለ አክሊሉ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

11 Nov, 19:00


ባለፋት 27 ዓመታት በደሴ ከተማ ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ማስገባቱን የአማራ ልማት ማህበር ገለጸ።

ደሴ- ህዳር 2/2017/ደሴ ፋና/ማህበሩ ለጣቢያችን በሰጠው መረጃ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ 23 የሚሆኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ አስገብቷል።

የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ፣ የትምህርት ቤቶች ግንባታና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ግንባታና ሌሎች ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

ባለፋት 27 አመታትም በጥቅሉ 77 ሚሊዮን 370ሺ ብር ወጭ ማድረጉንም ማህበሩ ጠቁሟል።

በቀጣይም የጀመራቸውን ተግባራት በማጠናከር የተሻለ ስራ እንደሚከውን ማህበሩ ገልጿል

      ሙሉቀን አበበ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

11 Nov, 10:23


የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ፣መሀበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ሰላም ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

ደሴ- ህዳር 2/2017/ደሴ ፋና/ሀብት አፈራለሁ ፣ የሀገሬን ሰላም እጠብቃለሁ ፣የኢትዮጵያን ብልፅግና አፋጥናለሁ በሚል ከደሴ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን በተገለፀበት መድረክ ወጣት ገዛኸኝ አንዳርጌ በብልፅግና ፖርቲ የወጣቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና በዋና ጽ/ቤት የወጣቶች አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ  ያቀረበው ፅሑፍ ያመለክታል።

ወጣቱ የሀገር ተረካቢ ብቻም ሳይሆን የሀገሩ ባለቤት ስለሆነ በነጠላ ትርክት ከመለያየት አንድ በሚያደርጉን በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት በመፍጠር ወጣቱ የድርሻውን መወጣት አለበትም ተብሏል።

በመድረኩ ከደሴ ከተማ ወጣቶች በተጓዳኝ የደሴ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

04 Nov, 13:48


የፌደራል ፖሊስ ፀጥታን ከማስከበር ባለፈ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የልማቱ ተሳታፊ እና አጋዥ እንደሆነ ተገለፀ።

ደሴ- ጥቅምት 25/2017/ደሴ ፋና/በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ቱሉ አዳሜ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በአየር መንገድ ስር የሚገኘው መሬት ከዚህ በፊት ታጥሮ ከመቀመጥ ባለፈ ለአካባቢው የሰላም ስጋት የነበረን ቦታ ፊደራል ፖሊስ በማልማቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህ ተግባርም ፌደራል ፖሊስ ፀጥታን ከማስከበር ባለፈ የልማት አጋር መሆኑን ያየንበት ነው በማለት በቀጣይም ከፀጥታው አካል ጋር በመጣመር የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ በልማቱም ከጎናቸው እንቆማለን ብለዋል።

የሬጅመንት 4 ምክትል አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሳ አህመድ እንደገለፁት ከዚህ በፊት ቦታው ታጥሮ ቁንጥር፣ አረምና ሳር ሲበቅልበት የነበረ በመሆኑ ለአካባቢው ስጋት ነበር ብለዋል።

ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር 25 ሄክታር መሬትን ከአጋር አካለት የማሽን እገዛን በማግኘት የፖሊስ አባላቱን በማሳተፍ ስንዴን በመዝራት ዛሬ ላይ ሰብሉ ደርሶ ለማጨድ በቅተናል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህም 300 ኩንታል የስንዴ ምርት ይገኛል።

ማህበረሰቡም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ተሳታፊ ስለነበር ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

ፌደራል ፖሊስ ባለማው ልማት የምግብ ፍጆታን ከመሸፈን ባለፈ የተገኘውን ምርት አቅም ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሚያካፍሉም ጠቁመዋል።

የፌደራል ፖሊስ ፀጥታውን በማስከበር የልማቱ አጋር በመሆን ከማህበረሰቡ ጋር በመተጋገዝ ሌሎችንም ያላግባብ እየባከኑ ያሉ መሬቶችን በመለየት ለማልማትም በእቅድ መያዛቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ሙሳ ተናግረዋል።

      ሰብለ አክሊሉ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

04 Nov, 12:11


መሀበረሰቡ አይነታቸውን ከሚቀያይሩ የስርቆት የወንጀል ድርጊት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ተገለፀ።

ደሴ- ጥቅምት 25/2017/ደሴ ፋና/የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ አይነት የማጭበርበርና የማታለል ድርጊቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱን ገልጿል።

ሞባይል ንጥቂያ፣ ማታለል እና ማጭበርበር፣ ቤት ሰብሮ ስርቆትን ለመከላከል ፖሊስ መሀበረሰቡን ባሳተፈ መልክ የቁጥጥር ስራን እየሰራ ነው።

ኮማንደር አበብባው አሻግሬ የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ለጣቢያችን እንደተናገሩት አካባቢያቸውን ከወንጀል ድርጊት ነፃ ያደረጉ እንደ አየር ጤና እና አረብ ገንዳ ቀበሌዎች ተሞክሮአቸው የተሻለ እንደሆነ አንስተዋል።

ወንጀልን በጋራ መከላከል እና አካባቢን ነቅቶ መጠበቅ ላይ የተሻለ ልምድ ያላቸውን አካባቢዎች በሁሉም የከተማዋ ቀጠናዎች ለማስፍት ይሰራል ብለዋል።

እሸቱ ወ/ሚካኤል

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

04 Nov, 11:54


በ2016 ዓ.ም ከነበረው የ73 በመቶ የንፁህ መጠጥ ውሀ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማሳደጉን የአማራ ክልል ውሀና ኢነርጅ ቢሮ ገለፀ።

ደሴ- ጥቅምት 25/2017/ደሴ ፋና/የአማራ ክልል ውሀና ኢነርጅ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ እንዳሉት በ2016 ዓ.ም 900 የሚሆኑ የውሀ ተቋማት መገንባታቸውን አንስተው በዚህም ከ450 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማደረግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም የክልሉን 73 በመቶ የነበረውን የውሀ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ያነሱት ምክትል ቢሮ ሀላፊው ከ10ሺህ በላይ የሚሆኑ የተበላሹ የውሀ ተቋማትን ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ተደርጓልም ሲሉ ገልፀዋል።

በውሀው ዘርፍ በርካታ አጋር አካላት ተሳትፏቸው ከፍተኛ እንደነበርም ተነስቷል።

በ2017 በጀት አመትም በወረዳ ደረጃ የሚገነቡ 800 የሚሆኑ የውሀ ተቋማት እንዳሉ የተናገሩት አቶ ጥላሁን በዚህም የደረስንበትን የ75 በመቶ የውሀ ሽፋን ወደ 78 የማድረስ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ስንታየሁ አራጌ

Dessie Fana FM /ደሴ ፋና ኤፍ ኤም 96.0

04 Nov, 10:16


በ2016 ዓ.ም 68.4 በመቶ የንፁህ መጠጥ ውሀ ሽፋን ማድረሱን የደቡብ ወሎ ዞን ውሀና ኢነርጅ መምሪያ ገለፀ።

ደሴ- ጥቅምት 25/2017/ደሴ ፋና/የመምሪያው ተወካይ ሀላፊ አቶ ፍሰሀ ዘውዱ 139 ሺህ የህብረተሰብ ክፍል የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በ2016 ዓ.ም 329 አዲዲስ የንፁህ መጠጥ ውሀ ግንባታዎችን መከወናቸውን ያነሱት አቶ ፍሰሀ በዚህም ከ68 በመቶ በላይ የውሀ ሽፋናቸውን ማሳደግ መቻላቸውን አንስተዋል።

እነዚህን ተቋማት ለመገንባት ከ187 ሚለየን ብር በላይ ወጭ መደረጉን ገልፀው በ2017 በጀት አመት ደግሞ ለአዳዲስ የውሀ ግንባታዎች እና ለጥገና ወደ 45 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።

እስከ አሁን 13 ወረዳዎች የግዢ ስራን የፈፀሙ ሲሆን ቀሪ 7 ወረዳዎች ደግሞ በቀጣይ ግዜያት የግዢ ስርአት ለመፈፀም ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ ያነሱት አቶ ፍሰሀ በዚህ አመት 406 አዳዲስ የውሀ ተቋማትን ለመገንባት እቅድ መያዙን ጠቅሰዋል።

በኢነርጅው ዘርፍ በዚህ አመት ከ350 በላይ ባዮ ጋዞችን ለመገንባት እቅድ መያዙን እና ከ500 ሽ እስከ 1 ሚሊየን ብር ወረዳዎች የራሳቸውን በጀት ይዘው ወደ ስራ እንደገቡና ማህበረሰቡም አማራጭ ኢነርጅን ለመጠቀም ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑም ተነስቷል።

ስንታየሁ አራጌ