Min Addis? @min_ddis Channel on Telegram

Min Addis?

@min_ddis


ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ሚዛናዊ ፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ወሬዎች የሚለቀቁበት የኢንፎቴይንመንት ቻናል ነው

Min Addis? (Amharic)

ምን ማን? እስካሁን በኦትፎ አፓ በተክሌው ጽሁፍ መመሪያ በምንጭ ትዕዛዝ እና አስደናቂ ነገር፣ መማሪያቸውን ከተቀበለው ፍያል ይልቁ ወደ ትምህርትም ካለ የሚከተሉ ሰምናዊ እና ተናላይ ሃምሌ ያገኙት መሳሪያ ቻናል። ይህ ቻናሉ በቀጣይ ገጽ ውስጥ በመተናል የተቀናጀ ኢንፎቴይንመንት የመጀመሪያ ውይይት ይደረጋል። የሚቀጥለው ወሬዛ ውጤቶቹ፣ የሃምሌ እና የመንፊስ ዕቅድ ልዩነቶች እንዲደረግ እና እንከታተል የሚኖሩ እና የተወካ ውርስናዎች፣ አረፍተነገርና የሡሌፍ ቃላት፣ የሚዛን ስርዓቶች እና እንዲጠቃቀሙ የሚፈሩ ውሳኔ ናቸው።

Min Addis?

20 Nov, 17:59


እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ትኩሳት😢
የትውልዱ ዝቅጠት ግን የት ላይ ነው ማብቂያው⁉️
@min_ddis

Min Addis?

20 Nov, 11:47


«በስመአብ ብለህ እረ*ደው»‼️
ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው በስመአብ ብለህ እረ*ደው የሚለው አሰቃቂ ቪዲዮ በርካቶችን አስቆጥቷል፣ አሳዝኗል እንደ ሀገር ከጊዜ ወደ ጊዜ ጨካኝ እንደሆንን ያሳየ ነው።
ሰው የሆነ ሰው እንዴት የራሱን አምሳያ በስምአብ/ቢስሚላሂ/ብሎ በቢለዋ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ እንደበግ ያ*ርዳል?
@min_ddis

Min Addis?

19 Nov, 07:53


ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ሊጀምር ነው

የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ በሚል ማስተላለፍ የጀመርነው ተወዳጁ ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘው ተከታታይ ፊልም በብዙዎቻችሁ የተወደደ መሆኑን አይተናል።

ኮርፖሬሽኑ ይህንን ስራ የባለቤትነት መብቱን ጠብቆ ካቆየው ዋልታ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ፊልም የመስራት መብቱን በሕጋዊ መንገድ በመግዛት የደራሲውን ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ሕልም ሊያሳካ በሚያስችል፣ ክብራቸውን እና የተመልካቹን ፍላጎት በጠበቀ መልኩ ከፍተኛ ወጭ በመመደብ ፊልሙ እንዲሠራ አድርገናል።

ይህ እንደ ብሔራዊ ጣቢያ ታሪክ ሰንዶ የማቆየት፣ የማስተላለፍ እና የማሳደ ይህንን የሕግ፣ የሞራል እና ሀገራዊ ሓላፊነታችንን እየተወጣን ባለንበት ወቅት የክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ ወራሽ ነኝ በሚሉ ሰዎች የፊልሙን መተላለፍ በፍርድ ቤት እንዲታገድ አድርገዋል።

ተቋሙ የደራሲውን ሥራ በወጋየሁ ንጋቱ ትረካ ከፍ ያደረገ እና በዚህም በይፋ ደራሲው ያመሰገኑት ተቋም ነው። አሁንም የደራሲውን ህልም የሚፈታ እና በህጋዊ እና እውቅና ባለው ይሁንታቸው የተላለፈውን መብት መነሻ በማድረግ ፊልሙን ለእይታ አብቅተናል።

ይሁንና አሁን የተከሰተው አይነት ጉዳይ ሲያጋጥም ችግሩን በሕግ አግባብ መፈታት አስፈላጊ በመሆኑ በፍርድ ቤት ስንከራከር ቆይተን እግድ የሰጠው  ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ሲያይ ቆይቶ ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ክርክሩ በስር የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲታይ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰጠው እግድ እንዲነሳ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መነሻ  በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የፍቅር እስከመቃብር ፊልም በኮርፖሬሽኑ የመዝናኛ ቻናላችን ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚጀምር  መሆኑን አንገልፃለን።
ምንጭ :- EBC
@min_ddis

Min Addis?

19 Nov, 07:39


አየር ላይ ህይወቱ አለፈ!!

ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ

ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣  በበረራ ቁጥር  ET 500 ፣ በAirbus A350 አውሮፕላን ተሳፋሮ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ።

እድሜው ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚገመተው ይህ ተሳፋሪ ከእህቱ አጠገብ አብሮ ቁጭ ብሎ በመብረር ላይ እያለ ፣ አውሮፕላኑ ነዳጅ ሞልቶ እና የበረራ ሰራተኞችን ቀፍሮ ከሮም፣ ጣልያን ተነስቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ እህቱ ለበረራ አስተናጋጆች ወንድሟ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠመው ትነግራቸዋለች፣ የበረራ አስተናጋጆቹም የህክምና ባለሞያዎች ካላችሁ ለእርዳታ እንፈልጋችኋለን ብለዉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ በበረራው ዉስጥ የነበሩ ወደ 5 የሚጠጉ  የህክምና ባለሞያዎች ወደ ግለሰቡ መጥተው ህይወቱን ለማትረፍ ተረባርበው የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ቢሰጡትም ግለሰቡ አየር ላይ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን በበረራ ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመዝናኛ ሚዲያ አስታውቀዋል ።

ምንጭ፡ መዝናኛ መጽሔት ዋሽንግተን ዲሲ
@min_ddis

Min Addis?

18 Nov, 17:56


በመጨረሻም ምክረ ሃሳብ ቀርቧል

Min Addis?

17 Nov, 11:01


በመርካቶ ቃጠሎ ተከስቷል🔥🔥

በመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ የእሳት ቃጠሎ ከቀኑ 6:30 ተከስቷል የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያረጉ ይገኛሉ
@min_ddis

Min Addis?

16 Nov, 06:02


ታይሰን ተሸነፈ

የ58ዓመቱ አንጋፋ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በአሜራካዊው ወጣት ተፋላሚ ጃክ ፖል 79 ለ 73 በሆነ ድምር ውጤት ተሸንፏል።

Via ዳጉ_ጆርናል
@min_ddis

Min Addis?

15 Nov, 18:51


ማይክ ታይሰን እና  ታዋቂው ዩቱዩበር  ጄክ ፓል ዛሬ በቴክሳስ ይገጥማሉ።

ጄክ ፖል 27 ዓመቱ ሲሆን ማይክ ታይሰን ደግሞ 58 አመቱ ነው::
@min_ddis

Min Addis?

15 Nov, 17:47


የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተረፈ

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ  ከቀኑ  8:00   ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

Via መናኸሪያ ሬዲዮ
@min_ddis

Min Addis?

15 Nov, 07:50


በወላይታ ሶዶ የ15 ዓመት ታዳጊዋን ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾ በጽኑ እስራት ተቀጡ

በወላይታ ሶዶ ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የወረዳው ፍ/ቤት አስታውቋል ።ተከሳሾቹ በቁጥር አምስት ሲሆኑ ጉርዛ ጉቡላ፣ጉቴ ጴጥሮስ፣ሙርቴ ሙኩሎ፣ወጣት ጩምቡሎ ጩጩሞ እና  ወጣት ካፍቴ ኢዮና  የተባሉ ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ በወላይታ ዞን በዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ሻላ ጽጾ ትፌ ቀበሌ ክልል ውስጥ ልዩ ሥሙ ጽጾ ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀባቸው ተገልፆል፡፡ የግል ተበዳይ የሆነችው በየነች ሞርካ የተባለች የ15 ዓመት ታዳጊ ስትሆን የጓደኛዋ ሠርግ ቤት ሄዳ ስትመለስ ተከሳሾች ሆን ብለው በቡድን ተደራጅተው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀሙባት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ተከሳሾቹን  ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል በሰውና በህክምና ሰነድ ማስረጃ አደራጅቶ ለአቃቤ ህግ ያቀርባል፡፡አቃቤ ህግም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ፍ/ቤት ያቀርባል።

በዚህም መሰረት የወረዳዉ ፍርድ ቤት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍ/ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በሳምራዊት ስዩም
@min_ddis

Min Addis?

12 Nov, 13:27


ሴት ልጅ ከወለድሽ ከቤት አባርሻለው ተብያለው ያለችው እናት ገና የወለደቻትን ህፃን መፀዳጃ ቤት ውስጥ ብትጥላትም በህይወት ተረፈች

ድርጊቱ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ መጠለያ በተባለ አካባቢ ትላንት ሰኞ ህዳር 2 ከቀኑ 10 ሰአት ከ45 ላይ ተፈፅሟል።

ገና የተወለደች ህፃን ከመፀዳጃ ቤት በህይወት ማውጣታቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ህፃኗን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመፀዳጃ ቤት ሲያወጡ የህፃኗ እናት እና አባት እራቅ ብለው ይከታተሉ እንደነበርም ለማወቅ ችለናል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ጉዳዩን ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አባትየው ሁለት ሚስቶች ያሏቸው ሲሆን ከሁለቱ ሚስቶች 12 ልጅ ወልደዋል። ከአሁኗ ባለቤታቸው 7 ልጆች ያሏቸው ሲሆን ይህችኛዋ ህፃን 8ኛ ልጅ መሆኗን እና ባሏ ለእናትየው ሴት ልጅ ከወለድሽ ከቤት አባርሻለው  እንዳላት መናገሯን አቶ ንጋቱ ለብስራት ገልፀዋል። በአሁን ወቅት ወላጅ እናት ስትወልድ የወለደቻት ሴት መሆናን ስታይ መፀዳጃ ቤት ውስጥ መጨመሯን ተናግራለች። ከከተተቻት በኃላ የልጅቷን ለቅሶ ከመፀዳጃ የሰሙ የአካባቢው ሰዎች ለኮሚሽኑ የአደጋ ባለሙያዎች ጥሪ አድርሰዋል።

በስፍራው ጥሪ ደርሶቸው የተገኙትን የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ቡድን መሪ የሆኑት  ነፃነት ጡጉማን ከብስራት ጋር ባደረጉት ቆይታ ባለሙያዎቹ ልጅቷን ከመጸዳጃ ቤት ለማውጣት የነበረው ቆይታ  አስቸጋሪ የሆነባቸው ሲሆን እግራቸው ተይዘው ወደ መፀዳጃ ቤት ጉድጓድ ተዘቅዝቀው ህፃኗን በህይወት እንድትወጣ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። ህፃኗን ከመፀዳጃ ቤት ለማውጣትም 45 ደቂቃ መፍጀቱን አክለዋል። በሰአቱ ወላጅ እናት እና አባት ራቅ ብለው ይከታተሉ እንደነበር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን የተናገሩት ነፃነት ህፃኗ በተጠቀለለችበት ጨርቅ የማን እንደሆነች ያረጋገጡት የአካባቢው ሰዎች ጥቆማ በመስጠታቸው እናትየው ልትያዝ መቻሉን ገልፀዋል።

በተያዘችበት ወቅት ባለቤቴ ሴት ልጅ ከወለድሽ ከቤት አባርሻለው ስላለኝ ድርጊቱን ልፈፅም ተገድጃለው ስትል ተናግራለች።  ገና የማጠባው ሌላም ልጅ አለኝ ስትል መናገሯን ብስራት ሰምቷል። ህፃኗ በመልካም ጤንነት ላይ የምትገኝ ሲሆን ህክምና ተደርጎላት ለአበበች ጎበናም የህፃናት ማሳደጊያ ተሰጥታለች።እናት እና አባትም ፖሊስ ይዞ ምርመራ እያደረገባቸው ይገኛል።

በትግስት ላቀው
@min_ddis

Min Addis?

11 Nov, 07:31


ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች መኖራቸው ተገለጸ‼️

ብሔራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ጸጋይ ብርሀነ ለአል ዐይን እንዳሉት ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ለ187 ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎት አድርጓል ብለዋል።

አሁን ላይ ማዕከሉ በሳምንት እስከ ሶስት በዓመት ደግሞ እስከ 100 ሰዎች ድረስ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የመስጠት አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶክተር ጸጋይ በግብዓት እጥረት ምክንያት በአቅሙ ልክ እየሰራ እንዳልሆነም ገልጸዋል።

የአካል ልገሳ ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው የሚሉት ዶክተር ጸጋይ ኩላሊታችንን መሸጥ እንፈልጋለን፣ ኩላሊታችንን ግዙን የሚሉ ዜጎች ወደ ማዕከሉ እንደሚመጡም አክለዋል።
Via:አልአይን
@min_ddis