ትክክለኛ ዋጋህ ትክክለኛ ቦታ ነው የሚገኘው።
አንድ አባት ከሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ልጁን እንዲህ ሲል ተናገረው
"ይህ የእጅ ሰዓት አባቴ በውርስ የሰጠኝ ነው፤ ከ200 ዓመታት በላይ የቀየ ነው አባቴም ከአባቱ የትሰጠው ነው። ነገር ግን እኔ ላንተ ከመስጠቴ በፊት ሂድ እና ሰዓት ቤቶች ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቀህ ብቻ ና።" አለው።
ልጁም በመጀመሪያ የሄደው የተበላሸ ሰዓት የሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር ጠይቆ መጣ እና በንዴት በብስጭት "አሮጌ ስለሆነ 5 ብር እንገዛሃለን" እንዳሉት ነገረው።
አባቱም ድጋሚ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ጋር ሄዶ እንዲጠይቅ ይነግረዋል። ልጁም ጠይቆ ይመጣ እና አሁንም ከ50 ብር በላይ እንደማይገዙት ይነግረዋል።
የመጨረሻ ልላክህ ብሎ "ሙዚየም ሄደህ ጠይቅ" ይለዋል አባቱ። ልጁም ጠይቆ ከመጣ በኋላ ደስታ የበዛበት ድንጋጤ ውጦት ትንፋሹ እየተቆራረጠ "አባቴ አንድ ሚሊዮን ብር እንደሚገዙኝ ነገሩኝ እኮ" አለው።
አባቱም መልሶ "ልጄ እንድታውቅ የፈለኩት የአንተንም ትክክለኛ ዋጋ (ቦታ) የሚሰጥህ ትክክለኛ ቦታ ላይ እንድትገኝ እንጂ የተሳሳተ ቦታ ላይ ሄደህ ሳይሳካልህ ሲቀር እንድትናደድ እንድትበሳጭ አይደለም። ምንጊዜም ያንተን ዋጋ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ዋጋ፣ ክብርና አድናቆት የሚሰጡህ ስለዚህ የተሳሳተ ቦታ ላይ አትገኝ!!
✨ውድ እቃ ያለ ቦታው ርካሽ ነው።✨
ከወደዱት ሼር እንዳይረሳ
@Mom_is_My_Hero