ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

@wadan_gurage_cup


👉ስፖርት የወጣቶች ስብዕና ከመገንባት በተጨማሪ የማህበረሰቡ የወንድማማችነት እሴት ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል፤ ስፖርት የዜጎች አእምሯዊ፣ አካላዊ፣ ስነልቦናዊ ብቃት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና አለው፤ ስፖርት ከመለያየት ይልቅ የመቀራረብ፣ከመጣላት ይልቅ የመፈቃቀር ኃይል አለው፡፡
👉 https://www.facebook.com/profile.php?id=100063561467671

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

01 Jun, 18:47


https://www.tiktok.com/@wadanibro/video/7375607605517143301?_r=1&u_code=dm6camb9346hc5&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e90e5gm2154lh9&share_item_id=7375607605517143301&source=h5_m&timestamp=1717267635&user_id=7040828192534774790&sec_user_id=MS4wLjABAAAA8eiGoot_hJQPECtEGG4AN5m_omMVrPvPpUx2OlV_q1U37oDdij68m5chdDsIWTcZ&social_share_type=0&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7373305364924417797&share_link_id=06ddbb54-3fed-43c8-9a01-2f636a6f83f9&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&enable_checksum=1

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

17 May, 18:28


ቀን 9/2016አ.ም❗️

1ኛው ተወዳጁን ዋዳን ሰንደይ ካፕ ውድድር ለመጀር መቃረባችንን የሚታወቅ ሲሆን እሁድ ግንቦት 18/2016አም ጦርሀይሎች ወረዳ 9 በሚገኘው አዳራሽ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ የዘንድሮ የዋዳን ሰንደይ ካፕ የተሳታፊ ቡድኖችን ተወካይ ባሉበት ውይይት ካደረግን ከአንድ ሳምንት በኋላ ግንቦት 25/2016አ.ም የመክፈቻ ጨዋታዎች በማድረግ የመጀመሪያውን አመት የዋዳን ሰንደይ ካፕ ውድድራችን በድምቀት የሚከናወን ይሆናል።

ይህንን ተሳቢ በማድረግ ሁሉም የዘንድሮ የዋዳን ሰንደይ ካፕ ተሳታፊ ቡድኖች በሙሉ በየ ቡድናችሁ ሁለት ሁለት ሰው እንድትልኩልን  ዘንድ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።

#በተጨማሪም..❗️❗️
የዘንድሮ 4ኛው ዋዳን ጉራጌ ካፕ  በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡን የሚታወስ ሲሆን የረቡዕ እና የአርብ ፆም በተጀመረበት በሁለተኛ ሳምንት በተቋረጠበት ለማስጀመር ዘርፈ በዙ ስራዎችን እየተሰሩ ሲሆን የዋዳን ጉራጌ ካፕ ተወዳዳሪ ቡድኖች ከወዲሁ ወደ ቅድመ ዝግጅት እንድትገቡ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን።

#ዋዳን_ለተሻለ_ነገ🔥❤️
#ዋዳን_ለዋዳናዊያን❗️❗️

ስፖርት ለጤንነት፣ ለፍቅር፣ ለአንድነትና ለመዝናናት ነው።

ስፖርት በጥንቃቄና ከስፖርታዊ ህጎች እውቅና ውጭ ከሆነ ገዳይ ነው።

ስፖርታዊ ዳኝነት በሁለቱም ወገን ጨዋነትና ፍትህን በማገናዘብ የሚከናወን ሲሆን ማህበረሰባችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ መድረክ መሆን ይችላል።

ስፖርት የወጣቶች ስብዕና ከመገንባት በተጨማሪ የማህበረሰቡ የወንድማማችነት እሴት ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ስፖርት የዜጎች አእምሯዊ፣ አካላዊ፣ ስነልቦናዊ ብቃት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና አለው።

ስፖርት ከመለያየት ይልቅ የመቀራረብ፣ ከመጣላት ይልቅ የመፈቃቀር ኃይል አለው፡፡

👉ያሰባሰበን እግር ኳስ ነው፤ ፍቅራችን፣ አንድነታችን፣ መከባበራችንና መደማመጣችን እሩቅ አልመን እሩቅ እንድንደርስ የረዱን ዋናዎቹ መሳሪያዎቻችን ናቸው።

👉https://t.me/wadan_gurage_cup

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

27 Mar, 03:12


😭የሀዘን መግለጫ ! 😭
ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን በሞት አጣች!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ በተጨዋች አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀን ለቤተሰብ ለወዳጅ፣ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው ለኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 20:24


ከደቂቃዎች በፊት የስድስት ተጨዋቾች ዝውውር ያጠናቀቀው ሳሬም እግር ኳስ ቡድን የአንድ ተጨዋች ዝውውር በመጨረስ ወደ ስብስባቸው የቀላቀልዋቸው የአዲስ ተጨዋቾች ቁጥር ሰባት አድርሰዋል።

1,ሀሰን አብድላ
2,ዳዊት አድራው
3,በረከት ዘውዱ
4,ሚኪያስ አበራ
5,ዳንኤል ግርማ
6, ፉዓድ ጥላሁን
7,አ/ሠላም

👉ጌታ ቋንጤ
1, አብራር አወል

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 20:05


መጋቢት 5/2016 አ.ም ልክ ለሊት ስድስት ሰዓት ሲል የሚዘጋው የዋዳን የሁለተኛ ዙር የተጨዋቾች ዝውውው ከመዘጋቱ በፊት ሳሬም እግር ኳስ ቡድን ስድስት ተጨዋቾችን ወደ ስብስባቸው መቀላቀል ሲችሉ በተመሳሳይ ጌታ ቋንጤ እግር ኳስ ቡድንን የአንድ ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 13:18


ጉራንዳይ እግር ኳስ ቡድን አራት ተጨዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ጉራንዳይ እግር ኳስ ቡድን ሲሳይ ብሩ፣ ኢፋ መንግስቱ፣ ራሞስ መሀመድ እና ቶማስ ትግስቱን ማስፈረማቸውን አረጋግጠዋል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 13:07


ፎያዲ ንቦቹ የመኑር ደሊልና የዳዊት ፍቅሬን ዝውውር በማጠናቀቅ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 12:59


ወገሬት እግር ኳስ ቡድን የሶስት ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።

በዚህ መሠረት የወገሬት እግር ኳስ ቡድን ዮናታን ደረጄ፣ ተስፋዬ ገብሬ፣ ታደለ እርስቱን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

14 Mar, 12:53


ዛጎራ እግር ኳስ ቡድን የሁለት ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።

ከ15 ቀናት ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ የሚዘጋው የዋዳን የሁለተኛ ዙር የተጨዋቾች ዝውውር በመጠቀም ዛጎራ እግር ኳስ ቡድን አሊ አደምና አሸናፊ ሰለሞን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ዋዳን ጉራጌ ካፕ_wadan gurage cup⏳️

01 Mar, 22:51


ገነት ደያስ ቸሩ በልሁን ሰሞኑን የተከፈተው የተጨዋች ዝውውር ተጠቅመው አዲስ ተጨዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።