ኢስላማዊ ትምህርቶች @eslamawi_tmhrt Channel on Telegram

ኢስላማዊ ትምህርቶች

@eslamawi_tmhrt


«ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ።»
👉እስላማዊ ሀዲስ
👉መራኪ ግጥም
👉ጠፋጭ አስተማሪ እውነተኛ ታርክ
👉አዝናኝ ቀልዶች ይለቀቃሉ
ወደ ግሩፕ ለመግባት https://t.me/Eslamawi_group
ለአስተያየት
@islamawi_tmhrt_Bot
👆👆በዝህ start ካሉ ቡሃላ አስተያየት ፃፉልኝ

እስላማዊ ትምህርት (Amharic)

እስላማዊ ትምህርት የተለያዩ ትምህርቶችን ማስተማር እና ማድረግ እንዲሆኑ ከሰይፉ ጋር ጠቀምና የሚገኙትን የአገልግሎት ጉግልሽ ለመቀሌ በመሆን ነው። ይህ ተቆጣጠር ግባ በሚቆጠረው ቡሃላ አገልግሎት ይግባኝ እና እስራትን በመውሰድ እስከ ግሩፕ ማድረግ ይችላሉ። የግሩፕ ላይ እንዴት ሁኔታውን ለማድረግ እንጠቀማለን ፣ ምሽት እና ፈጠር በትክክል እንደሚጠቀም የሚወርዱትን ትምህርቶች ከሚከተሉ አዝናኝ ቀልዳቸውን ማድረግ ይችላሉ። ይህንን ተጨማሪ ትምህርት ለማድረግ እና ገና ሊገርም እንደሚፈጥር መልእክት የሚመከርን በተለያዩ ፕሮመትን በመጠቀም ማገልገል ይችላሉ።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

26 Dec, 07:29


እኔ መቼ ወደ አላህ (ሰ ወ) እንደሚሄድ አላውቅም
ስለዚህ ዱንያ ማለት አሁን ያለንበት ግዜ ናት
ያለፈው አልፈዋል
ተስፋ የምናደርገውም ግዜ የማይታወቅ ነው
አሁን ያለህበት ግዜ ብቻ ነው አንተ ያለህ

ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብሏል :- በአካሉ ጤናማ የሆነ የነገ በማህበረሰቡ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ (ስጋት የሌለበት) ለአንድ ቀን የሚሆን ምግብ ያለው ሰው ዱንያ ሁሉ በእርሱ እጅ  የታያዘች ያህል ነው
t.me/Eslamawi_tmhrt
https://t.me/Eslamawi_tmhrt

ኢስላማዊ ትምህርቶች

11 Dec, 13:59


እናሸንፋቸው!!!

ወደፊት ለመሄድ ስትሞክር ወደኋላ ለመጎተት አንተን ለማደናቀፍ  ይተቹኋል, ይስቁብሀል, አይሆንም ብለው  ሊያቆሙህ ይታገላሉ ያለህን በሙሉ እንደሌለህ አድርገው ያሳጡሀል ነገር ግን ሁሉም ምቀኛ ስለሆኑ አይደለም!

የሚወዱህም ሰዎች ከመንገድህ የሚያስቀሩህ አሉ እንዳትጎዳባቸው በመስጋት ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ ልንገርህ እነዚህን ሁሉ አልፈህ የሄድክ ዕለት ድል ያንተ እና ያንተ ብቻ ትሆናለች!!!

ያኔ ወደኋላ ዞረህ የመጣህበትን መንገድ እያየህ ትገረማለህ ለሌሎችም ትልቅ ትምህርት ትሆናለህ!
t.me/Eslamawi_tmhrt
t.me/Eslamawi_tmhrt

ኢስላማዊ ትምህርቶች

02 Dec, 08:01


እንመን!!

አላህን ከጠየቅከው እመነው " አንኳኩ ይከፈትላችሁዋል እሹም ታገኙታላችሁ " ብሎ ቃል ገብቶልናልና ከጠየቅነው በኋላ እምነታችንን ሙሉ ለሙሉ በእርሱ ላይ ጥለን ራሳችንን ከጭንቀት ነጥለን መኖር መጀመር አለብን!

ጠይቆት አለማመን አላህን መጠሪጠር ነው ታማኝ አምላክ ነው የያዝከው  አትጠራጠር እመነው!!!

t.me/Eslamawi_tmhrt

ኢስላማዊ ትምህርቶች

30 Nov, 18:00


አንድ ሰው ከሀሊል ጂብሪልን እንዲህ ስል ጠየቀው ከሰው ልጅ በጣም የሚገርመው ነገር ምንድነው ?

እርሱም እንዲህ አለ:- ሰዎች ልጅነት ይደብራቸዋል ለማደግ ይቸኩላሉ ከዛ እንደገና ልጅ መሆን ይናፍቃሉ .... ገንዘብ ለመሰብሰብ ጤናቸውን ያባክናሉ ከዛ ጤናቸውን ለመመለስ ያወጣሉ ... ስለወደፊቱ ይጨነቃሉ የዛሬውን ይረሳሉ የዛሬውን አይኖሩም የወደፊቱን... እንደማይሞቱ ሆነው ይኖራሉ እንዳልኖሩ ሆኖ ይሞታሉ

t.me/Eslamawi_tmhrt

ኢስላማዊ ትምህርቶች

29 Nov, 19:48


በአላህ ተደገፍ!!!
ህይወትህን የሚቀይረው ከሰው ጠብቀህ የምታገኘው ነገር አይደለም፤ ፀጋው፣ ስጦታው፣ ቸርነቱ ከማያልቀው ከፈጣሪህ ከምታገኘው በረከት ነው ህይወትህ የሚቀየረው።

ወዳጄ በጭራሽ ከሰው እንዳጠብቅ፤ ሰው ማለት ሸንበቆ ነው የሆነ ቀን መቀንጠሱ አይቀርም! ከፈጣሪ ቀጥሎ ራስህን እመነው!!!

https://t.me/Eslamawi_tmhrt

ኢስላማዊ ትምህርቶች

04 May, 08:48


የኛስ አሻራ የታለ!?

ሁድሁድ - በባዕድ አምልኮ ተሰማርተው ለነበሩ የሰበእ ህዝቦች መስለም ምክኒያት ሆኗል፡፡

ጉንዳን - የነቢዩ ሱለይማን ግዙፍ ሰራዊት ትናንሽ ፍጥረታት ላይ አደጋ እንዳያደርስ አቅጣጫ አስቀይሯል፡፡

ቁራ - ንፁህ ነፍስ አጥፍቶ መላ ጠፍቶት ሲዋትት የነበረውን የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአቀባበር ሥርኣትን አስተምሯል፡፡

ዝሆን - የአላህን ቤት ከዕባን ለማፍረስ በተንቀሳቀሰው ጦር ላይ በማመጽ ከአምባገነኖች ጋር ለመተባበር አሻፈረኝ ብሏል፡፡

ዓሳ ነባሪ - በህዝባቸው ተበሳጭተው ከጨለማው ባህር ዉስጥ ለተጣሉት ለአላህ ነቢይ ዩኑስ (ዐ.ሰ.) መጠለያ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ሸረሪት - ድሯን በመተብተብ ታላቁን ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ.) ከጠላት ዐይን ጠብቃለች፡፡

እኮ የኔና ያንተ አሻራ የታለ…
‹በላጩ ሰው ለሰው ጠቃሚ የሆነው ሰው ነው፡፡› ይላሉ የአላህ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ.)

ኢስላማዊ ትምህርቶች

21 Apr, 09:11


عيد مبارك🌙⭐️🕌🕌
كل عام وانتم بخير

تقبل الله منا ومنكم صالح الٔاعمال
اعاده الله عالينا جميعا بالٔيمان ولبركات

ኢስላማዊ ትምህርቶች

04 Apr, 06:49


{ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَخُونُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ وَتَخُونُوٓاْ أَمَٰنَٰتِكُمۡ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ }

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ፡፡"
አንቀጹን መላልሰን እናስተንትን እስቲ።

አላህን እና መልዕክተኛዉን የካድንባቸው ቦታቸው አይጠፉንም መቸስ።
ክህደት በሶላት
ክህደት በፆም
ክህደት በዘካት
ክህደት በንግግር
ክህደት ሐራምን በመዳፈር
ክህደት እምነትን በማጉደል
ክህደት ኃላፊነትን ባለመወጣት
ክህደታችን መች ተቆጥሮ ያልቅና ...

የአላህ እና የመልዕክተኛው ትዕዛዛት በሙሉ ለኛ የተሰጡን አደራዎች ናቸው። እነርሱን አለመወጣት ክህደት ነው።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

30 Mar, 02:27


ተግብር ⑧
ጌታህን የምትማፀንበትና በፊቱ የምታለቅስበት ጊዜ ይኑርህ! ይህ ቀልብህ እንዲስተካከል ጠቃሚ ነገር ነውና።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

29 Mar, 08:30


ረመዷን (7)

በረመዷን ሱሑር ከቀመሱ በኋላ የሱብሒን ሶላት መጠባበቅ ለብዙዎች እጅግ ከባድ ነው። ግና ሰዓቱ ወሳኝ የኢስቲግፋር፣ የዚክር እና የዱዓ ሰዓት ነው።

በረመዷን ከሱብሒ በኋላ የሚተኙት እንቅልፍ ሲበዛ ጣፋጭና አጓጊ ነው። ግና ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክር እያደረጉ ቁርኣን እየቀሩ ቁጭ ማለት ትልቅ ምንዳ አለው።

ረመዷንን በዓመት አንድ ወር ብቻ ነው፣ በአግባቡ እንጠቀምበት ።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

28 Mar, 18:08


ረመዷን (6)
**

መስገዳችን ዓላማ አለው፣ መቆማችን ዓላማ አለው፣ ጎንበስ ቀና ማለታችን ዓላማ አለው፣ መራብ መጠማታችን ዓላማ አለው፣ መድከም መዛላችን ዓላማ አለው።
ዋናው ዓላማችን የፈጠረንን አምላክ ዉዴታ ማግኘት ፣ እሱ ለመልካም ባሮቹ ያዘጋጀዉን ጀነት መውረስ ነው።

አምላካችን ሆይ የቻልነዉን ያህል ልንታዘዝህ ደፋ ቀና እያልን ነው። በእዝነትህ ተቀበለን፣ ዉዴታህን ሸልመን።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

26 Mar, 18:09


ፆም ማሰርና መፍታት ለአላህ መታዘዝ ነው። አላህም የሚታዘዙትን ይወዳል። ፆመኛ ፆም ከያዘበት ጀምሮ እስኪያፈጥር ባለው ጊዜ ዉስጥ ዱዓው ተቀባይነት አለው። ፆም ማሰርያና መፍቻው (ሱሑርና ፍጡር) ላይ የሚደረግ ዱዓም ተቀባይነት አለው። በቀኑም በሌቱም ክፍለጊዜ ከዱዓ አትዘናጉ። ረመዷን በዓመት የሚመጣ ዕድል ነው።

ኢስላማዊ ትምህርቶች

26 Mar, 18:08


ኢስላማዊ ትምህርቶች pinned «የረመዷን ወርቃማ ዕድሎች   በረመዷን ወር ውስጥ የሚገኙት ኢማናዊ ዕድሎች በርካታና ምቹ ናቸው፡፡  ብልህ ሰው ማለት እነኚህን አላህን የሚገዛባቸዉን አጋጣሚዎች፣ በረከት የሚዘንብባቸውን ባለመልካም መዓዛ ወቅቶች በአግባቡ ይጠቀማል፡፡ አነስ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲሥ፣ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “መልካም (ነገሮችን) ጠይቁ፡፡ የአላህን ሥጦታዎች ለመቀበል እራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ በእርግጥ አላህ…»

ኢስላማዊ ትምህርቶች

25 Mar, 04:57


የረመዷን ወርቃማ ዕድሎች
 
በረመዷን ወር ውስጥ የሚገኙት ኢማናዊ ዕድሎች በርካታና ምቹ ናቸው፡፡  ብልህ ሰው ማለት እነኚህን አላህን የሚገዛባቸዉን አጋጣሚዎች፣ በረከት የሚዘንብባቸውን ባለመልካም መዓዛ ወቅቶች በአግባቡ ይጠቀማል፡፡
አነስ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲሥ፣ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “መልካም (ነገሮችን) ጠይቁ፡፡ የአላህን ሥጦታዎች ለመቀበል እራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ በእርግጥ አላህ ለሻው ሰው የሚያድላቸው ከእዝነቱ የሆኑ ሥጦታዎች አሉት፡፡ አላህን ለምኑ ነውሮቻችሁ እንዲደብቅላችሁና ለዛችሁን ጠብቆ እንዲያቆይላችሁ (ለምኑት)” (ጦብራኒ)
አቡ-ዘር (ረ.ዐ) እንዲህ ይሉ ነበር፡- “ሰዎች ሆይ! በእውነት ልምከራችሁ፡፡ ለመቃብሮች የብቸኝነት ኑሮ፣ በሌሊት ጨለማ ውስጥ ስገዱ፡፡ ለትንሳኤው ቀን መጨናነቅ፣ ዱንያ ውስጥ እያላችሁ ፁሙ፡፡ ያን የጭንቅ ቀን ፈርታችሁ መፅውቱ፡፡”
አል-አስወድ ኢብን የዚድ ፆም ያበዛ ነበር፡፡ አንድ ዓይኑ እስክትጠፋ ድረስ ያዘወትር ነበር፡፡ “አካልህን ለምን ይህን ያህል ታስቃያለህ?” ተብሎ በተጠየቀ ቁጥር “ዘላለማዊ ረፍቱን ፈልጌ” በማለት ይመልስ ነበር፡፡
ዓሚር ኢብን አብዲ ቀይስ ይህችን ዓለም ተለይተው የሚጓዙባት የመጨረሻዋ ሰዓት የቀረበች ጊዜ አለቀሱ፡፡ ምን አስለቀሰዎት? ተባሉ፡፡ እንዲህ የሚል መልስ ሰጡ፡- ያለቀስኩት ሞትን ፈርቼ አይደለም፣ ለመኖር ጓጉቼም አይደለም፡፡ ነገር ግን በፊ-ሰቢሊላህ ጉዞ ላይ ከሚኖረው ጥማት፣ ከቀዝቃዛው ወቅት የሌሊት ሶላት መለየቴ ነው የሚያስለቅሰኝ፡፡
አንድ የአላህ ወዳጅም እንዲሁ፣ ከሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ጊዜ በኃይለኛ ፍርሃት ተዋጡ፣ ተንሰቅስቀው አለቀሱ፡፡ ይህን ሁኔታቸውን የተመለከቱ ሰዎች ለምን? ብለው ሲጠይቋቸው እንዲህ በማለት ተናገሩ፡- “ፆመኞች ለአላህ ብለው ሲፆሙ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ ሰጋጆች ለአላህ ብለው ሲሰግዱ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ፣ አወዳሾች ለአላህ ብለው አምላካቸውን ሲያወድሱ ከነሱ ውስጥ ባለመሆኔ፣ እንጂ በሌላ አይደለም ያለቀስኩት፡፡ ይኸው ነው የሚያስለቅሰኝ፡፡”
በረመዷን ወር ውስጥ የሚገኘው የመፆም ዕድል በሌላ በምንም ነገር ሊለወጥ የማይችል እድል ነው፡፡ ከረመዷን ውጭ ሌሎች በርካታ የፆም ዓይነቶች ወይም የመፆሚያ አጋጣሚዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ ነገር ግን ልቡ በኢማን የተሞላና በእርግጠኝነት የተዋበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሌላው ሰው አይሳካለትም፡፡ ተሳክቶለት ቢፆምም አያሳምረውም፡፡ የረመዷን ፆም ግን ግዴታ ነውና ሁሉም ይፆመዋል፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳንዱ ሰው አስተካክሎና አሟልቶ ይፆመዋል ማለት አይደለም፡፡ አንዱ ግለሰብ ከሌላው ግለሰብ በልባዊነቱ ይለያያል፡፡ በዚህ ምክንያትም ነው፣ ምንዳው ከኔ ብቻ ነው በማለት አላህ ወደ ራሱ ያስጠጋው፡፡
የረመዷን ወር አላህን በመፍራትና ነፍስን በመቆጣጠር ራስን ማሳደግ የሚቻልበት ትልቅ እድል ይፈጥራል፡፡ ከሁሉም በላይ አሸናፊ የሆነው ጌታ፣ የፆምን ከፍተኛና ምጡቅ ዓላማ እንዲህ በማለት በእርግጥ ወስኗል፡-
 “እናንተ ያመናችሁ ሆይ!  ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ፥ በናንተም ላይ ተጻፈ፥ (ተደነባ)፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡”   (አል-በቀራህ፡ 183)
አላህ ይዘንላቸውና! ሸይኽ አሰ-ሰዕዲይ ከላይ የተጠቀሰውን አንቀፅ በመንተራስ፡- “በዚህ አንቀፅ ውስጥ አላህ ለባሮቹ ስለሰጣቸው ትልቅ ፀጋ ይናገራል፣ በቀደምት ህዝቦች ላይ ግዴታ እንዳደረገው ሁሉ በነሱም ላይ ግዴታ ማድረጉን፣ ይህን ያደረገበት ምክንያትም በየትኛውም ዘመን ለሚኖሩ ፍጡራኑ ጥቅም ሊል ከደነገጋቸው ህግጋትና ትዕዛዛቱ መካከል አንዱ ፆም በመሆኑ ነው፡፡” ብለዋል፡፡


ከ “የረመዳን ትርፋማ ስምምነቶች እና ወርቃማ እድሎች”
ዝግጅት፡- ዶ/ር በድር አብዱልሐሚድ  እና ዶ/ር ሙሐመድ ራቲብ አን-ናብሉሲይ
ትርጉም እና ጥንቅር፡- ዐብዱልከሪም ታጁ

ይቀጥላል …

ኢስላማዊ ትምህርቶች

23 Mar, 06:57


Baby tras and sufra
Contact 09 40 05 26 30

ኢስላማዊ ትምህርቶች

18 Mar, 07:04


ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይህ ወሰለም በረመዷን መምጣት ሶሐቦቻቸዉን ያበስሩ ነበር።
እንኳን ደስ አላችሁ፣ የተከበረው የረመዷን ወር መጣላችሁ።

4,019

subscribers

80

photos

10

videos