Falcon Grade 10 2017 E.C @falcongrade5 Channel on Telegram

Falcon Grade 10 2017 E.C

@falcongrade5


Falcon Academy grade 10 channel is dedicated to grade 10 students and their parents to send worksheets and exchange info

Falcon Grade 10 2017 E.C (English)

Welcome to Falcon Academy grade 10 channel! If you are a grade 10 student or a parent looking for resources to support your child's education, then this channel is for you. The Falcon Grade 10 2017 E.C channel, with the username @falcongrade5, is dedicated to providing worksheets, study materials, and information exchange specifically for grade 10 students of the 2017 Ethiopian calendar. At Falcon Academy, we understand the challenges that students face during their educational journey. That's why we have created this channel to serve as a valuable resource for grade 10 students and their parents. Whether you are looking for practice worksheets, study guides, or simply want to connect with other students and parents to exchange information and support, Falcon Grade 10 2017 E.C channel has got you covered. By joining our channel, you will have access to a community of like-minded individuals who are also committed to academic excellence. You can stay updated on the latest educational news, get tips on how to improve your study habits, and access a wide range of resources to help you succeed in your academic endeavors. Additionally, parents can also benefit from the channel by staying informed about their child's education and getting involved in their learning process. So, if you are a grade 10 student or a parent of a grade 10 student, don't miss out on the opportunity to join Falcon Grade 10 2017 E.C channel. Let us support you on your educational journey and empower you to achieve your academic goals. Join us today and be part of a supportive community that is dedicated to helping you succeed in grade 10 and beyond!

Falcon Grade 10 2017 E.C

08 Jan, 07:52


ውድ የፋልከን አካዳሚ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች
በቅድሚያ የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ ነገ ሐሙስ ጥር 1/5/17 ዓ.ም መደበኛው መማር ማስተማር የሚቀጥል ሲሆን ተማሪዎች አስፈላጊውን ቁሳቁስ አሟልታችሁ እንድትገኙ አሳስባለው። መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ኪዳኔ ብርሃኔ (ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል የስራ ሒደት መሪ)

Falcon Grade 10 2017 E.C

05 Jan, 17:01


ለተከበራችሁ ወላጆች
ነገ ተማሪዎች እስከ 6: 00 በትምህርት ቤት የሚቆዩ ይሆናል :: በሰአቱ በመገኘት እንድትወስዷቸው እያልን መቅረት በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ ሁሉም ተማሪ በትምህርት ቤት እንዲገኝ እናሳስባለን::

Falcon Grade 10 2017 E.C

03 Jan, 12:24


ለፋልከን አካዳሚ ተማሪዎች እና ወላጆች ቅዳሜ 26/04/2017ዓ.ም የchemistry እገዛ ትምህርት ከ2:00 እስከ 5:00 ሰዓት የሚሰጥ በመሆኑ ከ 10A-D ያሉ ተማሪዋችን እንድትልኩልን እናሳስባለን።

Falcon Grade 10 2017 E.C

20 Dec, 18:55


ለፋልከን አካዳሚ ተማሪ ወላጆች
እሁድ ታህሳስ 13/2017ዓ.ም የተማሪዎችን የሩብ ዓመት ውጤት(progress report)
ለወላጆች የምንሰጥ ስለሆነ ሁሉም የተማሪ ወላጅ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ከጥዋቱ2:00-6:00 ድረስ በመገኘት የልጆትን የስካሁን ዉጤት እና የባህርይ ሁኔታ ከወኪል መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ እንዲወስዱ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:-ይህ ፕሮግራም ለልጆት ሁለንተናዊ የትምህርት እንቅስቃሴ እና ለውጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው በእለቱ መቅረት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

Falcon Grade 10 2017 E.C

07 Dec, 06:28


ለፋልከን አካዳሚ ተማሪዎች እና ወላጆች ቅዳሜ 28/03/2017ዓ.ም የchemistry እገዛ ትምህርት እስከ 5:30 የሚሰጥ በመሆኑ ከ 10A-D ያሉ ተማሪዋችን እንድትልኩልን እናሳስባለን።

Falcon Grade 10 2017 E.C

28 Nov, 10:15


ለትም/ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች
ነገ አርብ በ20/03/17 ትም/ት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን ሰኞ መደበኛ ትም/ት የሚጀመር መሆኑን እንገልፃለን።
                                       ትም/ቤቱ

Falcon Grade 10 2017 E.C

24 Nov, 07:20


ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን):-

•  ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
•  አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
•  ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
•  በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
•  ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
•  በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን  ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
•  ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
•  በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

24 Nov, 07:20


በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች
ከህዳር 16-19/2017 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ቤታችን የአጋማሽ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡  የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ውጥረት ለመቆጣጠር :-
ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን :-
•  ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
•  ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ መሆኑን አውቀን በመርሀግብር የተመራ በቂ ዝግጅት ካደረግን የምንፈልገውን ዉጤት ማምጣት እንደምችል በማመን ከት/ቤት መልስ በቤት ዉሥጥ በመምህራን የተሰጡ የመማር ተግባራት / የቤት ስራ፣ የግል ስራ ወ.ዘ.ተ/ በአግባቡ መሰራትና እርማት መውሰድ፤ በተጨማሪም በቤት ዉስጥ ቋሚ የጥናት መርሀግብር ማዘጋጀት እና በተዘጋጀው  መርሀ ግብር መሰረት ጥናት ማከናወን፡፡
•  ማወቅ ያለብን አንድ ነገር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
•  ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
•  የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።

Falcon Grade 10 2017 E.C

15 Nov, 11:28


ከሰኞ 09/03/2017 ዓም ጀምሮ ከላይ በተለቀቀዉ ፕሮግራም መሰረት የመማሪያ ቁሳቁቹን አሟልታችሁ እንድትገኙ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

09 Nov, 10:08


በተመሳሳይ ከታች በሚለቀቀው ፕሮግራም የጥናት ደብተር እና ቁሳቁሶች አሟልታችሁ እንድትገኙ ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

08 Nov, 12:53


ከሰኞ 2/03/2017 ዓም ጀምሮ ከላይ በተለቀቀዉ ፕሮግራም መሰረት የመማሪያ ቁሳቁቹን አሟልታችሁ እንድትገኙ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

26 Oct, 15:31


💠 Modal verbs

🌀 Can
Used to ask ability or request

ማድረግ የምንችለውን ነገር ወይም ፍቃድ ለመጠየቅ እንጠቀማለን

Example: Mike tyson can fight 🤼
▻ Can i have a glass of water

🌀 Could

Used to explain past ability , suggestion , future possibility

Example: Back in my day i could fight a tiger.
▻What could possibly go wrong?
▻In the future cats could have 5 legs

🌀 May

Used to get permission🙋 for future possibility

Example: In the future cats may have 5 legs

🌀 Might

Used to explain present or future possibility

እዚህጋ ማወቅ ያለብን ነገር Mightን የምንጠቀመው ቡዙም እርግጠኛ ላልሆንበት ነገር ነው

Example: in the future cats 🐱🐱 might have 5 legs

🌀 Must

-- Used to talk about necessity or obligation

Example:- I must take my medicine 💉

🌀 Ought to

Used to talk about what is right and correct.

Example: You ought to do exercise more often.

🌀 Shall

Used to give suggestion

Example: What shall we do

🌀 Should

Used To give advice 🗣

Example: You should start sleeping regularly

🌀 Will

Used to talk about willingness , certain prediction and promise

Example: I'm willing to donate blood

▻Pandas 🐼 🐼 will go extinct 💀 by 2050

▻ I will start running.🏃

🌀 Would

-- Used to ask invitations and making arrangements

Example: I would like to get you something to eat

▻I would like that bed a little to the left

Falcon Grade 10 2017 E.C

18 Oct, 12:57


ስልክ ተደውሎ ከተነገራችሁ የተማሪዎች ወላጆች ውጭ ያስገባችሁት ማመልከቻ የሚፈፀመው በዚህ አግባብ ይሆናል።

Falcon Grade 10 2017 E.C

11 Oct, 11:24


ለፋልከን አካዳሚ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች
ከላይ በተላለፈው ፕሮግራም መሰረት ከፊታችን ሰኞ 04/02/ 2017ዓ.ም ጀምሮ የጥናት ትምህርት መሰጠት የሚጀመር ሲሆን ሁሉም ተማሪ በቂ ዝግጅት በማድረግ እንዲገኝ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:
1ኛ፦በደብዳቤ የተላከው መልዕክት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ላሉ ለሁሉም ተማሪዎች የሚያገለግል መሆኑን እንገልፃለን።
2ኛ፦የጥናት ትምህርቱ እስከ 10:30 የሚቆይ ስለሆነ ሁሉም ተማሪ የሚማርበትን ቁሳቁስ ይዞ መገኘት ይኖርበታል።
3ኛ፦እስከ አርብ 01/02/2017 የጥናት ትምህርት ባለመኖሩ የመውጫ ሰዓታችን 9:10 እንደነበረ ይታወቃል በዚህ ወቅት ምሳ የማትይዙ የነበራችሁ ተማሪዎች የምሳ መውጫ ካለቸው ተማሪዎች ውጭ የጥናት ትምህርት እስከ 10:30የሚቆይ ስለሆነ የምትመገቡትን ምሳ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችሗል።
ት/ቤቱ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

04 Oct, 03:08


በቀን 24/01/2017ዓም በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት ትምህርት የሚሰጠው እስከ 6:00 ብቻ መሆኑን እንገልፃለን ።
ት/ት ቤቱ

Falcon Grade 10 2017 E.C

25 Sep, 18:51


ለወላጆቹ እና ተማሪዎች
ነገ በ16/01/2017 ትምህርት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን ማለትም እስከ ቀኑ 6:00 መሆኑን እናሳውቃለን ።
ትምህርት ቤቱ ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

20 Sep, 12:17


ከላይ በተቀመጠው ክፍለ ጊዜ መሰረት ከፊታችን ሰኞ 13/01/2017ዓ.ም ጀምሮ የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማሟላት እንድትገኙ።
ትምህርት ቤቱ ።

Falcon Grade 10 2017 E.C

15 Sep, 04:19


FALCON ACADEMY HIGH SCHOOL
ለውድ የፋ.አ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች
የ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማክሰኞ፣ መስከረም 7፣2017.ዓ.ም ይጀመራል። ትምህርቱም የሚሰጠው ለግማሽ ቀን ይሆናል። ስለዚህ ወላጆች ይህን አውቃችሁ ልጆቻችሁን ከመስከረም 7፣2016ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኩ ስንል እናስታውቃለን።

በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን  ለወላጆች/ሕጋዊ አሳዳጊዎች በተለይም አዲስ ለሆኑት የሚከተሉትን ነጥቦች ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
#  ሁሉም የት/ቤታችን ተማሪዎች ሰደርያ፣ነጭ እጀ-ሙሉ ሸሚዝ፣ ሱሪ ጉልበት ድረስ መሰብሰብ የሚችል እና ለሴቶች ቀሚስ ከጉልበት በታች ዩኒፎርም መልበስ አለባቸው ፡፡ ካለ ት/ቤቱ ዩኒፎርም የሚመጣን ተማሪ ወደ ት/ቤቱ ቅጥር ግቢ የማናስገባ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡
#  ወንዶች ተማሪዎች ፀጉራቸው እኩል ሆኖ ባጭሩ መቆረጥ (መስተካከል) አለባቸው፣ ሴቶች ተማሪዎች ደግሞ ሹሩባ/ ቁጥርጥር መሠራት አለባቸው።
#  ማንኛውንም አይነት ጌጣጌጥ ( አምባር፣ ተንጠልጣይ ጉትቻዎች፣ የአንገት ሃብሎች እና የመሳሰሉትን) እና ኤሌክትሮኒክስ ( ሞባይል፣ ስማርት የእጅ ሰዓት፣ አይ ፓድ እና የመሳሰሉትን) ይዘው መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
ሁሉም ተማሪዎች የተሟላ መጽሐፍት ይዘው መምጣታቸውን ለማረጋገጥ የመግቢያ በር ላይ ፍተሻ ይኖረናል።
#  ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ በቂ ምግብ መያዝ አለባቸው፡፡ እባክዎ በምሳ ዕቃዎቹ ላይ የተማሪዎቹ ስም መለጠፉን ያረጋግጡልን፡፡
#  ወላጆች /ሕጋዊአሳዳጊዎች ተማሪዎች በቂ የሆነ የትምህርት መሣሪያዎች እንዳለው/ላት/ላቸው እርግጠኛ መሆን አለባቸው፡፡
#  ተማሪዎች ወደ ት/ቤቱ በሰዓቱ መምጣት አለባቸው፡፡ልብ ይበሉ የት/ቤቱ በር ከጥዋቱ 1፡00 ጀምሮ ክፍት ሲሆን ትምህርቱ  2፡00 ላይ ጀምሮ 9:10 ሰዓት ላይ ያበቃል፡፡
#  ተማሪዎች መታወቂያ በር ላይ ለአስተዳዳር ሰራተኞች /ለጥበቃሠራተኞች ማሳየት አለባቸው፡፡ ካለ ት/ቤቱ መታወቂያ ተማሪዎች እንዲወጡ  አይፈቀድላቸውም፡፡
ፋልከን አካዳሚ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል የስራ ሂደት

Falcon Grade 10 2017 E.C

13 Sep, 10:22


10G