መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝ @menfesawe12 Channel on Telegram

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

@menfesawe12


+ከተለያዩ ፅሁፎች የተገኙትን መንፈሳዊ ህይወትን የሚሰብኩ ፅሑፎችንና ትምህርቶችን እናካፍላችሁ፡፡

''አንብበን እንለወጥ።''

+መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

https://t.me/menfesawe12+

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝ (Amharic)

በዚህ ህይወት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአማርኛ መንፈሳዊ ህይወትን በመናገር ለመመልከት የሚገኙ የአሁኑ ፅሁፎች ተቀብላቢው። በዚህ ሆነ በበሽታዊ መጥተዋወቀባቸው። እናካፊላቸው፡፡ 'አንብበን እንለወጥ' የተለየ ተልዕኮ ስማ፡፡ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሉ፡፡ በሶስት ቀናት በአገሪቷ በአንድነት እንለዋለን። በዚህ መንፈሳዊ የተደረገ ውጤትና ለማስቀመጥ የሚገኙ እና የሚገኘውም ወረርሽዎች ሀሳብ አሉ፡፡ ይህ መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይህን ፅሁፎ ለዩኒክ ህዝብ በደህና እንጠንክር። ወይም ከተገኙ አስደናቂ ብዙኀል ጠንካራዊ ጉዳይን መምራት በለው።

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Jan, 17:26


✞  ጥር 4 የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል
የወንጌላዊ ዮሐንስ ድንቅ ታሪክን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለዮሐንስ በደረሰለት ውዳሴ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኮከብን ብለን ጠራንህ፤ የጽድቅ ፀሓይ ያሳደገህ ባጠገቡ (በጉያውም) ያስቀመጠህ ኮከብን ብለን ጠራንህ፤ በአፉ የሳመኽ በመታጠቂያውም ያስታጠቀኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፤ የተሰወረውን ምስጢር ያሳየኽ የጸጋውን ወንጌል የሰጠኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፤ ዮሐንስ እንዳንተ ያለ ማን ነው ታማልደን ዘንድ ማለድንኽ።

√ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በዚህ ክፍል ላይ ተጋድሎው ሕይወቱ እንደ ኮከብ የደመቀውን ዮሐንስን አመስግኖታል፤ ይህ ዮሐንስ ቊጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል ሆኖ የዘብዴዎስ እና የሰሎሜ ልጅ ሲሆን በእኛ ትውፊት እናቱን ማርያም ባውፍልያ ይላታል።

√ ጌታችን ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ ዐየ፤ ጠራቸውም እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከትለውታል። [ማቴ. 4፥21-22]

√ ጌታም ኹለቱን ወንድማማቾችን ቦአኔርጌስ ብሏቸዋል፤ ትርጓሜውም የነጐድጓድ ልጆች ማለት ነው። [ማር. 3፥17]

√ ጌታችን ምስጢረ መንግሥትን ለመግለጽ ወደ ታቦር ተራራ ይዞት ወጥቷል፤ በጌቴሴማኒም ምስጢረ ጸሎትን ሲያሳይ ከጌታ ጋር ነበርና "የምስጢር ሐዋርያ" ይባላል።

√ ጌታችን ይወድደው የነበረው ደቀ መዝሙር ርሱ ነውና "ፍቁረ እግዚእ" (የጌታ ወዳጅ) ሲባል በምሴተ ኀሙስም ምስጢረ ቊርባንን ሲመሠርት ከጐኑ የተጠቀመጠው ርሱ ዮሐንስ ነበርና ሊቁ “የጽድቅ ፀሓይ ያሳደገኽ ባጠገቡ ያስቀመጠኽ” ብሎታል፡፡

√ ጌታችን ሲጠራው የ25 ዓመት ወጣት እንደ ነበር ሄሬኔዎስ የተባለ ደቀ መዝሙሩ ጽፏል፡፡

√ ቅዱስ ጳውሎስ “Pillars of the Church- አዕማደ ቤተክርስቲያን” ብሎ ከሚጠራቸው ሐዋርያት አንዱ ዮሐንስ ነው። [ገላ. 2፥9]

[ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅና አውግስጢኖስ ስለ ዮሐንስ ሲመሰክሩ]

√ “ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ መስቀል ድረስ የተከተለ ብቸኛ ሐዋርያ ነውና ጌታም ዮሐንስ ካሳየው ፍቅር ከ100 (መቶ) ዕጥፍ በላይ እናቱን እናት አድርጎ ሰጠው፡፡ ምንኛ የታደለ ሐዋርያ ነው” ይላሉ፡፡ [ዮሐ. 19፥20-27]

√ ጌታችን በጸሎተ ኀሙስ ለደቀ መዝሙርቱ ትሕትናን ሊያስተምር ከእራት በኋላ ተነሥቶ ልብሱን አኑሮ “ወነሥአ መክፌ ዘለንጽ ወቀነተ ሐቌሁ” ይላል ዘርፍ ያላት ዝናር አንሥቶ ወገቡን ታጠቀ ሥራ የምታሠራ የምታስጌጥ ስትኾን ኢዮአብ ወደ ሰልፍ ሲገባ እየለበሳት ይገባ እንደነበረች ያለች ናት፤ ልብሰ መንድያ ይላታል በሺሕ ዘሓ (ድር) የተሠራች ናት።

√ “ወወደየ ማየ ውስተ ንብቲራ ወአኀዘ ይሕጽብ እገሪሆሙ ለአርዳኢሁ ወመዝመዘ በውእቱ መክፌ ዘቀነተ” በመታጠቢያው ውሃ ጨመረ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ ይላል።

√ ይህቺ የታጠቀበትን ለዮሐንስ ወንጌላዊ ሰጥቶት ጌታ በታጠቀበት ቢታጠቅ ሕገ ሥጋ ጠፍቶለታል ፍቁረ እግዚእ ያሰኘው ይኽ ነውና ሊቁ “በመታጠቂውም ያስታጠቀኽ” በማለት አመስግኗል፡፡

√ “በአፉ የሳመኽ” ማለቱ የሮሙ ንጉሥ ጢባርዮስ ቄሳር የጌታን ነገር አይሁድ በግፍ ጠልተው ተመቅኝተው ሰቅለውት እንደሞተ እንደተነሣ እንዳረገ ሰምቶ የጌታዬን እናት ማን ባመጣልኝ እኔ ቋሚ ለጓሚ፤ ሚስቴ ገረድ ደንገጥር በኾንላት ብሎ ተመኘ፤ ተመኝቶም አልቀረ “ወለአከ ኢየሩሳሌም ሰራዊተ ወሐራ ወአዋልደ ብዙኃተ ወኅጽዋነ” ይላል ወደ ኢየሩሳሌም ብዙ ደንገጥሮች ሰራዊትና ጭፍራ እንደዚሁም የሴት ደናግልና ባለሟሎችን በክብር አጅበው ያመጧት ዘንድ ላከ።

√ ጌታም የእናቱን ተድላ ነፍስ እንጂ ተድላ ሥጋን አይሻምና

እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም መንግሥት ክብር የሚበልጥና የሚያስደንቅ የጌትነቴን ክብር ታዪ ዘንድ በጎ ዕረፍት ወዳለበት ወደ ሰማይ አሳርግሽ ዘንድ ተነሥተሸ ቁሚ አላት፤ ከዚያም ወደ ገነት አግብቶ በገነት ላሉ ነፍሳት መድኀኒታችኊ እነኋት ርሷን አመስግኑ ብሏቸው አመስግነዋታል፡፡

በእርሱም ሐዘን እንዳይጸናበት ዮሐንስ ወንጌላዊን ላከለት ከዚያም ንጉሡን ስለ ጌታችን ሥጋዌ አስተማረው፤ ንጉሡም የሚቻልህም ከሆነ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንዳየኸው ሥዕሉን ሥለህ አሳየኝ አለው፤ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እሺ በርሱ ላይ የተፈጸመውን ሁሉ ሥዬ አሳይሆለኊ አለው፤ ከዚያም ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ጌታን እንደሰቀሉት አድርጎ ሣለው።

ብፁዕ ዮሐንስም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕል ሠርቶ ከፈጸመ በኋላ ራሱን ወደታች ዝቅ አድርጎ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ ሥዕል ተሳለመ፤ በዚችም ዕለት የዚሆ ሥዕል ከናፍር ከብፁዕ ዮሐንስ ከናፍር ጋር ለብዙ ሰዓት ተያይዞ ቆየ ይህም ጽንዐ ፍቅራቸውን ለማጠየቅ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የመድኅን ጌታ ሥዕል ንጉሥና በዚያም የቆሙ ሁሉ እያንዳዳንዳቸው እየሰሙት ወዳጄ ዮሐንስ ዮሐንስ እያለ ድምፅ አሰምቷልና ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ይኽነን ተናገረ፡፡

[ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በዚኽ መጽሐፉ ላይ]

የተሰወረውን ምስጢር ያሳየኽ የጸጋውን ወንጌል የሰጠኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ በማለት ለዮሐንስ የተገለጸለትን ሰማያዊ ምስጢር ተናግሯል። ይኸውም ቅዱስ ዮሐንስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት ሰማያዊ የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ተገልጾለት።

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ” እያለ ወንጌሉን ሲጽፍ መልአኩ ከውቅያኖስ አስኳሉ በወጣለት እንቊላል እየቀዳ ውሃውን ሲያፈስስ ዐየው።

ዮሐንስም በአድናቆት ሆኖ “ምን ያደርግልኻል” ብሎ መልአኩን ጠየቀው፤ “ይህንን ውሃ በዚኽ እየቀዳኊ አፍስሼ ለማድረቅ ነው” አለው፤ ዮሐንስም “ያልቅልኻልን” አለው፤ መልአኩም “ይኽስ ፍጡር ነው ቁም ነገር የለውም ይፈጸማል፤ አንተስ የማይፈጸመውን ባሕርየ እግዚአብሔርን እፈጽማለኊ ብለኽ ጀምረህ የለም” አለው፤ ያን ጊዜ ዮሐንስ “ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ” በማለት ወንጌሉን መጻፍ ጀምሯል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ከወንጌል በተጨማሪ ሦስት መልእክታትን ሲጽፍ፤ በ98 ዓ.ም በፍጥሞ ደሴት ሳለ የዓለም ፍጻሜ ነገር ተገልጾለት ራእዩን ከጻፈ በኋላ ጥር 4 እንደተሰወረ ይነገራል፤ የቅዱስ ዮሐንስ በረከት በዝቶ ይደርብን፡፡

ማጣቀሻ
መጽሐፈ ሰዓታት ንባቡና ትርጓሜው ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Jan, 22:06


ሽፍታው በመስቀል ላይ እያለ በአንድ ቃል ፀደቀ፡፡ከሐዋርያት አንዱ ሆኖ ተቆጥሮ የነበረው ይሁዳ ያን ሁሉ ድካሙን በአንዲት ምሽት አጥቶ ከመንግስተ ሰማያት ወደ ሲኦል ወረደ፡፡
ስለዚህ ማንም ሰው ስለ ራሱ መልካም ስራ አይመካ በራሳቸው የሚታመኑ ሁሉ ይወድቃሉና፡፡

አባ ዘንትያስ
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

10 Jan, 11:05


+ የተስፋ ጉንጉን +

በአንድ ዘመን ላይ የተሻሉ የሚባሉት ሰዎች ካማረሩ ችግር በርትቷል ማለት ነው። አዋቂው ስለ እውቀት መጥፋት ከተናገረ፥ አማኙ ስለ እምነት መድከም ካዘነ፥ ሀብታሙ ስለ ኑሮ ውድነት ካነሳ የዘመኑን መክፋት ልክ ያሳያል። ከጌታ ልደት የቀደመውን ዘመን ስንመረምረው፥ እጅግ የከፋ የጨለማ ዘመን እንደነበር የምንገነዘበው “የነቢያት አክሊል” የሚባለው ነቢዩ ኢሳይያስ ስንኳ “ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።” (ኢሳ 64፡6) እያለ ሲያዝን ስናገኘው ነው። ከፈጣሪው ጋር ቃል በቃል የሚነጋገር ነቢይ እንዲህ ካለ፥ ‘ለምዕመኑማ ምን ያህል በርትቶበት ይኾን?’ ያሰኛል።

የሀገራችን ሰው ሲተርት ‘ሲያልቅ አያምር’ ይላል። እውነትም ዘመኑ እያለቀ ነው መሠል፤ ነገሮች ሁሉ እየተበላሹ ነው። ዓለማችን እንደ ሃያኛው እና ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን ስለ ሰላም የጮኸችበት ጊዜ የለም። በዚያው ልክ እንደ እነዚህ ዘመናትም ሰላምን ያጣችበትም ጊዜ የለም። የብዙ ሰው ሕይወት መከራ ተዘርቶ መከራ የሚታጨድበት አውድማ ሆኗል። ጦርነት ባይኖር ስንኳ፤ በልቶ መጥገብ፥ ጠጥቶ መርካት፥ ተኝቶ ማረፍ ያልተቻለበት ሕይወት የቁም ስቃይ መሆኑ አይቀርም። አንዱ የዚህ ማሳያ በተለያየ ምክንያት ራሱን የሚያጠፋው ሰው መበራከት ነው። ‘እገሌኮ ራሱን አጠፋ’ ሲባል፥ አንዳንድ ሰው ‘በራሱ ላይ እንዴት እንዲህ ጨከነ?’ ብሎ ይገረማል። ሰው ሁሉ ነገር ሐዲድ ሲስተበት ራሱን ባያጠፋ ስንኳ ሞቱን ይመኛል። ዘመን ሲከፋ፥ ጊዜ ሲጠም፥ አቅም ሲከዳ፥ የእግዚአብሔር ነቢይ ስንኳ “አቤቱ፥ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና፥ ነፍሴን ውሰድ” (1 ነገ 19፡4) ብሎ ሞትን በፈቃዱ ይጠራል።

እንዲህ ያለን ዘመን ያለ ተስፋ መሻገር አይቻለም። ተስፋ ከመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ የሰው ልጅ ስንቅ ሆኖ እስከዛሬ አለ። አዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን ከመሠለ አባታቸው እና ገነትን ከመሠለ ቤታቸው ሲለዩ፥ እግዚአብሔር “ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔዴን ገነት አስቀመጠ” (ዘፍ 3፡24) ተብሎ ተጽፏል። ሊቃውንት ይኽንን ሲተረጉሙት እግዚአብሔር በመላእክት ያስጠበቀበት አንዱ ምክንያት አዳም "እግዚአብሔር ፈጽሞ ቢጣላኝ ኖሮ ገነትን ለሌላ ይሰጥብኝ ነበር እንጂ በመላእክት አያስጠብቀውም ነበር ብሎ ተስፋ እንዳይቆርጥ ነው" ይላሉ። ተስፋ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው። ዙሪያ ገባችን ሲጨልም ብርሃን እንዳለ የሚያስታውሰን ተስፋ ነው። ሐዘን ሲበረታበን እንደሚያልፍ ሹክ የሚለን ተስፋ ነው። ሰው በብዙ ነገር ‘ክፉ ነው’ ሊባል ይችላል፤ ተስፋን ከሌላው እንደሚነጥቅ ያለ ክፉ ግን በየትም የለም።

ቅዱስ ጳውሎስ “እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ” (1 ቆሮ 13፡13) በማለት ሦስት ጸንተው ከሚኖሩ ነገሮች መካከል ተስፋን ያካትተዋል። ተስፋን ለየት የሚያደርገው ግን ከእምነትም፥ ከፍቅርም ጋር ተገምዶ የሚገኝ በመሆኑ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እምነትን በራሱ “ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ” (ዕብ 11፡1) መሆኑን በመናገር ተስፋን ከእምነት ይገምደዋል። በሌላ መልእክቱ ደግሞ “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ፥ ተስፋ አያሳፍርም።” (ሮሜ 5፡5) ብሎ ፍቅርን ከተስፋ ይገምደዋል። ጠቢቡ “በሦስት የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም” (መክ 4፡12) እንዳለ፤ እምነትን ከተስፋ፥ ተስፋን ደግሞ ከፍቅር ጎንጉኖ የሚኖር አማኝም ክፉ ዘመንን የሚሻገርበትን ብልሃት ይዟል ማለት ነው። ሦስቱም ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ሲሆን ይጸናል። እምነትህን በእግዚአብሔር ላይ ከሆነ፤ ክፉውን ጊዜ ታልፈዋለህ። ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ ካደረግህ፥ በወደቁት መካከል ትቆማለህ። ፍቅርህ ለእግዚአብሔር ከሆነልህ፤ የጽድቅን ብርሃን ትለብሳለህ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ፥ በዚህ ዘመን፤ የሰው ልጅ በስልጣኑ፥ በሀብቱ፥ በትምህርቱ ይቅርና በቆመበት መሬት ላይ ስንኳ ተስፋ ማድረግ እንደማይችል እያየ ነው። በድንግዝግዙ ውስጥ የምናይበት የማይጠፋ ብርሃናችን፥ በመናወጹ ውስጥ የምንቆምበት የማይናወጽ ዐለታችን አንተ ብቻ ነህ። ለአዳም በሐዘን፥ ለኖኅ በቃልኪዳን፥ ለአብርሃም በስደት፥ ለሙሴ በበረሃ፥ ለዮሴፍ በእስር ቤት፥ ለሩት በሰው ሀገር የሰጠኸውን ተስፋ ለእኛም በያለንበት አትንሳን።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

09 Jan, 08:40


‹‹ኦ አንትሙ ሕዝበ ክርስቲያን እለ ተጋባእክሙ በዛቲ ዕለት ከማሁ ያስተጋባእክሙ በደብረ ጽዮን ቅድስት ወበኢየሩሳሌም አግዐዚት በሰማያት᎓᎓››
የክርስቲያን ወገኖች በዚች ዕለት እንደተሰበሰባችሁ፤ ነጻ በምታወጣ በደብረ ጽዮን በመንግሥተ ሰማያት ይሰብስባችሁ።

መልካም የልደት በዓል!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

09 Jan, 08:04


🎁 ደቂቃው ሳይሞላ ኑ ተቀላቀሉ እንዳያመልጣችሁ
🏃🏃👇
Request to JOIN

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Jan, 16:57


‹‹ወልድ ተሰጠን›› (ኢሳ.፱፥፮)

እንኳን አደረሳችሁ!


ነቢየ እግዚአብሔር ልዑለ ኢሳይያስ የታነገረው ይህ ቃል ለጊዜው በምርኮ በጭንቅ ለነበሩ፣ በሰናክሬም ዛቻ፣ በብልጣሦር የግፍ አገዛዝ አስጨንቋቸው ምድራዊ ሕይወታች በመከራ አዘቅት ሰጥሞ ለነበሩት ለእስራኤላውያን ቢሆንም የመከራው ጊዜ አልፎ ከስደት እንደሚመለሱ፣ በተድላ ደስታ የሚኖሩበት መልካም ጊዜ እንደሚመጣ ሲሆንም ፍጻሜው ግን በጽመት አዘቅት ሰጥመው፣ በመከራ ፍኖት ተጉዘው ኑረውም፣ ሞተውም የዲያቢሎስ ምሮኮኞች የሲኦል ግዞተኞች ለነበሩ ለአዳምና ለልጆቹ የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ከዲያሎስ አገዛዝ ከጨለማ ሕይወት እንደሚያወጣቸው የተነበየው ነው:: (ኢሳ.፱፥፮ አንድምታ)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ልዑለ ቃል ነቢየ ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ተውህበ ለነ፤ ወልድ ተሰጠን›› በማለት እንደተናገረው ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወልድ ሲወለድልን የጨለማው የሰው ልጆች ሕይወት በራ፤ ቤተ ልሔም አቅራቢያ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች እስካሉበት ቦታ ድረስ ባሕረ የብርሃን ወንዝ (የብርሃን ጎርፍ) ፈሰሰላቸው፤ በአዳምና ሔዋን በደል ምክንያት በሰዎችና በቅዱሳን መላእክት መካከል የነበረው የጠብ ግድግዳ ፈርሶ፣ ሰላም ተመልሶ ፍቅር ነግሦ በአንድ ላይ ሆነው ምሥጋና የባሕርይው ገንዘቡ ለሆነ ፈጣያቸው በተፈጠሩበት ዓላማ መሠረት አዲስ ምሥጋንን አቀረቡ፡፡ ‹‹መላእክት ከኖሎት ኖሎት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡›› (ሉቃ ፪፥፲፬ አንድምታ)

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Jan, 16:57


ብርሃናውያን መላእክት በጨለማ ላለው አዳምና ልጆቹ ከጨለማ የሚያወጣቸው ወልድ በተሰጣቸው (በተወለደላቸው) ጊዜ ተደስተው ‹‹..ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ፡፡›› (ሉቃ.፪፥፲፫)

ውድ አንባብያን! ይህን የተቀደሰ ዕለት በደስታ፣ በፍቅርና በሰላም እናከብር ዘንድ ከጥልና ከጥላቻ ርቀን፣ በንስሐ ነጽተን፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን፣ በወንድማማችነት ፍቀር ተሰባስበን ይሁን!

መልካም በዓል!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Jan, 01:17


"ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።" ሉቃ 2:11

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Jan, 09:55


+ ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ +

ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት ለማክበር በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከ 8:00 ጀምሮ እንገናኝ!

በቤተክርስቲያኑ ስንገኝ አሥር ጧፎች ይዘን እንምጣ። ሦስቱ በዝማሬው ጊዜ የምናበራቸው ሲሆኑ፥ የተቀሩት ሰባቱ ደግሞ በገጠር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የሚላኩ ናቸው።

የቻለ ሁሉ ደግሞ ከዝማሬው በኋላ በቤተክርስቲያኒቷ በማደር ድንቅ የሆነውን ማኅሌት ይሳተፍ፤ ቅዳሴውንም ያስቀድስ።

#ኑ_በብርሃኑ_ተመላለሱ!
#የአእላፋት_ዝማሬ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Jan, 05:46


+ አንዷን የእንባ ዘለላ ይቀበል ይኾን? +

አባ አንቶኒ ኮኒያሪስ የተሰኙ የግሪክ ኦርቶዶክስ ካህን በጻፉት "ፊሎካሊያ: የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት ቅዱስ መጽሐፍ" (Philokalia: The Bible of Orthodox Spirituality) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ለማስተማሪያነት ያሰፈሩት እንዲህ የሚል አንድ ጥንታዊ አፈታሪክ አለ:-

እግዚአብሔር ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱሳን መላእክቱን "ወደ ምድር ወርዳችሁ ከሁሉ ይልቅ እጅግ ብርቅዬ የሆነውን ነገር ይዛችሁልኝ ኑ" ብሎ ያዛቸዋል::

አንድ መልአክ ሌላ ሰው ለማዳን ብሎ ራሱን መስዋእት ያድረገን ሰው የደም ጠብታን ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ይህ በእኔ ዓይን እጅግ የተወደደ ነው:: በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬ ነገር ግን አይደለም::" አለው::

ሌላኛው መልአክ ደግሞ ሌሎችን ስታስታምም በያዛት በሽታ ምክንያት ያረፈችን የአንዲት ነርስ የመጨረሻ እስትንፋስ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በእርግጥ ስለሌሎች የሚከፈል መስዋእትነት በእኔ ዓይን እጅግ ታላቅ ዋጋ አለው:: ሆኖም ግን በዓለም ያለው እጅግ ብርቅዬው ነገር ይህ አይደለም" አለው::

በመጨረሻም አንድ መልአክ ንስሃ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰን ኃጢአተኛ አንድ ዘለላ እንባ ይዞ መጣ:: እግዚአብሔርም "መልአክ ሆይ ፥ በዓለም ላይ ያለውን እጅግ ብርቅዬ ነገር አመጣህ - ይኸውም የገነትን በር የሚከፍት የንስሃ እንባ ነው!" በማለት ተናገረ::

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር ከአእላፋት ዝማሬ በፊት በብዙ አጥቢያዎች መሐረነ አብ እንዲደርስ ያደርጋል። ሰዎች ጸሎቱን እየተከታተሉ በእንባ "ማረን፥ ይቅር በለን" እያሉ መሐረነ አብን ይጸልያሉ። የአንዳንዱ እንባ ያስደነግጣል፤ ያስፈራልም። የባለፈው ዓመት ዝማሬ ላይ ስንቱ በእንባ እየታጠበ እንደዘመረ መድኃኔዓለም ያውቀዋል። በአእላፋት ዝማሬ ቤተክርስቲያን መጥቶ፥ "ይህቺ ናት ለካ ቤተክርስቲያን!" ያለው እልፍ ነው። በዚያው ትምህርት ተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የገባውም ብዙ ነው! የዚህ ዝማሬ አንድምታው ቀላል አይደለም!

ቅዱስ መድኃኔዓለም ለምህረት ይኾንልን ዘንድ ከሚፈሰው እንባ አንዷን የእንባ ዘለላ ይቀበልልን ይኾን? እርሱ እንደ ቸርነቱ ያድርግልን! ሐዋርያው "ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ" (ፊል 4፡4) ብሎናልና፤ ሁኔታ ሳይገድበን እናመሰግንሃለን! እንዘምርልሃለንም!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

05 Jan, 17:54


የጌታችን ልደት እና የመላእክት አገልግሎት

በዲያቆን አለልኝ ጥሩዬ

ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በዓለም ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ጨለማ ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ኾነ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አማናዊው ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ‹‹ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኵሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፤ በጨለማ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው›› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው (ኢሳ. ፱፥፪)፡፡ ቀዳሚ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው በኾነ ጊዜም ቅዱሳን መላእክት በቤተ ልሔም ተገኝተዋል፡፡ ይህንም ቅዱስ ሉቃስ ‹‹ወግብተ መጽኡ ብዙኃን ሐራ ሰማይ፤ የሰማይ መላእክት በድንገት መጡ›› በማለት ገልጾታል (ሉቃ. ፪፥፲፫)፡፡ በድንገት መባሉም አመጣጣቸው ግሩም በመኾኑ ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ቀድሞ አመጣጣቸው ጻድቃንን ለመርዳት፣ ሰማዕታትን ከስለት ለመታደግ፣ የተቸገረውን ለማጽናት ነበር፡፡
ዛሬ ግን ስለ ሰው ፍቅር ከሰማይ የወረደውን፣ በጎል (በበረት) የተጣለውን፣ በጨርቅ የተጠቀለለውን አምላክ ከሰው ልጅ ጋር በአንድነት ለማመስገን መጡ፡፡ ‹‹ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ፤ ሰውና መላእክት፣ ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑ ዘንድ ተባበሩ›› እንዲል፡፡ መላእክት በተፈጥሯቸው የማይሞቱ (ሕያዋን) ሲኾኑ ሰው ደግሞ ሟች ነው፤ ሞት ይስማማዋል፡፡ በጌታችን ልደት ግን መላእክትና የሰው ልጆች በአንድ ማኅበር፣ በአንድ ቃል ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር›› እያሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ በአዳም ኀጢአት ምክንያት ፈርሶ የነበረው የመላእክትና የሰው ልጆች ማኅበር ከተቋረጠ ከብዙ ዘመን በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ ገና ተጀመረ፡፡ ይህ የምስጋና ኅብረትም ምድር እንደ ልብስ ተጠቅልላ ስታልፍ ወደ ፊት በምትመጣዋ በአዲሲቷ ዓለም፣ በአዲሱ ሰማይ፣ በአዲሱ ቤተ መቅደስ ይቀጥላል (ራእ. ፳፩፥፩-፬)፡፡
አንድነታችን እንደማያቋርጥና በሰማይም እንደሚቀጥል አረጋዊ መንፈሳዊ ሲገልጥም ‹‹እሉሂ ወእልክቱሂ በአሐዱ ኁባሬ አልቦ ማዕከሌነ ወማዕከሌሆሙ፤ በእኛ በደቂቀ አዳም እና በቅዱሳን መላእክት መካከል ልዩነት የለም›› ይላል፡፡ ይህም የኾነው በጌታችን መወለድ ምክንያት ነው፡፡ በጌታችን ልደት ምክንያት እኛም ዳግመኛ ተወለድን፡፡ የጌታችን ልደት የእኛም የክርስቲያኖች ዅሉ ልደት ነው፡፡ ከሦስቱ የቀጰዶቅያ አባቶች (The three Cappadocian Fathers) አንዱ፣ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ይህን ምሥጢር ሲገልጥ ‹‹The nativity of Christ is the birthday of the whole human race – የክርስቶስ ልደት የመላው ሰው የልደት ቀን ነው›› ሲል መስክሯል (Hyman of praise to the mother of God)፡፡
ሊቃውንት እንዳስተማሩን እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት እና ዓለምን ያዳነበት ምሥጢር ከምሥጢራት ዅሉ በላይ ነው፡፡ ይህን ምሥጢር ከማድነቅ ሌላ ሊናገሩት አይቻልም፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በመገረም ይህን ጥበብ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፡፡ ይህን ወዷልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ፷፮፥፲፯)፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም በቅዳሴው የእግዚአብሔርን ሰው የመኾን ምሥጢር እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹በጐለ እንስሳ ተወድየ አሞኀ ንግሡ ተወፈየ ወከመ ሕፃናት በከየ እንዘ ይስእል እምአጥባተ እሙ ሲሳየ፤ በእንስሳት በረት ተጨመረ፡፡ የንጉሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፡፡ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ፤›› (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ቍ. ፲፯)፡፡
በዚህ ታላቅ በዓላችን የምናደንቀው ሌላው ምሥጢር እግዚአብሔር ወልድ በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን፣ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የመወለዱ ረቂቅ ምሥጢር ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህን ድንቅ የሥጋዌ ምሥጢር ግሩም፣ ዕፁብ እያሉ ያደንቁታል፡፡ ሐዋርያውያን አበውን ተከትለው ከተነሡ የቤተ ክርስቲያን ጠባቆች (Apologists) መካከል አንዱ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ፩ኛ የእመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና፣ ፪ኛ ድንግል ማርያም አማኑኤል ጌታን መውለዷ እና ፫ኛ የማይሞተው አምላክ መሞት በእግዚአብሔር የዝምታ ሸማ የተጠቀለሉ ሦስት ምሥጢሮች መኾናቸውን ይናገራል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጸሐፈ አርጋኖን ድርሰቱ ይህን ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር በሚከተለው መልኩ ይገልጠዋል፤
‹‹ሦስቱን ደጆች ያልከፈተ የአብን ልጅ ጥበብ አደንቃለሁ፤ ያለ መለወጥ በኅቱም ድንግልና በመወለዱ፣ የመቃብሩን ደጅ ሳይከፍት በመነሣቱ፣ ደቀ መዝሙርቱ ተሰብስበው ወዳሉበት ቤት በተዘጋ ቤት በመግባቱ እና በሩን ሳይከፍት በመውጣቱ ስለነዚህም ሦስት ደጆች ልቤ አደነቀች፡፡ ከሁለቱ ይልቅ የመጀመሪያው እጅግ ያስደንቀኛል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱን ከዚህ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ አውቃቸዋለሁ፡፡ የመቃብሩን ደጅ የሚመስለው ነገር አለ (ዮሐ. ፳፥፲፱)፡፡ ብልጣሶር የተባለ ዳንኤልን በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ በጣሉት ጊዜ ጕድጓዱን በታላቅ መዝጊያ ዘጉት፡፡ ዳንኤልም በረሃብ እንደ ተጨነቀ ልዑል እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መልአኩን ወደ ነቢዩ ዕንባቆም ላከ (ዳን. ፮፥፲፮-፲፯)፡፡ በራሱም ፀጕር አንሥቶ ተሸክሞ ወስዶ ዳንኤል ወዳለበት ጕድጓድ አገባው፡፡ ዳንኤልና ዕንባቆም እንጀራውንና ንፍሮውን በልተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ዕንባቆምም ደጅ ተዘግቶ ሳለ ወጣ፡፡ ስለ ቤቱ ደጅም የሚመስል ነገር አለ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ ጴጥሮስን ከግዞት ቤት እንዳወጣው በሐዋርያት ሥራ ተጽፏል፡፡ ጴጥሮስንም ካወጣው በኋላ ደጁ ተቈልፎ ዘበኞች በዅሉ ወገን ይጠብቁ ነበር (ሐዋ. ፲፪፥፮)፡፡  ለእነዚህ ለሁለቱ ደጆች ለቅዱሳን የተገኘውን ምክንያት አገኘሁ፡፡ ስለ ድንግልናሽ ደጅ እጠናለሁ፤ ግን ምክንያት አላገኘሁም፡፡ በድንግልና የኖረች ሴትም አላየሁም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ነገር ኾኖ አያውቅም፡፡ ኢኮነ እምቅድመ ዝ ወኢኮነ እምድኅረ ዝ – ከዚህ በፊት አልተደረገም፤ ከዚህ በኋላም አይደረግም፤›› (አርጋኖን ዘቀዳሚት)፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ልደት፣ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የተፈጸመበት በዓላችን ነው፡፡ ለሞት ከመገዛት የዳንበት፤ ጨለማው ተወግዶልን የብርሃን ልጆች የኾንበት፤ የእባብ ራስ የተቀጠቀጠበት፤ ከምድር ወደ ሰማይ ያረግንበትና ከመላእክት ጋር ኾነን ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀረብንበት፤ ከነቢያት ኅብረት ጋር አንድ የኾንበት በዓል ነው፡፡ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመበትን ይህን ልዩ በዓል በመንፈሳዊ ሥርዓት ማክበር ይገባናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

#ማህበረ_ቅዱሳን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

04 Jan, 18:36


ሰንበት ትምህርት ቤት
ይህ ተቋም ትልቅ ነው…………………..
•  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቅኖና፣ እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይበረዝ ሳይከለስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የሚያደርግ ተቋም ነው፤
•  ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ምእመን የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅና እንዲረዳ የሚያደርግ ተቋም ነው፤
•  ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተምረው ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ፣ መልካምና በሥነ ምግባር የታነፁ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያደርግ ተቋም ነው፤
•  በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ (መክ. ፲፪፡፩) የሚለውን የአምላክ ተእዛዝ ወጣቶች እንዲፈጽሙ የሚያስችል ተቋም ነው፤
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መልእክት ሲያስተላልፉ
“ ሰንበት ትምህርት ቤት የቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ ትውልድ የሚፈራበት ትልቅ ተቋም ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በመጠበቅ እና በማስጠበቅ ለማስቀጠል በዚህ ዘመን ሰ/ት/ቤቶች  መጠናከር፣ ማደግ መስፋፋት እና አንድነት በጣም አስፈላጊ እና ተመሳሳይ አገልግሎት በሁሉም ቦታ ሥርዓቱን ጠብቆ ለማድረስ የሚረዳ በቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ ተሰጥቶት በሁሉም የቤተ ክህነት መዋቅር የሚሠራበት ግዙፍ መዋቅር ነው፡፡ ለዚህም ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካል በሙሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ድጋፍ እና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ” የሚል መልእክት አስተላለፉ፣ በመሆኑም ሁላችንም ይህንን ትልቅ የነገዋ የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ተስፋ የሆነውን ተቋም ልንከባከበው እና ልንደግፈው ይገባል፡፡

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

03 Jan, 07:09


ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 06:32


🌸የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ምሳሌ 10፥7🌸

ልደቱ ለአቡነ ተክለሐይማኖት
ታህሳስ 24 በዚህች እለት  በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስቅዱስ” ብለው ሥላሴን ያመሰገኑ ሐዋርያዊ መነኩሴ የወንጌል ገበሬ ሰዳዴ አጋንት የህሙማን ፈውስ የብዙዎች አባት የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ልደታቸው በታላቅ ክብር የሚከብርበት ታላቅ እለት ነው።💒

  የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው ፍጹም የሆነ ቃልኪዳናቸው አትለየን አሜን!!

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 06:03


በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም። ኃጢአትን ከፈጸሙና ከሠሩ በኋላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኃጢአት ነው። በዚህ አይነት ለኃጢአቱ ምክንያት እየደረደረ የሚጽናና ሰው ኃጢአትን እየለመደ ወደ ባሰ አዘቅት ከመውረድ በቀር ንስሐ ለመግባት አይችልም። ምንም ምክንያት ቢደረድር ኃጢአት ምን ጊዜም ኃጢአት ነውና። ለሠራነወ ኃጢአት የተለያዩ ምክንያቶችን በማበጀት ራሳችንን እያጽናናን ነፃ ለመሆን መጣር የለብንም ።

ስለ ሰሩት ኃጢአት ምክንያትን የደረደሩ አዳምና ሔዋንም ባቀረቡት ምክንያት ከመቀጣት አልዳኑም ። እግዚአብሔርም አዳም ስለ አቀረበው ምክንያት "የሚስትህን ቃል ሰምተኻልና ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዘዝኩህ ዛፍም በልተኻልና " በማለት ለኃጢአቱ የሚገባውን ቅጣት ሰጠው እንጂ አልተወውም። [ዘፍ3፥17] ይባስ ብሎ በእነርሱ ምክንያት በመጣው መርገም ቅጣቱ በትውልዳችን ሁሉ ሆነ እንደ እነርሱ ሁሉ እኛም ዘወትር ምክንያት በመደርደር ከኃጢአታችን የተነሣ ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ የምንሞክር ሆንን ስለዚህ ንስሐ ለመግባት በጣም ስንቸገር እንታያለን ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 13:03


🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Dec, 07:16


በኃጢአት የጎሰቆለው አዳም የሚታደስበትን ዜና ሊያበስር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

ንጹሕ ለሆነው ሙሽራ የተገባች አዳራሽ ትሆነው ዘንድ መመረጧን ሊያበሥራት መልአኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

ከኃጢአት ንጹሕ የሆነው መልአክ በደል ወዳልተገኘባት ንጽሕት ድንግል ተላከ፤

የፀሐየ ጽድቅን መምጣት ያበሥር ዘንድ ብርሃናዊው መልአክ ተላከ፤

በአባቱ እቅፍ ያለው አንድያ ልጅ በእናቱም እቅፍ እንደሚሆን ያበሥር ዘንድ መልአኩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፤

እንኳን ለበዓለ ብሥራት በሰላም አደረሰን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Dec, 07:09


ብስራተ ገብርኤል
ታህሳስ 22 ቀን በቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት ብስራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብስራቱን የነገረበት ቀን ነው፤ እንዴት ብስራቱንማ የነገራት መጋቢት 29 ቀን ካሉ ትክክል ነው፤ ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡ ታዲያ ዛሬ ለምን እናከብረዋለን ካሉ ምክንያቱ እንዲህ ነው፤ ምንግዜም ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር ነው በዚህ በዓቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን፤ ለቅሶ፤ ጾም፤ ጸሎት እንጂ ደስታ፤ ፌሽታ እልልታ፤ ጭብጨባ የለም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው ታቦት አውጥቶ በዓል ማክበርም ስህተት ነው ፍትሃ ነገስት አንድምታ አንቀጽ 15 ተመልከት ፤ ታዲያ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ዓይነት ስርዓት ሰሩ የመጋቢት 27 ስቅለቱን ጥቅምት 27 ቀን እንዲሁም የመጋቢት 5 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍት ቀን ወደ ጥቅምት 5 ቀን ዞሮ እንዲከበር አደረጉ፡፡ የመጋቢት 29 ብስራቱን ደግሞ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ ደቅስዮስ ይባላል በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ታአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Dec, 07:09


የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብስራቱ መከበር አለበት ብሎ ስርዓት ሰራ አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ እመቤታችን ተገለጸችለት ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ እንዳከበርከኝ እኔም አከብርሃለው አለችው፤ ሰማያዊ ልብስና ሰማያዊ ወንበር ሰጠችው ይህችን ልብስ ካንተ ሌላ ማንም አይለብሳትም ይህችንም ወንበር ካንተ ሌላ ማንም አይቀመጥባትም አለችው፡፡
የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱ ታህሳስ 22 በዛሬዋ ቀን ነው፡ ከእርሱ በኃላ ሌላ ኤጲስ ቆጶስ ተሾመ ልብሱን እለብሳለው በወንበሩም እቀመጣለው አለ ተው ይቅርብህ እመቤታችን እንዲህ ብላ ተናግራለች ይሉታል እርሱም ሰው እኔም ሰው እርሱም ኤጲስ ቆጶስ እኔም ኤጲስ ቆጶስ ብሎ በትዕቢት ልብሱን ለበሰው በወንበሩም ተቀመጠ ክፉኛ አወዳደቅ ወደቀ ሞተም ይህን ያዩ እመቤታችንን በጣም ፈሯት ይላል ተአምረ ማርያምን ላይ፡፡ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች፤ በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Dec, 06:36


+ መቃብራችን ምን ይላል? +

በሁላችንም ሕይወት ውስጥ ወደድንም ጠላንም የምንቀበለው አንድ እንግዳ አለ። ይህ እንግዳ ‘ላይህ አልፈልግም’ ብለው የሚደበቁት አይደለም። ይህ እንግዳ ‘ዛሬ የለም፥ ነገ ተመለስ በለው’ ብለው ሰው ልከው የሚሸኙት አይደለም። ይህ እንግዳ ‘ሒድልኝ፥ ከቤቴ ውጣልኝ’ ብለው የሚያዋርዱትም አይደለም። እርሱ ‘በዘገየ’ እንጂ ‘በቀረ’ የማንለው ከባድ እንግዳ ነው። ይህ እንግዳ እንደሌላው አስተናግደው የሚሸኙት ሳይሆን ሁሉን ጥለው ወደመጣበት የሚከተሉት ልዩ እንግዳ ነው። ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፥ እውቀት ያለው በእውቀቱ፥ ውበት ያለው በውበቱ ሊደልለው አይችልም። ‘ተወለደ’ የተባለለት ሰው ሁሉ ‘ሞተ’ ሊባልለት በውዴታ ግዴታ ይቀበለዋል። ስሙ ማን ይባላል? ምዕራባዊያኑ ‘ሁሉን እኩል አድራጊ’ የሚሉት፥ ዐረቦቹ ‘የእንቅልፍ ታላቅ ወንድም’ ብለው የሰየሙት ሞት ነው!

ሞት የተባለ እንግዳ መጥቶ ለጎበኘው ወዳጃችን የምንሰጠው የመጨረሻ ስጦታ ለቅሶ እና የመቃብር ድንጋይ ነው። ለቅሶው ጊዜያዊ፥ የመቃብር ድንጋዩ ዘላቂ እንደሆነ ይታሰባል። ታዲያ ወዳጅ ሲሞት የመቃብር ድንጋዩ ሕይወቱን ያንጸባርቃሉ በተባሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያሸበርቃል። ሕይወቱ ከፋም ለማም፥ የአንዱ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ” (2 ጢሞ 4፡7) የሚል ይጻፍበታል። የሌላዋ “በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው” (ራእ 14፡13) የሚል ይኖርበታል። የሌላው ደግሞ “ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ” (ፊል 1፡23) ይለናል። እነዚህን እና መሠል ጥቅሶችን ሁሉም ያለ አድልዖ ይጠቀምባቸዋል። 

መቃብራችን ስለ ሕይወታችን እውነቱን ቢናገር ኖሮስ? የመቃብር ድንጋያችን ባይዋሽ ስለ ሕይወታችን ምን ይል ነበር? 

እግዚአብሔርን በመፍራት እና በማገልገል ኖረን፥ መቃብራችን “የእግዚአብሔር አገልጋይ የሁሉ ወዳጅ ሆኖ አለፈ” ይል ይኾን? “መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” (ማቴ 25፡21) የሚለውን ጥቅስ እናገኝበት ይኾን? 

በዓለም ላይ በመዳከር ሕይወታችንን አሳልፈን፥ መቃብራችን “ኹሉ አለኝ እያለች፥ አንዳች ሳይኖራት ተሸኘች” ይል ይኾን? “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?” (ማር 8፡36) የሚለው አሳዛኝ ጥቅስ ተጽፎበት እናገኝ ይኾን? 

ኑሯችንን በስስት እና በስግብግብነት አሳልፈን፥ መቃብራችን “እርሱን እንዳትመስሉት፤ ትምህርት አድርጉት እንጂ!” ይል ይኾን? “በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ ወዮላችሁ!” (ማቴ 23፡25) የሚለው ጥቅስ ይኖርበት ይኾን? 

ዛሬ ብንሞት፥ ነገ መቃብራችን ምን ይል ይኾን? መቃብራችን ባይዋሽ፥ ምን ተጽፎበት ይገኝ ይኾን? 

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Dec, 04:18


⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች
┗━━━━━━━━━━━━━━┛


እና የሁሉንም የቅዱሳን አባቶች ትምህርት ማወቅ ከፈለጉ የቁልፍ 🔐 ምልክቱን ይጫኑ 👇

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Dec, 06:45


✞ ‹‹ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ! አምላክን በሥጋ የወለድሽ ከልጅነቴ ጀምሮ ተስፋዬ፣ አምባዬ፣ መጠጊያዬ፣ ጉልበቴ፣ የመመኪያዬ አክሊል፣ ክብሬ፣ ገናንነቴ ሆይ.......

✞ በክርስቲያን ሥርዓት ጠብቂኝ፡፡
✞ በክርስቲያን ሃይማኖት አጽኚኝ፡፡
✞ ክርስቲያን አድርጊኝ፡፡
✞ ክርስቲያን ልባል፣
✞ በክርስቲያንነትም ልኑር፡፡
✞ ልጅሽም በአባቱ ምስጋና በክበበ ትስብእት በመንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ፡፡››
#አርጋኖን_ዓርብ

https://t.me/kanbebnew

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

28 Dec, 21:56


https://vm.tiktok.com/ZMkkUNLa6/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

28 Dec, 21:56


"እግዚአብሔር አምላክ እንዳዘዘኽ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አክብረው፡፡" ዘዳ ፭:፲፪

መልካም ዕለተ ሰንበት

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

27 Dec, 13:22


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

27 Dec, 13:22


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7፡፡ ይህ ኃይለ ቃል የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን በሚፈሩት ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ. 1፡14፡፡

ታህሳስ 19 ቀን በዚህች ቀን ሠለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው እቶን እሳት ያድነናል" ያሉበት ዕለት እና ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።

የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን!
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

27 Dec, 10:11


"ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጦም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጦም ጦምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፡21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ  ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጦምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡

(ቅዱስ ኤፍሬም)

https://t.me/menfesawe12
https://t.me/menfesawe12
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

27 Dec, 06:07


በቲክ ቶክ መተናል አገልግሎቱን ፎሎው ላይክ ሼር በማድረግ እንድትደግፉ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን🙏🙏🙏

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

27 Dec, 06:03


https://vm.tiktok.com/ZMkkUNLa6/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

26 Dec, 11:45


ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ3ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ አንድ የሚያስገርመኝ ዜኖ የሚባል ፈላስፋ ነበር። ይህም ሰው ከዕለታት በአንዱ ቀን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ ድንገት ወደቀና ጣቱ ክፉኛ ተጎዳ። ከዚያም ከወደቀበት ሳይነሣ በእጆቹ መሬቱን እየመታ “እየመጣሁ ነውና እኔን ለመጥራት መድከምህ ከንቱ ነው” ሲል የአንድ ባለ ቅኔን ንግግር ተናግሮ እዚያው ራሱን አፍኖ ገደለ።

አትላንቲክ ውቅያኖስ አካባቢ የሚኖሩ Celts የሚባሉ ወገኖችም ነበሩ። እነዚህ ሰዎች ሞትን መፍራትን እንደ ትልቅ ውርደት አድርገው ስለሚያስቡ ትልልቅ ጥፋት የሚያመጡ ነገሮችን ሳይቀር ፊት ለፊት ይጋፈጡ ነበር። ለምሳሌ ቤቱ ሊያፈርስ ቢያዘምባቸው ወይም ግድግዳው ሊናድ ቢንደረደርባቸው ሮጠው ከዚህ አደጋ ለማምለጥ አይሞክሩም። በውቅያኖስም ውስጥ ሆነው ማዕበል ቢቀሰቀስ ወደ ኋላ አያፈገፍጉም። እንዲያውም ወጀቡ እስኪያልፍ ባሉበት ሳይንቀሳቀሱ ይቆማሉ። ሞትን ፈርተው ሸሹ እንዳይባሉ እነዚህን አስፈሪ ነገሮች ያደርጋሉ።

“ሕይወት” እግዚአብሔር የሰጠን ትልቁ ስጦታ ነው። እርሱ በቀጠረው ጊዜ እስኪጠራን ድረስ አለመታገስ የዚህን ስጦታ ዋጋ አለመረዳት ነው። እውነተኛ ጀብድ በዚህ አስቸጋሪ ዓለም ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ፈተናዎች ሁሉ ታግሎ ለማሸነፍ እስከ መጨረሻዋ ሕቅታ ድረስ መፋለም እንጂ ቀድሞ ሩጫ ማቋረጥ አይደለም። አንድ ክርስቲያን ሞትን እንደማይፈራ ማሳየት ያለበት “ሕያው የሚያደርገውን” የክርስቶስን ሥጋ እና ደም በመቀበል እንጂ ራሱን ለሞት በማጋለጥ መሆን የለበትም።

“ማምሻም ዕድሜ ነው” እንደሚባለው አይደለም በወጣትነት በሽምግልና ዘመን የቀረች ጥቂት ቀን እንኳ ታሳሳለች። ምክንያቱም ከመሰንበት ንስሐ መግባት፣ መጸጸት፣ መመለስ፣ የኋላውን ትቶ የፊትን ለመያዝ መዘርጋት አለና።


ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

26 Dec, 05:31


ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

26 Dec, 04:08


💁‍♀ ጥያቄ 3⃣
===========


🔴 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ለዘላለም ምን አይሆንም ነው ያላት

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

25 Dec, 09:36


 በእግዚአብሔር ቤት እና ለእግዚአብሔር የኾነ አገልግሎት

አገልግሎትን የሚቀድመው እግዚአብሔርን በትክክል ማወቅና እግዚአብሔርን መውደድ ነው። እግዚአብሔርን ለማወቅ እርሱን መስማት ያስፈልጋል። እርሱን ለመስማት በቃሉ እግር ስር መቀይመጥ ይጠይቃል። ለመቀመጥ ፈቃደኝነት ይጠይቃል። ለፈቃደኝነት ውሳኔ ይጠይቃል። 

ብዙ ሰው በገንዘቡም በእውቀቱም በጉልበቱም ለቤተ ክርስቲያን ያገለግላል። በእግዚአብሔር ቤት ማገልገል ይሉታል። በጥንቃቄ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። 
መጽሐፍ ቅዱስ በአድን ጊዜና ቦታ በተለያየ ዘርፍ ያገለገሉ እኅትማማች ታሪክ ጠቅሶ ግልጽ አድርጎታል። ማርያምና ማርታ ናቸው። ታሪካቸውን ቅዱስ ሉቃስ እንዲኽ መዝግቦታል :- 

ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው።  ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች።  ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።  ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥  የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” ሉቃ.10:38 

ጌታ የገባው ማርታ ቤት ነው እኅቷ አብራ ነበረች። ማርታ ጌታን ለማስተናገድ የተጣደፈችው ቶሎ ነው። የሚበላ መክተፍ ማብሰል የሚጠጣ ማቅረብ ቤቷን ማስተካከል ማጽዳት  ያዘች። ብዙ ደከመች። ልብ በሉ ይኽ ሁሉ ግን ለጌታ መስተንግዶ ነው። 

ማርያም ደግሞ  መሬት ላይ እግሩ ስር ቁጭ ብላ ዐይኗን አንጋጣ የሚናገረውን ትሰማለች። ምንም አትናገርም ዝም ብላ መስማት ብቻ። ድንገድ ማርታ ሲደክማት የእኅቷን እገዛ ፈልጋ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።” 

ጌታ በምላሹ “ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥  የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” ይላል። 

በጉልበት ከኾነ ብዙ የለፋችው ማርታ ነበረች። የተመሰገነችው ግን ማርያም ናት። ይልቁንም ማርታ ተነቀፈችበት። ምክንያቱ ምንድነው? 

፩. አገልግሎት የሚጀምረው ተቀምጦ ከመማርና የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ኾነ ከማወቅ ይጀምራል። እንዴት ኾኜ ማገልገል አለብኝ፣ በእውነቱ አገልግሎስ ምንድነው? መቀደስ? መዘመር፣ ከበሮ መምታት…. ምንድነው? እንዴት ኾኜ ባገለግል ነው እግዚአብሔር ደስ የሚሰኘው? ብሎ መወቅ። 

በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እያገለገልኩ ነው ወይስ የቤቱን ባለቤት እያገለገልኩ ነው? አብዛኛው በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አገልጋይ ነው። ይሮጣል ይደክማል፣ ያጸዳል፣ ማእድ ያዘጋጃል፣ ኮሚቴ ኾኖ ይሠራል። ነገር ግን የቤቱ ባለቤት የሚለውን ሰምቷል? የቤቱን ባለቤት ይታዘዘዋል? በትክክልስ ያውቀዋል?። 

ይኽንን ለመረዳት በጥቂቱ እንሞክር። የማገለግለው አገልግሎት ለመዳን ወይም ሌላው ሰው በመዳን መንገድ ይጠቀማል ወይ ብሎ መጠየቅ። ለመዳን ካላገለገለ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እያገለገለ እንጂ እግዚአብሔርን እያገለገለ አይደለም። 

መዝሙር አጥንተው የቀረቡ ወጣቶች ዛሬ አትዘምሩም ቢባሉ ወይም አንድ መዝሙር ቀንሱ ቢባሉ ምን ይላሉ? ቤተክርስቲያን ውስጥ ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ይከፍታሉ። ይኽ ከአገልግሎቱ ቀድሞ በጌታ እግር ሥር አለመቀመጥ ምልክት ነው። 

በበዓል እኔ ካልቀደስኩ እኔ ካልሰበኩ ብሎ ከተሽቀዳደመ፣ እኔ ድምጻዊ ነኝ እስቲ ዛሬ ልቀሽረው እያለ የሚቀድስ ዲያቆን ካህን በእግዚአብሔር ቤት ይለፋል ለእግዚአብሔር ግን አይደለም። ለራሱ ነው የሚያገለግለው። 

የሰበካ ጉባኤ አባል ለመኾን ቡድን አቋቁሞ አሳድሞ ከተመረጠ በእግዚአብሔር ቤት ያገለግላል የቤቱን ባለቤት ግን አይደለም። ይኽ አይነቱን ሰው ነው ጌታ “ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ” ያለው አይነት ሰው ነው።

ማእድ ቤት (ኪችን) የሚያገልግሉ እኽቶች ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ሰው ተቀይሯል ቢባሉ በማግሥቱ ቤተ ክርስቲያኑ በእግሩ ይቆማል። በእውኑ ይኽ በእግዚአብሔር ቤት የሚደረግ ስራ እንጂ ለእግዚአብሔር የሚደረግ አገልግሎት አይደለም። 

አገልግሎት ረዥም ሰዓት እስኪገባን እስክንረዳው ድረስ በእግሩ ስር መቀመጥ ነው። 

መሬት የተቀመጠ ሰው አይወድቅም። ቀድሞም መሬት ላይ ነው ወዴት ይወድቃል። የቆመ ሰው ነው የሚወድቀው። አገልግሎት በጌታ እግር ሥር መቀመጥ ስለሆነ ነው። የመጨረሻው ትኅትና ነው። 

ለወንበር ለሥልጣን የሚጋፋ ጳጳስ ቄስ ዲያቆን በእግዚአብሔር ቤት የሚደረግ ግብግብ እንጂ በፍጹም አገልግሎት አይኾንም። 

2. የማርያም አገልግሎት ኮሽታ የለበትም። እኽቷ ማርታን ዞር ብላ አላየቻትም። ማርታ ደግሞ በጣም ትንኮሻኩሻለች። እቃ ታመስቃቅላለች ድምጽ አለ። ማርታ የጌታ ልብና ዓይን ወደ እርሷ የሚያተኩር መሰላት ግን አልነበረም ገሰጻት እንጂ። 

ሁላችን እናገለግላለን የምንል ማርታ እና ማርያም ነን። ከነዚኽ የወጣ የለም። በጣም የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ብኩን (ቢዚ) የሚያደርገን ምንጣፉን፣ ወንበሩን፣ ማጽዳቱን ሻማ ጧፍ መለኮስ፣ መዝመር ምግብ ማብሰል መቀደስ፣ ኮሚቴ ስብሰባ  ብዙ ጉዳይ ላይ እንውላለን። ማርታ ሥራ ላይ ናት ማርያም ደግሞ ጽሞና ማሰላሰል ላይ ናት። አንዱ ድምጽ ያለው አገልግሎት ነው ሌላው ደግሞ ዝምታ የተሞላበት አገልግሎት ነው። 

እኛ በእግዚአብሔር ቤት እንመጣና የማርያም አገልግሎት ትተን ወይም ረስተን የማርታን አገልግሎት እንቀጥላለን። ጳጳስ ነኝ፣ ቄስ ነኝ፣ ዲ/ን ነኝ፣ እኔ ሕንጻ አሰሪ ነኝ፣ እኔ ሰበካ ጉባሬ ነኝ እንላለን። ነገር ግን በእግዚአብሔር እግር ሥር ግን አንቀመጥም። በራሱ ቤት ኾነን ለራሱ ለእግዚአብሔር ግዜ የለንም። እንዲኽ ከኾነ በእግዚአብሔር ቤት እየሰራሁ እንጂ ለቤቱ ባለቤት እየሰራሁ አይደለም። እነዚኽ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት የሚያገልግሉ የሚሰሩት ለራሳቸው እንጂ ለቤቱ ባለቤት አይደለም። 

ያ የምትሰራትን ስራ ወይም አገልግሎት አቁሙ ብትባሉ መረበሽ ትጀምራላችሁ። አልያ እገሌ እገሌት የተሻለ ብትሠራው ብትባሉ ዝም ትላላችሁ? 
እገሊት ከእኔ ተሽላ ነው? እሱ ምን ስለኾነ ነው? እኔ ከነንማን አንሼ ነው? እኔ እያለሁ እሷ ትናንት መጥታ፣ እኔኮ መስራች ነኝ። ስንት መከራ እዚኽ አይቻለሁ፣ እገሊት የነ እንትና ግሩፕ ስለሆነች ነው….. የማይባል የለም። ይኽ ለራስ መሥራት ይባላል። ምክንያቶቹን ኹሉ በደንብ አጢኗቸው? የግል ስሜት እንጂ የጌታ ፍላጎት አይደሉም። 

ኦሮሞ ተበድሏል፣ የብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስ፣ የአንድ ጎሳ የበላይነት የሚለውን የጳጳሳት የወንበር ግፊያ በዚኽ ቃል ለኩት። የልማት አርበኛ ሕንጻ ያሰሩ፣ መንበረ ጵጵስና የገነቡ፣ ሆቴል የገዙ እያልክ ቀጥል። የማርታ አገልግሎት። በቤቱ ለማገልገል እንጂ እግዚአብሔርን አያገለግሉም። 

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

25 Dec, 09:36


እግዚአብሔር ደግሞ በእግሬ ስር ሳትቀመጥ እንዴት ማገልገል እንዳለብህ አታውቅም ብዙ ደከምክ ግን በከንቱ ነው አትድከም  ይልሃል እንደ ማርታ። በቤቱ እንዴት እንደሚገለገል ባለቤቱ ነው ማስተማር ያለበት። በእግሩ ስር ሳትቀመጥ በእርሱ ቤት እንዴት ማገልገልን እንዳለብህ ከየት ተማርክ? ከእግዚአብሔር ካልተማርክ የተማርከው ከሰይጣን ነው። ወንድምህን በመውደድ ሳይሆን እንዴት መጥላት እንዳለብህ ፣ እኔ ካላገለገልኩ ብዬ መገለባበጥን ማን አስተማረኝ? በአድማ ማሳመጽን ማን አስተማረኝ? ሰይጣን!! 

ሰይጣን የሚነግርህ ወንድምህ ወይም እኅትሽ ያንቺስ ተግባር ልትወስደው ነው አንተ ከዕይታ ውጭ ልትሆን ነው። ዝም ብለህ ቆመኽ አስቀድሰህ ልትሄድ ነው ይልሃል። ስንት ዓመት ያገለገልከው እገሌ ሊነጥቅህ ነው ይልሃል። 

ሰይጣን ይመጣና ሲኖዶሱ በአማራ ተሞልቷል። ኦሮሞ ተንቋል ይለዋል። እናንተ እንትን ስለኾናችሁ ለእኛ ሕዝብ ሲያልቅ ዝም ብላችኋል እንደውም ደግፋችኋል ይለዋል። ሲኖዶሱን በአንድ እግሩ ያቆሙታል። ከየት ተማሩት ማን አስተማራቸው? እንደ ማርታ ንጭንጭ። እኅቷን ወንድሙን ለጌታ ቤት አገልግሎት ያማሉ፣ ያድማሉ። ማርታዎች ናቸው። 

ከጌታ የተማረ ሰው ግን “እኔ የማገለግለውን አገልግሎት አንተ ብታገለግለው ይበልጥ ጥሩ ነው። እጅግ ደስ ይለኛል። እንደውም ጥሩ ታግዛለኽ። አንተ በወንበሩ ተቀመጥ እኔ መሬት እቀመጣለሁ” ይላል። ማርያሞች ናቸው ማለት ነው። መሬት የተቀመጠ ሰው ወድቆ አያውቅም። የሚዘል የሚንጠለጠል፣ የሚሯሯጥ ነው የሚወድቀው። እነዚኽ ሰዎች ሰው እንደ ረጋገጡ፣ ስም እንዳጠፉ፣ እንዳሳደሙ ነው የሚኖሩት። ለታይታ እረፍት የላቸውም። እነዚኽ ሰዎች ሲወድቁ ዳግም አይነሡም። 

መዝሙር ለመዘመር ፕሮግራም ለማሟላት እንጂ በመዝሙሩ እግዚአብሔርን አድምጠውበት አያውቁም። በተሰጥኦው ዜማ ይረካሉ እንጂ በቅዳሴው ተመስጠውበት አያውቁም። ይቀድሳሉ ያስቀድሳሉ ግን አይቀደሱም። 

ማርያም በምትሰማው ተመስጣ እግዚአብሔርን ሰምታበታለች። ኮሽታ አልነበረም፣ ስለ ተቀመጠች አትወድቅም፣ ከማንም አትፎካከርም አታሳድምም አትከራከርም። ራሷን አታነጻጽርም። ጌታ ከትሑታን ጋር ነው። መሬት ላይ መቀመጥ ትሕትና ማለት ነው። 

ትሕትና ወደ ጥበብ ይመራል፣ ጥበብ ደግሞ እግዚአብሔርን ያሳውቃል። እግዚአብሔርን ስታውቅ የበደለህን ይቅር ማለት ትጀምራለኽ። እንዴት ማገልገል እንዳለብኽ ትረዳለኽ። 
 
መ/ር ንዋይ ካሳሁን

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

24 Dec, 18:20


ከጠላት ፈተናዎች ተጠንቀቅ!

ዲያቢሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያቢሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል፡፡

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያቢሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡፡ ስለዚህም የክፉውን ዲያቢሎስ ዲያቢሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡፡

ለአፍታም ቢሆን ብቻህ እየተዋጋ እንዳለህ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል፡፡ "አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቆጣው? በልቡ:: አይመራመረኝም ይላልና፡፡" (መዝ ፲ ፥ ፲፪ -፲፫) ጥሩርና ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።›› (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ፡፡ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።" (ኢሳ. ፫፥፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ሰይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያቢሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜም ይዋጋናል፣ ይሸነግለናል በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል፡፡

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም፡፡ ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፤ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው፡፡ በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ ምክንያቱም ዲያቢሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመስል ይችላል፡፡ በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል፡፡ አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ፡፡ ይልቅስ ከዲያቢሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር፡፡

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገ. ፳ ፥ ፱)

በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱ ሁለንተናህ አድርገው።

(ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስና ሥራዎቹ ገጽ 43-45 - ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

23 Dec, 19:57


+• የተሻለው መንገድ •+

አንድ ነገር በሕይወታችን ሲፈጠር በብዙ አይነት መንገድ ምላሽ ልንሰጥ እንችላለን:: አንዳንዴ የቃየን መንገድ መፍትሔ መስሎ ብቅ ይላል:: የቃየን መንገድ ግን ቅናት እና ቁጣ የሚያጋፍሩት መንገድ ነው:: ቀለል ሲል ፊት ወደማጥቆር፥ ባስ ሲል ወደ ጠብ፥ ሲጦዝ ደግሞ ወደ ነፍሰ ገዳይነት ያደርሳል:: አንዳንዴ ደግሞ የሳኦል መንገድ ራሱን ይገልጣል:: ይህ መንገድ ደግሞ ፈጣሪን ያስረሳል:: አህያ ልትፈልግ ወጥተህ እግዚአብሔር ለንግስና እንደጠራህ ሳይቀር ሊያስረሳህ ይችላል:: ከከፍታህ ትወድቅና እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሳይቀር ታሳድዳለህ:: መጨረሻህ መቅበዝበዝ፥ ሰላም ማጣት እና የማይረባ አሟሟት ይሆናል::

እንዲህ ያሉ መንገዶች ብዙ ናቸው:: በደስታም ሆነ በሐዘን ወቅት ራሳቸውን መፍትሔ አስመስለው ይቀርባሉ:: ለክርስቲያን ግን አንድ ከሁሉ የተሻለች መንገድ አለች::

በሕይወትህ ውስጥ በከንቱ የሚያሳድዱህ ሰዎች ይኖራሉ:: በዚህ ጊዜ የበቀል መንገድ ራሷን መፍትሔ አድርጋ ታቀርባለች:: "ምን አደረግሁ?" ብለህ ትነሳና "ቆይ እሠራላቸዋለሁ" ወደሚለው ትደርሳለህ:: ይህቺ መንገድ "አትበቀልም፥ በሕዝቦችህ ልጆች ላይ ቂምም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ" (ዘሌ 19:18) የሚለውን ትእዛዝ እየጣስክ መሆኑን እንድትረሳ ታደርግሃለች:: አንተ ግን ይህቺን መንገድ ተዋትና የጸሎት መንገድን ተከተል:: ጌታችን "ለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" (ማቴ 5:45) ማለቱን አስታውስ:: ይህቺን መንገድ ብትከተል በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ትሆናለህ::

ዓለም ነገረ ሥራዋ ሁሉ ግራ ቀኝ የሌለው ሲሆን እየታዘብክ ሊሆን ይችላል:: በዚህ ጊዜ የጭንቀት መንገድ ሹክ ሊልህ ይመጣል:: "በቃ እንዲህ ሆነ ማለት ነው? ነገሮች እንዲህ ተበላሹ?" ብለህ እንድትጠይቅ ያደርግሃል:: ጭንቀት ቤቷን ትሠራብሃለች:: ሁሌ ትብሰለሰላለህ:: ከውስጥህ የሚሰማህ እረፍት ይጠፋል:: አንተ ግን ይህቺን መንገድ ተዋትና የጸሎት መንገድን ተከተል:: ጌታችን "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" (ማር 14:38) ማለቱን፤ ዳግመኛም "እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።" (ሉቃ 21:36) እንዳለ አስታውስ:: ይህቺን መንገድ ብትከተል በወጀብ ውስጥ ስንኳ ሆነህ ሰላምህ አይጠፋም::

ጸሎት ምርጫ የሌለው የክርስቲያን መንገዱ ነው:: ጭንቀት ቢመጣብህ ጸልይ:: ሐዘን ቢደርስብህ ጸልይ:: ደስታ ብታገኝ ጸልይ:: ብትታመም ጸልይ:: ብትድንም ጸልይ:: ሰዎች ቢበድሉህ ጸልይ:: ሰዎችን እየበደልክ ራስህን ስታገኘውም ጸልይ:: ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።" (1 ተሰ 5:17) የሚለውን እያስታወስክ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ጸልይ::

ዜና አበው ላይ "ክንፍ የሌለው ወፍ፥ ትጥቅ የሌለው ወታደርና፥ የማይጸልይ ሃይማኖተኛ አንድ ናቸው::" የሚል ቃል አለ:: እንግዲህ እወቅበት! ክንፍ እንደሌለው ወፍ እና ትጥቅ እንደሌለው ወታደር እንዳትሆን ሁሌም ጸልይ!

🖋 Fresenbet G.Y Adhanomhttps:
//t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

23 Dec, 14:29


🗣የአእላፋት ዝማሬ 10 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።



👇👇👇
https://t.me/janyared_2

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Dec, 19:29


🌟🌟🌟በገና አባት የተሸፈነ ቅዱስ አባት🌟🌟🌟

+++ቅዱስ ኒቆላዎስ ገባሬ መንክራት (St.Nicholas the wonder worker)+++

ቅዱስ ኒቆላዎስ (St.Nicholas-Santa Claus) በሮማ መንግስት ዘመን በኤዥያ ውስጥ በምትገኝ ሜራ በምትባል አገር (የአሁኗ ቱርክ) ግሪካዊ ከሆኑ ክርስቲያን ቤተሰቦቹ ተወለደ፡፡ የዚህም ቅዱስ እናቱ ጦና (Tona) አባቱ ኤጲፋንዮስ ይባላሉ፡፡ እኒህም እግዚአብሔርን የሚፈሩና ባለጠጎችም ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከሞቱ በኋላ ንብረታቸውን የሚያወርሱት፣ ለልባቸውም ደስታን የሚመግብ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ዕድሜያቸው እየገፋ በመምጣቱም ምክንያት በተስፋ መቁረጥ ተከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ያለ አምላክ በእርጅና ዘመናቸው ልክ ጻድቁ ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥን እንደጎበኘ እነርሱንም በቸርነቱ ጎበኛው፡፡ ቅዱስ የሆነም ልጅን ሰጣቸው፡፡ ይህም ልጅ ገና ታናሽ ሳለ መንፈሰ እግዚአብሔር የሞላበት ነበር፡፡ ዕድሜውም ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ዕውቀትና ጥበብን ይቀስም ዘንድ ወደ መምህራን የተላከ ቢሆንም፣ ከመምህሩ ከተማረው ይልቅ ከመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ይበልጥ ነበር፡፡

መሠረታዊ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርቶች በልጅነቱ ተምሮ በማጠናቀቁ በዲቁና መዓርግ ተሾመ፡፡ በኋላም የአጎቱ ልጅ አበምኔት በሆነበት በአንዱ ገዳም አርዑተ ምንኩስናን (የምንኩስናን ቆብ) ጭኖ የቅድስና እና የትሕርምት ሕይወትን ኖሯል፡፡ በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱም የቆሞስነትን መዓርግ አግኝቷል፡፡

ለዚህም ቅዱስ አባት እግዚአብሔር ተአምር እና ድንቅን የማድረግ ፤ሕሙማንንም የመፈወስ ታላቅ ጸጋ ሰጥቶታል፡፡

#ለጋስ (የስጦታ) አባት

በሜራ ከተማ የሚኖር ቀድሞ ባለጠጋ የነበረ በኋላ ግን ሃብት ንብረቱን ያጣ አንድ ሰው ነበረ፡፡ በድህነቱ ምክንያት ሊድራቸው ያልቻለ ሦስት ዕድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሰይጣንም እነዚህን ልጆቹን በዝሙት ሥራ ገንዘብ እየሰበሰቡ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ያደርጋቸው ዘንድ ክፉ ሐሳብን በሕሊናው አመጣበት፡፡ እግዚአብሔርም በዚህ ሰው ልቡና ውስጥ ሰይጣን የተከለበትን ክፉ ሐሳብ እና ምን ሊያደርግ እንደተነሣሣ ለቅዱስ ኒቆላዎስ ገለጠለት፡፡

     ቅዱስ ኒቆላዎስም የእናት የአባቱ ገንዘብ ከሆነው ላይ መቶ ዲናር ወስዶ በስልቻ (sack) ጠቅልሎ ማንም ሳያየው በምሽት ወደዚያ ደሃ ሰው ቤት በመሄድ በመስኮት በኩል ወረወረለት፡፡ ያም ደሃ ከየት እንደመጣ ያላወቀውን 100 ዲናር በቤቱ ባገኘ ጊዜ ተደነቀ አምላኩንም አመሰገነ፡፡ ያሰበውንም ክፉ ሐሳብ ተወ። በገንዘብ እጦት ምክንያትም ከትዳር የዘገየችውን የመጀመሪያ ልጁን ዳረ፡፡ በሌላም ቀን ቅዱስ ኒቆላዎስ ሁለተኛ ልጁን መዳር ይችል ዘንድ፣ አሁንም ተጨማሪ መቶ ዲናር ገንዘብ በጥቅል ስልቻ አድርጎ በመስኮቱ በኩል ወረወረለት፡፡ ይህንንም ገንዘብ ዳግመኛ በቤቱ ያገኘው ደሃ ሰው እንዲህ ያለውን ቸርነት በስውር የሚያደርገው ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ አይቶ ያውቅ ዘንድ ጉጉት አደረበት፡፡ ቤቱንም በንቃት መከታተል ጀመረ፡፡

ቅዱስ ኒቆላዎስም እንደ ለመደው ለሦስተኛ ጊዜ መቶውን ዲናር የያዘውን ስልቻ በመስኮት ሲወረውር ወዲያው ተዘጋጅቶ ይጠብቀው የነበረው ሰው ፈጥኖ በሩጫ ከቤቱ ወጣ። ሊያየው ይመኘው የነበረ ያንንም ቸር ሰው ሊቀ ጳጳሱ ኒቆላዎስ ሆኖ አገኘው፡፡ ከእግሩ ስርም ተደፍቶ ልጆቹን ከድህነት እና ከኃጢአት ሕይወት ስለታደገለት ሊያመሰግነው ቢሞክርም ቅዱስ ኒቆላዎስ ግን ምስጋናውን እምቢ አለ፡፡ ይህን ሐሳብ በልቡ ያኖረ እግዚአብሔርንም ያመሰግን ዘንድ ለመነው፡፡

        ከዚህ ታሪክ በተጨማሪም ለሕፃናት እና ለተቸገሩ ሰዎች ያደረገው ልግስና የብዙ ብዙ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት መታሰቢያውን በልግስና የሚያከብሩት። 

       በአጠቃላይ ይህ ቅዱስ አባት በዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ስለ እምነቱ ብዙ ስቃይ እና እስራት ደርሶበታል፡፡ ፋታ በማይሰጥ መከራ እና ግርፋት ውስጥ እያለ የራሱን ሕመም ከማዳመጥ ይልቅ በውጪ ላሉ ለልጆቹ ምዕመናን የሚያበረታታ እና በእምነታቸው እንዲጸኑ የሚያደርግ መልእክትን ይጽፍላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ኒቆላዎስ በ325 ዓ.ም ለአውግዞተ አርዮስ ከተበሰቡት 318ቱ ሊቃውንት መካከል አንዱ የነበረ የዚህች ኦርቶዶክሳዊት እምነት ባለውለታ ነው፡፡ ከአርባ ዓመታት በላይ በሊቀ ጵጵስና መንበር በጎቹን ከነጣቂ ተኩላ እየጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን ካገለገለ በኋላ በሰማንያ ዓመቱ አርፏል፡፡

(ቅዱስ ኒቆላዎስ በእኛ (በኢትዮጽያ) የስንክሳር መጽሐፍ ላይ የእረፍቱ መታሰቢያ የሚያዝያ ወር በገባ በአስራ አምስተኛው ቀን እንደሆነ ተመዝግቧል፡፡ ኒቆላዎስም ማለት ‹መዋኤ ሕዝብ - ሕዝብን የሚያሸንፍ› ማለት ነው።)

       የልደት በዓል እግዚአብሔር አብ ልጁን ለዓለም የሰጠበት በመሆኑ ‹የሥጦታ በዓል› በመባል ይጠራል፡፡ ይህንንም በማሰብ ለድሆች በመራራት ለተቸገሩት ቸርነት በማድረግ እናከብረው ዘንድ ምሳሌ እንዲሆነን ቅዱስ ኒቆላዎስን እናስባለን፡፡ ምንም ዓለም አፈ ታሪክ አድርጋ ብታወራውም፣ የዚህንም ቅዱስ ማንነት እንዳይታወቅ በፈጠረቻቸው ተረቶች ብታጠለሸውም እኛ ግን የ‹ገና አባት› ብላ ከሰየመቻቸው የፈጠራ ሰው ጀርባ እውነተኛ የሆነውን ይህን ቅዱስ አባት እናስበዋለን፡፡

+++++ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛ ኃጢአተኞቹንም በዚህ ጻድቅ ሰው ጸሎት ይማረን!!!+++

ምንጭ:– -መጽሐፈ ስንክሳር
              -Coptic synaxarium

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

20 Dec, 18:51


ጌታ ሆይ

እባክህ ባልሰማህም ጥራኝ ባልመጣም ጥራኝ

ጴጥሮስ በባህር ላይ እንደለመነህ "ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ" እንደ አልዓዛር "ውጣ" ብለህ በቅዱስ አጠራር ጥራኝ።
እንደ ማቴዎስ ከቀራጭነት ገበታዬ ላይ
እንደ ዘኬዎስ ከዛፍ ላይ
እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰረገላዬ ላይ
ብቻ ባገኘኸኝ ቦታ ላይ ጥራኝ

📕 የግዮን ወንዝ
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

20 Dec, 18:42


+++ የማያሳፍር ተስፋ +++

ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው “የተስፋ አምላክ” ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? “ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ” ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16)

"ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ"

"ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!"

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

20 Dec, 18:40


ሰው ቢጠላችሁ፣ ሰው ቢሸሻችሁ፣ ስታጡ ጓደኛም ቢከዳችሁ፣ ምንም ብትሆኑ፣ ማለዳም ተነስታችሁ ገንዘብ ብታጡ፣ ስራም ብታጡ ቢቸግራችሁ፣ ዳኛም ባይፈርድላችሁ፤ ዝም ብላችሁ አንድ ቃል በሉ "#እግዚአብሔር_ከእኔ_ጋር_ነው!"

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

18 Dec, 16:19


#የተባረከች_አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች

#የተባረከች_ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች

#የተባረከ_ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል

#የተባረከች_ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች

#የተባረከ_አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም

#የተባረከች_አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች

#የተባረከች_ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች

#የተባረከች_እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች

#የተባረከች_እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

15 Dec, 05:52


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ታኅሣሥ 6 ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን "ለድንግልና ሰማዕት ቅድስት አርሴማ" : "አባ አብርሃም" እና "ቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊው" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅድስት አርሴማ ድንግል "*+

=>እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5:11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::

*ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
*ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
*ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
*ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
*ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::

¤ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

+አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቁዋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-

1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::

+ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::

+ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በሁዋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::

+በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ:: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::

+በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::

+ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::

+አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::

+የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::

+ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው::
ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::

+የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮዽያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::

+ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::" (መዝ. 75:5)

+በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::

+ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት::


እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

13 Dec, 17:26


ሰይጣን መንፈሳዊ ሕይወትን ለመኖር ወስነህ ስትጀምር በእነዚህ ሁለት ሐሳቦች ይዋጋሃል።

1. አንተ ለዚህ ሕይወት እንደማትሆን እና መቼም እንደማትለወጥ ሹክ ይልሃል። ይህን የሚያደርገው ተስፋ ቆርጠህ የያዝከውን ሩጫ እንድታቆም ነው። የሚገርመው ግን መለወጥ ባትጀምር ኖሮ ሰይጣን “አልተለወጥህም” አይልህም።

2. ገና ከመጀመርህ የደረስህ እና ለመፈጸም ጥቂት የቀረህ አስመስሎ ያሳይሃል። ብዙ ርቀህ እንደ ሄድህ አስበህ ልክ እንደ ጥንቸሏ ተዘናግተህ እንድትተኛ እና የጽድቅ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው ትዕቢት እስረኛ እንድትሆን ያደርግሃል። አሁንም ሰይጣን “ደርሰሃል” እያለ ሲክብህ ገና እግርህን ለማንሣት የምትጣጣር እንደ ሆንህ አቅምህን በደንብ ያውቀዋል።

ጀማሪ ስትሆን ሰይጣን “አትችልም” ብሎ ተስፋ በማስቆረጥ ወይም “ደርሰሃል” እያለ ያለ ልክ በማመስገን ወጥመዱ ውስጥ ሊጥልህ ይሞክራል።

“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና”  2ኛ ቆሮ 2:11

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Dec, 18:08


"እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Dec, 09:41


"የደግ ሰው ሀገሩ መንግሥተ ሰማያት በልቡናው ውስጥ ናት። በልቡናው አድሮ የሚያበራለት የሦስቱ አካላት (የሥላሴ) ብርሃን ነው። ከነጽሮ፤ ከንጽሐ ነፍስ ለደረሱ ሰዎች የሚነፍስላቸው የመዐዛ ነፋስ መንፈስ ቅዱስ ነው"

(አረጋዊ መንፈሳዊ )

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Dec, 09:31


"ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ....."

አባ ሕርያቆስ - ቅዳሴ ማርያም

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Dec, 17:01


ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Dec, 11:17


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Dec, 11:16


ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

03 Dec, 20:34


ምክረ አበው

ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና " አባ ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ " አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው " በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡

እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡

ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው " ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ " ብሎ እንዳዘዘን፡፡

+ከተለያዩ ፅሁፎች የተገኙትን መንፈሳዊ ህይወትን የሚሰብኩ ፅሑፎችንና ትምህርቶችን እናካፍላችሁ፡፡

''አንብበን እንለወጥ።''

+መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

https://t.me/menfesawe12+

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

03 Dec, 20:30


"ከእናንተ እያንዳንዱ በመጾሙ ያገኘውን ጥቅም ውስጡን (ሕሊናውን) ይጠይቅ ዘንድ እማልዳችኋለሁ፤ እማፀናችሁማለሁ! ብዙ ጥቅም እንዳገኘ ከተረዳ ይህን ያገኘው በመበርታቱ ምክንያት እንደ ኾነ ይቍጠር፡፡ ምንም ነገር ያላገኘ እንደ ኾነ ግን ቀሪውን ጊዜ ተግቶ በመጾም የንግድ ዕቃዎችን (መንፈሳዊ በቁዔትን) ለማግኘት ይጠቀምበት፡፡

ወርሐ ጾሙ እስከሚፈጸም ድረስ ባዶ እጃችንን እንዳንቀርና ታላቅ የኾነ ትርፍን እናግኝ ዘንድ ራሳችንን ልል ዘሊላን አናድርግ፡፡ በዚህ መንገድ የጾምን ዋጋ ልናጣ አይገባምና፡፡ እስከ አሁን ድረስ የጾሙን ድካም ታግሠናልና፡፡ የጾምን ድካም ታግሠው እያለ የጾምን ፍሬ ጻማ አለማግኘት አለና፡፡

@menfesawe12
@menfesawe12
@menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

24 Nov, 17:26


በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፉት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፣ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ።(ምሳ 16፥32)

ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ ለሰውነትህ ጾም አስተምረው። "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።

ጌታ ወደ ገሊላ የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር።(ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።

መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
@menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Nov, 13:27


👉 Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕መፅሀፍ📕በPDF ታገኛላቹ።

1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open

2.ሕማማት......................Open

3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open

4.አባቶችህን እወቅ...........Open

5.ሃይማኖተ አበው............Open

7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open

8.የብርሃን እናት...............Open

9.ማህሌተ ፅጌ................Open

10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open

11.ተግባራዊ ክርስትና........Open

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Nov, 12:13


💒 ባሕረ ኤርትራን በበትሩ ከፍሎ እስራኤልን ያሻገረው❓️



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Nov, 04:02


እግዚአብሄር ከእንቅልፍህ እንድትነሳ ከረዳህ አሁንም
በአንተ ላይ እቅድ አለው ማለት ነው።

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Nov, 06:09


ለሰው ከኹሉ አስቀድሞ ራሱን ማወቅ ይገባዋል። ራሱንም ማወቅ ማለት አላዋቂነቱን ማወቅ ማለት ነው። አላዋቂነትንም አለማወቅ ያለአላዋቂነት፣ የድንቍርና ፍጻሜ ነው።
አድማሱ ጀንበሬ

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Nov, 04:09


ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

(የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም)

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Nov, 03:58


ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል
ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ
ናሁ ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Nov, 06:07


“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።”
[ገላትያ 6: 1]
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Nov, 08:20


ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን::

ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ”በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “ …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።

መጋቢት ፳፯ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።

ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ። ጲላጦስም በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭

መጋቢት ፳፯ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱን በጠቅላላ አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡

የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሣ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Mahibere kidusan


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Nov, 04:20


📚 ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ሊቅ ስም ማን ይባላል



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

05 Nov, 21:52


ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

(#በዲያቆን_መላኩ_ይፍሩ)

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

05 Nov, 21:52


"+ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም
ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ::
የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱምቁስል እኛ ተፈወስን:: +"+ (ኢሳ. 53:4)


✞✞✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Nov, 17:41


አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግስት ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ . . . ደካማ ለሆንኩ ለእኔ ያለ አንተ የሚያፀናኝ የለም። ለምፍገመገም ለእኔ ያለ አንተ ደጋፊ የለኝም። ለወደቅሁ ለእኔ ያለአንተ የሚያነሳኝ የለም። ለአዘንኩ ለእኔ ያለአንተ የሚያረጋጋኝ የለም። ለድሀው ለእኔ ያለ አንተ መጠጊያ የለኝም፡፡

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Nov, 17:37


ለቅዱስ ኤፍሬም፣ ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተለመነች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን፤ ልጆቿን ትጎብኘን መልካም ዕለተ ሰንበት፡፡

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Nov, 17:36


“ንብ የምትሞተው መቼ ነው?”

የጥበበኛ ነፍስ መገለጫዋ ይሄ ነውና ሁል ጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ፡፡ ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል፡፡ ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” እያላችሁ አመስግኑ /ኢዮብ.1፥21/፡፡

እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድነው? በሽታ ነውን? ታድያ ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና፡፡ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን? ታድያ ይሄ እኮ ምግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው፡፡ ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ወቀሳ ነውን? ታድያ ተጐጂዎቹ’ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚመሰክሩብን እንጂ እኛው አይደለንም፡፡ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች” እንዲል ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛው አይደለንም /ሕዝ.18፥4/፡፡ ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምውት በሆነ ሰው ልትቆጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

https://t.me/menfesawe12
https://t.me/menfesawe12
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Nov, 10:02


አባታችን የሰላም መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ሆይ ስለ እኛ ለምንልን ጸሎታችንንም በመድኃኒዓለም ፊት አሳርግልን። ልጆችህን ጎብኘን፤

" ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ሆይ፤ ለእርዳታ ፈጽመው ለሚፈጥኑት እግሮችህና ሰኰናህ ሰላም እላለሁ። ዑራኤል ሆይ፤ በስደት ወራት ለድንግል የምድረ ግብፅን መንገድ ያመለከትካት አንተ ነህ ሦስት ዓመት እያለቀሰችና እያዘነች በስደት ከቆየች በኋላ ተመልሳ ወደ ሀገሯ እንድትገባ የደስታ ምስራች ያበሠርካት አንተ ነህና።
ዑራኤል ሆይ፤ መዝናኛዋ በጽርሐ ጽዮን ለሆነና ነፍስን ከሲኦል የኵነኔ ፍርድ ለማውጣት የሲኦል ጐዳና መረገጫው ለሆነው ተረከዝህ ሰላም እላለሁ።
ዑራኤል ሆይ፤ ከፈጣሪህ ይቅርታን አስገኝተህ የኃጥኣንን ነፍስ የምትጐበኝ ነህና በዚያች የቁርጥ ፍርድ ቀን የሲኦልን ደጃፍ እንዳናይ።
ስለእመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል ኪዳንህ እንማፀናለን። አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ዑራኤል አምላክ ሆይ፤ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆች እኛን አገልጋዮችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ለዘላለሙ አሜን። "   

          መልክአ ዑራኤል

-መጀመሪያ የሥጋ ሐኪም የነበረ በኋላ የነፍስ ሐኪም የሆነው የኤማሁሱ መንገደኛ የእመቤታችን ባለሟል  ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ጥቅምት 22 በዓለ ዕረፍቱም ነው

በረከቱ ይደርብን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Oct, 05:16


"ከሴቶች ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ ከተለዩ የተለየሽ በውስጧም የኪዳን የሕግ ጽላት ያለባት የምትባይ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ። ካዳኑም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ዓስሩ ቃላት ናቸው። ካለመለወጥ ሰው የሆነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን መጀመሪያ ስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንፁሃን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው።"

    የእሁድ ውዳሴ ማርያም

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

29 Oct, 18:21


"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡”

ማኅሌተ ጽጌ

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

29 Oct, 08:12


"የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ኾይ ዛሬ ከኃጢኣታችን ታድነን ዘንድ እንለምናለን ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ አውጣን። ከሞተ ኃጢኣት ዛሬ አድነን። ከዚኽ ዓለም ነውር ኃጢኣት እና ርኩሰት ነፃ አድርገን።"
                        ድርሳነ ገብርኤል
የቅዱስ ገብርኤል ልመናውና አማላጅነቱ በልጆቹ በኹላችን ላይ ይኹን!

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

28 Oct, 07:13


አባቶቻችን እንዲህ አሉ፦

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም።"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው።"
አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል።"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ።"
አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል።"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው።"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው። ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል።"
አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል።"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት።"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ።

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ።"
አባ ኤፍሬም አረጋዊ

(Deacon Henok Haile)

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

26 Oct, 17:19


እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ወቀዳሜ ሰማዕት)፣ ለቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት፣ ለቅድስት ሐና ነቢይት፣ ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ለደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት (ካቶሊካውያን የገደሏቸው)፣ ለቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት እንዲኹም ለአባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

ዳግመኛም ዛሬ  ጥቅምት 17 ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)፣ ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ፣ አባ ገሪማ ዘመደራ፣ አባ ጰላሞን ፈላሢ፣ አባ ለትጹን የዋሕ እንዲኹም ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆጵሮስ) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

24 Oct, 17:25


ጌታ ሆይ ቸርነትህ ብዙ ነው፤ አይነገርምም፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በሚያምንብህና በሚወድህ አፍ ሁሉ ስምህ የታወቀ ነው፡፡ በሕግ ከታወቁ ምስጋናዎች ሁሉ ከውስጣቸው የሚመስልህ የለም፡፡ የዓይኖቼ ብርሃንና የሥጋዬ ብርታት ከከበረው ስምህ ወገን ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የከበረ ስምህን በአንደበቴ ዘወትር የተሾመ አድርገው፡፡

(ግብረ ህማማት)

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Oct, 17:09


አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።"
መልክአ ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ጠላት ይጠብቀን

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Oct, 07:55


🔗 ጥያቄ
-----------------


ከሙሴ እስከ ዮሐንስ መጥምቁ ድረስ የነበረ ሕግ ❓️

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Oct, 17:04


ሰላም የችግሮች አለመኖር ሳይሆን በፈተናዎች ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ውጤት ነው።

እግዚአብሔር የሚሰጠውን ሰላም የትኛውም ኃይል ሊወስደው አይችልም!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

18 Oct, 05:55


እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር
***
በብዙ መልካም የሆነ ሰውን አንድ ክፉ ነገር ብናይበት ብዙ መልካም ነገሩን ሳይሆን ክፉ ነገሩን አይተን ጉድለት ይሰማናል። አእምሯችን ነጭ ወተት ላይ አንዳረፈ ዝንብ ክፉውን ትኩረት ሰጥቶ ያያል፤ ልባችንም መውደድ ይከብደዋል። ይህ ግን የሥጋ እውቀትና ግብር ነው።
እግዚአብሔር እንደዚህ ቢሆን ኖሮ መወደድ እና መዳን አይገኝም ነበር። በእርሱ ዓይን ብዙ ክፋታችን የተገለጠ ነውና። ነገር ግን እርሱ መልካም ስለሆነ በኃጢአት እየኖርን ጠላቶቹ እያለን ወደደን፤ ያውም እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር። ለዚህ ቸርነትና ፍቅር አንክሮ ይገባል! (ሮሜ. 5፥10)
ይህ አምላካዊ ቸርነት በእኛ ዘንድ ለእምነት፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ምንጭ ነው። እምነት ማለት ሳይገባን ክፉዎች ሆነን የወደደን እና ቀድሶ እና አክብሮ መልካም ልጆቹ ያደርገን ዘንድ ወደ እርሱ የጠራን አምላክ መኖሩን ተረድቶ በእርሱ ታምኖ መኖር ነው። ከዚህም ምሥጋና እና ደስታ ይወጣል። (ዮሐ. 14፥1)
ፍቅር ደግሞ በሥራ እግዚአብሔርን መምሰል ነው፤ እሱ ያለ ጥቅም እና ማዳላት ሁሉን ይወዳልና፤ ጠላቶች ሆነን ሳይቀር ወዶናልና። በእኛ ውስጥ ያለውን ክፋት አይቶ ሳይተወን መልካም አድርጎ መፍጠሩን አስቦ ሊያድነን መጥቷልና።
ተስፋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ርስትን እየጠበቁ መከራን መታገስ እና የክርስቶስን መምጣት መጠበቅ ነው። እኛን ያድን ዘንድ አንድያ ልጁን ለመከራ አሳልፎ የሰጠ መልካሙ እረኛችን እና አባታችን የማይሰጠን ምን ነገር አለ? የሚጠቅመንን እና ቃል የገባልንን ሁሉ ይሰጠናል። (ሮሜ. 8፥32)
ፍቅር ግን ከሁሉም ይበልጣል አለ ሐዋርያው። እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ሕግን ሁሉ ፈጽሟልና። (1ኛ ቆሮ. 13፥13)

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

16 Oct, 06:36


የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።

ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።

"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር !  እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።

አቡነ ሺኖዳ  ሳልሳዊ

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

16 Oct, 06:31


እንኳን ለቅዱስ ዲዮናስዮስ ሐዋርያዊ፣ ለአባ ጰንጠሌዎን ዘጾማዕት፣ ለቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ (ዕን. ከ1 - 3 ያንብቡ)፣ ለቅድስት ሐና ነቢይት (የሳሙኤል እናት - 1ሳሙ. ከ1 - 2ን ያንብቡ)፣ ለቅዱሳን ኡሲፎርና ኡርያኖስ (ሰማዕታት)፣ ለአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ (ፍልሠቱ) እንዲኹም ለቅዱስ ሄኖስ ነቢይ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

ዳግመኛም ዛሬ  ጥቅምት 6 ቀን ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም፣ አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን፣ አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል፣ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ፣ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፣ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ፣ ቅድስት ሰሎሜ፣ አባ አርከ ሥሉስ፣ አባ ጽጌ ድንግል እንዲኹም ቅድስት አርሴማ ድንግል ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

14 Oct, 18:53


እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ፣ ለቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ (ጳጳስ ወሰማዕት)፣ ለቅድስት ሐና ሰማዕት (እናቱ)፣ ለቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (ከ12ቱ ሐዋርያት) እንዲኹም ለአባ ጳውሎስ ሰማዕት (አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

ዳግመኛም ዛሬ  ጥቅምት 5 ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት፣ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም፣ ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ፣ ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ እንዲኹም ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

14 Oct, 05:19


መጽሐፍ ቅዱስ "ኖኅ ጻድቅ፣ ፍጹም ነበር "ብቻ አላለም፤ በትውልዱ የሚል ጨመረ እንጂ ዘፍ. ፮ ÷፱ ። በዚያ ክፉ እና በተበላሸ ትውልድ መካከል ጻድቅ ሆኖ ተገኘ። ደጋጎቹ ከክፉዎች ጋር በመኖራቸው ያገኙት ጥቅም ይሄ ነው፤ ማለትም ከክፉዎች ጋር ጻድቃን ሆነው በመገኘታቸው በሌሊት በሰማይ ላይ እንደሚያበሩ ከዋክብት ሆኑ። ዛፍ እንኳ በነፋስ ወዲያ እና ወዲህ ሲወዛወዝ ይጠነክራል።

ክፉዎችም ከደጋጎች ጋር ተቀላቅለው በመኖራቸው ይጠቀማሉ። ደጋጎችን ሲያዩ በኃጢአታቸው ያፍራሉ ፤ ይሳቀቃሉ። የመዋረድ ሥሜት ይሰማቸዋል። ከኃጢአት ባይታቀቡም እንኳ በሥውር የሚያደርጉትን በአደባባይ ለማድረግ አይደፍሩም። ኃጢአት እና ነውረኛ ነገር በአደባባይ በግልጥ አለማድረጉም ቀላል ነገር አይደለም። የሌሎቹ መልካም ሕይወት የእነዚህን ክፋት ወቃሽ፣ ምሥክር እና ዳኛ ይኾንባቸዋልና። በደጋግ ሰዎች መኖር ምክንያት በኃጢአት መሳቀቅ እና ራስን መውቀስ ቀላል የማይባል ራስን የመለወጥ የመጀመርያ ደረጃ ነው። በእነርሱ መኖር በሕሊና መሳቀቅ በኃጢአት ከመደሰት እና ከመኩራራት፣ ኃጢአታዊ ምኞትን ሁሉ በዘፈቀደ ከመከተል እንደ ልጓም ያዝ ያደርጋል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

https://t.me/menfesawe12
https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

13 Oct, 16:55


ትመጫለሽ አይደል?

ቤተመቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም
በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል - ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም

በልማድና በእምነት መሀል – በተወጠረ መንፈሳችን
በጎጥ በጎሳ በታጠረ - በተፍረከረከ አንድነታችን
ስቀለው ስቀለው እንጂ – ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን

ለክፋት ባደገደገ - በጎ ግብር በራቀው
ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ ፍኖት በናፈቀው
ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው

በረከሰ ማንነት ነው – ንዒ ማርያም የምንልሽ ከልዑሉ ሚካኤል ጋ ከደስተኛው ገብርኤል ጋ
            ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ
            ነይ ርግባችን የምንልሽ
በሚገባን ንጽህና – ሆነን አይደለም ድንግል
ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም.... ትመጫለሽ አይደል?

ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ - ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል
ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና..... ትመጫለሽ አይደል?

ስለተጠራው ስምሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

ስለኪዳንሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

አልቦ ምግባር ብንሆንም - እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ

ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Oct, 21:30


እንኳን ለሊቁ አባ ሕርያቆስ፣ ለቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ እንዲኹም ለቅድስት ቴክላ ሰማዕት ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏

ዳግመኛም ዛሬ  ጥቅምት 2 ቀን ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)፣ ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ፣ ቅዱስ አቤል ጻድቅ፣ ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) እንዲኹም ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

10 Oct, 08:05


ኦ! አቤቱ ጌታዬ አምላኬ ፥ በርኅሩኅነትህ መልስልኝ ፥ አንተ ለእኔ ማን ነህ? እሰማህ ዘንድ ተናገረኝ ፥ እነሆ በፊትህ የልቦናዬ ጆሮዎች ተከፍተዋልና፥ አቤቱ ጌታዬ ክፈትና  "ለነፍሴ፥ እኔ ነኝ መድኃኒትሽ በላት" ይህን ድምፅ በሩጫ ተከትዬ በመጨረሻም አንተን ልይዝህ እፈልጋለሁ!"

#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Oct, 23:31


#መስከረም_29

#ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቅድስት አርሴማ ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕት ቅድስት አርሴማ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_መስከረም)

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Oct, 17:35


የዚህ ዓለም ፈተና የሚያስጨንቅ ነው፤ ከራሳችን፣ ከሰዎች እና ከአጋንንት በብዙ እንፈተናለን። እንወድቃለን፤ እንነሣለን። ኃዘን እና ምሬት ይጎበኙናል።
ግን ግን ከመስቀሉ የሚወጣው ሠላም እና ደስታ ሁሉን አልፎ የሚያጸና ነው። የመስቀሉን ነገር በልቡ አምኖ የሚኖር (ተዘክሮ መስቀልን ከልቡ የማይለይ) ኃዘን እና ፈተና ሊሰብረው አይችልም። ጥልቅ የሆነ ነጻነት፣ ደስታ እና ሠላም አይለየውም። የመዳናችን ምሥጢር ለልብ ደስታን፣ መታመንን እና ሠላምን የሚሰጥ ነውና። ምእመናን ወደ ቁርባን ለመቅረብ መማር ያለብንን የድኅነት ትምህርት ጨምቆ የሚያቀርበው ትምህርተ ኅቡኣት እንዲህ ይላል፦
"እኛን ስለማዳን ተሰቀለ። በመስቀሉም ሕይወታችን፣ ቤዛችን እና ጽንዓችን ሆነልን። ይኸውም የማያልቅ ደስታ ያለበት ረቂቅ ምሥጢር ነው። የሰው ነፍስ ሁሉ ይህን ይዛ ብትገኝ ከእግዚአብሔር የሚለይ ክፉ መኞት ከዚህ ደስታ ሊለያት አይችልም።"

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Oct, 13:07


''የመሬት መንቀጥቀጥ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚናገር ዐዋጅ ነጋሪ ነው።ቀድሞ ይከሰትና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን እንድንለወጥና መዓቱን ከእኛ እንድናርቅ ያደርገናል፡፡"

"እያንዳንዱ ሰው የፈራው የመሬቱን መንቀጥቀጥ ሲኾን እኔ የፈራኹትን ግን የመሬት መንቀጥቀጡን ምክንያት ነው።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ-የክርስቲያን መከራ ገፅ 88 ገ/እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Oct, 14:22


https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Oct, 14:21


እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ መከራ እንዳትገባ አያደርግም። አንዳንድ ጊዜ በወጀብ ውስጥ መንገድ ያዘጋጅልሃል። ግፊው በሚበዛበት ዐውሎ ነፋስ እያለፍህ ተፍገምግመህ እንዳትወድቅ ጉልበትህን ያጸናል፤ ኃይልን ያስታጥቅሃል። እንዲህ እያደረገ በመንፈስ ያጎለምስሃል።

እግዚአብሔር ዳንኤልን በአናባስት ጉድጓድ ከመጣል፣ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት ከመግባት፣ ጳውሎስና ሲላስን ወደ ወኅኒ ከመውረድ ሊያድናቸው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ አላደረገም። አምላካችን ፈተና ካለባቸው ቦታዎች ሁሉ ሊያወጣን ቃል አልገባምና። ነገር ግን በመከራ ጊዜያችን ሁሉ ከእኛ እንደማይለይና በእውነት ይዘነውም እንደ ሆነ በድል ነሺነት እናጠናቅቅ ዘንድ እንደሚረዳን ቃሉን ሰጥቶናል።

የጌታ እናት እመቤታችን የተወደደ ልጇን ይዛ በግብጽ በረሃ እንደ ወፍ ከተንከራተተች በኋላ ሕፃኑን የሚፈልገው ክፉ ሄሮድስ ሲሞት ተመልሳ ወደ ገሊላ ገብታለች። እንደ ድንግል ጌታን በመሐል እጅህ ብትታቀፍ እንኳን  ግብጽ መውረድ  አይቀርልህም። ይሁን እንጂ የመጣብህን መከራ ድል ነሥተህ ወደ ገሊላ መመለስህም እርግጥ ነው።

"ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል"
                              1ኛ ቆሮ 10፥13

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

04 Oct, 09:19


የጽጌ ጾም

በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ንጉሥ ሄሮድስ ሥልጣኔን ይቀማኛል በሚል ቅናት ተነሣሥቶ እርሱን ለማስገደል አሰበ፡፡ ያንጊዜም ጌታችን በተአምራት መዳን ሲቻለው የትዕግሥት፣ የትሕትና አምላክ ነውና በለበሰው ሥጋ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ በመልአኩ ተራዳኢነት፣ በአረጋዊው ዮሴፍ ጠባቂነትና በሰሎሜ ድጋፍ ከገሊላ ወደ ግብፅ ተሰዶ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ቆይቷል፡፡ ሄሮድስም ጌታችንን ያገኘው መስሎት በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የሚገኙ ሀለት ዓመት ከዚያ በታች የሆኑ አንድ መቶ ዐርባ አራት ሺሕ ሕፃናትን በግፍ አስፈጅቷል፡፡

በተአምረ ማርያምና በማኅሌተ ጽጌ ተጽፎ እንደሚገኘው ጌታችን በግብጽ ምድር በስደት ሳለ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከእነዚህ መካከልም ውሃ በጠማቸው ጊዜ ውሃ እያፈለቀ ማጠጣቱና ይህንን ውሃ ክፉዎች እንዳይጠጡት መራራ ማድረጉ፤ ለችግረኞችና ለበሽተኞች ግን ጣፋጭ መጠጥና ፈዋሽ ጠበል ማድረጉ፤ ‹‹የሄሮድስ ጭፍሮች ደርሰው ልጅሽን ሊገድሉብሽ ነው›› ብሎ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ እመቤታችንን በማስደንገጡ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ድንጋይ ሆኖ እንዲቆይ ማድረጉ፤ መንገድ ላይ የተራዳቸው ሽፍታ ሰይፉ በተሰበረች ጊዜ እንደ ቀድሞው ደኅና እንድትሆን ማድረጉ፤ እንደዚሁም የግብጽ ጣዖታትን ቀጥቅጦ ማጥፋቱ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የጌታችንና የእመቤታችን የስደት ወቅት በወርኃ ግንቦት ነው፤ ነገር ግን ዘመነ ጽጌ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የስደቱ ጊዜ በዘመነ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡ ይህ የእመቤታችን አበባነትና የጌታችን ፍሬነትም እንደ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና አባ ጽጌ ድንግል ባሉ ሊቃውንት ድርሰቶች በሰፊው ተገልጧል፡፡

የጽጌ ጾም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያሉት አርባ ቀናት ዘመነ ጽጌ (ወርኃ ጽጌ) እንደሚባሉ ይታወቃል። በነዚህም ቀናት በየቤተ ክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩ መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት፣ በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐተ እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋከብት ምድር በጽጊያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው። በወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሳዊ አገልግሎት መነሻው ‹‹መልአኩ ሕፃኑና እናቱን ወደ ግብጽ ይዘሃቸው ሽሽ፤ ሕፃኑን ሊገድሉት ይሻሉና›› ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሰረት ሕፃኑን እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ዮሴፍ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው። (ራእይ ፲፪፥፲፮)

በዐሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባት አባ ጽጌ ብርሃን ‹‹የሮማን ሽቱ የቀናንም አበባ የምትሆኝ ማርያም ሆይ ፥ በረሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪ ጠወልግ ድረስ በስደትና በለቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሶሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህም ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር።›› ብለዋታል፡፡ እንዲሁም አባ አርከ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‹‹ሰቆቃወ ድንግል›› በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፦ ‹‹ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሽ ጊዜ የደረሱብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንዳጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር።››

በዚህ ወቅት በሚገኙ ሰንበታትም ሊቃውንቱ ሌሊቱን ሙሉ ስለ እመቤታችን አበባነትና ስለ ጌታችን ፍሬነት የሚያትት ትምህርት የያዙትን ማኅሌተ ጽጌና፣ ሰቆቃወ ድንግልን ከቅዱስ ያሬድ ዚቅ ጋር በማስማማት ሲዘምሩ፣ ሲያሸበሽቡ ያድራሉ፡፡ ቅዳሴውም በአባ ሕርያቆስ የተደረሰውና ምሥጢረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ሥላሴንና ነገረ ማርያምን የሚተነትነው ቅዳሴ ማርያም ነው፤ ምንባባቱም ከዚሁ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ናቸው፡፡

የማኅሌተ ጽጌና የጾመ ጽጌ አጀማመር የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው። በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጥዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌተ ጽጌና ከሰቆቃወ ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው። ዝክሩም በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፥ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢው ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው። ዐቅመ ደካሞች ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል። ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው።

የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ዜና ገድል የጽጌን ጾም አስመልክቶ የሚከተለውን ይተርካል፦ ‹‹አባ ጽጌ ብርሃን የተባለው አባት እንደ መዝሙረ ዳዊት መቶ ኀምሳ አድርጎ ማኅሌተ ጽጌን ደረሰ። አባ ጽጌ ብርሃን ይህንን በደረሰበት ጊዜ የወረኢሉ ተወላጅና የደብረ ሐንታው አባ ገብረ ማርያም አማካሪው ነበር። ድርሰቱንም ሲደርስ ቤት እየመታና በአምስት ስንኝ እየከፋፈለ ነው። አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም ከመስከረም ፳፮ ቀን እስከ ኅዳር ፭ ቀን ማኅሌተ ጽጌን ለመቆምና የጽጌን ጾም ለመጾም በየዓመቱ በደብረ ብሥራት እየመጡ ይሰነብቱና ቁስቋምን ውለው ወደየ በአታቸው ይመለሱ ነበር።›› ከአባታችን የገድል ክፍል ለመረዳት እንደሚቻለው አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም የጽጌን ማኅሌት መቆም ወቅቱንም በፈቃዳቸው መጾም የጀምሩበ ዘመን በዐሥራ አራተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው።

ከዚያ ወዲህ ግን ጥቂት በጥቂት እያለ አብያተ ክርስቲያናት በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ጀመሩ። ጥቂት መነኩሳትና አንዳንድ ምእመናን በፈቃዳቸው ወቅቱን መጾም ጀመሩ። በዘመናችን በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ስለ ተለመደ ከማታው በሦስት ሰዓት ይደወላል። ሴት ወንዱ፥ ትንሹም ትልቁም ይሰባሰባል፤ ማኅሌተ ጽጌው እየተዜመ፤ አስፈላጊ የሆነው በጽናጽል በከበሮ እየተወረበና እየተሸበሸበ እስከ ጥዋቱ ፲፪ ሰዓት ድረስ ተቁሞ ይታደራል። የጽጌ ጾም የውዴታ (የፈቃድ) እንጂ የግዴታ አይደለም። የእመቤታችን ስደት በማሰብ ከትሩፋት ወገን የሚጾም ስለሆነ ምእመናን ሁሉ እንዲጾሙት አይገደዱም፤ የሚጾመው የማይጾመውን ለምን አልጾምክም ብሎ ሊፈርድበት ስለ ራሱም እየጾምኩ ነው ብሎ መናገር አይገባውም። የፈቃድ መሆኑንም የሚያሳየው ይኸው ነው፤ የማይጾመውም በልቡ ያመሰግናል፤ ስደቷን እያሰበ ማኅሌቷን እየዘመረ ያሳልፋል።

አምላካችን እግዚአብሔር የጽድቅ ፍሬን ሳናፈራ በሞት እንዳንወሰድ በቸርነቱ ይጠብቀን፤ አሜን፡፡

#ማኅበረ_ቅዱሳን

https://t.me/menfesawe12

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Oct, 17:27


"የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት ለኾነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል።"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Oct, 19:02


የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው፤ ኪሩቤል ለሚሸከሙት ዙፋኑ ሆንሽ፤ የተከበርሽ ሆይ እናመሰግንሻለን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ እርግብ ሆይ ስምሽን በልጅ ልጅ እንጠራለን፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Oct, 19:02


‹‹የአምላክ እናት ሆይ! ተራዳኢነትሽ እኛን ለማዳን ብርቱ ነው፡፡ የእኛን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ለማድረስ ሌላ (ተራዳኢ) አትሺም፡፡ የሕይወት እናት ነሽ፤ ይህም እውነትና የታመነ ነው፡፡ አዳም ዳግም የተሠራብሽ እርሾ ነሽ፡፡ ሔዋን ከኃፍረት ነጻ የወጣቺብሽ ነሽ፡፡ አንቺን ካልቀደምሽልን በቀር ማንም ፍጹም መንፈሳዊ መሆን አይቻለውም፤ ማንም እግዚአብሔርን በመንፈስ ማምለክ አይችልም፡፡ በአንቺ በቅድስተ ቅዱሳን ካልሆነ በቀር ማንም እግዚአብሔርን በማወቅ አይመላም፤ በአንቺ እንጂ፣ ካለ አንቺ ማንም ካለአንቺ አልዳነም፡፡ ድንግል እናታችን ሆይ! እግዚአብሔርን ገንዘብ ካደረግሽው ከአንቺ በቀር፣ ያለአንቺ ማንም ምሕረትን በጸጋ አላገኘም፡፡ ስለ ኃጥኣን የአንቺን ያህል ማን ተጋድሎ ፈጸመ? ንስሐን ስለሚሹ ኃጥኣን ማን የአንቺን ያህል ድርሻውን ተወጣ፣ ማንስ ለመነ?››
--
https://t.me/menfesawe12

6,035

subscribers

335

photos

12

videos