መዲነቱል ዑሉም @medinetululoom Channel on Telegram

መዲነቱል ዑሉም

@medinetululoom


https://t.me/medinetululoom

[email protected]

መዲነቱል ዑሉም (Amharic)

መዲነቱል ዑሉም የቴሌግራም ክፍል ነው ውጤት ያለው ቦታ ማብሰሽ ላላተጅ ይህን ገንዘብ ለመከተል እና ለመዝገብ በሚል ሰዎችን በፍጥነት ወቅታዊ መረብ አስተያየታትን ለማስገባት ነው። መዲነቱል ዑሉም በአልሴር እና በኢንሰትጣት ላይ በሚገኙበት ጊዜ ታሪካዎችን እና መረጃዎችን እንድናገኙ ለማከብረብ እንዲሁም መረጃዎቹን በቀላሉ ለመፈጸም እንዲሁም በተፈጠረ ጊዜ የምንፈጸም የዝርዝር መረጃዎቹን እና በጤንነታችሁ ልምዳችሁን የምንቀጥለውን ሰዎችን ምንጭ።ለማለት በባህል በሚፈልጉ ተድያሞችን ሰውሰው እና በማንም እርምጃ እንዲሁም ያገናኘውን የምንከፈል ነገር እንድናሳርፉ።

መዲነቱል ዑሉም

23 Nov, 02:31


أَصْـبَحْنا وَأَصْـبَحَ المُـلْكُ لله وَالحَمدُ لله ، لا إلهَ إلاّ اللّهُ وَحدَهُ لا شَريكَ لهُ، لهُ المُـلكُ ولهُ الحَمْـد، وهُوَ على كلّ شَيءٍ قدير ، رَبِّ أسْـأَلُـكَ خَـيرَ ما في هـذا اليوم وَخَـيرَ ما بَعْـدَه ، وَأَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما في هـذا اليوم وَشَرِّ ما بَعْـدَه، رَبِّ أَعـوذُبِكَ مِنَ الْكَسَـلِ وَسـوءِ الْكِـبَر ، رَبِّ أَعـوذُ بِكَ مِنْ عَـذابٍ في النّـارِ وَعَـذابٍ في القَـبْر.


☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
صباح الخير

መዲነቱል ዑሉም

22 Nov, 04:03


إنا لله وإنا إليه راجعون
የኡስታዛችን ኢልያስ አባት ወደ ማይቀረው ሀገር ተሸጋግረዋል አላህ ከፍ ያለውን ጀነተል ፊርደውስ ከሚወዱት ጋር ያርጋቸው እያልን የመዲነቱል ዑሉም አስተማሪዎችና ተማሪዎች የተሰማንን ታላቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰባቸውም መፅናናትን ከፈጣሪያችን አሏህ እንጠይቃለን::

(በያለንበት ፉቲሀ እንቅራላቸዉ)

መዲነቱል ዑሉም

21 Nov, 19:18


Live stream finished (46 minutes)

መዲነቱል ዑሉም

21 Nov, 18:32


Live stream started

መዲነቱል ዑሉም

21 Nov, 13:10


ምሽትዎን በመዲነቱል ኡሉም መድረሳ🌼🌼🌼
ዘወትር ሀሙስ 3:30 የሰይዳችንን ሸማኢል ኪታብ በቀጥታ በቻናላችን ።

ቀጠሮዎትን ከኛ ያድርጉ።

صلوا على خير خلق الله

💫اَللَّهُمَّ صَلِّ عَلى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ اَلْفَاتِحِ لِمَا أُغْلِقَ وَ اَلْخَاتِمِ لِمَا سَبَقَ نَاصِرِ الْحَقِّ بَالْحَقَّ وَ الْهَادِي إلى صِرَاطِكَ الْمُسْتَقِيمِ وَ عَلَى آلِهِ حَقَّ قَدْرِهِ و مِقْدَارِهِ الْعَظِيم

መዲነቱል ዑሉም

21 Nov, 11:35


ከከዋክብት መንደር ክፍል 2


። በመካው የዳዕዋ ዘመን አብረዋቸው ሆኑ። ወደ መዲና ሲሰደዱ፣ በዋሻው ታሪክና ከዚያ በኋላ እስኪሞቱ ድረስ ከርሳቸው አልተለዩም።

በተቡክ ዘመቻ የሙሰሊሞችን አርማ ተሸካሚ ነበሩ። በዘጠነኛው ዓመተ ሂጅራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሕይወት እያሉ የሐጅ ሥርዓትን መርተዋል።



ሰይዳችን አቡበክር አስሲዲቅ ለነቢያችን በመከላከል አንደኛ ነበሩ። በነፍሳቸውና በሀብታቸው ይከላከሉም ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ እየሰገዱ ሳለ ዑቅባ የተባለ ሰውዬ ይመጣና አንገታቸውን በለበሱት ሻል አንገታቸውን አጥብቆ ያንቃቸዋል። ያኔ ሰይዱና አቡበክር መጥተው ዑቅባን ገፍትረው “እንዴት ጌታዬ አሏህ ነው ስላለ ብቻ ትጋደሉታላችሁ? ለነቢይነቱም መስካሪ ተአምራት ይዞ እያለ ትጋደሉታላችሁ?” በማለት ተከላከሉላቸው።
:
በእውነትም ሲዲቅ “እውነተኛ ኖዎት” ነቢዩ ንም (ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጣም ይወዱ የነበሩ ታላቅ ሷሓቢይ ናቸው።

👉ከርሳቸው ሞት በኋላም እርሳቸውን ተክተው የሙስሊሞች ኸሊፋ ሆነዋል። የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ምትክ (ኸሊፊቱ ረሱሊላህ) የሚል ማእረግም በሙስሊሞች አግኝተዋል።
አቡበክር (ረ.ዐ) በወገኖቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እና ተግባቢ ሰው ነበሩ።
በቁረይሽ የዘር ሐረግና ታሪክ እውቀትም አቻ አይገኝላቸውም።
ጸባየ መልካም ነጋዴ ነበሩ። ሰዎች የርሳቸውን እውቀት፣ ተሞክሮና መልካም ባህሪ በመሻት በጣም ይቀርቧቸው ነበር። ከርሳቸው ጋር መቀማመጥንም ይወዱ ነበር።በርሳቸው እጅ፣ ዑስማን፣ ጦልሐ፣ ዙበይር፣ ሰዕድ እና ዐብዱረህማን ኢቢን አውፍ ሰለሙ።

የዕቁብ ኢቢን ሱፍያን በታሪክ ዘገባቸው እንዳወሱት፣ አቡበክር ሲሰልሙ አርባ ሺህ (የወርቅ ሳንቲሞች) ነበሯቸው። ወዲያውኑ በአላህ መንገድ መጸወቱት። ለአላህ ሲሉ ስቃይና መከራ ያስተናገዱ ሰባት ባሪያዎችን ገዝተው ነጻ ለቀቁ። እነርሱም ቢላል፣ ዓሚር ኢቢን ፋሀይራህ፣ ዚኒራህ፣ ነህዲያህንና ልጇን፣ የበኒ ሙእመል እንስት አልጋይና ኡምሙ ዓቢስ ናቸው።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
“የትኛውም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ይከብደዋል። ለመቀበልም ያመነታል። አቡበክር ሲቀር። እርሱ ግን ወዲያውኑ እንደጠራሁት ሳያመነታ ተቀበለኝ።

ሱላችን እነዲህ ብለዋል
“በባልደረባነትና በገንዘብ ከማንም በላይ የደገፈኝ አቡበክር ነው። ከአምላኬ ውጭ የመጨረሻውን ፍጹማዊ ፍቅር የምለግሰው ሰው ቢኖር ኖሮ ያ ሰው አቡበክር ይሆን ነበር። ቢሆንም የእስልምና ወንድማማችነት እና ፍቅር አስተሳስሮናል።” (ቡኻሪ፣ ሙስሊምና ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ቢከተብ ቢከተብ አያልቅም

መዲነቱል ዑሉም

20 Nov, 18:20


ከመተኛታችን በፊት

ውዱእ እናድርግ

ሲዋክ እንጠቀም

የቻልነውን በሰላት እንበርታ

ሱረቱል ሙልክ

አያተል ኩርስይ አንዘንጋ

የለሊቱን ክፍል ለመነሳት ኒያ እናርግ

ሌሉቱን በተውበት አሳምረን እንጀምር።

መልካም መናም ለማየትም አተኛኘታችንን እናድስ
አሏህ የወፍቀን

《በመናም ያየኝ ሰው በትክክል እኔን አይቶኛል ሸይጧን በኔ አይመሠልምና》ብለዋል
《مَنْ رَآنِي فِي الْمَنَامِ فَقَدْ رَآنِي ؛ فَإِنَّ الشَّيْطَانَ لَا يَتَمثّلُ بِي



ነገ ሀሙስ ነው መፆምን አትዘንጉ

መዲነቱል ዑሉም

20 Nov, 07:42


ከረሱል አንደበት
ክፍል 2
ሂጃማ–ዋግምት–cupping ጥቅም ከረሱል አንደበት

إنَّ أفْضَلَ ما تَداوَيْتُمْ به الحِجامَةُ
ከምትታከሙባቸው ህክምናዎች በላጩ ዋግምት ነው

የዋግምት ህክምና የሰውነት አካል ላይ እንደ ብርጭቆ ወይንም ኩባያ ያለ እቃ በመድፋት እና ቆዳን በመምጠጥ የሚካሄድ ጥንታዊ የባህል ህክምና


በሀዲስም ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምርጥ ህክምና መሆኑን ከመምከር አልፈው ራሳቸውም ተሰርተዋል።

እጅግ ብዙ ለሆኑ
በሽታዎች እንደሚጠቅም ረሱላችን ነግረውናል

በዋግምት/ሂጃማ(cupping) አማካኝነት የሚወጣው ደም ምንድን ነው?
በዋግምት አማካኝነት የሚወጣው የተመረዘና(እና በጣም የጠቆረ ደም በህክምናው አጠራር congestion (tharembosis) statgmant blood ይባላል። ይህ ደም በደም መተላለፊያ ባንባዎች ላይ በመርጋት የደም ዝውውርን በማስተጓጎል የተለያዩ በሽታዎችን ያመጣል።
.።
የዋግምት/ሂጃማ(cupping) ጥቅሞች
ለራስ ምታት ፡ጭንቀትእና ቅጥቅጣት
ለአስም እና ሳይነስ
ለወገብ ህመም
ለነርቭ
ለአላርጅክ
ለጡንቻ መሸማቀቅ
ለሪህ፡ ለብርድ፡ቁርጥማት
ለድም ግፊት

ዋግምት ቆሻሻ ደምን ከማስወጣት ባለፈ የደም ትቦዎችን የማፅዳት እና ጤነኛ የደም ዝውውር እንዲኖር የማድረግ ኃይል ስላለው እንደ ብጉር፣ ችፌ ፣ ምርቅዝ እና የመሳሰሉ የቆዳ በሽታዎችን ለማከም እንደሚረዳ የዘርፉ ባለሙያዎችና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡

ተጨማሪ ሀዲሶች

قل رسول الله صلى الله عليه وسلم : إِنْ كَانَ فِي شَيْءٍ مِنْ أَدْوِيَتِكُمْ خَيْرٌ فَفِي شَرْبَةِ عَسَلٍ، أَوْ شَرْطَةِ مِحْجَمٍ، أَوْ لَذْعَةٍ مِنْ نَارٍ وَمَا أُحِبُّ أَنْ أَكْتَوِيَ

- وَقَالَ الأَنْصَارِيُّ: أَخْبَرَنَا هِشَامُ بْنُ حَسَّانَ: حَدَّثَنَا عِكْرِمَةُ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ احْتَجَمَ فِي رَأْسِهِ.

ሂጃማ የነቢዩ ሱና ነው!

መዲነቱል ዑሉም

20 Nov, 02:27


أَصْـبَحْنا وَأَصْـبَحَ المُـلْكُ لله وَالحَمدُ لله ، لا إلهَ إلاّ اللّهُ وَحدَهُ لا شَريكَ لهُ، لهُ المُـلكُ ولهُ الحَمْـد، وهُوَ على كلّ شَيءٍ قدير ، رَبِّ أسْـأَلُـكَ خَـيرَ ما في هـذا اليوم وَخَـيرَ ما بَعْـدَه ، وَأَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما في هـذا اليوم وَشَرِّ ما بَعْـدَه، رَبِّ أَعـوذُبِكَ مِنَ الْكَسَـلِ وَسـوءِ الْكِـبَر ، رَبِّ أَعـوذُ بِكَ مِنْ عَـذابٍ في النّـارِ وَعَـذابٍ في القَـبْر.


☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
صباح الخير

መዲነቱል ዑሉም

19 Nov, 17:21


ከነብያችን ተአምራቶች

لقد أرسلنا رسلنا بالبينات

ከእለታት በአንዱ ቀን ቁረይሾች ለነብያችን ተአምር እንዲያሳዩ ጠየቋቸው። ወደ ሙሉ ጨረቃ ተመልክተው ጨረቃዋን እንዲከፍሉ ሀሳብ ሰነዘሩ። አሏህም ተአምሩን በኛ ነብይ እጅ ሰራ ጨረቃይቱ ሁለት ቦታ ተሰንጥቃ ተንጣለለች። በአንዴም አላበቃ ተደገመ።
ቁረይሾችም አሉ ። አይናችን ላይ ደገመብን።
ይህንን ለማጥራት ከመሀላቸው አንድ ሰው ለንግድ የወጡትን ይህንን ጉድ ካዩ እንጠይቃቸው ሚል አስተያየት አቀረበ።
ከተለያየ ቦታ የመጡ ነጋዴዎችም ተጠየቁ። እነሱም አሉ በዛች ቀን ጨረቃ ተከፍላ ስትገጠም አይተናል። ሆኖም ግን ቁረይሾች በዚህም ማመን አልፈለጉም። አሏህም በቁርአን ላይ እንዲህ ይላል

اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ (١) [ሱረቱ አል ቀመር: 1]

* ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡


وَإِن يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ (٢) [ሱረቱ አል ቀመር: 2]

* ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡


وَكَذَّبُوا وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ وَكُلُّ أَمْرٍ مُّسْتَقِرٌّ (٣) [ሱረቱ አል ቀመር: 3]

* አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡


ሳይንስ ከቁርአን ጋር ሲጋጭ ካያችሁ ሳይነሱ ገና አጥንቶ አልደረሰበትም ማለት ነው። በዚህ ክስተት ዙርያ ሳይንስ ትክክለኛነቱን አረጋግጧል። ይህ በቁርአን ማመን ለማይፈልጉ ትልቅ መንገድ ነው። naasa ያወጣውን መግለጫ ማየት ይቻላል።
ፎቶም ከላይ ተያይዟል

መዲነቱል ዑሉም

19 Nov, 13:19


✍️✍️✍️
በህይወታችን ሁሉ ወኪል ምናደርገው አደራ ምንለው። ታሪካችንን እንደሚቀይር ምናምነበት፣ ከተስፋ ቢስነት ወደ ወኔ ማእከል ሚያስገባን። ከባድ ሚመስለውን ማዕበል አሳልፎ ወደ ውቡ ደሴት ሚያዘልቀን። የዱንያም የአኸራም ጭንቃችንን በሙሉ ልብ ጀባ ብለነው ማናፍርበት።

🌼🌼አልወኪል🌼🌼

رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا (٩) [ሱረቱ አል ሙዘሚል: 9]

* (እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ وَكَفَى بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا (٥٨) [ሱረቱ አል ፉርቃን: 58]

* በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡

አልወኪል ባልክ ቁጥር መመክያህ፣ መጠግያህ ፣ተያዥህ ፣ዋስህ እንደሆነ ትረዳለህ። ከአንተ እንጂ ከወከልከው ጌታህ በላይ የሚሆን ነገር በዱንያ እንደሌለ ይገለጥልገል።

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْعَزِيزِ الرَّحِيمِ (٢١٧) [ሱረቱ አሽ ሹዐራእ: 217]

* አሸናፊ አዛኝ በኾነው (ጌታህ) ላይም ተጠጋ፡፡

አል ወኪልን ስታስብ ረፍት ይሰማሃል። ወደፊት እሱን በተሻለ ሁኔታ እንዴት ልገዛው እንጂ እንዴት ልኑር ሀጃዬ እንዴት ሆኖ ይሆን ሚለው ገድም አይሰጥህ። የእፎይታ ህይወት ይኖርሀል። ሌሎች በሰበብ ሲንጠለጠሉ አንተ ሰበብ እያደረስክ ወኪል ካደረከው ጌታህ መልካምን ትከጅላለህ።
ትጠነክራለህ።የጥንካሬህ ምንጭ ጠንካራ ምርኩዝ እንደሆነ ጥቂቶች እንጂ አያውቁም።

وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ

🌟🌟🌟* በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡
ጥያቄ??
ከአሏህ ስሞች ዱአ ስታደርጉ ቀድሞ አፋችሁ ላይ ምን ይመጣል

መዲነቱል ዑሉም

19 Nov, 05:40


🌹ሰላተ ዱሃ መስገድ 🌹

ሰላተ ዱሃ
ፀሀይ ከወጣች በኃላ የሚሰገድ የዝሁር ወቅት ከመግባቱ በፊት ሚጠናቀቅ።
ዝቅተኛው 2 ረከአ
መካከለኛ 4 ረከአ
ከፍተኛው 8 ረከአ የሆነ
የሰው ልጅ 360 አካባቢ መገጣጠሚያ አሉት በነዚህ ሰዳቃ ማውጣት አለበት እንዴት ?
ሰላተ አዱሀ ላይ የሚሰገድ 360የሰውነት ክፍሎች ላይ ሰደቃ አወጣ ማለት ነው ፡ 2.4.8. አላህ ያገራለት ይስገድ

አላህ ያግራልን

መዲነቱል ዑሉም

18 Nov, 15:32


◦ ስም ሙሀመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም
◦ የአባት ስም አብዱሏህ ኢብን አብዱል ሙጠሊብ ኢብኑ ሀሺም ኢብኑ አብዲመናፍ ኢብኑ ቁሰይ ኢብኑ ኪላብ ኢብኑ ሙር ራ ።
◦ የእናት ስም አሚና ቢንት ወህብ ኢብኑ አብዲ መናፍ ኢብኑ ዙህራ ኢብኑ ኪላብ ኢብኑ ሙር ራ
◦ እናታቸው እና አባታቸው የዘር ግንዳቸው ኪላብ ላይ ይገናኛል
◦ የትውልድ ቦታ መካ
◦ የትውልድ ዘመን የዝሆኑ አመት በመባል ሚታወቀው ሰኞ ቀን ወርሀ ረቢአል አወል
◦ አባታቸው የሞቱት ነብዩ ሙሀመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሆድ ውስጥ እያሉ በወጣትነታቸው ነበር።
◦ ከእናታቸው በኋላ ያጠባቻቸው የአቡለሀብ የቀድሞ ባርያ የነበረቸው ሱወይባ ትባላለች። 4 አመታቸው ድረስ ሐሊመቱ ሰዕዲያ አጥብታቸዋለች።
◦ የጥቢ አባታቸው የሐሊማ ባለቤት አል ሓሪስ ኢብኑ አብዱል ዑዝዛ ነው።
◦ እናታቸው ነብዩ ሙሀመድ 6 አመት ሲሆናቸው የአባታቸውን ቀብር ለመዘየር ወደ መዲና እየሄዱ ሳለ። መካና መዲና መሀል ምትገኝ አብዋእ ምትባል ቦታ ላይ አርፈዋል
◦ እስከ ስምንት አመታቸው ድረስ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ ጋር በሀበሻይቱ ኡሙ አይመን ተንከባካቢነት አደጉ።
◦ ከስምንት አመታቸው በኋላ አያታቸው ስለሞቱ አጎታቸው አቡጧሊብ የማሳደጉን ሀላፊነት ተቀበሉ
◦ ይቀጥላል

መዲነቱል ዑሉም

18 Nov, 08:46


ሐሊመቱ አሰዕዲየህ ስለ ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) የልጅነት ዘመን ስትናገር «ጽልመት በወረሰው ሌሊት ብርሃን የሚሆነን የነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ብሩህ ፊት እንጂ መብራት አልነበረም» ትላለች።

መዲነቱል ዑሉም

17 Nov, 18:21


ከመተኛታችን በፊት የሚባል ዱዓ

بِاسْمِكَ رَبِّي وَضَعْتُ جَنْبِي، وَبِكَ أَرْفَعُهُ، فإِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا، بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِينَ

ጌታዬ ሆይ በስምክ ጎኔን አሳርፌያለሁ፡፡ በስምህም አነሳዋለሁ፡፡ ነፍሴን በዚያው ካስቀራሀት እዘንላት፡፡ ከላክካት ደግሞ መልካም ባሮችህን በምትጠብቅበት ስልትህ ጠብቃት፡፡

ቢስሚከ ረብቢ ወዳእቱ ጀንቢ ወቢከ አርፈኡህ ኢን አምስከተ ነፍሲ ፈርሐምሃ ወኢን አርሰልተሃ ፈሀፈዝሃ ቢማ ተሀፈዝ ቢሂ ኢባደከ አስሳሊሂን

➡️➡️ሱረት አል-ሙልክ ከቁ1-30
ከመተኛታችን በፊት ሁል ግዜ መቅራት
ከቀብር ቅጣት ነጻ ታወጣለች

➡️➡️ወዱእ አድርጎ በመተኛትህ እስቲግፋር የሚያረግ መለይካ ይመደብልሀል።


💚💚 ረሱልን በመናቤ ማይበት አዳር ይሁን ብለህ የደጋጎች የሳልሆችን አተኛኝ ተኛ። ለሙእሚን እንቅልፉም ኢባዳ ነውና።
መልካም አዳር።🌷🌷

https://t.me/medinetululoom

ነገ ሰኞ ነው መፆም አትርሱ

መዲነቱል ዑሉም

16 Nov, 23:07


"አንዋዑ-ሶላዋት" ‹‹የሶላት አይነቶች››
ይነበብ ይነበብ ይነበብ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሃ 2) የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አህዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሶላቱ-ለይል፡-
- ከፈርድ ሶላት በኋላ የተወደደ የሶላት አይነት ቢኖር በለሊቱ ክፍል የሚሰገደው ሶላቱ-ለይል ነው፡፡
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም(ጾም) ነው፡፡ ከፈርድ ሶላት ቀጥሎ ከሶላት ሁሉ በላጩ የለይል ሶላት ነው" (ሙስሊም 1163)፡፡
- የለይል ሶላት አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው የሷሊሆች ሃይማኖታዊ ልማድ ነው፡-
አቢ ኡማመተል-ባሂሊይ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የለሊት ሶላትን አደራችሁ! እሱ ከናንተ በፊት የነበሩት የሷሊሆች ልማድ ነው፣ ወደ ጌታችሁም መቃረቢያ ነው፣ ኃጢአትንም ማስተሰረያ ነው፣ ከወንጀልም ከልካይ ነው" (ቲርሚዚይ 3549፣ ሐኪም አል-ሙስተድረክ 1/308፣)፡፡
- የለይል ሶላት የሙተቂኖች(አላህን ፈሪዎች) እና እውነተኛ የአር-ራሕማን ባሮች መገለጫ ነው፡-
"አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮቹ ውስጥ ናቸው። ያንን ጌታቸው የሰጣችውን ተቀባዮች ሆነው፤ (በገነት ውስጥ ይሆናሉ)። እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሠሪዎች ነበሩና። ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ። በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነሱ ምሕረትን ይለምናሉ" (ሱረቱ-ዛሪያት 15-18)፡፡
"የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ ሰላም የሚሉት ናቸው። እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው።" (ሱረቱል ፉርቃን 63-64)፡፡
"እርሱ የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶች ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የመግገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሐዲ ነውን?በለው)፤ እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይተካከላሉን? በላቸው፤ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።" (ሱረቱ-ዙመር 9)፡፡
- የለይል ሶላት ሰዎችን ጀነት በሰላም ለማስገባት ምክንያት ከሚሆኑት መልካም ተግባራት አንዱ ነው፡-
ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላም(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "እናንተ ሰዎች ሆይ! (በመሐከላችሁ) ሰላምታን አብዙ፣ ምግብንም አብሉ፣ ሰዎች በተኙበት በለሊት ስገዱ፣ ጀነትን በሰላም ትገባላችሁና" (ቲርሚዚይ 2487)፡፡
- የዱንያም ሆነ የአኼራ ሐጃችንን አላህን በመለመን ቀጥታ ምላሽ የምናገኝበት አንዲት ሰዓት አለች የተባለችውም በዚሁ በለሊቱ ወቅት ነው፡፡ አላህ የባሮቹን ዱዓእ 24/7 ሰሚ የሆነ አምላክ ቢሆንም፡ ይህቺ ሰዓት ግን ምንም አይነት ዱዓእ ተመላሽ የማይሆንባት፡ ወዲያው ምላሽ እንደሚሰጥባት ሙሉ ቃል የተገባላት ልዩ ሰዓት ናት፡-
ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡- ‹‹በለሊት ውስጥ አንዲት ሰዓት አለች፡፡ (ይህችን ሰዓት) ማንም ሙስሊም የሆነ ሰው አላህን የዱንያም ሆነ የአኼራን መልካም ነገር የሚጠይቅ ሆኖ አያገኛትም፡ አሱኑ(የለመነውን) የሰጠው ቢሆን እንጂ!፡ እሱም ሁሌም በየለሊቱ ነው›› ሲሉ ሰማኋቸው" (ሙስሊም 757)፡፡
- ሶላቱ-ለይልን መነሳት የሚፈልግ ሰው ማታ በሚተኛበት ጊዜ ነይቶ መተኛት አለበት፡፡ እንቅልፍ አሸንፎት እንኳ ለሊቱ ቢያመልጠው በኒያው ያገኘው ዘንድ!፡-
አቢ-ደርዳእ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከለሊቱ ክፍል ተነስቶ ለመስገድ የነየተ ሆኖ ወደ መኝታው የመጣ ሰው፡ እስኪያነጋ ድረስ እንቅልፍ ቢያሸንፈው፡ በነየተው ሰበብ ይጻፍለታል፡፡ እንቅልፉ ደግሞ ከጌታው የሆነ ሶደቃ ይሆንለታል" (ነሳኢይ 3/258፣ ሐኪም፡ አል-ሙስተድረክ 1/311)፡፡
- ለለይል ሶላት አላህ ወፍቆት የሚነሳ ሙስሊምም በነቃና በተነሳ ጊዜ እንዲህ ይበል፡-
عن عُبَادَةُ بْنُ الصَّامِتِ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: " مَنْ تَعَارَّ مِنَ اللَّيْلِ، فَقَالَ: لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، الحَمْدُ لِلَّهِ، وَسُبْحَانَ اللَّهِ، وَلاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ، وَلاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ، ثُمَّ قَالَ: اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي، أَوْ دَعَا، اسْتُجِيبَ لَهُ، فَإِنْ تَوَضَّأَ وَصَلَّى قُبِلَتْ صَلاَتُهُ "
ዑባደተ ኢብኑ-ሷሚት(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከለሊቱ ክፍል ነቅቶ፡- ‹‹ላ ኢላሀ-ኢለላህ፣ ወሕደሁ ላሸሪከ-ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዓላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፣ አልሐምዱ-ሊላህ፣ሱብሓነላህ፣ ወላ-ኢላሀ ኢለላህ፣ ወላሁ አክበር፣ ወላ ሐውለ፡ ወላ ቁወተ፡ ኢላ-ቢላህ›› ያለ ሰው፡ ከዛም ‹‹አላሁመ-ኢግፊር ሊ›› ቢል ወይም ዱዓእ ቢያደርግ ተቀባይነትን ያገኛል፡፡ ዉዱእ አድርጎ ከሰገደም ሶላቱ ተቀባይነትን ያገኛል" (ቡኻሪይ 1154)፡፡
- ሶላቱ ለይልን ለመስገድ የተነሳ ሙስሊም መጀመሪያ ቀለል ባሉ ሁለት ረከዓዎች ሶላቱን መክፈቱ የተወደደ ተግባር ነው፡፡ ከዛም አቅሙ የፈቀደውን ያህል መስገድ ይችላል፡-
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከናንተ አንዳችሁ ለሊት (ለሶላት) ከተነሳ፡ ሶላቱን ቀለል ባሉ ሁለት ረከዓዎች ይክፈት" (ሙስሊም 768)፡፡
አዒሻህ(ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለሊት ለመስገድ ሲነሱ ሶላታቸውን ቀለል ባሉ ሁለት ረከዓዎች ይከፍቱ ነበር" (767)፡፡

አላህ ይወፍቀን 🤲🤲🤲🤲🤲

3,905

subscribers

263

photos

12

videos