Wollo university kombolcha campus student union @wollostu Channel on Telegram

Wollo university kombolcha campus student union

@wollostu


ይህ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች ህብረት በኩል መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇
https://t.me/wollostu

👇👇👇👇👇👇
ለጥያቄ፡ ለአስተያየትወ ይሄን ይጠቀሙ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
@Wollouniversitystudentunionbot

Wollo University Kombolcha Campus Student Union (Amharic)

ይህ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች ህብረት በኩል መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ትራንስ፣ በተማሪዎች ህብረት በኩል እና ውይይት ጠቀም የሚሆንን የሚገኝ ቻናል ነው፡፡ በቴክኖሎጂ የተነሳውን ስለሆነ ማንኛውንም ቴክንኖል በመጠቀም ከተመለከቱ በፊቻ እንረዳን፡፡ በቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለበለጠ መረጃ በሚከተለው ችሎታ ለበቀለው በተማሩ የቴክኖሎጂ ኮምቦልቻ የሚያምናን እድል ነው፡፡ ያልቻለው ችሎታ መተከል ማድረግ እንችላለን፡፡

Wollo university kombolcha campus student union

23 Jan, 19:19


Channel photo updated

Wollo university kombolcha campus student union

20 Jan, 17:40


ለተማሪዎች ህብረት የፓርላማ ተወካይ ላላስመረጣችሁ የትምህርት ክፍሎች

ውድ ተማሪዎች የ2017/18 የተማሪዎች ህብረት ፓርላማ እያስመረጥን መሆኑ ይታወቃል ከዚህ በፊት ማስታወቂያ በማውጣት ጥሪ ቢደረግም ተገኝታችሁ አልመረጣችሁም በመሆኑም በወጣላችሁ መርሃ ግብር ተገኝታችሁ እንድትመረጡ እያሳሰብነ ባትገኙ ያለተወካይ የምናልፈው ይሆናል።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

20 Jan, 08:18


ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ ባጋጠመን የመብራት መቆራርጥ ምክንያት የምግብ ቤት መግብያ ስዓት እስከ 6:00 ስዓት የተራዘመ መሆኑን እናሳወቃለን።

የተማሪውች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

18 Jan, 18:02


ለ1ኛ አመት ተማሪዎች ለሆናችሁ ለድጂታል መታወቂያ ያልሞላችሁ በተለቀቀውሊንክ መረጃችሁን እንድትጭኑ በተጨማሪም የተሟላ መረጃ ያልሞላችሁ ስምዝርዝራችሁ ከዚህ በታች ስላለ በማየት እንድታስተካክሉ እያሳወቅነ የመጨረሻ ጊዜ እስከ ቀን 12/05/2017 እንድታጠናቅቁ።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScMLjFG45jvtXAyTw75yvEbxY4NPFnZtQJ8WfjN3eEiCc6rDg/viewform?usp=header

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

16 Jan, 08:03


NOTICE
To: All Unregistered First- and Second-Year Students
Subject: Urgent Registration Update
This is to inform all first- and second-year students who have not yet completed their registration process to report to the Registrar's Office (Room 902) TODAY, 08/05/2017.
Failure to complete your registration by the end of the day will result in being unable to attend classes, exams, and other academic activities.
Registrar's Office
KIoT STU https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

14 Jan, 14:19


ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ኤክስቴንሽን መርሀ -ግብር አመልካቾችበሙሉ

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት በሪሚድያል መርሀ ግብር ለመማር የምትፈልጉ አመልካቾች ከቀን 06-09/05/2017 ዓ.ም ብቻ ሬጂስትራር ቢሮ ቁጥር 801 በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ፡፡

ሬጅስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

13 Jan, 13:06


በ2017 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲያችን የተመደባችሁ አዲስ የሬሜዲያል ተማሪዎች ነገ ጥር _06/2017 አ.ም. አጠቃላይ ገለጻ _ ስለሚደርግላችሁ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ሰአት፦ 2:30

ቦታ፦ መመረቂያ አዳራሽ

Wollo university kombolcha campus student union

11 Jan, 03:28


ማስታወቂያ
ለሁሉም ከ2ኛ ዓመት በላይ የሆናችሁ ለግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ
ውድ ተማሪዎቻችን የ2017/18 የተማሪዎች ህብረት ፓርላማ እያስመረጥን መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ከዚህ ቀጥሎ በተገለፀው መርሀ ግብር መሰረት በመማርያ ክፍሎቻችሁ በመገኘት ለፓርላማ የሚሆኑ ተወካዮቻችሁን እንድትመርጡ የሚል መልክታችንን እናሳውቃለን።

የኮ/ቴ/ኢን ተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ

Wollo university kombolcha campus student union

07 Jan, 05:02


"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ"

ለመላው የዩንቨርስቲያችን የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎች፣ለመላው የዪንቨርስቲያችን ማህበረሰብ እንኳን ለ2017 ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ።በእርግጥ ብዙዎቻችን ከቤተሰብ ተለይተን ስለምናከብር  እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ማለት እንደመሳለቅ ነው ሊያስብላችሁ ይችላል ነገር ግን ተማሪነት ስናስብ ልክ ህይዎትን ባሰብነ ቁጥር ከድካም በኋላ የሚገኝ እረፍት ፣ከሲቃይ በኋላ የሚመጣ ተድላ፣ከድህነት በኋላ የሚመጣ ሲሳይ ፣ከሞት በኋላ የሚገኝ ዳግም መነሳት እናስባለን ተማሪነትም ከዚህ የህይዎት አዙሪት ውስጥ አንዱ በመሆኑ  በዓሉን  በዪንቨርስቲችን ነገን በማስብ በደስታ እናከብራለንበየዓመቱ የልደት በዓልን እናከብራለን የጌታ ልደት ከሌሎች ልደቶች ይለያል፡፡ እንደምናውቀው የታላላቅ ሰዎችን ልደቶች ማክበር የተለመደ ነገር ነው፡፡ ለአንድ አካባቢ ሕዝብ ወይንም ለሰው ልጆች በሙሉ አንድ ቁምነገር ያበረከተ ሰው ይከበራል፡፡ በዚህም ክርስቶስ ምን አደረገ? ምን አስተማረ? ምን አመጣ? ብለን ልንጠይቅ ይገባል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት የተወለደው ለክብሩ የሚመጥን ፣ዙፋኑን የሚያንፀባርቅ፣ሀያልነቱን የሚመሰክር ሌላ ስፍራ ጠፍቶ ሳይሆን ዝቅ ብሎ መስራት ከፍ ብሎ መታየትን ስለሚያመጣ እንደሆነ መገመት አያዳግትም።
በዓሉ በመተሳሰብና በመረዳዳት የምናልፍበት፤ የታመሙት የሚድኑበት፤በጭንቀትና በመከራ ላይ የሚገኙትን  ሰላምንና መረጋጋትን የሚገኙበት ፤ከአገራቸውና ከቄያቸው ርቀው በስደት ላይ ያሉትን የሚፅናኑበት፤ በየማረሚያ ቤቶች ያሉትን  የምናስብበት፣ ያዘኑትን የምናፅናናበት፣ ወላጆቻቸውን ያጡትን ልጆች የምናበረታታበት፣  እንዲሆን እየተመኘን በዓሉን የሰላምና የደስታ በዓል ያድርግልን።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

02 Jan, 14:31


ለሁሉም 2ኛ ዓመትና በላይ ለሆናችሁ የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ

የ2017/18 የተመሪዎች ህብረት ፓርላማ እያስመረጥን መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም የምርጫ ሂደቱን በተመለከተ እና ለምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ህግና መመሪያ ገለፃ ስለሚደረግ ከ2013-2016 ባች ያላችሁ ተማሪዎች በወጣላችሁ ፕሮግራም _ መሠረት ነገ ማለትም በ25/04/2017 ዓ/ም በመመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ ስንል እናሳውቃለን።

1. የ2013 እና 2014 ባች ተማሪዎች ጧት 2:30

2. የ2016 ባች ተማሪዎች ከሰዓት 9:30

የኮ/ቴ/ኢን ተማሪዎች አገልግሎት

Wollo university kombolcha campus student union

01 Jan, 14:13


ለአንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ
ጊዚዊ መታወቂያ እየተሰጠ ስለሆነ ሪጅስትራል በመሔድ እንድትወስዱ።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

29 Dec, 17:15


https://event.webinarjam.com/register/311/9p5g2i16

Wollo university kombolcha campus student union

29 Dec, 17:15


Registration link for online info session on February 4

Wollo university kombolcha campus student union

28 Dec, 15:58


ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት ስፖርት ውድድር ወሎ ዩኒቨርሲቲ ወክለዉ በእግር ኳስ⚽️⚽️⚽️⚽️ ስፖርት የተመለመሉ ተማሪዎች ስም ዝርዝር:-

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

25 Dec, 09:08


ለከፍተኛ ት/ት ተቋማት ስፖርት ውድድር ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩትን ወክለዉ በእግር ኳስ⚽️⚽️⚽️⚽️ ስፖርት የተመለመሉ ተማሪዎች ስም ዝርዝር:-

ማሳሰቢያ
ነገ በቀን 17/04/2017 ከተማ ለልምምድ ስለምትሔዱ 8:25 ዋናው በር እንድትገኙ
የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

23 Dec, 19:05


በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (RemedialProgram) ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የምዝገባ ቦታ የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች ደሴ ግቢ፣ የማህበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ኮምቦልቻ ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን፤ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ
ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ
የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ
አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ
ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና ሌሎች የግል መገልገያ ቁሳቁሶች መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መምጣት አይፈቀድም፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

Wollo university kombolcha campus student union

17 Dec, 08:33


ለሁሉም የዩንቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት የሚያስፈጉ  ክፍያ የሚጠይቁ መፃሀፍት ከዚህ በታች ባለው ሊንክ  በየትምህርት ክፍላችሁ  እየገባችሁ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
https://drive.google.com/drive/folders/1MQoVSxoFwGZKK4U8Ob35ff_9i-sIXhkG

https://drive.google.com/drive/folders/11PBJeHO9BcKaKBiifMUftBHtjaaduxXQ

https://drive.google.com/drive/folders/124Tg73ClLhEhs09Dt0dipY6-cpYD9DZg


https://drive.google.com/drive/folders/1ahNUFlrzYEqZfEh0mdjkwdiigr-fsE8n

Wollo university kombolcha campus student union

13 Dec, 05:46


የወሎ ዩንቨርስቲ  ኮምቦልቻ  ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ተማሪዎች በሙሉ ቅዳሜ ማለትም 05/04/2017 ከጠዋቱ 3:00  በከፍታ ፕሮጀክት  የዩንቨርስቲን
ቆይታ እና ስነተዋልዶ በተመለከተ የተለያዩ ስልጠናወችን ለመስጠት  የተዘጋጁ ሲሆን በቀኑና እና በስዓቱ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።

ከዕለቱ ዝግጅት በተጨማሪ የእኛን ምልከታ በዚሁ እንግለፅላችሁ"... የወንድን ልጅ አዕምሮ ጨርቅ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁለት ነገሮች ቢኖሩ ያልተገራ የወሲብ ፍላጎት እና ተቀምጦ መመኘት ናቸው።
በወንድ ሕይወት ውስጥ ታላቁ ነጥብ ወሲብ አይደለም። በወንድ ሕይወት ውስጥ ታላቁ የህይወት ነጥብ ትግል ነው።
ሕይወትን መታገል አለብህ። መፋለም አለብህ። መጠንከር አለብህ።
ወሲብ ከተዋጊነት ቀናቶችህ አመሻሽ ላይ የምታገኘው የህይወት ማጣፈጫ ቅመም ነው።
ሴቶች በብልሀታቸው እና በጥበባቸው ይኖራሉ።
ወንዶች ግን በፍልሚያ ነው የምንኖረው። ጠንካራ ታጋይ ካልሆንክ ሕይወት በአይኗ ቂጥ ትገላምጥሀለች።
ከፍ ከፍ ያለችው ሮማ ስትወድቅ ወንዶቿ የት ነበሩ?ሴት ጭን ስር!
አቴና፣ ስፓርታ፣ አክሱም፣ ሞንጎል ሲወድቁስ?
አሁንም ወንዶቻቸው ጭን እየጋለቡ ነበር!..."



የመሰብሰቢያ ቦታ block 3201

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

12 Dec, 08:00


Registration links for the programs:
Registration link for DLS: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZmvNdhvDD30Xhs3dR8qHcfEFQL7d0UTQD-XA5tYUwpcl7cw/viewform?usp=sf_link
Registration link for Career Compass: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe6RVteAe1bAwNMfE-zVllQZuvJ_L0NL25pasj3WhRDSevHKQ/viewform

Wollo university kombolcha campus student union

12 Dec, 07:59


Career Compass120-150 first-year students per university, on a first-come, first-served basis.
Digital Literacy Skills (DLS)280 students per university, across all batches, on a first-come, first-served basis.

Wollo university kombolcha campus student union

10 Dec, 10:55


ማስታወቂያ
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል እግር ኳስ ውድድር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሀሙስ በ03/04/2017 ዓ.ም ምልመላ ስለሚኖር
የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በዕለቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በግቢው ኳስ ሜዳ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡


ማሳሰቢያ
በዕለቱ ያረፈደና ያልተገኘ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

06 Dec, 15:09


ሁሉም የግቢያችን  አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፓስፖርት ሳይዝ (3*4) ፤ ጀርባው (background) ነጭ የሆነ ሶፍት ኮፒ ፎቶግራፍ እንድታዘጁ እና እንድትጭኑ ማሳወቃችን ይታወቃል ስለሆነም ከዚህ በታች ስማችሁ ከተዘረዘራችሁ ተማሪዎች  ወጭ ካላችሁ በድጋሜ እንድትጭኑ በጥብቅ  እናሳስባለን ።
የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

05 Dec, 14:04


ማስታወቂያ

ለተማሪዎች በሙሉ

የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ዉድድር ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ የኢትዬጲያ ዩንቨርስቲዎች ስፖርት ማህበር አሳዉቋል።በዚሀም መሰረት ለተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን በየስፖርት አይነቱ ምልመላ ተካሂዶ ስልጠና በቅርብ መጀመር ስላለበት ከዚህ ጀምሮ እስከ 01/04/2017ዓ.ም ድረስ በተማሪዎች ስፖርትና ክበባት አስተዳደር ቢሮ በአካል እየመጣችሁ እንዲትመዘገቡ ስንል በአክብረት

የዉድድር አይነቶች

1. የወንዶች እግር ኳስ

2. በአትሌቲክስ (አጭርና መካከለኛ ርቀት ሩጫ) በሁለቱም ጾታ

3. ወርልድ ቴኳንዶ በሁለቱም ጾታ

4, የባሀል ስፖርቶች(ቡብ ፣ባለ 12 ጉድጓድ ገበጣ ) እና ቸዝ በሁለቱም ጾታ

• መመረቂያ አዳራሽ የተማሪዎች ስፖርትና ክበባት አስተዳደር

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

04 Dec, 14:07


##ማስታወቂያ
ለኮምቦልቻ ኢንስቲትዩት ስራ አስፈጻሚዎች እና በአጠቃላይ በግቢው ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ በነገው እለት ማለትም ሀሙስ ቀን 26/03/2017ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚካሄደው የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በግቢያችን ከጧቱ 2:30 በስማርት አዳራሽ ስለሚከበር በሰዓቱ በመገኘት እንድትታደሙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል ።


የሴቶች :ህጻናት እና ወጣቶች
ማህ/ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ቡድን

Wollo university kombolcha campus student union

04 Dec, 04:07


ማስታወቂያ

በ2016 ዓ.ም ኤግዚት/የመውጫ ፈተና/ ያልወሰዳችሁ መደበኛ እና ኤክስቴንሽን/ክረምት/ ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 ዓ.ም ት/ት ዘመን የመውጫ ፈተና ያልወሰዳችሁ መደበኛ እና ኤክስቴንሽን/ክረምት/ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም ጥር ወር ውስጥ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እና ከቀን 25- 27/03/2017 ዓ.ም ድረስ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 209 በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ በማለት እናሳስባለን፡፡

ሬጅስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

04 Dec, 04:05


ማስታወቂያ

ምዝገባ ላላካሄዳችሁ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም ት/ት ዘመን የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ በተለያዬ ምክንያት ምዝገባ ያላካሄዳችሁ ተማሪዎች የመጨረሻ የምዝገባ ቀን 25/03/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ምዝገባውን እንድታካሂዱ እያልን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣን ማንኛውንም ተማሪ በቅጣት በቀን 26/03/2017 ዓ.ም ብቻ የሚስተናገድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሬጅስትራር እና አልሙናይ ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

02 Dec, 14:08


ሁሉም የግቢያችን  አዲስ ገቢ የ1ኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፓስፖርት ሳይዝ (3*4) ፤ ጀርባው (background) ነጭ የሆነ ሶፍት ኮፒ ፎቶግራፍ እንድታዘጋጁ እና እስከ ቀን 27/03/2017 ዓ.ም ድረስ  ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንድትጭኑ በጥብቅ እናሳስባለን።
http://10.172.76.20/

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

25 Nov, 16:24


የዚህ መረጃ ባለቤት ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ ።

Wollo university kombolcha campus student union

25 Nov, 16:11


.ማስ ታወቂያ
ለ1ኛ ዓመት አዲስ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
በ2017 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲያችን የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ነገ ህዳር 17/2017 አ.ም. አጠቃላይ ገለጻ ስለሚደርግላችሁ በመመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ሰአት፦ 2:30
ቦታ፦ መመረቂያ አዳራሽ

የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች መ/ግብርና የጋራ ኮርሶች ም/ዲን ጽ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

24 Nov, 15:34


በድጋሜ !!!!

ውድ የዩንቨርስቲያችን አዲስ ገቢ ተማሪወች እንኳን የፍቅር ፡ የሠላም ወደሆነው ዩንቨርስቲያችን በሰላም መጣችሁ እያልን ተማሪወቻችን ወደ ወሎ ስትመጡ ፍቅርን ፡ሠላምን አንግባችሁ እንደመጣችሁ  ሁሉ ዩንቨርስቲያችንም መገለጫው ፍቅር፡ ሰላም ነው በድጋሜ እንኳን  ደህና መጣችሁ ፡፡

ዩንቨርስቲ  ዋናው አላማው እውቀትን ማሳወቅ ሳይሆን ስለእውቀት ምንነትእና ጥቅም ማስረዳት ነው( ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ) ዩንቨርስቲ ትናት ከተማራችሁበት ት/ቤት በምንም አይለይም ትናት ተምራችሁ ትፈተኑ ነበር ዛሬም ተምራችሁ ትፈተናላችሁ ፡፡ ይሄ ፈተና ብዙ አያስደንቃችሁም ምክንያቱም ደግም ነገ ህይዎት ለምትፈትናችሁ ፈተና መጀመሪያችሁ ነው ፡፡ ዛሬ መምህሮቻችን ይፈትኑናል ውጤትም ይሰጡናል ነገ ህይዎት ትፈትናችኀለች ውጤታችሁንም ትሰጣችኀለች፡፡ አለም እያንዳዱ ሰው ልዩ ልዩገፀ - ባህሪ ወክሎ የሚጫወትባት  አስቂኝ የትያትር መድረክ ናት።

ውድ ተማሪዎች ወጣትነት ለእናንተ ምንድን ነው? ወጣትነታችሁ በምን ልታሳልፋት ነው?  ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!
ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!
ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው።
ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...።ወደየት እንደምትሔድ የማታውቅ መርከብ ንፋሡም አያግዛትም አያግዛትም አደል የሚባለው ስለሆነም  እንዴት እንደምንራመድ ሳይሆን ወዴት እንደምንራመድ ማወቅ አለብን አዎ የምንሔደው  ወደ ስኬት ነው? መልሳችሁ አዎ ከሆነ እናተነታችሁን አውቃችሁ ለስኬት ተዘጋጁ ያው መቸስ ውሃ የተቀደደለትን ቦይ አደል የሚከተለው ሰለሆነም እናተም ለስኬት ስትዘጋጁ ስኬት እናተን ይከተላል።
መልካም የትምህርት ዘመን!!!!

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

23 Nov, 19:23


ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንኳን ወደ  ፍቅር  እና  የጥበብ  ዩኒቨርሲቲ  ወደ  ሆነው  ወሎ ዩንቨርስቲ  ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በደኅናመጣችሁ                                                                                     

ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ፍቅር እና የጥበብ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ እያልን የተማሪዎች ኅብረት በተማሪዎች የተዋቀረ ለተማሪዎች እንዲሁም ለጊቢው
ማኅበረሰብ በሙሉ ድልድይ በመሆን ሰላማዊና ውጤታማ የመማር ማስተማር ለማስፈን የሚሰራ
መዋቅር ነው። በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖራችሁ የግቢ ዉስጥ ቆይታ ተማሪዎች ለሚኖራችሁ
ማንኛውም ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት እና ለሚመለከተው አካል በማቅረብ እንዲሁም
የሚያስፈልጋችሁን እገዛ በማድረግ የኮ.ቴ.ኢ ተማሪዎች ኅብረት ሁልጊዜም ከጎናችሁ መሆናችንን እየገለፅን መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።                                                  

በዚህ የቅበላ ፕሮግራም ተማሪዎችን በመቀበል እና በማስተባበር የበኩላችሁን ስትወጡ ለነበራችሁ ተማሪ ህብረት እና አደረጃጀቶች እንዲሁም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ የላቀ ምስጋና እናቀርባለን።🙏🙏🙏                                                                                                                                                                     
❖ አዲስ ገቢ ተማሪዎች አዳድስ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ  https://t.me/wollostu

    ወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ ተማሪዎች ህብረት
መልካም የትምህርት ጊዜ!!!
የጥበብና የፍቅር ዩንቨርሲቲ !!!

Wollo university kombolcha campus student union

22 Nov, 15:50


🔔🔔ማስታወቂያ🔔🔔


ለአንደኛ አመት የ2016ዓ.ም ባች ተማሪዎች በሙሉ።

ወደ አርክቴክቸር ዲፓርትመንት ለመግባት የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁ ከላይ የተያያዘውን ይመስላል።

ማሳሰቢያ
reserved የሚለው ተጠባባቂ ስለሆናችሁ በትግስት ጠብቁ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ት/ት የሚጀመርበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ ይሆናል።

የአርክቴክቸር ት/ት ክፍል

Wollo university kombolcha campus student union

21 Nov, 18:49


የዶርም ምደባ ይሄን አፕ በመጠቀም ማየት ትችላላችሁ

Wollo university kombolcha campus student union

21 Nov, 17:21


ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

ውድ የዩንቨርስቲያችን አዲስ ገቢ ተማሪወች እንኳን የፍቅር ፡ የሠላም ወደሆነው ዩንቨርስቲያችን በሰላም መጣችሁ እያልን ተማሪወቻችን ወደ ወሎ ስትመጡ ፍቅርን ፡ሠላምን አንግባችሁ እንደመጣችሁ  ሁሉ ዩንቨርስቲያችንም መገለጫው ፍቅር፡ ሰላም ነው በድጋሜ እንኳን  ደህና መጣችሁ እያልነ እናተን ለመቀበል የትራንፖርት ስርቪስ ስለተዘጋጀ ደሴ  መነሀሪያ እና ኮምቦልቻ መነሀሪያተገኝታችሁ  እንድትጠቀሙ እናሳስባለን ።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

20 Nov, 18:41


https://forms.gle/962CsWYwfAfwnkvW7

Wollo university kombolcha campus student union

20 Nov, 15:10


🔔🔔🔔Exam date❗️❗️❗️ 🚨🚨🚨

(AADS)

https://t.me/Arch_15

Wollo university kombolcha campus student union

19 Nov, 10:24


Dear all student, Hello and Good day!
Please share this link to students and motivate them to apply.
If any help is needed please tell them to contact us.
https://airi.net/hackathon/safespeak-2024/

airi.net
SafeSpeak-2024

Wollo university kombolcha campus student union

17 Nov, 16:53


ለአንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ
የትምህርት ክፍል (የዲፓርትመንት)  መረጣን በተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ ስለሚሰጥ ረቡዕ (11/3/2017) ከጧቱ 2:30 ላይ መመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ ይሁን። በእለቱ ሁሉም ትምህርት ክፍሎች በሃላፊዎቻቸው አማካኝነት ገለጻ ስለሚያደርጉ ስለምትፈልጓቸው ትምህርት ክፍሎች በቂ መረጃ ታገኛላችሁ። ይህም ለምርጫው ግንዛቤ ስለሚሰጣችሁ ሁላችሁም እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።
የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

13 Nov, 12:19


https://ee.kobotoolbox.org/x/sV9emwsP

Dereja Data Collection form for Wollo University 2025 Graduates students

Wollo university kombolcha campus student union

12 Nov, 18:45


For all kiot graduating  student
Dereja will hold an orientation session for all graduating students on Thursday, November 14, 2024, at the Graduation Hall. The orientation event will begin at 8:30 a.m. in the morning and will take place at the Graduation Hall of the Kombolcha Institute of Technology. All graduating class members and internship students are required to attend this mandatory session.
The purpose of this session is to provide valuable guidance and insights to the graduating students as they embark on their academic journey, enhance Employability and Job readiness skill. We believe that this session will be instrumental in helping the graduating students navigate their career paths and make informed decisions about their future.
We respectfully request that your office assist us in delivering and spreading this information to the schools and departments under your jurisdiction. Your assistance will guarantee that every student is aware of the occasion.
We appreciate your assistance in making sure that all graduating students are informed of the next orientation session

KIOT STU

Wollo university kombolcha campus student union

12 Nov, 10:23


Attention!! It is a serious training program that you all first year students should attend.

KIOT STU

Wollo university kombolcha campus student union

11 Nov, 10:11


#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ።

የተመደባችሁበትን ግቢ ለማወቅ 👇
Telegeram Bot: @WU_Registrar_bot
Website: https://tinyurl.com/wu-Registrar-s

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

31 Oct, 16:09


To all KIoT faculties and students

Please join us this Saturday, November 2, 2024 Morning (2:30 - 6:00 LT) at Graduation Hall, Wollo University, Kombolcha Institute of Technology for an insightful conversation on Technology and Entrepreneurship.

Keynote speaker Hailemikael Adugna, will be sharing his expertise on digital transformation and hackathon.
Make sure you join us! Save your seat.                     

KIOT STU

Wollo university kombolcha campus student union

30 Oct, 18:22


Here is the link👇
https://debo.gov.et/myRoom/start/5_million_coders_and_cyber_security-367

Wollo university kombolcha campus student union

29 Oct, 16:10


በ2016 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት(Remedial Program) የተማራችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በ2016ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርስቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት(Remedial Program) ተማሪዎች ውጤታችሁን በሚከተሉት የኦንላይን አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃልን፡፡
➤ Telegeram Bot:- @WU_Registrar_bot
➤url:- https://tinyurl.com/wu-remedial-r-2016
C
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

Wollo university kombolcha campus student union

27 Oct, 10:05


ከአፓረንት የተመለሳችሁ ተማሪዎች ከምዝገባ በኋላ መረጃችሁን የምትሰጡ ይሆናል

Wollo university kombolcha campus student union

27 Oct, 10:00


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScbIcrNCCygYm1P98cwEMXT8lehlLRL8wIk__HilKTLtlRAGA/viewform?usp=sf_link
ፎቶ በትክክል ላላስገቡ ተማሪዎች ማስገቢያ ፎርም

Wollo university kombolcha campus student union

26 Oct, 14:45


ከዚህ በታች ስምቻሁ የተዘረዘራችሁ ተማሪዎች በሙሉ ለመታወቂያ ያስገባችሁት ፎቶ እና ስልክ ቁጥር የተሰሳተ ስለሆነ ቀጥሎ ባለው ሊንክ እንድታስገቡhttps://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfkWXJlURHoe6m4ah0NEUhiCmlRmD6jqKLGlfv_me8iDSnDVA/viewform?usp=sf_link

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

24 Oct, 17:05


የግቢያችን ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ   የተመራቂ ተማሪዎች የትምህር መረጃዎች(cv) የማስተዋወቅ ስራዎችን በቀጥታ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር  ስለምንሰራ የትምህርት መረጃችሁን በፎቶ በማዘጋጀት እንድሁም
About us
Motivation later
Additional Skill of  and its authenticate  detail
እና መሰል መረጃወችን በማዘጋጀት በነጻ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ከመዉጣቱ በፊት በዚህ ሊንክ www.Prefixethiopia.com ለድርጅቶች ማመልከት እንደምትችሉ እናሳውቃለን

ለበለጠ መረጃ @yohabmam

Wollo university kombolcha campus student union

21 Oct, 17:14


for all freshman  student final exam scheduled

Wollo university kombolcha campus student union

19 Oct, 08:32


👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች አንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ለዚች ልዩ ቀን አደረሳችሁ እያልን በዛሪው እለት ማለትም 9/02/17 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አዳራሽ የወሎ ዩኒቨርስቲ የሴኔት አባላት፣የክብር እንግዶች፣ተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ተማሪ ወላጆች በተገኙበት ከወሎ ባህል ቡድን ጋር በደማቅ ሁኔታ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
    ውድ ተመራቂ ተማሪዎች አንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ደስአለን💐💐💐

Wollo university kombolcha campus student union

18 Oct, 11:15


🎓🎓🎓🎓🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች ከጅማሮው እስከ ፍፃሜው በፈተና ታጅባችሁ ለዚህ ስለበቃችሁ  ክብርና ምስጋና ይገባችኋል እንኳን ደስ አላችሁ!!! ተማሪነት በብዙ ፈተናዎች የታጀበ  መሆኑን ያለፋበት ሁሉ ህያው ምስክር ናቸው በተለይም የዩኒቨረስቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በብዙ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ቸግሮት ተፈትናችሁ ለዚህ በቅታችኋል፡፡አዎ ስንኖር ሁሉም የድል አክሊሎች የጀግንነት ኒሻኖች የአሸናፊነት ዋንጫዎች በጠቅላላው የምድር በረከት የሚገኘው ፈተናዎች ሲታለፉ ነው::እናንተም ሁሉንም ውስብስብ ችግሮች አልፋችው ለዚህ ስለበቃቸሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ት/ት ምንጊዜም በየትም ሀገር ቢሆን ከዘመን እና ከቦታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በአለም መጀመሪያ አደለንም ወይም በስልጣኔ ታሪክ መጀመሪያ ላይ አደለንም፡፡ በአለም መጨርሻም ላይ አደለንም ይልቁንም በመካከል እንጅ በኋላችን ብዙ ዘመናት አልፈዋል በነዚህ ዘመናት ውሰጥ አባቶቻቸን በብዙ ትግል ደከመው ያሰገኙላቸሁ የሰልጣኔ ቅርሶች ይገኛሉ እወ በኢኮኖሚ የደቀቀች ሀገር ተረክባችሁ ይሆናል ፤ የትምህርት ፖሊሲዋ በየግዜው የሚዘበራረቀባት አገር ተረክባችሁ ይሆናል ነገር ግን ለዘመናት በሀገራቸን ላይ ከተደረገው ስውር ሴራ እንጻር የትም የሌለ ነጻነት በማንም ያልተበረዘ ማንነት ተረክባችኋል፡፡ እነሆ ከዚህ በኋላ ስውር የእውቀት አለም መጋረጃ ለእናንተ ተገልጡዋል፡፡ከእውቀት መቅደስ ሚስጢር ተካፋይ ብቁ እጩ መሆናችሁ ተረጋግጡዋል፡፡ስለሆነም ዋናው የእውቀት ፍለጋ ዋናው ትምህርት ቤት ከፊት ለፊታችሁ ይገኛል፡፡ እስካሁን በዩኒቨርስቲአችሁ ቆይታቸሁ ለህይወታችሁ የሚሆን ትጥቅ ይዛችኋል። ለችግሮቸመፈቻ ቁልፍ እውቀት መሆኑን ተረድታችኋል ስለሆነም ይህን ነባራዊ አለም ለመቀበል ልክ በአለት ላይ እንደተሰራ ቤት የጸናችሁ እንጂ የምትሸበሩ አደላችሁም :: የእምዬ ኢትዮጲያ ሀገራችን መጪ ጊዜዎቿ በእናንተ ነው የሚወሰነው ሆኖም ግን በተማራችሁበት የሙያ መስክ ብቻ በመሰማራት ራሳችሁን እና ወገናቸሁን አገልግሉ በሚል ምክር መታሰር የለባችሁም ፡፡ ይልቁንም የልባቸሁን መሻት ተከተሉ እንጂ፡፡የስለጠናቸሁበት ሙያ መነሻቸሁ እንጂ መዳረሻቸሁ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ከዩኒቨርሲቲ የቀሰማችሁት አውቀት መስፈንጠሪያ እንጂ መታሰሪያ ገመድ አይሁንባችሁ የሰው ልጅ ሲፈልግ ታምረኛ ሲፈልግ ስበበኛ ይሆናል፡፡ በቆይታችሁ በዩኒቨርስቲያችን ላደረጋችሁት መልካም ስብእና ሁሉ ምስጋናችንን እያቀረብን መልካም የህይዎት ዘመን እንድሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ!!!!!

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

18 Oct, 09:41


🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
እንኳን  ደስ አላችሁ!!!
ከ9:00 ስዓት ጀምሮ ባይንደር ስለምንሰጥ በተወካይ በኩል ተማሪዎች ህብረት ቢሮ በመምጣት እንድትወስዱ ። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

16 Oct, 15:49


🔊🔊ማስታወቂያ
ለግቢያችን ፍሬሽ ተማሪዎች
ውድ ተማሪዎች እንኳን ለ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያልን በቀጣይ ቀናቶች የትምህርት ክፍል(Department ) የምትመርጡ መሆኑ ይታወቃል ። ስለሆነም ኮምቦልቻ ካምፓስ ውስጥ ከሚገኙ የትምህርት ክፍሎች አንዱ የሆነው የስነ ህንጻ (Architecture ) ትምህርት ክፍልን መቀላቀል የምትፈልጉ ስለ ትምህርት ክፍሉ ማብራሪያ ለመስጠት መድረክ ስለተዘጋጀ ሀሙስ (07/02/2017ዓ.ም )ከምሽቱ 2:00 በትምህርት ክፍሉ ህንጻ ተገኝታችሁ እንድትሳተፉ እናሳስባለን ።

Wollo university kombolcha campus student union

08 Oct, 10:47


ማስታወቂያ
በ2017 የመደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 የመደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች መኖራችሁ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ተማሪ በኦንለይን እስከ 02/02/2017 ዓ.ም ድረስ student detail or admission detail በተለይ በርዝ ዴት በፈረንጆች አቆጣጠር ( SYSTEM ላይ M/D/YEAR FORMAT መሰረት )እንድትሞሉ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለማንኛዉም ተማሪ ድግሪም ሆነ ማንኛዉንም መረጃ የማንሰጥ መሆኑንን እናሳስባለን፡፡

ሪጅስትራር እና አልሙናይ ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

08 Oct, 10:44


ማስታወቂያ
በ2017 ት/ት ዘመን ከኢንተርንሽፕ ለምትመለሱ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ት/ት ዘመን _ ኢንተርንሽፕ ወጥታችሁ የምትመለሱ ተማሪዎች መኖራችሁ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ዉጭ ላይ የነበራችሁበትን የኢንተርንሽፕ ስራ ጨርሳችሁ ወደ ግቢ የምትገቡት እና የኢንተርንሽፕ ኮርሶችን የምትመዘገቡበት ቀን ከ30/01-1/02/2017 ዓ.ም ሲሆን ግቢ ከገባችሁ በኋላ ከትምህርት ክፍላችሁ ጋር የምታጠናቅቁት ስራ ቀድማችሁ እንዲታጠናቅቁ በማለት የ2017 ት/ት ዘመን 5ኛ ወሰነ ትምህርት ምዝገባ እና መማር ማስተማር ጥቅምት 9-10/02/2017 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

07 Oct, 14:35


ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል
መታወቂያ በተመለከተ ከዚህ በፊት በማስታወቂያ  ያሳወቅነ ቢሆንም በሳይበር መጨናነቅ ምክንያት ከA+ የጫናችሁትን መረጃ ከዚህ በታች በላው  ላይ እስከ ቀን 28 /01/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትሞሉልን
እናሳስባለን።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfkg9R5lhgW2htMq28gprwTOAm4T_R4ntSWvAmB_AL8q5BSxQ/viewform?usp=sf_link


ማሳሰቢያ
"ለመመገቢያ ካርድ አገልግሎት የሚውል ስለሆነ በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በጥንቃቄ ጉድለት ለሚፈጠረው ችግር ተማሪው ራሱ ሃላፊነት የሚወስድ መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡"



የተማሪዎች ህበረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

07 Oct, 11:02


🔊🔊 ማስታወቂያ
ለተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ መጽሔት ማሰራትን ይመለከታል 🎓🎓🎓
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የመመረቂያ መጽሔት መስራት የምትችሉ አካላትን በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ስለምንፈልግ
ተማሪዎች ህብረት ቢሮ እስከ ቀን 28/01/2016ዓ.ም ድረስ በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
የተማሪዎች ህብረት

Wollo university kombolcha campus student union

02 Oct, 13:18


አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል
መታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፓስፖርት ሳይዝ (3*4) ፤ ጀርባው (background) ነጭ የሆነ ሶፍት ኮፒ ፎቶግራፍ
እንድታዘጋጁ እና A+ ድረ-ገጽ (Personal Information) ላይ እስከ ቀን 24/01/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትጭኑ በጥብቅ
እናሳስባለን።

ማሳሰቢያ
•  የምታስገቡት ፎቶግራፍ ጀርባው (background) ነጭ መሆን አለበት
•  የምታስገቡት ፎቶግራፍ 3*4 መሆን አለበት
•  የምትጠቀሙበትን ስልክ ቁጥር ማስገባት አለባቹሁ

ይህንን ሳያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከቀን 24/01/2017 ዓ.ም ጀምሮ የካፌን ጨምሮ ማንኛውንም የግቢውን
አገልግሎት መጠቀም የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህበረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

27 Sep, 05:59


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎቻችን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ

መልካም በዓል

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

25 Sep, 08:07


ማስታወቂያ
ለ2013 እና 2014 ባች ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም ት/ት ዘመን የ2013 እና 2014 ባች ተማሪዎች ምዝገባ ቀን በ 13/01/17 እና 14/01/17 ዓ.ም መሆኑን በማስታወቂያ መግለፃችን ይታወቃል።

በመሆኑም በዚህ ቀን ምዝገባ ያላካሄዳችሁ ተማሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ 16/01/17 ዓ.ም ድረስ ምዝገባውን እንድታደርጉ እያልን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን ።

ለሬጅስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት

👉የተማሪዎች ህብረት

Wollo university kombolcha campus student union

24 Sep, 18:43


የሐዘን መግለጫ

የምንኖርበት ዓለም ያልተሟላ፣ የርኩሳን ፈተና ያለበትና ስቃይን ያዘለ ከመሆኑም በላይ መጨረሻው በሞት የሚደመደም ነው። “ሞት ማንም እርግጠኛ ሊሆንበት የሚችለው ብቸኛ እውነት ነው”   “የእኛ ሕይወት ማለት ያልተሟላን ኑሮ መኖር ነውን?፤ ሞትስ ልናመልጠው የማንችለው የሁላንችንም ዕጣ ፈንታ ነውን?
መኖር ስትሻ ነው፣ ሞት የሚያሰጋህ
ኑሮ ሲቀልህ ነው፣ መሞት የሚገርምህ!!!!

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ የ5 ዓመት የቴክስታይል ምህድስና ተማሪ የነበረችው ሽታየ ተፈሪ ባጋጠማት ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ጎደኞቿ መፅናናትን እንመኛለን።

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
     👉የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

20 Sep, 15:47


2017 EC kIOT dormitory placement

.
KIOT  STU

Wollo university kombolcha campus student union

19 Sep, 10:04


የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል 👇
https://result.ethernet.edu.et/

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

11 Sep, 15:39


ለሁሉም የሪሚዲያልና የአፓረንት ተማሪዎች በሙሉ የተደረገው የተማሪዎች ጥሪ እናተን የማያካትት ሲሆን የአፓረንት ተማሪዎች በጊዚአዊነት መግቢያ ቀን መስከረም 30/01/2017 መሆኑን እያሳወቅነ የሚቀየር ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

11 Sep, 08:13


ለዩንቨርስቲያችን ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ በዓል አደረሳችሁ

🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

በፈጣሪ ቸርነት 2016 አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ፅኑ፣ ብርቱ ህዝብ እና የማይሸነሽ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል እኛብንፈልግም ባንፈልግም ዘመን ይለወጣል ያለፈው አመት በመከራ ያለፈንበት አንዱ ገዳይ ሌላው ተገዳይ የሆንበት መሆኑ ይታወቃል ። እነዚህ ወገኖች ወደው የተገኙበት ፈቅደው የዋሉበት አደለም ምን አልባት  መማር ቢፈቀድላቸው ተምረው ለሀገር የሚጠቅሙ ፤መስራት ቢፈቀድላቸው የፋብሪካ ማናጀር፣ የግል ድርጅት ባለቤት፣ አስመጭና እና ላኪ አምራችና አካፋፋይ መሆን ይችሉ ነበር እውነት ነው ያለፈው አመት የምንሻገርበት ነገ እና የምንደርሰበት ተስፋ  ከፊታችን የለም ብለን እንድናስብ፤ ዕጣፈታችን ሠርቶ እና አልምቶ ማደር ሳይሆን ከዚህ በተቃራኒ ነበር። የ2017 አመት ያለፈው ሁሉ እረስተን አሻግሮ የሚያሳየን በማጣታችን የሞት ሸለቆ ዘለን የማንገባበት ፤ነግቶ በመሸ ቁጥር የሀገር ስጋትን ሳይሆን ተስፋን የምናይበት ልክ 2016 አመት ላይ ሁነን 2015 አመት ወይም ትናትን እንደናፈቅነ 2017 አመት ነገን እንጅ ያለፈውን የማንናፍቅበት እንዲሆለን መልካም ምኞታችን ነው።
መልካም በዓል

የተማሪውች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

10 Sep, 15:26


ማስታወቂያ
05/13/2016 9.
ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች (ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ- ምረቃ) የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 10 እና 11/2017 ዓ.ም ሲሆን መስከረም 13/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መምጣት አይፈቀድም፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

Wollo university kombolcha campus student union

29 Jun, 08:19


የመውጫ ፈተና የወሰደችሁ የዩንቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ ከአሁኑ ስዓት ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናያሳወቅነ የሶፍትዌር ፣ ኢንዱስትሪያል ፣ ስነ-ህንፃ ትምህርት ክፍል 100% ያሳለፉ ሲሆን እንደ ኢንስቲትዩት ከተፈተኑት ተማሪዎች 75% ማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል እናመሰግናለን!!!!


የተማሪዎች ህብረት
https://t.me/wollostu