ፊቅህን ለመረዳት @easyfiqh Channel on Telegram

ፊቅህን ለመረዳት

@easyfiqh


📚 አል ፊቅሁ አል ሙየሰር

📚 ፊቅህን በቀላል አቀራረብ ማቅረብ ይማሩ

📚 ቁርዓን እና ሱነን መሰረት ባደረገ መልኩ ከኡለማዎች አቋሞች ለመረጃ የቀረበዉን መለየት የሚችሉበትን ክህሎት ያዳብርልዎታል

ፊቅህን ለመረዳት (Amharic)

ፊቅህን ለመረዳት telegram አድራሻ ነው እናቱ 'easyfiqh' እናቱ አል ፊቅሁ አል ሙየሰር በእርስዎ ወይም ባለእክሎችዎ እኮ የፊቅሁ አቀራረብ ማቅረብን ለመማር ይማሩ። የዕጩን መምፅርቶችን እና ሱነን መሰረት በቁርዓን እና አንደኛዉ መልኩ ከኡለማዎች አቋሞች ለማረጋገጥ የቀረበዉን መለየት እና መልኩዎን ለጥናት መለየት ለመለየት የሚችሉበትን ልጆችን እና እትዮጵያዎችን የሚታወቅ ክህሎት ይሰጣል።

ፊቅህን ለመረዳት

23 Mar, 16:18


ታላቅ የዳዕዋ ኮንፈረንስ በጉብሬ ከተማ ነሲሓ መስጂድ

ቅዳሜ መጋቢት 17 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

የረመዳንን መቃረብ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ታላቅ ፕሮግራም

ተጋባዥ እንግዶች
1,ሸይኽ ኢሊያስ አሕመድ
2,ኡስታዝ ሰልሰቢል ሀጅ ዙመካን
3,ኡስታዝ ዐብዱልካፊ ሙሐመድ

በተጨማሪም በጉራጌ ዞን የዳእዋ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ያላቸው ኡስታዞች፣ ዱዓቶችና ጀመዓዎች የሚታደሙበት የማይቀርበት ፕሮግራም ነው

___
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
@merkezuna

ፊቅህን ለመረዳት

12 Feb, 13:28


ርዕስ ፦ ላኢላሀ ኢለላህ

🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ

ርዝመት፦ 57:17 ደቂቃ

💾 መጠን፦ ጥራት ያለው 26.55 MB

@nesihastudio

ፊቅህን ለመረዳት

08 Jan, 16:08


Coming Soon...

#_ነሲሓ_ቲቪ_1000

ፊቅህን ለመረዳት

05 Dec, 12:35


ውዱዕ አደራረግዎን ይገምግሙ

____
ፊቅህን ለመረዳት
@easyfiqh

ፊቅህን ለመረዳት

07 Nov, 11:29


የተሸጠ እቃ አይመለስም አይለወጥም!

አንዳንድ ሱቆች ላይ ተለጥፎ የምናገኘው ማስጠንቀቂያ እንደሸሪዓ ተቀባይነት የሌለው መስፈርት ነው። ገዥ የገዛው ነገር ላይ እንከን ካገኘ እቃውን መልሶ በሌላ የመቀየር ወይም ገንዘቡን የማስመለስ መብቱ የተጠበቀ ነው። ሻጭ የዚህ አይነት ማስጠንቀቂያ ስለለጠፈ ብቻ የገዥን መብት ማሳጣት አይችልም።

የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቅፅ 13 ገፅ 197

t.me/abujunaidposts

ፊቅህን ለመረዳት

06 Jul, 11:26


🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐

1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤
«ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።

ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد
አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።

3. ሐጅና ዑምራ፦ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ፦ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን ይሰጣሉ፤

- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው። የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው።

- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

- ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል
ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

- የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።

- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

- ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

- በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ሆኖም ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም።

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
ህዳር 23/ 2004 ዓ.ል

----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts

ፊቅህን ለመረዳት

02 Jul, 17:22


ሰው መሆንህ ክብር መሆኑን ካመንክ ሌሎችም ሰው መሆናቸውን አስታውስ!



7122 SMS | ከፍታ
_
ወደ 7122 በ SMS ok ብለው ቢልኩ መሰል ማስታወሻዎችን ያገኛሉ
https://t.me/sms7122

ፊቅህን ለመረዳት

12 Apr, 20:46


አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ!
ውድ የነሲሓ የበጎ አድራጎት ቤተሰቦች:


ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ከፊታችን እየመጣ ላለው ታላቁ እንግዳችን ለረመዳን ወር አላህ በሰላም ያድርሳችሁ እያልን፣
"ረመዳንን ይዤ በምን አፈጥራለሁ?" እያሉ በማሰብ ለሚጨነቁ ወገኖቻችን የማስፈጠር ፕሮግራም ቀርጸን ለናንተው ውድ ቤተሰቦቻችን አቅርበናል።

ለአንድ ቤተሰብ ለማስፈጠሪያ ያዘጋጀነው ዝርዝር የሚከተሉትን ያካትታል።
- ተምር 3 ኪሎ፣
- የሾርባ እህል 10 ኪሎ፣
- ሩዝ 5 ኪሎ፣
- ዘይት 3 ሊትር፣
- መኮረኒ 3 ኪሎ፣
- ፓስታ 3 ኪሎ፣
- ዱቄት 10 ኪሎ!


ይህን ለአንድ ቤተሰብ የተዘጋጀ ፓኬጅ በጥሬ ገንዘብ 2, 100 ብር በመክፈል ወይም በአይነት በማበርከት እነዚህን ቤተሰቦች "ረመዷንን እናስፈጥር!" በማለት ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ጥሪውን ያስተላልፋል።


🏦 በዚህ የማስፈጠር መርሀግብር ለመሳተፍ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶች ይጠቀሙ፦

1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000328070778
2) ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
1357377300001
3) አዋሽ ባንክ
01410797317600
4) ዳሽን ባንክ
7913417861611
5) ንብ ባንክ
7000016912412

🤳 ለበለጠ መረጃ በ 0972747474 ላይ ይደውሉ!

በዚህ የከፍተኛ ምንዳ መሰብሰቢያ ወር የሚያፈጥሩበት አጥተው በጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን በማገዝ ታላቅ ምንዳን ከአላህ እናግኝ!

ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ለመቀላቀል
t.me/NesihaCharityMain

ፊቅህን ለመረዳት

06 Apr, 13:14


«ዝክረ ረመዳን App»

ለረመዳን በእውቀት እንዘጋጅ

ከማስታወቂያ ነፃ የሆነ ድንቅ የፆም ህግጋት መማሪያ አፕ ይጫኑና ለረመዳን ይዘጋጁ!

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nesiha_org.HTML

ከጎግል ፕለይ ማውረድ ላልቻላችሁ Apk ፋይል አታች አድርገናል
www.nesiha.com


@nesihastudio

ፊቅህን ለመረዳት

31 Mar, 19:31


ባለቤትህን አዝናና...
(የአላህ መልችክተኛ በምሽት ከአኢሻ ጋር እያወሩ ይራመዱ ነበር) ቡኻሪ ዘግበውታል

@tenbihat

ፊቅህን ለመረዳት

27 Mar, 03:50


ልጆቻችሁን አሳትፏ! (በድጋሜ)

ሸይኽ ሀይሰም ቢን ሰርሃን በተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርት በሚሰጡበት የዩትዩብ መድረክ ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የልጆችን ተሳትፎ በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።

እኛም የልጆቻችሁን ተሳትፎ ለአለም እንድታካፍሉ ጥሪ እናቀርባለን። ባለፉት ቀናት በርካታ ቪድዮዎች የደረሱን ሲሆን አንዳንድ ተከታታዮች በጠየቁንም መሰረት የመላኪያ ግዜውን አራዝመናል።

አዝካርና የዲን መልችክቶች፣ የቤተሰብ ፍቅርና ለልጆች የሚተላለፉ ምክሮችን በልጆቻችሁ አንደበት ከ2 ደቂቃ ባልበለጠ በጥሩ ጥራት ቀርፃችሁ ከእሁድ መጋቢት 26/2013 በፊት በሚከተለው የቴሌግራም አድራሻ ላኩልን።

@nesihakids

N:B– ልጆቻችሁ ማንነታቸውን ገልፀው እንዲጀምሩ አድርጉ።


https://youtube.com/playlist?list=PLBFEt29we81SNO_IyPK2lzghsFsSP8fxo


@Tenbihat

ፊቅህን ለመረዳት

23 Jan, 16:58


🔖 የቁርአን ወዳጆች

🎙 አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ

⌚️ የ 50 ደቂቃ ሙሀደራ

🔗 Share Link
https://t.me/abujunaidposts/147

----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts

ፊቅህን ለመረዳት

01 Jan, 05:29


በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን?

በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!!

በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!!

ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!!

(وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا * تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا * أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا * وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا * إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا * لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا * وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا)

አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም]
Surah Maryam 88 - 95

ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...
ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ!

የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን?

እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ። ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል» አህካም አህሉዚማህ

የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!!

በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን። ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)

አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
[Surah Al-Qalam 8 - 10]

ወላሁ አዕለም

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!

____
አቡጁነይድ ረጀብ 24/1437 ዓ.ሒ / ሜይ 1/ 2016 ከጥቂት ማሻሻያዎች ጋር

https://t.me/abujunaidposts/141

ፊቅህን ለመረዳት

11 Oct, 14:03


🍂 ቁርአን የልብ ብርሃን!

⌚️ የ 60 ደቂቃ ሙሀደራ

🎙 አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ

🔗 Share Link
https://t.me/abujunaidposts/97

----------------
📮የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts

ፊቅህን ለመረዳት

28 Aug, 21:16


ወቅታዊ መእክት!

🔊 [ዓሹራ እና የፊርዓውን ፍፃሜ]

🎙 ኡስታዝ ጣሀ አህመድ

በሂጅራ አቆጣጠር ዛሬ ቅዳሜ የሙሀረም ወር 5ኛው ቀን ላይ እንገኛለን፤ ቀጣዩ ሀሙስ መስከረም 10/2011 ወይም ሙሀረም 10/1440 ዓ.ሒ ነው። በሙሀረም ወር የድል ቀን የሆነውን አስረኛውን ቀን እንፆማለን።

ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ አሹራን ስለመጾማቸው ተጠይቀው፤ «ያለፈን የአንድ አመት ወንጀል ያስምራል» ብለዋል።

በመሆኑም በኡስታዝ ጣሀ አህመድ በ2002 በጃሊያ አዳራሽ ከቀረበው የነብዩ ሙሳ ታሪክ የተወሰደውን የ10 ደቂቃ የድምጽ መልዕክት ያዳምጡ።

🏷 ለሌሎች ወንድምና እህቶች ለማድረስ ከተከታዩ ሊንክ ዳውንሎድ ያደርጉ ዘንድ በማህበራዊ ድረ ገፆች ፖስት እናድርግላቸው።

Http://goo.gl/ndDKMW

አላህ የሁላችንንም ጾም እንዲቀበለን እና ወንጀሎቻችንን እንዲምረን፣ መልካም ስራንም ሁሉ እንዲያገራልን እንለምነዋለን

👍🏻 ነሲሀ ኢስላማዊ ስቱዲዮ
Http://telegram.me/nesihastudio

ፊቅህን ለመረዳት

26 Aug, 17:33


የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ

የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም በዒባዳ ያሳልፉታል።

ሺዓዎች ግን ስለ ዓሹራ ቀን ሲያስቡ ሚታወሳቸው የታላቁ ሰሀቢይ የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ልጅ ሁሰይን የተገደሉበት ቀን መሆኑ ብቻ ነው። ሺዓዎች በዚህ ቀን ሀዘናቸውን ለመግለፅ እራሳቸውን የሚጎዱ ብዙ ነገሮችን በስፋት ይፈፅማሉ። ጭንቅላትንና ሌሎች አካሎቻቸውን በስለት መብጣትና ማድማት (ተጥቢር)፣ ፊታቸውን መደብደብ (ለጥም፣) እራስን በሰንሰለት መግረፍና ማንገላታት፣ በእንብርክክ መሄድ፣ ብዙዎችም ዘንድ ጥቁር መልበስና የለቅሶ ሙሾ ማውረድ ብሎም በራስ ላይ ኩነኔን መጥራት የተለመዱ የአሹራ ትእይንቶቻቸው ናቸው።

በእጅጉ ይገርማል፤
ለኛ ለአህሉሱና ደስታን ሲያላብሰን፣ ተስፋን አሰንቆ ድልን ሲያበስረን፤ ለወንጀላችን ማርታን ለማግኘት ሩጫ ውስጥ ሲከተን፤

ለሺአዎች ግና፤
የሀዘን የዋይታ፣ የውድቀት የሽንፈት ማስታወሻ፣ የተስፋ ማጨለሚያ ነው!!

ሁሰይን የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ በኢስላማዊ እውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ሰሀቦች አንዱ ኗቸው።


ቀረውን ከተከታዩ ሊንክ ያንብቡ
http://clearfaith.blogspot.com/2015/10/blog-post.html?m=1

ፊቅህን ለመረዳት

15 Aug, 21:21


@abujunaidposts

ፊቅህን ለመረዳት

05 Aug, 05:02


ፕሮጀክቱን በማስተዋወቅ ተባበሩን

ዳሩ–ተውሒድ የወቅፍ ፕሮጀክት

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

የወቅፉ ገቢ ለምን ይውላል?
√ ነሲሓ ቲቪ
√ ነሲሓ መስጂድና መድረሳ
√ ዳሩል ሀዲስ ኢስላማዊ ኮሌጅ
√ የቁርአን ሒፍዝ ሀለቃት
√ ኢልም ተኮር ኮርሶች
√ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞዎች
እና ሌሎችም አንፀባራቂ የዳዕዋ ስራዎች

ኒያዎን በsms ያሳውቁ 0972757575

ኒያዎን ለወቅፍ አካውንት ገቢ ለማድረግ
ንግድ ባንክ 1000337985328
T.me/darutewhidweqf