Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ) @konso_zone_gov Channel on Telegram

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

@konso_zone_gov


Communication is the bridge between people and Government !
https://heylink.me/konsozonecomms/
www.konsozone.org
https://t.me/KonsoZone

Konso Zone gov't communication affairs dep't (Amharic)

ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ የአማርኛ ቋንቋ ቋንቋውን በጥንቃቄ እና በመሰረታዊ ውጤታዊ መረጃዎች ለማግኘት እና ለመረጃውን ይመልከቱ ይሆናል። በዚህ መድረሻ ኮንሶ ዞን ከተገኘቻቸው ድረ-ገጽ የአማራ ምክር ቤት እና አመታት ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም የድምፅ ቦታዎች አለከል በተለያዩ ሁኔታዎች ከጉልበት እና ከአቅም ማዝ ውጤት ላይ እንዲታይ የሚገኙበት ዕድሜ ነው። የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች ከሌላው እና ከሌሎቹ ዜና መምረጥ ውጤትን ለማድረግ መሠረት አማራ አስተያየቶችን ገንዘባ።

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

20 Feb, 04:43


#Ethio_Konso በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ፣ የወረዳውን ሠላምና ፀጥታን የሚያስከብሩ ከ500 በላይ ሰልጣኝ...
https://youtube.com/watch?v=n4o-9-cX0PA&si=v8dXZd7TgomVkl6p

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

17 Feb, 17:12


#Ethio_Konso በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ቀጠና 1 ሠፈር 2 የቡርቁዳ ታራቴ አምባ መንደ...
https://youtube.com/watch?v=8DckfNI-Gnk&si=InQIKyeHUpNZSQTs

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

11 Feb, 17:33


#Ethio_Konso የፓርቲው አደረጃጀቶችን ማጠናከርና የተፅዕኖ አድማሳቸውን ማስፋት በሁለተኛው ጉባኤ አፅንኦት የተሰጠዉ ጉዳይ ነው- አቶ ዳዊት ገበየሁ፣

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገበየሁ ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የፓርቲው ስኬቶች እና የታዩ ጉድለቶች በጥልቀት የተፈተሹበትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የተቀመጡበት መሆኑን ተናግረዋል።

ለአንድ ፓርቲ አደረጃጀት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶችን በማጠናከር የፓርቲው አመራርና አባላት ታቅፈዉ መንቀሳቀሳቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

ክልሉ ከተደራጀ አጭር ጊዜ ቢሆንም የፓርቲው እሳቤዎች፣ አቋሞችና ለሕዝብ ያለዉ ዉግንና ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ በአንድ ዓመት ዉስጥ ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ አዳዲስ አባላት ወደ ፓርቲው መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል።

ፓርቲው በሀገራችን ለዘመናት የነበሩ ስብራቶችን ለመጠገን የተቋቋሚ ፓርቲ በመሆኑ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት የፓርቲው አደረጃጀቶች ግንባር ቀደም ሊሆኑ እንደሚገባም አቶ ዳዊት አስገንዝበዋል።

ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ለማሳካት በፓርቲው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ተፈፃሚ ለማድረግ የአመራሩንና የአባላትን የጥራትና የብቃት ደረጃ ማሳደግ..👇
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02WKuoJqAtP6viQwJ7TmWDoACXCUmDCenRdeTt81bpzm2sm6bUny5ujwr9TDumQuA4l&id=100069055695172&mibextid=RtaFA8

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

11 Feb, 17:30


#Ethio_Konso ኢትዮጵያ ለ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ እንኳን በደህና መጣችሁ ብላ ስትቀበል ሁሉም ተሳታፊዎች ኢትዮጵያን በእውነትም ምድረ ቀደምት ያደረጓትን የታሪክ ሀብቷን፣ ብዝኃነት የሞላውን ባሕሏን እና አስደማሚ መልክዓ ምድሯን ለመመልከት ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ አበረታታለሁ። ከጉባኤው ባሻገር ከጥንታዊ የቅርስ ስፍራዎች እስከ ደማቅ ባሕሎች፤ አቻ የለሽ የተፈጥሮ ውበቶችን ጨምሮ ልታውቋቸው የሚገቡ ብዙ መዳረሻዎች አሉ።

ወደቤታችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ!

Itoophiyaan wayita Yaa'ii Gamtaa Afrikaa 38ffaaf anaadhufu jettee keessummootashee simattu hirmaattonni hundi waantoota Itoophiyaa dhugumaan biyya duree taasisan: qabeenyaa seenaashee, aadaawwanshee daneessa ta'aniifi teessuma lafashee ajaa'ibsiisaa ta'e daawwachuuf turtii isaanii akka dheereffattanin isaan jajjabeessa. Yaa'ichaan cinatti iddoowwan hambaa duriirraa kaasee hamma aadaawwan babbareedaa, miidhaginaa uumamaa gita hinqabne dabalatee hawwattota beekuu qabdan hedduutu jira.

Gara mana keessaaniitti anaadhufu!👇
https://youtu.be/fM6HeY-YiE8?si=qccgTFXm5IjxoBF1

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

03 Feb, 10:51


#Ethio_Konso የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዥ ፈፀሙ፣

የደቡብ ኢትዮጵ ክልል መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አመራሮች  እና ሠራተኞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቀሪ ስራዎች ማጠናቀቂያ የሚውል ከ108 ሺህ ብር በላይ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።

የሁላችንም ኩራት ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት አመራሮቹና ሰራተኞቹ "በኅብረት ችለናል፤ እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት ከ108 ሺህ ብር በላይ የቦንድ ግዥ በመፈጸም ዳግም አሻራቸውን አሳርፈዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
                 ጥር 26/2017 ዓ.ም

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

03 Feb, 07:41


#Ethio_Konso የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለከተማችን ውበት ከመስጠት ባሻገር ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ይፈጥ...
https://youtube.com/watch?v=5QZSm0kri0E&si=CG7P8MDcZ6cwZmEq

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

02 Feb, 09:14


#Ethio_Konso ሰበር ዜና!!

ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ክቡር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል። ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

በተያያዘ ዜና ጉባኤው ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና ክቡር አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

#prosperity

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

31 Jan, 16:36


https://www.facebook.com/konsozone.org/videos/923702583084261/?app=fbl

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

31 Jan, 04:21


#Ethio_Konso የኮንሶ ልማት ማህበር እየሰራቸው ካለው በርካታ የልማት ስራዎች በቅርቡ የሚጠናቀቁትን ይፋ አደረገ፣

ከሕዝቡ ተገኝቶ ለህዝቡ እየተጋ ያለው ልማት ማህበሩ ካስጀመራቸው በርካታ የልማት ስራዎች ውስጥ ከ2-4 ወራት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ትኩረት ካደረገባቸው መካከል በካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ የድንገተኛ ህክምና ማዕከል፣ የፋሻ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዘመናዊ ቤተመጻሕፍት፣ በሠገን ገነት እና በኮሪያ ዶካቱ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ እየተገነቡ ያሉት እያንዳንዳቸው 4 የመማሪያ ክፍሎችን የያዙ ሁለት ሕንጻዎች ይገኙበታል።

ለዝርዝር መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

https://www.facebook.com/100069055695172/posts/pfbid02fw6RR5bRVM1tvXHrTp2bBzh8xYCEmx3gxg7CktmVAU1PUBWWMNGMSzs15WEaWi6rl/?app=fbl

ጥር 22/2017

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

18 Dec, 15:25


#Ethio_Konso ችግሮችን በውይይት መፍታት የስልጣኔ መገለጫ በመሆኑ የሚፈጠሩ ችግሮችን በአንድነትና በመግባባት በመፍታት ዘላቂ ሠላም መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ፣

በኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ የተመራው ልዑክ በሠገን ዙሪያ ወረዳ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሠገን ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሙሽ እሸቱ ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ አለመግባባቶች የህዝቡ ፍላጎት ሳይሆኑ ሠላምን የማይፈልጉ አካላት የፈጠሯቸው ችግሮች መሆናቸውን አስረድተዋል።
https://www.facebook.com/share/1BGqY6oMEx/

https://goo.by/SRXyau

መረጃ
ከስፍራው - በዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ታህሳስ 09/2017 ዓ/ም

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

18 Dec, 14:03


#Ethio_Konso በኮንሶ ዞን የ2017 በጀት አመት  የማአጠሜ አባላት የማፍራት ስራ ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ፣
____
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ በሌ ማአጠሜ ከጀመረ አመታት እንዳስቆጠረና በ2016 ዓ.ም 70% የሚሆነውን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ገልጸው፣ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት መሰረት ተደርጎ የሚሰራበት መሆኑ የዘንድሮውን ዓመት ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ አሰፋ በመክፈቻ ንግግራቸው ከዚህ ቀደም የህክምና ክፍያን መክፈል ባለመቻል ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለሞት ይዳረግ እንደነበር አስታውሰው፣ የጤና ስርአቱን ፍትሀዊ ለማድረግ ማአጠሜ ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ መሳይ አክለውም በ2016 ዓ.ም ከ41ሺ በላይ አባላትን ማፍራት የተቻለ ቢሆንም

Read Full
       👆

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
            ታህሳስ 9/2017

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

17 Dec, 16:32


#Ethio_Konso የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲጎለብት የተፈጥሮ መስዕቦቻችንን መንከባከብ ያስፈልጋል:- የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኮንሶ ዞን ጌና ወረዳ የሚገኘውን የተፈጥሮ መስህብና ባህላዊ ቤት ጎብኝተዋል ።

ሚኒስትሯ በአካባቢው የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የተሰራው የእርከን ስራንም በእጅጉ የሚያስደስት ተግባር እንደሆነም አንስተዋል።

በመስክ ምልከታው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አማረ አቦታ እንዲሁም የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ የምስራች ገመደ፣የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የዞንና የከተማ አመራሮች ይገኛሉ።

#SERS
ታህሳስ 08/2017 ዓ .ም

Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)

17 Dec, 16:29


#EthioKonso የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎበኙ

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሆስፒታሉ ያሉበትን ችግሮች ተመልክተዋል።

ሆስፒታሉ ችግር ናቸዉ ብሎ ያነሷቸዉን በመውሰድ ከፌደራል እስከ ዞን ድረስ ከሚመለከታቸው አካላት በመነጋገር ለመቅረፍ እንደሚሰራም ሚኒስትሯ አብራርተዋል።

የሙያውን ስነ ምግባር በማክበር ክቡር የሆነዉን የሰዉን ልጅ ህይወት በማስቀጠል የበኩላቸውን አስተዋዕፆ እንዲያበረክቱ መልዕክታቸዉን ያስተላለፉት ሚኒስትሯ በተጨማሪ በከተማዉ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተጀመረዉን የማስፋፊያ ህንፃም ጎብኝተዋል።

#SERS

ታህሳስ 08/2017 ዓ .ም

1,127

subscribers

6,211

photos

39

videos