Jinka University's Official Channel @jkupir Channel on Telegram

Jinka University's Official Channel

@jkupir


This is the official channel of JKU Public and International relations directorate

Jinka University's Official Channel (English)

Welcome to Jinka University's Official Channel on Telegram! Join us on this platform to stay updated on all the latest news, events, and announcements from JKU Public and International Relations Directorate. As the official channel of the university, we strive to provide you with accurate and timely information regarding various programs, initiatives, and activities happening at Jinka University. Who is it? Jinka University is a leading educational institution in Ethiopia, known for its commitment to excellence in teaching, research, and community engagement. Established with the goal of providing quality education to students from diverse backgrounds, JKU has grown to become a hub of knowledge and innovation in the region. What is it? The official channel of JKU Public and International Relations Directorate, @jkupir, serves as a direct communication channel between the university and its students, staff, alumni, and the general public. By joining our channel, you will have access to updates on academic programs, research projects, partnerships, and other important information related to the university. Don't miss out on the opportunity to connect with Jinka University and be a part of our vibrant community. Stay informed, engaged, and inspired by joining Jinka University's Official Channel today! We look forward to having you as part of our growing online community.

Jinka University's Official Channel

06 Jan, 19:18


#JinkaUniversity

በ2017 ዓ.ም በአቅም ማካካሻ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ጥር 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ጥር 15/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች እንዲሁም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

@tikvahuniversity

Jinka University's Official Channel

02 Jan, 14:44


የገና ስጦታ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃግብር አካሄደ።

**ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም**

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከአካዳሚክ፣ የምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የዘንድሮውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የማእድ ማጋራት መርሃግብር አካሂዷል።

የማዕድ ማጋራቱ በጂንካ ከተማ ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት አማካኝነት የተመለመሉ በጂንካና አካባቢዋ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችና የኢኮኖሚ አቅም ችግር ያለባቸው አካላትን ያሳተፈ ነው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተገኙ ሲሆን የአቅም ውስንነት ያለባቸው ወገኖች በዓልን ሲያከብሩ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን ማህበራዊ ሀላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅበት ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ኩሴ ገልፀው የሀገር ባለውለታዎችን በተቻለ መጠን ማገዝ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

ድጋፉ የተደረገው እስከ አንድ መቶ ለሚደርሱ አባወራዎችና እማወራዎች መሆኑንም የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ መ/ር ሰሙ ይታፈሩ ገልፀዋል።

Jinka University's Official Channel

31 Dec, 18:55


https://www.facebook.com/share/p/19bJKNGZ3B/

Jinka University's Official Channel

31 Dec, 07:17


የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አመታዊ የውስጥ ለውስጥ ስፖርት ውድድር ንቅናቄ ተጀመረ።

በየአመቱ የሚካሄደው የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ የውስጥ ለውስጥ የእግር ኳስ ውድድር በትላንትናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 21/2017ዓ.ም በተማሪዎች በማህበራዊ ሳይንስና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጆች መካከል እንዲሁም በሰራተኞች በኩል ደግሞ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅና በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን መካከል የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።

Jinka University's Official Channel

27 Dec, 12:06


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ሆስፒታሎች ሀላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

*ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም**

ጂንካ
ዩኒቨርሲቲ በሪያው ከሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታል ሀላፊዎች ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ እንደ አንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመዘኛና ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች (Key Performance Indicators) ተደርጎ የሚቆጠረው ዩኒቨርሲቲዎች ከአቻ ተቋማትና ከኢንዱስትሪ ሴክተሮች ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩት የስራ እንቅሰቃሴ አንዱ ነው።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ከግምት ውስጥ ከማስገባትም ባሻገር ተማሪዎች ተግባር ተኮር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ያስችለው ዘንድ ከኢንዱስትሪ ተቋማት፣ ከአቻ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሆስፒታሎችና ሌሎች ብሄራዊና አለምአቀፍ ከሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም አያሌ ትምህርታዊና ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በዛሬው እለትም በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባሪነት ፕሬዚደንቱ ኩሴ ጉዲሺ(ዶ/ር) እና የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ የሆኑት መ/ር ኢብራሂም ጀማል በተገኙበት ከጂንካና ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታሎች እንዲሁም ከኮይቤ፣ ከጋዘርና ከካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የስራ ሀላፊዎች ጋር በቀጣይ በጋራ ሊሰሯቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተቋማት እርስ በእርስ ተቀናጅተው በትምህርት፣ በስታፍ ልውውጥ፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በምርምርና በሌሎች ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በጋራ መስራት ካልቻሉ በሀገር ደረጃ ወደታለመላቸው አላማና ግብ መድረስ እንደሚቸግራቸው አብራርተው ዩኒቨርስቲው አሁን እየሰራባቸው ካሉ የትብብር ስራዎች የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካዩ መ/ር ኢብራሂም ጀማል እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት መ/ር ኤርሚያስ ዋቤቶ ሆስፒታሎቹ የተግባር ትምህርታቸውን ለመከታተል ለሚላኩ ተማሪዎች ለሚያደርጉት መልካም እንክብካቤ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ደግሞ በመ/ር ደሳለኝ ሎንጎ ቀርቧል።

በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩ የሆስፒታሎች ሀላፊዎች በርካታ ሀሳቦች ተነስተው በመጨረሻም የስምምነት ውሎችን በመፈራረም ውይይቱ ተጠናቋል።

ያለንን ውስን ሀብትና እውቀታችንን አቀናጅተን ማህበረሰባችንን እናገለግላለን የትምህርት ጥራትንም እናሻሽላለን!!

*እውቀት ለለውጥ*

//የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ቢሮ//

Jinka University's Official Channel

26 Dec, 18:46


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሰራተኞች የስነምግባር መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የውስጥ መመሪያዎችን በሴኔት አስፀድቆ ወጥ የአሰራር ስርዓት ዘርግቶ ከሚንቀሳቀስባቸው የስራ አግባቦች የሰራተኞች የስነምግባር መመሪያ ቁጥር 06/2013 አንዱ ነው።

ይህን መመሪያ በሚመለከት ለተመረጡ የአስተዳደር ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር አለሙ አይላቴ ሰራተኞች መብትና ግዴታቸውን አውቀው ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ያስችላቸው ዘንድ መሰል የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠናዎች የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የስነምግባር ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መርሆችና ስለዲሲፕሊን ጥፋትና እርምጃዎች የስልጠናው አንኳር ትኩረቶች ነበሩ።

Jinka University's Official Channel

27 Nov, 10:07


Jinka University holds ELIP and HDP launching program today on 27th of November 2024.

Both ELIP(English Language Improvement Program) and HDP(Higher Diploma Program) are among in service trainings that are being held at JKU specifically to enhance the teaching learning process, and to insure the quality of education in general at the University.

Based on the clarification that has been delivered by the academic program director of the university Mr Worku Abera, both English Language Proficiency and the skills that help to deliver best teaching activity, are the backbones of quality education. So, he mentioned that those two types of the training are the main things which are the Office of Vice President for Academic, Research, Community Services and Technology Transfer is being committed to train the academic staff.

Jinka University's Official Channel

27 Nov, 09:09


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ #የግብርና ትኩረት አቅጣጫ እንቅስቃሴውን እንደቀጠለ ነው።

በሶስት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማለትም በግብርና፣ በቱሪዝምና ሀገር በቀል እውቀት እንዲሁም በአግሮፕሮሰሲንግ የልህቀት ማእከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ በተለያዩ ልጥፎቻችን ማሳወቃችን ይታወሳል።

ከእንስሳት እርባታና የእርሻ ስራዎችን ከማሻሻል በተጨማሪ በአካባቢ ጥበቃ አያሌ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በዛሬው እለት ማለትም ህዳር 18/2017ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የግብርና ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች የሞሪንጋ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል።

ከ1000 በላይ የሞሪንጋ ችግኞች መተከላቸውን የገለፁት የግብርና ኮሌጅ ዲን መ/ር ግርማ ዳዊት ሞሪንጋ(አለኮ) እንደ አካባቢው የተለመደ ተክል ከመሆኑም በላይ ለምግብነትና ለመድሀኒትነት ካለው ጥቅም አንፃር ትኩረት አድርገን የምንሰራበት ይሆናል ብለዋል።

በተጨማሪም የሞሪንጋ ችግኞችን በስጦታ መልክ ላበረከተው ለኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳና ላስተባበሩ አካላት መ/ር ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Jinka University's Official Channel

09 Nov, 04:55


እንደቀጠለ ነው.......

ዛሬም ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ፎረም አባላት የGC4 ትግበራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አደረጃጀት መካከል አንዱ በሆነው በተማሪዎች ፎረም ፅ/ቤት አስተባባሪነት የፎረሙ አባላትና የተለያዩ ክበባት አባላት ያሳተፈ የግቢ ውስጥ የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል።

በፅዳት ንቅናቄው ላይ የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አምባ ጩፋ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ ምስጋና ደስታና ሌሎች የፎረሙ ስራ አስፈፃሚዎች የተገኙ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መሄድ እንዳለበትና በንቁ ተነሳሽነት መስራት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

"ጂንካ ዩኒቨርሲቲን አረንጓዴ፣ ንፁህ፣ ግልፅና ተወዳዳሪ ካምፓስ(Green, Clean, Clear and Competent Campus) እናደርጋለን"

Jinka University's Official Channel

04 Nov, 17:07


የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄዱ።

**ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም**

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንቅስቃሴን ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ከተማሪዎች፣ ከመካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ ማካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።

በዛሬው እለትም የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ ሰራተኞ(የአካዳሚክና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን) ያሳተፈ ውይይት ተካሂዷል። በውይይት መድረኩ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሁሉም ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር) የጋራ መግባባትን ለመፍጠርና ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣት የሚረዱ ነጥቦችን በማንሳት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚሁ መድረክ የመጀመሪያው ሩብ አመት የአፈፃፀም ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በአቶ ገነሚ ቡቅሚ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም ሰፊ የጋራ ውይይት በማካሄድ እንዲሁም ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከርና በስራ አጋጣሚ የሚከሰቱ ክፍተቶችን በመድፈን መቀጠል እንደሚያስፈልግ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል።

Jinka University's Official Channel

04 Nov, 08:23


በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በመሰራት ላይ ያለ የካይሳ የተፈጥሮ ሃብት አያያዝና እንክብካቤ ስራ (Participatory adoption of Gully rehabilitation mechanism in Aari and South Omo Zone Ethiopia):-
- የጋቢዮን ክትር ሥራ
- የተዘጉ የውሃ መተላለፊያ ከልቨርት የመክፈት ሥራና
- ከወተርሼድ ተሰብስቦ ጎርፍ ሆኖ የሚመጣን አደገኛ ውሃን መውጫ የማሳየት ሥራ

Jinka University's Official Channel

02 Nov, 12:49


https://www.facebook.com/share/p/14zFauEiW8/

Jinka University's Official Channel

02 Nov, 05:02


ተጀመረ...

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን GC4 በሚል ፅንሰ-ሀሳብ ዩኒቨርሲቲውን አረንጓዲ፣ ንፁህ፣ ግልፅና ተወዳዳሪ ካምፓስ ለማድረግ አዲስ ፕሮጀክት ቀርፆ እየሰራ እንደሆነ ባለፉት ተከታታይ ልጥፎቻችን ማሳወቃችን ይታወሳል።

ይህንን የGC4(Green, Clean, Clear, Competent Campus) የመፍጠር እቅድንና ፅንሰ-ሀሳቡን በሚመለከት ለሁሉም ነባር ተማሪዎች በየኮሌጆቻቸው ስልጠናና የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ መካሄዱ ይታወቃል።

እነሆ በዛሬው ዕለት(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) ከማለዳው 12:00 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤትና የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ሁሉም የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት እንዲሁም የሁሉም የክበባት አባላት የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚደንት የሆኑት ዶ/ር አለሙ አይላቴ በፅዳት ዘመቻው ላይ የተሳተፉ ሲሆን የቀይ መስቀል፣ የህብረ-ገፅ የስነ-ጥበብ፣ የበጎ አድራጎት እንዲሁም የስብዕና ግንባታና excellence ክበባት አባላትና ሌሎች የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት አባላት ተገኝተዋል።

በቀጣይም ወጥ በሆነ ፕሮግራም ሁሉንም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችንና ሰራተኞች ያማከሉ የስራ ዘመቻዎች እንደሚከናወኑ እቅድ መያዙንም ተገልጿል።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲን "አረንጓዴ፣ ንፁህ፣ ግልጽና፣ ተወዳዳሪ ካምፓስ(Green, Clear, Clean and Competent Campus) እናደርጋለን"!!

Jinka University's Official Channel

31 Oct, 17:34


#Urgent

ለነገ አርብ (ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) ከጠዋቱ 2:30 ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ለማካሄድ ታስቦ የነበረው የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ወደ ሰኞ ጠዋት 2:30 መቀየሩን በትህትና እንገልፃለን!!

Jinka University's Official Channel

31 Oct, 06:19


ማስታወቂያ ለJKU አጠቃላይ ሰራተኞች

ነገ አርብ ማለትም (ጥቅምት 22/2017ዓ.ም) ከጠዋቱ 2:30 ላይ በአዲሱ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።

አጀንዳ፡ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ለመገምገምና የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር//

የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት

Jinka University's Official Channel

16 Oct, 16:56


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የስብዕና ግንባታ እንዲሁም የአረንጓዴ፣ ንፁህ፣ ግልጽና ተወዳዳሪ ካምፖስ(GCCCC) የመፍጠር ፕሮጀክት ላይ አበክሮ እንደሚሰራ ገለፀ።

**ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም***

በዘንሮው የትምህርት ዘመን ዩነቨርሲቲው ከምን ጊዜውም በላይ በተማሪዎች የእውቀትና የስብዕና ግንባታ ላይ በሰፊው ለመስራት ማቀዱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር) ገለፁ።

በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም በጤና ሳይንሰ ኮሌጅ ተማሪዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም የተጀመረው ስልጠና በዛሬው እለትም ለሌሎች ኮሌጆች ተማሪዎች የአረንጓዴ፣ ንፁህ፣ ግልፅና ተወዳዳሪ ካምፓስ (Green, Clean, Clear and Competent Campus) የመፍጠር ፅንሰ-ሀሳብን በሚመለከት ሰፊ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ይህንን ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የተማሪዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ የGCCCC ፕሮጀክት በውጫዊ ውበት ብቻ ላይ የሚሰራ ሳይሆን ብቁ፣ ተወዳዳሪና ገበያው የሚፈልጋቸው ተማሪዎችን በማፍራት ላይ ያላሰለስ ጥረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ በተማሪዎች በኩል በርካታ የግልፅነትና በተቋሙ በሚስተዋሉ አንዳንድ ችግሮች ዙርያ ሀሳብና ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ፣ በአካደሚክ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና እንዲሁም በተማሪዎች ዲን ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ ከተማሪዎች ጋር በጋራ ምሳ በመብላት የዛሬውን ፕሮግራም አጠናቀው በነገው እለት ስልጠናው ለተቀሩት ኮሌጅ ተማሪዎች የሚሰጥ ይሆናል።