ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች @brshchekolata Channel on Telegram

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

@brshchekolata


ግጥሞችና አጫጭር ታሪኮች የሚያገኙበት Chanel







Join on this link
👇👇👇👇👇👇
t.me/brshchekolata
t.me/brshchekolata
For any suggestion or comment
👇👇👇👇👇👇
@Brhant

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች (Amharic)

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች ትችላላችሁ! የወርቅ ታሪኩን ጥንቆሻል ወደ ተማሪዎቹ ጠቀምና በመስራት ፍቅርን ለቆልን የሚለውን ያገለገላል!
እባኮን ለማግኘት የቡድኖችን ሊንክ ላይ '@brshchekolata' አድርጉ። ይህ ቱሪኮች ውስጥ በአሁኑ የቴምባላሕ ግምታ በመምጣታ ለፍቅር ፣ አጫጭራቶች፣ ግጥሞች እና ሌላዊነት በውስጥ የገናና ልዩ ታሪኩን ለመስጠት ያንብቡ። nnአጫጭርን ሲጠቀሙ፣ ግጥም እና ፍቅርን ማቀርብ እና እንዲሰርቅን ለመማር ይምጣል። ወይም ሌላኛን ታሪኩን የሚያገኙ የምርምርዎችን እና መስፋፋቶችን ለመለያየት ያግኙ። አካባቢ ሰርተው ለመተንተኑ ስለ ልምምጥ፣ ችግሮቹን ሊስተም ለመተላለፍ ይችላል። nnአሁን በወርቅ ታሪኮችን ስለ ፍቅርና በግጥም መንቀሳቀስ እና ሳምንቱ ለመስጠት የምንሆንባትን መልስ አግኝቶና ለመስማት ይከላከልላት።

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

15 May, 20:48


@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

22 Jun, 20:24


በህይወት ዘመናችን ሶስት ሰዋች ይገጥሙና…🚶🧍🧎
@brshchekolata
በህይወት ዘመናችን ሶስት ሰዋች ይገጥሙና። እና እነዛ ሰዋች በህይወታችን ትልቅ ነገር አስቀምጠው ያልፋሉ።
የመጀመሪያዋቹ ሰዋች አንተ የምትወዳቸው የምታስብላቸው እነሱ ግን ላንተ ቦታ የሌላቸው ሰዋች ናቸው።ፈጣሪ እነዚህን ሰዋች ወደ ሂወትህ ሲያመጣ አንተን ጠንካሪ ለማድረግ እና አቅምህን እንድታውቅ ነው።
ሁለተኛው ወደ ህይወታችን የሚመጣው ሰው እሱ የሚወደን እኛ የማንወደው ግዜ የማንሰጠው ሰው ነው ያ ሰው ለኛ ሲል ብዙ እርቀትን ይጓዛል። ያንን ሰው ፈጣሪ ወደ ህይወታችን የሚያመጣው ፍቅርን መቀበል እንድንችል እድል በኛ ላይ ስትሆን በአግባቡ እንድንጠቀም ነው።
ሶስተኛው በህይወታችን የሚገባው ሰው እኩል መዋደድ እኩል መተሳሰብ ያለበት ነው እንደዚህ አይነት ሰው ወደ ህይወታችን ሲገባ የፀሎታችን ምላሽ የተገኘበት ግዜ ነው። እግዚያብሄር መልስ ሲሰጥ የሚጠቅመንን የዘላለም ህይወትን በመስጠት ነው።

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

08 Dec, 19:49


አሜን የመጨረሻው ክፍል
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ህይወት ብዙ አቅጣጫዋች ይኖሯታል እነዚህ አቅጣጫዋች ደግሞ ወደ መረጥንበት የህይወት መስመር ይወስዱናል።ምን አልባት የመረጥነው መንገድ ልክ እንዳላለቀ መንገድ ውጣ ውረድ ዳገት ቁልቁለት ኮረብታው ጠጠሩ ሊያስቸግረን ይችላል።ዋናው ነገር እነዚህን ውጣ ውረዶች እንዴት ልለፈው ብሎ ማሰብ ነው።ምን አይነት ምቹ ጫማ ባደርግ ይሄን መንገድ በቀላሉ ማለፍ እችላለሁ የሚለው ጥያቄ መመለስ ነው የመጀመርያው ውሳኔ ሊሆን የሚገባው።ምን አልባትም እኮ ባለቀው መንገድም መተን እኮ የተቀደደ ወይም የተበጠሰ ጫማ ብናደርግ የመንገዱ ጉዞ እና ምቾት ማጣታችን ያው ነው የሚሆነው።ሂወትም እንደዚህ ነው ምንም የተደላደለ ነገር ቢኖርም በሂወት ጉዞ ላይ ልክ ጫማው ተበጥሶ ምቾት እንደነሳው ወይም መንገዱ ባለማለቁ እንደተፈጠረው ምቾት ማጣት ፈተናዋች ይፈጠራሉ።ዋናው ነገር ግን እንዴት አድርጌ ከፊቴ የተደቀነውን መሰናክል ልለፈው የሚለው ነው።
አሜንን በማጣቴ ደስታዬን ተቀምቻለሁ ነገር ግን ከኔ ደስታ በላይ መቅደም ያለበት የልጁ ህይወት ነው።ይኼን እያሰብኩኝ እያሰላሰልኩኝ ድንገት ከሀሳብ ማዕበል ብንን ስል ለካ ሰአቱም ሄዶ እኔም የያዝኩትመፅሀፍ አንድ ገፅ እንኳን ሳልገልጥ የመጀመሪያው ገፅ ላይ ነኝ። ተነሳሁኝና የቀረውን ሰአት ለመተኛት ወደ ውስጥ ገባሁ ቃልን እንዳልረብሻት ቀስ ብዬ ገብቼ ተኛሁ።
ብዙም ሳልቆይ የወፎቹ ጫጫታ ከተኛሁበት አነቃኝ።ምንም ነገር ሳልናገር ተነስቼ ለባብሼ ወደ ቤተክርስትያን ሄድኩኝ።ለአሜንም አልደወልኩም ከመጣ አገኘዋለው ብዬ እንደ ድሮ ግዜ ቀጠሮ ሄድኩኝ።ስሄድ ግ ከኔ ቀድሞ አሜን ደርሶ ጠበቀኝ።ልክ እንዳየሁት እናቷ ገበያ ሄዳ እንደቀረችበት ህፃን ልጅ እያለቀስኩኝ እቅፍ አድርጌው አለቀስኩኝ።
እሱም ሁኔታዬ እና እያሳለፈው ያለው ነገር ተደራርቦበት ተቃቅፈን ማልቀስ ጀመርን።እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ እንባውን ከአይኖቹ ላይ እየጠረኩኝ ለማረጋጋት ሞከርኩኝ።እሱም በትንሹም ቢሆን መረጋጋት ቻለ።ከዛ ሁለታችንም አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለብን ነገርኩት።እሱም በጭንቀት እሺ ምን አድርግ ብለሽ ትመክሪኛለሽ አለኝ፦እኔም ምን ያህል በሱ እንደተጎዳሁከሱ ሌላ ወንድ ያለ መስሎ እስከማይሰማኝ ድረስ እንደወደድኩት ነገርኩት።እሱም ለኔ ያለውን ስሜት ነገረኝ ግን ምን ዋጋ አለው ነገሮች ሁሉ መስመራቸውን ስተዋል።
ሁለታችንም ቃል ተገባብተን አንተም ለልጅህ ስትል እኔን እንደተውከኝ እና እኔም ያንተን ሰላም በልጅህ ውስጥ እንድታገኝ እኔም አንተም እየተዋደድን የ አንድ ትንሽዬ ልጅ ህይወት ለማትረፍ የከፈልነው የፍቅር መስዋትነት መሆኑ ገብቶን በሰላም እንድንለያይ ቃል አስገባሁት።ነገሮች ከባድ ቢሆንም የአንድ ቀን ጥፋት የዘላለማችን ሊሆን የሚችለውን የፍቅር የህይወት አሳጥቶናል።ከዚህን በኋላ ላንገናኝ እሱም ለኔ ሲል እኔም ለሱ ስል የወደፊት ህይወታችንን ለማሳመር ቃል ተገባብተን በዛሬዋ ቀን በመድሀኒአለም ቤተክርስትያን አልቅሰን ተቃቅፈን መልካም ህይወት እርስ በእርሳችን ተመኛኝተን ተለያየን

ወደ እቤት ስገባ ቃል ተነስታለች እንደተለመደው ቁርስ ሰርታ ቡና አቅርባ ጠበቀችኝ።እኔም የሆዴን በሆዴ የልቤን ህመም በልቤ ይዤው ምንም እንዳልተፈጠረ የሰራችሁን ቁርስ መብላት ጀመርን።
እኔ እና አሜን የመረጥነው መንገድ መሰናክል ቢበዛበትም የወሰነው ውሳኔ ህመም ቢበዛበትም ወደፊት ሊፈጠሩ ከሚችሉ ህመሞች ግን አይብስም። "ዛሬ ላይ ታመን ለነገው ቀናችን ፈውስ ሆነናል"
ቃልና ወንድሜም ከኔ ህይወት ተምረው ነጋቸውን ለማሳመር ሲሉ ዛሬ ላይ ጥሩ ነገር ለመስሪት እየሞከሩ ነው።
እግዚያብሄር ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው ነገ ለኔ የተሻለውን እንደሚያዘጋጅልኝ አምናለሁ።ለአሜንም እንደዛው ምን አልባት አሜንን ወደ እኔ ህይወት ያመጣው ከፈጠረኝ ፈጣሪ ጋር እንዳወራ አብዝቼ ወደ እሱ እንድቀርብም ይሆናል።እናም በሰው መደገፍ አንድ ቀን መውደቂያን እንደሚያበላሽ እንድረዳም አድርጎኝ መደገፊያዬን ፈጣሪዬን ብቻ አድርጌ ሀዘኔን መከፋቴን ቀንሻለሁ። የተፈጠረውን በሙሉ ሁሉም ለበጎ ነውና ስለማያልቀው ቸርነትህ አሜን አሜን አሜን ብዬ ተቀብያለሁ።

ሁል ግዜ የምንመርጠው መንገድን ከመወሰናችን በፊት ለምን ብለን ቆም ብለን እናስብ ለምን የሚለውን መልስ ካገኘን እንዴት እና በምን የሚሉ መንገዶችን እናስብ እናስተውል........
የኔ እና የአሜን ታራክ መጨረሻችን መለያየት ሆኗል ለምን ብለን ስንጠይቅ አንድ ምንም የማያውቀው ልጅ በህይወት ለማትረፍ እንዴት ለሚለው ነገር እሱ የልጁን በህይወት መኖር ሲያስብ ደስተኛ ይሆናል እኔም የሱ ደስታ ያኖረኛል መጀመሪያችን ባለማስተዋል ጀምረነዋል መጨረሻችንን ግን በማስተዋል አድርገነዋል ሰው ካሰበው እግዚያብሄር የፈቀደው ነውና የሚሆነው በድጋሜ አሜን ብዬ ተቀብዬ ከአሜን ጋር ያለኝን ታሪኬን ጨርሻለሁ ህይወት ግን ከአሜን ውጪ ይቀጥላል
@brshchekolata
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

22 Oct, 17:48


Channel name was changed to «ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች»

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

22 Oct, 16:13


Join on this link
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

16 Oct, 18:25


Join and share this link
👇👇👇👇👇👇
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

09 Oct, 18:06


Join on this link
@brshchekolata
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

09 Oct, 12:06


@brshchekolata
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

08 Oct, 17:53


Join on this link
👇👇👇👇👇
@brshchekolata
@brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

07 Oct, 19:00


Join on this link
👇👇👇👇👇
t.me//Brshchekolata
t.me//brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

07 Oct, 17:48


አሜን ክፍል( 31)
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ለብዙ ነገር ያሰብኩት አሜን ዛሬ ላይ ልጅ እንዳለው ማመን ከበደኝ። ይባስ ብሎ ደሞ ቤተሰቦቿን ይቅርታ ጠይቆ እንደመጣ ማሰቡ በጣም ከባድ ነገር ሆኖብኛል።
ቃል ስለተፈጠረው ነገር ለወንድሜ ነግራው ነገ ከአባቴ ጋር እንደሚመጡ ነገረኝ።እኔም እቤት ዛሬ መሄድ አለብኝ ብዬ ልብሶቼን ሰብስቤ ከቃል ጋር ለመሄድ ተነሳን።



ሰፈር ስንደርስ ውስጤ ተረበሸ መድሀኒአለም ቤተክርስትያንን ተሳልመን የአሜንን በር እያየሁ ወደ ቤቴ ገባው።እንደ ቀልድ የተጀመረ ፍቅር ገና ምኑንም ሳላጣጥመው የመለያየት አፋፍ ላይ ቆሜ ወደ ገደሉ ስገባ እንጂ ምንም መውጫ መንገዱ ሊታየኝ አልቻለም።ውስጤን ምንም እንዳልሆንኩኝ ለማሳመን ፊቴን በፈገግታ ሞልቼ የልቤን ሀዘን እና ስብራት ማንም እንዳያውቅ አምቄ በውስጤ ቀብሬ ይዤዋለው።




ቃል ወድያውኑ መለወጤን ስታይ በጣም ተገርማለች። ዛሬ እናንተ ጋር አድራለሁ ብላኝ ስለመጣች ቤት ስናፀዳ ምግብ ስንሰራ ዋልን።አመሻሹ ላይ ቤተክርስትያን እንሂድ ተባብለን አብረን ወጣን። ቃለ ጉባዬ ሰምተን ከጨረስን በኋላ ፀሎት ለማድረግ ወደ አውደ ምህረቱ ሄድኩኝ። እናም ከሰው ልጅ ልደብቀው የምችለውን ስሜቴን ፈጣሪ ያውቀዋልና በምህረቱ ይጎበኘኝ ዘንድ ደጁ ላይ ወድቄ ማልቀስ እና ብርታቱን እንዲሰጠኝ አጥብቄ ለመንኩት።እንባዬን ጠርጌ ተነስቼ ወደ ቃል ጋር ስሄድ እንደኔ የከፋው ሰው በወንዶች መግቢያ በር ጋር ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል።
ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲያለቅስ አይቼ አላውቅም እና ፀሎቱን እንዲሰማው ለፈጣሪዬ ፀሎቴን አደረስኩኝ።ቀና እስከሚል መጠበቅ ጀመርኩኝ። ቃል ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ እኔ መጣች።እንሂድ ስትለኝ እሺ ብዬ እየተሳለምኩኝ ልጁ ቀና አለ።ልቤ ለሁለት ሲከፈል እየተሰማኝ ነው እንደዛ ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ የነበረው የኔ አሜን ነበር።እሱ እንዲያየኝ ስላልፈለኩ ቶሎ እንሂድ ብያት ቶሎ ሄድን።እቤት ስንገባ ቡና አፈላለው አንቺ ቁጭ በይ ብያት ማቀራረብ ጀመርኩኝ።መጀመሪያ እራት አቅርቤ አብረን በላን።

ስንጨርስ ቡና ማፍላት ጀመርኩ ቡናውን እየጠጣን ወንድሜ ለቃል ደውሎ እረጅም ሰአት አወሩ።እኔም ሲኒውን አነሳስቼ መፅሀፍ ይዤ ቁጭ አልኩኝ።
አውርታ ከጨረሰች በኋላ በጣም ደክሞኛል ገብቼ ልተኛ ስትል እሺ እኔም መፅሀፍ ላንብብ አልኳት። እሷም ገብታ ተኛች እኔም ደሞ መፅሀፉን ይዤ ወደማያልቀው የትዝታ አለም ውስጥ ገባሁ። እሱን አለማሰብ ይከብዳል በተለይ ደሞ ቅድም ቤተክርስትያን ውስጥ ካየሁት በኋላ ስላለበት ሁኔታ ማሰብ ጀመርኩኝ።ድንገት ከሀሳቤ ስልክ ተደውሎ ካለሁበት ሀሳብ አወጣኝ።
ሳየው አሜን ነበር ላለማውራት ወስኜ ነበር ግን ደሞ የቅድሙ ሁኔታውን ሳስበው ስልኩን አንስቼ ሆሎ ስለው በደከመ ድምፁ እንዴት ነሽ አለኝ እኔም ደና መሆኔን ነገርኩትና ስለሱ ጠየኩት።እኔ ደና አይደለሁም በአንድ በኩል አንቺ በሌላ በኩል ደሞ ከሳምንታት በፊት ያወኩት ልጄ እንቅልፍ ነስታችሁኛል አለኝ። አሁን እሱ እንዴት ነው ስለው አሁን ምንም አይልም እኔን ካገኘ በኋላ እኔን ካጣ ግን በጣም ይጎዳል የጤናሁ ሁኔታ በኔ እጅ ላይ ነው ለዛ ነው እንደዚህ አይነት ውሳኔ ውስጥ የገባሁት አለኝ።በኔ ስህተት ወደ እዚህ አለም እንዲመጣ አድርጌዋለው መልሼ ደሞ በኔው ስህተት ወደ መጣበት መመለስ አልችልም። ብሎኝ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ምንም ላረጋጋው ስላልቻልኩኝ ከሰማሁት በኋላ ነገ ቤተክርስትያን መተህ እናውራበት አንተ ተረጋጋ የሚል ምላሽ ሰጠሁት። እሱም እሺ ብሎ መልሶ ደግሞ ደጋግሞ ይቅርታ ጠየቀኝ እኔም እሺ ሰላም ያሳድርህ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት።
ይቀጥላል.......................................

ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Brshchekolata
t.me/brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

06 Oct, 18:50


አሜን ክፍል( 30)
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ከምን እንደምጀምርልሽ አላውቅም ከሰማሺኝ በኋላ ይቅርታ እንድታረጊልኝ አልጠብቅም።ምክንያቱም ውሳኔው ያንቺው ነው። ብሎ ለመናገር ዳር ዳር ማለት ጀመረ።እኔም እሺ ንገረኝ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩኝ። እጁ ላይ ያለውን ሰአት አስር ግዜ እያሽከረከረ ይኸውልሽ እኔ ማለት አሁን እንደምታውቂኝ አይነት አሜን አለበርኩም። በጣም ዱርዬ አስቸጋሪ ነበርኩኝ።በተለይ ደሞ ግቢ በነበርኩባቸው ግዜያት እራሴን ማንነቴን አጥቼ ነበር።በዛን ሰአት ከብዙ ሴቶች ጋር እሆናለው አሳልፋለሁ።እና ግቢ በነበርኩባቸው ግዜያት የግቢው ቆንጂዬ ከሆነችው ኤደን ከምትባል ልጅ ጋር ተዋወኩኝ። እናም ብዙ ነገሮችን ከሷ ጋር አሳለፍን።አንድ ቀን የጓደኛዋ ልደት ላይ በጣም አመሸን ጠጣን አንድ ላይ አደርን። ከወራቶች ቆይታ በኋላ እንዳረገዘች ስትነግረኝ እኔም እንደማልፈልግ ነገርኳትና ብር ሰጥቼ እንድታስወርድ ነገርኳት። እሷም ትምህርቷን በኔ ምክንያት አቋረጠች።እኔም ተምሬ ተመረኩኝ።ይኼ ነገር ከተፈጠረ በኋላ ግን ወደ እራሴ ተመለስኩኝ በኔ ምክንያት ትምህርቷን ያቋረጠችን ሴት እያሰብኩኝ ሰላሜን አጥቼ ለብዙ አመታቶች እሷን እያሰብኩ ነበር ሂወቴን የቀጠልኩት። እንባ እያነቀኝ ይኼን ያህል ከፀፀተህ ለምን አትፈልጋትም ነበር ?እሷን ለመፈለግ ለምን አልሞከርክም? ስለው እሱም አይኗን የማይበት ድፍረት አለበረኝም አለኝ።እሺ አሁን ይኼ ካንተ መጥፋት ጋር ምን አገናኘው ብዬ ስጠይቀው እሱም አሁን ይኼ የፈራሁትና ብዙ አመት የተሰቃየሁበት ጥፋቴ በሬን አንኳኩቶ ሰተት ብሎ ገብቷል ብሎ አንገቱን ደፋ።አልገባኝም ብዬ መልሼ ጠየኩት ኤደን አድራሻዬን ፈልጋ ካለሁበት ድረስ መታ ነበር አለኝ።

እኔም ሰውነቴን ፍርሀት እየከበበው እና ይኼ እኮ ጥሩ አጋጣሚ ነው ይቅርታ ለመጠየቅ ስለው በረጅሙ ተንፍሶ አንቺ እንደምታስቢው ቀላል አይደለም ብቻዋን አይደለም የመጣችው አለኝ።እኔም ጭንቅላቴ ውስጥ ብዙ ጥያቄዋች እየተመላለሱብኝ ከነዛ ሁሉ ጥያቄዋች መሀል እና ከማን ጋር ነው የመጣችው የሚለውን ጥያቄ ጠየኩት እሱም ከብዙ ዝምታዋች በኋላ ልጁን አላስወረደችውም ከልጇ ጋር ነበር የመጣችሁ ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ አንደ ወደ በሩ አንዴ ወደ እኔ እየመጣ መንቆራጠጥ ጀመረ።እኔ የነገረኝን ነገር መቀበል ከብዶኝ በፍርሀትና በለቅሶ ውስጥ ተዋጥኩኝ አሜንን ምን አለ ባላወኩት የሚል ስሜት ውስጥ ገባሁኝ።እሺ አሁን ለምን ይኼን ያህል ግዜ ቆይታ ለምን አሁን መጣች ስለው ልጁ አባቴን አሳዩኝ ብሎ ነው። በዛ ላይ የቤተሰቦቿ ጫና አለ አሁን ልጁ አምስት አመት ሊሞላው ነው።ገና በዚህ እድሜው ቤተሰቦቿ የልጁን ጭንቅላት በጥያቄ መርዘውታል። እናም በዚህ ምክንያት የጤናው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰም ነው ወደ እኔ የመጣችው። እና እኔም ፀበል ብዬ የሄድኩትየሷን ቤተሰቦች ይቅርታ ጠይቄ ልጅነቱንም አምኜ እንድቀበል ነበር።እኔም የጠየቀችኝን ነገር ለልጄ ስል አድርጌዋለሁ።ይቅርታን አልጠበኩም ግን ለጥያቄዋችሽ መልሶች እንድታገኚ ነው።ይቅርታ አልጠብቅም ግን ገና አዲስ ሂወት ከመጀመሬ ሂወቴ ባጠፋሁት ጥፋቶች አሁን እየተቀጣው ነው። የፍርድ ቀኔን እየተቀበልኩኝ ነው ሲለኝ ትቼው ወደ ውስጥ እያለቀስኩ ገባሁ። እሱም ብዙ ሳይቆይ ወጣ ቃልም ሁሉንም ነገር ስናወራ የነበረውን ስለሰማች ወደ እኔ መጣች። አቅፋኝ እሳም አብራኝ አለቀሰች።




ይቀጥላል.......................................

ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Brshchekolata
t.me/brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

02 Oct, 17:05


አሜን ክፍል( 29 )
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ዛሬ ፈተና የምንጨርስበት የመጨረሻው ቀን ነው።በጠዋት ተነስቼ ልብስ እየቀየርኩ እያለ ቃል ተነሳች።ባትነሳ ኖሮ ዝም ብዬ ለመውጣት እያሰብኩኝ ነበር። ስትነሳ ሀሳቤን ቀይሬ አልጋ ማንጠፍ ቤት ማፅዳት ጀመርኩኝ። እሷም ቁርስ ለመስራት ገባች።ወንድሟ ሁኔታዋቼን አይቶ ምን እንደሆንኩኝ ጠየቀኝ። እኔም ምንም ሳላንገራግር እንባ እየተናነቀኝ አሜን ፀበል ሄዶ ከመጣ ጀምሮ ፀባዩ እንደተቀየረብኝ ነገርኩት። እሱም አይዞሽ ሁሉም ይስተካከላል አንቺ ብቻ ግዜ ስጪው ብሎ አፅናናኝ።
ትንሽ ቀለል አለኝ።ቃልም ወድያውኑ ቁርስ አቀራረበችና አንድ ላይ መብላት ጀመርን።በልተን ከጨረስን በኋላ እሱም ወደ ስራ እኛም በሩን ዘግተን ወደ ትምህርት ቤት ሄድን። ጓደኞቻችን ተሰብስበው ቁጭ ብለዋል ሰላም አልናቸውና ፈተናው እስከሚጀመር ማውራት ጀመርን።የመጨረሻ ፈተና ዛሬ ነው ስንጨርስ ለምን ወተን ፈታ አንልም አለ ከመሀከላቸው ትንሳዬ የሚባለው
የክላሳችን እብድ የሆነ ልጅ አብዛኛዋቹ በሀሳቡ ተስማሙ አንዳንድ ልጆች ደሞ ሌላ ቀን የሚል ሀሳብ አመጡ።

በዛ መሀል ሀሳብ ያልሰጠሁት እኔ ብቻ ስለነበርኩኝ ሀሳብሽ ምንድነው ዝምታ አይፈቀድም ሲሉኝ ብዙ ላለማውራት እሺ እስማማለሁ ብዬ ወሬውን አሳጠርኩት።ብዙ ሳይቆይ ፈታኙ መጣና አቀማመጣችንን አስተካክሎት ፈተናውን እንድንጀምር አደረገን።ፈተናው ቢጠና ቀላል ነው ሁሉም ቀሏቸው ነበር የሚሰሩት እኔም የማውቀውን ሰርቼ የማላቀውን ገምቼ ወጣሁኝ።ብዙም ሳትቆይ ቃልም ወጣች።በቃ እንሂድ አልኳት አይ አንቺ ሂጂ እኔ ትንሽ ቆይቼ እመጣለሁ አለችኝ እሺ በቃ ቻው ብያት ወደነ ቃል ቤት ሄድኩኝ።
ካለሁበት ድብርት ውስጥ ሊያስወጣኝ የሚችለው አሜን ብቻ እንደሆነ አውቃለው ቢሆንም ግን ከራሴ ጋር ትልቅ ጦርነት ውስጥ ነኝ እሱን ላለማሰብ እየሞከርኩኝ ግን ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም።እቤት እንደደረስኩኝ ገብቼ ተኛሁኝ።ብገላበጥም እንቅልፍ የሚባል ነገር ሊወስደኝ አልቻለም።ትንሽ ጋደም እንዳልኩኝ ወንድሜ ደወለ። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ሰሞኑን እንደሚመጣ ነገረኝ እሺ አባዬን ሰላም በልልኝ ስለው ከሱ ጋር ነው አብረን እምንመጣው ናፍቃኛለች አይናን ልየው እያለኝ ነው አለኝ በቃ አብራችሁ ኑ ብዬው ስልኩን ዘጋሁት።
ስልኩን እንደዘጋሁት የቃልን ድምፅ ሰማሁ ከሰው ጋር ናት እያወራች ገባች።ስትጠራኝ ዝም አልኩኝ ከዛ መጣችና ጠራችኝ ሰው ይፈልግሻል ተነሺ አለችኝ እኔም እየተነጫነጭኩኝ ተነሳሁ።ወደ ሳሎን ስገባ ፊት ለፊት ያለው ሶፋ ላይ አሜን ቁጭ ብሏል። ሳየው በጣም ነበር የደነገጥኩት።ፊቱ ጠቋቁሯል ሰውነቱ በጣም ከስቷል ጭራሽ አሜን አልመስልሽ አለኝ ቆሜ እያየሁት እንባዬ ዱብ ዱብ አለ።😔😔😔😔😔😔😔😔



አሜንም ወደ እኔ መጣና አቅፎ በጣም ይቅርታ አንቺን ላለማስጨተነቅ ነበር አሁን ግን ትልቅ ጥፋት እንዳጠፋሁ አውቃለው ሲለኝ ምንም ምላሽ አልሰጠሁትም ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። እንባዬን ጠርጎልኝ ነይ ቁጭ በይ ሁሉንም ነገር ላስረዳሽ ብሎ ቁጭ አልን።


ይቀጥላል.......................................

ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Brshchekolata
t.me/brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

14 Sep, 17:21


❤️❤️እንደ እናት ❤️❤️
ክፍል አራት
ውጪው በሳርና በሚያማምሩ ዛፎች የተዋበ ነው።ሁሉም ቁምጣና እጃቸው ላይ ጅራፍ ይዘው ሁሉም ከያሉበት ሆነው ያንን ጅራፍ ያጮሀሉ።በጎቹም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እየተሯሯጡ የአከባቢው ውበት ሆነዋል።ፊት ለፊታችን ነጭ በጣም የሚያምር ፈረስ አንድ ልጅ እየጋለበ ወደኛ እየመጣ ነው።ቶሎ ወደኛ ደርሶ አስጋልቦኝ እያልኩኝ ሳስብ ቀረብ እያለ ሲመጣ ከኔ በፊት የተወለደው ወንድሜ ግዛቸው ነው።መቶ ሰላም አለንና ፈረሱን ይዞ ሊገባ ሲል እንዲያስጋልበኝ ጠየኩት።እሱም አንዴ ጠብቂኝማሽ እምዋን አይቼ ልምጣ ብሎኝ ገባ።ብዙም ሳይቆይ እናቱን አይቶ ከመጣ በኋላ ፈረሱ ላይ እንድወጣ ጠየቀኝ እሺ ብዬ ለመውጣት ስሞክር ፈራሁ መላኩ በአንድ በኩል ግዛቸው በአንድ በኩል ይዘውኝ እንደምንም ብዬ ወጣሁ ከወጣሁኝ በኋላ ጩኸቴን አቀለጥኩት።አውርዱኝ ብላቸውም አልሰማም አሉኝ በመከራ እየፈራሁም ቢሆን ከፍታውን ለመድኩት።በፈረሱ እየሄድኩኝ እያለ ወድያው ከቤት ቅልጥ ያለ ጩኸት ተጮኸ።ግዛቸው ወይኔ እምዋ ብሎ እየሮጠ ሄደ መላኩም አቅፎ አውርዶኝ አብረን ወደ እቤት ስንገባ ሁሉም እያለቀሱ ነው።እምዋ እምዋ እያሉ ሲያለቅሱ ወላጅ እናቴ እንደሞተች ገባኝ።እኔ ለቅሶም ሆነ እንደዚህ አይነት ግር ግር ሳይ የመጀመሪያዬ ነው።በጣም ነበር የደነገጥኩት።ሁሉም እያለቀሱ ነው መላኩም አቀርቅሮ ጥግ ጋር ቁጭ አለ ጭንቀት ውስጤን ሲወረው እየሮጥኩኝ ወጥቼ ብቻዬን ቁጭ አልኩኝ ምን ማረግ እንዳለብኝ ምንም አላውቅም የሰው አለቃቀስና ጩኸት በጣም ነው የሚያስፈራው ብዙም ሳይቆይ መላኩ ያለሁበት ቦታ መጣ በእናት ከዚህ ቦታ እንራቅ ዝም እስከሚሉ ድረስ ጭንቀት አልችልም አልኩት።ብዙም እንድንርቅ ስላልፈለገ በቃ መኪና ውስጥ እንሁን ብሎ መኪና ውስጥ ቁጭ አልን ድምፃቸው ቢሰማም እነሱን እያየው በሰቀቀን ከማልቅ መኪና ውስጥ መሆናችንን ወድጄዋለሁ።ከየቤቱ ሁሉም እየተጠራራ እያለቀሱ ይገባሉ ጩኸቱ የባሰውኑ በጣም በረታ።እቴቴን ጠርቻት ወደ እቤት መሄድ ብንችል ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን ይኼ የኔ ምኞት ነው።
ትንሽ ጩኸቱና ለቅሶው እየቀዘቀዘ መጣ።እቴቴም እኔን ፍለጋ ነው መሰለኝ ከግቢ ስትወጣ አየኋት መኪናውን ክላክስ ሳረግ ወደ እኛ መጣች ፊቷ በጣም ቀልቷል አይኖቿም አባብጠዋል።እዚህ ነሽ እንዴ ከአይኔ ስትጠፊ የት ሄድሽ ብዬ ነው በቃ እዚሁ ቁጭ በይብላኝ ልትሄድ ስትል አቅፌ አይዞሽ አለሁልሽ ብያት ወደ ውስጥ ገባው እሷም ወደ ትልቁ ቤት ሄደቾ።
እዛው መኪና ውስጥ ቁጭ ባልንበት ሰአቱም መሸ በጣም ጨለመ መላኩ በይ እንግባ ብሎኝ ይዞኝ ገባ።ስገባ ጠዋት በፍቅር የተቀበሉኝ ሰዋች ፊት ነሱኝ።ይባስ ብለው በአጠገባቸው ሳልፍ እቺ አሁን ምኗን እምዋን ይመስላል አንዴም እንኳን የእንባ ዘለላ ከአይኗ አልወረደም እያሉ ስለኔ ማውራት ጀመሩ።ምንም እንኳን የፈለጉትን ቢያወሩም ከውስጤ አዝኜ ነበር።እንደምንም ብዬ ነገሮችን በትግስት ለማሳለፍ እየሞከርኩኝ ነው።መላኩም ሁኔታው ስለገባው ጆሮ አትስጫቸው ዝም ብለሽ እለፊው እያለ ነገሮችን በዝምታ አለፍኩኝ።በጣም ስለመሸ እቴት ለእኔ መኝታ ማመቻቸት ጀመረች እራት የለም እዚህ ጋርአረፍ በሉ ብላንሌላ ቤት ቦታ አዘጋጀችልን።ግዛቸው ወደ እኛ ጋር ሲመጣ አቀፍኩትና አለቀስኩኝ።ምንም እንደ እቴት ባትሆንልኝም እጄን ይዛ ያለቀሰችው ጭንቅላቴ ውስጥ ስለቀረ እሱን አቅፌው እስኪወጣልኝ አለቀስኩኝ እሱም እኔ ሳለቅስ አይቶ አለቀለ እንዳይለቀስ ስለተባለ እረፍ ለማለት ወደኛ ሲመጡሁኔታችን አላስችሎል ብሏቸው አብረውን አለቀሱና ቶሎ ዝም አስባሉን እኔም ወደ ተዘጋጀልን መኝታ ልሄድ ስል ግዛቸው እራት ይዞልን መጣ።እኔና መላኩ ትንሽ ከበላን በላን በኋላ ከድነን አስቀምጠን ተኛን እነሱ እስከሚነጋ ድረስ እየሰሩ ሊያድሩ ነው መሰለኝ አንተኛም አሉ።እኛ እዛው ተኛን።
ይቀጥላል.......................................
ከወደዳችሁት join on this link
👇👇👇👇👇👇👇
t.me//brshchekolata
t.me//brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

11 Sep, 15:42



🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻HAPPY NEW YEAR🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
I wish you guys :
🌻Health
🌻Laughter
🌻pure joy and
🌻peace of mind in tz New Year

🌻🌻May 2014 E.C be an🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻extraordinary one for you🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻guys !
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 Join on this link 🌻🌻🌻👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me//brshchekolata
t.me//brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

05 Sep, 18:14


ልጄ አለው አለኝ
ችግርነና ሀዘን ከደጄ ቆመዋል
የቤቴ ማገሩ ለመውደቅ አጋድሏል
ይሄንን ስላወቀ ሆዴ በጣም ፈርቷል
ለሚመጣው ሰግቶ እንባዬም ይፈሳል
ችግር ሲመጣ አይጠፋም ነበር መውጫ ቀዳዳ
በሩም ተዘጋብኝ ቀኑም ጨልሞብኝ ገባሁኝ እዳ
ችግር ችግር ወልዶ መሸከም እስኪያቅተኝ
ምነው ፈጣሪዬ ብዬ እንደለመንኩኝ
የፀሎቴን ምላሽ ወድያው አገኘሁኝ
እኔስ መስሎኝ ነበር ፊቱን ያዞረብኝ
ለካስ የማይረሳ ትልቅ አባት አለኝ
በጭንቀቴ ቀን ልጄ አለው የሚለኝ።


ከወደዳችሁት joni on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/brshchekolata
t.me/brshchekolata
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

30 Aug, 18:30


አሜን ክፍል( 28)
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ጠዋት ከእንቅልፌ ቃል ቀሰቀሰችኝ ልብሳችንን ቀያይረን ከወንድሟ ጋር አብረን ቁርስ በልተን አንድ ላይ ወጣን። ድሮ ስለ ፈተና እያወራን ነበር የምንሄደው ዛሬ ግን ሁለታችንም ዝም ተባብለን ትምህርት ቤት ደረስን ብዙም ሳንቆይ ወደ ፈተና ገባን።ጥያቄው ላይ ትኩረት ማድረግ ከበደኝ ሀሳቤ ሁሉ አሜን ጋር ነው።ቶሎ ጥያቄዋቹን መልስ ሞልቼ ወድያውኑ ወጣሁ። እንደወጣሁ ለአሜን ደወልኩለት ይጠራል አያነሳም። ቀጥታ ወጥቼ ወደ ሰፈር የሚወስደውን ታክሲ ይዤ ሄድኩኝ።ሰፈር ስደርስ መልሼ ደወልኩለት አሁን አያነሳም ወደ እቤት ገባሁኝና ትንሽ ለመረጋጋት ሞከርኩኝ።እቤቱ በዚህ ንዴት መንፈስ መግባት አልፈለኩም እና እሱ እስከሚደውል ብጠብቅም አልደወለልኝም እሱ እንዳለው ፈተናውን ስንጨርስ እናወራለን ብዬ ቃል ሳትመጣ ወደነ ቃል ቤት ለመሄድ ስነሳ ቃል ደረሰችብኝ የግቢው በር አንኳኳች እሷ መሆኗን አውቄ ነበር።ስከፍተው ግን ፍፁም ያላሰብኩት ሰው በሬ ላይ ቆሟል። አሜን ነበር ግን ጭራሽ እሱ አይመስልም ስትመጪ አይቼሽ ነበር በይ ዝጊና ነይ እጠብቅሻለውብሎኝ ከበሩ እራቅ ብሎ ቆመ።እኔም ቶሎ ዘግቼ ወጣሁኝ ምን እንደተፈጠረ ለመስማት ጓጉቻለው ውስጤ ደሞ በፍርሀት ተውጧል በሩን ከመክፈቴ በፊት ቆሜ በረጅሙ ተነፈስኩኝ ።ከፍቼ ወጣሁኝ ሰላም አልኩት ግን ፊቱ ላይ ምንም ደስታም ሆነ የናፍቆት ስሜት አይታይበትም በዚህ አጭር ቀን ውስጥ ምንድነው እንደዚህ የለዋወጠህ ምን ሆነህ ነው አንተስ ለምን እንደዚህ እራስህን ጣልክ ብዬ ውስጤ ውስጥ ያለውን ጭንቀትና ጥያቄዋቼን ባንዴው ዝርግፍ አረኩበት።እሱም ከነዚህ ሁሉ ጥያቄዋቼ አንዱንም ሳይመልስልኝ መልሶ ፈተና እንዴት ነበር ብሎ ጥያቄ አቀረበልኝ እኔም ምንም አይልም ጥያቄዋቼን መልስልኝ ካልሆነ ልሂድ አልኩት እሱም ሂጂ በቃ በተረጋጋ መንፈስ እናወራለን አለኝ።እኔም ንዴቴን እሱ እንዲያውቅብኝ ስላልፈለኩኝ መልስ ሳልሰጠው መንገዴን ይዤ ወደ ቃል ጋር መሄድ ጀመርኩኝ።ንዴት ውስጥ እና እልህ ውስጥ ከተተኝ መንገድ ላይ ያየኝ ሁሉ ዞር እያለ ያየኛል ምንም መረጋጋት አልቻልኩም ነበር።ታክሲ ወድያውኑ ሳልቆም አገኘው መንገዱም ክፍት ስለነበር ወድያውኑ ደረስኩኝ።ስገባ ቃል አልገባችም ነበር ስልኬን አጥፍቼ ገብቼ እስከሚወጣልኝ ድረስ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ ከዚህን በኋላ አልደውልም ብዬ እራሴን አሳመንኩት።ትንሽ ለመተኛት ብሞክርም እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም።ቃል ስትመጣ ምን ሆነሽ ነው ብላ በጥያቄ እንዳታጨናንቀ እራሴን አጠንክሬ ምግብ ሰርቼ ቡና አቀራርቤ ጠበኳት።እሷም ብዙ ሳትቆይ መጣች። እቤቱን አደማምቄ ስለጠበኳት ጥያቄዋቿን አስረሳኋት ዛሬ ፈተናው እንደቀለለሽ ያስታውቃል ደስ ብሎሻል ወይስ ምን አዲስ ነገር ተገኘ አለችኝ እኔም የሆዴን በሆዴ ይዤ አረ ምንም አዲስ ነገር የለም ዝም ብዬ ነው ይልቅ ምሳችንን እንብላ ቁጭ በይ አልኳትና ለማቀራረብ ገባሁ።እሷም ቁጭ አለች እና መጠበቅ ጀመረች።እኔም አቀራርቤ አንድ ላይ መብላት ጀመርን።ትንሽ በልቼ በይ ብዪ ቡናውን ላፍላ ብዬ ተነሳሁ። ቡናውን ስንጨርስ ትንሽ ወጣ ብለን እንዞራለን ስትል አይ አልወጣም አነባለው አልኳት እሷም እሺ አለችኝ። ቡናውን ጠጥተን ስንጨርስ በቃ ወጣ ብዬ እመጣለው አጥኚ አለችኝ እኔም እሺ አልኳት እሷም ወጣች እኔም አነሳስቼ ገብቼ ተኛሁኝ።እሱን ላለማሰብ ብዙ ጥረት እያረኩኝ ነው።ስልኬን መዝጋቴ መፍትሄ እንዳልሆነ አውቃለው ብቻ እማረገው ግራ ገብቶኝ እየተወዛገብኩኝ ነው።በመጨረሻ ቃል መጣች ምነው ቶሎ ተመለሽ ስላት ባክሽ ላንብብ አለችኝ እሺ በቃ አንብቢ እኔ ልተኛ ነው።ጠዋት ቀስቅሺኝ ወንድምሽ ሲመጣ እራት ብሉ እንዳትቀሰቅሽኝ አልኳት እንዴ ቆይ ወጥቼ ከመመለሴ ምን ነክቶሽ ነው ባንዴው ተቀይረሽ የጠበቅሽኝ አለችኝ ጠዋት ቀስቅሺኝ ሰላም እደሪ ብያት ትቻት ገባሁ።
ይቀጥላል.......................................

ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Brshchekolata
t.me/brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

29 Aug, 17:16


❤️❤️❤️እንደ እናት❤️❤️❤️
ክፍል ሶስት
እቴቴ ሁሌም አንድ ነገር ስለኔ ያሳስባታል ለቤተሰቦቼ ያለኝ ምልከታና ለሷ ያለ ፍቅር ከመጠን በላይ መሆኑ ያስጨንቃታል።እኔ ደሞ እሳን ብቻ እንጂ ሌላ እቴትን የሚጋራብኝ ሰው አልፈልግም።እቴት ገጠር እያለች ልጅ ባለመውለዷ የአከባቢው ሰዋች ብዙ ስላወሩባት ልቧ ስለተሰበረ ነበር ወላጅ እናቴ እኔን አሳልፋ የሰጠቻት እሷም ወድያውኑ እዛ ያላትን ንብረት በሙሉ ሸጣ አዲስ አበባ ውስጥ እኔ ነኝ ያለ እቤት ሰርታ ከሰው አፍ ወታ የሰላም ኑሮ መኖር የጀመረችው።ቤተሰቦቼን እንዳልረሳ በየግዜው መተው እንዲጠይቁ ታደርጋለች እኔ ግን ምንም አይመስለኝም።እንደውም ሲመጡ የሚሄዱበትን ቀን ነበር የምቆጥረው።ይኼ ሁኔታዬ እሳን በጣም ከመውደዴ የተነሳና ከሰጠችኝ ፍቅር የመጣ ነው።
የልደት ቀኔን ባከበርኩኝ በሶስተኛው ቀን እለተ ሀሙስ ላይ ስልክ ተደወለ። እቴትም አንስታው ለእረጅም ሰአት ስታወራ ቆየች ማን እንደደወለ ስለማውቅ ጆሮ ሰጥቼ አልሰማሁም ነበር።ስልኩን አውርታ ስትጨርስ በሀሳብ ጭልጥ አለች።እኔም እሱን አይቼ ከሄደችበት የሀሳብ ጉዞ ለመመለስ ስል እቴቴ ብዬ ድምፄን ጮክ አድርጌ ጠራኋት እሳም ደንገጥ ብላ ከሄደችበት የሀሳብ ጉዞ መለስ አለች።ምነው ምን ተፈጠረ ብዬ ስጠይቃት እህቴ በጣም ታማለች በነብስ ድረሺ ነው የሚሉኝ ብላ ነገረችኝ።እና በቃ በነብስ ትደርሻለሽ እኔ ምንም አልሆንም እስከምትመጪ አርፌ እጠብቅሻለው ስላት አይ እንደሱ አይደለም አይንዬንም ይዘሽ ነይ አይንሽን ልታይ ትፈልጋለች ስትለኝ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ብቻዬን ተቀመጥኩኝ።እቴትም ይኼ ግዴታ ነው ነገ እንሄዳለን ብላ ወደ ውስጥ ገባች።መሄድ ባልፈልግም ለሷ ብዬ ጥያቄውን መቀበሌ ግዴታ ሆነብኝ።እሺ በቃ ብዬ እንደምንሄድ ነገርኳት እሳም መኝታ ቤት ገብታ ለማረፍ ጋደም አለች።እንደተጨነቀች ስለገባኝ እንዲቀላት ብዬ የምትወደውን ቡና ለማፍላት ሽር ጉድ ማለት ጀመርኩኝ።መጀመሪያ እሳት አቀጣጥዬ ቡናውን አጥቤ ቆላሁ። የምትወደውን ፋንዲሻም አፈንድቼ ፈጭቼ ከጨረስኩኝ በኋላ ጀበና ውስጥ ጨምሬ እቴትን ለመቀስቀስ ሄድኩኝ።ጀርባዋን ለማሳረፍ እንጂ እንቅልፍ የሚባል አልወሰዳትም።ከተኛችበት እንድትነሳ ውጋት ሆንኩባት ስትነሳ አይኗን በእጄ ሸፍኜ ወደ ሳሎን ወሰድኳት።ሳሎን ስንደርስ እጄን ከአይኗ ላይ አውርጄ ሰርኘራይዝ አልካት እሳም ፈገግ ብላ እደጊልኝ የኔ ልጅ ብላ ግንባሬን ሳመችኝ።እኔም እንድትቀመጥና እራት እንድትበላ እጇን አስታጠብኳት ቡናውእስከሚፈላ ቶሎ በልተን ጨረስን።ፋንድሻው አቅርቤ እኔም ቡናው ሲፈላ መቅዳት ጀመርኩኝ።ቡናው እሷ እንደምትፈልገው አርጌ ስላፈላው ተመችቷቷል።ቡናውን ከጨረስን በኋላ በይ ለነገ እንዘጋጅ ቶሎ እንተኛ ብላኝ አነሳስቼ ለነገ ልብስ ለማዘጋጀት ወደ ውስጥ ገባሁ አዘጋጅቼ ስጨርስ ለእቴት እድሜ እንዲሰጥልኝ ፀሎት አርጌ ተኛሁ።

በለሊት ከእንቅልፋ ተነስታ ቁርስ ሰርታ አቀራርባ ቀሰቀሰችኝ።እኔም መሄዴን እያሰብኩኝ በጣም አስጠልቶኝ እሷን ላለማስከፋት በማሰብ ተነሳሁኝ።ተነስቼ ታጥቤ የተዘጋጀውን ቁርስ አብረን መመገብ ጀመርን።ለሊት ስለሆነ ብዙም መብላት አልቻልንም የቀረውን ለውሻው ሰታ ተነስቼ እንድለባብስ ነገረችኝ እኔም ገብቼ ልብሴን ቀየርኩኝ ይዤ የምሄደውን ልብስ በትንሽ ሻንጣ አድርጌ እሷ እስከምትነሳ መጠበቅ ጀመርኩኝ።እሷም ብዙ ሳትቆይ መጣች።አብረን ተያይዘን ኮንትራት ታክሲ ጠርታ ጉዞ ጀመርን።መንገዱ አድካሚ እንደሚሆን ቀድማ ስለነገረችኝ እራሴን አዘጋጅቼ ነበር።መንገዱን ሙሉ ስንጓዝ እኔም ስልኬ ላይ እቴትም ሀሳቧ ላይ ነበርን።አይደረስ ነገር የለ ከብዙ ሰአታት በኋላ አንድ ቦታ አርፈን ነገ ደሞ በጠዋት ተነስተን እንሄዳለን ብለው አንድ አነስተኛ ሆቴል ገብተን አረፍን። ባለ ታክሲውም የእቴት የቅርብ ወዳጅ ስለነበረ እሱም እዛው አልጋ ይዞ አደረ።እራታችንን እዛው ከበላን በኋላ ነገ በጠዋት ለመነሳት ቀጠሮ ይዘን እሱም አልጋ ወደያዘበት ቁጥር ገባ።
እኛም ወደ ክፍላችን አመራን።ድካምም ስለነበር ወድያውኑ እንደተኛን እንቅልፍ ወሰደን።
የወፎቹን ጫጫታ ሰምታ እቴት ከእንቅልፋ ብድግ ብላ ቀሰቀሰችኝ እኔም ወድያው ተነስቼ ልብሴን ለብሼ መተጣጠብ ጀመርኩኝ ለሱም ደውለንለት ቁርስ ለመብላት እታች እየጠበቅነው እንደሆነ ነገርነው።እሱም ብዙም ሳይቆይ ወድያውኑ መጣ።እንቁላል ፍርፍር አዘን መብላት ጀመርን።በልተን ስንጨርስ እቴት በሉ ቶሎ እንሂድ ብላ ሂሳብ ከፍላ ወጣን። አሁንም መንገዱ አሰልቺ ቢሆንም ጋቢና ተቀምጬ ዘፈን እየቀያየርኩኝ ከልጁ ጋር እያወራሁ መንገዱን ለማቅለል ሞከርኩኝ።ከብዙ ሰአት ቆይታ በኋላ ወደ ሰፈሯ የሚያስገባውን መንገድ እየጠቆመችን መሄድ ጀመርን።ትንሽ ቆየት ብላ እዚ በር ጋር አቁመው ብላ ሲያቆመው ከየት መጡ የሚያስብሉ ልጆች መኪናውን ዙሪያውን ከበቡት።ሹፌሩ ሲወርድ ሁሉም አስነዳን እያሉ መጠየቅ ጀመሩ በአንድ በኩል ደሞ እቴቴን እያቀፉ ተራ በተራ ይሟታል።እሷን ስመው ሲጨርሱ ወደኔ መጡ እኔንም አገላብጠው ከሳሙኝ በኋላ ምራቃቸውን እንትፍ እንትፍ ሲሉብኝ ተናድጄ ፌታቸው ፊቴን በእጄ ጠረኩኝ።ወደ ውስጥ የያዝነውን እቃ ተቀብለው አብረን ገባን።ግቢው በሳር ጎጆ የተሸፈነ እና ዙርያውን ደሞ ላሞች ፈረሶች በጎች እና ዶሮዋች አሉ።
አንደኛው ቤት ደሞ ትንሽዬ ጥጃ ታስራ አጠገቧ ደሞ እዛው እንጀራ እምትጋግር ሴት ትታየኛለች።ወድያውኑ አይታን እጇ ላይ ያለውን ሊጥ በቀሚሶቿ ጠርጋ እኛን ሰላም ለማለት እየሮጠች ወጣች።እሷም እንደሌሎቹ አገላብጣ ሰላም አለችንና ወደ ትልቁ ቤት ግቡ ብላ ፊት ለፊት እየመራችን ሄደች።እኛም ተከትለናት ገባን።እቤት ውስጥ ስንገባ ቤቱ እንዳለ በሰው ተሞልቷል ሁለት ቄሶች አሉ ስንገባ ሁሉም አክብረውን ከመቀመጫቸውብድግ እያሉ ሰላም አሉን።ወንድሞቼም እህቶቼም አባቴም አለ እናቴን በአይኔ ስፈልጋት ትንሽዬ አልጋ ላይ ጋደም ብላለች ሁሉንም ሰላም ብለን ከጨረስን በኋላ ወደ እሷ አመራን።በጣም ታማለች ከተኛችበት አልጋ ላይ መነሳት እራሱ አትችልም።እቴቴን ተከትዬ አብሪያት ቁጭ አልኩኝ። እቴቴም እህቷን አይታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች እኔም እቴት ማልቀሷን አይቼ አለቀስኩኝ።ብዙም ሳትቆይ እጄን እንድሰጣት ጠየቀችኝ እኔም እጄን ሰጠኋት እንባዋ እጄ ላይ ዱብ ዱብ አለ ምንም ነገር አታወራም እያቃሰተች ብቻ ዝም ብላ ታየኛለች እኔም ግራ ገብቶኝ አያታለው።በአንድ በኩል እቴት እያለቀሰች ነው በአንድ በኩል ደግሞ ወላጅ እናቴ እጆቼን ይዛ እያስጨነቀችኝ ነው።ወላጅ አባቴ መቶ ከመንገድ ነው የመጣችሁት አረፍ በሉና ማዕድ ቅረቡ ብሎ እጄን ከእጇ አስለቅቆ እቴትን ይዞ ምግብ እንድንበላ ቁጭ አልን በመሀል ሹፌሩ ግራ ተጋባአብሮኝ ቁጭ ብሎ ምግብ መጣ እቴት አልበላም ብላ ስትል ወላጅ አባቴ ተቆጥቷት መታ ከኛ ጋር በላች የሚጣፍጥ የስጋ ወጥ ነበር።ሹፌሩን ማነህ ግን ወንድሜ ማን ብለን እንጥራህ አሉት እሱም መላኩ ብላችሁ ጥሩኝ አላቸው።እውነትም መላኩ ብለው በል እሺ ብላ ብለውት ጨመሩልን።በልተን ስንጨርስ መቀመጡ ስለጨነቀኝ መላኩን እንውጣ አልኩት እሱም ቁጭ ማለቱን ስላልወደደው አብረን ወተን ዞር ዞር ማለት ጀመርን።
ይቀጥላል....................................
ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@brshchekolata
t.me/brshchekolata
t.me/brshchekolata

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

27 Aug, 20:58


ይኼ የኔ ቻናል ነው
👇👇👇 👇👇
@brshchekolata
ለሀሳብና ለ አስተያየት
👇👇👇👇👇
@brhant
አጠር ያሉ የፍቅር ታሪኮችን እና ግጥሞችን የሚያገኙበት ቻናል
@brshchekolata
Join the channel by inviting your friends and relatives

ግጥሞችና አጫጭር የፍቅር ታሪኮች

22 Aug, 09:24


አሜን ክፍል ( 27 )
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏



ከአሜን ጋር ከተገናኘን ዛሬ ሶስት ቀን ሞላን በጣም ናፍቆኛል።ነገ ደሞ ፈተና ልንጀምር ነው እሱም ነገ ይመጣል።ጠዋት ስነሳ የመጀመሪያ ስራዬ ስልክ ከደወለ ወይም ቴክስት ካረገልኝ ወይም ስልኩ ክፍት ከሆነ ደውዬ ማየት ነው።እንደተለመደው ስደውል ስልኩ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ነው።ቃል ከኔ ቀድማ ከእንቅልፋ ተነስታ ለወንድሟ ቁርስ እያቀረበችለት ነበር። እኔም የተኛንበትን አልጋ አንጥፌ ወደነ ቃል ጋር ሄድኩኝ ሰላም ካልኳቸው በኋላ ቃል ነይ ቁርስ ቀርባል አለችኝ እኔምፊቴን ታጥቤ አብረን በላን።
ወንድሟ እረፍዶበት ስለነበር ተጣድፎ ወጣ።እኔና ቃል በልተን አነሳን። ቃል ለነገ ፈተና እንዘጋጅ ብላ የነገውን ኘሮግራም ማየት ጀመረች።እኔም የበላንበትን አንስቼ ቤት አስተካክዬ ከቃል ጋር ለማንበብ ገባው።
ጥያቄዋችንን መስራት ጀመርን።በመሀል በሀሳብ አሜንን እያሰብኩ እንደምንም እራሴን ማጥናት እንዳለብኝ እያሳመንኩ አጠናን።በመሀል ወሬ ጀመርን ዛሬ እቤት ደርሼ መምጣት አለብኝ ልብስ ይዤ እመጣለው አልኳት ቃልም በቃ እኔም ከሚደብረኝ አብረን ደርሰን እንመጣለን አለችኝ እሺ ተባባልን።በቃ ይበቃኛል እኔ ልብስ ልቀይር ብዬ ከመነሳቴ ስልኬ ጠራ ደስ ብሎኝ ስልኬን ሳየው የአሜን ስልክ አለበረም ወንድሜ ነው።በጣም በንዴት መንፈስ ሆኜ ሳይታወቀኝ አቤት ብዬ ጮህኩኝ ወንድሜም ምላሼ አስደንግጦት ነው መሰለኝ መልሶ ሄሎ አለኝ።እኔም ደንገጥ ብዬ ወደ እራሴ መለስ አልኩኝና ድምፄን ለስለስ አድርጌ አቤት ወንድሜ አይሰማም አልኩት እሱም ይሰማል እንዴት ነሽ ለፈተና እየተዘጋጀሽ ነው አለኝ እኔም አዋ ደና ነኝ እያጠናን ነው አልኩት።
ብር ልኬልሻለው አውጪና ተጠቀሙበት አለኝ እሺ አልኩትና ስለ አባቴ ሁኔታ ጠየኩት አሁን እቤት ውስጥ መራመድ ግቢ ውስጥ መዞር ጀምሯል አሁን ደና ነው አለኝ።
ፈጣራ ይመስገን እንደዚህ ወደ ቀድሞው ሁኔታው ይመለሳል ብዬ አላሰብኩም ነበር።
እና በቃ አጥኑ ቻው ብሎኝ ስልኩን ዘጋው።
አኔም ልብሴን ቀይሬ ቁጭ አልኩኝ ቃል አየችኝና አሜን ደና ነው አለችኝ እኔም አዋ ደና ነው አልኳት።በቃ እኔም ልልበስና እንሄዳለን አለችኝ እሺ አልኳትና እስከምትለብስ ጠበኳት።ወድያውኑ ለብሳ መጣች በሩን ዘጋግተን ወደ እኛ ቤት ሄድን።
ሰፈር ስንደርስ የአሜንን በር በር ማየት ን።ጀመርኩኝ በጣም ነው የናፈቀኝ።እቤት ከፍተን ገባን ቃል ቁጭ አለች።እኔም እምፈልገውን ልብስ ላመጣ ገባው።
የምፈልገውን ልብስ በትንሽ ቦርሳ አድርጌ አጣጥፌ ከተትኩኝ።ቃልን መጣው ምሳ እዚው ሰርተን እንብላ ብዬ ለመገዛዛት ወጣሁኝ።
ሽንኩርት ቲማቲም ዳቦና እንቁላል ገዝቼ ወደ እቤት ተመለስኩ።ቃል የፎቶ አልበም ካለበት ቦታ አንስታ እያየች እየሳቀች ነው።እኔም ገብቼ መስራት ጀመርኩኝ።ሰአቱ ዘጠኝ ሊሆን ደቂቃዋች ብቻ ነው የሚቀሩት።አሜን እስካሁን አልደወለም ስልኬን አንስቼ ስደውል ስልኩ ጠራ ደስ አለኝ።ግን ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ።አሁንም መልሼ ደወልኩኝ አላነሳውም።የጣድኩትን ሽንኩርት እረስቼው አሮ ከለሩን ቀይሯል ቃል እንዳታየው ወድያው ስቶቩን አጥፍቼ ያረረውን ደፍቼ መልሼ ሽንኩርቱን ከትፌ መስራት ጀመርኩኝ።ሽንኩርቱ በጣም አቃጥሎኝ እንባ ካይኔ ወረደ ግን የሽንኩርቱ ማቃጠል ሳይሆን እያቃጠለኝ ያለው የአሜን ስልክ አለማንሳት ነበር።በሽንኩርቱ አመሀኝቼ አስኪወጣልኝ አለቀስኩ።ቃል እንዳታየኝ እንባዬን ጠርጌ መስራት ጀመርኩኝ።ምነው ድምፅሽ ጠፋ ምን ላግዝሽ ስትለኝ ካጠገቤ እንድትሄድ ወንድሜ የዛኔ ልብሶቹን መነቃቅሮ ስለሄደ የሱን ልብስ አስተካክዪ አልካት እሳም ለማስተካከል ሄደች።
እኔም ሰርቼ ጨረስኩኝ አቀራርቤ ጠራኋት።መጣችና ታጥበን በላን።

ትንሽ እንቆይና እንሄዳለን እስከዛ ልጠብ ብዬ የበላንበትን አጣጥቤ ጨረስኩ።ከዛ ልብሴን ይዤ የገዛሁትን ሽንኩርትና ቲማቲም እንዳይበላሽ እሱንም ይዘን በሩን ዘግተን ወጣን።ብር እናውጣ ብያት ብር ለማውጣት ሄድን ብሩን ካወጣሁ በኋላ ሽንኩርት ቲማቲም ፓስታ መኮረኒ ገዛሁ።አብረን ይዘን እነ ቃል ጋር ሆድን።እዛ እንደደረስን እኔ ልተኛ ነው ደክሞኛል ብዬ ገባሁና ጋደም ብዬ ለአሜን አሁንም መልሼ ደወልኩኝ አሁንም ስልኩ አይነሳም።ብዙም ሳይቆይ መጥቻለው እደውላለው ብሎ ቴክስት አደረገልኝ።ን

ቢያንስ አሁን እዚህ ነው ያለው ብዬ ተረጋጋሁኝ ይደውላል ብዬ ስልኬን አይን አይኑን ማየት ጀመርኩኝ።ቃል ብቻዋን ሲደብራት እኔ ጋር መጣች እኔም የተኛሁ ለማስመሰል ስትጠራኝ ዝም አልኳት እሷም ወንድሟ እስከሚመጣ አጠገቤ ስልኳን ይዛ ቁጭ አለች።
ትንሽ ቆይቶ ስልኬ ጠራ ዘልዬ ተነስቼ ስልኬን አየሁት አሜን ነው እሱ መሆኑን ሳውቅ ስልኩን ይዤ እየሮጥኩኝ ወጣሁና ስልኩን አነሳሁት ሄሎ ስለው ሰላም እንዴት ነሽ አለኝ ድምፁም የሱ አይመስልም ነበር መልስ ሳልሰጠው መልሼ ስልኩን አየሁት ግን የሱ ስልክ ነው ድምፄን ቀነስ አርጌ ሰላም ነኝ ምነው ድምፅህ ስለው ድካሙ ነው አለኝ ነገ ፈተና ነሽ መልካም ፈተና አለኝ እሺ ግን ደና ነህ አልኩት አዋ ፈተናሽን ጨርሺና ስለሁሉም ነገር እናወራለን አሁን ደክሞኛል ልተኛ አለኝ።እሺ ነገ ከፈተና ስወጣ አንገናኝም ስለው ፈተናሽን ጨርሺ እና እንገናኛለን አሁን ልተኛ መልካም ፈተና ሰላም እደሪ ብሎ ስልኩን ዘጋው።
እኔም ወደ ቃል ጋር ሄጄ መልሼተኛሁ ምነው ሰላም አይደለሽም ስትለኝ ደና ነኝ እንዳቀሰቅሱኝ ሰላም እደሩ ብያት ተኛሁኝ።
ይቀጥላል.....................................


ከወደዳችሁት join on this link 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/Brshchekolata
t.me/brshchekolata