TIKIVAH-ETH @tkvah_news123 Channel on Telegram

TIKIVAH-ETH

@tkvah_news123


TIKIVAH-ETH (English)

Are you interested in staying up to date with the latest news and trends in the world of Ethereums? Look no further than the TIKIVAH-ETH Telegram channel! As the go-to source for all things related to Ethers and blockchain technology, TIKIVAH-ETH provides its subscribers with timely updates, in-depth analysis, and valuable insights into the world of cryptocurrency. Who is TIKIVAH-ETH? TIKIVAH-ETH is a community of passionate individuals who share a common interest in Ethereums and the potential of blockchain technology. Whether you are a seasoned investor, a curious beginner, or simply interested in staying informed, TIKIVAH-ETH welcomes everyone to join their channel and be a part of the conversation. What is TIKIVAH-ETH? TIKIVAH-ETH is a Telegram channel dedicated to delivering high-quality news, updates, and analysis on all things related to Ethereums. From market trends to upcoming developments, TIKIVAH-ETH covers a wide range of topics to keep its subscribers informed and engaged. With a team of expert contributors and a growing community of followers, TIKIVAH-ETH has quickly become a trusted source of information in the cryptocurrency world. So, why should you join TIKIVAH-ETH? By becoming a member of the TIKIVAH-ETH Telegram channel, you will gain access to exclusive content, expert opinions, and real-time updates that can help you make informed decisions in the world of Ethereums. Whether you are looking to stay ahead of the latest trends, expand your knowledge, or connect with like-minded individuals, TIKIVAH-ETH offers a valuable resource for anyone interested in the future of blockchain technology. Don't miss out on the opportunity to join the TIKIVAH-ETH community today. Stay informed, stay connected, and stay ahead of the curve with TIKIVAH-ETH. Subscribe now and be part of the conversation!

TIKIVAH-ETH

23 Nov, 08:14


የኢለን መስኩ ኒውራሊንክ በካናዳ አካል ጉዳተኞች ላይ ቺፕ ለመቅበር ፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ!

የአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢለን መስክ ንብረት የሆነው የባዮ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኒውራሊንክ ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያውን ችፕስ በሰው አእምሮ ውስጥ መቅበሩ ይታወሳል፡፡

የመስክ ባዮቴክ ኩባንያ የ30 አመት እድሜ ባለው ግለሰብ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ችፕ የገጠመው ባለፈው ጥር ወር ላይ ነበር።ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ባለፈው ነሀሴ ወር ሁለተኛውን ሙኩራ አሌክስ በሚል ስም ለሚጠራ አካል ጉዳተኛ አዕምሮ ውስጥ መግጠሙን እና ግለሰቡም ለውጥ በማሳየት ላይ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

ኩባንያው በሌላኛዋ የሰሜን አሜሪካ ሀገር ካናዳ አካል ጉዳተኞች ላይ እንዲሞከር ፈቃድ እንዳገኘ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ከሆነ የካናዳ ጤና ዩንቨርሲቲዎች ማህበር የኒውራሊንኩን ቺፕ የመንቀሳቀስ ችግር ላጋጠማቸው ዜጎች መግጠም የሚያስችለውን ቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ዝግጁ ናቸው፡፡

የሳንቲም መጠን ያላትን ቺፕ የሰው ልጅን እንቅስቃሴ ፍላጎት ከሚያዘው የአእምሮ ክፍል ላይ በቀዶ ጥገና እንድትቀመጥ የሚደረግ ነው።ይህቺ ቺፕ የአእምሮን እንቅስቃሴ በመመዝገብና የእንቅስቃሴ ፍላጎትን ወደሚተረጉም ማቀላጠፊያ መተግበሪያ ወይም አፕ ለማስተላለፍ ጥቅም ላይ ትውላለች።

ባሳለፍነው ነሀሴ በቀዶ ጥገና አማካኝነት ቺፕ የተገጠመለት እና በጀርባው ላይ በደረሰበት ጉዳት የእጅ እና እግር መገጣጠሚያ አጥንቶቹን ማንቀሳቀስ አይችልም የተባለው አሌክስ ይህች የኒውራሊንክ ችፕስ ከተገጠመችለት በኋላ በኮምፒውተር ጌም መጫወት ጀምሯል ተብሏል፡፡እንደ ዘገባው ከሆነ ግለሰቡ በተገጠመለት ቺፕ አማካኝነት አልታዘዝ ሲሉ የነበሩት የተወሰኑት ነርቮቹ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡(አልአይን)

   

TIKIVAH-ETH

22 Nov, 03:34


በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረግ ግጭት እና ጦርነት መቀጠሉ የህዝቡን መከራ እና ሰቆቃ አባብሶታል።

የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ የሆነው ህዝብ ፤ ግድያ እና መፈናቀልን ጨምሮ ጦርነቱ ያደረሰበት ቀውስ እንዲያበቃ በአደባባይ ድምጹን አሰምቷል።

በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል ከአንድም ሁለት ጊዜ ከሀገር ውጭ የተሞከረው የሰላም ንግግር አልሰመረም ። ህዝቡ ተፋላሚዎች ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኝተው ችግሩን በሰላም ይፈታሉ ብሎ በሚጠብቅበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በየራሳቸው መንገድ የአስገዳጅ የአዳዲስ ወታደር ምልመላ እና አፈሳ እያከናወኑ ነው የሚል ስሞታ ይሰማል።

ይህ ደግሞ የሰላም ጥሪ የሚያሳተጋባውን የክልሉን ነዋሪ ተስፋ ከማሳጣት አልፎ ክልሉን ብሎም ሀገሪቱን ለተጨማሪ የቀውስ ዓመታት እንዳይጋብዝ አስግቷል።

     

TIKIVAH-ETH

21 Nov, 09:17


#Update

ዛሬ 320 የትግራይ ተዋጊዎች  ትጥቅ አውርደው አስረክበዋል።

የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎች ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊትም ታጣቂዎች ያወረዷቸውን ትጥቆች ርክክብ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት 320 የትግራይ ተዋጊዎች ቀላል መሳሪያዎችን አውርደው በማስረከብ ወደ ተሃድሶ ያስልጠና ማዕከል አቅንተዋል።

እንደ ተነገረው ከሆነ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ስልጠናና የማቋቋሚያ ድጋፍ በማድረግ ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ስራ ይሰራል።

https://t.me/TKVAH_NEWS123

TIKIVAH-ETH

21 Nov, 06:32


#tearline

Pre-Market ላይ 1$ ነው ከተጀመረ የተወሰነ ጊዜ ቆይቷል ወደ 2 ሚልየን ተጠቃሚዎች አሉት listing በቅርብ መሆኑንም ይፋ አድርገዋል

መጀመር ለምትፈልጉ 👉https://t.me/TearlineAI_Bot/app?startapp=sZNcAeFI_0

TIKIVAH-ETH

20 Nov, 14:29


#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።


#Somaliland

TIKIVAH-ETH

19 Nov, 17:13


#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።

አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

https://t.me/TKVAH_NEWS123

TIKIVAH-ETH

18 Nov, 17:49


#ማስታወሻ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እና ለማመልከት 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

TIKIVAH-ETH

18 Nov, 08:45


በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ...

በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።

ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አጋርቶ ነበር ።

https://t.me/TKVAH_NEWS123

TIKIVAH-ETH

18 Nov, 07:03


#MondayMotivation

ወጣቱ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ

በፈጠራ ሥራዎቹ 14 የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል፤ የፈጠራ ባለሙያና የድርጅት ባለቤት ወጣት ኢዘዲን ካሚል፡፡

ወጣት ኢዘዲን ካሚል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ካሸነፈ በኋላ በርካታ ዕድሎች እንዳገኘ ይናገራል፡፡

በ2010 እና 2011 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊ እንደነበር የሚገልጸው ወጣት ኢዘዲን፣ የፈጠራ ሥራዎቹ የተሻለ ሀብት፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ያስቻለው መሆኑን ይናገራል፡፡

ወጣቱ የፈጠራ ሥራዎቹን ተግባራዊ ወደ ማድረግ መግባቱን በመግለፅ፣ አሁን ላይ የቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት ነው። ለ18 ሠራተኞችም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ከ400 በላይ ተቋማት በሱ ድርጅት የበለፀጉ የሶፍትዌር ውጤቶች እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የሚገልጸው ወጣቱ፣ በሥራዎቹ 14 ሽልማቶች ማግኘት መቻሉን ያስረዳል፡፡ #ኢፕድ

https://t.me/TKVAH_NEWS123

TIKIVAH-ETH

17 Nov, 12:02


ፎቶ፦ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ " ድንች በረንዳ " እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ተነስቶ ነበር።

እሳቱ ከቀኑ 6:30 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ሳይዛመትና የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

ስለ አደጋው ምክንያት የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እሳቱ በተነሳበት ወቅት የእሳትና ከደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽንን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር። አንድ የኮሚሽኑ አካል በቦታው ሱቆች እየተቃጠሉ እንደነበር ገልጸዋል።

እኚሁ አካል በሥራ እየተጣደፉ ስለነበር ወደ በኃላ ዝርዝር ሁነቱን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል። በቃላቸው ከተገኙ ቀጣይ ተጨማሪ ማብራሪያ የምናቀርብ ይሆናል።

በቅርቡ መርካቶ " ሸማ ተራ " ከፍተኛ የእሳት አደጋ ደርሶ በርካታ ዜጎች ንብረታቸውን ማጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። የዚሁ የአደጋው ምክንያት እና አጠቃላይ የደረሰው ውድመት " ተመርምሮና ተጣርቶና ለህዝብ ይፋ ይደረጋል " ከተባለ ሳምንታት ቢቆይም እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

የፎቶ ባለቤት ፦ የአዲስ አበባ እሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

@tikvahethiopia