ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚 @kemetsehafalem Channel on Telegram

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

@kemetsehafalem


ሰኞ ኢትየጵያዬን በሙዚቃ🇪🇹🎤

ማክሰኞን ከዝነኞች አንደበት💡💡💡

ሀሙሰን ወግ ግጥም እና ልበወለድ

እሁድን ከየት ወዴት💡💡💡

#ለማንኛውም_አስተያየት

@Temesgentemuu

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚 (Amharic)

ከመፅሐፍት አለም is a Telegram channel dedicated to sharing knowledge and information from around the world. With a diverse range of topics covered, this channel aims to educate and enlighten its audience on various subjects. From science and technology to history and culture, ከመፅሐፍት አለም provides valuable content that sparks curiosity and engages the mind. Whether you're interested in learning about different cultures, exploring new ideas, or expanding your knowledge, this channel has something for everyone. Join ከመፅሐፍት አለም today and embark on a journey of discovery and learning from the comfort of your own device. Who knows what fascinating information you'll come across next? Stay informed, stay curious, and stay connected with ከመፅሐፍት አለም. #ለማንኛውም_አስተያየት @Temesgentemuu

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

03 May, 16:05


 የጅራፍ_ንቅሳት
(ኤፍሬም ስዩም)
=====//=====
ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑት ይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።

#ገጣሚ ኤፍሬም_ስዩም

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

23 Jan, 09:58


ጥቂቶች ብቻ የሚታደሉት የማስታወስ አቅም ተሰጥቶታል፣ የመረጃ ቋት ነው፣ ጠቅላላ እውቀት፣ በተለይ ስፖርት ፣ በጣም በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ፈረንጆቹ "Go-to person" የሚሉት አይነት ነው፣ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋቾች የግል ታራካቸውን ቢፈልጉ የሚሄዱት ገነነ ጋር ነው፣ የማያውቁትን ይነግራቸዋል፣ የረሱትን ያስታውሳቸዋል፣ የተጠራጠሩትም ያረጋግጥላቸዋል፣ He was
passionate for knowledge! ትልቅ ሰው አጥተናል፣

ነብስ ይማር ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

27 Sep, 19:11


..
አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከ አማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ። አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል። ልጅም አባቱን ማነው ሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል። አባትም በር ለይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነሱ ናቸው ይለዋል። ልጁም ይገረምና ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል። አባትም የኮረኮሩት ያህል ይስቅና፦
እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም ! ብሎ መለሰለት።
_______

#ደራሲው
( በዓሉ ግርማ )

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

31 Aug, 17:37


የተወዳጁ የአውሮፖ ሻምፒዮንሰሊግ የምድብ ድልድል

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

15 Aug, 04:54


የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ!
#ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤
#ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡

ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡

ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡

ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል
ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration
ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡

ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ' የበለጠ ዋጋ
አለው፡፡ ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣

➤መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡

➤ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡

የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡
ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት
መልካም ነበር!” በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ #በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡

ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን - 20 #ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i
(Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?)

የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤
የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል።

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

28 Jul, 03:48


#ፌስታሌን

የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያህ ይተምኑልሃል፤ ጫማ ከሌለህ እግርህ አይታይም፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩትን ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ... ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማል።

ድርሰት በረከት በላይነህ
መድረክ ትወና እያዩ ፈንገስ
_____________________________

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

14 Jul, 09:53


እንኳን ለ 47ተኛው የልደት ቀን አደረሰክ
ቴዳችን የኢትዮጵያ እንቁ
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

07 Jul, 09:45


ሰኔ 30 እና ትዝታችን ሰንቶቻችን በዚ ቀን 👇👇👇 #ተደባደብን #የፍቅር ደብዳቤ ሰጠን #በትምህርት ውጤታችን አዘንን ከየቱ ነበራቹ???
public poll

ተደባደብን🤼‍♂ – 32
👍👍👍👍👍👍👍 40%

የፍቅር ደብዳቤ ሰጠን💌 – 28
👍👍👍👍👍👍 35%

በትምህርት ውጤታችና አዘንን😔 – 21
👍👍👍👍👍 26%

👥 81 people voted so far.

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

07 Jul, 09:44


ሰኔ 30 እና ትዝታችን

ሰንቶቻችን በዚ ቀን
👇👇👇
#ተደባደብን🤼‍♂
#የፍቅር_ደብዳቤ_ሰጠን💌
#በትምህርት_ውጤታችን_አዘንን😔

ከየቱ ነበራቹ???

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

20 Jun, 10:03


አንዳንድ ሰው እየተበደለ ችሎ ሚኖረው
አፀፋውን መመለሰ አቅቶት ሳይሆን አሰተሳሰቡ ከበዳዩ ሰለሚሻል ነው!!

      ,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
   ••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

31 May, 08:46


"ህልም ማለት ያ በተኛህበት የምታየው አይደለም፣

...ለመተኛት ጊዜ ማይሰጥህ እንጂ"።

,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

07 May, 03:05


🌊 በመንገድ ሰታልፍ ያየከው ንፁ የውሃ ኩሬ ስትመለስ ደፍርሶ እና አፈር ተቀላቅሎበት ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ።

"አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ።

በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች መልሰን እናገኛቸዋለን።

,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

15 Apr, 01:51


 የጅራፍ_ንቅሳት
(ኤፍሬም ስዩም)
=====//=====
ከጀርባህ ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደድህ የዘላለም ምትራት
የፋሬስ የሳዶቅ ያለማመን ደባ
የጲላጦስ ግርፊያ የሄሮድስ ካባ
ከፊትህ የወጣው የደም ጎርፍ እና እንባ
ላንተ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራህ ነውና የመዳን አለኝታ
ጅራፍ እና ቡጢ ምራቅና ሃሞት
ለአይን ደስ የማይል የስቃይ ደምግባት
በደም የተረጩ ቅዱሳት አልባሳት
እኒህ ናቸው ውበት የጌታ ደምግባት
የመዳን አለኝታ የዘላለም ምትራት
ውዴን ያላያችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
ምራቅ ተቀብቷል
ቡጢ ተቀብሏል
ኃጢዓት ተሸክሟል
በቁንዳለው መሃል የደም ጎርፍ ይፈሳል
የፍቅር ንጉስ ነው የእሾህ አክሊል ደፍቷል
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ያልሰማችሁ
ፍቅሩን ልንገራችሁ
ዐይኑ ፍቅር ያለቅሳል
ጎኑ ደም ይረጫል
ፅህሙ ተነጭቷል
ልብሱ ሜዳ ወድቋል
በቃሉ ቅዱስ ነው ይቅርታን ይሰዋል
ከፍቅር ትከሻው የዓለም ደዌን አዝሏል
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለእሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰው ልጆች ድፍረት ክብሩን አይቀንስም
ስለሰው መድከሙም ኃይሉን አያወርድም
ስሙ እግዚአብሔር ነው
ስሙ ይቅርታ ነው
ስሙ መሀሪ ነው
የፈረሱን ብርታት ብቃቴ ነው የሚል
ብዛቱን ተማምኖ የሚታበይ ልዑል
በ'ሱ ስም ይወድቃል በስሙ ይጣላል
ስሙ ሁሉን ቻይ ነው ሁሉንም አድራጊ
ታላቁን የሚጥል ለታናሽ ተዋጊ
ውዴን ያላያችሁ
ድምጹን ላሰማችሁ
እኔ ልንገራችሁ
ፍቅሩን ላሳያችሁ
ከጀርባው ላይ ያለው የጅራፍ ንቅሳት
እኛን የመውደዱ የዘላለም ምትራት
ለርሱ ስቃይ ናቸው ለኛ ግን ደስታ
መከራው ነውና የመዳን አለኝታ
እናም ጌታችን ሆይ...
ያመኑት ይፅናኑ የወጉህም ይዩህ
በደም የተረጩ ልብሶችህን ለብሰህ
አሜን ጌታችን ሆይ ናልን ተመልሰህ።

#ገጣሚ ኤፍሬም_ስዩም

,,,,,🌹💚💛🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

05 Apr, 19:47


ቀጭን ፈታይ እመቤት

#Ethiopia | ከጂጂ ጋር ብሔራዊ ቲያትር ተቀጥረን እንሰራ ነበረ ከዚያም በጣም ጓደኛ ሆንን ጂጂ ወሬዋ በጣም ደስ ይላል።

አንድ ቀን ቦሌ ሮክ ኬክ ቤትተቀጣጠርን የዛን ዕለት ያልጠበኩት ነገር ሆነ።

ጂጂ ያገርልብስ ለብሳለች ቀይ ጥለት ከፊቱ በቀይ ጥልፍ የተጠለፈ ጫማዋ ደግሞ ከስክስ ነበረ።

ከዚያ ከታክሲ ስትወርድ በጣም ታምር ነበረ አይ ቁንጅና አይ ቁመና ወዲያው መኪናቸውን እያቆሙ ወንዶች

"ቆንጆ ዛሬ ቀኑ ምንድነው? ፋሲካ፣ ቅዱስ ዮሀንስ፣ ዳመራ?" እያሉ ይጠይቋት ነበረ።

እሷም ጠጋ ብላ

"የሀገሬን ሸማኔኑሮውን እንዲያሻሽል የሱን ጥበብ ለመልበስ ግዴታ አመትባል መጠበቅ የለብኝም!"
ትል ነበረ::

ምን አለቺኝ ትዕግስት ስለ ነጠላ መዝፈን አለብን አለችኝ በጣም ገረመኝ I said are you crazy? አልኳት

ግድ የለሽም መዝፈን አለብን ብላኝ ቀኑ ደረሰና እሷ ወደ አሜሪካን ሀገር ሄደች።

ሸማ ነጠላውን ለብሶ 2፣
አይበርዳቸው አይሞቃቸው፣
ሀገሩ ወይና ደጋ ነው፣
አቤት ደም ግባት ቁንጅና፣
አፈጣጠሩውብነት፣
ሀገሬ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ቀጭን ፈታይ እመቤት፣
በእምዬ ማሪያም በአዛኝቱ፣
ኑሪልኝ እናት አለሚቱ ፪
ኩታህን ያገሬ ሰው ፣
ጃኖህን ያገሬ ሰው ፣
ኩታህን ያገሬ ሰው ፣
ያምራል ኮርተህ ልበሰው፣
ብላ ዘፈነችልን

🙏

ድምፃዊት Tigist Bekele Mamo

©ኤፍሬም ስዩም

••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

21 Mar, 03:44


ትላንት በህይወትህ ያለፈውን መጥፎ ቀን ማጥፋትም
መቀየርም መሰረዝም አትችልም!!

የምትችለው መቀበል ብቻ
ነው:: ትላንትን አምነህ ተቀብለህ ዛሬን በደስታ ኑር፡፡

አስተውል
ዛሬ አዲስ ቀን ነው ከቀኑ ጋር አዲስ መሆን ያንተ ፋንታ ነው!!

የተወለወለ ቤት በጭቃ እግርህ ብትገባ ቤቱን ታበላሸዋለህ ልክ
እንደዛው በትላንት መጥፎ ሀሳብ ዛሬንም ከተቀበልከው
እንደዛው ነው! ❀
ዛሬ ★ አዲስ ★ቀን ★ ነው ★
እኔ ደስተኛ ነኝ
ትላንትን አምኜ ተቀብያለሁ✿
ዛሬን በደስታ እኖራለሁ ❀
ነገን በተስፋ እጠብቀዋለሁ
ሁሌም ሲነጋ ቀኑ አዲስ ነው ከቀኑ ጋር አዲስ መሆን የኛ ፋንታ
ነው!

ከትላንት መጥፎ ነገር እንፋታ ለዛሬ የታጨን ሙሽሮች ነንና!!!

••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

06 Mar, 08:16


ድሮ እስከመቼ ነው መኪና የማልገዛው እያልኩ በራይድ እሄድ ነበር ። አምና መቼ ነው ግን በራይድ የምሄደው እያልኩ በታክሲ እሄዳለሁ

አሁን ፦

ዋናው ጤና ነው እያልኩ በግሬ እየሄድኩ ነው 🤕

ነገሰ??

<<ዝቅ ለግዜው ከፍ በግዜው>> ዋናው ተሰፋ አለመቁረጥ ነው🕺

💚💚💚💛💛💛

,,,,,🌹💚🌹💛🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━
  ┊┊┊┊┊
  ┊┊┊┊
  ┊┊┊
┊┊💛
💚
💚

ከመፅሐፍት አለም 🌍📚🌏📚🌎📚

05 Mar, 14:18


ከዘመን ብሎኬት ከሕንጻ ድርድሩ
ከሕግ አልባም ሰዎች ከሚሽከረከሩ
ባለቀሚሷ ነች የተዋበች ኩሩ።

ግና

እሷም ብትሆን ትቅር መጽሐፍ ነው ፍቅር
በቀረች ሕይወቴም አንዳች አላማርር
የእረፍቴ ሥፍራ ድንጋይ ነው መቃብር!

💚💚💚💛💛💛

,,,,,🌹💚🌹💛🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
┏━━━━ "" ━━┓
💚@kemetsehafalem💚
💛@kemetsehafalem💛
@kemetsehafalem
━ "" ━
  ┊┊┊┊┊
  ┊┊┊┊
  ┊┊┊
┊┊💛
💚
💚

2,346

subscribers

663

photos

13

videos