በ አንድሮሜዳ ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ👀
ወደ ግቢ ለመግባት ያለው ዝግጅት እና ሽርጉድ እንዴት ነው❓🕺🕺🕺🕺💃💃💃።
የ በሶ ፡ ዳቦ ቆሎ ፡ ኩኪስ ፡ የለውዝ ቅቤ እና ሌሎችም የማቆያ ምግቦች ዝግጅት ተጧጡፏል አሉ።😋😋😋🙈🙈🙈
📚 የመጀመሪያውን ሴሚስተር አሪፍ ውጤት ለመስራትስ ምን ያህል ዝግጅት አድርጋችሗል🎃
😋 4 ነጥብ ማምጣት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ❓ 1000% እርግጠኛ ሁኜ የምነግራችሁ በብልጠት ካነበባችሁ 4 ነጥብ የማታመጡበት ምንም ምክንያት የለም🤗።
📚 ግቢ ላይ ፈተና በተጋነነ መልኩ አያከብዱባችሁም🤠። ስለዚህ በብልጠት ፅንሰ ሀሳቡን እየተረዳችሁት ካነበባችሁ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ። ውጤታችሁን ዝቅ የሚያደርጉባችሁ በ assignment ሊሆን ይችላል🫤።
📚 ስለዚህ assignment ስትሰሩ አሪፍ ፅሁፍ ያለው ተማሪ ነው መፃፍ ያለበት🤩። cover page ጁን አሪፍ አድርጋችሁ አሳምሩት ። በቃ የግቢ መምህሮች አሳይመንቱ አሸብርቆ ደምቆ ሲያዩት ማርክ ያሸክሟችሗል።
📚 ተወዳጆች ሆይ ስለዚህ ዝቅተኛ 3.5 እንዲሁም ከፍተኛ 4 ከእናንተ እጠብቃለሁ።
📚 እየውላችሁ ስሙኝማ ፡ ኸሯ አንተ ምን ሁነሀል ፍላጎትህን መኖር ትፈልጋለህ ❓፡ ኸረግ አንቺሽ ክህሎትሽን ማበልፀግ ትፈልጊያለሽ😊❓ የልጅነታችሁን ህልም መማር ትፈልጋላችሁ❓ 12 አመት የተማርከው የምትፈልገውን ዲፓርትመንት ለመማር ነው አይደል🤓❓ የወገንሽን ስቃይ ለማስታገስ ከ ለጋ እድሜሽ ጀምሮ ዶክተር መሆን ነው ኣ የምትፈልጊው❓በፍትህ እጦት የጎበጠውን ህዝብ ቀና ለማድረግ ካለሽ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ዳኛ መሆን ነው ኣ የምትፈልጊው❓ ሀገርህን ለማተራመስ( ማለቴ ለመምራት😤) ፓለቲካል ሳይንስ ነው ኣ ማጥናት የምትፈልገው❓ ሀገርህ በቴክሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ እምርታ እንዲታስመዘግብ ኢንጂነሪንግ ነው ኣ መማር የምትፈልገው❓ ኤኮናሚስት❓ ማናጀር❓ ሳይካትሪስት❓ወዘተ መሆን ትፈልጋላችሁ❓
📚 ስለዚህ የነዚህ ህልማችሁ እና ፍላጎታችሁ መንገድ ጠራጊ የመጀመሪያው ሴሚስተር ነው። ዳይ ወደ ስራ‼️
በ ስነ - ልቦና ስ ዝግጁ ናችሁ❓
አዎ በስነ ልቦና ዝግጁ መሆን አለባችሁ።🥺🥺 ምክንያቱም
1ኛ) ከቤተሰብ ቁጥጥር እና ተፅዕኖ ውጭ ናችሁ። ራሳችሁን የምትመሩት ና የምታስተዳድሩት ራሳችሁ ብቻ ናችሁ። ስለዚህ ይኸን ነፃነት እንዴት በአግባቡ እንጠቀምበት🤔? ቅድሚያ ትኩረት መስጠት ያለባችሁ ለ ትምህርታችሁ ና ለአላማችሁ ነው።
2ኛ) የጓደኛ ተፅዕኖ( peer influence) ጓደኛን ለመምሰል ብሎ ፡ ለመቀላቀል ተብሎ ፡ ወደ አልባሌ ሱስ መግባት😱
ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ ነን ፡ ነፃነት አገኘን ብላችሁ
📌 የማታነቡ ከሆነ
📌 ትምህርታችሁን በአግባቡ የማትከታተሉ ከሆነ
📌Over( ጭፈራ ቤት) መውጣት የምታበዙ ከሆነ
📌 ቺክ የምታሳድዱ ከሆነ ወይም ወንድ የምታሳድጂ ከሆንሽ 🙈
📌 አልባሌ ሱስ ውስጥ የምትዘፈቁ ከሆነ
📌 እና ሌሎችም መጥፎ ወይም ትምህርታችሁን የሚያስተጓጉሉ ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ
ጊዜያችሁን አባክናችሁ☹️ ፡ ቤተሰብን ላልተገባ ወጪ ና ኪሳራ ዳርጋችሁ😣 ፡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ሻንጣችሁን ጠቅልላችሁ ወደ መጣችሁበት ትመለሳላችሁ🙅♂🤷♀።
ግቢ ላይ እየቀለድኩ እያሾፍኩ እማራለሁ ማለት ዘበት ነው ምክንያቱም ኩረጃ በፍፁም የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ግቢ ገብታችሁ
📌 ለማንበብ
📌 ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም
📌 ራሳችሁን በአግባቡ ለመምራት
📌 አላማችሁን ለማሳካት
📌 የሚደርስባችሁን ጫና ለመቋቋም
ራሳችሁን በ ስነ ልቦና በደንብ ማዘጋጀት ይጠበቅባችሗል።
ይኸን ስንል ግቢ ገብታችሁ አትዝናኑ ማለት አይደለም። ኸረ ፈታ በሉ please enjoy ። ግን ትምህርታችሁን በማይጋፋ መልኩ ፡ እናንተን ለመጥፎ ሱስ በማይዳርግ መልኩ።pls አደራ🙏
ሌላኛው አንገብጋቢ ጉዳይ ደግም የምትፈልጉትን department ማግኘት ነው።
😌 Department ስትመርጡ
📌 የእናንተን ፍላጉት ፡ የእናንተን skill (ክህሎት) ፡ ዝንባሌ ፡ አቅም መሰረት ያደረገ መሆን አለበት።
📌 በቤተሰብ ተፅዕኖ ፡ በጓደኛ ተፅዕኖ ወዘተ መሆን የለበትም።
እዚጋ ብዙዎች ጋ የሚስተዋለው ነገር ብዙ ብር ክፍያ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ ፡ ቶሎ ስራ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ አንዳንድ ተማሪዎች ያለ ዝንባሌያቸው ዲፓርትመንት ሲመርጡ ይስተዋላሉ። ስለዚህ😳
📌 ፍላጎታችሁን ፡ የትምህርት ክህሎታችሁን ፡ ጫናዎችን የመቋቋም ዝግጁነታችሁን ና አቅማችሁን መሰረት አድርጋችሁ ብትሞሉ አሪፍ ነው።😍
የምፈልገውን Department እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
📚 ጥሩ ውጤት ከሰራችሁ የምትፈልጉት ዲፓርትመንት መግባት ትችላላችሁ😉።
ጥሩ ውጤት እንዴት እንስራ?
1ኛ) ግቢ ገብታችሁ የምትወስዱት የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት እጅግ በጣም በጣም በጣም ጠቃሚ ነው🤓። 50% ከመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ። የመጀመሪያውን ሴሚስተር ቅጥቅጥ አርጋችሁ ማንበብ ነው።✌️
እንደመታደል ሁኖ የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸው ኮርሶች የተወሰኑት 11 እና 12 የተማራችሗቸው ናቸው። ስለዚህ ያላችሁን አጋዥ መፅሀፍ ፡ PDFs እና የተለያዩ ማቴሪያሎችን እንዳትጥሏቸው፡ ወደ ግቢ ይዛችሁት ሒዱ😘..
በቀጣይ ለ ሀይስኩል ተማሪዎች አሪፍ አሪፍ tip እና ምርጥ ውጤት የምታመጡበትን መንገድ እነግራችኋለው(እኛን ለምን ተውከን እንዳትሉኝ ውዶቼ😅😘...I'll try ሁላቹም beast እንድትሆኑ🫶)