ለትውልድ | LETIWULID 🦋 @letiwulid Channel on Telegram

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

@letiwulid


🔰ንቃት ለትውልድ🔰
ቤተሰብ ይሁኑ! 🙏

ለትውልድ | LETIWULID 🦋 (Amharic)

ይቡጡላል! በአንድ በላይ እንዴት ነበር? እናምራለን! ታስተዳዳሪ ስራ ለትውልድ በእኚህ ታላቅ መልእኽት! 'ለትውልድ | LETIWULID' ከተደረገ በዚህ ታስተዋወቂዎችን እና አዳምጠን እንዲሆን ለትውልድ ድምጽን ይዘን ነው። ለትውልድ የሚለው ጥያቄ በአንድ አነስተኛ እምነት ውስጥ ስለ ነበርን? በተለዋዋጩ እና ምክንያቶችዎን በተመሳሳይ ህጎች ‘ለትውልድ | LETIWULID’ ከታዘዘው አዝናኝ እርምጃዎችን አንዴት አልተወገዘም! በአብዛኞችና ሰነዶች ከፍተኛ ትኩረት አያሌዎች ተናጋሪን ለትውልድ ነን። ለትውልድ የሚለው ክትታቸው በአንድ ጊዜ መግብያት ይችላል። ለትውልድ ራእይቱ ውስጥ ለካርታዎች በሚሳቡ ተነች! በመለያ ለትውልድ አገልግሎቶችን ስለመከታታቸው የተነሳ እርምጃዎን እንወሯለን።

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

13 Sep, 03:50


ማንንም አይጠብቅም!
:
እርሱ ፍተሃዊ ዳኛ ነው። ለጥቂቶች አዳልቶ የሚዘገይ፣ በጥቂቶችም ጨክኖ የሚፈጥን አይደለም። ጊዜ ሳያዳላ ይፈርዳል። በአግባቡ የተጠቀመውን ይሸልማል፣ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ ያሳለፈውንም በሚገባ ይቀጣል። በጊዜ አለንጋ ከመገረፍ ራሳችሁን ጠብቁ። ሳቁ፣ ተጫወቱ፣ አሹፉ፣ ቀልዱ ነገር ግን በፍፁም በውድ ጊዜያችሁ አታሹፉ፣ በፍፁም ትልቁን ስጦታችሁን አታዋርዱት። ራሳቸውን የገዙ፣ ስሜታቸውን የተቆጣጠሩ፣ ስራቸውን በአግባቡ የሰሩ፣ ሁሌም ከዛሬያቸው የሚያተርፉ ሰዎች ጊዜ ጌታ ያደርጋቸዋል፣ ክብር ላይ ክብርን ፀጋ ላይም ፀጋን ይጨምርላቸዋል። በምትኩ በህይወታቸው ያረፈዱትን፣ ጊዜያቸውን በስንፍና የጨረሱትን፣ ሲበዛ ግዴለሽና ደንታቢስ ይሆኑትን፣ አቅማቸውን በዋዛፈዛዛ ያባከኑትን የስራቸውን ይከፍላቸዋል፣ ባይፈልጉትም በግድ ይቀጣቸዋል፣ እንደተጫወቱበት በተራው ይጫወትባቸዋል፣ አንገት ያስደፋቸዋል፣ አሸማቆ ወደ ኋላ ያስቀራቸዋል።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@mikre_aimro

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

21 Aug, 06:03


ቁሳዊ ስኬት
:
ግብህ
ቁሳዊ ስኬት አይደለም፤ ጥቅም አልባ ዝና አይደለም፤ ለማህበረሰቡ የማይጠቅም፣ አገልግሎት የሌለው ንብረት አይደለም። የፈለከውን ገንዘብ ማግኘትህ ስኬታማ አያደርግህም፤ የፈለከውን ገንዘብ አለማግኘትህም ስኬት አልባ አያደርግህም። ሳይኖርህ ለሰው መኖር፣ ለሰዎች መትረፍ ትችላለህ። በተቃራኒው እያለህ ከእራስህ በላይ ላትኖር ትችላለህ። ያለውንና የሌለውን የሚለየው አንደኛው የስኬት መለኪያ ለሰዎች መኖር፣ ሌሎችን መርዳት፣ ለወገን መድረስ መቻል ነው። መኖርህ፣ ንብረት ማፍራትህ፣ ሃብት ማካበትህ ለውጥ እንድታመጣ ካላደረገህ ምንም ትርጉም የለውም። ቁስ ቢበዛ ነገ ወይ እርሱ ይጠፋል ወይም አንተ ጥለሀው ትሔዳለህ።
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@mikreaimro

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

20 Aug, 17:43


THE SCIENCE OF GETTING RICH
ወይም የሀብት ሳይንስ በሚል የተተረጎመው መጽሐፍ 5 አንኳር ሀሳቦች፦

1. ሳይንሱን ካወቅክ ሀብታም መሆን ትችላለህ

ሀብታም የመሆን ሳይንስ አለ፤ እሱም እንደ አልጄብራ ወይም የሂሳብ ዓይነት ትክክለኛ ሳይንስ ነው። ሀብትን የማግኘት ሂደትን የሚቆጣጠሩ አንዳንድ ህጎች አሉ፤ እና ማንኛውም ሰው እነዚህን ህጎች  ከተማረና ለህጎቹ ከታዘዘ፣ ያ ሰው በእርግጠኝነት ሀብታም ይሆናል።

2. ለየት ባለ መንገድ መስራት አለብህ

ሀብታም የሆኑ ሰዎችን ስናጠና ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ችሎታ ወይም ተሰጥኦ የሌላቸው በሁሉም ረገድ አማካኝ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህም እነዚህ ሰዎች ሀብታም የሆኑት ሌሎች ሰዎች የሌላቸው ተሰጥኦና ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን፣ ነገሮችን በሆነ ለየት ባለ መንገድ በመስራታቸው እንደሆነ ያሳየናል።

3. ካፒታል የለኝም አትበል ችግሩ ካፒታል አይደለም

የመነሻ ካፒታል ማጣት ማንንም ሀብታም ከመሆን አያግድም፤  መነሻ ካፒታል ሲኖርህ ግን ለማደግ ይበልጥ ቀላል እና ፈጣን ይሆንልሃል፤ ነገር ግን መነሻ ካፒታል ያለው ሰው ቀድሞውኑ ሀብታም ስለሆነ እንዴት ሀብታም መሆን እንዳለበት ማሰብ አያስፈልገውም።  ነገር ግን ምንም ያህል ድሃ ብትሆን ነገሮችን በሆነ መንገድ መሥራት ከጀመርክ ሀብታምና ካፒታል ያለህ መሆን ትጀምራለህ።

4. አሁንም እድሎች አሉ

ማእበሉን በመታገል ፈንታ ከማእበሉ ጋር አብሮ ለሚሄድ ሰው ብዙ እድሎች አሉ፡፡ ስለሆነም የፋብሪካ ሰራተኞች እንደ ግለሰብም፣ እንደ ቡድንም እድልን አልተነፈጉም፡፡ ሰራተኞች በቀጣሪዎቻቸው በዝቅተኛ ደረጃ ሆነው እንዲቀሩ ሊደረጉ አይችሉም፡፡ እንደ መደብ አሁን ያሉበትን ደረጃ ሊይዙ የቻሉት ነገሮችን በተወሰነ መንገድ ስለማያደርጉ ብቻ ነው፡፡

5. የተትረፈረፈ ሀብት አሁንም አለ

ማንም ሰው በድህነት ውስጥ የሚኖረው ያለው የሀብት አቅርቦት የተወሰነ ስለሆነ አይደለም፡፡ ለሁሉም ከሚበቃው በላይ የሀብት አቅርቦት አለ፡፡ አንዲት ሀገር በከፍተኛ የእርሻ ልማት የምታመርተው ጥጥ፣ ሱፍ፣ ሀር እና በፍታ እያንዳንዱን የዓለም ህዝብ ሰሎሞን ከክብሩ ጋር ከለበሰው ይልቅ እንዲለብስ የሚያስችል ነው፡፡ ሁሉንም በቅንጦት መመገብም ያስችላል፡፡


#የሀብት_ሳይንስ_መጽሐፍ
https://t.me/Elodia_G

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

06 Jul, 17:08


እራሳችሁን አስቀድሙ!

መጀመሪያ እራሳችሁን አድኑ፣ አስቀድማችሁ በደህንነታችሁ እርግጠኛ ሁኑ፣ ባላችሁበት  ሁኔታ ሰላም ይሰማችሁ። ትናንታችሁ ጠባሳ የጣለባችሁ ሳያንስ ዛሬም እናንተው በፍቃዳችሁ ተጨማሪ ጠባሳ እራሳችሁ ላይ አትጣሉ። ከህመማችሁ ለመንፃት መተው ያለባችሁን ነገር ተዉ፤ ስለወደፊት ህይወታችሁ የሚገዳችሁ ከሆነ እስራታችሁን ፍቱ፣ በእርግጥም ህይወትን በሙላት መኖር ካሻችሁ የይቅርታ ልብ ይኑራችሁ። ሸክማችሁን አራግፉ፣ ለደህንነታችሁ ዋስተና አስቀምጡ፣ በምርጫችሁ ወደፊትን ተመልከቱ፣ ኋላ ከቀረውና ከተበላሸው ይልቅ የሚመጣውና ማስተካከል የምትችሉት ጉዳይ ላይ አተኩሩ።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

27 Jun, 18:20


ሳትጀምር አትሸነፍ!
:
እግርህን ሳታነሳ አትሰበር፤ ባልሆነው አትሸበር፤ ባልተከሰተው አትታሰር፤ ገና ለገና ሊመጣ ይችላል በተባለ የወረደ መላምት ትልቁን ሃሳብህን አትቅበረው። ውድቀትም ይግጠምህ ስኬት ሞክሮ ማየትን የመሰለ ነገር የለም። ምንም ነገር ልታልም ትችላለህ መሳካቱን ልታውቅ የምትችለው ግን ስታደርገውና ስታደርገው ብቻ ነው። ምንም ነገር ሊሆንም ላይሆንም የሚችልበት መንገድ እኩል ነው። የህይወትህ ሚዛን እምነትና አመለካከትህ ነው። እንዲሳካ የምትፈልገው ነገር ቢኖር በፍረሃት ውስጥም ሆነህ ማድረጉ ካለማድረግ የተሻለ ነው። ድፍረት፣ እድገት፣ መነቃቃት፣ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድርጊት ውስጥ ሆነህ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው። የበይ ተመልካች የምግቡን ጠዓም ሊያውቅ አይችልም፤ በፍረሃት ታስሮ፣ በስጋት ውስጥ ወድቆ ሳይሞክር የቀረም ሊገጥመው የሚችለውን መልካም ነገር ሊያውቅ አይችልም።
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

05 Jun, 19:28


የተፃፈ ነገር የለም!
:
አንዳች አስቀድሞ የተወሰነልህና አንተ ምድር ላይ መጥተህ በተግባር የምትገልፀው ነገር ከቶ የለም። ድርሰት ሲኖር ተዋንያን ይኖራሉ። በዚህም ሁኔታ የሰው ልጅ የተፃፈ ወይም የተደረሰ ህይወት ካለው እኛ እየኖርን ሳይሆን እየተወንን ነው ማለት ነው። የህይወት አመክንዮ ግን ፈፅሞ ከዚህ የተለየ ነው። ብዙ ጊዜ "የተፃፈልኝን ነው የምኖረው፣ ይሔ የአርባ ቀን እድሌ ነው ምንም ማድረግ አልችልም፣ ተፈርዶብኛል።" እያሉ የሆነባቸውን ነገር ሁሉ ፈጣሪያቸው እንዳመጣባቸው የሚጠቅሱ ሰዎች ከእያንዳንዱ ምርጫቸው በስተጀርባ ለሚመጣው ውጤት ሃላፊነት ለመውሰድ ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ፈጣሪ የትኛውንም የሰውን ልጅ ሰነፍ አድርጎ አልፈጠረውም፣ ሰነፍ እንዲሆንም አልፈረደበትም፣ አምላክ ማንም ወድቆ እንዲቀር አይፈልግም። ሁላችንም ነፃ ፍቃድ (Free will) አለን። ያሰኘንን ህይወት ከመኖር በላይ የምንፈልገውን ነገር የማምለኩ ነፃነትም ጭምር በፈጣሪያችን ተሰጥቶናል። ጣዖት አቁመው የሚሰግዱለት ሰዎችም እየኖሩ ነው፣ ፈጣሪዬ አምላኬ ብለው የሚያመልኩት ሰዎችም እኩል እየበሉና እየጠጡ እየኖሩ ነው። ፈጣሪ ፈራጅ ቢሆንና ነፃነትን ባይሰጥ መጀመሪያ እንዲጠፉ የሚፈርድባቸው እነዛ አምላክነቱን ክደው ለጣዖት የሚሰግዱትን ነበር።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

01 Jun, 06:27


ኑሮህን ኑር!

መስታወት ፊት ቆመህ የእራስህን ገፅ መመልከት ሲኖርብህ ካንተ እንደሚሻሉ የምታስባቸውን ሰዎች ህይወት እየተመለከትክ እራስህን የማይረባ ቅዠት ውስጥ አትክተት። ምንም እንኳን ማህበራዊ ህይወት አስፈላጊ ቢሆንም ማህበራዊ ቅናትና ፉክክር ግን አላስፈላጊ ነገር ነው። ብዙ ሰው ጠልፎ የሚጥለውን እንቅፋት ከፊቱ አስቀምጦ በፍጥነት ይሮጣል፣ የውድቀቱ ምክንያትም እራሱ ይሆናል። የውድቀቱ ጠባሳ ይኖራል ሲሽቀዳደማቸው የነበሩ ሰዎች ግን የሆነ ጊዜ አይኖሩም። አንድ ሰሞን የእርሱ ከእንተና በልጦ መገኘት ከምንም በላይ ያሳስበው ነበር፣ የሆነ ጊዜ የእርሱ አለማደግና የጓደኛው ማደግ ያብከነክነው ነበር፣ የሆነ ሰሞን ከሚያገኛቸው ሰዎች ሁሉ አንሶ መገኘቱ እንቅልፍ ይነሳው ነበር። በስተመጨረሻ ግን እነዚህ ሁሉ ሰዎች አጠገቡ አይኖሩም። ብቻውን የሚቀረው እርሱና እርሱ ብቻ ነው። ጅማሬህ ከማንም ጋር ቢሆንም ፍፃሜህ ግን ከእራስህ ጋር ብቻ ነው፣ ማንንም አይተህ አዲስ ነገር ብተጀምር የመጨረሻው ግብህ ብቻህን ውጤታማ መሆን ነው፣ ማንንም እንዲያግዝህ ብትጠይቅ ዋናውን ስራ የምትሰራው እራስህ ነህ።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

26 May, 20:18


ፍቅርን ያዘው!
:
ፈታኝ አጣብቂኝ ውስጥ ብትገባም፣ አለመግባባት፣ አለመረዳዳት ላሰብከው ግንኙነት መሰናክል ቢሆንብህም፣ ቅድሚያ መስጠት የሚገባህ ነገር ግን ያላስቀደምከው፣ ትኩረትህን የሚፈልግ ነገጰር ግን ያልሰጠሀው ነገር ቢኖርም የፍቅርን ጉዳይ በፍቅር መንገድ ለመፍታት ቅድሚያ ስጥ። የቃላት ጋጋታ፣ ጣፋጭ ንግግር፣ ጊዜያዊ ማሽቃበጥ ለፍቅር ጥላው ቢሆን እንጂ መገለጫው ሊሆን አይችልም። ፍቅርን መኖር ካለብህ በትክክለኛው፣ በአስደሳቹ፣ ስሜት በሚሰጠውና በአምላክ በተባረከው ፍቅር ውስጥ እራስህን አስገባ። ፍቅር ብረሃን ነው። የለም ወይስ አለ የሚል ሰጣገባ ውስጥ ከምትገባ ቢኖር ምን ይጠቅመኛል? ምን አተርፋለሁ? በህይወቴ ብተገብረው፣ ብኖረው ምን አገኛለሁ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ለእራስህ የምትሰጠው ክብርና ፍቅር ከሌሎች ከሚሰጥህ ጋር የተቆራኘ መሆን አይጠበቅበትም። ፍቅር የመሆንህ ዋነኛው ምክንያት እራስህን መቀበል መቻልህና ማንነትህን መውደድህ ነው።
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

02 Mar, 06:31


ድል አለን!
:
ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከትሽ እስከ ትልቅ ሁላችን እንደክብራችን ሁላችን እንደ ኢትዮጲያዊነታችን ድል አለን። ድል ሲባል አንድ ሰሞን የሚነሳ በሌላ ጊዜ የሚወድቅ አይደለም፣ ድል ሲባል በቁስ ወይም በገንዘብ የሚገለፅ ድል አይደለም ድላችን የማንነት ነው፣ ድላችን የእኛነት ነው፣ ድላችን የኢትዮጲያዊነት ብሎም የጥቁር ህዝቦች ጌጥ ነው። ማንም ብቻውን ተዋግቶ ያላሸነፈው፣ ማንም ልብቻው ተጋፍጦ ያላለፈው፣ ማንም ከኢትዮጵያዊነት በላይ ዘሩን ያላስቀደመበት፣ ሁሉም በኢትዮጵያውያዊነቱ እራሱን የሰጠበት፣ በህብረት የተፋለመበት፣ በሃሳብ በአላማ አንድ ሆኖ ተባብሮ ድል ያደረገበት፣ ወራሪውን ሃይል ያሳፈረበት ዘመን የማይሽረው፣ ታሪክ የማይረሳው ታላቅ ድል አለን። እኛ ዛሬ እኛን ስለመሆናችን፣ እያንዳንዳችን የሚያኮራንን ማንነት ስለመያዛችን፣ በየራሳችን ቋንቋ፣ በየራሳችን ባህል ስለመታወቃችን፣ ውስጣችን በጀብድ ልባችንም በንቃት ስለመሞላቱ ዋናው ምክንያት የአያት ቅድመ አያቶቻችን አርበኝነት ነው።


እንኳን ለ128ኛ የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

25 Feb, 15:46


የምትሰጠው አትጣ!

የሚሰስት ትርፍ የለውም፣ መስጠት የማይወድ በረከት የለውም፤ እርካታ የለውም። መኖር በመስጠት ውስጥ ነው። ስትሰጥ የምታገኘውን ስጦታ፣ የሚሰማህን ስሜት ምንም ብታደርግ አታገኘውም፣ ምንም ብትፈፅም ሊሰማህ አይችልም። የህይወት ትርጉም የአምላክን ፀጋ በእኛ በኩል ለሰዎች ማሻገር ነው። ሁሉን የሚሰጥ ደግ አምላክ፣ ቸር ፈጣሪ ነው። ባህሪው መስጠት ነው፤ ንፉግነት የለበትም። የእርሱን ባህሪ ለሚከተለው ሌላ ይጨምርለታል፤ ለማይሰጠው ለንፉጉም የሚገባውን ባይከለክለውም እንኳን በመስጠት የሚያገኘውን የተትረፈረፈ በረከት ግን ያሳጣዋል። ለጋስ ለመሆን ከሰፊ አዛኝ ልብ ውጪ የሚያስፈልግ ነገር የለም።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

15 Jan, 18:34


God said, "love your enemy" and I obeyed & loved myself.

እግዚአብሔርም አለ፦ "ጠላትህን ውደድ" እኔም አከበርኩትና እራሴን ወደድኩ።


- Khalil Gibran

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

10 Jan, 19:03


ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-

“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምሩና ከዚያም ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚል እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው እሳቤ ከተንሻራተቱ በኋላ በመጨረሻ “አልችል” በማለት ይደመድሙታል፡፡

እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!


❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

09 Jan, 16:56


🍸ብርጭቆ ተጋበዝ!

በመጀመሪያ ባዶ ብርጭቆን ተመልከት። ከዚያም የተወሰነ ያህል ውሃ ጨምርበት። ከዚያም አፍስሰው... ተመልሶ ባዶ ይቀራል አይደል?

አሁን ራስህን ተመልከት

🥃 አሁንም ብርጭቆውን ግማሽ ያህል ውሃ አድርግበት። ከዚያም የተወሰነ ያህል አፍስሰው። ድጋሜም የተወሰነ ያህል አፍስስ... አሁንም እንደዛው አፍስሰው… ብርጭቆው ባዶ መቅረቱ አይቀርም አይደል?

እንዲህ ብታደርግስ?

🥃 ብርጭቆውን ሙሉ ውሃ ሙላው። ከዚያም የሞላው ላይ ውሃ መጨመርህን ቀጥል። ብርጭቆው ሲጎድል ይታይሃል? በፍጹም ሊጎደል አይችልም። እንዲያውም ይፈሰዋል አይደል?

እስኪ ምን ተረዳህ? ጊዜ ውሰድና አሰብ አድርግ።

🥃 በትክክል! ራስህን ምን ያህል ትወዳለህ? ራስህን ሳትወድ፣ ራስህን ሳታከብር፣ ለራስህ ሳይኖርህ በፊት ለሰዎች የምትሰጠው ማንኛውም ገንዘብ፣ ክብር፣ ፍቅር አንተን ባዶ ያስቀርሃል። ባዶነትህን ደሞ የሚወድልህ አይኖርም!
ስለዚህ?

☑️ አዎ በቅድሚያ ሙሉ ለሙሉ ራስህን ውደድ፣ ለራስህ ክብር ይኑርህ፣ የራስህ ነገር ይኑርህ። ከዚያ ለሌሎች ሞልተህ መፍሰስ ትጀምራለህ። ቅድሚያ ለራስህ ስጥ! አይዞህ ይህ ኃጢአት ወይም በሰዎች የመከፋት ዝንባሌ አይደለም። ራስህን ከልብ መውደድ ስትችል ሌሎችንም ከልብህ መውደድ ይቻልሃል፤ ራስህን የእውነት ስታከብር... የራስህ ነገር ሲኖርህ ሌሎችም እንዲኖራቸው የምትመች ትሆናለህ። አንተ እንደ ብርጭቆው ነህ ወይ ሞልተህ መፍሰስ አሊያም ባዶ ሆነህ መቅረት ያንተው ናቸው።

/በራስ መተመመን መጽሐፍ/
©Teklu Tilahun
THANK YOU FOR READING
ELODIA READING📚📖
ኤሎድያ ንባብ📚📖

#share and join for more👍

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

08 Jan, 18:40


ማንም በሌለበት!
:
በዛ በጨለማ
ማንም በሌለበት፣ ጠያቂ በማታገኝበት፣ አይዞህ ባይ አበርታች፣ በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የሚደግፍህ በሌለህ ሰዓት ምን እያደረክ ነበር? ስለሆነብህ እያማረርክ ወይስ ምሬትህን ለመቀየር ጠንክረህ እየሰራህ? ብቸኝነትህን እየረገምከው ወይስ እራስህን ለመገንባት እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀምከው? እድለኛ እንዳልሆንክ እያሰብክ ወይስ ሁኔታውን ለመቀየር እየተፋለምክ? ብቻህን ስትሆን የሚኖርህ ማንነት ያንተ ትክክለኛው ማንነት ነው። አንተና ፈጣሪ ብቻ የምታውቁት የግል ሚስጥርህ ይኖራል። በገባህ ልክ እለት እለት ለብቻህ የምትፋለምለት ሃሳብ ይኖርሃል። "ብቻዬን ነኝ፣ ሰው የለኝም፣ የሚያግዘኝ አላገኘውም፣ የማደርገው ነገር በማንም ተቀባይነት አላገኘው፣ ማንም አላመነበትም።" ብለህ አታቆመውም።
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

01 Jan, 19:38


እራስህን ምረጥ!

ብቻህን ብትቀርም፣ ብትገፋም፣ ስምህ ቢጠፋም፣ ቦታ ባይሰጥህም
እራስህን ምረጥ፣ ለራስህ ታመን፣ ለራስህ ኑር፣ እራስህንም ከልብህ ውደደው። አንተ ያልመረጥከውን ማንነት ማንም አይመርጥልህም፣ አንተ ያልወደድከውን ስብዕናህን ማንም አይወድልህም፣ አንተ የማታከብረውን ሰውነት ማንም አያከብረውም። ያለህ ነገር በሙሉ በእግዚአብሔር ተመርጦልህ እንጂ አንተ መርጠሀው አይደለም፤ የተሰጠህ በሙሉ ያንተ በመሆን እንደምታተርፍ ስለታወቀ እንጂ ቢጎዳህ በፈጣም አይሰጥህም ነበር። ብቸኝነትህ ዋናው የስኬትህ ቁልፍ ነው። ብቸኝነት ነፃነት አለው፣ ከብዙ እስራት ነፃ የሚያወጣ ነፃንተ፣ ገደብህን አልፈህ እንድትሔድ የሚያግዝ ነፃነት፣ ህልምህን እንድትኖር፣ ደስታህን እንድታጣጥም፣ ለራስህ ጊዜ እንዲኖርህ የሚያደርግ ነፃነት አለው።
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

29 Dec, 19:18


የመቀላቀል አባዜህን አስተካል!
:
ትኩረትህን አሰልጥን፣ በመሃል የሚመጡ ሃሳቦችን ሞግታቸው፣ አዕምሮህን ከሚያናጋ አጫጭር ነገር እራስህን ቆጥብ፣ በአንዴ አንድ ነገር ብቻ የመስራት ልምድ አዳብር። ከእያንዳንዱ ተግባር ጀርባ ውስጣዊ እርካታና ጠዓም አለ፣ ከእያንዳንዱ እቅድና ሃሳብ ጀርባ ውጤት አለ። በአንድ ጊዜ ሃሳብህ ላይ ብቻ ካላተኮርክ ተግባሩ ከንቱ ምኞት ነው፤ ተግባሩን በሙሉ ልብህ ካልሰራሀው፣ ደጋግመህ ካላረምከው፣ ተገቢውን ጊዜ ካልሰጠሀው የፈለከውን ውጤት በጠበከው ጥራት የማግኘት እድልህ እጅጉን አናሳ ነው። ከመቀላቀል በላይ ለፈለከው ነገር እራስህን ስጥ፣ ከማምታትት በላይ በአንዴ አንድ ነገር ላይ ብቻ አተኩር። የልፋትህን ውጤት፣ የድካምህን ፍሬም በፈለከው ጥራትና መጠን ልክ አግኘው።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

23 Dec, 18:25


ልብሽ ይማርካል!
:
መንፈስሽ ይስባል፤ ቀልብን ይሰርቃል፤ ውስጥን ያረጋጋል፤ መንፈስን ያድሳል። ነፍስሽ እንቁ ነች፤ ማንነትሽ ግሩም ነው፤ ስብዕናሽ ድንቅ ነው። በስብራት ውስጥ የተሰራ፣ ፈተናዎችን ያሸነፈ፣ እራሱን የመሰለ፣ እራሱን የሆነ ነው። መልካም ውብ ሴት መሆን፣ ማራኪ የተከበረች አክባሪ ሴት መሆን ክፍያው ብዙ አይደለም፤ ቅንነት፣ መልካምነት፣ ደግ አሳቢነትና በእራስ መተማመን ብቻ ነው። መንገስ ከፈለግሽ በቁመናሽ ሳይሆን በማንነትሽ ንገሺ፤ መወደድ ከፈለግሽ በገፅታሽ ሳይሆን በአንቺነትሽ ተወደጂ፤ እንዲቀበሉሽ፣ እንዲደመሙብሽ፣ እንዲደነቁብሽ ከፈለግሽ በተክለሰውነትሽ ሳይሆን በስብዕናሽ አስደምሚ፣ በቅንነትሽ አስደንቂ፣ በሰውነትሽ አስገርሚ።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

20 Dec, 19:35


እራሳችሁን አስቀድሙ!
:
መጀመሪያ እራሳችሁን አድኑ፣ አስቀድማችሁ በደህንነታችሁ እርግጠኛ ሁኑ፣ ባላችሁበት  ሁኔታ ሰላም ይሰማችሁ። ትናንታችሁ ጠባሳ የጣለባችሁ ሳያንስ ዛሬም እናንተው በፍቃዳችሁ ተጨማሪ ጠባሳ እራሳችሁ ላይ አትጣሉ። ከህመማችሁ ለመንፃት መተው ያለባችሁን ነገር ተዉ፤ ስለወደፊት ህይወታችሁ የሚገዳችሁ ከሆነ እስራታችሁን ፍቱ፣ በእርግጥም ህይወትን በሙላት መኖር ካሻችሁ የይቅርታ ልብ ይኑራችሁ። ሸክማችሁን አራግፉ፣ ለደህንነታችሁ ዋስተና አስቀምጡ፣ በምርጫችሁ ወደፊትን ተመልከቱ፣ ኋላ ከቀረውና ከተበላሸው ይልቅ የሚመጣውና ማስተካከል የምትችሉት ጉዳይ ላይ አተኩሩ።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!
@MentalCounsel

❤️ LIKE & SHARE

ቤተሰብ ይሁኑ👉 https://t.me/letiwulid

ለትውልድ | LETIWULID 🦋

19 Dec, 19:24


ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር!

#ትኩረታችሁን_ስራችሁ_ላይ_አድርጉ!"

አንድ ሰው ይህንን አጭር ታሪክ ሲናገር ሰማሁት፡-

አንዲት ራቁቷን የሆነች እንግሊዛዊት ሴት አንድ ቻይናዊ የሚያሽከረክረውን ታክሲ አስቁማ ገባች፡፡ ቻይናዊው የታክሲ ሹፌር ደጋግሞ ከላይ እስከታች ሲያያት ጊዜ እንግሊዛዊቷ አስተያየቱ ስላሳሰባት፣ “ምነው! ራቁቷን የሆነች ሴት አይተህ አታውቅም እንዴ?” አለችው፡፡

ቻይናዊው በመመለስ፣ “ከላይ እስከታች ያየሁሽ ራቁትሽን ስለሆነሽ ሳይሆን፣ ከላይ እሰከታች ደጋግሜ ያየሁሽ የምትከፍይኝን ገንዘብ የያዝሽበትን ስፍራ ስላጣሁት ነው፡፡”

ከታሪኩ የምንማረው ትምህርት፣ እንደ ቻይናዊ የታክሲ ሹፌር ሁኑ፡፡ ትኩረታችሁን ከሚስበውና ከሚበታትነው ነገር ላይ አንሱና ትኩረታችሁን ዋናው ተግባራችሁና ቢዝነሳችሁ (ስራችሁ) ላይ አድርጉ፡፡

THANK YOU FOR READING
ELODIA READING📚📖
ኤሎድያ ንባብ📚📖

#share and join for more👍

@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING
@Elodia_G ንባብ @Elodia_G READING