Tikvah-University @tikvah_university Channel on Telegram

Tikvah-University

@tikvah_university


Tikvah-University (English)

Welcome to Tikvah-University, your go-to source for all things education and personal development! This Telegram channel is dedicated to providing valuable resources, tips, and insights to help you reach your full potential. Whether you're a student looking to excel in your studies, a professional seeking career guidance, or simply someone who wants to continue learning and growing, Tikvah-University has something for everyone. From study hacks and time management techniques to motivation and self-improvement strategies, this channel covers a wide range of topics to support your academic and personal success. Join our community of like-minded individuals who are committed to continuous learning and growth. Let Tikvah-University be your guide on the journey to becoming the best version of yourself!

Tikvah-University

21 Nov, 16:39


አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በግንቦት 2017 ዓ.ም ለሚያካሒደው 5ኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ሲምፖዚየም የምርምር ረቂቅ መቀበል ጀምሯል፡፡

ሲምፖዚየሙ የሚካሔደው 👇
ግንቦት 1 እና 2/2017 ዓ.ም

ረቂቅ የማስገቢያ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ጥር 12/2017 ዓ.ም

የምርምር ወረቀት ለማስገባት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://cmt3.research.microsoft.com/ASTUIRS2025/

ለበለጠ መረጃ፦
ያዴታ ጪምዴሳ (ዶ/ር) - 0947372481
ፈድሉ ከድር (ዶ/ር) - 0911301849

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Nov, 16:39


መቐለ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ትምህርት መስጠት የሚያስችለውን ዘመናዊ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ አስመርቋል።

የዲጂታል ትምህርት (E-Learning) ለመስጠት የሚያስችሉ ሰባት ተመሳሳይ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ መገንባታቸው ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Nov, 16:39


መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተመርቃችሁ ኦርጂናል ዲግሪ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ የተቋሙ የቀድሞ ምሩቃን ምዝገባ በማድረግ መውሰድ እንደምትችሉ ገልጿል፡፡

በዚህም ከዚህ ቀደም የተሰጣችሁን ቴምፖራሪ (Temporary) ኦርጂናሉን እና አንድ ኮፒ በመያዝ እስከ ህዳር 20/2017 ዓ.ም በዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 28 መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በመንግሥት የተማራችሁ ምሩቃን የሙያ ግዴታችሁን መጨረሳችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ ከገቢዎች ሚኒስቴር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Nov, 16:39


11ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠና የመክፈቻ መርሐግብር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተካሒዷል፡፡

ስልጠናው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ሰላም ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተመለመሉ 1,500 ወጣቶች ለ22 ቀናት በሚቆየው 11ኛው ዙር ስልጠና ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

በጎ-ፈቃድ ሰልጣኞቹ ስነ-ምግባር፣ አመለካከት፣ ክህሎት እና አካል ብቃት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባር-ተኮር ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Nov, 16:39


#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን የኢንፊኒክስ ሆት 40፣ ኖት 40፣ ዜሮ 40 ሞባይል ስልኮችን እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ በመጠቀም እና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ብቻ ከላይ በተጠቀሱት ሽልማቶች ይንበሽበሹ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia  ለ TikTok @Infinixet  እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።

Tikvah-University

21 Nov, 13:15


#ይመዝገቡ

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር 2024/25 ፕሮግራም ይፋ ሆኗል፡፡

በ9ኛው ዓለም አቀፍ የ2024/25 አይሲቲ ውድድር ለመሳተፍ የምትፈልጉ እስከ ታህሳስ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

ኔትዎርኪንግ፣ ክላውድ ኮምፒውተር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድሩ ከሚደረግባቸው የአይሲቲ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ።  

በሁዋዌ የICT ውድድር (Huawei ICT Competition 2024-2025) ለመሳተፍ በቅድሚያ የሁዋዌ ICT አካዳሚ አባል ይሁኑ።

የአካዳሚው አባል ለመሆን 👇
https://e.huawei.com/en/talent/portal/#/

ለውድድሩ ምዝገባ ለማድረግ 👇
https://bit.ly/SAR2024-2025

@tikvahuniversity

Tikvah-University

21 Nov, 13:15


በ2017 ዓ.ም ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በመግባት ላይ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ለሆኑ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ ተማሪዎች ለህዳር 12 እና 13/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 15:53


ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 15:53


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 14:14


አህመድ አብተው (ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

አህመድ አብተው (ዶ/ር) ከህዳር 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀን ህዳር 9/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል፡፡

አህመድ አብተው (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የኢንዱስትሪ ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡

ከጥቅምት 2/2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 14:14


#MekdelaAmbaUniversity

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በ2016 ዓ.ም Freshman ፕሮግራም መቀጠል ያልቻላችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ያልተማራችሁ (ዊዝድሮዋል ሞልታችሁ የወጣችሁ) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሁለቱም ግቢ (ቱሉ አውሊያ እና መካነ ሰላም) የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ (ቱሉ አውሊያ ካምፓስ) መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ጥደረጋል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 08:57


#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተከታዮቹ የሙያ መስኮች ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ተፈላጊ የሙያ መስኮች፡-
➫ Special Needs and Inclusive Education (MA level)
➫ Structural Geology (MSc/PhD)
➫ Geochemistry (MSc/PhD)
➫ Paleontology (MSc/PhD)
➫ Mining Geology (MSc/PhD)
➫ Economic Geology (MSc/PhD)
➫ Petrology (MSc/PhD)

መስፈርቶች፡-
- የአካዳሚክ ውጤት ለወንድ ከ3.00 በላይ እና ለሴት ከ2.75 በላይ
- የምርምር እና መመረቂያ ውጤት ከፍተኛ የሆነ/ች
- እድሜ ለመጀመሪያ ዲግሪ ከ35 ዓመት በታች እና ለማስተርስ ዲግሪ ከ45 ዓመት በታች

የሥራ ቦታ፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 6/2017 ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ተጨማሪ መረጃ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ወኪል ቢሮ ወይም የዩኒቨርሲቲው የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ፖ.ሳ.ቁ. 1020 ጅግጅጋ መጠየቅ ይቻላል፡፡

@tikvahuniversity

Tikvah-University

20 Nov, 06:53


#JimmaUniversity

በ2017 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በዋናው ግቢ

በ2016 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን የተከታተላችሁ ተማሪዎች በቅርቡ https://portal.ju.edu.et ላይ የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት አጠቃላይ ውጤታችሁን ማወቅ የምትችሉ ሲሆን፤ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ከላይ በተጠቀሰው ቀናት በተመሳሳይ የሚፈጸም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በ2017 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ግዜ በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Tikvah-University

19 Nov, 15:30


#WolkiteUniversity

በ2017 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3x4 መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር በውጤታችሁ መሰረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity