የዋቸሞ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ ከአምስት ዩኒቨርስቲዎች ለተወጣጡ የተማሪ ህብረትና ና የሰላም ፎረም አባላት ለተከታታይ አምስት ቀናት የቆየ ስልጠና ከ youth Awareness and Mindset Growth (YAMG) ጋር በመተባበር በኢትዮጲያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) አማካኝነት ሲሰጥ ቆይቷል።
በስልጠናውም የተሳተፉት የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፣የወራቤ ዩኒቨርስቲ ፣የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፣የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ና የጅማ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት ና የሰላም ፎረም ተወካዮች ነበሩ።
የ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወረ መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ ሰዎች መብታቸውን እንዲያውቁና የመብት ጥሰት ሲያጋጥማቸው እንዲጠይቁ በማገዝ ላይ ነው።
ይህ ኮሚሽን የሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ እውነትን እያጣራ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ሰዎች የደረሰባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትም ወደዚህ ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ ወደ ሆነ ኮሚሽን በመምጣት የተፈፀመባቸውን በደል በማሳወቅ ፍትህ ማግኘት ይችላሉ።
በቀጣይ ጊዜያት ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁ ለማሳወቅ እንወዳለን።
የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
👇👇👇👇
For real and complete information visit
https://t.me/WCUSU
https://www.facebook.com/wcusu2010
https://youtube.com@wcuinfo594
@WCUSTPRb