ክርስትና (kiristiyanummaa) @frebefkr Channel on Telegram

ክርስትና (kiristiyanummaa)

@frebefkr


Christians channal ፍቅር መድሀኒት ነው ለዛም ነው መድሀንያለም ምንለው እየሱስ ያድናል jaalalli moo'aa dha yesus jalaladha kanaaf yeroo hunda nii mo'a!
Farfannaa(መዝሙር)Kadhannaa፦ፀሎት፤Lallaba፦ስብከት፤asosama garagaraa hundafiyyu ልቦለዶችም ለሁሉም ተቀላቀሉን። @frebefkr 👣 http://t.me/Yefkrfrebot

ክርስትና (kiristiyanummaa) (Amharic)

ህዝቦች አሉን እና ኤሌምሲን መጽሐፍትን ለመከበሩ ክርስትህን ችሎታ እድሜአችን ከክርስቶሽን ማጽሐፍ አድርጉ በመጠቀም። ክርስትህን ሥርዐት ከላይ የሕልፍ ቅድመት የክርስቶሶችና ክርስትያስ ወጪ ስሚ፡የፈተና እና ክርስትህና እምነት። እንደዚህም ፓላውዴ እንዲሆን፡፡ በአምነኛ የፈረሳ የእናት ክርስትያን ይቤዠሃል፡፡ በስሜተኝት እና በግንባታቁም ከሆነም ከዛምር ጋር የምስጋና ቧንቧ ዋላማ ክሳ: ግንባቶቹን እና የግንባተኛ ሰዎች በተመለከተ መጠቀም፡፡ ይህን ቦታዎች ብሏል ነገርን ለመለምለም መልእክቶችን ከበሮ እና ከነጻ ሊያለም ይጠይቃል፡፡ በክርሱ ሊጐርም የሚገባቸውን ጨዋታዎች ከመቅረብ በፊቱ ጸሀፊዎችን በመኖሩ ለቤተመንግሥታችን በዚህ ቦታ ለናሀብ ምናልባት ይዘምሩ።

ክርስትና (kiristiyanummaa)

04 Feb, 06:04


1ኛ ዮሐንስ 5 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፤
¹⁵ የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ የለመነውንም ነገር እንደ ተቀበልን እናውቃለን።

ክርስትና (kiristiyanummaa)

19 Jan, 05:35


እረኛዬ

የኔ እረኛ የማይተኛ
ከቶ ያልሆነ ሙያተኛ
ጥሎኝ ማይሸሽ እውነተኛ
ከነጣቂው ቀማተኛ

ሚጠብቀኝ ቀን ከለሊት
የሚመራኝ ወደ እረፍት
ልምላሜ በሞላበት
ሚያሰማራኝ ያለስጋት

ስቅበዘበዝ ሚፈልገኝ
ለክፉ አውሬ የማይተወኝ
አንድ እረኛ እኔስ አለኝ

ልቤን በእርሱ ጥዬዋለው
ድምፁን ለይቼ አውቀዋለው
በሱ ጋጣ ውዬ አድራለው

ማን ከእጁ ይነጥቀኛል
እረኛዬ ነውና ሀያል
ስሙም ኢየሱስ ይባላል
ለዘላለም ይጠብቀኛል
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

19 Jan, 05:34


እረኛዬ

የኔ እረኛ የማይተኛ
ከቶ ያልሆነ ሙያተኛ
ጥሎኝ ማይሸሽ እውነተኛ
ከነጣቂው ቀማተኛ

ሚጠብቀኝ ቀን ከለሊት
የሚመራኝ ወደ እረፍት
ልምላሜ በሞላበት
ሚያሰማራኝ ያለስጋት

ስቅበዘበዝ ሚፈልገኝ
ለክፉ አውሬ የማይተወኝ
አንድ እረኛ እኔስ አለኝ

ልቤን በእርሱ ጥዬዋለው
ድምፁን ለይቼ አውቀዋለው
በሱ ጋጣ ውዬ አድራለው

ማን ከእጁ ይነጥቀኛል
እረኛዬ ነውና ሀያል
ስሙም ኢየሱስ ይባላል
ለዘላለም ይጠብቀኛል


@yisbekwengalu
@yisbekwengalu

ክርስትና (kiristiyanummaa)

14 Jan, 19:33


✝️Egziabher yimesgen!✝️
✝️Yezelalem amlak y'Esra'el qedus [Egziabher] keff yibel✝️
✝️[Yimesgen!]amen!✝️
✝️1)Bchayen hogne bechawn endemibekagn astemaregn awo gebagn beqa egziabher yibekal. Yalemannm degaf ena egeza esu bechawn yibekal!
✝️2)bebzu neger wust asalfogn ewnetegna amlkon astemaregn beka ahun gebtogn new mzemrew gebtogn new mamesegnew gebtogn new mamelkew beqa!.
✝️3)bemigodu besewoch kalat yemayhonu keldoche yemiastelu sedboche kene tekerefu and beand yemayhonu tsebayoch kene tefakqu begize hidet kess be kes kene lay tenesu.
✝️4)bemiyammu meretatoch ena tekqebaynet matat zmmtan temarkugn.
✝️5)betesale yEgziabher kal melase tegereze behamet temolto yagema yeneberewn afen bekalu boreshew.
✝️6)sew slesew kfat siawera sew hullem melkam,hullem kefum endalhone be erase asayegn sew malet sil yekalu mestawot hullem kefite new erasen salay selesew endalawera sew salweks befit erasen endmeleket aynen ateraw sew mulu endalhone temarku hullachnm endemnatefa degmo erasachnn kalfeteshn yemirrechu merz tsebayoch bezuuu endehonu temarkugn yihchi alem mood weym blt bela metasbew hullu farnnet yemecheresha mognenet enam wedkqet endehone teredaw beka.
✝️7)yaleEgzibher menor endemalchl awku temarku ene lerase endemalhon egzibher bechawn (enkuan kelela sew kerasem belay) endemiasfelgegn teredahu. Egziabher eko dnk new yhen yastemaregn mannew :-Egziabher becha new!✝️amen!✝️
@frebefkr
@frebefkr
@frebefkr✝️

ክርስትና (kiristiyanummaa)

13 Jan, 04:32


Dnet
Awo besrachn sayhon be eyesus krstos sera denenal degmon hatyategnoch nen ena nesha bngeba yikr yilenal gn gn gn! Frd ale mn aynet frd endehone gn semay bet yemnay yihonal mhret endale endezaw frdmm ale lehulum endesraw yissetewal yilal ye egziabher kal ena eyesus siawera degmo ahun lferd almetawn yilal egnanliadnen bemeta gize malet new besemay yalew abbatu gn endemiferd yinegrenal. So tsdqm be eyesus sra ale frdm begna sra lay ale!.
Egziabher yirdan! Beewnet amen!!!

ክርስትና (kiristiyanummaa)

31 Dec, 14:51


(Hojii Ergamootaa 2 )
------------
17 'Guyyaa gara dhumaatti akkana in ta'a jedha Waaqayyo,foon-qabeessa hundumaaf hafuura koo nan kenna,ilmaan keessanii fi intaloonni keessan raajii in dubbatu;dargaggoonni keessan mul'ata in argu,maanguddoonni keessanis abjuu in abju'atu.
18 Eyyee, guyyoota sanatti hojjetoota koo warra dhiiraa fi dubartiidhaafhafuura koo nan kenna, raajiis in dubbatu.
19 Wanta dinqisiisaa ol waaqa irraa, milikkitas gad lafa irraa,dhiigaa fi ibidda, aara lafa gurraachessus nan argisiisa;



17 እግዚአብሔር ይላል፡— በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤
18 ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ።
19 ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤

(Acts 2:17-19)

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
መንፈሳዊ ልብ ወለድ
ክፍል አንድ

ዛሬም እንደተለመደው የወፎቹ ዝማሬ አልነበረም የቀሰቀሰው::ትጉሁ መሆንን ለሚሹ እና ለሆኑት ነዉ የእነሱ ጣፋጭ ዝማሬ ማንቂያ የሚሆናቸው::አላርም በሁለቱም ስልኩ አራት ጊዜ ሞልቶ ነዉ የሚተኛው በአንደኛው ካልነቃ ሁለተኛው ከ10ደቂቃ በኋላ ይጮሃል በእንቅልፍ ልቡ እየተነጫነጨ ተነስቶ ይዘጋውና ተመልሶ ይተኛል ሶስተኛውም ከ10ደቂቃ በኋላ ሲጮህ ስልኩን ይዘጋና ጠረጴዛው ላይ ወርውሮ ይጠቀለላል አራተኛው ከመጮሁ በፊት እናቱ ትደርስና አላርሙን አጥፍታ ትቀሰቅሰዋለች... ይህ በየእለቱ ይደጋገማል::

* * * * *
"ይሄን ሙያ ግን ወደሀው ነዉ የገባህበት? " ከላይ የለበሰውን ነጭ ጋወን አውልቆ ከመኪናው ኋላ ወንበር ላይ በግዴለሽንት በመወርወር "ለምን እንደዛ አልሽኝ? " አላት:: "ይሄ ሥራ ፍላጎት ከሌለህ ለመስራት አዳጋች ነዉ :: ብዙ ጊዜ አየሁህ ለታማሚዎች የምታሳየው ፊት ደስ አይልም.. ቶሎ ትበሳጫለህ. ነርስ ሊኖረው የሚገባውን ግብረገብነት መችም ተምረሀዋል::.ፈገግ አለና ምንም ምላሽ ሳይሰጣት መኪናው አስነሳ:: የሆስፒታሉን ግቢ ለቀው እንደወጡ "እናቴ ናት በሰዎች ተመክራ ግቢ ከሄደ የባሰ ይበላሻል ብላ ኮሌጅ እንድማር ያደረገችኝ::እኔ ሆቴላችን ላይ ከልጅነት ጀምሮ እሰራ ስለነበር እሱን የምትሰጠኝ መስሎኝ ነበር... እሷ ግን ፊልዱንም ባህሪውን ለማሻሻል ይጠቅመዋል ብላ ነበር የመረጠችልኝ... የፈረደባት " በዚህ ዘመን ሰው ራሱ ወስኖ የራሱን ሕይወት መምራት የማይችል ሰው መኖሩ እያስገረማት ስሜቱ እንደተረበሸ ስላየች ምንም ልትጠይቀው አልደፈረችም:: ከብዙ ዝምታ በኋላ ዞሮ አየት አደረጋትና "አንቺስ ሥራውን ወደሽው ነዉ? "..ከልቧ ፈገግ አለችና "በእርግጥ ያላሰብኩት ነበር የደረሰኝ ግቢ እያለሁ ግማሽ ሴሚስተር ለመቀበል ከብዶኝ ነበር እያደር ስመጣ ግን አለመውደድ አልቻልኩም የእግዚአብሔርም ፍቃድ ነዉ ብዬ ስለተቀበልኩ ሙያውን አክብሬ እና ወድጄው እየሰራሁበት ነዉ ::" መኪናውን የሆቴል ፓርኪንግ ጋር አቁሞ "እድለኛ ነሽ.. ከምንም በላይ የእርሱ ፍቃድ ነዉ ዋናው.. ምሳ መብላት ያለብን አይመስልሽም? ግብዣ በእኔ ነዉ አታስቢ " ሁለቱም እየተሳሳቁ ከመኪናው ወረዱ::...

* * * *
አዜብ የልጇ ሻሎም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሄዱ ውስጧን እረፍት አሳጥቷቷል::እንደ ኤለመንተሪይ ተማሪ በየጊዜው ሆስፒታል እየተጠራች "ልጆት ባህሪውን ሊቀይር ካልቻለ ልናባረው እንገደዳለን " የሚል ማስጠንቀቂያ ትቀበላለች::የእናትነት ክብሯ ግድ ሳይሰጣት እግራቸው ላይ እየወደቀች ለአንድ እድል ትማፀናቸዋለች::.. አንዳንዴ ማታ ከ6:00ሰዓት ካለፈ መኪናዋን እየነዳች ከግቢ ትወጣለች... በየ ግሮሰሪው ቤት እየገባች ትፈልገዋለች... በጊዜ ገባ ከተባለ 5:00ሰዓት ላይ መኪናውን እየነዳ በስካር ውስጥ ሆኖ ወደ ቤት ይመለሳል::..... 5ዓመታት አለፉ እረፍት አጥቶ ካሳጣት...


ይቀጥላል....



@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
ክፍል ሁለት

"አማራጭ ያልኳቸውን ሁሉ ሞከርኩ ግን.. " አንገቷን በማቀርቀር ከአይኗ የሚፈሰውን እንባ በሶፍት ለመግታት ሞከረች::ፌኔት ከተቀመጠችበት በመነሳት አዜብ ከተቀመጠችበት ሶፋ ላይ ሄዳ በመቀመጥ ትከሻዋን ይዛ ለጥቂት ደቂቃ ሁለቱም በዝምታ ተዋጡ::ፌኔት የእናትና ልጅን ባህሪ እያነፃፀረች በሃሳቧ ትገረማለች::እሷ ካየችው ነገር ተነስታ እናቱ ከነገረችውም ነገር በመነሳት ሻሎም ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ ነዉ ብላ ደምድማለች አዜብን ከገባችበት ሀዘን እና ጭንቀት ለ ለማውጣት ለእራሷ የቤት ሥራ ሰጠች..

* * * * *

ሻሎም እንደለመደው ከእንቅልፉ ለመነሳት የእናቱ ቅስቀሳ ያስፈልገው ነበር.. ጭንቅላቱ እንደከበደው ከእንቅልፉ አይኖቹን እያሸ ተነሳ በአልጋው ላይ እንደተቀመጠ በአይኖቹ እያማተረ እናቱን ፈለጋት::ግን እንደቀድሞው አላርሙን አጥፍታ አልቀሰቀሰችውም ነበር::ትዝ ሲለው ማታ ሰክሮ ስድስት ሰዓት ሲገባ የግቢው ጠባቂ ነበር ደግፎት ያስገባው::ስልኩን ሲያየው የተሞላ አላርም አልነበረም:: ሰዓት መቁጠሪያውን ሲያይ በድንጋጤ እራስ ምታቱም ጠፋ:: ከቀኑ 5:00ሰዓት ይላል ::"ማሚ "እያለ ወደ ሳሎን ወረደ..

* * * * *
"ቆይ እኔ ያልገባኝ.. " በጣቷ ዝም እንዲል ነገረችው::"ቀድመህ የማይናገረውን ብላ ጥያቄው በኋላ ይደርሳል::" አለችው.. አዜብ እንደዛሬ ተቆጥታው ያወራችበትን ቀን ለማስታወስ ሞከረ.. እሱ የሚያውቃት እናቱ ተቆጥታው አታውቅም::አንገቱን አቀርቅሮ መመገቡን ቀጠለ:: "እሺ አህንስ ማውራት እችላለሁ? " ምግቡን አጠናቆ ሁለቱንም በየተራ አፈራርቆ እያየ::ፌናት አካኋኑ ፈገግ አስባላት እና ሹካዋን በማስቀመጥ "ሻሊ አንተ የ25ዓመት ወጣት ነህ:: እንዳየሁት ከሆነ ግን ገና የልጅነት ጊዜውን እንዳልጨረሰ ህፃን ልጅ ጥበቃ ይደረግልሃል::እሱን እንተወውና ከዛሬ ጀምሮ እዚህ ቤት ጥቂት ጊዜ እንድቆይ ማሚ ግብዣ አድርጋልኛለች:: በዚህ ሳምንት እንድታርፍ ደግሞ ሆስፒታል ፍቃድ ተሰጥቶሃል::" ሻሎም ግራ በመጋባት አዜብን አያት.. አንገቷን ሰበቅ በማድረግ ከገበታው ተነሳች.. አንገቱን ወደ ፌኔት በማዞር አብራሪልኝ በሚል አይነት አስተያየት አያት::...

ይቀጥላል..
.


@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
ክፍል 3

"ሻሊ ለምንድነዉ እንደዚህ የምታፈጥብኝ? በቃ ልነግርህ የምችለው ይሄን ነዉ ሌላውን ነገር በጊዜያት ሂደት የምትረዳው ይሆናል::" የጠቀለለውን ፓስታ ወደ ሳህኑ በመመለስ ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ ውጭ አመራ::ፌኔት ነገሩን ትንሽ ካጤነች በኋላ የበሉበትን ሳህን በማነሳሳት ወደ ማዕድ ቤቱ አመራች::

* * *
አዜብ እየቀለደች ስለመሰለው አልጋው ላይ ከጎኗ ሄዶ ቁጭ አለ::"ሻሊ እንደድሮ ለማባበል አትሞክር እስከዛሬ ልጄን በገዛ እራሴ ስገድለው ነበር ከዚህ በኋላ ግን ስህተቴን ልደግመው አልችልም::" ቀልዷን እንዳልሆነ ከአይኖችዋ ተረዳ ከአልጋው በመነሳት ፀጉሩን እያከከ ወዲያ ወዲህ ሲል ቆይታ አንድ ሃሳብ ሲመጣለት ወደ እናቱ ቀረብ በማለት ጉርበቷ ስር በርከክ ብሎ"ማሚዬ እንደድሮ አላመሽም የአባቢን ቀን ይስጠኝ 2 ሰዓት ሳይል ቤት እገባለሁ::".. አዜብ ከተቀመጠችበት በመነሳት "ልብስህን ቀይር" አለችው::

* *
"እንዴት ነዉ ቦታውን ወደድከው? " በፌዝ መልክ እያያት ሳቀ"እስር ቤት ተስማምቶሃል ወደድከው ተብሎ ይጠየቃል እንዴ? " አዜብ እና ፌኔት ተያይተው ተሳሳቁ:: "ባይሆን ቆንጆ እራት ጋብዛችሁኛል::
"በሚመጥንህ ቦታ ነዉ የተገኘሀው.. በዚህ ሰዓት ከማይመጥንህ ቦታና ሰው ጋር እራስህን ሳትሆን.. በመጠጥ ናውዘህ ነበር.. እናትህን ልታመሰግን ይገባሃል::" ከአፉ ክፉ ቃል ሊያወጣ አስቦ ፌኔትን ስለሚያከብራት ብቻ ከማውራት ተቆጠበ::እንዴት አድርጎ እነሱን ሸውዶ መሄድ እንዳለበት እያሰላ እያለ ሆቴሉ ላይ ሁለት የጠጡ ሰዎች እረብሻ አስነሱ:: አዜብ ዞራ ስታይ የምታውቀው ሰው ነዉ ከወንበሯ ብድግ በማለት ወደ ጥሉ ስፍራ አመራች ፌኔትም ተከተለቻት ሻሎም አጋጣሚውን ተጠቀመበት ጊዜ አላባከነም ነበር::

* * * *
"አረ አዜብ ብያንስ ውስጥ ገብተሽ ጠብቂው ያን ሁሉ አውርተን ይመጣል እኮ የት መሄጃ አለው? "..በር በሩን ስታይ ከቆየች በኋላ ወደ ውስጥ ገባች:: ፌኔት ወደ ጠባቂው በማምራት ሲመጣ ደግፎት እንዲያስገባው በመንገር ወደ ውስጥ ዘለቀች::
* * *
በስካር ውስጥ ሆኖ እየነዳ ስለ ብዙ ነገር ያስባል የልጅነት ጊዜው ሊያስታውሳቸው የማይወዳቸው ጊዜያቶች:: ሁሉም ከፊት ድቅን ይሉበታል:: የአባቱ ሞት እሱ ብቻ የሚያውቀው ሚስጥር.. ከአዕምሮው ለማጥፋት ይመስል የመኪናውን ፍጥነት ጨመረው:: በማዞሪያው መኪናውን ሊያዞር ሲል ትዝ ይለዋል ከባድ ግጭት ወደ ጭንቅላቱ.. ከሰውነቱ የሚፈሰው ደም ሁሉም ነገር እየጨለመበት ሄደ.. ሁሉም ነገር የሆነው በቅፅበት ነበረ ....


ይቀጥላል......,



@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
ክፍል አምስት

"እንደዚህ እንዲሆን አልነበረም.. "

"አውቃለሁ ፌኑ:: በፀፀት እራስሽን እንድትጎጂው አልፈልግም:: አንቺ የቻልሽውን አድርገሻል አደጋው ባይፈጠር ዕቅድሽ ይሳካ ነበር:: ፈጣሪ እኛ ካሰብነዉ ሌላ አስቦ ይሆናል::"
ፌኔት የአዜብ" ፈጣሪ "ማለቷ ቢያስገርማትም ከመጠየቅ ግን ተቆጠበች::

* * *

ሻሎም ዓይኖቹን ከከፈተበት ቅፅበት አንስቶ አዜብን ሊያናግራትም ሆነ ሊያያት ፍቃደኛ አልነበረም:: ሆስፒታል ተኝቶ በቆየባቸው ጊዜያቶች ሁሉ የእርሷን ክፋት በየትኛው ክፋት እጥፍ አድርጎ እንደሚመልስባት ነበር ሲያሰላስል የቆየው::.
"አይበቃህም እራስህንም እናትህንም ለትናንት ጥፋትዋ መቅጣት? " ህሊናው ወቀሳውን ሲጀምር ያስቆመዋል::
"ገና በእሷ ምክንያት የፈሰሰውን የአባቴን ደም መች መለስኩና " ለእራሱ ምላሹን ይሰጣል::

* * *
ከሆስፒታል መልስ የሰዉ ግርግር ሲያበቃ መኝታ ክፍሉን መዋያው አደረገ:: የሚሰሙትን ስሜቶች ከሰዎች ጋር ሊያወራቸው የፈለገውን ሁሉንም በወረቀት እየፃፈ ያስቀምጣል::ከእነዛ ውስጥ ደግሞ ቃላቶችን እየመዘዘ ለየብቻ ይፅፍና መስኮቱ አጠገብ ግድጊዳው ላይ ይለጥፋል::በዊልቸር ስለሆነ የሚንቀሳቀሰው ወደ ሳሎን ላለመውረድ እና ክፍሉ ለመቆየት ሰበብ ሆኖለታል::
በሩ ስንኳኳ ዊልቸሩን በእጁ እየገፈ ወደ በሩ ተጠጋ::
"ሻሊ ፌኔት ነኝ ክፈትልኝ"
ጥቂት ካቅማማ በኋላ ከፈተላት:: አቅፋው ሰላም በማለት ወደ ውስጥ ዘለቀች:: በምድር ላይ በእናቱ ምክንያት ሴት የሚባል ፍጥረትን ቢጠላም ለምን ፌኔትን ሊጠላት እና ሊያርቃት እንዳልቻለ እንቆቅልሽ የሆነበት ነገር ነዉ:: በሩን በመዝጋት ወደ እርሷ በመዞር "ሥራ አሪፍ ነበር ፌኑ? "
"መልካም ነበር.. ምግብ አትበላም አሉ " ቦርሳዋን አልጋው ላይ በማስቀመጥ በቀኝ እጇ የያዘችውን ፒዛ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችው::
"አዘንሽልኝ በቃ"
"ስለ እራሱ ግድ የማይሰጠው ጓደኛ ይዤ ምን ላድርግ ታዲያ"
"ትረባው ቢበቃስ "
"የጀመርከው አንተ.. ባይሆን ከተለመደው ቤት ነዉ ያመጣሁልህ እኔም እርቦኛል ደግሞ" መክፈት ጀመረች..

"ለስላሳ? "
"አይ ቀዝቀዝ ያለ ውሃ"
ወደ ፍሪጁ ዊልቸሩን እየገፋ ሄደ::
ክፉሉን በዓይኗ ስትቃኝ በግድጊዳው ላይ በለጠፋቸው ወረቀቶች ላይ ዓይኗ አረፈ:: ከተቀመጠችበት በመነሳት ወደ መስኮቱ አመራች::
ማስወገድ, ትላንት, ማንፃት, የእራስ ዓለም, መተኪያ.. ሁሉንም ካነበበች በኋላ አንዱ ቃል ላይ በመገረም ፈዛ ቀረች...ለስላሳውን እና ውሃውን ጠረጴዛው ላይ በማስቀመጥ::
"የማይገባሽ ነገር ላይ ጊዜ ማጥፋት መልካም ነዉ ብለሽ?.. "
"አንዱን ቃል ብቻ ልጠይቅህ"
"አንዱን ብቻ ከሆነ ይብራራልሻል"
"አረሜን.. ይሄን ቃል ፍታልኝ " ወደ እርሱ አመራችና አልጋው ላይ ተቀመጠች::
"እሱን ቃል ከምፈታልሽ.. "
"አትጨርሰው ሻሊ... እኔ እንዳሰብኩት እንዳይሆን ፍቺው" ዓይኗ እንባ አቅሮ ነበር::
"አንቺ ምን አሰብሽ? " በመገረም ጠየቃት::
"ምን አልባት አንተ ከምታስበው በላይ ላውቅህ እችላለሁ ሻሊ.. ቃላቶችን በሶስት መንገድ ገጣጥሞ ትርጉም ስለመስጠት አባቴ ያሰለጠነኝ ነገር ነዉ::"

"ኦውው.. ገርሞኛል ብቻ!.. የእኔም አባት አሰልጥኖኝ ነበር:: ምን ፍቺ ሰጠሽው? "

"አዜብን ምን ልታደርጋት ነዉ? "
"እኔ ሳልሆን የሰራችው ክፋቷ ነዉ.. "

"እናት እኮ ናት... እና አረሜን ያልከው ለእርሷ ነዉ"

"አልተሳሳትሽም... አረም ምን እንደሚደረግ መችም ለአንቺ አልናገርም"

ፌኔት ሻሎም ያሰበውን ስታውቅ ለእራሷ ዘገነናት::ከፊቷ ያለውን ሰው ፍፁም እንደማታውቀው ተሰማት::
ቦርሳዋን ይዛ ተነሳች እና ወደ በሩ አመራች::
"ልታስቆሚኝ እንዳትሞክሪ!"
በሩን ከፍታ ወጣች::

ግድ አልሰጠውም ነበር::

ይቀጥላል...........




@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
መንፈሳዊ ልበ ወለድ
ክፍል አራት

ለእርሷ እያንዳንዱ ደቂቃ የውጥረትና የጭንቀት ነበር::ከምንም በላይ አዕምሮዋ ውስጥ የሚመላለሰውን ወቀሳ መሸከም ተስኗታል::.. መጠጋቱን ስለፈራች አንድ ወንበር ላይ ጥግ ይዛ ተቀምጣ አልጋ ላይ እራሱን ስቶ የተኛውን ልጇን በለቅሶ እና እንቅልፍ በማጣት በደከሙ አይኖችዋ ታየዋለች::...
"ባለቤትሽን አንገብግበሽ አንድ ቀን ሳያርፍ ሞተ ዛሬ ደግሞ ልጅሽ ሊከተለው ነዉ::"
"አይሆንም" ብላ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች:: ሻሎም ወደ ተኛበት አልጋ በፍጥነት አመራች.. ለመጀመሪያ ጊዜ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት ቻለች::በፋሻ የተጠቀለለው እግሩ ላይ አይኗ አረፈ.. አንድ እግሩ በመኪና አደጋው ጊዜ በጣም ተጎድቶ ስለነበር ሲነቃ ለመራመድ እንደሚያዳግተው ዶክተሩ ነግሯት ነበር::
"እግዚአብሔርን ልታመሰግኚ እንጂ ልታማርሪው አይገባም::መኪናው በከፍተኛ ፍጥነት ላይ ስለነበር በሚታጠፍበት ጊዜ አንዱ ጎማ ነበር የወለቀው:: በዛ ሰዓት በሱ አቅራቢያ ሌላ መኪና ኖሮ ቢሆን ከዚህ የከፋ አደጋ ይፈጠር ነበር::ፖሊሶች ወዲያው እዛ ቦታ በመድረሳቸው ከሰውነቱ ብዙ ደም ሳይፈስ እርዳታ ተደርጎለታል.. ይሄ የእግዚአብሔር ሥራ ነዉ በፈጣሪ ያምናሉ መችም.. ወይዘሮ አዜብ እየሰሙኝ ነዉ? "
የፖሊሱ ንግግር በአዕምሮዋ ውስጥ ለምን እንደሚመላለስ ሊገባት አልቻለም::.. "በፈጣሪ ያምናሉ? " ይሄን ንግግሩ ፈገግ አስባላት.. ፈገግታዋ ከስቃይ እንጂ ከደስታ የመነጨ አልነበረም...

* *
#ከአምስት ዓመት በፊት

ለሻሎም ይሄ ቀን ለእርሱ ሊዩ ነበር:: የኢንትራንስ ፈተና መጨረሱ አንዱ ነገር ሲሆን የተወለደበት ቀን በመሆኑ ደግሞ ድርብ ደስታን ፈጥሮለታል ከልደቱ ባሻገር የቤታቸውን ገመና ሊፈታና እንደስሙ ለቤታቸው የሰላም ምንጭ ለመሆን ያወጣው ዕቅድ ይበልጥ ቀኑን ልዩ አድርጎለት ነበር :: ወጣ ያለ ባህሪ እንዳለውና አስቸጋሪ ልጅ እንደሆነ እናቱ ሁሌም ለሰዎች ስትናገር ስለሚሰማ እናትነቷን ይጠራጠራል::እሱ እስከሚያውቀው ድረስ እናት የልጅ ገመና ሸፋኝ ናት:: አንድም ቀን እንደምትወደው ነግራ ስለማታውቅ በጓደኞቹ እናት ሲቀና ያደገው:: ቤተክርስቲያን ከአባቱ ጋር እንጂ ከእሷ ጋር የሄደበትን ጊዜ አያስታውሰውም::
"ቤት ውስጥም እግዚአብሔር ይመለካል" የሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን ላለመሄድ ማስተባበያዋ ነበር::
"ሁለታችንም መጣጣም አልቻልንም እኔ ገና ወጣት ነኝ እሱ ደግሞ የመሞቻ ቀኑን የሚቆጥር..እና እኔ አዜብ ምን እዳ አለብኝ.. ባይሆን ነገ ጥዋት ሁለቱም ቸርች ስለሚሄዱ በተለመደው ቦታ ዜና እንገናኝ ሰውዬውን አዘጋጂልኝ " ከኳየር ወደ ቤት ሲመለስ አዜብ በስልክ ከጓደኛዋ ጋር ስትናገር የሰማው ጆሮን ጭው የሚያደርግ ንግግሯ ነበር::...በእድሜው ሁሉ የእናቱን ክፋትና የአባቱን ታጋሽነት እና የአባትነት ፍቅሩን እያየ ነበር ያደገው:: አንድ ቀን ትለወጣለች በሚል ተስፋ ይኖር ነበር::.."ዛሬ በልደት ቀኔ እናቴን ቀርቤ ላወራትና እሷ ፍቅርን መስጠት ባትችል እንኳ አድጌያለሁና ግቢ ከመሄዴ በፊት አባቴን እና እናቴን መሃከላቸው በመግባት ፍቅርን በዚህ ቤት እዘራለሁ ሰላምም ይመጣል ...ስሜን ልኑረው እስኪ.. ይሄን ማድረግ አያቅትህም ሻሊ"
ከእንቅልፉ እንደተነሳ በዚህ ንግግር ነበር ቀኑን የጀመረው:: ፈተናውን አጠናቆ ልደቱን ለማክበር ወደ ቤት ሲያቀና ግን በሕይወቱ ይከሰታል ብሎ ያልጠበቀውን ማንነቱን በመጥፎ የለወጠ ነገር ከፊቱ ተጋረጠበት:: በአባቱ የልደት ስጦታ ፈንታ የአባቱን የእሬሳ ሳጥን እና በድን የሆነውን ሰውነት ተቀበለ:: በዛው ቀን "አንገብግባው እኮ ነዉ የገደለችው.. ከእሷ ጋር ተጣልቶ በንዴት በፍጥነት ሲነዳ እኮ ነዉ አደጋው የደረሰው.." ሃዘን ነዉ ብሎ ማውራት ከማያቆመው አፋቸው እውነቱን የተረዳው...ከዛን ቀን ጀምሮ ነበር ሻሎም ሻሎምነቱን ያጣው ...


ይቀጥላል.........




@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
ክፍል 7

እንድታወራ በዓይኑ
ተማፀናት::
ያለገደብ የሚፈሰውን እንባዋን በእጆችዋ ለመግታት እየሞከረች ልታስታውሰው ወደማትፈልገው ትላንት በሀሳቧ ሄደች::
"አባት ታውቃለህ እኔ አላውቅም.. የስጋውን!..በሰቆቃ ነዉ ያደግኩት የእናቴን ህመም እያየሁ እንደህፃን ስትሰደብ በስካር ገብቶ እስከሞት ሲያሰቃያት.. ልጅነቴ ያ ነበር ግን እሷን ከዛ ባርነት ለማውጣት እማር ነበር.. ተስፋዬ ትምህርቴ ነበር.."ሳድግ የእናቴን እንባ አብሳለሁ..አባቴን እና መሰሎቹን በዓለም መድረክ ቆሜ ከሥራቸው እንዲቆጠቡ ከክፋታቸው እንዲመለሱ አጋልጣቸዋለሁ..ግን እኔ አልቀጣቸውም "እል ነበር::
"እማዬ ለምን መቅጣቱን አልፈለግሽም? "
"እግዚአብሔር ይፈርዳል ሰው ግን ለመፍረድ እና ለመቅጣት የሚያበቃው ንፁህ ማንነት የለውም ትለኝ ነበር እናቴ እግዚአብሔርን በመፍራት ውስጥ ሆኘ እንዳድግ ነዉ ያስተማረችኝ::..10ኛ ክፍል እያለሁ አባትህ እና አባቴ ወደ ቤታችን መጡ:: ሕልሜን ሊነጥቁኝ ከራዕዬ ሊያጎድሉኝ:: እናቴ በለጋነቷ ተዳረች እኔም የእሷን ገፈት ቀማሽ ሆንኩኝ::..አቅሙ አልነበረኝም እና ተሸነፍኩ እናቴም ተስፋዋን ተነጠቀች:: አባትህ ጥሩ ሊሆንልኝ ሞከረ አስተማረኝ 12 እስክደርስ ምንም ሊነካኝ አልወደደም.. ለውጥ አልነበረውም:: እናቴ ያረፈች ቀን ግን የተበደለችው አዜብ ተገለጠች::የምኖረው ለእሷ ነበር.. እሷን ሲነጥቀኝ የሕይወት መሪህዬን ቀየርኩት እግዚአብሔር ስለማይቀጣ እኔ እቀጣቸዋለሁ ብዬ ተነሳሁ:: አባትህን ጨምሮ ብዙ መሰሎቹን ቀጣሁ አባትህ ላይ በማመንዘር መሰሎቹን ደግሞ ሕይወታቸውን ገሃነም በማድረግ::..አባትህ ግን የተለየ ነበር እያወቀ ዝም!....መቅጣቱ ሲታክተኝ.. ከጌታ ቤት መኮብለሉ አቅም ሲነሳኝ ለአንተ እና ለአባትህ መኖር እጀምራለሁ ባልኩት ቀን.. ይቅርታ ሳልጠይቀው እንኳ የልደት ኬክህን አመጣለሁ ብሎ በወጣበት በዛው ቀረ ለአንተ እንኳ ልኑር ስል አረፈድኩኝ መሰለኝ አንተም ተለወጥክ..በእኔ ቦታ ተተክተህ ልትቀጣኝ ጀመርክ.. እኔም አረሞቼን ልነቅል ተነሳሁ እኔም የአንተ አረም ሆንኩኝና ልትነቅል ተከተልከኝ "

በሁለቱም መካከል ረጅም ሰዓት ዝምታ ሰፈነ ...
ሻሎም የሰውነቱን መንቀጥቀጥ ማቆም አልቻለም "አጋጣሚዎች ወይስ የተወሰነ?... ማነዉ በዳዩ ማንስ ነዉ ተበዳዩ? " የሁለቱም ጥያቄ ነበር..

* * *
"እሺ ወይዘሮ አዜብ..ዛሬ ወደ ቤቶት የመጣሁት.. እእ ይህን ስነግሮት እያዘንኩኝ ነዉ.. የሙያ ስነምግባሬ እንደማይፈቅ አውቃለሁ..ሻሎም ጓደኛዬ ነዉና ያንን ለማድረግ ተገደድኩ::"
"አልገባኝም ዶክተር"
"ሻሎም የደረሰበት አደጋ ቀላል ነበር.. እግሩ መራመድ ይችላል "
አዜብ በድንጋጤ እና ባለማመን ብድግ አለች.. ሻሎም ወደ ሳሎኑ እየተራመደ መጣ..


ይቀጥላል.............


@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት )
ክፍል 6

ፌኔት በሩን ዘግታ ከወጣችበት ሰዓት ጀምሮ አዕምሮው ላይ ያልጠበቃቸው ጥያቄዎች መፈጠር ጀመሩ:: "አረሜ ነዉ ያልከው ሰው ከነቀልከው በኋላ መልካም ፍሬ እንደነበር ቢገባህስ ፀፀቱን ትችለው ይሆን?.. እናትህን ለምን እንደዛ ታደርግ እንደነበር አውርተሃት ታውቃለህ?.. ሞተህ ቢሆንስ? ንስሃ አልገባህም ከጌታ ቤት ኮብልለሃል የት ነበር ነብስህ የምትሄደው?... ከእግዜሩ ከእናትህ ከሰዉ.. ከራስህም ሳትሆን እየኖርኩ ነዉ ትላለህን?... አንድ ደቂቃ እንኳ ለእራስህ ጊዜ ሰጥተህ አስበህ ታውቃለህ?... " የአዕምሮውን ጥያቄዎች ለማስቆም ጆሮውን በሁለት እጆቹ ደፈነ:: አዕምሮው ግን መጠየቁን አላቆመም ነበር...

* * * * *
"ምግብ ከበላ ሶስት ቀኑ አንቺም መመጣት አልቻለሽ.. "
"የእኔ መምጣት አለመምጣት የሚፈጥረው ለውጥ የለም አዜብ.. አንቺ ነሽ ለዚህ ልጅ ህመሙም መድሃኒቱም::.. በአንቺ ምክንያት ብዙ ዓላማ የነበረው ልጅ ዛሬ ላይ አጥፊ ሆኖ አረሜን ካልነቀልኩ ይላል"
"አረሜን? " አዜብ ቃሉ አስደነገጣት.. ስልኩን ከጆሮዋ አንስታ ለአፍታ አሰብ በማድረግ ወደ ጆሮዋ መለሰች
"ሁለታችሁንም ማጥፋት ካልፈለግሽ እጅሽን ስጪው... "
"ለማ.. ለማነዉ እጄን የምሰጠው ፌኑ ?" ተርበተበተች
"ለልብሽ ጌታ ለተውሽው ገፍተሽ ከቤትሽ ላወጣሽው.. ለእርሱ እጅሽን ስጪ መከራከሩ መሟገቱ አይበቃሽም? ምን እስክትሆኚ ነዉ ቆይ? "
አዜብ በሁለት ዓይኖችዋ እንባዋ ያለማቁረጥ መፍሰስ ጀመረ..ፈልጋው ግን አልነበረም::እግሯ መብረክረክ ሲጀምር የአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠች::
"እንዳታረፍጂ አዜብ.. እንዳታረፍጂ!"
ፌኔት ስልኩን ዘጋችው:: እሷ ግን ጆሮዋ ላይ እንዳደረገች ነበር.. ብዙ ሰው መክሯታል እንድትመለስ ነግሯታል ግን የዛሬውን ያህል ልቧን ዘልቆ አጥንትን የሚደርስ አልነበረም:: ስልኳ ላይ መልዕክት ሲገባ በመደናገጥ ከጆሮዋ በመደናገጥ አነሳችው እና ስልኳን አየች ዓይኖችዋን ማመን ስላቃታት እየሮጠች ከመሳቢያው ውስጥ መነፅሯን በማውጣት አድርጋ አየችው.. "እማዬ ምግብ ከበላሁ ቆየሁ እኮ" ይላል:: ብዙ ጊዜ ለምናው መብላትን አልፈለገም ነበር በደስታ ብዛት እንባዋ አልቆም እያላት ወደ ማዕድ ቤቱ በፍጥነት አመራች::

* * * *
ሻሎም ምግቡን በልቶ እስኪጨርስ አጠገቡ ቆማ በስስት ታየዋለች:: እንደድሮው "ህጂልኝ "ብሎ አላባረራትም::በየመሃሉ ቀና እያለ እንድትበላ ይጋብዛታል.."በቃኝ አሁን በላሁ" ትለዋለች ፈገግታዋን እየቻረችው::..ይሄን ፈገግታ ካየ እጅግ ስለቆየ በመገረም ያያታል...
"ጠገብክ? "
"በጣም!"
"ትንሽ ልጨምርልህ.. ትንሽ"
"አረ እማዬ በጥጋብ መሞትም አለ "ሳያውቀው ነበር ያመለጠው ከ ሰባት ዓመት በፊት አባቱ ነበር ሁሌም እንደዚህ የሚላቸው ሁለቱም ዝም ብለው ከቆዩ በኋላ በእጁ አልጋው ላይ እንድትቀመጥ ጠቆማት አላንገራገረችም::ዊልቸሩን እየገፋ ይበልጥ ቀረብ አለና ዓይኖችዋን በጥልቀት ማየት ጀመረ.. ብዙ ህመሞች የፈሰሱ እንባዎች...ከሰባት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አተኩሮ አያት..ፊቷ ተሸብሽቧል ጠቁሯል ሰውነቷ እጅግ ከስቷል..ከዓይኖቹ ሊፈስ የነበረውን እንባ እንደምንም በመግታት እጇ ላይ ያደረገችውን ቀለበት እስካሁን አውልቃ ባለመጣሏ እየገረመው ቀኝ እጇን በመያዝ ቀና አለና..
"እማዬ ንገሪኝ አሁን ትንሽ ልጅ አይደለውም ሁለታችንም ከመጥፋታችን በፊት ያኔ የተፈጠረውን ሳትደብቂኝ ንገሪኝ " አላት...


ይቀጥላል...........



@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


#አረሜን (ፀሐፊ ምህረት)

😱የመጨረሻው ክፍል 8😱

"በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ እንዳለ አየሁ ::አንቺ እንደዛ ባልሽኝ ጊዜ ልጄ መልዕክት ላከልኝ ቀርቦ አወራኝ.. ህመም የሚቀለው ለነብስ ከሚቀርብ ሰው ጋር ስታወሪ ነዉ ለካ.. እያወራሁት ምን አስብ እንደነበር ታውቂያለሽ.. ምን ያህል የእግዚአብሔር ምህረት ለእኔም ለልጄም እንደበዛልን ሁለታችንም ጠፊዎች ነበርን::ያኔ መሸነፍ እንዳለብኝ ገባኝ ሻሎምን ካወራሁት እና ይቅርታ ከጠየቅኩት በኋላ ከብዙ ዓመታት በኋላ እራሴን በፊቱ አዋረድኩ::.. ፊቱን አልነሳኝም ወዲያው ተቀብሎኝ ነበር.. ይሰማኝ ነበር በልጅነቴ በቤቱ ስሆን የነበረው ያ መንፈስ...ከዚህ ነበር ለዘመናት ጠላት ከቤቱ ያጎደለኝ.. በንጋታው ሻሎም ይቅርታ ሊጠይቀኝ እኔን ለመበቀል ሽባ ያደረገውን እግሮቹን እየተራመደበት መጣ... እግዚአብሔር ዓመታት ሳይፈጅ ወዲያው የፀሎቴን ምላሽ ሰጠኝ.. "
"እማዬ.. " ሻሎም መኝታ ክፍሏን ከፍቶ ገባ::
ሁለቱም ቆመው በፈገግታ ተቀበሉት::
"ወሬያችሁን ለእኔ ብላችሁ ማቆማችሁ ሳያንስ በእግራችሁም ቆማችሁ? "
"ጀመረህ ደግሞ.. ና እቀፈኝ እስኪ" አዜብ ንግግሩ እያሳቃት እጇን ዘረጋችለት:: አጥብቆ አቀፋት::
"እምም.. በቃ እናትና ልጅ ተታረቃችሁና እኔ ተረሳሁ? "
ፈገግ አለና እያቀፋት ወደ ጆሮዋ ጠጋ በማለት "አመሰግናለሁ ስለሁሉም" አላት::
"ቁርስ ብሉና ትንሽ ከከተማ ወጣ ብንልስ? "
"አይ እማዬ ዛሬ የግድ ሆስፒታል ሥራ መጀመር አለብኝ"
ሁለቱም በመገረም እርስ በእርስ ተያዩ::
"እናንተ ቁርስ አዘጋጁ እኔ ልብሴን ልለባብስ::"
ወደ ክፍሉ ሲገባ ከፊት ለፊቱ ግድጊዳውን የሞላውን ወረቀቶች ሲያይ ቀፈፈው::መልሶ ሊያነባቸው አልወደደም:: በፍጥነት ሄዶ አንድ በአንድ እየገነጠለ አነሳ ግድጊዳው ንፁህ ሲሆን ውስጡም ፍፁም ንፁህነት ተሰማው::..ወረቀቶቹን ሰብስቦ ከክፍሉ ወጣ::..እየተጣደፈ ሲወጣ አይተውት ሥራቸውን አቁመው ተከተሉት::..."መጥፎ ጠባሳዎቻችን እንደዚህ ወረቀቶች ነደው አመድ ይሁኑ"...
"አሜን" አዜብ እና ፌኔት እየሰቁ እንባቸው ይወርድ ነበር::

* * * *
ሆስፒታል በመጀመሪያው ቀን ቆይታ ድንቅ ጊዜን ከታማሚዎች ጋር አሳለፈ::ታካሚዎችን በሚያወራበት ሰዓት ሲበረቱ ሲያይ እዛ መገኘቱን ወደደው::.. በግዴለሽነት የሰራባቸው ወቅቶች ፀፀቱት::
"ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆን ምንድነዉ ግን የሚጎድልበት? " ለምሳ በወጡበት ሰዓት ነበር ፌኔትን የጠየቃት::
"ስጋን ለዓለማዊ ነገር ማስለመድ በጀመርን ጊዜ የከበረው ነገር ቀሎብን የቀለለውን ማክበር እንጀምራለን::..በዛ ምክንያት የሞላውን ቤታቸውን ጥለው የሞላ የሚመስል ግን ያላቸውን ነጥቆ ባዶአቸውን ወደሚቀሩበት ቤት ይኮበልላሉ.. ያጡ የጎደለባቸው መስሏቸው::..መጉደል ማለት የምንፈልገው ሳይሆን የሚያስፈልገንን ማጣት መሆኑን ብዙዎች አልገባንም ወይም ገብቶን መቀበል አልፈለግንም::ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆን የሚያስፈልግህን አታጣም ለዛ ምንም የሚጎድልብህ ነገር አይኖርም::
በመልሷ ተገርሞ ፈዞ አያት::
"አይንህን ትሰብረው"
"ልታሳፍሪኝ እየሞከርሽ ነዉ?...እኔ ምልሽ እሁድ እሁድ ብቻ ነዉ እንዴ ፕሮግራም እማዬ እሁድ እንሄዳለን ብላኝ... ?
"መሄድ ፈልገህ ነዉ? "
"በጣም! "
"ዛሬ እኛ ቸርች የወጣቶች ፕሮግራም አለ ብጋብዝህስ.."
"በደስታ.. "

* * * *
"ቸርች ፕሮግራም እንዴት ነበር? "
"ድንቅ ነበር እማ ድጋሚ የተወለድኩ ያህል ነዉ የተሰማኝ"
አቅፎ ሳማትና ሶፋው ላይ ከአጠገቧ ተቀመጠ.. ፀጉሩን እያሻሸችለት ከቆየች በኋላ..
"አባዬ ሆስፒታል ታሞ ገብቷል አሉ " ደንገጥ ብሎ አያት
"እሱንም ይቅርታ ሳልጠይቀውና ሳላደርግለት እንዲያመልጠኝ አልፈልግም::"
"አሁን ልትሄጂ ነዉ?"
"አዎን ማርፈድ አልፈልግም::"
"እኔም አብሬሽ እሄዳለሁ..አያቴን ላውቀው እፈልጋለሁ::"
ፈገግ ብላ መስማማቷን አንገቷን በመነቅነቅ ገለፀችለት::

* * * *

ማዳመጫውን ጆሮው ላይ ሰክቶ በጀርባው አልጋ ላይ በመተኛት ዓይኖቹን ጨፈነ::በዝማሬው ውስጥ እራሱን ስላገኘ በመገረም እየደጋገመ ይሰማዋል... አብሯት ሲዘምር ውስጡ በሃይል ሲሞላ ልቡ ሲጠነክር ይሰማው ነበር

"በድሎ ከማያውቅ
ታላቁ ተበዳይ
ይቅርታን ብንማር
እያስታመምን ሳይሆን
እየወጉን ሳለ ነዉ መማር
.
.
.
ስለሻረልን ሳይሆን
እየቆሰልን ሳለ ነዉ መማር::"
ከአልጋው በመነሳት ነጭ ወረቀት በማንሳት
"የበደለን በመማር እንጂ አረም ነዉ ተብሎ በመንቀል ነፃ አይኮንም" ይሄን ከግድጊዳውም ከልቡም አተመው::



👋👋 ተፈፀመ🖐️🖐️🖐️🖐️


(ፀሐፊ ምህረት )

@frebefkr
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

30 Dec, 09:28


ሰላም ቅዱሳን እንዴት ናችሁ እግዚኣብሄር ይመስገን ዛሬ ደግሞ አረሜን በሚል ልቦለድ መጥተናል እንደምትባረኩበት አምናለሁ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ!

Join share
@frebefkr

ክርስትና (kiristiyanummaa)

29 Dec, 18:44


ቆራጥ ሁን!

ታሪክህን የሚቀይረው ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንተ ቆራጥነት ነው! ከሰዎች ብዙ አጠብቅ! ሰዎችን አንዳስቀመጥክ አታገኛቸውም ጊዜና ሁኔታ ይቀይራቸዋል። ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ማለት ስትጀምር በአመለካከት ከፍ ማለት ትጀምራለህ።

“በርታ ሰውም ሁን፤...
— 1ኛ ነገሥት 2፥3

#inspire Ethiopia
@SisayAzusaPreaching

ክርስትና (kiristiyanummaa)

23 Dec, 10:45


እባካችሁን በእግዚአብሔር ፍቅር ስሙት።