😘(አለመኖር )#️⃣
"አዎ መሸነፍ ነዉ።
ፍቅር መሸነፍ ነዉ።
ፍቅር መያዝ ነዉ።
ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነዉ።
ፍቅር ከምክንያት ዉጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነዉ።
ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ዉጪ መሆን ነዉ። ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነዉ።
ያስፈራል ፍቅር፣የማይታከሙት ህመም፣
የማይጠገን ቁስል ፣
የማያባራ እንባ እና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል ።"
"የሚያስፈራው ያፈቀርሽዉ ሰዉ ሳይሆን፤ ማፍቀር ራሱ ነዉ ካፈቀርሽ በኋላ 'እኔ' ምትይዉ ሁሉ ይጠፋል ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ። በፈቃደኝነት ከራስሽ ምታስቀድሚዉ እና ምታስበልጪዉ ሌላ ሰዉ ይኖራል ማለት ነዉ።"
"ፍቅር ያለ ዉጊያ መማረክ ነዉ ፤ እጅ መስጠት፤ ወዶ መግባት፤ ከራስ መነጠል ፣መጥፋት በማያዉቁት አለም ዉስጥ ገብቶ መሰደድ ፤ አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል።
••●◉Join us share
💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@fkrbefkr143
@fkrbefkr143
✽»🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽»🌺