South Wollo Zone Gov. Communication Department

@swzgcd


South Wollo Zone Gov. Communication Department

03 Apr, 17:50


የተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ

South Wollo Zone Gov. Communication Department

30 Mar, 16:17


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተቸገርንበትና በሁለቱም እምነቶች ፆም ወቅት የምግብ ድጋፍ ማድረጉ የሕዝብ አለኝታነቱን ያሳያል ሲሉ በደጋን መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናገሩ፡፡

ደጋን - መጋቢት 21/2016 (ደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን)
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተቸገርንበትና በሁለቱም እምነቶች ፆም ወቅት የምግብ ድጋፍ ማድረጉ የሕዝብ አለኝታነቱን ያሳያል ሲሉ በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በደጋን መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዳቦ ዱቄት በኦሮሚያና በአፋር ክልል በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በደጋን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፉአድ መሐመድ ባንኩ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶችን ለማበረታታት የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በማኅበራዊ አገልግሎት ኃላፊነቱንም ለመወጣት ለችግረኞች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አክለዋል፡፡

በዚህም ከዞኑ ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በተገኘ መረጃ መሠረት ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደጋን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ 2 ሽህ ተፈናቃዮች ግምቱ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 300 ኩንታል የዳቦ ዱቄት ባንኩ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ከአሁን በፊት በአራት መጠለያ ጣቢያዎች 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ መደረጉንም አውስተዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቋሚነት እስኪቋቋሙ ድረስም ከመንግስት ጎን በመሆን ባንኩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርግም ጠቁመዋል፡፡

በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ተወካይ ቤተልሔም ብርሃኑ እንዳሉት ደግሞ ከ44 ሽህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች በሀገሪቱ ከተለያዩ ክልሎች ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎችና በማኅበረሰቡ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥም 35 ሽህ የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው ብለዋል፡፡

ለነዚህ ወገኖችም መንግስት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም አመላክተዋል፡፡ ይሁንና እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የምግብ፣ የመጠጥ ውኃና ሌሎች አስፈላጊና መሠረታዊ የሆኑ ድጋፎች ስለሚያስፈልጓቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጭምር ከመንግስት ጎን በመሆን የተቻላቸውን ያህል እንዲደግፉም ጠይቀዋል፡፡

አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት እንዲቋቋሙም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ስለመሆኑም የገለጹት ቤተልሔም ብርሃኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስላደረገው ድጋፍ በዞኑ አስተዳደር ስም አመስግነዋል፡፡

ከተፈናቃዮች መካከል መሐመድ እንድሪስና ኤሌኒ ኢብራሂም በነበሩበት አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ሰፊ ሐብታቸው እንደወደመ ተናግረዋል፡፡ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ ከመጡ ሦስት ዓመት እንዳለፋቸው ያስረዱት ተፈናቃዮቹ እስካሁን መንግስትና መንግስታዊ ልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ የምግብና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዳደረጉላቸው ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ባለፉት ወራት በክልሉ ባጋጠመ የሰላም መደፍረስ ጋር በተያያዘ ድጋፉ የተቆራረጠ በመሆኑ መቸገራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በችግርና በሁለቱም የእምነት ተከታዮች ጾም ወቅት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የምግብ ድጋፍ ማድረጉ ለሕዝብ ያለውን ወገንተኝነት ያመላክታል ብለዋል፡፡

መንግስት አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመልሳቸው ፍላጎታቸው እንደሆነ የገለጹት ተፈናቃዮቹ እስከዛውም ድረስ በዚህ አካባቢ ሠርተው ራሳቸውን የሚችሉበት መንገድ እንዲመቻችላቸውም ጠይቀዋል፡፡
*
የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ
መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግባቸው አማራጮች ቀጣዮቹ አድራሻዎች ናቸው። ሊንኮቹን በመጫንና በመወዳጀት ፈጣንና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት ቤተሰባችን ይሁኑ!

ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/Southwollozonecommunicationaffairoffice
ቴሌግራም፡ https://t.me/+zufNKt2lSgIwNGFk
ኤክስ ገጽ፡ https://twitter.com/WolloNews?t=Lrv74tG3nMkhl51mvR4_QA&s=09
ቲክቶክ - tiktok.com/@user6700427471177
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/p/Cb1bEhbK0hw/?utm_medium=copy_link
ዩቱዩብ፡ https://youtube.com/channel/UC5WAkOJxv-uE3HxyTQepVrA
ዌብ ሳይት፡ https://www.southwollocommunication.gov.et