======+====
የሞት ሞቴን ልፅፍ
ከነጩ ሜዳ ለይ ቃላትን ላነጥፍ
እየተሽቀዳደምኩ ሀሳበን ሳጣርስ
ሁሉም ፈለሱብኝ አጣው የልብ የሚደርስ።
በቀለም በብዕር በልኬት በምትር
በዘር በክልል በርስት በመንደር
አንቺን የሚመስል አጣሁኝ ሚታጠር።
አቤት ግዜ አቤት ቃላት፤
መጥበቤ ታወሰኝ እራሴን ታዘብኩት።
አቅልሜ ለክቼ
ብቆይም ለፍቼ
አንቺን እረሳውሽ ከሰፈር ገብቼ።
አልገርምም ነጩን አጨክይቼ
ነገርን በቁና ስሰፍር ቆይቼ
አነሳሴ ቢምር
እንደ መቶ ሜትር
አቦ ተሸነፍኩ እሩጫ ሳልጀምር።
በተቀበዣዠረ በማይሆን ስሜት
እፅፋለሁ ብዬ ፁፌንም አጣሁት።
አቤት ዳሌ አቤት ደረት
አቤት ቁመት አቤት ሠውነት
ጀመረኩኝ ጫወታ ከአካል ከጠጉርሽ
ኤጭ
እንደመንግስት መግለጫ ሁሉን ሸፋፍነሽ
አርቴፊሻል በሬ ወለደ ሆንሽ።
ዳሌሻን እያልኩኝ
ለምርጫ ቦርድ ሪፍረንደም ጣፍኩኝ
ፀጉርሽን እያልኩኝ
በሠላም ሚኒስተር ሠላሜን አጣሁኝ
ከንፈርሽን ብዬ እንደተጠጋሁኝ
በሁዳዴ በአብይ ፀም ረከስኩኝ።
በጠራራ ፀሀይ
እንዲያው ባደባባይ
መቀመጫ ኖሮ ብቀመጥ ከላይ
ሰው ሲቸገር አሿፊ አታላይ
ምሆን ይመስለኛል ሳስበው አንዳንዴ
ልክ እንዳልኩሽ ስገልጠው መውደዴ
መበልፀግ ነው ብዬ መዛለው ጎራዴ።
✍ምንተስኖት ሱሌይማን መሀመድ
ቀን፦12/04/2017