ከምስራቅ ሃረርጌ እስከ ህንድ ንጉስነት የዘለቀው ጀብድ
ከሰሞኑ የአንዱአለም ጎሳ ሙዚቃ የቢሊሌን ታሪክ ወደ ኃላ ተመልሰን እንድናስታውስ አድርጎናል።
ይህ ጀግኖቻችንን ፍለጋ አሁን ላይ ደግሞ ወደ መሊክ አምባር ወይም ዋቆ መዞር አለበት።
ከሐሮማያ ተነስቶ ህንድን ስለመራው ንጉስ አምበር መዘከሪያው ሰአት አሁን ነው።
በባርነት ከኦሮሚያ ተሽጦ ሄዶ የባርነትን ቀንዲል ደርምሶ ንጉስ የሆነ የኛው ጀግና መሊክ አምባር ዋቆ።
በህንድም ከ50,000 በላይ ወታደሮችን መርቷል ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆኖ ሃገሪቱን ገዝቷል።
በስልጣን ዘመኑም ለህንድ ሃገር እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳበረከት የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።
የሐሮማያው ተወላጅ መሊክ አምባር ከ1548 እስከ 1626 በምድር ላይ የኖረ ሲሆን ኦሮሚያ በነበረበት ወቅት ስሙ ዋቆ የነበረ ሲሆን በኃላ ላይ ይህ ስያሜው ወደ መሊክ አምባር እንደተቀየረ መረጃዎች ይጦቅማሉ።
ታድያ ከሰሞኑ አንዱአለም ጎሳ ቢሊሌን በሙዚቃው እንዳስታወሰን ማን ነው ጀግና ታሪክ አስታዋሽ ሙዚቀኛ ስለዚህ ጀግና ንጉስ መሊክ ወይም ዋቆ ሚዘክርልን።
መንግስት እነዚህን የመሳሰሉ ታሪኮቻችንን መንገድ በስማቸው በመሰየም፣ ሃውልት በማቆም፣ የፖስታ ቤት ቴምብር በእነሱ ስም በማዘጋጀት እና የተለያዩ ነገሮችን በስማቸው በማቆም ለቱሪዝሙ ዘርፍ እንዲረዳ መስራት አስፈላጊ ነው።
የባርነትን ቀንዲል የሰበረው የምስራቁ ሃረርጌ ንጉስ መሊክ አምባር ወይም ዋቆ።
✍️ ኢሳ ዩሱፍ