ፋና 90( Fana broadcasting corporate ) @ethifana_90 Channel on Telegram

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

@ethifana_90


ለኢትዮጵያውያን #እውነተኛ የመረጃ ምንጭ ብሎም #ማመሳከሪያ ለመሆን ስንሰራ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ነው፣
#ኢትዮጵያ_ብዙ_ይገባታል! #የመረጃ_ፍጥነት_መገለጫችን_

@ethifana_90

ፋና 90( Fana broadcasting corporate ) (Amharic)

ፋና 90( Fana broadcasting corporate ) ከተለያዩ ቢሮዎች ፣ ፐንዩች ፣ ድምፅዋም መንግስታት እና ከዚህነት አስመልክተናል ፡፡ ፊራም ብሔሮ (Fana Broadcasting Corporate) ለዘላቂ ሬዲዮ ቻናል የተለያዩ ፖሊስ መሆኑን በተመለከተ መረጃ፣ ድንቅ ስራዎችን ፣ የአስተዳደር የመንግሥት ግ ን ሊቀነስ የሚችል ሆኖ ባተረፈው ቻናሎች በሚገኘው አሰፋ ቻናሎች መመሪያ የሚሆነውን ሞዳሊዎች እና አስተካእታ ወደ ቻናል ቤተሰብና ቡድን ዝርዝር እያደገች ፡፡ ፋና 90 በፌስቢንከ እተመስርቶ The ቻናሉ ከአንድ ስነስር በኋላ ባሉት ይሁንታይ እና ብለታዊ ሀለውላት ላይ የሚሞታውን የሰርጉ እና ዌቶች አባልነት ያልጨካነውን እንዲሏት በነገሪቱ ላይ ያደረጉት የፈጠራ መጣህሚንበሬን ሕዝባዊ ስልቶችን ማበረታታቷት እና የሌሎች ትክክለኛ መልሶችን ለማግኘት በቅድሚያቸዋለው ፡፡

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

14 Jun, 07:34


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየሰጡት ባሉት ምላሽ÷ ባለፉት አራት ዓመታት የተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ልናሳካው ያሰብነውን ዕቅድ በታሰበለት ልክ እንዳይሄድ አድርገውታል ብለዋል፡፡ ያልተገነባ ሰው ተቋም አይገነባም፤ ያልተገነባ ተቋም ደግሞ ሀገር አይገነባም…

https://www.fanabc.com/ጠቅላይ-ሚኒስትር-ዐቢይ-አሕመድ-ለህዝብ-ተ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 17:46


የኑክሌር ኃይል ልማትን የተመለከተ አገር አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኑክሌር ኃይል ልማትን የሚመለከት አገር አቀፍ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ከቱርክ፣ ከኮሪያ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨሪሲቲ፣ ከማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የዘርፉ አስተባባሪ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ብሔራዊ የኑክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ…

https://www.fanabc.com/የኑክሌር-ኃይል-ልማትን-የተመለከተ-አገር/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 17:45


ኢትዮጵያና ኢኳቶሪያል ጊኒ የተፈራረሙት ስምምነት https://www.youtube.com/watch?v=g7XI0yoQuxA

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 17:45


በአማራ ክልል እየተወሰደ ያለው የህግ ማስከበር እርምጃ https://www.youtube.com/watch?v=MHQCfvbI5n0

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 17:44


በደሴ ከተማ በሕግ ሲፈለጉ የነበሩ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

በደሴ ከተማ በሕግ ሲፈለጉ የነበሩ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ   አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ አስተዳደር በቧንቧ ውሃ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በሕግ ሲፈለጉ የነበሩ ታጠቂዎች ይዘውት በነበረውን ቦንብ በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።   የ4ኛ ፖሊስ…

https://www.fanabc.com/በደሴ-ከተማ-በሕግ-ሲፈለጉ-የነበሩ-ታጣቂዎ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:40


በአቶ አደም ፋራህ የተመራው የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ የገርጂ መኖሪያ መንደርን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፍራህ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤትና የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ትናንት የተመረቀውን የገርጂ መኖሪያ መንደር ጎበኘ ። አመራሮቹ በገርጂ የመኖሪያ መንደር የኮርፖሬሽኑን መሪዎች የፕሮጀክት አመራር ብቃትና ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን አስፈላጊነት አይተንበታል ያሉ ሲሆን ፥…

https://www.fanabc.com/በአቶ-አደም-ፋራህ-የተመራው-የከፍተኛ-አመ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:39


በክልሎች በተዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሎች በተዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮዎች ባዘጋጁት መድረክ በአራት ረቂቅ ሕጎች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ረቂቅ ሕጎቹ በክልሎች የሚዘጋጁ የጠበቆች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት እና የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረቂቅ ሕጎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለፉት ሶስት አመታት የተሰሩ የሕግ ማሻሻያዎች እና የነበሩ ተግዳሮቶችም በመድረኩ ተነስተዋል፡፡

የፀረ ሽብር ሕግ፣ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዋጅ፣ የሚዲያ ሕግ፣ የጠበቆች አስተዳደር፣ የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች የአስተዳደር ስነ-ስርዓት፣ የጦር መሳሪያ የንግድ ህግ የተሻሻሉ ሕጎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ክልሎች ከፌደራል ሞዴል ሕጉ ጋር በማነጻጸር አካባቢያቸውን ታሳቢ በማድረግ አራቱ ህጎች ላይ ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ በመድረኩ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደውን ጨምሮ የክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በፈትያ አብደላ
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8e%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8b%98%e1%8c%8b%e1%8c%81-%e1%88%a8%e1%89%82%e1%89%85-%e1%88%95%e1%8c%8e%e1%89%bd-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%8d%e1%8b%ad%e1%8b%ad/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:17


ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ በገባችባቸው የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ከነዳጅ ሽያጭ 98 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በተጀመረ በ100 ቀናት ውስጥ ሩሲያ ወደ ውጭ በምትልከው ነዳጅ 98 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ተብሏል፡፡ ምዕራባውያን ሀገራት ሩሲያን ለማግለል እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን በርካታ የኢኮኖሚ ማእቀቦች በመጣል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቷን ለማቋረጥ ቢሞክሩም፥ ሞስኮ ከነዳጅ ሽያጭ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ማግኘት መቀጠሏን መቀመጫውን ፊንላንድ ያደረገ የሃይል እና…

https://www.fanabc.com/ሩሲያ-ከዩክሬን-ጋር-ግጭት-ውስጥ-በገባችባ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:17


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ ከፓርላማው ለሚነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል። ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ…

https://www.fanabc.com/ጠቅላይ-ሚኒስትር-ዐቢይ-ነገ-ከፓርላማው-ለ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:17


ኢጋድ እና ጣሊያን በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ከጣሊያን ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ። የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል። ዶክተር ወርቅነህ በዚህ ወቅት ጣሊያን የኢጋድ የረጅም ጊዜ ወዳጅና የኢጋድ አጋሮች ፎረም ሊቀ መንበር መሆኗን አስታውሰዋል።…

https://www.fanabc.com/ኢጋድ-እና-ጣሊያን-በቀጠናዊ-ጉዳዮች-ላይ-በ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

13 Jun, 10:16


አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ። አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም…

https://www.fanabc.com/አቶ-ደመቀ-መኮንን-ከጣሊያን-የውጭ-ጉዳይ-ሚ/

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

27 Jun, 08:07


አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ሁለት ሳምንታት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀሪ የግንባታ ስራዎች በማጠናቀቅ የውሃ ሙሌት እንደምትጀምርና በእነዚህ ሁለት ሳምንታትም ሃገራቱ ከስምምነት ለመድረስ መወሰናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና ውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ እየተካሄደ ባለው ድርድር ዙሪያ ምክክር መደረጉን አስታውሷል፡፡

በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በተጠራው በዚህ ስብሰባ ከሶስቱ ሃገራት በተጨማሪ የጉባኤው አባል የሆኑት ኬንያ፣ ማሊ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሪዎች መገኘታቸውን ጠቅሷል፡፡

መሪዎቹ የናይል እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳይ በመሆኑ ከአፍሪካ የሚመነጭ የመፍትሄ ሃሳብ እንደሚያስፈልገው ማንሳታቸውንም ገልጿል፡፡

በዚህ ረገድም የግድቡ ድርድር ስላለበት ሂደት ከኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ መግለጫዎች ቀርበው በቀጣይ ስለሚኖረው ሂደት አቅጣጫ ተቀምጧልም ነው ያለው፡፡

በዚህም በግድቡ ሙሌት እና አስተዳደር ላይ የሚደረገው ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲጠናቀቅም ከስምምነት መድረሳቸውንም ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን መመልከት መጀመሩ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲገለጥ የአፍሪካ ህብረት እና የመሪዎች ጉባኤ ቢሮ አባላት ድርድሩን እንዲደግፉ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብጽ ከቃላት መካረር እና አላስፈላጊ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አቅጣጫ ተቀምጦ ልዩ የመሪዎች ስብሰባ መጠናቁንም ነው የገለጸው፡፡
@ethifana_90

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

27 Jun, 08:05


ሰበር ዜና የግድቡ ሙሌት ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ምኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የታላቁ የኅዳሴ ግድብን ስምምነት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ከሁለት እስከ ሶስት ባሉ ሳምንታት ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

ትናንት ማምሻውን ለኢትዮጵያውያን ግርታ የሚፈጥር ዜና ከወደ ኻርቱም እና ካይሮ ከተሰማ በኋላ ዛሬ ማለዳ ምኒስትሩ "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች መፈለግ" በሚል መርኅ ሶስቱ አገሮች ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ "የግድቡ የውኃ ሙሌት ስምምነት እስኪፈጸም እንዲዘገይ ከስምምነት ተደርሷል" የሚል መግለጫ አውጥተዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ቢሮ የቴክኒክ ኮሚቴዎች በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ከስምምነት ለመድረስ ድርድራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከመሩት የቪዲዮ ኮንፍረንስ በኋላ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ሁሉም ወገኖች ስምምነት ሳይደረስ ግድቡን ውኃ መሙላትን ጨምሮ ምንም አይነት የተናጠል እርምጃ ላለመውሰድ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

12 Jun, 18:41


አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሰጠው የእፎይታ ጊዜ የወቅቱን ፈተና ለማለፍ ከማገዝ ባለፈ እንደ ሃገር ዴሞክራሲን መለማመድ እንድንችል አንድ እርምጃ ወደፊት የገፋ አጋጣሚ መሆኑን ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት በምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከሰጠው የእፎይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ኮቪድ19 አሁን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው ወረርሽኙ ለሁሉም የመጣ ከመሆኑ አንጻር በጋራና በሁሉም አቅጣጫ መዋጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ወረርሽኙ በተለይም በክረምቱ ወቅት ከፍ ያለ ጉዳት ያደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንስተው፥ ወረርሽኙ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ለ6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የሚደረገው ዝግጅት መስተጓጎሉን አውስተው አሁን ላይም ሃገር አቀፍ ምርጫው ውሳኔ ማግኘቱን አንስተዋል።
ህገ መንግስቱ በየአምስት አመቱ ምርጫ እንደሚካሄድ ይደነግጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ህገ መንግስታዊ አካሄድን ተከትሎ የቀረበለትን የህገ መንግስት ማሻሻያ ትርጉም ተመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል ብለዋል።
በዚህ መሰረትም አሁን ያሉት የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች የወረርሽኙ ስጋት ተቀርፎ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ እንዲቀጥሉና ምርጫው ከ9 እስከ 12 ወር ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ወስኗልም ነው ያሉት።
ሂደቱ የሃገራችን ዴሞክራሲ ራሱን በራሱ እያጎለበተ እንደሚሄድ ማሳያ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ክስተቱንም የወቅቱን ፈተና ከማለፍ ባሻገር እንደሃገር ዴሞክራሲን ለመለማመድ እንድንችል አንድ እርምጃ ወደፊት የገፋ ነው ብለውታል።
ማንኛውም ሃገራዊ ነገር ለህዝብ እንደሚደረግ አውስተውም፥ ምክር ቤቱ የሰጠው የእፎይታ ጊዜ ለፓርቲዎች ሳይሆን ውሳኔው ለህዝቡ ደህንነት የተላለፈ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ምርጫው ምርጫውን ለማከናወን ሲባል በሚከወኑ ሁነቶች ምክንያት የሚፈጠርን አደጋ ለመቀነስ በማሰብ መራዘሙንም አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲያብብ እና ሀገራዊ መግባባት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ገዢው ፓርቲ በቀጣይ ጊዜያት በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ እና እየተመካከረ መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል።
ምንም እንኳ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያየ አመለካከት ቢኖረንም ያለችን ሀገር አንድ በመሆኗ ለዚህች አንድ ሀገር ስንል በሰከነ፣ በሰለጠነና ነገን አርቆ በሚያይ በሳል ስሜት ውይይት እና ምክክር ማድረጋችንን አናቋርጥም ነው ያሉት።

በተለይም የሀገሪቱን መፃኢ ዕድሎች በሚወስኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ እየደረሱ ነገሮችን ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አሁን የትኛውም ተግባር ለአንድ የተወሰነ አካል ተጠቅልሎ የሚሰጥበት ወቅት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኮሮናቫይረስ በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና የመቀነስ ተግባር የሁሉም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የስራ ዕድል ፈጠራን መደገፍ፣ አዳዲስ የልማት እድሎችን መጠቀም፣ ግብርናው በተለየ መንገድ ሄዶ ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻል፣ አምራች ኢንዱሰትሪው ከውጭ የሚገባውን ምርት መቀነስ እንዲችል አቅሙን እንዲጨምር ማድረግ እና አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን መፈለግ የእያንዳንዳችን የቤት ስራ በመሆኑ በሀሳብና በስትራቴጂ የበኩላችንን መወጣት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ይህ ጉዳይ ሀገርን እንደ ሀገር ህዝብን እንደ ህዝብ ለማኖር የሚከናወን ሀገራዊ ስራ በመሆኑ ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች ሊሰሩበት የሚገባና ሀገሪቱን ከፈተና የሚያወጣ ምንገድ መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ ይገባናል ብለዋል።

መጪውን ምርጫ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና ተዓማኒነት ያለው ለማድረግ በጋራ በቂ ዝግጅት እያደረግን እንቆያለን ሲሉም ነው ያስታወቁት።

በዚህ ረገድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህብራት፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከታዋቂ ሰዎች እና ከሌሎች የሚመለከታቸው ሰዎች ጋር ኮሮናን የመከላከሉ ስራን በማያውክ መንገድ እንሰራለን ብለዋል።

በመንግስት በኩል ይህንን አጋጣሚ ሀገር እና ህዝብን ለማዳን ግዳጅ እንደተሰጠው፣ ሀላፊነት እንደተጣለበት አድርጎ ይቀበለዋል፤ አንደገዢ ፓርቲ እንደተጨማሪ የሀላፊነት ጊዜ ያየዋል ነው ያሉት።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔንን ሁላችንም በዚህ መልኩ ከተቀበልን፣ ምክር ቤቱ የህዝብን ደህንነት በበቂ ሁኔታ ለማስጠበቅ በማለም እንዳሳለፋቸውአድርገን ካመንን ከፊታችን መልካም ተግባር የምንፈፅምበት ጊዜ ተዘርግቷል ብለዋል።

በመሆኑም ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኢኮኖሚ ተዋንያን፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ የሀገር
ሽማግሌዎች እና የሚመለከታቸው ገንቢ ተግባር የሚያከናውኑ አካላት ጋር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ከፊትታችን የተጋረጠውን የኢኮኖሚ ቀውስ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደረስ በብቃት ለመወጣት፣ ሊደቀን የሚችለውን ረሃብና የምግብ እህል እጥረት ለመቋቋም እና ከሉዓላዊነት ጋር የተገናኙ ጥቃቶችን በቁርጠኝነት ለመመከት እና መጪውን ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ተዓማኒ ለማድረግ በጋራ ለመስራት ጥሪ አቀርበዋል።
@ethifana_90

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 11:42


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ ወሰኑ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት በዛሬው እለት የጋራ ስብሰባ አካሂደዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ በተካሄደው በጋራ ስብሰባቸውም 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተራዘመው የህዝብና ቤት ቆጠራ አሁንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለህዝብ ጤናና ደህንነት ሲባል ለሶስተኛ ማራዘም ማስፈለጉን ተገልጿል።

የምክር ቤቶቹ አባላት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቆጠራው እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳቡን በ5 ተቃውሞ፣ በ13 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቀውታል።

@ethifana_90

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 11:40


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በስብሰባውም የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በአንድ ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ተመልክቷል።



በረቂቅ አዋጀጁ ዙሪያ የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ፥ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በ2 ተቃውሞ፣ በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 11:39


አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ25 ነጥብ 8ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚደረግበት 15 መንገዶችን ከተለያዩ ተቋራጮች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

መንገዶቹ አንድ ሺ ሀያ ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ሲሆኑ÷ አንድ ከባድ የመንገድ ጥገናና አንድ የጠጠር መንገድን ጨምሮ ቀሪዎቹ በአስፋልት ደረጃ የሚገነቡ ናቸው ተብሏል።

መንገዶቹን ሰርቶ ለማጠናቀቅም እንደየ መንገዱ ሁኔታ ከአንድ አመት እስከ አራት አመት ጊዜን የሚወስዱ መሆናቸው ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ ከፍተኛ ህዝባዊ ጥያቄ ይነሳባቸው ከነበሩትን መንገዶች መካከል ወደ ግንባታ ለመሸጋገር በመብቃታቸው ለአገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያበረክቱ ት አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

ቀደም ብለው ከተፈረሙ መንገዶች መካካል በውላቸው መሰረት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ 20ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ እንዲሸጋገሩ መደረጋቸውን አብራርተዋል።



አያይዘውም 21የመንገድ ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን÷ በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የሚገኙ 15ፕሮጀክቶች ወደ ፍጻሜቸው እየተቃረቡ መሆናቸውን ዋና ዳሬክተሩ ገልጸዋል።

የእነዚህ 15 መንገዶች ግንባታ ወጪም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ፕሮጀክቱን ከፈረሙ 11ተቋራጮች መካከልም 7ቱ ሀገር በቀል ተቋራጮች ናቸውም ነው የተባለው ።
መንገዶቹ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙና በጠጠር ደረጃ የነበሩ ከመሆናቸውም ባለፈ ለተለያዩ እንቅስቃሴዎች ምቹ ያልነበሩና ለዘመናትም የህዝብ ጥያቄ ሆነው የቆዩ መሆናቸው ተነግሯል ።
በጥቅሉ የመንገድ ፕሮጀክቶቹ የጎን ስፋት በገጠር 10 ሜትር ሲሆኑ በዞን ፣ በቀበሌ ፣በወረዳ ፣እና በዞን እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ስፋት ይኖራቸዋል ተብሏል።

መንገዱ ሲጠናቀቅም በአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮና ኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ የተገለፀ ሲሆን ÷እንደ ሀገርም የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ለማሳለጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ የራሱን ጉልህ ሚና ይጫወታል ተብሏል።

በትዝታ ደሳለኝ

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 08:48


አሜሪካ በኮሪያ ጉዳይ ጣልቃ እንዳትገባ ሰሜን ኮሪያ አስጠነቀቀች።

በሁለቱ ኮሪያውያን ሃገራት መካከል ጣልቃ መግባት በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብላለች፡፡

አሜሪካ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ስላለው ግንኙነት አስተያየት መስጠት የሚያስችል መሰረት የላትም ስትል ሰሜን ኮሪያ ተናግራለች፡፡

ዋሽንግተን ቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያለ እንከን እንዲከናወን የምትፈልግ ከሆነ አደብ ገዝታ ልጥቀመጥ ይገባል ሲል የሃገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል ፡፡

መግለጫው የተሰጠው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ለት ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የነበራትን የግንኙነት መስመሮች በማቋረጧ ቅር መሰኘቱን ከተናገረ በኋላ ነው።

አሜሪካ የራሷን ችግር ሳትቀርፍ በሌሎች ሃገራት ጉዳይ ባትገባ መልካም ነው፡፡

ግድየለሽ አስተያየቶችን መስጠትም አይጠቅማትም፡፡ በሃገሯ ለተከሰተው የፖለቲካ ትኩሳት መፍትሄ ብታበጅ ይሻላታል።

አለበለዚያ ልትቋቋመው የማትችለው አስቸጋሪ ነገር ይገጥማታል›› ሲሉ በሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ክዎን ጆንግ ጉን ከብሄራዊ ዜና አገልግሎት KCNA ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ‹‹ምላሷን ብትሰበስብ›› ይሻላታል፡፡ አይ ካለች ግን ‹‹ቆሌዋን የሚገፍፍ›› ዱብ ዕዳ ይገጥማታል ብለዋል፡፡

ቆጠብ ማለት ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫም ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ምርጫውን ለማደናቀፍ አሊያም ዶናልድ ትራምድ ዳግም ለመመረጥ በሚያደርጉት ጥረት ላይ ምን ዓይነት ችግር ልትፈጥር እንደምትችል ግን አልተገለጸም ሲሉ ሴኡል በሚገኘው አሳን የፖሊሲ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ ጀምስ ኪም ተናግረዋል፡፡

@ethifana_90

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 08:47


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት ላይ እየተወያየ ነው።

የ2013 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት 476 ቢሊየን 12 ሚሊየን 952 ሺህ 445 ብር እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

በዚህም በ2013 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ ሥራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን ለፌዴራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች ብር 133 ቢሊየን 321 ሚሊየን 561 ሺህ፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 160 ቢሊየን 329 ሚሊየን 788 ሺህ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 176 ቢሊየን 361 ሚሊየን 602 ሺህ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 6 ቢሊየን በጠቅላላ ብር ነው የተያዘው።

የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት በተመለከተ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አቶ አህመድ ሺዴ በማብራሪያቸውም፦ የ2013 በጀት ግብዓትን ከውጤት ጋር የሚያዛምድ እንዲሁም ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

በ2013 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ የገንዘብ ሚነስትሩ አቶ አህመድ አክለው ተናግረዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚው ከገጠመው ተግዳሮት እንዲላቀቅ መንግስት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ቀርጾ በመተግበር ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅትም ከ2008 በጀት ዓመት ጀምሮ ተቀዛቅዞ የነበረው ኢኮኖሚ እያንሰራራ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት በተመለከተ በቀረበው የበጀት መግለጫ ላይ ከተወያየ በኋላ ለዝርዝር እይታ ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በመቀጠልም 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ለማቅረብ የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ስለማዛወር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁምን የሚያፀድቅ መሆኑን ከምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀቅድም ይጠበቃል።

ፋና 90( Fana broadcasting corporate )

11 Jun, 08:45


አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በምግባችን ከጓሯችን መርሃ ግብር ችግኝ ተክለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ያስጀመረውን የክረምት በጎ ፍቃድ አስመልክቶ ነው ምክትል ከንቲባው ከ50 የአዲስ አበባ ሰፈሮች የተውጣጡ 50 በጎ ፍቃደኞች ጋር በመሆን በመዘጋጃ ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ ተከላ ያካሄዱት።

በዛሬው እለት በተካሄደው የችግኝ ተከላ ላይ የተሳተፉት 50 ወጣቶች በየሰፈራቸው ችግኝ የመትከል ስራ የሚያስተባበሩ መሆኑም ታውቋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ብግሩ ላይም ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የከተማ ግብርና መርህ ያደረገና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የምግብ እጥረት ከወዲሁ ለመሙላት ምግባችን ከጓሯችን በሚል መርህ የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም የምግብነት ይዘት ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና መትከል እንደሚገባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

በፀጋዬ ንጉሱ
@ethifana_90