Daniel Broker @danielkibretdn Channel on Telegram

Daniel Broker

@danielkibretdn


ዲ/ን ዳንኤል ክብረት Dn Daniel Kibret

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት Dn Daniel Kibret (Amharic)

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት Dn Daniel Kibret በሰው እና ተስፋን የሚገኝ የሙያ ቻንሎች ላይ ተጠቃሚ በሆነ አማርኛ ድጋፍ እና ሥራ እንኳን ለመግባት የተጠቀሰ ስለዚህ በኢንተርኔት ፕሮፌሰር ክቡር እና አዳዲስ የኢስመር አገልግሎት ይላሉ. ለተጨማሪ መረጃ እና መዝገበ አስተማሪዎች ከታሪ አሰልጣኞች እና ለሁሉም የመናገር ግንኙነት፣ ንግግር እና ችግር እንዲሰጡ ይመረጣል።

Daniel Broker

25 Oct, 04:47


Channel photo updated

Daniel Broker

25 Oct, 04:45


Channel name was changed to «Daniel Broker»

Daniel Broker

12 Feb, 08:34


📝✔️️እውነተኛ  ፍቅር) ✏️❤️🔯📍1እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው፡፡ 📍2ለፍቅር ሁነኛ ማረጋገጫ እምነት ነው፡፡📍3ማንም ሰው አይናችን ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ነገር ግን ልባችን ውስጥ ዘልቆ የሚገባው አንድ ልዩ ሰው ነው፡፡📍4ራስህን እንድትሆን ለማይፈቅድልህ የፍቅር ወዳጅነት ራስን አሳልፈህ አትስጥ፡፡ 📍5በሌሎች የመፈቀርን ሀሰብ ከመውደድ በፊት፤ መጀመሪያ ራስን መውደድን ተማር፡፡📍6በማይረባ ድንጋይ ጊዚያቸውን እንዳባከኑ ሲገባቸው በእጃቸው የነበረው እንቁ እንደነበር ይገነዘባሉ፡፡ 📍7አንድን ሰው ለመልኩ ብቻ አናፈቅረውም፣ ለአለባበሱ ወይም ለምርጥ መኪናውም ልናፈቅረው አይገባም፤ የምናፈቅረው እኛ ብቻ ልንሰማው የምንችለውን ዜማ ስለሚያቀነቅኑ ነው፡፡📍8ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም ፣ ወይም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍም አይደለም ፣ ወይም ተቃቅፎ መታየም ሳይሆን ማንም ሊያስደስታችሁ በማይችልበት መንገድ ደስታን ሊፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው፡፡ 📍9ፍቅር እውር አይደለም ፣ ሌሎች በቀላሉ ሊያዩትን ያልቻሉትን ነገር እንዲያዩ የሚያስችል እንጂ!👍10ላረጋግጥልሽ የምፈልገው ነገር ቢኖር፣ ምን ያህል እንደምናፍቅሽና አንቺ ካጠገቤ ርቀሽ አለም ምን ያህል ባዶ እንደሆነችብኝ ነው፡፡     Share  ur  friends !!!!!!!!@loveDiary01   @loveDiary01   For any  comment inbox '''''''👉          💕  @habteshG 💕

Daniel Broker

12 Feb, 08:33


ፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል፡፡ በዚያ ጠንካራ ነፋስ ትከሻ ላይ ሲጫን ነው ንሥር ዕረፍት የሚወስደው፡፡ ክንፉን ብቻ ዘርግቶ በዕረፍት ስሜት ከደመና በላይ የኃያሉን ዐውሎ ዐቅም ተጠቅሞ ይንሸራሸራል፡፡

•••
አንተንም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- መከራንና ፈተናን አትፍራ፤ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና፡፡ መከራውንና ችግሩን፤ ፈተናውንና ግብግቡን የአዳዲስ ሐሳቦች መነሻ፤ የጥንካሬህ መለኪያ፤ ዐቅምህን የምትሰበስብበት አጋጣሚ፣ ወደላይ የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል አድርገው፡፡ እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ፤ ከችግሩም አትደበቅ፤ መከራን ለበረከት ተጠቀምበት፡፡

•••
ንሥር ሳይፈትን አያምንም፤ አይተማመንምም፡፡ ሴቷ ንሥር ባል ማግባት ስትፈልግ አንድ እንጨት ታነሣና ወንዱ እየተከተላት ወደ ላይ ትመጥቃለች፡፡ እስከ ሰማይ ጥግ ከደረሰች በኋላም ያንን እንጨት ትለቀዋለች፡፡ ያን ጊዜ ወንዱ እንጨቱ መሬት ከመድረሱ በፊት በፍጥነት በመወርወር መያዝና ለሴቷ መልሶ ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡ ሴቷም እንጨቱን ተቀብላ እንደገና ወደ ቀጣዩ ከፍታ ትመጥቅና እንጨቱን መልሳ ትጥለዋለች፡፡ አሁንም ወንዱ ንሥር ከእንጨቱ የውድቀት ፍጥነት ቀድሞ ያንን እንጨት በመያዝ ለሴቷ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ወንዱን ለሰዓታት ያህል ይጠብቀዋል፡፡ ከፍታው እየጨመረ፣ እንጨቱም ይበልጥ እየተወረወረ ይሄዳል፡፡ ሴቷ ንሥር ወንዱ ንሥር ፈጣንና የተወረወረለትን ለመያዝ ያለውን ቆራጥነት እስክታረጋግጥ ድረስ ፈተናው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ቆራጥና ፈጣን፣ ማንኛውም ችግር የማይበግረው መሆኑን ስታረጋግጥ ባልነቱን ትፈቅድለታለች፡፡

•••
ንሥርም እንዲህ ትልሃለች፡- በግላዊ ሕይወትህ፣ በንግድህም ሆነ በሌላው ኑሮህ ከሰዎች ጋር መወዳጀት፣ አብሮ መሥራትና መንገድ መጀመር ያለብህ ለዓላማቸው ምን ያህል ጽኑና ቆራጥ፣ ትጉና አይበገሬ መሆናቸውን አረጋግጠህ መሆን አለበት፡፡ ሳታረጋግጥ መግባት ትርፉ ፀፀት ነው፡፡ እንኳን ሌሎችን ራስህንም ለአዲስ ተልዕኮ ከማሠማራትህ በፊት ፈትነው፡፡

•••
ንሥር በሕይወቱ የሚመጡ ለውጦችን እንደመጡ በአጋጣሚ አይቀበላቸውም፡፡ ተዘጋጅቶና ዐቅዶ እንጂ፡፡ ሴቷ ዕንቁላል የመጣያ ጊዜዋ ሲደርስ ባልና ሚስቱ ዕንቁላል ለመጣያ ምቹና ተስማሚ የሆነውን ቦታ ያፈላልጋሉ፡፡ ያ ቦታ ማንኛውም ዓይነት ጠላት የማይደርስበት፣ ከከፍታዎች ሁሉ በላይ የሆነና ከማንኛውም ዓይነት አደጋ ራስንና ልጆችን ለመከላከል የሚመች መሆን አለበት፡፡ ቦታው በባልና ሚስቱ ከተመረጠ በኋላ ወንዱ ወደ መሬት ወርዶ እሾህ ለቅሞ ወደ ተራራው ንቃቃት ያመራል፡፡ በዚያም ይደለድለዋል፡፡ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ወርዶ አስፈላጊ የሆኑትን እንጨቶች ሰብስቦ ወደ ንቃቃቱ ይመጣና በእሾሁ ላይ ይረመርመዋል፡፡ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ምድር ይመለስና እሾህ ሰብስቦ ወደ ጎጆው ያመራል፤ በእንጨቱም ላይ ይረበርበዋል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ወደ መሬት ተመልሶም ለስላሳ ሣር ያመጣና በእሾሁ ላይ ያነጥፋል፡፡ በአምስተኛ ጉዞውም እሾህ አምጥቶ በሣሩ ላይ ያደርጋል፡፡ በስድስተኛ ጉዞውም በእሾሁም ላይ ሣር ይነሰንሳል፡፡ በመጨረሻውና በሰባተኛ ሥራው ላባዎቹን በመካከል ላይ ያደላድላቸዋል፡፡ በጎጆው ዙሪያ የተደረገው እሾህም ዙሪያውን ከጠላት ያጥርለታል፡፡

•••
እነሆ ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ምንጊዜም ለለውጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡ ነገሮች ድንገት እንዲደርሱብህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ አስበህ፣ ተዘጋጅተህ፣ ወስነህ፣ ሂሳብ ሠርተህ እንጂ፡፡ ኑሮህ በድንገቴና በአጋጣሚ የተሞላ አይሁን፡፡ የቻልከውን መጠን ያህል ተዘጋጅ እንጂ፡፡ መጽሐፉስ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› አይደል የሚለው፡፡ ለማደግ ተዘጋጅ፣ ለመማር ተዘጋጅ፣ ለጓደኝነት ተዘጋጅ፣ ለማግባት ተዘጋጅ፣ ለመውለድ ተዘጋጅ፣ አዲስ ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅ፣ ቤት ለመሥራት ተዘጋጅ፣ መኪና ለመግዛት ተዘጋጅ፣ ለምትለውጣቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ይኑርህ፡፡

•••
ንሥር ትዳሩን በእኩልነት ነው የሚመራው፡፡ ወንዱ ንሥር ጎጆውን ሠርቶ ሲጨርስ ሴቷ ወደ ጎጆው ትገባና ዕንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ ትዳርን በእኩልነት ነው የሚመሩት፡፡ እርሷ ዕንቁላል ስትጥል እርሱ ደግሞ አካባቢውን ከጠላት ይጠብቃል፡፡ ወደ መሬት እየተመላለሰም ምግብ ይሰበስባል፡፡ ልጆችን መመገብ፣ ማሳደግ፣ በረራ ማለማመድ፣ ከጎጇቸው ርቀው እንዲያድኑ ማሠልጠን የሁለቱም የጋራ ኃላፊነት ነው፡፡ ድርሻ ይካፈላሉ እንጂ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች አይሆኑም፡፡

•••
ስለዚህም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ትዳር የእኩልነት ጉዞ ነው፡፡ የሥራ ድርሻ ክፍፍል እንጂ የበታችና የበላይ ክፍፍል አይኖረውም፡፡ ሁሉም የችሎታውንና የተፈጥሮውን የሚያደርግበት፣ የጋራ ኃላፊነት የሚወሰድበት ቤት ነው ትዳር፡፡

•••
ንሥር ልጆቹን ደስታንም መከራንም ያስተምራቸዋል፡፡ የንሥር ጫጩቶች አምሮና ደኅንነቱ ተጠብቆ በተሠራው ጎጆ ይፈለፈሉና ወላጆቻቸው እየመገቧቸው እዚያ ጥቂት ያድጋሉ፡፡ ለዐቅመ ንሥር ሲደርሱ የምቾቱ ድልቅቂያ ያበቃና ሴቷ ንሥር ጫጩቶቹን ከጎጆዋ እያወጣች ዐለቱ ላይ ትጥላቸዋለች፡፡ ጫጩቶቹ በፍርሃት ይዋጡና ተመልሰው ወደ ጎጆው እየዘለሉ ይገባሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ማደፋፈሪያ ነው፡፡ የማያድሩበት ቤት አያመሻሹበትም ይባል የለ፡፡‹ሰው እናትና አባቱን ይተዋል› የሚለው በእነርሱም መጽሐፍ ላይ ሊኖር ይችላል ማን ያውቃል፡፡ ለጥቂት ጊዜያት እንዲህ ታለማምዳቸውና በቀጣዩ ጊዜ ከጎጆው አውጥታ ወደ ዐለቱ በመጣል የጎጆውን ለስላሳውን ክፍል ታነሣባቸዋለች፡፡ እነርሱም እንደለመዱት ወደ ጎጆው ሮጠው ዘለው ሲገቡ እሾሁ ይቀበላቸዋል፤ ያቆስላቸዋል፣ ያደማቸዋልም፡፡ እነርሱም እንዲያ የሚወዷቸው እናትና አባታቸው ለምን እንደሚያሰቃዩዋቸው ግራ እየገባቸው ወደ ዐለቱ ተመልሰው ይወጣሉ፡፡

•••
ከጎጆው ውጭ በአድናቆት መቆማቸውን የምታየው እናታቸው ከዐለቱ ገፋ ታደርጋቸውና አየር ላይ እንዲንሳፈፉ ትለቃቸዋለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አየሩን የቀዘፉት ጫጩት ንሥሮች በፍርሃትና በድንጋጤ ተውጠው ወደ ታች ሲወረወሩ አባታቸው ይመጣና ከመውደቃቸው በፊት ቀልቦ በትከሻው ተሸክሞ ወደ ዐለቱ ያወጣቸዋል፡፡ እነርሱም በደስታ ይዋኛሉ፡፡ እናት ስትወረውር፣ አባት በአየር ላይ ሲቀልብ፣ ልጆችም ሲወረወሩና ሲጨነቁ፣ አባታቸው ሲቀልባቸው ሲደሰቱ ጥቂት ጊዜያት ያልፋሉ፡፡ በአካል እየጠነከሩ፣ ከመከራውም ከደስታውም እየተማሩ፣ አካባቢውንም እየለመዱት ይሄዳሉ፡፡ በመጨረሻም ራሳቸውን ችለው ይበራሉ፡፡ ከወላጆቹ ጋር ኖሮ የሚያረጀውን እንደ ኡመሬ ያለዉን ቢያዩ ኖሮ ንሥሮች ምን ይሉ ይሆን? (ኡመሬ በድሬዳዋ ከተማ በተወለደበት በእናትና አባቱ ቤት አድጎ ስራ ይዞ፤ አግብቶና ወልዶ ጡረታም ከወጣ በኃላ አሁንም በወላጆቹ ቤት የሚኖር ወዳጃችን ነዉ፡፡)

•••
ለዚህ ነው ንሥር እንዲህ የሚለው፡- ለልጆቻችን ከልክ ያለፈ ክብካቤ መስጠት የትም አያደርሳቸውም፡፡ መከራውንም፣ ችግሩንም፣ ፈተናውንም፣ ትግሉንም፣ ተግዳሮቱንም እንዲለምዱት ማድረግ አለብን፡፡ አፈር አይንካህ፣ የፈሰሰ ውኃ አታቅና፣ ማንም በክፉ አይይህ፣ እንደ ዕንቁላል ትሰበራለህ፣ እንደ መስተዋት ትሰነጠቃለህ እያሉ ነገ በእውኑ ዓለም የማያገኙትን ቅንጦትና ምቾት ብቻ ማሳየቱ የትም አያድርሳቸውም፡፡ እሾሁንም፣ ዐለቱንም፣ መወርወሩንም፣ መውደቁንም፣ መታገሉንም፣ ማሸነፉንም ይልመዱት፡፡ ነገን በጥቂቱ ዛሬ እናሳያቸው፡፡ የሚወዱን ሰዎች ማለት የሌለ ገነት ፈጥረው የሚከባከቡን ማለት ብቻ አይደሉም፡፡ ሰው መሆን ለሚያጋጥመው ተግዳሮት ሁሉ ዝግጁ እን

Daniel Broker

12 Feb, 08:33


አስደናቂው "#የንሥር" ተፈጥሮ
[ በዲን ዳንኤል ክብረት ]
*★★★*

★ ንሥሮች ይታደሱ ዘንድ ዛሬ በድጋሚ ለጠፍኩት።

~ ውኃ እየተጎነጩ ቀስ ብለው የሚያነቡት ጦማር ነው። እርስዎ ማንበብ ከሰለችዎ በጽሑፉ የሚጠቀም ሌላ ሰው ይኖራንና ሳይሰስቱ ይኽን ጦማር #SHARE_SHARE እንዲያደር ይመከራሉ። ገለቶማ።

#ETHIOPIA | ~ ሰሞኑን የንሥር ምስል ያለበትን [ የአብን ] ዓርማ ያዩና የተመለከቱ ወገኖች ዓርማውን እንደተለመደው ከዚያ ከፈረደበት 666 ጋር በማያያዝ ግርግር ሊፈጥሩ ሲሞክሩ ባየሁ ጊዜ እኒህን ወገኖች ስለ ንሥር በቂ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ በአንድ ወቅት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ንሥር የጻፈው አስደናቂ ጽሑፍ ትዝ አለኝና ታነቡት ዘንድ አምጥቼ ለጠፍኩላችሁ። ረጋ ብላችሁ ደጋግማችሁ አንብቡት። ስለ እውነት ሁላችሁም ከጦማሩ እንደምታተርፉ ተስፋ አደርጋለሁ።

•••
ንሥር (eagle) እጅግ ግዙፍ ከሆኑ የአዕዋፍ ዝርያዎች አንዱ ነው፡፡ ክብደቱ እስከ 6.7 ኪሎ ሲደርስ ቁመቱ ደግሞ ከአንዱ ክንፉ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ 2 ሜትር ተኩል ይደርሳል፡፡ በዓለም ላይ እስከ ስድሳ የሚደርሱ የንሥር ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡

•••
በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ንሥር የትንሣኤ ሙታን፣ አርቆ የማሰብ፣ ወደ ላይ የመምጠቅና የመነጠቅ፣ የጥበቃና የምናኔ ተምሳሌት ሆኖ ተገልጧል፡፡ ግብጻውያን ደግሞ የተቀበሩ ሰዎችን አጋንንት እንዳይደርሱባቸው በመቃብራቸው በር በድንጋይ ላይ የንሥርን ምስል ያስቀርጹ ነበር፡፡ ይጠብቃቸዋል ብለው፡፡ በግሪክ አፈ ታሪክ የአማልክት ንጉሥ የሚባለው ዜውስ በንሥር የሚመሰል ነበር፡፡ ጥንታውያን የአሜሪካ ሕዝቦች እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው የንሥርን ላባ በመስጠት ክብራቸውንና ፍቅራቸውን ይገልጡ ነበር፡፡ ሞቼ የተባሉት የፔሩ ሕዝቦችም ንሥርን ያመልኩት ነበር ይባላል፡፡ ንሥር ይህንን ያህል ቦታ በሕዝቦች ባሕል ውስጥ ሊይዝ የቻለው በተፈጥሮው በታደላቸው የተለያዩ ጸጋዎች የተነሣ ነው፡፡

•••
ንሥር ከእንስሳት ሁሉ ወደ ሰማይ በመነጠቅ የሚስተካከለው የለም፡፡ እርሱ የሚደርስበትን የሕዋ ከፍታ የትኛውም ዓይነት ወፍ አይደርስበትም፡፡ አንዳንድ አዕዋፍ እስከ ተወሰነ ድረስ ቢከተሉትም እንኳ እርሱ ግን ጥሏቸው ማንም በማይደርስበት የሰማይ ጥግ ብቻውን ይንሸራሸራል፡፡ ለዚህም ነው ጥንታውያን ሰዎች በሐሳብ የመምጠቅ፣ ማንም ከማይደርስበት የጸጥታ ሕዋ ላይ አእምሮን የማሳረግ፣ ተራ ነገር ማሰብና ተራ ነገር መሥራት ከሚችሉ ደካማ ልቦች ርቆ በሉዓላዊ ሐሳብ ላይ የመምጠቅ ምሳሌ ያደረጉት፡፡

•••
ታድያ ይኼ ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ከቁራዎችና፣ ከሌሊት ወፎች፣ ከጥንብ አናሣዎችና ከድንቢጦች፣ ከተባዮችና ከነፍሳት ጋር እዚህ ምን ታደርጋለህ? በወረደ ሐሳብ ለምን ትመስላቸዋለህ? ውጣ ወደላይ፤ ሂድ ዐርግ፣ ምጠቅ ተመሰጥ፣ እስከ ተወሰነ ቦታ ድረስ ዝንብና ትንኝ፣ እስከ ተወሰነ ቦታ ድረስም ነፍሳት፣ እስከ ተወሰነም ቦታ ድንቢጦችና የሌሊት ወፎች፣ እስከ ተወሰነውም ቁራዎችና ጥንብ አንሣዎች ይከተሉህ ይሆናል፡፡ ሐሳብህን ከፍ፣ አእምሮህንም ሉዓላዊ፣ ልቡናህንም ምጡቅ፣ አመለካከትህንም ከፍ ያለ ባደረግከው ቁጥር ግን ደካሞቹ ከሥር እየቀሩ ከሚመስሉህ ከንሥሮች ጋር ብቻ በጸጥታው ሕዋ ላይ ትንሳፈፋለህ፡፤ሂድ ዐርግ፡፡

•••
ንሥር እጅግ አስደናቂ የሆነ የማየት ችሎታ የተሰጠው ፍጡር ነው፡፡ እስከ አምስት ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ውስጥ አንዲትን ትንሽ ጥንቸልን አንጥሮ ማየት ይችላል፡፡ የንሥር ዓይን ከጭንቅላቱ በተነጻጻሪ ሲታይ እጅግ ታላቅ ነው፡፡በንሥር ዓይን ውስጥ በአንድ ሚሊ ሜትር ስኩዌር ረቲና አንድ ሚሊዮን ለብርሃን ስሱ የሆኑ ሴሎች አሉት፡፡ ሰዎች ስንት ያለን ይመስላችኋል? ሁለት መቶ ሺ ብቻ፡፡ የንሥር አንድ አምስተኛ ማለት ነው፡፡ ሰው ሦስቱን መሠረታዊ ቀለሞች ብቻ ማየት ሲችል ንሥር ግን አምስቱን ማየት ይቻለዋል፡፡ እንዲያውም ከሩቁ አንጥሮ በማየት ንሥርን የሚተካከለው እንስሳ የለም የሚሉ ጥናቶችም አሉ፡፡
ንሥር የሚፈልገውን ለማሰስ እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ዙሪያ ይዞራል፡፡ ሲያገኝ ግን ሌላውን ነገር ሁሉ ትቶ በሚያድነው ነገር ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ ‹ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት› የሚለውን የአማርኛ ብሂልና ‹jack of every thing master of non› የሚለውን የእንግሊዝኛ አባባል በደመ ነፍስ ዐውቆታል፡፡ ከትኩረቱ ፈጽሞ ንቅንቅ የለም፡፡ ምንም ዓይነት ግርዶሽ፣ ምንም ዓይነት መሰናክል፣ ምን ዓይነት መደለያ አያዘናጋውም፣ ተስፋም አያስቆርጠውም፡፡ የዚያን የአደኑን ነገር በንቃትና በትጋት እስከ መጨረሻ ይከታተለዋል፡፡ እንዲሁ አይወረወርም፤ ጊዜና ሁኔታ ይመርጣል፡፡ ጊዜና ሁኔታ ሲገጥሙለት ትኩረቱን ሰብስቦ በመወርወር ታዳኙን ይሞጨልፈዋል፡፡

•••
ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ደጋግመህ አስብ፤ ለመወሰን ጊዜ ውሰድ፤ ዙር ተዟዟር፡፡ ልፋ ድከም፤ አንድ ጊዜ ለመቁረጥ ሺ ጊዜ ለካ፡፡ በመጨረሻም ዒላማህን ለይ፡፡ አስተካክል፡፡ ትኩረትህንም በዒላማህ ላይ ብቻ አድርግ፤ ምንም ዓይነት ማታለያ፣ ምንም ዓይነት መደለያ፣ ምንም ዓይነት ማሰናከያ፣ ምንም ዓይነት ፈተና፣ ምንም ዓይነት ተስፋ መቁረጥ ከዓላማህ ሊያግድህ አይገባም፡፡ ማየትና ማሰብ ያለብህ ሁሉም ሊያየውና ሊያስበው የሚችለውን ተራ ነገር አይደለም፡፡ ሊታይ የማይችለውን ለማየት፣ ሊለይ የማይችለውን ለመለየት፣ ሊተኮርበት ያልቻለውን ለማተኮር ጣር፡፡ ዒላማህን ካገኘህ አትልቀቅ፤ ጊዜና ሁኔታ አመቻችና ዒላማህ ላይ ተወርወር፡፡ ያንተ ከመሆን ማንም አያግደውም፡፡

•••
ንሥር በምንም ዓይነት የሞቱ እንስሳትን አይበላም፡፡ እርሱ እቴ፡፡ በሕይወት ያለውን እንስሳ የገባበት አሳድዶ፣ ከተደበቀበት ጠብቆ አድኖ ይበላዋል እንጂ እርሱ እንደ ቁራና ጥንብ አንሣ የሞተ ላይ አያንዣብብም፡፡ እንደ አራዳ ልጆች ከተበላ ዕቁብ ጋር አይጨቃጨቅም፡፡ ቀላል ነገር ቢያጣ በግና ፍየልም ቢሆን ተወርውሮ አድኖ፣ ከዐለት ላይ ፈጥፍጦ እንደ አጥንት ወዳጅ አበሻ ቅልጥም ሰብሮ ይበላል እንጂ የሞተ ጥንብ ሲያልፍም አይነካው፡፡ ያቺን ከባዷንና በድንጋይ የተሸፈነችውን ዔሊ እንኳን ከዐለት ስባሪ ላይ ከስክሶ ድንጋይዋን አራግፎ ይበላታል እንጂ እንደ አበሻ ማን እንዳረደው ያላወቀውን ነገር አይበላም፡፡

•••
ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ልቡናህንና ኅሊናህን፣ አእምሮህንና መንፈስህን ምን እንደምትመግባቸው አስብ፡፡ የሞተ፣ የማይሠራ፣ የተበላሸ፣ ጊዜው ያለፈበት፣ ቁራና ጥንብ አንሣ የሚጫወቱበትን አትመግበው፡፡ ፊልምና ፕሮፓጋንዳ፣ ዋዛና ፈዛዛ፣ የወረዱና የበከቱ አስተሳሰቦችን አትመግበው፡፡ ከተፋና ለብለብ ሐሳቦችን አትጋተው፡፡ ይልቅ አድን፣ ድከም፣ ልፋ፣ ተሟገት፣ ተመራመር፣ እንደ ዔሊ ድንጋይ የከበደውን አስተሳሰብ ገልብጠህ፣ ፈንክተህ ተመገብ፤ ድካምና፣ ጽሞና፤ ማሰብና መመርመር የሚሻውን ንባብ ውደድ፤ ሳይለፉና ሳይደክሙ እንደ ሞተ እንስሳ ሥጋ የትም የሚገኘውን ነገር ሳይሆን ጥረትና ግረት የሚሻውን፤ ላብ ጠብ የሚያደርገውን ሞያና እንጀራ ፈልግ፡፡

•••
ንሥር ዐውሎ ይወዳል፡፡ ሰማዩ ሲጠቁርና ደመናው ሲሰበሰብ ወጀቡም ሲያይል ሌሎች አዕዋፍ በዐለት ንቃቃትና በጫካው ችፍርግ ውስጥ ይደበቃሉ፤ በቤት ታዛ ሥርም ይሠወራሉ፡፡ ንሥር ግን ደስ ይለዋል፡፡ ወጀቡና ዐውሎው ሲጀምር ንሥር የንፋሱን ኃይል በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይለካበታል፡፡ የነፋሱን አቅጣጫ በመከተልም ይበራል፡፡ ራሱን ወደ ላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫ

Daniel Broker

12 Feb, 08:31


በአንድ ሀገር ውስጥ በጣም የታዋቀ አንድ ዐዋቂ ሰው ነበረ አሉ።ያንን ሀገር የሚገዛም ደግሞ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር አሉ።ህዝብ ወደዚህ አዋቂ ዘንድ ይሄድና ፤ "እባክህ እንደው ከፈጣሪ አማልደህ ይኼንን ክፉ ንጉሥ አስወግድልን" አሉት።
"ለምን ?"ብሎ ሲጠይቃቸው።
"በቃ አንፈልገውም ይወገድልን"አሉት።ዐዋቂም እሺ አለ።ክፉ ንጉሥም ተወገደ።ሌላ ንጉሥም መጣ።የመጣው ንጉሥም ደግሞ የባሰ ሆነ።ለውጡ ከጅራፍ ወደ ጊንጥ ሆነ።ሕዝብ አዲስ የመጣውን ንጉሥ ትንሽ ጊዜ ካየው በኃላ ወደ ዐዋቂው ዘንድ ሄዶ "ይኸንንም ንጉሥ አስወግድልን አለ።

ለውጡ ከጊንጥ ወደ እፍኝት ሆነ።ሁለተኛውም እንዲወገድ ሆኖ ሌላ ንጉሥ መጣ። ሦስተኛ የመጣው ንጉሥም ከመጀመርያው ከሁለኛውም ንጉሦች የባሰ ሆነ። ወዲያው ሕዝብ ዝም አለ።ንጉሡ ቢያደምጥ ዐዋቂው ቢያደምጥ፣ምንም ድምጽ ጠፉ።ሕዝቡ ዝም አለ። ወደ ንጉሡ የሚሄድ የለም ወደ ዐዋቂው የሚሄድ የለም።በዚህ ጊዜ ንጉሡ ወደ ዐዋቂው ዘንድ መልዕክተኛ ላከ። ወደ አንተ ጋ ሕዝብ መጥቶ ያውቃል?"
አዋቂው "አልመጣም ሲል መለሰ።

ንጉሡ ዕድሜው ይርዘም ብሎስ ያውቃል?"
አያውቅም"
ዕድሜው ይጠርስ ብሎ ያውቃል?"
"አያውቅም"
አሁን አደጋ ላይ ነን ፤አሁን ነው ህዝብን ማድመጥ"አለ ይባላል ንጉሡ።

፦"እናም ሕዝብ ዐውቆ ዝም ሲል ዝምታውን ማድመጥ ያሰፈልጋል ዝምታው ሌላ ወጀብ ይዞ ሳይነሳ ..........!

ምንጭ ፦ 👉ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች

ማንበብ የተሻለ ሰው ያገርጋል

Daniel Broker

06 May, 17:31


https://twitter.com/civil_security/status/1390348089936994304?s=19

Daniel Broker

09 Feb, 18:52


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን "አኖሬዎስ ንጉሥ" : "አባ ዳንኤል" : "ቅድስት ጣጡስ" : "ወአባ አቡናፍር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ቅዱስ አኖሬዎስ ወአባ ዳንኤል +"+

=>አኖሬዎስ የሚለው ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ተወዳጅ ነው:: በሃገራችንና በሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ተጠርተዋል:: ቅድሚያውን ግን ቅዱሱ ንጉሥ አኖሬዎስ ይወስዳል::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ተወልዶ ያደገው በሮም ከተማ ሲሆን የደጉ ንጉሥ ዐቢይ ቴዎዶስዮስና የመርኬዛ ልጅ ነው:: ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሙሽራው እና ደጉ አርቃዴዎስ ወንድሞቹ: ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ደግሞ አጐቱ ናቸው:: በልጅነቱ ክርስትናን የተማረው ከታላቁ ቅዱስ አርሳኒ ነው::

+ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ቅዱስ አርሳኒ እንደ ተራ ሰው እየገረፈና እየቀጣ አሳድጐታል:: ቴዎዶስዮስ ቄሣር (አባቱ) ባረፈ ጊዜ የሮም ግዛትን በስምምነት ከወንድሙ አርቃዴዎስ ጋር ተካፈሉ:: በ390ዎቹ አካባቢም አኖሬዎስ በሮም: አርቃዴዎስ በቁስጥንጥንያ ነገሡ::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ይሕንን ዓለም አልፈለገውምና ወደ ገዳም ልኮ አንድ ባሕታዊ (አባ አውሎጊስ ይባላል) አስመጥቶ ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸመ:: አክሊለ ሦኩንም በወርቅ ዘውዱ ውስጥ አደረገው::

+ልብሰ ምንኩስናውን በሰንሰለት በውስጥ አሥሮ በላዩ ላይ የመንግስቱን ካባ ደረበ:: ቀን ቀን እንደ ንጉሠ ነገሥት ሲፈርድ: ሲተች: የተበደለ ሲያስክስ: የተቀማ ሲያስመልስ ይውል ነበር::

+ሌሊት ደግሞ ባጭር ታጥቆ ሲወድቅ ሲነሳ: ሲጸልይ ሲሰግድ: ያለ ዕረፍት ያድራል:: መቼም ቢሆን ከደረቅ ቂጣ: ከጨውና ከጥሬ ጐመን በቀር ሌላ ምግብን አይቀምስም:: ይኸውንም ጾሞ ውሎ ማታ ብቻ ይመገብ ነበር::

+ይሕንንም ሲያደርግ ሰሌን ሰፍቶ: ያንን አሽጦ እንጂ በሌሎች ገንዘብ አልነበረም:: ሰዎች እንዳይጠረጥሩትም "በእልፍኙ ውስጥ ሚስት አለችው" እያለ ያስወራ ነበር:: በዚያ ላይ መልኩ ያማረ ስለ ነበር በዚህ የጠረጠረው የለም:: በዚህ መንገድ ከአባ አውሎጊስና ከደቀ መዝሙሩ ጋር ሆኖ ለ40 ዓመታት ተጋደለ::

+"+ አባ ዳንኤል ገዳማዊ +"+

=>በ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻና በ5ኛው መጀመሪያ በግብጽ ውስጥ ከነበሩ ከዋክብት አንዱ ሲሆን መንኖ ገዳም ከገባባት ቀን ጀምሮ በፍጹም ተጸምዶ: ከእህል ተከልክሎ: ቅጠል እየበላ ለ40 ዓመታት ተጋደለ:: አንድ ቀን ግን ተፈተነ:: በትዕቢት "ከእኔ የሚበልጥ ማን አለ?" ሲል በማሰቡ ፈጣሪ መልአኩን ልኮ ገሰጸው::

+ቀጥሎም "ሒድና ንጉሡን አኖሬዎስን እየው:: እሱ ንጉሥ ቢሆንም በቅድስና ይተካከልሃል" አለው:: አባ ዳንኤልም በደመና ወደ ሮም ሒዶ ቅዱሱን ንጉሥ ተገናኘው:: ቅድስናውን ዐይቶም ለቅዱስ አኖሬዎስ ሰገደለት:: እያለቀሰም ወደ በዓቱ ተመለሰ::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ግን ከመምሕሩ ቅዱስ አውሎጊስና ከደቀ መዝሙሩ ጋር መንግስቱን ትቶ: ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ ከአባ ዳንኤል ጋር ተቀመጠ:: ከተጋድሎ በሁዋላም 4ቱም ቅዱሳን በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

+"+ ቅድስት ጣጡስ ሰማዕት +"+

=>በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደዚህች ቅድስት ወጣት መልከ መልካም አልነበረም ይባላል:: ቅድስት ጣጡስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን (በዘመነ ሰማዕታት) የነበረች ሮማዊት ክርስቲያን ስትሆን መልኩዋን ያየ ሁሉ ይደነቅ: ይደነግጥም ነበር::

+እርሷ ግን ለወንድሞቿ እንቅፋት እንዳትሆን በፊቷ ላይ ዐይነ ርግብ ጣል አድርጋና እንደ ነገሩ ለብሳ ትኖር ነበር:: (እንዲህ ነበሩ እናቶቻችን!!!) ታዲያ በዘመኑ እስክንድሮስ የሚባል አረማዊ "ለጣዖት ስገዱ" እያለ ክርስቲያኖችን ሲገድል የእርሷ ተራ ደረሰ::

+በዐውደ ስምዕ (በምስክርነት አደባባይ) ላይ አቁሟት "ፊቷን ግለጡልኝ" አለ:: ቢገልጧት ከመልኩዋ ማማር የተነሳ ፈዘዘ:: እጅግ በመፍጠንም "ላግባሽ?" አላት:: "ሙሽርነቴ ሰማያዊ ነውና አይሆንም!" አለችው:: ለመናት: አልሰማችውም:: አስፈራራት: አልደነገጠችም::

+ከዚያ ግን ገላዋን አስገረፈ:: ከአካሏም ስለ ደም ፈንታ ወተት ፈሰሰ:: ተበሳጭቶ ለአራዊት ጣላት:: እነሱ ግን ሰገዱላት:: በእሳትም ፈተናት:: እርሷ ሁሉንም ታግሣ ጸናች:: በመጨረሻው ግን በዚህች ቀን አስገደላት:: ፈጣሪዋ ክርስቶስም በሰማያዊ አክሊል ከለላት::

+"+ ቅዱስ አቡናፍር ገዳማዊ +"+

=>ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት: አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር::

+ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል:: ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል::

+መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር:: ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ::

+እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት::

+ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም: ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በሁዋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ::

+ከብዙ ቀናት መንገድ በሁዋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም::

+ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ ክርስቶስ ነውና::

+አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ (በቀልት) በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ (ንጹሕ ምንጭ) ፈለቀች::

+ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ60 ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ በፍኑትዮስን (የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው) ላከላቸው::

+ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ምንጯም ደርቃለች::

=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን ያሳድርብን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን::

=>ኅዳር 16

Daniel Broker

09 Feb, 18:52


#የሐዲስ_ኪዳን_ጉባኤ_ተዘክሮ

#የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች_ ትርጓሜ

#"እርሱከመላእክትይበልጣል"

👉 #ክፍል(12)


በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን

👉https://youtu.be/CPKMi4MmsNUበዩቱብ በዩቱብ ለምትከታተሉ!

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn

Daniel Broker

09 Feb, 18:52


💠💠💠 ሰውና ዝንጀሮ ተዛዝነው በኖሩባት አገር ኢትዮጵያ ዛሬ
ሰው ሰውን የሚያርድባት ሆነች በቃ?!✟✟✟

ጻድቁ ብርሃነ ዓለም ተክለ ሃይማኖት በአካለ ሥጋ በህሉና መንፈስ ደብረ ሊባኖስ ሳሉ ደቀ መዛሙርታቸው ጥቂት ለቁመተ ሥጋ የሚሆኑ ጥራጥሬ ይዘሩ ነበር። በኋላ ዝንጀሮ እየመጣ እየበላ አስቸገራቸው። ሂደው ቢነግሯቸው "ልጆቼ ተዋቸው እኛ ወደ ጫካቸው መጣን እንጅ እኛ አልመጣንባቸው" ብለው ነበር የመለሱላቸው።

ዛሬ ይህንን ሳስብ ሥጋዊ ሆኜ እንባ እያጠረኝ ነው እንጅ አልቅስ አልቅስ ይለኛል። ምነው ለዝንጀሮ በተራራባት ሀገር ሰው በሰው ደም የሚታጠብ ሆነ!

በኋለኛውም በአስራ አራተኛው ክ/ዘመን የነበሩት የንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ወንድም አቡነ ዮሴፍ ይህንን የምሕረት ሥራ አድርገውታል።

ዛሬ አጽማቸው ባለበት ላስታ በሚገኘው ገደል ውስጥ እጅግ ብዙ ዝንጀሮዎች አሉ። እኔም ባለፈው ዓመት አይቻቸዋለሁ። ከዕለታት ባንዳቸው አንድ ገበሬ ዘር ዘርቶ እያረሰ ሲያለቅስ አቡነ ዮሴፍ አገኙት። ምን ሆነህ ታለቅሳለህ ቢሉት እናቴ ሙታ ሂጄ እንዳልቀብር ዘሩን ዝንጀሮ ሊበላብኝ ሆነ መተኪያ ዘር ደግሞ የለኝም አላቸው። እርሳቸውም ሂድ እኔ እጠብቅልሃለሁ ብለውት ቀብሮ ተመለሰ።

ከዚህ በኋላ አቡነ ዮሴፍ የሀገሩን ሰዎችና ዝንጀሮዎችን ይዘው ሽምግልና ተቀመጡ። እንዲህም አሏቸው።
ገበሬዎችን፦ እናንተ ቀድሙን(ቃርሚያውን) ጨርሳችሁ አታጭዱባቸው ስታጭዱ ጥቂት ለዝንጀሮዎች ተውላቸው። እነርሱም እጅ ነስተው ተቀበሉ።
ዝንጀሮዎችን፦ እናንተም እሸቱንና ክምሩን አትንኩ ሲያጭዱ ከሚተርፍላችሁ በቀር አሏቸው። ዝንጅሮዎችም ለጥ ብለው ሰግደው ትእዛዛቸውን ተቀበሉ። ይኼው ዛሬ ድረስ በዚያ አካባቢ ዝንጀሮ ሳርና ከመከር የቀረውን ይበላል እንጅ ዘር ወይም እሸት፣ ክምር፣ ስጦ አይበላም።

ዛሬ አንዱን ከአንዱ ከመንቆርና ከማናቆር በቀር ሽማግሌም የለም። እንኳንስ ለእንስሳት በሰው ደም ምቾት ሊያመጣ ደም የጠማው ትውልድ በዝቷል። ጠባያቸው የማይገናኝ ዝንጀሮና ሰው በተስማሙባት ሀገር ቋንቋየን አትመስልምና ልቀቅልኝ እያለ ሰው እንደ ጥራጊ የሚደፋባት የስግብግቦች ምድር ሆነች።

አክሱም ያሉ እናቶች አሁን ድረስ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ለወፎች ጥሬ ይዘው ይሄዳሉ። አጉራ ዘላዩ ትውልድ ደግሞ ወንድሙን እኅቱን የዋሃን ሕጻናትን እያረደ በእነርሱ መቃብር ላይ ቤት ሰርቶ መዝናናት ያምረዋል።

ኢቶዮጵያ እኮ በድርቅ ዘመን ራሳቸውን አቁስለው ከቁስላቸው ትሎች ለወፎች የመገቡ ቅዱሳን የነበሩባት ናት።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሳና ነብር እየመገቡ የኖሩባት ቦታ ናት። ምድረ ከብድ።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ አረጋዊ ዘንዶን መሰላል ያደረጉባት ሀገር ናት። ደብረ ዳሞ።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ ሳሙኤል አንበሳን መጓጓዣ ያደረጉባት ሀገር ናት። ዋልድባ።


ኢትዮጵያ እኮ እለ አባ አምደ ሥላሴ እሾህ የወጋውን አንበሳ የሚያወጡባት ሀገር ናት።

ኢትዮጵያ እኮ እለ እምነ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ለሰይጣን ምሕረት የለመኑባት ቤተ ሣሕል ናት!
ደብረ ምሕረት
በእውነት ሃይማኖት ይኑረውም አይኑረውም ምሕረት የሌለው ሰው ኢትዮጵያዊ ነኝ አይበል!

🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋
ለውሻ የራራሽ እመ ብርሃን ከውሻ ለከፋን ልጆችሽ ከመሐሪው ልጅሽ ለምኝልን። ለኢትዮጵያም የምሕረት ጠል አውርጅላት!
የምሕረት አሞላክ የሚራራ ልብ ይስጠን!እርሱም ይራራልን!
🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋
አባ ገብረ ኪዳን ነኝ ወልደ ምሕረታ ለቡርክት ማርያም!
ጥቅምት ፬ /፳፲፪ ዓም ስቶክሆልም!