THIQAH @thiqaheth Channel on Telegram

THIQAH

@thiqaheth


THIQAH (Arabic)

مرحبا بكم في قناة THIQAH على تطبيق تليجرام! هل تبحث عن مصدر موثوق للمعلومات والمحتوى القيم؟ إذا كانت الإجابة نعم، فأنت في المكان الصحيح. THIQAH هي قناة تليجرام مميزة تهدف إلى نشر المعرفة والمعلومات الهامة في مجالات متنوعة. سواء كنت تبحث عن نصائح صحية، أخبار تقنية، تحفيز يومي، أو أي شيء آخر يثري حياتك، فإن THIQAH هي القناة المثالية لك. يمكنك الاشتراك في القناة الآن لتبقى على اطلاع دائم بكل جديد ومفيد. انضم إلينا اليوم واستفد من المحتوى الذي نقدمه لك بشكل يومي. نحن هنا لتقديم المعرفة بطريقة ممتعة ومفيدة. انضم إلينا الآن وكن جزءًا من مجتمع THIQAH المتميز!

THIQAH

08 Feb, 13:11


የባንግላዴሽ ተቃዋሚዎች የቀድሞዋን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተሰብ መኖሪያ ቤት  "ማቃጠላቸው" ተሰምቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በአንድ ሌሊት በፈጸሙት ጥቃት የሼክ ሀሲና ደጋፊዎች ቤት እና ንብረት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡

የጥቃቱ መንስዔ የሼክ ሀሲና ደጋፊዎች የሽግግር መንግስቱን ለመቃወም አደባባይ ለመውጣት በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ማድረጋቸው ነው፡፡

የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲና በስደት ከሚገኙባት ህንድ ሆነው ስለተቃውሞው ንግግር ያደርፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ 

ተቃዋሚዎቹ ቤቱን ለማፍረስ ዶማና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይዘው የገቡ ሲሆን፤ ኤክስከቫተር መኪና ይዘው የገቡ መኖራቸውም ተዘግቧል፡፡
#Algezira

@ThiqahEth

THIQAH

08 Feb, 13:09


ትራምፕ "አናሳ ነጮችን ጨቁናለች" ባሏት ደቡብ አፍሪካ ላይ ማዕቀብ ጣሉ።

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በነጮች የሚተዳደር መሬት ያለ ካሳ እንዲወረስ የሚፈቅድ ህግ አፅድቋል። 

ደቡብ አፍሪካ እስራኤልን በጋዛው ጦርነት በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መክሰሷ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርን ማስቀየሙ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ኢራን ጋር በንግድ፣ ፀጥታ እና የኑክሌር ማበልጸግ ፕሮግራም የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈጸሟ በአሜሪካ ዘንድ አልተወደደም። #thenationalpulse

@ThiqahEth

THIQAH

08 Feb, 13:07


ከራዳር ተሰውሮ የነበረው አውሮፕላን ተከስክሶ ተገኘ።

የአሜሪካ ባህር ጠባቂ ኃይል የተሰባበረውን የአውሮፕላን ቅሪት ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል።

አውሮፕላኗ በአላስካ ግዛት 10 ሰዎችን ጭና የነበረ ሲሆን፣ ወንዝ ዳር ተከስክሳ ተገኝታለች።

አውሮፕላኗ ከአናክላት ወደ አላስካ እየበረረች በነበረበት ወቅት ነበር ከራዳር የተሰወረችው። #bernama

@ThiqahEth

THIQAH

07 Feb, 12:17


"ፍርድ ቤቱ በጋዛው ጦርነት በግልጽ ለፍልስጤም ያደላ አካሄድ ተከትሏል" - ትራምፕ

"የትራምፕን እርምጃ የፍርድ ስራየን በገለልተኛ እና ያለአድልዎ እንዳልሰራ ጫና ይፈጥርብኛል" - ICC

ትራምፕ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። ተቋሙ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ቤተሰቦች ወደ አሜሪካ እንዳያቀኑ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዜዳንቱ ማዕቀቡን የጣሉት ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ፣ ''ወዳጅ ሀገር'' ሲሉ በጠሯት እስራዔል ላይ የሚያራምደው አቋም የተዛባ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡  

"ፍርድ ቤቱ በጋዛው ጦርነት በግልጽ ለፍልስጤም ያደላ አካሄድ ተከትሏል" በማለት ወቅሰዋል፡፡ 

የዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒም ኒታንያሁ በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በማለት የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ፣ ትራምፕ ፍርድ ቤቱ ላይ በጣሉት ማዕቀብ መደሰታቸውን ገልጸው ፕሬዝዳንቱን አመስግነዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የትራምፕን እርምጃ የፍርድ ስራየን በገለልተኛ እና ያለአድልዎ እንዳልሰራ ጫና ይፈጥርብኛል ብሏል፡፡ 

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቫንደርሊን በበኩላቸው የትራምፕ ውሳኔ አለማቀፍ ፍትህ እንድጠፋ ያደርጋል ሲሉ ተችተዋል፡፡
#thedefensepost   #ashraqalawusat #irishnews

@ThiqahEth

THIQAH

07 Feb, 11:19



#Update #Ethiopia

ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ።

ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ ተገልጾ ነበር።

በዚህ መሰረት ቁጥራቸው 88,717 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸው ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡

እስከ አሁን ድርስ የህትምት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የህትምት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተባለ ሲሆን የሲስተም መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሲስተም ማሻሻያዎችን ማከናውን፣ የህትመት እና ስርጭት ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተጨማሪ የህትመት ማሽኖችን ወደ ስራ ማስገባት እና አትሞ በፍጥነት ማሰራጨት እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

@ThiqahEth     @tikvahethiopia

THIQAH

07 Feb, 07:15


"2,000 አስክሬኖችን ሰብስቢለሁ። 900 የሚሆኑት ሆስፒታል ተልከዋል" - ድርጅቱ

በምሥራቅ ኮንጎ የሟቾች ቁጥር 3,000 እንደሚጠጋ ተ.መ.ድ አስታውቋል።

ተ.መ.ድ ከኤም 23 ጋር በመተባበር እስካሁን "2,000 አስክሬኖችን ሰብስቢለሁ" ያለ ሲሆን፣ "900 የሚሆኑት ወደ ሆስፒታል ተልከዋል" ብሏል፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በ"አማጺው ኤም 23 ቡድን" መካከል የተደረገው ጦርነት ከፍተኛ ወውድመት ማስከተሉን በሀገሪቱ የሚገኘው የተ.መ.ድ ተልዕኮ ምክትል ኃላፊ ቪቪያን ቫንድ ፒር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት "አማጺ ቡድኑ" በተቆጣጠራት የጎማ ከተማ ወረርሽኝ ስጋት መኖሩን ጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ለአንድ ሳምንት የዘለቀውን ዘመቻ በመግታት ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አውጇል፡፡
#voiceofamerica

@ThiqahEth

THIQAH

06 Feb, 08:31


''በደቡብ አፍሪካ ጸረ-አሜሪካዊነት ተስፋፍቷል''  - ማርክ ሩቢዮ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ፣ ደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳለፍነው ረቡዕ በደቡብ አፍሪካ ''አዲስ የመሬት አጠቃቀም ህግ'' ያስፈልጋል ማለታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት እንድሰፍን ምክንያት ሆኗል፡፡

ትራምፕ የራማፎዛ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ መሬት ያለ አግባብ እየወረሰ ነው ሲሉ ወንግለዋል። ፡፡

በጆ ባይደን አስተዳደር በነጩ ቤተመንግስት ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አንድሪው ባቲ፣ ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ ላይ ማራመድ የጀመሩት ፖሊሲ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነነት የሚጎዳ ነው በማለት ተችተውታል፡፡ #newsbytes

@ThiqahEth

THIQAH

06 Feb, 08:28


"ዓለማቀፍ ተቋማት በሉዓላዊነታችን ጣልቃ እንዲገቡ አንፈቅድም'' - አርጀንቲና

አርጀንቲና ከዓለም ጤና ድርጅት እንደምትወጣ ማስታወቋ ታውቋል።

ፕሬዝዳንት ዣቪየር ሚሌ አርጀንቲና በዓለም ጤና ድርጅት የሚኖራትን ተሳትፎ እንድታቆም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጀራርዶ ወርዚን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ፣ ''ዓለማቀፍ ተቋማት በሉዓላዊነታችን ጣልቃ እንዲገቡ አንፈቅድም'' ብለዋል፡፡

የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ማኑዌል አዶርኒ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ የገለልተኝነት ችግር ይታይበታል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

የአርጀንቲና ከዓለም ጤና ድርጅት የመውጣት ሃሳብ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከድርጅቱ እንደምትወጣ ከገለጹ ከሳምንት በኋላ ነው፡፡    #aninews

@ThiqahEth

THIQAH

06 Feb, 08:23


ኤለን መስክ የአቬሽን ዘርፉ ገጠመውን ችግር ለመፍታት እንሰራለን አሉ፡፡

ቢሊየነሩ መስክ የሚመሩት የመንግስት አቅም ድፓርትመንት (DOGE) በአቬሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ የደህንነት ችግሮችን ለመቅረፍ ማስተካከያ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

መስክ በግል የኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የአሜሪካ አውሮፕላኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የመከስከስ አደጋ እየገጠማቸው መሆኑን ከፌደራል አቬሽን ባለስልታን ማወቅ ችያለሁ ብለዋል፡፡

ከቀናት በፊት የፌደራል አቬሽን ባለስልጣን የቅድመ አየር መንገድ ደህንነት መግለጫ ሲስተም ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ክስተቱ የደህንነት ስጋትን ፈጥሯል ያሉት መስክ፤ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በመሆን የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ማሻሻያዎች እንደደረጉ እንሰራለን ሲሉ አብራርተዋል፡፡ #dailypost

@ThiqahEth

THIQAH

05 Feb, 16:46


#Ethiopia

"አንድ ታዳጊ ወጣት ተገሏል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል" - የሹፌሮች አንደበት

"ምን አጠፋን? ምን እናድርግ? ህግና መንግስት አለ ብለን ነው በትግስት እየጠበቅን ያለነው የ200 ብር ትራንስፖርት 1000 ብር ከፍለን በየ ቦታው ተሳቀን አሁን ገደሉን፣ አቆሰሉን እያልን፤ ያሳዝናል።

ዛሬ 28-05-2017 ጠዋት 2፡10 ከገንዳውሃ ጎንደር እየተጎዝነ ከ10 በላይ አባዱላ ተዘርፎል በጣም የሚያሳዝነው አንድ ታዳጊ ወጣት ተገሏል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል።

እስከመቼ ይሄ ጉዳይ? እንደ ክልል የፀጥታ ችግር ስላለ በትግስት መመልከት ስለሚገባ ሁሉም በየቀኑ እየሞትንና ደም እያነባን ዝም አልን እስከመቼ?

ከገንዳውሃ እስከ ጎንደር ያለው መንገድ ከዚህ በፊት አብዛኛውን ጊዜ የማዕከላዊ ጎንደር የፀጥታ ችግር ይበዛ ነበር። አሁን ግን እነሱ አስተካክለው መንገዱን ሰላም ሲያደርጉ ምዕራብ ጎንደር በእጅጉ ብሷል ለምን?

ትኩረት ለምዕራብ ጎንደር ዞን። የፀጥታ መዋቅር ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ችግሩን ባፋጣኝ እንዲስተካከል ሀሳቤን እያለቀስኩ አካፍላለው። ጎንደር አውሮፖ ሆነብን"
ሲል የሹፌሮች አንደበቶ አስታውቋል።

@ThiqahEth

THIQAH

05 Feb, 15:42


#Ethopia

በትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።

አደጋው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከቆቦ ከተማ ወደ ድሬዳዋ ሲያመራ ከነበረ ዶልፊን ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተፈጠረው አደጋም የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

#ThiqahEth

THIQAH

05 Feb, 15:38


''ቤታችንን ለቀን አንሄድም'' - ፍልስጤማውያን

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከእስራዔሉ አቻቸው ጋር በተገናኙበት ወቅት አሜሪካ በመልሶ ማልማት እቅድ ጋዛን ማስተዳደር እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ ይደረጋል ማለታቸው፤ ነዋሪዎቹን አስቆጥቷል።

ቁጣቸውን ከገለጹ ፍልስጤማውያን መካከል ሳሚር አቡ ባዝል የተባለ የጋዛ ነዋሪ፣ ''ትራምፕ ከነሀሳቡ፤ ከነአመለካከቱ ሲዖል ይግባ፤ የትም አንሄድም፤ እኛ የእሱ የእጅ ገንዘብ አይደለንም'' ሲል ቁጣውን አሰምቷል፡፡

ለፍልስጤም እታገላለሁ የሚለው የሀማስ ቡድን፣ ''ፍልስጤማውያንን የሚጨቁን እና ለቀጠናው መረጋጋት አስተዋጽኦ የማያደርግ'' ሲል ነቅፎታል።

ሳውድአረቢያን ጨምሮ አንዳንድ የአረብ ሀገራት ደግሞ የትርምፕን አስተያየት አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ተቃውመውታል፡፡  

በተመሳሳይ መልኩ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው ፍልስጤማውያንን የማዘዋወር እቅድ አውግዘዋል፡፡

በርካታ ፍልስጤማዊያኑም፣ "ቤታችንን ለቀን አንሄድም" ሲሉ ከወዲሁ ሞግተዋል።
#anadoluagency #trtworld #easterneye

@ThiqahEth

THIQAH

05 Feb, 10:44


የአፍሪካ ልማት ባንክ በማዕድን ግብይት እንዲፈጸም የሚያስችል እቅድ አቀረበ፡፡

ባንኩ፣ ''የወርቅ ደረጃ'' ሲል የገለጸው የመገበያያ ዘዴ የአህጉሪቱ ሀገራት ማዕድን ላይ የተመረኮዘ የግብይት ማስተካከያ ላይ እንዲያተኩሩ አሳስቧል፡፡

እንደባንኩ መረጃ ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ የተፈጥሮ ማዕድናት 30 በመቶ የሚሆነው አፍሪካ ውስጥ ይገኛል፡፡

እቅዱ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ሀገራት ቅድመ ስምምነት የተደረገበት የማዕድን ሀብት መጠን ሊያሟሉ እንደሚገባ ባቀረበው እቅድ ገልጿል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲስ ያቀረበው እቅድ የአፍሪካ ሀገራት የሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘባቸውን በሌሎች ሀገር ማዕድናት በመለወጥ የንግድ ስርኣትን ማቀላጠፍ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
#iaafrica

@ThiqahEth

THIQAH

05 Feb, 10:42


''የሚጣልብንን የቀረጥ ስጋት ማሰብ ከሚጣልብን ቀረጥ በላይ ይጎዳናል'' -  ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር

ማሌዥያ የአሜሪካን ቀረጥ ሳያሳስባት የንግድ ልውውጡዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ሀገራቸው ከቻይና፣ ሩሲያና ብራዚል ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

አንዋር የአሜሪካ፣ ''ታሪፍ ሊያመጣብን የሚችለውን ጫና ፈርተን ከሌሎች ሀገራት ጋር የምናደርገውን የንግድ ግነኙነት አናቋርጥም'' ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ለፓርላማ አባላት ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ ''የሚጣልብንን ቀረጥን ስጋት ማሰብ ከሚጣልብን ቀረጥ በላይ ይጎዳናል'' ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ #asiaone

@ThiqahEth

THIQAH

04 Feb, 14:16


''ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አውጃለሁ'' - ኤም 23 ቡድን

ኤም 23 ቡድን ጊዚያዊ የተኩስ አቁም ማወጁን ገለጸ።

በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገርለት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ "አማጺ ቡድን" ''ጊዚያዊ የተኩስ አቁም አውጃለሁ'' ብሏል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለአንድ ሳምንት በቆየው ጦርነት ከ900 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን የተ.መ.ድ የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡    #france24

@ThiqahEth

THIQAH

04 Feb, 13:18


ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ተጨማሪ ቀረጥ ጣለች፡፡

በፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርቶቿ ላይ የ10 በመቶ ታሪፍ የተጣለባት ቻይና ከአሜሪካ በምታስገባቸው የድንጋይ ከሰል እና ነዳጅ ዘይት ላይ የ15 በመቶ ታሪፍ መጣሏን አስታውቋለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በግብርና ማሽኖች፣ ረዥም ተሸከርካሪዎቨች እና ፒክ አፕ መኪኖች ላይ የ10 በመቶ ጭማሪ አድርጋለች፡፡

ከቻይና እና ሜክሲኮ ጋር ታሪፍ ተጥሎባት የነበረችው ካናዳም በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ጭማሪ በማድረግ የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች፡፡
#asianews

@ThiqahEth

THIQAH

29 Jan, 15:24


ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ 20 ሰዎች ህይታቸው አለፈ፡፡

በአደጋው 17 ደቡብ ሱዳናዊ፣ ሱዳናዊ እና አንድ ቻይናዊ ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን የደቡብ ሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ጋትዎች ቢፓል ተናግረዋል፡፡

ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ሁለቱ የበረራ አባላትና አንድ ህንዳዊ እንዲሁም አንድ የሀገሪቱ ዜጋ ከአደጋው ተርፈው ወደ ሆፒታል መላካቸውን የጁባ ዓለማቀፍ አየር መንገድ ዳይሬክተር ኢንጅነር ሳልህ አኮት ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ተጓዦች ግሬተር ፒዎነር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ (GPOC) የተባለ የነዳጅ ዘይት ካምፓኒ ሠራተኞች እንደነበሩ ተነግሯል።

ሠራተኞቹ ለ28 ቀናት በሥራ ቆይተው ከዩኒቲ ግዛት እየተመለሱ በነበረበት ወቅት አደጋው እንደተፈጠረ ሚኒስትሩ ለራዲዮ ታማዙጂ አረጋግጠዋል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የአቪየሽን ባለስልጣን ስለሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁ ተዘግቧል፡፡ #Anadolu #Shine #Reuters

@ThiqahEth

THIQAH

29 Jan, 12:34


"በፈቃደኝነት ሥራ ለሚለቁ የመንግስት ሠራተኞች የ8 ወራት ደመወዝ እንከፍላለን" - ትራምፕ
 

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያሳለፉት ውሳኔ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችንና ሠራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የያዙት ዕቅድ አካል ነው ተብሏል።

ፕሬዜዳንት ትራምፕ፣ "በፈቃደኝነት ሥራ ለሚለቁ የመንግስት ሠራተኞች የስምንት ወራት ደመወዝ እንከፍላለን" ማለታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

የትራምፕ አስተዳደር ለፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች በላከው ኢሜይል በፕሮግራሙ መካተት የሚፈልጉ ሠራተኞች እስከ ጥር መጨረሻ ቀነ ገደብ እንደተሰጠ እና ደመወዛቸውን ለመክፈል ቃል እንደተገባላቸው ያሳያል።

በአሜሪካ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ የፌደራል መንግስት ሠራተኞች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 10 በመቶ የሚደርሱት ሠራተኞች ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@ThiqahEth

THIQAH

28 Jan, 19:20


ካናዳ ለውጭ ዜጎች ስትሰጠው በነበረው የትምህርት እድል ላይ ገደብ መጣሏ ተሰምቷል፡፡

አዲሱ ውሳኔ ከውጭ ሀገር ወደ ካናዳ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ያለመ ነው ሲል የካናዳ የስደተኞች፣ ዜግነት ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በካናዳ የውጭ ሀገር ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በሀገሪቱ የመኖሪያ ቤት እጥረት እንድያጋጥም እና የጤና አጠባበቅ ስርዓቱ ተመጣጣኝ እንዳይሆን አድርጎታል ብሏል፡፡

በ2025 በካናዳ የትምህርት እድል የሚያገኙ የውጭ ዜጎች ባለፈው አመት እድሉን ካገኙት ጋር ሲነጻጸር 10 በመቶ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡ #legit

@ThiqahEth

THIQAH

28 Jan, 19:17


ማይክሮሶፍት የቻይናውን ቲክቶክ ለመግዛት ንግግር ጀምሯል ተባለ፡፡

ሁለቱ ኩባንያዎች በሽያጩ ዙሪያ እየተነጋገሩ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሀገራቸው ኩባንያዎች ቲክቶክን ለመግዛት "የጨረታ ጦርነት" ሲያደርጉ ማየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ ንብረት የሆነውን ቲክቶክ በባይደን አስተዳደር ታግዶ የነበረ ሲሆን፤ ትራምፕ በመጡ በአንድ ቀን ውስጥ ወደ አገልግሎት ተመልሷል፡፡

ባይትዳንስ 170 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ደንበኞች ያሉትን ቲክቶክ ለአሜሪካ ኩባንያዎች ከመሸጥ ይልቅ ቢታገድ እንደሚመርጥ ገልጾ ነበር፡፡ #theguardian

@ThiqahEth

THIQAH

28 Jan, 19:15


ኮካ ኮላ በሦስት የአውሮፓ ሀገራት ያሰራጫቸውን የመጠጥ ምርቶች እንዲሰበሰቡ ጠየቀ፡፡

ካምፓኒው የመጠጥ ምርቶቹ እንዲሰበሰቡ የጠየቀው ከጤና ጋር የተያያዘ የደህንነት ችግር ስላለባቸው ነው ብሏል፡፡

ኮካ፣ ''ክሎሬት'' የተባለው የኬሚካል መጠን ከፍተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኬሚካሉ በካምፓኒው ስር በሚመረቱ ሦስት ምርቶች ማለትም በኮካ፣ ስፕራይት እና ፋንታ ምርቶች ላይ እንዳለ ተገልጿል።

ሀገራቱ ቤልጀም፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድ ሲሆኑ፣ ወደ እንግሊዝ የተከፋፈሉት ምርቶች ተጠቃሚዎች ዘንድ ስለደረሱ መመለስ አልቻልኩም ሲል ገልጿል፡፡ #associatedpress

@ThiqahEth

THIQAH

28 Jan, 19:12


ህዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሰርቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስለጣን መልቀቃቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሎስ ቫቼቪች በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቀሰቀሰውና ለሁለት ወራት የዘለቀውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሀይል ለመግታት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡

ተቃውሞው በአርሶ አደሮችም ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ምርቶች ወደ ከተማ እንዳይገቡ እገዳ በመጣል ትግሉን ተቀላቅለዋል፡፡

ቫቼቪች፣ ''በማህበረሰቡ ዘንድ ውጥረቶች ተባብሰው እንዳይቀጥሉ በማሰብ ከላይ የገለጽኩትን ውሳኔ አሳልፊያለሁ'' ሲሉ ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን በይፋ አረጋግጠዋል፡፡ #politico

@ThiqahEth

THIQAH

24 Jan, 18:41


የናይጄሪያ ጦር 31 አሸባሪ ኃይሎችን መግደሉን አስታወቀ፡፡

ጦሩ አንድ ከፍተኛ የታጣቂ ኃይል አዛዥን ጨምሮ 31 ታዋጊዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ሲል ገልጿል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ታጣቂዎች በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛቶች በዛምፋራና ሶኮቶ ውስጥ በርካታ ጥቃቶችን በማድረስ፤ ንጹሃንና የጸጥታ ኃይሎችን ሲገድሉ ነበር ሲል አስታውቋል፡፡

ከ2023 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዙ ጥቃቶች 615,000 ዜጎች እንደተገደሉ የናይጄሪያ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ አመላክቷል፡፡ #aa

@ThiqahEth

THIQAH

24 Jan, 18:37


''ፑቲን የኑክሌር ክምችቶችን የመቀነስ ሀሳብን ይደግፋል''  - ትራምፕ

ዶያልድ ትራምፕ ከሩሲያና ከቻይና ጋር የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ክምችትን በመቀነስ ላይ ለመነጋገር ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውን ተከትሎ ፑቲን በአወንታዊ  መንገድ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል።

ትራምፕ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለማምረት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወጪ እየተደረገ ነው በሚል ድርድር ማድረግ  እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2019 የኑክሌር መሳሪያ ምርትን ለመቀነስ ከስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቀችው ሩሲያ የጦር መሳሪያው የመጠቀም እድል ሊኖራት የሚችለው “የመጨረሻ አማራጭ”ሲሆን ብቻ እንደሆነ ፕሬዝዳንት ፑቲን ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ #rtnews

@ThiqaEth

THIQAH

24 Jan, 10:01


ኤርትራውያን "በህገወጥ የሰዎች አዛዋሪዎች ድርጊት መሰማራታቸውን" አንድ ሪፖርት አመላከተ፡፡

"በቡድን የተደራጁ የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ስደተኞች ላይ ግፍ በመፈጸምና በህገወጥ የሰው ዝውውር በስፋት በመሳተፍ ላይ" እንደሚገኙ ተቀማጭነቱን ኔዘርላንድ ያደረገው የኮኒ ረጅከን ጥናት ተቋም አመላክቷል፡፡

ተቋሙ 124 ኤርትራውያን ስደተኞችን በጥናቱ ለናሙናነት የተጠቀመ ሲሆን፤ "ሁሉም ስደተኞች 'ወደ ኔዘርላንድ እንልካችኋለን' ተብለው ከተወሰዱ በኋላ በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እጅ መውደቃቸውን ነግረውኛል" ብሏል፡፡

ስደተኞቹ ሊቢያ ከገቡ በኋላ በሃገራቸው ዜጎች ከሚደርስባቸው ስድብና ድብደባ ባለፈ ወደ ቤተሰቦቻቸው እየደወሉ ገንዘብ እንድያስልኩ ይገደዳሉ ሲል የኮኒ ረጅከን ጥናት ያመላክታል፡፡ #brusselssignal

@ThiqahEth

THIQAH

24 Jan, 09:58


አሜሪካዊው ዳኛ ትራምፕ የዜግነት መብት እንዲቆም ያስተላለፉትን ትዕዛዝ አገዱ፡፡

ዳኛ ጆን ኮግነር ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ቀጥተኛ የአሜሪካ ዜግነት መብት እንዲቆም ያሳለፉትን ውሳኔ ህገ መንግስታዊ አይደለም በሚል በጊዜያዊነት አግደውታል፡፡

ኮግነር ዴሞክራቶች በሚያስተዳድሯቸው አራት የአሜሪካ ግዛቶች አሪዞና፣ ዋሽንግተን፣ ኢሊኖይስና ኦሪጎን ተግባራዊ እንዳይደረግ አዘዋል፡፡

በፕሬዝዳንቱ ውሳኔ መሰረት የሚወለዱ ህጻናት በአባታቸው፣ በእናታቸው አሜሪካዊ ካልሆኑ በስተቀር አሜሪካ ስለተወለዱ ብቻ የአሜሪካን ዜግነት ማገኘት አይችሉም፡፡

በዚሁ ድንጋጌ መሰረት በዓመት ከ150,000 የሚበልጡ ህጻናት በትራምፕ አዲስ ህግ ምክንያት ዜግነት አያገኙም፡፡
#asiaone

@ThiqahEth

THIQAH

17 Jan, 11:02


በአንጎላ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰማ፡፡

በተያዘው የጥር ወር በጥርጣሬ ከተለዩት 400 ሰዎች ውስጥ 75 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ 20 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

የአንጎላ ባለስልጣናት የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ወረርሽኙ የተከሰተው 1.2 ሚሊዮን ህዝብ በሚገኝባት የሉብዳ ግዛት ነው ተብሏል፡፡ #lusa

@ThiqahEth

THIQAH

17 Jan, 11:00


"የሱዳን ጦር የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ነው"- አሜሪካ

አሜሪካ የሱዳን ጦር የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ነው ስትል ወነጀለች፡፡

ሱዳናውያን "ህዝብ በብዛት በሚኖርባት በዋና ከተማዋ ካርቱም የጦር መሳሪያው ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል" በሚል ስጋት ላይ ይገኛሉ ሲሉ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ከሳምንት በፊት በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጂነራል ሀምዳን ዳጋሎ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃ ነበር፡፡

ማዕቀቡ ንጹሃንን በቦምብ በመግደል እና ርሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም ወንጀል ነው ተብሏል፡፡ #semafor

@ThiqahEth

THIQAH

15 Jan, 10:16


የግብጽ ህዝብ በ72 ቀናት ውስጥ በ250,000 መጨመሩ ተገለጸ፡፡

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 107 ሚሊዮን መድረሱን የግብጽ የህዝብ ስብስብ እና ስታቲክስ ማዕካዊ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ዋና ከተማዋ ካይሮ 10.4 ሚሊዮን ዜጎችን በመያዝ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ከሚያስተናግዱ የሀገሪቱ ከተሞች ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በ2030 የግብጽ ጠቅላላ ህዝብ ቁጥር 117 ሚሊየሸን ሊደርስ እንደሚችል የማዕከላዊ ኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡ #middleeastmonitor

@thiqahEth

THIQAH

14 Jan, 10:53


የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች በኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ላይ ለመወያየት ለሶስተኛ ጊዜ ተሰብስበዋል፡፡

በጀኔቫ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ከኢራን የተወከሉ ተደራዳሪዎች ከፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና ጀርመን ባለስልጣናት ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

ኢራን ለድርዱሩ ውጤታማነት የተጣሉባት ማዕቀቦች እንዲነሱላት የስምምነቱ አካል አድርጋ ማቅረቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድዔታ ካዜም ጋሪባብዲ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል፡፡

ውይይቱ ቀጥተኛ፣ ግልጽ እና ገንቢ ነው ያሉት ጋሪባብዲ በሁለቱ ወገን ያለው ንግግር ቀጣይነት እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡ #iraninternational

@ThiqahEth

THIQAH

13 Jan, 07:10


"ቅኝ ገዥ ኃይሎች በአፍሪካ ግጭትን እያቀጣጠሉ ነው"  - ጄነራል አልቡርሃን

የሱዳን ሉዓላዊ ምክርቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በካርቱም ከጊኒ ቢሳው አቻቸው ኡማሮ ሲሴኮ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት፣ "አፍሪካ በውጭ ጣልቃ ገብነት እየተናጠች ነው" ያሉት አልቡርሃን ለዚህም በደፈናው የውጭ ኃይሎች ሲሉ የጠሯቸውን ሀገራት ወቅሰዋል።

ጄነራሉ፣ "አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የድሮውንና ዘመናዊውን ቅኝ ግዛት ለመታገል ያሳዩትን ቁርጠኝነት እንደግፋለን" ብለዋል።

በሱዳን በቀጠለው የርስበርስ ጦርነት አልቡርሃን የሚመሩት የሀገሪቱ ጦር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ እያደረገች ነው በሚል በተደጋጋሚ ይከሳል። #anadoluagency

@ThiqahEth

THIQAH

13 Jan, 07:08


በሰደድ እሳት አደጋው የሟቾች ቁጥር 26 ደረሰ።

አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ብቁ ያልሆኑ" ያሏቸውን የካሊፎርኒያ ግዛት አመራሮች ለአደጋው ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።

በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ የተከሰተውን የእሳት አደጋ አሁንም ድረስ ማስቆም አልተቻለም።

የሰደድ እሳቱ በሰዓት 70 ማይል ወይም 110 ኪሎ ሜትር እየሸፈነ እንደሚገኝ ተገልጿል። #gulfnews

@ThiqahEth

THIQAH

11 Jan, 17:10


የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ አዲስአበባ ገቡ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሶማሊያዉ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ገብታ የነበረውን የባህር በር ለማግኘት የሚያስችል ስምምነትን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጹ፣ ኢትዮጵያንም በአለማቀፍ መድረኮች ላይ ሲወነጅሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ በአንካራ ቱርክ አሸማጋይነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ዉጥረት ለማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት እና በአዲስ አበባ ስለሚኖራቸው ቆይታ እስካሁን የተገለጸ ነገር ባይሮርም ስለአንካራው ስምምነት ለመወያየት እንደሆነ ይጠበቃል።

የሶማሊያው ኘሬዝዳንት አዲስ አበባ ሲገቡ የግብጽ የኤርትራና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በግብጽ  የሶማሊያን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ እንሰራለን ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሶሚሊያ ፕሬዝዳንቷ አዲስ አበባ፣ የኤርትራና የሶማሌ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደግሞ ካይሮ ይገኛሉ። #pmoffice #villasomalia

@ThiqahEth

THIQAH

08 Jan, 07:25


"በኢራን በሞት ፍርድ የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ከአመት ወደ አመት እየጨመረ መጥቷል" - ቮልከር ተርክ

በኢራን የሞት ቅጣትን እየጨመረ መምጣቱ ሀገሪቱን ተከትሎ ድርጊቱን በዘላቂነት እንድታቆም ተ.መ.ድ ጠይቋል።

በተ.መ.ድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ቮልከር ተርክ፣ "በኢራን በሞት ፍርድ የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ከአመት ወደ አመት እየጨመረ መጥቷል" ሲሉ ተናግረዋል።

ተርክ፣ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት 2024 ብቻ 900 ኢራናውያን የሞት ፍርድ ቅጣት እንደተላለፈባቸው አመላክተዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 40 የሚሆኑት በአንድ ሳምንት ውስጥ እርምጃ የተወሰደባቸው እንደሆኑ ገልጸዋል። #voa

@ThiqahEth

THIQAH

06 Jan, 20:27


"በዓሉ ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ" - ኮሚሽኑ

የበዓል ስራዎች በሚከናወኑበት ጊዜ ሁሉንም ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ  ከማከናወን መቆጠብና ስራዎችን በቅድመ ተከተል፣ እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን መከፋፈል ያስፈልጋል።

በአንድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ሶኬቶችን ደራርቦ አለመጠቀም፣ ጋዝ ሲሊንደር ከመለኮስዎ በፊት በጋዝ ሲሊንደር መስመር ውስጥ ያፈተለከ ጋዝ አለመኖሩን ማረጋገጥ።

ከሰል በሚጠቀሙበት ጊዜ የከሰል ምድጃውን ከቤት ውጪ በማድረግ ከሰሉ ጢሱን እንዲጨርስ ማድረግና ወደ ቤት ካስገቡ በኋላም በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር ማድረግና ስራዎን ካጠናቀቁ በኋላም ምድጃውን ከቤት በማውጣት እሳቱን በውሃ በማጥፋት፣ ቤቱን ማናፈስ።

ለክብረ በዓሉ ወይም ለብርሃን አገልግሎት የለኮሱት ሻማ  ከመጋረጃና ከሶፋ፣ ከሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጋር እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግና ከመተኛትዎ በፊት ወይም ከቤት በሚወጡ ጊዜ የለኮሱትን ሻማ ማጥፋትዎን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

በንግድ ማዕከላትም ነጋዴዎች የንግድ ሱቆቻቸውን ዘግተው ከመውጣታቸው በፊት የተዘነጉ የኤሌክትሪክ ሶኬቶችን እና የተለኮሱ ሻማዎች ካሉ መጥፋታቸውንና መቋረጣቸዉን ማረጋገጥ።

ከዚህ ዓልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸዝም አደጋዎች ኮሚሽን መ/ቤቱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች  በ939 ፈጥነው ያሳውቁ። (ምንጭ፦ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን)

@ThiqahEth

THIQAH

06 Jan, 20:27


መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ የእምነቱ ተከታዮች ደስታ የሚያስደስታችሁ ወዳጆቻቸው በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ ክፉ የማንሰማበት፣ የራቀን ሰላም የሚመለስበት፣ የተስፋፋው መነቋቆር የሚቀንስበት፣ የቀደመ ፍቅራችን የሚመለስበት በዓል እንዲሆን ቲቃህ ኢትዮጵያ ከወዲሁ ይመኛል።

በድጋሚ መልካም በዓል ተመኘን!

ክፉውን ሁሉ ያርቅልን!

@ThiqahEth

THIQAH

03 Jan, 06:36


የአዉሮፓ ህብረት አለመረጋጋት ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል።

የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው ብራስለስ ሁከትና ብጥብጥ በመቀስቀሱ የጸጥታ ኃይሎች ወታደራዊ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

ድንገት  በተቀሰቀሰው  አመጽ ከ60 በላይ ተሽከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ 160 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወሰቋል።

የሁከቱ መንሰኤ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፣ ወጣቶች በፖሊስ ላይ ርችት ሲተኩሱና ድንጋይ ሲወረዉሩ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ከተሰራጨው ቪዲዮ ለመመልከት ተችሏል። #rtnews

@ThiqahEth

THIQAH

03 Jan, 06:30


የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሶማሊያ ገቡ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሰላም አስከባሪ ኃይሎች ስምሪት ዙሪያ ለመምከር ወደ ሞቃድሾ አቅንተዋል።

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም ድጋፍ ሰጭ ኃይል (AUSSOM) ውስጥ የሚኖራትን ሚና በተመለከተ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለአንድ አመት በዘለቀ ውዝግብ ውስጥ ቢቆዩም አንካራ ላይ ባደረጉት ስምምነት ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማምተዋል። #borkena #cnn #bloomberg

@ThiqahEth

THIQAH

03 Jan, 06:24


"ነገሮችን በትክክል ለማስኬድ ይህን አስተማሪ ፍርድ አስተላልፈናል" - ኮንጎ

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፍርድ ቤት 13 ወታደሮችን በሞት ፍርድ ቀጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ይህንኑ ቅጣት፣ "ነገሮችን በትክክል ለማስኬድ ይህን አስተማሪ ፍርድ አስተላልፈናል" ብሎታል።

ወታደሮቹ የተፈረደባቸው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ባሳዩት "የስራ ላይ ፀባይ/ድሲፕሊን /" እንደሆነ ተገልጿል።

ወታደሮቹ፣ "የግድያ እና ዝርፊያ" ወንጀሎች መፈጸማቸውን ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።  #nrws24

@thiqaheth

THIQAH

29 Dec, 08:47


በደቡብ ኮሪያ በአውሮፕላን አደጋ ከ124 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ።

181 ሰዎችን ጭኖ ከታይላንድ የተነሳው Boing 737-800 አውሮፕላን ደቡብ ኮሪያ አየር ማረፊያ ላይ እያረፈ በነበረበት ወቅት ነው አደጋው የደረሰው።

የአደጋው መንስኤ አውሮፕላኑ እያረፈ በነበረበት ወቅት የፊተኛው ጎማ ተበላሽቶ ከኮንክሪት ግንብ ጋር በመጋጨቱ ተንሸራቶ በመውደቁ ነው ተብሏል።

የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች 32 የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ከአደጋው የተረፉትን ለማዳን እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል። #bowenislandundercurrent

@thiqaheth

THIQAH

26 Dec, 21:20


"እኔን ጨምሮ የተ.መ.ድና የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረቦች ደህና ነን"  - ቴዎድሮስ አድሃኖም  (ዶ/ር)

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)፣ የመን ውስጥ ከአየር ጥቃት መትረፋቸውን ገልጸዋል።

"እኔን ጨምሮ የተ.መ.ድና የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረቦች ደህና ነን" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ባልደረባቸው እንደቆሰለና አንድ ሰው እንደተገደለ ፅፈዋል።

ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ በእስር ላይ የሚገኙ የተ.መ.ድ ሰራተኞች እንዲለቀቁና በየመን ያለው የሰብዓዊ እርዳታ እንድሻሻል ምክክር መደረጉን አስታውቀዋል።

ተልዕኳቸውን ጨርሰው በመመለስ ላይ እያሉ እስራዔል በሰንዓ አየር ማረፊያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ባልደረባቸው እንደቆሰለና ሌላ በቦታው የነበረ ግለሰብ ህይወቱ እንዳለፈ አብራርተዋል።

የተጎዳው የአየር ማረፊያ እስከሚጠገን በስፍራው እንደሚቆዩም ገልጸዋል። #WHO

@ThiqahEth

THIQAH

26 Dec, 21:19


"33 ታራሚዎች ሞተዋል ከ1500 የሚበልጡት አምልጠዋል" - የሞዛምቢክ ፖሊስ

በሞዛምቢክ አወዛጋቢውን ምርጫ ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመጽ አሁንም ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል።

ከማረሚያ ቤት አምልጠው ከወጡት 1,534 ታራሚዎች መካከል 150 የሚሆኑት እንደገና ተይዘው መመለሳቸውን የሞዛምቢክ ፖሊስ ጄነራል ኮማንዶ በርናርዶ ራፋይል አስታውቀዋል።

"33 ታራሚዎች ሞተዋል ከ1500 በላይ አምልጠዋል" ተብሏል።

የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት ላይ የተካሄደውን ምርጫ ገዥው የፍሬሊሞ ፓርቲ ማሸነፉን አውጆ እንደነበር ይታወቃል።  #legit

@Thiqaheth

THIQAH

25 Dec, 10:36


ንብረትነቱ የአዘርባጃን የሆነ አውሮፕላን ሩሲያ ውስጥ ተከሰከሰ።

አደጋው እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር በግልጽ ባይታወቅም 20 ሰዎች በህይወት ተገኝተዋል ተብሏል።

ከባኩ ወደ ቺቺኒያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን 64 ተጓዦችን እና አምስት የበረራ አባላትን በውስጡ ይዞ ነበር ነው የተባለው።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ለማረፍ ትንሽ ሲቀረው መሆኑ ተገልጿል። #meduza

@ThiqahEth

THIQAH

24 Dec, 12:57


''ጥቃቱ የአፍሪካ ቀንድ እንዳይረጋጋ በሚፈልጉ ሦስተኛ ወገኖች የተፈጸመ ነው''  - ኢትዮጵያ

የኢትዮጵየያ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጠው መግለጫ፣ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዶሎው በሚገኘው የሶማሊያ ጦር ፈጽመውታል ላለችወሰ ውንጀላ ምላሽ ሰጥቷል።

ይህንኑ ውንጀላ፣ ''ከእውነት የራቀ ውንጀላ ነው'' የሚል ምላሽ ሰጥቶበታል።

ሚኒስቴሩ አክሎ፣ ''ሁለቱ ሀገራት በአንካራ ያደረጉትን ስምምነት ለማሰናከል የሚጥሩ አካላትን ልንፈቅድላቸው አይገባም'' ብሏል።

ኢትዮጵያ ወደ ፊት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከሶማሊያ መንግስትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ መስራቷን እንደምትቀጥል በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በወጣው መግለጫ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች ዶሎው በሰፈረው የሶማሊያ ጦር ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ስትል ሶሚሊያ መወንጀሏ ተዘግቦ ነበር።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች የፈጸሙት ጥቃት "ሆን ተብሎ ታቅዶበት የተፈጸመ ነው" ሲል ከሶ ነበር። #MoFAE

@ThiqahEth

THIQAH

24 Dec, 09:20


''ሶማሊያ ባቀረበችልን ጥያቄ መሰረት የግብጽ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ተልዕኮው ይካተታሉ''  - ባዲር አብደላቲ

ግብጽ በአዲሱ የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል (AUSSOM) ውስጥ እንደምትሳተፍ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ አረጋግጠዋል፡፡

ይህ የተባለው የግብጽና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከካይሮ በሰጡት መግለጫ ነው።

ባዲር አብደላቲ፣ "ሶማሊያ ባቀረበችልን ጥያቄ መሰረት የግብጽ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ተልዕኮው ይካተታሉ'' ብለዋል።

ሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስትር ደኤታዋን ወደ ኢትዮጵያ ስትልክ፣ ሚኒስትሩ አህመድ ሞዓሊም ፊቂ ደግሞ ግብጽ ገብተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ከተስማሙ በኋላ ውይይት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡ #ahramonline

@ThiqahEth

THIQAH

24 Dec, 07:10


ባንግላዴሽ ህንድ የቀድሞዋን ጠቅላይ ሚኒስትር አሳልፋ እንድትሰጣት ጠየቀች።

በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀሲና ወደ ሀገር ተመልሰው በህግ ፊት እንዲቀርቡ ጥያቄ ማቅረቡን የባንግላዴሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው፣ ጥያቄው እንደቀረበ አረጋግጠው "በዚህ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ የምናቀርበው አስተያየት የለንም" ብለዋል።

በስደት ላይ የሚገኙት ሀሲና ባሳለፍነው ነሐሴ ተማሪዎች ያስጀመሩትን ሀገራዊ ተቃውሞ መቋቋም ተስኗቸው ወደ ጎረቤት ሀገር ህንድ ኮብልለው ጥገኝነት ጠይቀዋል። #dw

@ThiqahEth

THIQAH

24 Dec, 06:57


የኢትዮጵያ ወታደሮች ዶሎው በሰፈረው የሶማሊያ ጦር ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ስትል ሶሚሊያ ወነጀለቸ፡፡

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች የፈጸሙት ጥቃት "ሆን ተብሎ ታቅዶበት የተፈጸመ ነው" ሲል ከሷል፡

ሱማሊያ ይህን ውንጀላ ያሰማችው፣ በውጭ ጉዳይና ዓለማቀፍ ትብብር ሚንስትር ደኤታዋ ዓሊ ኦማር የተመራ የልዑካን ቡድኗን በአንካራው ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር እንድመክር ወደ ኢትዮጵያ መላኳ ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ ነው።

ሞቃድሾ ተፈጽሞብኛል ስላለችው ጥቃት ከኢትዮጵያ በኩል ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡#borkena

@thiqaheth

THIQAH

23 Dec, 20:41


የሞዛምቢክ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአወዛጋቢው ምርጫ ገዥው ፖርቲ ማሸነፉን አወጀ።

ፍርድ ቤቱ ጥቅምት ላይ የተካሄደውን ምርጫ አሁን ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የፍሬሊሞ ፖርቲ አሸንፏል ብሏል።

ምርጫው በተካሄደበት ወቅት በማጭበርበር የተሞላ ነበር ያሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አድማ ጠርተው ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ነበር።

የፍሬሊሞ ፓርቲ እ.ኤ.አ ከ1975 ጀምሮ 35 ሚሊዮን ህዝብ ያላትን ሞዛምቢክን እያስተዳደረ ቆይቷል። #timeslive

@ThiahEth

THIQAH

23 Dec, 20:38


ሶማሊያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዔታ የተመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ልካለች።

የልዑካን ቡድኑ በአዲስ አበባ በሚኖረው ቆይታ ከሁለት ሳምንታት በፊት በቱርክ ስለተፈጸመው "የአንካራ ስምምነት" ላይ እንደሚመክር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ አመልክቷል።

በመግለጫው፣ "በመደጋገፍ እና መከባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ ጥቅም እና ትብብር እድሎች" ላይ የሚያተኩር ቆይታ ይሆናል ተብሏል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዲዔታ አሊ ኦማር የተመራው ልዑክ የሁለቱን ጎረቤት ሀገራት ግንኙነት ወደ ነበረበት ይመልሳል የተባለ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። #FRoS

@ThiqahEth

THIQAH

23 Dec, 14:20


የጃፓን ግዙፍ የተሸከርካሪ አምራች ካምፓኒዎች ሆንዳ እና ኒሳን ለመዋሃድ ማቀዳቸውን አስታወቁ፡፡

ሁለቱ ግዙፍ ተሽርካሪ አምራች ድርጅቶች ጃፓን በዓለም ላይ በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ምርት በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እድትሆን በማለም ነው ለመዋሃድ ያሰቡት ተብሏል፡፡

ውህደቱን እውን ለማድረግ የሁንዳ ሥራ አስፈጻሚ ቶሺሂሮ ሚቤ እና የኒሳን ስራ አስፈጻሚ ማኮቶ ኡቺዳ ዛሬ የመግባቢያ ስምነት ተፈራርመዋል፡፡

ሆንዳ እና ኒሳን ከተዋሃዱ በዓለም ላይ ከቶዮታ እና ቮልስዋገን በመቀጠል ሶ
ሦስተኛውን ግዙፍ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ እንደሚመሰርቱ ተዘግቧል፡፡

ሁለቱ ግዙፍ ተቋማት 2026 ላይ አዲሱን ካምፓኒ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ #aljazeera

@ThiqahEth

THIQAH

23 Dec, 14:15


ዓለምባንክ ለኢትዮጵያ ''የፋይናንስ ዘርፍ ፕሮጄክትን ለማጠናከር (FSSP) '' ያለውን የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ፡፡

ባንኩ ብድሩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት በሰፊ ተግዳሮት ውስጥ እያለፉ እንደሚገኙ ጠቁሟል፡፡

በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው ይህ ብድር፣ ብሄራዊ ባንክን ለማዘመን እና የገጠመውን የፋይናስ አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ እንደሚረዳ ገልጿል።

እንዲሁም የንግድ ባንክን እና የልማት ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ነው ባንኩ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማረጋጋት ይውላል የተባለው ብድር የሚሰበሰበው ከዓለም አቀፍ የልማት ማኀበራት (IDA) እንደሆነ መግለጫው ተመላክቷል፡፡

ባንኩ በዚህም የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ፕሮጄክትን ለማጠናከር (FSSP)'' ያለውን የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። #apanews

@ThiqahEth

THIQAH

22 Dec, 13:57


በቀይ ባህር ዘመቻ ላይ የነበሩ የአሜሪካ ባህር ኃይል ጀቶች ተጋጩ።

ጀቶቹ ሂዝቦላህ በንግድ መርከቦች ላይ የፈጸመውን ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነበሩ ተብሏል።

የአሜሪካ ጦር ከሂዝቦላህ የተቃጡትን ፀረሚሳዔል ጥቃቶችን ማክሸፍ ችያለሁ ሲል አስታውቋል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንዶ (CENTCOM) የተጋጩትን ጀቶች ሲያበሩ የነበሩት ሁለቱ አብራሪዎች እንዳልተጎዱ ገልጿል። #abcnews #aninews

@thiqaheth

THIQAH

22 Dec, 13:55


በጀርመን የገና በዓል ገበያ ላይ በደረሰው ጥቃት 5 ሰዎች ሲገደሉ 200 የሚሆኑት ቆሰሉ።

ጥቃቱን አድርሷል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ የሳዑዲ አረቢያ ዜግነት ያለው እንደሆነ ተዘግቧል።

በማግደቡርግ ከተማ የደረሰው ጥቃት በጀርመን ያለውን የስደተኞችን አያያዝ ጉዳይ አሳሳቢ አድርጎታል ነው የተባለው። #irishindependent

@thiqaheth

THIQAH

22 Dec, 13:53


ሩሲያ 100 ድሮኖችን ወደ ዩክሬን አስወነጨፈች።

የድሮን ጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶችን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

ከተወነጨፉት ጥቃቶች ውስጥ ግማሽ ያህሉ መክሸፋቸውን ዩክሬን አስታውቋል።

በጥቃቱ እስካሁን የደረሰ ጉዳት አልተመዘገበም ነው የተባለው። #radiofreeeurope

@thiqaheth

THIQAH

21 Dec, 15:39


ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ማክሮን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተቀብለዋቸዋል።

ማክሮን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት በትናንትናው እለት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። #pmoffice

@ThiqahEth

THIQAH

21 Dec, 15:31


ተ.መ.ድ በኮንጎ ያሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል ለተጨማሪ አንድ አመት እንዲቆይ ወሰነ።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮው (MONUSCO) ከሀገሪቱ እንዲወጣ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ግጭት ከበዛበት የምሥራቅ ቀጠና ርቆ እንዲሰፍር የጸጥታው ምክር ቤት ዓርብ'ለት በነበረው ጉባዔ ወስኗል።

ተ.መ.ድ ከ2023 ጀምሮ 11,000 አባላት ያሉትን የሰላም አስከባሪ ኃይል ከM23 ጋር ግጭት ውስጥ በገባችው ዲ አር ሲ አሰማርቷል። #sabcnews

@ThiqahEth

THIQAH

29 Nov, 07:04


ለሁለት ወራት ይቆያል የተባለው የእስራዔልና የሂዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለተኛው ቀን ተጣሰ፡፡

በእስራዔልና በሂዝቦላህ መካከል የተፈጸመው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል ተብሏል።

ሁለቱ ኃይሎች ከስምምነቱ በኋላም የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ለተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣስ አንዱ ሌላኛውን ተጠያቂ እያደረገ ሲሆን፣ ሂዝቦላህ ከስምምነቱ በኋላ የሮኬት ጥቃት ማድረሱ ተዘግቧል፡፡

በስምምነቱ መሰረት እስራዔል ጦሯን ሙሉ በሙሉ ከሊባኖስ እንድታስወጣ ተደርጎ ነበር።

ተመሳሳይ መልኩ ሂዝቦላህ ደግሞ የሊታኒ ወንዝ ሰሜናዊ ክፍልን ለቆ እንዲወጣ ተደርጎ ነበር፡፡ #washingtontimes

@ThiqahEth

THIQAH

28 Nov, 10:15


ኢትዮጵያ ከIMF የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ ብድር ማግኘቷ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ከIMF 251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማገኘት ያስችላታል የተባለው ስምምነት ተፈጽሟል።

ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር በተራዘመ ብድር አቅርቦት (ECF) ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ውይይት በአመራሮች ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሷል ተብሏል።

ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆች አመት 2024 IMF በ4 አመታት ውስጥ ተመላሽ የሚሆን የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ ብድር አቅርቦት አግኝታለች።

የብድር አቅርቦቱ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጥ ማድረጓ እና የውጭ ምንዛሬ በገበያ ላይ የተመሰረተ እንድሆን እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ የመጣ መሆኑ ተመላክቷል። #borkena

@ThiqahEth

THIQAH

27 Nov, 15:06


የቀድሞው ተጫዋች የጆርጂያ ፕሬዝዳንት ሆኖ ተሾመ።

የጆርጂያ ገዢው ድሪም ፓርቲ የቀድሞውን የእግር ኳስ ተጫዋች ሚካሄል ካቨላሽቪሊን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሹሟል።

ካቨላሽቪሊ ራሱን ከእግር ኳስ ካገለለ በኋላና ፕሬዚዳንት ሁኖ ከመመረጡ በፊት የሀገሪቱ ፓርላማ ምክትል አፈጉባኤ ሆኖ ሰርቷል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት ዲሴምበር 29/2024 በዓለ ሲመታቸውን እንደሚፈፅሙ ታውቋል። #associatedpress

@thiqaheth

THIQAH

27 Nov, 07:37


"የ3 ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መታገድ የሲቪል ቦታ እየወረደ መምጣቱን ያሳያል"  - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

አለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ሶስት  የሲቪክ ማህበራት መዝጋቱን ተቃውሟል።

መንግስት፣ "የፓለቲካ ገለልተኝነት የላቸውም" ያላቸውን AHRE, CARD እና LHR ስራቸውን እንድያቆሙ ለተቋማቱ በፃፈው በደብዳቤ አሳስቧል።

ይህን ተከትሎም አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ "የ3 ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መታገድ የሲቪል ቦታ እየወረደ መምጣቱን ያሳያል" ብሏል።

እንደዚህ አይነት ምክንያቶች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት ስራ ላይ ጫና ለማሳደር ሲጠቀሙበት የቆየ መሆኑንም ገልጿል።

መንግስት ውሳኔውን እንድቀለብስና እገዳውን እንዲያነሳም ድርጅቱ ጠይቋል።#borkena

@thiqaheth

THIQAH

27 Nov, 07:31


እስራኤል እና ሂዝቦላህ ተኩስ ለማቆም ሥምምነት ላይ ደረሱ።

ላለፉት 14 ወራት በጦርነት ውስጥ የቆዩት ሁለቱ ወገኖች ከሰዓታት በፊት ተኩስ ለማቆም መስማማታቸውን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል።

የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ማኪቲ፣ ሥምምነቱን በበጎ እንደሚቀበሉት ለባይደን መናገራቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ በበኩላቸው፣ ካቢኒያቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዳጸደቀላቸው ለባይደን አስረድተዋል። #mehernewsagency #aljazeera

@thiqaheth

THIQAH

25 Nov, 10:43


በኡራጋይ የግራ ዘመሙ ፓርቲ ሀገራዊ ምርጫውን አሸነፈ፡፡

የተፊካካሪው ግራ ዘመም ፓርቲ እጩ ያማንዱ ኦርሲ፣ የወግ አጥባቂው ገዥ ፓርቲ መሪውን አልቫሮ ዴልጋዶን በማሸነፍ አዲሱ የኡራጋይ ፕሬዝንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ኦርሲ ከድሉ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ ''እድገት የሚያመጣና ሀገሪቱን ወደፊት የሚያራምድ ፕሬዝዳንት እሆናለሁ'' ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

''ኡራጋይ አንድ መሆኗን የሚገልጽ ሀሳብ እናራምድ'' ብለዋል አዲሱ ፕሬዝዳንት፡፡ #upi

@thiqaheth

THIQAH

24 Nov, 15:17


በፓኪስታን በተፈጠረ ድንገተኛ አመጽ ከ80 በላይ ሲገደሉ፣ 156 የሚደርሱት ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ።

አመጹ የተፈጠረው አንድ ታጣቂ የሺያ ሙስሊም ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ነው።

በኩራም ግዛት የሺያና ሱኒ ሙስሊሞች በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ እንደገቡ ተዘግቧል።

አመጹ የተቀሰቀሰባት የኩራም ግዛት ፓኪስታን ከአፍጋኒስታን ጋር የምትዋሰንባት ድንበር ናት። #bbc

@thiqaheth

THIQAH

24 Nov, 15:15


ሂዝቦላህ በአሽዶድ የባህር ኃይል ላይ ጥቃት ማድረሱን ገለጸ።

ቡድኑ በደቡብ እስራኤል በሚገኘው የባህር ኃይል ላይ የድሮንና የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

ሂዝቦላህ በአሽዶድ ላይ ጥቃት ሲያደርስ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንም አረጋግጧል።

የእስራኤል ጦር በአሽዶድ የባህር ሀይል ላይ ደረሰ ስለተባለው የድሮን ጥቃት የሰጠው ምላሽ የለም።#ashiraqalausat

@thiqaheth

THIQAH

24 Nov, 15:13


ኢራን ከጀርመን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ጋር ውይይት ልታደርግ መሆኑ ተሰማ።

ኢራን ከሶስቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደምትመክር ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ፣ ውይይቱ በሚኒስትር ድዔታዎች አማካኝነት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

የሀገራቱ ውይይት በመጪው አርብ ዲሴምበር 29 እንደሚጀመር ቃል አቀባዩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። #mehernews

@thiqaheth

THIQAH

24 Nov, 15:12


በአውስትራሊያ በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 138 ሰዎች ታሰሩ።

የአየር ንብረት ለውጥ አድርሶብናል ያሉትን ጫና ለመቃወም አደባባይ የወጡ ዜጎች የመርከብ ጉዞን አስተጓጉለዋል ተብሏል።

የኒው ሶውዝ ዌል ፖሊስ፣ ወደ ኒው ካስትል የሚጓጓዙ መርከቦችን ያስተጓጎሉ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።

የተቃውሞ ሰልፉን በበላይነት በአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ተሟጋቾች ያስተባበሩት እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ቢያንስ 138 ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል።

#thestraitstimes

THIQAH

24 Nov, 08:10


"በእስራኤል ጥቃት ከሞቱት ውስጥ እስራዔላውያን ታጋቾች ይገኙበታል" - ሀማስ

"አሁን ላይ ማረጋገጫ መስጠትም ሆነ ውድቅ ማድረግ አልችልም" - እስራኤል

እስራኤል ሆስፒታል ላይ ኢላማ ባደረገው ጥቃቷ በ48 ሰዓት ውስጥ 128 ንጹሐንን ገድላለች ተብሏል።

እንደጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ  እስራኤል ለተከታታይ ሁለት ቀናት ባደረሰችው ጥቃት ከሞቱት ውስጥ ሰባት የቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።

የሀማስ ቃል አቀባይ አቡ ኡባይዳ አንድ የእስራኤል ታጋች የእስራኤል ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት መገደሏን ገልጿል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በበኩሉ፣ "አሁን ላይ ማረጋገጫ መስጠትም ሆነ ውድቅ ማድረግ አልችልም" ብለው ምርመራ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።#gmanews

@thiqaheth

THIQAH

23 Nov, 08:28


ኔቶ እና ዩክሬን በመጪው ማክሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርጉ ነው ተባለ።

የስብሰባው አላማ ሩሲያ ስለፈጸመችው የሀይፐርሶኒክ ሚሳዔል ዙሪያ ለመወያየት እንደሆነ ተዘግቧል።

በዚህም በደረሰው ጥቃት ሳቢያ የዩክሬን ምክር ቤት ሊያካሂድ የነበረውን ስብሰባ ሰርዟል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከጥቃቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ የምዕራባውያን የአየር መከላከያ አዲሱን ሚሳዔል ለማስቆም አቅም የለውም ሲሉ ተናግረዋል። #npr

@thiqaheth

THIQAH

23 Nov, 08:24


"4 ዜጎች ሰማዕት ሁነዋል፣ 23ቱ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል" - የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር

በእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 4 ሰዎች ሲሞቱ 23 ቆስለዋል።

የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ቤሩት ባስታ ድስትሪክት በሚገኝ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ያደረሰው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የሊባኖስ የጤና ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ "4 ዜጎች ሰማዕት ሁነዋል፣ 23ቱ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል" ሲል  አስታውቋል።

እስራኤል ከመስከረም ወር ጀምሮ በሊባኖስ በከፈተችው ዘመቻ በድምሩ 3600 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ : 15,300 ቆስለዋል። #aa

@thiqaheth

THIQAH

23 Nov, 08:21


"ጀርመን የታውረስ ሚሳዔልን በፍጥነት እንድትልክ እንጠይቃለን" - የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት ጀርመን ለዩክሬን የታወርስ ሚሳዔል እንድትልክ ወሰነ።

የህብረቱ የፓርላማ ፕሬዚዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፣ ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳዔል እንድትጠቀም ያለንን ድጋፍ እናሳያለን ብለዋል።

ሜትሶላ አክለው፣ "ጀርመን የታውረስ ሚሳዔልን በፍጥነት እንድትልክ እንጠይቃለን" ነው ያሉት።

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ፣ ከሳምንት በፊት ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል።#rfe

@thiqaheth

THIQAH

20 Nov, 21:33


በኮንጎ 'የህገመንግስት ለውጥ ሊደረግ ነው' መባሉን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ።

የየዴሞክራቲሪ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፍሊክስ ስሼኬድ አዲስ ህገ መንግስት ለማርቀቅ በሂደት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ለዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ዋስትና የሚሰጥ ነው የተባለው አዲሱን ህገመንግስት ለማፅደቅ ከፓርላማ አባል 60 በመቶ ድምፅ ማግኘት ይጠበቅበታል።

በዚህም የዋና ተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ጆሴፍ ካቢላ ሀገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ እንድደረግ ለሀገሪቱ ዜጎች ጥሪ አቅርበዋል። #abcnews

@thiqaheth

THIQAH

17 Nov, 09:32


በጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ መኖሪያ ቤት አጠገብ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተገለጸ።

የእስራዔል ፓሊስ ቅዳሜ ምሽት ከተሰነዘሩት ጥቃቶች ሁለቱን ማክሸፉን አስታውቋል።

በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የኒታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ማን እንደፈጸሙ አልተገለጸም።

ጥቃቱ ሲፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነቤተሰቦቻቸው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳልነበሩ ፖሊስ አብራርቷል።

የኒታንያሁን ቤት ኢላማ ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። #anadoluagency

@thiqaheth

THIQAH

16 Nov, 18:02


"ጦርነቱ በጣም በቅርቡ ይቆማል"  - ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር የገባችበት ጦርነት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ፍንጭ ሰጥተዋል።

እንደ ዘለንስኪ ገለፃ ለጦርነቱ መቆም ምክንያት የሆነው የትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት ነው።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት በአጭር ቀን ውስጥ አስቆመዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል። #lbc

@thiqaheth

THIQAH

14 Nov, 18:40


ሂውማን ራይትስ ዎች የዘር ፍጅት ፈፅማለች ሲል እስራዔልን ወነጀለ።

አለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) እስራኤል "የጦር ወንጀል" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል" ሰርታለች ብሏል።

ተቋሙ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እስራዔል በጋዛ ባለው ጦርነት በሀይል በተደረገ ማፈናቀል እና የዘር ፍጅት ወንጀል ተጠያቂ ናት ሲል ገልጿል።

90 በመቶ የሚጠጉ የጋዛ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል ነው ያለው። #morningstar

@thiqaheth

THIQAH

14 Nov, 18:13


"7.3 ሚሊዮን ኢትዮጵያውን በወባ በሽታ መያዛቸው ተረጋግጧል"  - WHO

በኢትዮጵያ ከ7 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወባ መጠቃታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 1,157 ሰዎች በወባ በሽታ መሞታቸውን ድርጅተ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የወባ በሽታ በኢትዮጵያ ትልቅ የጤና ስጋት መሆኑንም ጠቁሟል።

69 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች የወባ በሽታ አደጋ ባለበት አካባቢ እንደሚኖሩ አመላክቷል። #anadoluagency

@thiqaheth

THIQAH

14 Nov, 03:54


ሩሲያ የአፍሪካን 20 ቢሊዮን ዶላር ብድር ሰረዘች።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ለአፍሪካ ሀገራት በብድር መልክ ከሰጠችው ገንዘብ ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን መሰረዟን አስታውቀዋል።

እንደ ፑቲን ገለፃ  ከሆነ ሀገራቱ ገንዘቡን ለልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠቀሙበት በማሰብ ነው ብድሩ የተሰረዘው።  

የ2024 የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ ከሁለት ሳምንት በፊት መካሄዱ ይታወሳል።
#uawire

@thiqaheth

THIQAH

14 Nov, 03:46


"ፈረንሳይ የቅኝ ግዛት ወንጀል ፈፅማለች" - አዘርባጃን

በባኩ እየተካሄደ በሚገኘው የኮፕ 29 ጉባዔ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሊየቭ ፓሪስ በኒው ካሌዶኒያ ወንጀል ፈጽማለች ሲሉ ወንጅለዋል።

ይህን የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተከትሎ የፈረንሳይ ኢኮሎጂ ሚኒስትር ፓኒየር ሩንቸር በጉባዔው ለመሳተፍ ወደ አዘርባጃን የሚያደርጉትን ጉዞ ሰርዘዋል።

ሩንቸር እንደጉባኤ አዘጋጅ ሀገር ተቀባይነት የሌለው ንግግር ነው ያደረጉት ብለዋል።

ከፈረንሳይ የመገንጠል ፍላጎት ያላት ኒው ካሌዶኒያ ሰሞኑን በተነሳ አመፅ 13 ሰዎች በፈረንሳይ ፓሊሰሰ ተገድለዋል። #aljazeera

@thiqaheth

THIQAH

10 Nov, 12:52


ኳታር ከእስራኤል እና ሀማስ ሽምግልና ራሷን አገለለች።

ኳታር ከዚህ ውሳኔዋ ቀደም ብላ በዶሀ የሚገኘው የሀማስ ቢሮ እንዲዘጋና ቡድኑ ለቆ እንዲወጣ አሳስባለች።

የገልፍ ሀገሯ ኳታር የሀማስ ቢሮ እንዲዘጋ የወሰነችው ከአሜሪካ በተደጋጋሚ ጫና ስለደረሰባት መሆኑ ተገልጿል።

ዶሀ ከአሜሪካ እና ግብፅ ጋር በመሆን የጋዛ ጦርነት እንዲቆም ጥረት ስታደርግ ነበር። #politico

@thiqaheth

THIQAH

10 Nov, 12:50


እንግሊዝ በ2025 ለ45,000 ሠራተኞች የስራ ቪዛ አቀረበች።

እንግሊዝ በግብርና እና እንስሳት እርባታ ዘርፍ የገጠማትን የሠራተኛ እጥረት ለመቅረፍ ከጥር ጀምሮ የሠራተኛ ቪዛ ለማቅረብ ማታቀዱን አስታውቃለች።

አዲሱ እቅድ የሀገሪቱን የምግብ ምርት አቅርቦት ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ከ18 አመት በላይ የሆነ እና ጤንነቱ የተረጋገጠ ማንኛውም ሰው ህጋዊ ፈቃድ ባለው ቀጣሪ ተቋም በኩል ቪዛ ማግኘት እንደሚችልም ተመላክቷል።

ሀገሪቷ በ2025 ለ45,000 ሠራተኞች የስራ ቪዛ እንዳቀረበች ተነግሯል። #nairametrics

@thiqaheth

THIQAH

09 Nov, 16:19


በፓኪስታን አጥፍቶ ጠፊ ባቡር ጣቢያ ላይ በፈጸመው ጥቃት 20 ሲሞቱ 53 ሰዎች መቆሰላቸው ተነገረ።

ጥቃቱ ስልጠና አጠናቀው ወደ ስምሪት ሲሄዱ በነበሩ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የኩዌታ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጥቃቱ የባሎችስታን ነጻነት ግንባር (BLF) ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ ጥቃቱን አውግዘው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ፈጣን ህክምና እንድያገኙ ለህክምና ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ #shine #novinite

@thiqahEth

THIQAH

09 Nov, 16:14


''ከኢራን የተላከ ትራምፕ ላይ ግድያ ሊፈጸም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል''  - አሜሪካ

''በእስራዔልና በጸረ  ኢራን ወገኖች የተቀነባበረ ሴራ ነው''  - ኢራን

ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ትዕዛዝ ተቀብሎ ከምርጫ በፊት በፕሬዝዳንቱ ላይ ግድያ ሊፈጽም ነበር የተባለ ተጠርጣሪ መያዙን የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ፍትህ ቢሮው፣ ከኢራን የተላከ ትራምፕ ላይ ግድያ ሊፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል" ነው ያለው።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማዔል ባጋይ በበኩላቸው፣ በሀገራቸው ላይ ተመሳሳይ ውንጀላ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ፣ "በእስራዔልና በጸረ ኢራን ወገኖች የተቀነባበረ ሴራ ነው" ሲሉ ነው ውንጀላውን ውድቅ ያደረጉት።

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ በዜግነት አፍጋኒስታዊ እንደሆነ በገለጸው የ51 አመቱ ተጠርጣሪ ፋራድ ሻከር ላይ ክስ እንደመሰረተበት አስታውቋል፡፡ #anadoluagency   #asiaone

@thiqaheth

THIQAH

08 Nov, 16:20


በሆላንድ እስራዔላውያንን ኢላማ ባደረገው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ።

እንዲሁም በድርጊቱ የተጠረጠሩ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአምስተርዳም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የእስራዔሉ ማካቢ እግር ኳስ ቡድን ከሆላንዱ አያክስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ለድጋፍ የሄዱ እስራዔላውያን በአምስተርዳም ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

የእስራዔል መንግስት ዜጎቹን ለማምጣት ሁለት የጭነት (cargo) አውሮፕላን ወደሆላንድ መላኩ ተዘግቧል፡፡ #5pillars

@thiqaheth

THIQAH

08 Nov, 16:17


የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (SADC) በሞዛምቢክ ጉዳይ ለመምከር ''ልዩ ጉባዔ'' ጠራ፡፡

ሳድክ ጉባዔውን የጠራው በሞዛምቢክ እየተባባሰ በቀጠለው አመጽ ዙሪያ ለመምከር እና መፍትሄ ለማበጀት ነው ተብሏል፡፡

አመጹን ተከትሎ ትላልቅ የንግድ ተቋማት የንብረት ዘረፋና የገንዘብ ውድመት እንደገጠማቸው ገልጸዋል፡፡

የሞዛምቢክ መከላከያ ሚኒስቴር አመጹን ለማረጋጋት ተጨማሪ የጦር አባላትን ማሰማራቱን ቢገልጽም የዜጎች ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ መጥቷል፡፡

የሞዛምቢክ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ባሳለፍነው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ባለመቀበላቸው ነው ነው አመጹ የተቀሰቀሰው፡፡ #sabcnews

@thiqaheth

THIQAH

07 Nov, 18:31


ኦላፍ ሾልዝ የገንዘብ ሚኒስትራቸውን ከኃላፊነት አነሱ፡፡

የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ የፖለቲካ ተቀናቃኛቸውን እና የገንዘብ ሚኒስትሩን ክርስቲያን ሊንድመርን ከኃላፊነት አንስተዋል፡፡

በሦስት ፓርቲዎች ጥምረት እየተመራች የምትገኘው ጀርመን አሁን ላይ ፖለቲካዊ ቀውስ ገጥሟታል ተብሏል፡፡

ፓርቲዎች በትላልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ማለትም በበጀት አስተዳደር፣ ስደት እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ላይ መስማማት አለመቻላቸው ተዘግቧል፡፡ #malaymail

@thiqaheth

THIQAH

07 Nov, 18:28


ሩዋንዳ ወደጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ ላከች፡፡

በጦርነት ለተጎዳችው ጋዛ የተላከው ድጋፍ 19 ቶን የምግብ እህልና የህክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ድጋፉን አስመልክቶ የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ኪጋሊ ''ጦርነቱ እንዲቋጭና የንጹሃን ህይወት እንዲጠበቅ ፍላጎት አላት'' ብሏል፡፡ #anadoluagency

@thiqaheth

THIQAH

07 Nov, 18:26


ማሊ የተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪ ሀይል በህዳር ወር ጠቅልሎ እንደሚወጣ አረጋገጠች፡፡

የሰላም አስከባሪ ተልዕኮው በተያዘው ህዳር ወር አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ለቆ እንደሚወጣ የማሊ ወታደራዊ መንግስት አስታውቋል፡፡

ማሊ ተ.መ.ድ ያሰማራው ሀይል ተልዕኮውን በአግባቡ አልተወጣም በሚል ከባለፈው አመት ጀምሮ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ስታነሳ ቆይታለች፡፡

15, 2024 አባላትን የያዘው የተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪ ሀይል (MINUSMA) ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ ላለፉት 9 አመታት በሀገሪቱ ሰፍሮ ይገኛል። #rabiulislam

@thiqaheth

THIQAH

07 Nov, 10:53


በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የጅምላ እስር እንድቆም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ፡፡

አምንስቲ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በክልሉ ያሉ ካምፖች በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች መሞላታቸውን ባወጣው በሳተላይት የተደገፈ የምስል ማስረጃ አረጋግጧል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የጸጥታ አካላት ''ህግን ለማስከበር እና የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ'' በሚል ሰበብ የጅምላ አፈሳ እየፈጸሙ ነው ሲል አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ዳኞችና ምሁራኖች የዘፈቀደ እስሩ ቀዳሚ ሰለባ መሆናቸውንም በሳተላይት ባወጣው መግለጫ አብራርቷል፡፡

የአምንስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ፣ "ኢትዮጵያ ብሄራዊ፣ ቀጠናዊና አለማቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎችን ባለመወጣት አዲስ ምዕራፍ ጀምራለች'' ብለዋል፡፡ #amnestyinternationaluk

@thiqaheth

THIQAH

07 Nov, 10:50


''በትብብራችን እናተርፋለን በውዝግባችን ደግሞ እንከስራለን''  - ቻይና

''የጋራ ወዳጆች ሁነን አንቀጥላለን''  - ሩሲያ

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ከቻይናው አቻቸው ፕሬዝዳንት ዥ ጀፒንግ ጋር የመጀመሪያ የስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡

በምርጫው ላገኙት ድል ፕሬዝዳንት ትራምፕን እንኳን ደስ አለዎት ያሉት ፕሬዝዳንት ዥ፤ ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በተገቢው መንገድ ያስተካክላሉ ብለዋል፡፡

የቻይና - አሜሪካ ግንኙነት የሁለቱንም ሀገራት የጋራ ጥቅም በማስከበር ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ፣ ጤናማ እና ዘላቂ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በአንጻሩ ሌላኛዋ የዓለም ሀያላን ሀገር ሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕን በከፍተኛ ድምጽ በማሸነፍዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

ፑቲን ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ድሜትሪ ሜድቬዴቭ ተገኝተዋል፡፡

''ፕሬዝዳንት ትራምፕ አንድ ጠቃሚ ጥራት አለው፤ ነጋዴ መሆኑ ሁለቱ ሀገራ ኢኮኖሚየቻውን ለማሳደግ ይጠቅማል'' ሲሉ ሜድቬዴቭ በቴሌግራም ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ #aa  #miamiherald

@thiqaheth

THIQAH

06 Nov, 15:37


ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እየላኩላቸው ይገኛሉ፡፡

የእስራዔሉ ጠ/ሚ ቢኒያም ኒታንያሁ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የመልካም ምኞት መልዕክት በማስተላለፍ ቀዳሚ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ደግሞ ሁለተኛው ናቸው፡፡

ሁለቱ መሪዎች ገና ምርጫው ሰይጠናቀቅ በሂደት እያለ ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

ትራምፕ መመረጣቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ደግሞ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ የዩክሬኑ ፕ/ት ቮለድሚር ዘለንስኪ፤ የፈረንሳዩ ፕ/ት ኢማኑዔል ማክሮንና የህንዱ ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞድ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከተቋማት መካከል የዓለም እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንቲፋንቲኖና የአውሮፓ ህብረት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ #theweek

@thiqaheth

THIQAH

05 Nov, 14:37


#AddisAbaba

በሕገ-ወጥ እርድ የተከናወነ ከ2,800 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ሥጋ ማስወገዱን ድርጅቱ አስታወቀ፡፡

በሦስት ወራት ውስጥ ከ1, 800 በላይ የእንስሳት እርድ ለማከናወን በእቅድ ተይዞ እንደነበር የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

"ከእቅዱ ውስጥም ከ1 መቶ 2 ሺሕ በላይ በሚሆኑ እንስሳት ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እርድ ተከናውኗል" ብለዋል፡፡

ኃላፊው ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አርሶአደር እና ከተማ ግብርና ኮሚሽን እንዲሁም ከሌሎች ጋር በመሆን በሕገ-ወጥ እርድ ላይ የክትትል ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ተገልጸዋል።

በክትትላቸውም የሚያጋጥሙ ሕገ-ወጥ እርዶችን የሚያስወግዱት አሰራር ስለመኖሩ አስረድተው፤ በሦስት ወራት ውስጥ ከ2 ሺሕ 8 መቶ ኪሎግራም በላይ የሚመዝን በሕገ-ወጥ መንገድ የተከናወነ እርድ መወገዱን ጠቁመዋል፡፡

የሩብ ዓመቱ የበዓላት ወቅት እንደነበር፤ የሚከናወነው የእንስሳት እርድ የሚጨምርበት ሁኔታ እንዳለም ገልጸዋል፡፡

ለህብረተሰቡ ደህንነቱ የተጠበቀና የተመረመረ የእርድ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸው፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የጨመረበት ሁኔታ መኖሩንም አመላክተዋል፡፡ #AhaduRadio

@thiqaheth

THIQAH

05 Nov, 13:52


''በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል''  - አሜሪካ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስር አቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ብሊንከን ለሁለት አመታት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነት (COHA) ሙሉ በሙሉ እንድተገበር ጠይቀዋል፡፡

ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ጥረት እንደሚፈግፉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ የውስጥ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ፖለቲካዊ ውይይት ማካሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሀገራቸው አሜሪካ በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት እንደሚያሳስባት በስልክ በተደረገው ውይይት ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማት ሚለር ተናግረዋል፡፡  

ብሊንከን እና አቢይ በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ቀጠናዊ ውጥረትም ተመካክረዋል ተብሏል፡፡ #usembassyaddisababa

@thiqaheth

THIQAH

05 Nov, 06:15


"በዓባይ ወንዝ ላይ የሚወሰዱ የተናጠል እርምጃዎችን እቃወማለሁ" - ግብፅ

የግብፅ የውሃ ሀብትና ተፋሰስ ሚኒስትር ሀኒ ሰዊላም ሀገራቸው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የሚያከናውኑትን ልማት እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ የአለማቀፉን ህግ መሰረት አድርገን ልንሰራ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ፣ ይሁን እንጂ የትኛውም የተፋሰሱ አባል ሀገር የተናጠል እርምጃ መውሰድ የለበትም ብለዋል።

ሰዊላም ይህን ያሉት ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡና በግብፅ የተካሄደውን የተፋሰስ ወንዞች አስተዳደር (River Basin Management) ስልጠና ለወሰዱ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በሰጡበት ወቅት ነው። #egyptindependant

@thiqaheth

THIQAH

05 Nov, 06:12


በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ3000 አለፈ።

13 ወራት በዘለቀው የእስራኤል እና ሂዝቦላህ ግጭት ከ3000 በላይ ሊባኖሳውያን መገደላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ አሀዝ ባለፉት 20 አመታት ከተገደሉት ዜጎች በእጥፍ በልጦ ተገኝቷል። #time

@thiqaheth

THIQAH

04 Nov, 14:29


''ኢራን ኃይለኛ ጥቃት ለማድረስ እቅድ ይዛለች'' - ሪፖርት

ቴህራን፣ ''ውስብስብ እና አዲስ''  ያለችውን ጥቃት ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኗን ለተለያዩ አረብ ሀገራት በዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖቿ በኩል ገልጻለች ሲል ዌል ስትሪት ጆርናል ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፡፡      

ኢራን በእስራዔል ላይ 'አደርሰዋለሁ' ላለችው ጥቃት ካሁን በፊት ያልተጠቀመቻቸውን ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በጥቅም ላይ እንደምታውልም ሪፖርቱ ያስረዳል።

ሪፖርቱ፣ "ኢራን ኃይለኛ ጥቃት ለማድረስ እቅድ ይዛለች" ይላል።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ካሚኒ፣ ሀገራቸው በእስራዔልና በአሜሪካ ላይ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ተናግረው ነበር፡፡

አሜሪካ በበኩሏ፣ እስራዔል የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች በኋላ ኢራን ምላሽ እንዳትሰጥ ስታሳስብ ቆይታለች፡፡ #ukrinform  #wsj

@thiqahEth

THIQAH

04 Nov, 14:25


''ባሳለፍነው ሳምንት 50 የፍልስጤም ህጻናት በእስራዔል ጥቃት ህይወታቸውን አጥተዋል''  -  UNICEF

እስራዔል በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በጋዛ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 50 ህጻናት መገደላቸውን የተ.መ.ድ ህጻናት ፈንድ (UNICEF) አስታውቋል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው በሰሜን ጋዛ በምትገኘውና እስራዔል ሰሞኑን ተደጋጋሚ ጥቃት በፈጸመችባት የጃባሊያ ግዛት ነው፡፡

የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ሩሴል ባሉት መሠረት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተጠለሉባቸው ሁለት የመኖሪያ ህንጻዎች የእስራዔል ጥቃት ኢላማ ነበሩ። #alitopchi

@ThiqahEth

THIQAH

04 Nov, 10:03


በዩጋንዳ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ የተከሰተ የመብረቅ አደጋ የ14 ሕፃናት ሕይወት ተቀጠፈ።

ፓላቤክ በተሰኘው የስደተኞች በመጠለያ ካምፕ በደረሰው የመብረቅ አደጋ የእግር ኳስ ጨዋታ እረፍት ላይ የነበሩ 14 ታዳጊዎች ሞቱ።

ከሟቾቹ ባሻገር፣ 34 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሰለባ መሆናቸው ተሰምቷል።

የስደተኞች መጠለያ ካምፑ ከ80 ሺሕ በላይ ሰዎች የተጠጉበት ነው። #TRTAFRICA

@ThiqahEth

THIQAH

04 Nov, 08:53


በኢንዶኔዥያ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ 10 ሲሞቱ፣ ከ10 ሺሕ በላይ ተፈናቀሉ።

የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች የጉዳት መጠኑን እያጠኑ ነው የተባለ ሲሆን፣ 10 ሺሕ 295 ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

አደጋው የተከሰተው የቱሪስቶች መዳረሻ በሆነው የሎዎቶቢ ላኪ ላኪ ተራራ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት ላይ እንደተከሰተ ተገልጿል፡፡

ነዋሪዎችን ከአካባቢው ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ ቃል አቀባይ አብዱል ሙሃሪ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ቢያንስ 10 ሲሞቱ፣ ከ10 ሺሕ በላይ መፈናቀላቸው ተሰምቷል። #trtworld

@thiqaheth

THIQAH

04 Nov, 08:48


እስራዔል የእግረኛ ጦሯን ወደ ሶሪያ አሰማራች፡፡

እስራዔል የእግረኛ ጦሯን ወደ ሶሪያ ማሰማራቷ ተሰምቷል።

የዘመቻው ዋና አላማ ከኢራን ጋር ግንኙነት አለው የተባለውን የሶሪያ ዜግነት ያለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

ሶርያዊው አሊ ሱሌማን አል አሲ እስራዔል በተቆጣጠረቻቸው የጎላን ኮረብታዎች የሚደርሱትን ጥቃቶች ያቀነባብራል በሚል ነው ከእስራዔል ውንጀላ የቀረበበት፡፡

አሊ ሱሌማን በአሁኑ ወቅት በእስራዔል ወታደሮች መያዙን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ #pbsnews #news18

@thiqaheth

THIQAH

04 Nov, 08:45


የናይጄሪያ ፖሊስ በሳይበር ወንጀል የጠረጠራቸውን 113 የውጭ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።

የናይጄሪያ ፖሊስ በሳይበር ወንጀል የጠረጠራቸውን 113 የውጭ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነግሯል።

የፖሊስ ቃል አቀባዩ ኦሉምይዋ አጆቢ ተጠርጣሪቆቹ፣ ''ከፍተኛ ደረጃ'' ተብሎ የሚገለጸውን የሳበር ወንጀል ፈጽመዋል ብለዋል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል 87ቱ ወንዶች ሲሆኑ 26ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

አክለው፣ በፖሊስ ከተያዙት ተጠርጣሪዎች ውስጥ በብዛት የቻይናና የማሌዥያ ዜጎች እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡ #punchnewspapers

@thiqaheth

THIQAH

03 Nov, 19:01


"10,000 ወታደሮች አደጋው ወደተከሰተበት ስፍራ ተሰማርተዋል''  - ስፔን

በስፔን የተከከሰተው የጎርፍ አደጋ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ የሀገሪቱ ጦር እና ፖሊስ አባላት የአደጋ ጊዜ ስምሪት መላካቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

10,000 ወታደሮች አደጋው ወደተከሰተበት ስፍራ መሰማራታተውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ጎርፉ በሀገሪቱ ታሪክ ከባድ አደጋ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በአደጋው እስካሁን ድረስ 215 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የቫሌንሺያ ግዛት አስተዳዳሪዎች አሁንም ቢሆን ከጸጥታ አካላት ተጨማሪ የሰው ኃይል እንዲመደብላቸው በመጠየቅ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ #dawn

@thiqaheth

THIQAH

03 Nov, 18:54


"ዓለም አቀፋዊ የበላይነትን ለመጋፈጥ ሁሉንም አስፈላጊ መስፈርቶች እንጠቀማለን'' - ኢራን

ኢራን በእስራዔልና በአሜሪካ ላይ ጠንካራ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል አስታወቀች፡፡ 

የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ሁለቱ ሀገራ በኢራን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ካላቆሙ ሀገራቸው የአጸፋ እርምጃ እንደምትዋስድ አስጠንቅቀዋል፡፡

ካሚኒ፣ ''ዓለም አቀፋዊ የበላይነትን ለመጋፈጥ ሁሉንም አስፈላጊ መስፈርቶች እንጠቀማለን'' ሲሉ ተደምጠዋል፡፡  

እስራዔል ከአንድ ወር በፊት ከኢራን የተሰነዘረባትን የሚሳዔል ጥቃት ለመበቀል ከሳምንት በፊት በኢራን ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች፡፡ #albawaba

@thiqaheth

THIQAH

02 Nov, 14:01


እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችው ጥቃት 52 ሰዎች ሲገደሉ 72 የሚሆኑት ቆስለዋል።

እስራኤል በሊባኖስ አደረሰችው በተባለ ጥቃት 52 ሰዎች ሲገደሉ፣ 72 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል።

እስራኤል እና ሂዝቦላህ ግጭት ውስጥ ከገቡበት ከባለፈው ወር ጀምሮ 2,900 ሊባኖሳውያን ተገድለዋል።

13,150 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሊባኖስ የሚካሄደው ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት እንድደረግ ጥረት ቢደረግም እስካሁን ድረስ አልተሳካም። #hindustantimes

@thiqaheth

THIQAH

02 Nov, 13:56


#Update #Dera

"አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 ሚሊዮን ብር ከፍለን ሌላውን እየፈለግን ነበር ግን ቀድመው ጀናዛቸውን ላኩልን" - ቤተሰቦች

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር መገደላቸው መገለጹ ይታወሳል።

የዛሬ ወር ገደማ ሸይኹ የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር እሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የአንድ አካባቢ ሰዎች በታጣቂዎች የታገቱት።

በወቅቱ ከታገቱት ሰዎች በተጨማሪ ከ80 በላይ የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውም ተገልጿል። በተደረገው የገንዘብ ድርድር ከታገቱት ሰዎች መካከል የሸይኹ እናትና ባለቤታቸው ጨምሮ ጥቂት ሰዎች የተለቀቁ ቢሆንም ሼይኽ ሙሀመድ መኪንን ጨምሮ 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተገድለዋል።

አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 የሚሆነው ከፍለው ቀሪውን እየፈለጉ እንደነበር፣ ነገር ግን ቀድመው ጀናዛ ላኩልን የተፈፀመብንን ከባድ ግፍ ነው ያጣነው ታላቅ አሊም፣ አስታራቂ ሽማግሌ የነበሩ ሰው ነበር ያለምንም ምክንያት ነው በግፍ የተገደሉት መባሉን ሀሩን ሚዲያ አስነብቧል።

@thiqaheth

THIQAH

01 Nov, 15:27


#Update

በስፔኑ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 205 ደረሰ።

በስፔይን ቫሌንቪያ ከተማ በተከሰተው የከፋ የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 205 አሻቅቧል።

ጎዳናዎች አሁንም ድረስ አደጋ በደረሰባቸውና በተገለበጡ ተሽከርካሪዎች ተሞልተዋል።

በቫሌንቪያ የንጹህ ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፤ የስልክ አገልግሎት ተስተጓጉሏል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት በመጪዎቹ ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጥል በመግለፅ ከወድሁ ጥንቃቄ እንድደረግ አሳስበዋል። #scrippsnews

@thiqaheth

THIQAH

01 Nov, 13:41


#Ethiopia #Dera

ታግተው የነበሩት የመስጅድ ኢማም ከነ 12 ቤተሰቦቻቸው መገደላቸው ተሰማ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ አካባቢ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 ቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ መገደላቸው ተሰምቷል።

ሼይኽ ሙሀመድ ከሳምንታት በፊት የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው የተገለጸው።

ከቀናት በኋላ በተደረገ የገንዘብ ድርድር የኢማሙን እናት እና ባለቤት ጨምሮ ጥቂት ሰዎች መለቀቃቸው ተጠቁሟል።

ኢማሙን ጨምሮ 12 ቤተሰቦቻቸው ግን በዛሬው እለት መገደላቸው ተሰምቷል። ግድያው የተፈፀመው መንግስት "አሸባሪ" ብሎ በፈረጀው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አማካኝነት መሆኑን ከስፍራው ለሀሩን ሚዲያ የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ። #ሀሩንሚዲያ

@thiqaheth

THIQAH

01 Nov, 07:50


35 "የአይኤስአይኤስ" ታጣቂዎች በአሜሪካ ጥቃት መገደላቸው ተሰማ።

አይኤስአይኤስ በበኩሉ በዚህ ዓመት ብቻ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ 153 ጊዜ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

አሜሪካ በሶሪያ በሚገኘው የቡድኑ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሟን የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ (USCETCOM ) አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በኢራቅና በሶሪያ በሚገኙ የአይኤስአይኤስ ይዞታዎች ላይ የሚደረገው ኦፕሬሽን ከባለፈው አመት በእጥፍ ጨምሯል ብሏል፡፡

አይ ኤስ አይ ኤስ በበኩሉ፣ በዚህ አመት ብቻ ኢራቅና ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ቦታዎች ላይ 153 ጊዜ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል፡፡ #telegraphindia

@thiqaheth

THIQAH

01 Nov, 07:44


የእስራዔል ጦር የሰው ኃይል እጥረት ገጥሞታል ተባለ፡፡

ከሃማስና ከሂዝቦላህ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችው እስራዔል በአሁኑ ሰዓት ሁለት ብርጌድ ተጠባባቂ ወታደሮች ብቻ እንዳሏት ጦሩ አስታውቋል፡፡

እስራዔል በሊባኖስ ተጨማሪ የውጊያ ግንባር ለመክፈት አቅዳለች በተባለበት ወቅት ነው እስራኤል የወታደር እጥረት እንደገጠማት የተዘገበው፡፡

ከአንድ አመት በላይ የዘለቀው ጦርነት ያሰለቻቸው ወጣቶች ጦሩን የመቀላቀል ፍላጎታቸው ቀንሷል ተብሏል፡፡

ይህ ክስተት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢኒያም ኒታንያሁና በመከላከያ ሚኒስትሩ ዮኣቭ ጋላንት በኩል ልዩነት መፍጠሩ ተሰምቷል፡፡ #france24 #defencesecurityasia

@thiqaheth

THIQAH

31 Oct, 15:45


በሞዛምቢክ የምርጫ ውጤትን ለመቀወም የወጡ ቢያንስ 10 ሰዎች በፖሊስ ተገደሉ፡፡

የሞዛብቢክ መንግስት በሀገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ 'ምርጫው ተጭበርብሯል' ባሉ ዜጎች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ምርጫው ከጅምሩ ግልጸኝነት የጎደለው እንደሆነ አለማቀፍ ታዛቢ ድርጅቶችም ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱን ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 10ሩ በፓሊስ መገደላቸው ተመላክቷል።

ሞዛምቢክ በፈረንጆቹ 1975 ከፖርቹጋል ነጻ ከወጣች በኋላ ላለፉት 40 አመታት በፍረሊሞ ፓርቲ እየተመራች ትገኛለች፡፡ #irishexaminer

@thiqaheth

THIQAH

31 Oct, 15:41


#Update!

በስፔን የሟቾች ቁጥር ከ95 ማለፉ ተሰማ።

በቫሌንሽያ ከተማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ
የሟቾች ቁጠር ከ95 ማለፉ ተሰምቷል።

አደጋው በድልድዮችና ህንጻዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በማድሪድና ባርሴሎና ከተሞች ት/ቤቶች እንድዘጉ፤ የባቡር ትራንስፖርት በጊዜያዊነት እንዲቆሙ ተወስኗል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በጎርፉ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት መልሰን እንገነባቸዋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። #irishexaminer

@thiqaheth

THIQAH

30 Oct, 15:21


ሶማሊያ የኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈጻሚ በሦስት ቀናት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች፡፡

ላለፉት ሰባት ወራት በሶማሊያ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈፃሚ በመሆን ያገለገሉት አቶ አሊ መሀመድ በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።

በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና አለም ዓቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የተጻፈው ደብዳቤ፣ አቶ አደም ለቀው እንዲወጡ የተወሰነው ከድፕሎማሲያዊ ኃላፊነታቸው ውጭ የ1961ዱን የቬና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት ጥሰው በመገኘታቸው ነው ብሏል።

ባሳለፍነው አመት ሚያዝያ ላይ በሞቃድሾ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሃመድ በ72 ሰዓታት ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡ #horseedmedia

@thiqaheth

THIQAH

30 Oct, 15:18


ፈረንሳይ በትላንትናው እለት ብቻ 100 ሰዎችን የቀጠፈውን የእስራዔል ጥቃት አወገዘች፡፡

ፓሪስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ፣ በተለይ የጤና ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች እንደሚያሳስቧት ገልጻለች፡፡

ፈረንሳይ፣ እስራዔል በጋዛ የምታደርገውን ጫና እንድትቀንስና ሰብዓዊ እርዳታ በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆን አሳስባለች፡፡

እስራዔል በትናንትናው እለት ጋዛ ውስጥ በሚገኝ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ባደረሰችው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 100 መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ ፈሰንሳይ ድርጊቱን በጥብቅ አውግዛለች። #aa

@thiqaheth

THIQAH

27 Oct, 10:21


#Update!

በፊሊፒንስ የሟቾች ቁጥር 100 ደረሰ።

ከሦስት ቀናት በፊት በደረሰው የአውሎ ነፋስ አደጋ የሀገሪቱ ግማሽ ህዝብ ማለትም
ወደ 5.7 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

በአደጋው የጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው በውል አልተገለፀም።

የፊሊፒንስ የብሔራዊ አደጋ ኤጀንሲ "ብዙ ዜጎችን በህይወት ለማትረፍ እየሞከርን ነው" ብሏል።

ከቀናት በፊት በአውሎ ነፋሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 76 መሆናቸው መገለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ ወዲህ ደግሞ የሞቾች ቁጥር ቁጥር 100 ደርሷል። #digitaljoirnal #afp

@thiqaheth

THIQAH

27 Oct, 10:16


ኢራን የፀጥታው ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጠየቀች።

ኢራን ይህን ጥሪ ያቀረበችው እስራኤል በትናንትናው እለት ያደረሰችውን ጥቃት እንድመረምርላት መሆኑ ተገልጿል።

የኢራን የውጭ ጉዱይ ሚኒስቴር ለተ.መ.ድ በፃፈው ደብዳቤ፣ "የእስራኤል መንግስት እርምጃ ቀጠናውን እንዳይረጋጋ በማድረግ ለዓለም አቀፍ ሰላም ስጋትን ፈጥሯል" ሲል ወቅሷል።

ሚኒስቴሩ አክሎ፣ ኢራን "የዓለም አቀፍ ህግን መሰረት በማድረግ ለሽብር ጥቃት ህጋዊ ምላሽ የመስጠት መብቷን ልትጠቀምበት ትችላለች" ሲል አስታውቋል። #mehernews

@thiqaheth

THIQAH

26 Oct, 19:54


በሱዳን በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ጥቃት 124 ሰዎች ተገደሉ።

ከ100 በላይ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

በጄነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው ቡድን በኤል ገዚራ ከተማ ባደረሰው ጥቃት 124 ንፁሃን መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ ጄነራል አቡአግላ ከይካል የተባለው የጦር መሪ እጁን ለሀገሪቱ ጦር መስጠቱን ተከትሎ የፈጥኖ ደራሹ ሀይል ተደጋጋሚ ውጊያዎችን ከፍቷል። #onmanorama

@thiqaheth

THIQAH

26 Oct, 19:52


"ኢራን ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ገደብ አይወስናትም"  - አባስ አራግቺ

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅሟን እና የግዛት አንድነቷን ለማስከበር ወደኋላ አትልም ብለዋል።

ኢራን በእስራኤል ላይ የወሰደችው እርምጃ አንዱ የአቅም ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

እስራኤል ከሦስት ሳምንት በፊት ከኢራን ለደረሰባት የሚሳዔል ጥቃት በወሰደችው የአፀፋ እርምጃ 9 የኢራን ወታደሮች ተገድለዋል። #irna

@thiqaheth

THIQAH

26 Oct, 19:52


እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈፀሟ ተሰማ።

እስራዔል በሦስት አቅጣጫ የሚሳዔልና የድሮን ጥቃት መፈፀሟን የእስራኤል እና የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

ኢራን ኦክቶበር 1/2024 ከ250 በላይ የሚሳኤል ጥቃት ከፈፀመች በኋላ እስራኤል የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ በተደጋጋሚ ስትዝት ነበር።

የኢራን ብሄራዊ ቴሌቭዥን በዋና ከተማዋ "ከባድ ፍንዳታዎች" መሰማቱን ዘግቧል።

የእስራዔል ጦር በኢራን ላይ በፈፀመው ጥቃት ከነዳጅ ጣቢያዎች ይልቅ ወታደራዊ ካምፖችን ኢላማ እንዳደረገ ገልጿል።
#axios #thenewarab #afp

@thiqaheth

THIQAH

25 Oct, 15:08


በፊሊፒንስ 76 ሰዎች በድንገተኛ የአውሎ ነፋስ አደጋ ህይወታቸው አለፈ፡፡

ከደቡብ ቻይና የተነሳው አውሎ ነፋስ ያስከተለው ከባድ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ 320, 000 ሰዎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡

36 በረራዎች መሰረዛቸውንና 7510 ሰዎች በአየር ማረፊያና ለሰዓታት መስተጓላቸውንና የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በአውሎ ነፋስ አደጋ በተደጋጋሚ የምትጠቃው እስያዊቷ ሀገር ፊሊፒንስ ባለፈው ወር መስከረም ላይ ባጋጠማት ተመሳሳይ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አልፎ ነበር፡፡ #aljazeera

THIQAH

25 Oct, 09:43


ካናዳ ስደትኞችን መቀበል በጊዜያዊነት እንደምታቆም አስታወቀች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ካናዳ የህዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ የዜጎቿንና የስደተኞችን ቁጥር ለማመጣጠን እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሟላ የጤና አገልግሎት፤ የቤት አቅርቦት እና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማዳረስ የተረጋጋ የህዝብ ስርጭት ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2021 የተሰራ ጥናት እንደሚያመላክተው 23 በመቶ የሚሆኑት የካናዳ ዜጎች በውጭ ሀገር የተወለዱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡

ካናዳ ከእስያ፣ መካከለኛው ምሥራቅና አፍሪካ የሚሄዱ ስደተኞችን ታስተናግዳለች፡፡ #France24

@thiqaheth

THIQAH

24 Oct, 11:16


ኡጋንዳ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የመጀመሪያውን ሞት አስመዘገበች፡፡

በሀገሪቱ 155 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ኡጋንዳ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽ ወደሀገሯ መግባቱን ያረጋገጠችው ከሦስት ወር በፊት ነበር፡፡

ወረርሽኙ በዓለም የጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ተደርጎ ተፈርጇል፡፡
#dailymonitor

@thiqaheth

THIQAH

23 Oct, 16:35


#Update

ሂዝቦላህ በሀሸም ሳፈዲን ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ።

የሊባኖሱ ታጣቂ ቡዲን ሳፈዲን በእስራኤል የአየር ላይ ጥቃት መገደሉን አረጋግጧል።

የእስራኤል ጦር ሀሰን ናስራላህን በመተካት ቡድኑን ለአንድ ወር የመሩት አዲሱ የሂዝቦላህ መሪ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቆ ነበር።

ሂዝቦላህ እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት በሁለት ወር ውስጥ ሁለት መሪዎቹን ተነጥቋል። #shafaqnews

@ThiqahEth

THIQAH

23 Oct, 10:23


አዲሱ የሂዝቦላህ መሪ መገደሉን የእስራዔልል ጦር አስታወቀ፡፡

ሀሰን ናስራላህን በመተካት የቡድኑ መሪ ሆነው የተመረጡት ሀሸም ሳፈዲን የተገደሉት በቤሩት በተፈጸመ የአየር ላይ ጥቃት ነው፡፡

ሂዝቦላህ የሀሸም ሳፈዲንን ግዲያ በተመለከተ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

የሂዝቦላህ የቀድሞ መሪ ሀሰን ናስራላህ በተመሳሳይ ጥቃት በእስራዔል የተገደሉት ባሳለፍነው ወር መስከረም ውስጥ ነበር፡፡ #euronews

@thiqaheth

THIQAH

22 Oct, 15:56


የምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል ያሉ ሞዛምቢካውያን ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ።

ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ብሄራዊ ምርጫ ባካሄደች ማግስት በገጠማት ግርግር ፖሊስ ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

ምርጫውን ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል የተባሉት ተቀናቃኙ ፖለቲከኛ ቬናንሲዮ ሞንድላኔ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አውጀዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ሁለት የፖዴሞስ ፓርቲ አባላት በጸጥታ ሀይሎች መገደላቸው ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ #rtnews #upi

@thiqaheth

THIQAH

22 Oct, 15:52


ደቡብ ኮሪያ ዩክሬንን ልታስታጥቅ እንደምትችል አስታወቀች፡፡

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ ማድረጓን የምትቀጥል ከሆነ ለዩክሬን ተመሳሳይ ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ደቡብ ኮሪያ ገልጻለች፡፡

ይህ የደቡብ ኮሪያ እቅድ ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን እንዳትወስድ ለማስጠንቀቅ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከቀናት በፊት፣ ''ሰሜን ኮሪያ 10,000 ወታደሮችን ወደ ሩሲያ ለመላክ ተዘጋጅታለች'' ማለታቸው ይታወሳል፡፡ #TheIndependent

@thiqaheth

THIQAH

21 Oct, 13:18


የፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ተቀናቃኙ ቱርካዊ ፖለቲከኛ ፋቱላህ ጉለን አረፉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2016 የከሸፈዉን የቱርክ መፈንቅለ መንግስት በማሴር የተከሰሱት የ83 ዓመቱ ጉለን መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ አለማቀፋዊ እስላማዊ ንቅናቄን በማስተባበር ይታወቃሉ፡፡

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ''የጨለማው ድርጅት መሪ ሙቷል'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉለን ላለፉት ስድስት ወራት በጠና ታመው በህክምና ሲረዱ መቆየታቸው ተዘግቧል፡፡ #foxnews

THIQAH

21 Oct, 13:13


የእስራዔል ብርጌድ አዛዥ በሃማስ ተገደለ፡፡

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በጋዛ የሚገኘውን የ401ኛ ጦር መሪ የነበሩት ኮሎኔል ኤሳን ዳክሳን ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ወታደራዊ አዛዡን በሃማስ ያጣው የእስራዔል ጦር በዛሬው ዕለት የሃዘን ቀን አውጆ ውሏል፡፡ 

ኮሎኔል ዳክሳን የተገደሉት ከቀናት በፊት ከ80 በላይ ፍልስጤማውያን በእስራዔል ጥቃት በተገደሉባት በሰሜን ጋዛ በምትገኘው ጃባሊያ ግዛት ነው፡፡#ANI

@ThiqahEth

THIQAH

20 Oct, 20:15


"ዶክሜንቱ በምን መልኩ እንደወጣና ማን እንዳወጣው ለህዝብ ግልጽ ይደረጋል" - አሜሪካ

አሜሪካ ሾልኮ በወጣው የእስራኤልን የጥቃት እቅድ በዝርዝር የያዘው ዶክመንት ላይ ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች።

እስራኤል የምትፈፅማቸውን ጥቃቶች ዝርዝር የያዘው ሚስጥራዊ መረጃ በትናንትናው ዕለት ከፔንታጎን ሾልኮ ወጥቷል።

ጥብቅ መረጃው እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው እርምጃ የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ ድጋፍ እንዳለበት ያሳያል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን "ዶክሜንቱ በምን መልኩ እንደወጣና ማን እንዳወጣው ለህዝብ ግልጽ ይደረጋል" ብለዋል። #scrippnews #axios #cnn

@thiqaheth

THIQAH

20 Oct, 07:30


የአፍሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ከቁጥጥሬ ውጭ ሆኗል አለ።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ጂያን ካሰያ፣ በአህጉሪቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ መምጣቱን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ፣ "በስብሰባ እና በውይይት ላይ ብቻ አተኩረን የምንቀጥል ከሆነ ስኬታማ አንሆንም" ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ሳምንት ገንዘብና ቁሳቁስ የማሰባሰብ እና ክትባት የማሰራጨት ስራዎች እንዲጀመሩ አሳስበዋል። #thestar

@thiqaheth

THIQAH

20 Oct, 07:25


ከ70 በላይ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት መገደላቸው ተሰማ።

ከሟቾቹ ውስጥ ብዙዎቹ ህፃናትና እናቶች እንደሆኑ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ የከፈተው አዲስ ዘመቻ 15ኛ ቀኑን ይዟል። #aa

@thiqaheth

THIQAH

20 Oct, 07:23


የሶማሊያ ጦር 30 የአልሸባብ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ጦሩ ለ48 ሰዓታት በቆዬው ዘመቻው ሦስት አባላቱ ብቻ እንደቆሰሉበት ገልጿል።

የሶማሊያ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ፣ ጦሩ በፈጸመው ጥቃት የቡድኑን የውጊያ አቅም በማዳከም ረገድ ለውጥ አሳይቷል ብሏል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በማዕከላዊ ሶማሊያ ጋልሙዱግ በሚገኘው የአልሸባብ ወታደራዊ ስፍራ ላይ ነው።

ከሦስት ቀናት በፊት አልሸባብ በፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ላየሰ በፈፀመው ጥቃት 7 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸው ይታወቃል። #voa

@thiqaheth

THIQAH

19 Oct, 10:45


ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ የተላከ ድሮን ወድቆ ማገኘቷን ገለጸች፡፡

ፒዮንግያንግ ጎረቤቷ ሴዑል በድጋሚ ድሮን የምትልክብኝ ከሆነ ''ጦርነት እንደማወጅ'' አድርጌ እወስደዋለሁ ስትል አስጠንቅቃለች፡፡

ወድቆ ተሰባብሮ የተገኘው ድሮን የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች ይጠቀሙበት እንደነበር ታውቋል፡፡

ድሮኑ በዋና ከተማዋ አቅራቢያ መገኘቱን የገለጸው የሰሜን ኮሪያ ጦር ደቡብ ኮሪያ ከእንደዚህ አይነት የጦርነት ቅስቀሳ እንድትታቀብ አሳስቧል፡፡ #DW #KCNA

@ThiqahEth

THIQAH

19 Oct, 07:56


የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ።

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።

የድሮን ጥቃቱ በሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ መፈጸሙ ነው የተነገረው።

የእስራኤል ጦር ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ መነሻው ከሊባኖስ የሆን ድሮን በኬሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻው በቤቱ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ የሚገኝበት ኬሳሪያ አካባቢ የሄዝቦላህ የጥቃት ኢላማ ሲሆን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም መስከረም 24 ላይ ጥቃት ተፈጸሞበት ነበር። #አልአይን

@thiqaheth

THIQAH

18 Oct, 17:19


"ታላቁ መሪያችንን በሀዘን እናስበዋለን፣ ወንድማችን ሰማዕትነት ከፍሏል" - ሃማስ

ሀማስ መሪው ያህያ ሲንዋር መገደሉን አረጋገጧል።

"ታላቁ መሪያችንን በሀዘን እናስበዋለን፣ ወንድማችን ሰማዕትነት ከፍሏል" ሲሉ በኳታር የሚገኘው የሃማስ ክንፍ መሪ ካህሊል አል ሀያ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ሀማስ የሲንዋርን መገደል ይፋ ያደረገው እስራኤል መሞቱን ካስታወቀች ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

እስራኤል ታጋቾች እስኪለቀቁ ጦርነቱ ይቀጥላል ብትልም ቡድኑ በበኩሉ ጦርነቱ ካልተቋጨ ታጋቾችን እንደማይለቅ ገልጿል። 

እስማዔል ሀኒዬህ ከተገደሉ በኋላ የሀማስ መሪ ሆነው የተመረጡት ሲንዋር የኦክቶበር 7 ጥቃት ዋነኛ መሪ እንደነበሩ ተገልጿል።   #gulftoday

@thiqaheth

THIQAH

18 Oct, 11:23


በሶማሊያ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ጥቃት 7 ሲሞቱ 6 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰማ።

አልሸባብ ኃላፊነቱን የወሰደበት ይህ የሽብር ጥቃት የደረሰው በመድናዋ ሞቃድሾ በሚገኝ ካፌ ላይ ነው።

ካፌው ጄነራል ካህየ ፖሊስ አካዳሚ አጠገብ እንደሚገኝ የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

እንደ ፖሊስ ማብራሪያ ከሆነ፣ የቦምብ ፍንዳታው የደረሰው ሰላማዊ ሰዎች በካፌው ዙሪያ ባሉ ዛፎች ተጠልለው የእረፍት ጊዚያቸውን እያሳለፉ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ #aljazeera

@thiqaheth

THIQAH

18 Oct, 11:21


''ለዓለም ጦርነት አንድ እርምጃ ተቃርበናል'' - ዘለንስኪ

ሰሜን ኮሪያ 10,000 ወታደሮችን ወደ ሩሲያ ለመላክ ተዘጋጅታለች" ስትል ዩክሬን ገለጸች።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሰሜን ኮሪያ የምድር ኃይልና የቴክኒክ ባለሙያዎችን ጨምሮ ብዛት ያላቸው ወታደሮችን ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኗ የኢንተሊጄንስ ባለሙያወቼ ነግረውኛል ብለዋል፡፡

በፒዮንግያንግ እርምጃ የተበሳጩት ፕሬዝዳንቱ፣ ''ለዓለም ጦርነት አንድ እርምጃ ተቃርበናል'' ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ ይህንን ሀሳብ የተናገሩት ከአዲሱ የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩት ጋር ባደረጉት የመጀመሪያ ውይይት ወቅት ነው፡፡ #inews

@thiqaheth

THIQAH

17 Oct, 19:22


ያህያ ሲንዋር !

ምንም እንኳን ከሃማስ በኩል ይፋዊ ማረጋገጫ ባይሰጥም እስራኤል የሃማስን መሪ ያህያ ሲንዋርን ጋዛ ውስጥ እንደገደለች አሳውቃለች።

ሲንዋር በእስራኤል " እጅግ በጣም በጥብቅ " የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።

እስራኤል የምታየው " ከጥቅምት 7ቱ ጥቃት ጀርባ ዋናው አቀናባሪ / ማስተርማይንድ እሱ ነበር " ብላ ነው።

በወቅቱ ከ1,100 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ተወስደዋል።

ሲንዋር የሃማስ ከፍተኛ መሪ ሆነው የተመረጡት ኢስማኤል ሃንያ ኢራን ውስጥ በሃምሌ ወር ከተገደሉ በኃላ ነው።

በአንድ ወቅይ ሲንዋር ፦

" እንመጣላችኃለን። በፈጣሪ ፍቃድ !! የቁጥር ገደብ በሌለው ሮኬት እንመጣላችኋለን ፤ ምንም ገደብ በሌለው የወታደር ማዕበል እንመጣላችኋለን ፤ ሚሊዮኖች ዜጎቻችን ይዘን እንመጣላችኋለን " ብለው ነበር።


ሲንዋር የተወለዱት በጋዛ ካሃን ዮኒስ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ እኤአ በ1962 ነበር።

22 አመታት በእስራኤል እስር ቤት አሳልፈዋል። ለእስር ተዳርገው የነበረው በ1988 2 የእስራኤል ወታደሮችን በማፈንና በመግደል ነው።

እኤአ 2011 ላይ በእስረኞች ልውውጥ አማካኝነት ከእስራኤል እስር ቤት ሊወጡ ችለዋል። ከ2017 አንስቶም በጋዛ ውስጥ ያለውም የሃማስ ኦፕሬሽን ሲመሩ ቆይተዋል።

ከዚህ ቀደም እስራኤል ሲንዋርን " ጨካኝ " እና ሃይለኛ " ስትል ነበር የገለጸችው።

እስካሁን ሃማስ ስለ ግድያው የሰጠው ማረጋገጫ የለም። የእስራኤል ጦር ግን " ሲንዋርን አስወግደነዋል " ብሏል።

@thiqaheth

THIQAH

17 Oct, 15:15


አዲሱ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በእስራዔል ጥቃት ተገደሉ፡፡

በቅርቡ የሃማስ መሪ ሆነው የተመረጡት ያህያ ሲንዋር በሞርታር ጥቃት መገደላቸውን የእስራዔል ጦር አስታውቋል፡፡

ሲንዋር መሪ ሆነው የተሾሙት ኢራን ውስጥ በእስራዔል ጥቃት የተገደሉትን የቡድኑን መሪ ኢሳማኤል ሃኒያን በመተካት ነበር፡፡

የግድያውን በተመለከተ ከሃማስ የተሰጠ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ የለም፡፡  #guidofawkes

@thiqaheth

THIQAH

16 Oct, 14:33


በናይጄሪያ ነዳጅ የያዘች መርከብ ፍንዳታ 105 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡

በናይጄሪያ በጅጋዋ ግዛት በተፈጠረው ነዳጅ በያዘችው መርከብ አስከፊ ፍንዳታ ከ105 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

ከሟቾቹ መካከል 97 ሰዎች ወዲያውኑ፣ ስምንቱ ደግሞ ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መሞታቸውን ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

አደጋው በ50 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱም ተነግሯል።

አደጋው የተከሰተው አሽከርካሪው 68 ማይል ከተጓዘ በኋላ ፍጥነት መቆጣጠር ባለመቻሉ እንደሆነ የአካባቢው ፖሊስ ቃል አቀባይ ላዋን አዳም ተናግረዋል፡፡ #ntd

@thiqahEth

THIQAH

16 Oct, 14:27


''በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት አይኖርም'' - ኒታንያሁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኒታንያሁ በሊባኖስ ከሂዝቦላህ ጋር ለገቡበት ግጭት የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበላቸውን እቅድ ውድቅ አድርገውታል፡፡

ኒታንያሁ ይህን ያሉት ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑየል ማክሮን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሊባኖስ ያለውን የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ አይቀይረውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በዚህም "በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት አይኖርም" ነው ያሉት። #msn

@thiqaheth

THIQAH

16 Oct, 14:24


አሜሪካ ወታደራዊ ድጋፌን ላቋርጥ እችላለሁ ስትል እስራዔልን አስጠነቀቀች፡፡

አሜሪካ ለእስራዔል የምትሰጠውን ድጋፍ የምታቆመው በጋዛ የሚደርሰው የሰብዓዊ እርዳታ እስራዔል በምትፈጽመው ጥቃት ሳቢያ በመስተጓጎሉ ነው፡፡

ዋሽንግተን ይህን ውሳኔ የወሰነችው ተ.መ.ድ በጋዛ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ምንም አይነት የሰብዓዊ እርዳታ አለመድረሱን ከገለጸ በኋላ ነው፡፡

በመሆኑም የሰብዓዊ እርዳታው በ30 ቀናት ውስጥ ተደራሽ ካልሆነ ለእስራዔል ወታደራዊ ድጋፉን እንደማትሰጥ አስታውቃለች፡፡ #thebing

@thiqaheth

THIQAH

16 Oct, 14:23


የሱዳን ጦር ዋና ከተማዋን መልሶ መቆጣጠሩን ገለጸ፡፡

በጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሀገሪቱ ጦር ዋና ከተማዋን ካርቱምን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ማድረጉን የጦሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

ካርቱምን መልሶ ለመቆጣጠር ለሳምንታት የዘለቀ ውጊያ ማድረጉን የገለጸው ጦሩ፤ አሁን ላይ በሁሉም ግንባሮች የማጥቃት እርምጃ እየወሰድኩ ነው ብሏል፡፡

እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ከሆነ የሀገሪቱ ጦሩ ኦምዱርማን፣ ባህሪና አል ሙቅራንን በከፊል ተቆጣጥሯል፡፡ #sudantribune

@thiqaheth

THIQAH

14 Oct, 13:07


ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ድሃ ሀገራት ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

በዓለም ላይ 26 ድሃ ሀገራት ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ በአስከፊ የገንዘብ እጦት ሁኔታ እንደሚገኙ የዓለም ባንክ አስታውቋል፡፡

ባንኩ 26ቱ ሀገራት በዓለም ላይ ካለው ድሃ ማህበረሰብ 40 በመቶውን ይይዛሉ ብሏል፡፡

ከፍተኛ ብድር፣ ጦርነት እና በተለያየ ጊዜ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ለችግሩ እንደምክንያት ተጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ በጥናቱ ካካተታቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ አፍጋኒስታንና የመን ይገኙበታል፡፡ #voanews #gnnhd

@tbiqaheth

THIQAH

14 Oct, 12:57


''ኢራን ለጦርነትም ለሰላምም ዝግጁ ናት''  - አባስ አራግቺ

''ጦርነትን አንፈልገውም ግን አንፈራውም'' ሲሉ የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒትር አባስ አራግቺ ተናገሩ።

በባግዳድ ከኢራቅ አቻቸው ፉአድ ሁሴን ጋር የመከሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀገራቸው ወደፊት ለሚፈጠረው ነገር ሁሉ ዝግጁ ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን በመካከለኛው ምሥራቅና የገልፍ ሀገራት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ሚኒስትሩ መቀራረብና መወያየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

''ጦርነትን አንፈልገውም ግን አንፈራውም'' ያሉት አራግቺ በጋዛም ሆነ በሊባኖስ ሰላም እንድሰፍን እንታገላለን ማለታቸው ተዘግቧል፡፡#irnanews

@thiqaheth

THIQAH

13 Oct, 19:43


ኒታንያሁ የተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሊባኖስ ለቆ እንዲወጣ ጠየቁ።

የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰላም አስከባሪው ኃይል "የሂዝቦላህ መደበቂያ" ሆኗል በማለት ነው ለቆ እንዲወጣ የጠየቁት።

ተ.መ.ድ በበኩሉ፣ በሊባኖስ ካሰማራቸው የሰላም አስከባሪዎች ውስጥ አምስቱ በእስራኤል ጦር ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል።

ድርጅቱ አክሎ፣ የእስራኤል ጦር በስፍራው መገኘት "የሰላም አስከባሪ ኃይሉን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" በማለት አውግዟል። #skynews

@thiqaheth

THIQAH

13 Oct, 09:52


IMF የብድር መጠኑን በ36% ቀነሰ።  

ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለአባል ሀገራቱ ከሚሰጠው ብድር በየአመቱ 36 % ወይም 1.2 ቢሊዮን ዶላር ለመቀነስ ውሳኔ አስተላልፏል።

የIMF ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጅየቫ፣ የብድር መጠኑ እንዲቀንስ የተደረገው  ከፍተኛ የወለድ መጠን በመኖሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

ውሳኔው  የተቋሙን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ ብድር ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት ድጋፍ ለመስጠት ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። #thenation

@thiqaheth