ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈 @ethiopianpoem1 Channel on Telegram

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

@ethiopianpoem1


የተለያዩ በመድብል ደረጃ ለንባብ የበቁ እና ያልበቁ የፍቅር ፣ የሀገር ፣የትዝታ ፣ እና ሌሎች ሀገርኛ ጣዕመ ዜማ ያላቸውን ግጥሞች ያልተሠሙ ወጎች እንዲሁም የገጣሚያንና የታዋቂ ሰዎች ታሪኮችን ያገኛሉ።ግጥም ከቃላት ስደራ በላይ የእውነትና የእምነት ውጤት ፤ የምስጢር ዋሻ ነው፡፡አባላችን ይሁኑ
@ethiopianpoem1
አሰተያየት እና ግጥሞች ካሏችሁ
👉👉 @Yoyo556

ግጥም እና ወግ መድብል (poem) 📜📜🔈 (Amharic)

የበቁ እና የፍቅር ፣ የሀገር ፣ የትዝታ ፣ እና ሌሎች ሀገርኛ ጣዕመ ዜማ እና ታዋቂ ሰዎች በመድብል የተለያዩ የግጥም ወጎችን ለመሸላት አስተዳዳሪ ሊኖረው ይችላል። እናዝናለን የግጥም ሳይንሳዊ መረጃዎችን እና አስተማሪ ተጨማሪ ሰዎችን በእልፍ ያውቃል። በግጥም ላይ የሚሰጥ እውነትና እምነት በመንቀሳቀስ በሁሉም የሚኖረው ውጤት ፣ ምስጢር ዋሻ እራሱንና እናቱን ለማስተናገድ ይህን ግጥም ይቀርባል። እሱም ከሩቅ ጌታ ማኅበረ ቅዱሳንን ይመስለኛል። ግጥም ከዩአምን መሳርቱን ለማስተናገድ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚፈልገው ሰዎች በርስ ተገኝተዋል። ከእምነት በተነሳ በአመልካቾቹ፣ በወንዞችና በወንድሞቻቸው እጳር ለሚያምር ሠዓት ህመም ነው። በዚህ መረጃ እና ወጎችን ካሏችሁትን ግጥሞች በቅድመ ጊዜ የተለያዩን ነዋሪዎች ይለዋል።

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

15 Aug, 18:54


ስለ ተሳምክ ደስ አይበልህ ስለመሳም ማወቅ ከፈለክ ክርስቶስን ጠይቀው........ስለ ይሁዳ ይነግርሀል🙏💟💟
♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙       ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ 𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

15 Aug, 18:54


ከሰው መሀል ነኝ ምናልባትም ሁካታ ከሚፈጥሩትም ዋነኛዋ ልሆን እችላለው
ግን............. የምጮኸው እና የማውከው ውስጤ ያለውን ጩኸት ላለመስማት ነው😔💔💔
♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙       ⌲

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

30 Jul, 12:09


Join this plat form. Touch the link below

https://t.me/hulepay_official_bot?start=r06038893510

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

04 May, 11:41


ራእይ እያለ እንደሌለ!

(“ራእይን ማወቅና መኖር” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ከራእይ አውድ አንጻር፣ ይህንን ጽሑፍ የምናነብ ሰዎች በሶስት እንከፈላለን፡-

1. ምንም አይነት ራእይ የሌለን ወይም ራአያችንን የማናውቅ፡፡
2. ራእይ እያለንና እያወቅነው በዚያ አቅጣጫ መሄድ ያልቻለን፡፡
3. ራእያችንን በማወቅ በዚያ አቅጣጫ መንገድ የጀመርን፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ ምድር ላይ ካለምንም ራእይ (ካለምንም ዓላማ ማለት ነው) የሚወለድ ሰው አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ልዩነቱ ያለው ከተወለድን በኋላ የምልፍባቸው ሁኔታዎችና ያሳደጉን ሰዎችም ሆነ የአካባቢያችን ሕብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ ያመጣብን ጫና ራእይ እያለን ልክ እንደሌለን ኖረን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡

ራእይ እያለን ልክ እንደሌለው ሰው ታስረን እንድንቀመጥ ከሚያደርጉን እንቅፋቶች መካከል የሚገኙትን ይገኙበታልና በጥንቃቄ መመልከቱና ከመንገዳችን ላይ ማስወገዱ አስፈላጊ ነው፡፡

1. ባለፈው ታሪክ መኖር

የራእይ ጉዳይ ከወደፊታችን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ የወደፊታችንን በሚቀርጽ ጉዳይ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ካላቸው ነገሮች አንዱ የኋላችን ላይ የማተኮር ሁኔታ ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችንና ልምምዳችን በወደፊቱ ራእያችን ላይ መልካም መዋጮን የማድረጉን ያህል ወደ ኋላ ሊጎትተንም እንደሚችል በማሰብ ያለፉ ስህተቶችን በጥንቃቄ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡

ሕይወት እስከኖርን ድረስ የስህተትም ሆነ የስኬት ልምምዶች እንዳሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን የተለያየ ገጽታ ያላቸውን ልምምዶች በተገቢው መንገድ መያዝ ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሃሳባችን እየተመላለሰ ውስጣችንን የሚያደክመውን ያለፈ ስህተት ጉዳይ ማሸነፍ አስፈላጊ ነው፡፡ ልናተኩር የሚገባን በወደፊት ራእያችን ላይ ሊሆን ሲገባው ባለፈው ታሪክ መያዝና ወደኋላ መጎተት ከብዙ ስኬታማ ጉዞ የሚገታን ጉዳይ ነው፡፡

2. የስኬት ማጣት ፍርሃት

ፍርሃት ብዙ አይነት ገጽታ አለው፡፡ ይህ ስኬትን የማጣት የፍርሃት አይነት ማንኛውም አዲስ ነገርን ለመጀመር የሚፈልግ ሰው የሚጋፈጠው ፍርሃት ነው፡፡ በፊታችን ልንገባበት የምናስበውና ራእይ ብዙ ነገራችንን ዋጋ ሊያስከፍለን ስለሚችል ምናልባት ካልተሳካ ሊደርስብን ይችላል የምንለው ቀውስ ያስፈራናል፡፡ በተሳካ ሁኔታ ወደፊት ለመቀጠል ግን ይህንን እንቅፋት ማሸነፍ ግን የግድ ነው፡፡

የስኬት ማጣትን ፍርሃት ለማስወገድ ካስፈለገ የስኬትን ትርጉም በሚገባ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ስኬት ማለት አለመድከም፣ አለመወላወል፣ እንቅፋትን አለመጋፈጥ፣ አለመውደቅና … እንደሆነ ከማሰብ መጠበቅ አለብን፡፡ በዚያ ምትክ ስኬት ማለት የብዙ ውጣ ውረዶች ጎዳና መሆኑን በመገንዘብ ሁኔታዎች ለጊዜው ተሳኩም አልተሳኩም ከራእያችን አቅጣጫ አንጻር ወደፊት የመሄድን ልምምድ ማዳበር የግድ ነው፡፡

3. ሰው-ተኮር መሆን

በእያንዳንዱ በምናደርገው ነገር ላይ ሰዎች ያላቸው አመለካከት ምን እንደሆነ የመጨነቅ ዝንባሌ ካለን፣ ራእያችንን በጽንአትና በትኩረት ለመከተል ያስቸግረናል፡፡ ራእዩን ለይቶ ለማወቅ፣ ለመቅረጽና ለመከተል በተነሳ ሰው ላይ ሰዎች የተለያዩ ወደ ኋላ ሊጎትቱ የሚችሉ አመለካከቶችን ሊያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ ይህንን የተለመደ እውነታ ደግሞ ለማለፍ የቆረጠ ማንነት ያስፈልጋል፡፡

እኛ እውነት ሆኖና በሚገባ ገብቶን በምንከተለው ራእይና ዓላማ ላይ ሰዎች ምንም አይነት አመለካከት ለመያዝ መብት እዳላቸው መቀበል ልቦናን ያሳርፋር፡፡ ሰዎቹ የሚያስቡትና የሚናገሩት ላይ ከማተኮር ይልቅ ራእያችን ላይ ማተኮር ስኬታማ ያደርገናል፡፡ በተጨማሪም፣ የሚቃረን ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ከመስማት ይልቅ ሊያበረታን የሚችል ሃሳብ ያላቸው ሰዎች አካባቢ መሆን ይበጃል፡፡

4. የክህሎት ችግር

አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን ራእያቸውን ወደማወቅ ቢመጡም ያንን በውስጣቸው የሚያውቁትን ራእይ በምን መልኩ መስመር እንደሚያስይዙት፣ እንደሚገልጹትና ተግባራዊ ወደመሆን እንደሚያመጡት መላውን አያውቁትም፡፡ ይህ ሁኔታ ከክህሎት ጋር የተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው ራእዩን ካወቀ በኋላ ወደ የት እንደሚወስደው ካላወቀ ያንን ክህሎት የማሳደግ ጉዞ ሊጀምር ይገባዋል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የክህሎቱ አቅም ሲያንሳቸውና ያንንም ማሳደግ ካልፈለጉ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባውን ራእይ-ተኮር ጉዞ ከብዙ ፍልስፍና ጋር በማነካካት የራእይ እውነታ የማጣጣል ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች፣ የምንኖረው አስቀድሞ የተወሰነልንን ነገር ስለሆነና እኛ በዚያ ነገር ላይ ምንም ቁጥጥር ስለሌለን የመጣውን ዝም ብለን መቀበል እንዳለብን ያስባሉ፡፡ ይህ የተዛባ ፍልስፍና ከራእይ ቀጠና ያወጣናል፡፡

Dr Eyob

https://t.me/elelanjobs

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

21 Apr, 10:15


I’m earning money by completing tasks such as testing apps and playing games on https://freecash.com/r/109293750282607861946. If you sign up through my link you can open a free case and win up to $250. https://freecash.com/r/109293750282607861946

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

12 Apr, 15:45


Be bishooftu ketema wst yetezegaje ye modeling wididir
Ticket available @0928886272

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

05 Apr, 15:39


Ye Hitsanat Festival Be Debre Zeyt ( Bishoofttu) ketema Wst. agugagi Wididir Ena Shilmat Betechemarim Yizolachu Metoal.

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

03 Apr, 14:18


እናቴ
አንድ ቅጠል ቢረግፍ
አንድ ዛፍ ይበቅላል
አንድ ቀን ቢጨልም
አንድ አለም ይነጋል
አንድ እናት ብታጣ
መድረሻው ይጠፋል።

አናቴ ይስጥሽ ከ እድሜዬ
ከኔ ላይ ቀን ሶ አንቺ ላይ ጨምሮ
ደስታሽን ያብዛልሽ
ሀዘንሽን እኔ ላይ ከምሮ

ህልምሽን ሳልኖረው
አልጣሽ ከ ጎኔ
ያንቺ መኖር ነውና
የሚሰጠኝ ወኔ፣

𝔅𝔦𝔯𝔞🖤🌒

@ethiopianpoem1
@yoyo556

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

03 Apr, 14:17


#የአዝማሪው_እሮሮ
.
.
.
ተቀበል ይለኛል መሸታ ቤት ገብቶ
ምኑን ልቀበለው ሁሉን ተቀራምቶ
በባዶ መሸለል በባዶ ፉከራ
የልብን ጠባሳ አጥቦ ላያጠራ
ልፋ ቢለኝ እንጂ እንደው የኔ ነገር
ቃላት ተደርድሮ አይገነባም ሀገር

yoni mak

@ethiopianpoem1
@yoyo556

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

03 Apr, 14:15


🥝 ጥሬ ነኝ

አዎ አሁንም ፡ ጥሬ ነኝ
መብሰል የሚባለው ፡ገና የሚቀረኝ
እሰይ አበጀው ፡እንኳን ጥሬ ሆንኩኝ
ከኔ በፊትማ ፡ ቸኩለዉ የበሰሉ
ማርች ናቹ ተብለዉ ፡በስብሰው ተጣሉ
ታዲያ ለምን ብዬ አሁን እበስላለው ?
ቀድመው የበሰሉት : ሲጣሉ እያየው ።
yonimak


@ethiopianpoem1
@yoyo556

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

03 Apr, 14:14


# አንፃራዊ_ጽድቅ
.
ሰው በሰው ጨከነ ፥ ውሎ ሲያድር ከፋ
ቅንጣት ርህራሄ ፥ ከልቡ ላይ ጠፋ
እኛ ግን ስንጓዝ ፥ በምንዱባን መሃል
ምፅዋት ባንሰጥም ፥ ሐዘን ይሰማናል
በል አንተው ፍረደን ፥ ያለኸው ሰማይ
ከንፈር መጠጣችን ፥ አያፀድቅም ወይ?
-----// በርናባስ ከበደ//-----

@ethiopianpoem1
@yoyo556

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

10 Mar, 11:26


🎉🎉Big discount 🎉🎉

Be Debrezeyt bishoftu ketema wst March 8 bemasmelket yetezegajew ehud 03/07/2015
program ticket
@ 0922998288
@yoyo556
Yezih channel teketay yehonachu BIG DISCOUNT kedmew lemigezu 10 sewoch bonus 1 ticket free 🆓

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

08 Mar, 10:48


March 8 yesetoch ken bemasmelket leyet Yale ena Des yemil program be Debrezeyt ( bishoftu) ketema wst yetezegaje liyu program Ehud 03/07/ 2015. Tawaki artist yemigegnubet.
Ticket available @ 0922998288

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

13 Feb, 10:11


Balew ye network mekuaret mknyat Wididiru laltewesene gize terazmual

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

31 Jan, 17:50


ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈 pinned «ታላቅ የ ግጥም ውድድር ይህ ውድድር ከ yekatit 1 -15 ድረስ ለ 15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ይሆናል። ፨ መወዳደር የምትፈልጉ የምትወዳሩበትን  የራሳችሁን ግጥም  @yoyo556 ልካቹ ተወዳደሩ ፨ ተከታታዮቻችን ደግሞ ❤️ በመንካት የወደዱትን ይምረጡ *wididru kemejemeru befit yalachun gitim @yoyo556 lay melak alebachu. @ethiopianpoem1 ፨ የአሸናፊው…»

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

31 Jan, 17:49


ታላቅ የ ግጥም ውድድር

ይህ ውድድር ከ yekatit 1 -15 ድረስ ለ 15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ይሆናል።
፨ መወዳደር የምትፈልጉ የምትወዳሩበትን  የራሳችሁን ግጥም  @yoyo556 ልካቹ ተወዳደሩ
፨ ተከታታዮቻችን ደግሞ
❤️ በመንካት የወደዱትን ይምረጡ
*wididru kemejemeru befit yalachun gitim @yoyo556 lay melak alebachu.
@ethiopianpoem1

፨ የአሸናፊው ሽልማት  admin & 250 mb

       GOOD LUCK!!

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

03 Jan, 18:25


ውድ ደንበኛችን
የ2014 በጀት ዓመትን በስኬት ማጠናቀቃችንን አስመልክቶ ስለአብሮነትዎ ምስጋና Telebirrይሄንንም በማስመልከት እስከ ነሀሴ 5 የሚቆይና በስጦታ የሚያንበሸብሽ የምስጋና 🎀pakage🎀 ይዘን መተናል አንድ ሰው ሲጋብዙ የ 5 Birr ስጦታ ያገኛሉ::የእርሶ መጋበዣ link https://t.me/Telebirr_officialbot?start=r06038893510 ነው እናመሰግናለን፡፡🙏#Ethio-Telecome

ግጥም እና ወግ መድብል (poem)📜📜🔈

19 Nov, 19:04


ይሄም_ያልፋል
🌿የአያቴ ዘመን ተሻጋሪ ምክር!
🔴“አምላክህ ስራዉ ግሩም ነዉ፤ ስታዝን አምላክህ ግሩም ነዉ...ሁሉን ያዉቃል” ብላ አያቴ ስታወሬ ብዙ ጊዜ ሰምቻታለሁ፡፡
🔴ሁሉን ማወቅ...አምላኬ ሁሉን እንደሚያዉቅ ጥርጥር የለኝም፡፡ ግን ሌላኛዉ አካሌ “እሱ ሁሉን እያወቀ እኔ እንዲህ መባዘኔ ለምን ይሆን?” ይላል ... ብዙ ነገር ተስፋ አድርጌ ነገን የተሻለ ለማድረግ እየጣርኩ ነዉ ግን እሱ ሁሉን ያዉቃል፡፡
🔴 ሁሉን በሚያዉቅና በሚችል አምላክ ጥላ ስር ያለ ሰዉ “እራሴ ማወቅ አለብኝ ብሎ የራሱን ፊደል ሲቀምር አይገርምም?
🔴የሰዉ ልጅ መስራት አለበት፣ ማለም አለበት ያ መልካም ነገር ነዉ፤ ግን ልቤ ዛሬን መስራትና መታተር ሲገባዉ ነገ ምን ይሆን?” ብሎ ይጨነቃል...ይጠበባል፡፡
🔴አያቴ አንድ ቀን እንዲህ አለችኝ “ልብህን ገታ አድርገዉ፣ ቀዝቀዝ አድርገዉ...ነገን እንዴት እሆን?” ሲል “ነገን ምን ትሆናለህ? ብቻ ወደላይ ተመልከት!” በለዉ፡፡
🔴ይኸዉልህ አንድ ታሪክ ላጫዉትህ፡፡ በአንድ ሀገር ንጉስ የነበረ ትልቅ ሰዉ ነበር፡፡ ይህ ሰዉ ሁሉን በእጁ እንደተቆጣጠረና ከሱ በላይ ሌላ ምንም ንጉስ እንደማይስተካከለዉ ሁሌ ለህዝቡ ሰብስቦ ንግግር ያደርጋል፡፡
🔴አንድ ቀን ያልታወቀ ጠላት በህዝቡ ላይ ተነሳ...ንጉሱም ይህንን ጠላት ለመግጠም ወጣ፤ ብዙ ሰራዊት ይዞ ተፋለመ...ብዙ ህዝብም አለቀ፡፡ ነገር ግን የጠላት ሀይል እየበረታ ሄዶ የንጉሱን ሰራዊት በታተነዉ፡፡
🔴ንጉሱም ነፍሱን ሊያድን ለብቻዉ በፈረሱ ሸመጠጠ...ጠላቶቹ ከኋላ በቅርብ ርቀት እየተከታተሉት ነበር፤ትልቅ ገደል ጋር ደረሰ...አይዘል ነገር ገደሉ ትልቅ ነዉ፡፡
🔴አይመለስ ነገር ጠላቶቹ ከኋላ እየገሰገሱ ነዉ፡፡ “በቃ የኔ ነገር አሁን አበቃ...ለጠላት እጄን ከምሰጥ እስከነፈረሴ እዚህ ገደል ዉስጥ ብገባ ይሻለኛል!” ብሎ ቆረጠ፡፡
🔴ነገር ግን አምላኩ “ተዉ ይሄም ያልፋል!” ሲለዉ የተሰማዉ መሰለዉ...እንደምንም ብሎ ድንጋዩ ስር ራሱን ደብቆ ፈረሱን ወደጫካዉ አባረረዉ...ጠላቶቹም ሳይደርሱበት አጥተዉት ተመለሱ፡፡
🔴ንጉሱም ወደሃገሩ ተመልሶ ህዝቡን እንደገና አደራጅቶ፣በጦርና በስልት ሰራዊቱን አዘጋጀ፡፡ ለብዙ ወራት ሰራዊቱን የጦር ልምምድ ከተለማመደ በኋላ የወጋዉን የጠላት ሰራዊት በድንገት አጠቃ፡፡ በቀላሉም ድሉን ተቀናጀ፡፡
🔴ባሸነፈ እለት ማታ ድግስ አድርጎ ከህዝቡ ጋር እየበላ እየጠጣ ሳለ በልቡ እንዲህ አለ “አሁን ማን ያክለኛል? የትኛዉስ ንጉስ ይችለኛል??” አምላኩ አሁንም በልቡ “ይህም ያልፋል!” አለዉ፡፡
🔴“ልጄ ቢርብህም ቢጣፍጥህም ሃዘንህም ደስታህም ያልፋሉ፡፡ አምላክህ ግሩም ስለሆነ በሱ ተመካ እሱን ተማምነህ ኑር! ይኸዉ ነዉ ልጄ”
🔵የአያቴ ዘመን ተሻጋሪ ምክር ልቤ ዉስጥ አሁንም ድረስ ሹክ ይለኛል፡፡
🎖 ዉብ  ምሽት 🎖

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@ethiopianpoem1
@yoyo556

on TikTok @yonimak1673