ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ @astawesegnregasa Channel on Telegram

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

@astawesegnregasa


የአሰታወሰኝ ረጋሳ የተለያዩ ግጥሞች እና የመድረክ ስራዎች
እዚህ ቻናል ላይ ይለቀቃሉ

ቻናሉን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ (Amharic)

እንኳን አደረሰው! በአሰታወሰኝ ረጋሳ በተለያዩ ግጥሞች እና መድረክ ስራዎች ከመሆኑ በፊት የአሰታወሰኝ ረጋሳ እና ለእርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ። ይህ ቻናል በሚለዋዋጋቸው ጨረታዎች ላይ የአስታወሰኝ ረጋሳን በመቀላቀል ሜዳ እዩ። በአስታወሰኝ ረጋሳ የመዝናኛ ትእዛዝ እና የልዩ ዝምታው ለሚሰሙ ሕዝቦች ይለቀቃል። ቻናሉን በስተቀር ቤተሰብ እና መኮᆯሞን እንደሚል እንዳሉ ከሌሎች ታዳጊዎች ጋር ያድርጉ።

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

19 Nov, 09:57


ያልፋልልልልልል


@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

14 Nov, 05:29


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::


@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

30 Oct, 12:18


አቅጣጫዬ

በዕውቀቱ ስዩም




❤️❤️

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

22 Oct, 15:38


ሰዎች እንዴት ናችሁ

ይሄን Group ግቡና እዩት እስኪ ስለዚህ Application ካልሰማችሁ ብዙ ቪዲዮዎች ሰርቻለሁ Check አድርጉት እንደዚህ አይነት ስራ መስራት የምትፈልጉ ብር ታገኙበታላችሁ
እኔ እየሰራሁበት ነው

👇መግቢያ link👇

@popolivestream
@popolivestream
@popolivestream
@popolivestream

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

22 Oct, 15:32


poppo livestream app ከስር የተዘረዘሩትን ስራዎች በመስራት ገንዘብ የምንሰራበት ፕላትፎርም ነው

1.Live በመግባት:
# Account ከፍተን አፑን መጠቀም ከጀመርን ቀን ጀምሮ እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ በቀን ለ 1ሰዓት ያክል live ላይ ስንቆይ 10,000 point ይሰጠናል (ለሴቶች)

# 7 ቀን ካለፈን በኋላ ይሄ ሽልማት ያበቃና በቀን ለ 1ሰዓት live ላይ ስንቀመጥ 2,000 point ይሰጠናል ( ለሴቶች)


2.ከ Party የምናገኘው:

# በየቀኑ party ላይ ለ 2 ሰዓት ስንቀመጥ 800 point ይሰጠናል (ለሴቶች)
# ሌላው party ላይ point ሚገኘው ጊፍት ሲሰጠን ነው

3.ጌም በመጫወት

# አፑ ውስጥ ያሉትን ጌሞች የሰበሰባችሁትን ኮይን በመጠቀም እየተጫወቱ ለማትረፍ መሞከር (መክሰርም ግን አለ😁)



4.ጋምብል በማድረግ
# ጋምብል ማድረግ ማለት ልክ እንደ 3ተኛው ሆኖ ይሄ ግን ጊፍት በመስጠት ነው ለማትረፍ የምትሞክሩት








@popolivestream

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

22 Oct, 12:03


በዕውቀቱ ስዩም






❤️

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

19 Oct, 21:46


ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ!
ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ!
(አሌክስ አብርሃም)

ፍቅር ብቻውን መልስ የሚሆንበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
በማንም ላይ መፍረድ ከባድ ነው። ሲቸገሩ መርዳት አለመቻል ከሚፈጥረው ህመም
ለመራቅ ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን እንርቃለን። ዓይናቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ ላለማየት ዓይናችንን እንሰብራለን።የአቅማችንን መደገፍ እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል። የተወለድንበት እና ያደግንበት ስር የሰደደ አብሮነት፣ መረዳዳት አሁን እግር ከወርች ካሰረን ኑሮ ጋር አብሮ አልሄድ ብሎ አስጨንቆናል።

ረስተነው ወደወዳጆቻችን መንገድ ከጀመርን ፣ልንደውል ስልክ ካነሳን በኋላ ባዶ አይናቸው እጃችሁ ከምን ቢለንስ ብለን ተመልሰናል። ከመሄዳችን በላይ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን አንደበታቸው ሳይሆን ኑሯቸው ሁኗል። የተጨነቀ መንፈስ፣ የተጨነቀ አየር። የማንንም እርዳታ የማይፈልጉ መንፈሰ ፅኑ ወዳጆቻችን ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነውባቸው በዓይናቸው ባዶ ኪሳችንን ሲቃኙ ብናይ መርዳቱ ቢቀር አንታዘባቸውም። "እንትናም ተቸገረ?" ብለን አናሾካሹክም።

ይገባናል ሰው ወደገደል ቢወድቅ አዳነውም አላዳነውም አጠገቡ ያገኘውን ሳርም ይሁን ቅጠል በደመነፍስ ጨምድዶ እንደሚይዝ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።ልብሳችንን አንቀው የሚማፀኑን እኛም የሌሎችን ልብስ አንቀን መንጠልጠላችንን ያውቃሉ። የመያያዙ መጨረሻ፣ የገደሉ ጫፍ የት እንደሆነ ማን ያውቃል?! እጃችን እየዛለ ነው። ደመነፍስ ላይ ነን። ማንንም ለመዳን እንይዛለን በማንም እንያዛለን። ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ። ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።


አሌክስ አብርሃም





@astawesegnregasa
@astawesegnregasa
😔😔

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

17 Oct, 13:44


በዕውቀቱ ስዩም 😍




❤️
@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

16 Oct, 11:55


።።።።። አፈቀርኩሽ መሰል።።።።።

ስትመጭ ሳይሽ ልቤ ደንግጥ ይልብኛል
ካጠግብሽ ስሆን ደስታ ይሰማኛል
ሳቅና ጨዋታሽ በህልሜ ይታየኛል
ሳላይሽ ከዋልኩኝ ቅርቅር ይለኛል

ምን ብየ ልንገርሽ
ሳስብሽ የማድረው ውስጤን ሳምሰለስል
እንጃ እኔስ ጠረጠርኩ አፈቀርኩሽ መሰል

✍️በ ባልክየ አቻምየለህ

@ t.me/b1a2l9

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

12 Oct, 01:37


ያማል

እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማልሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?ካፑችኖ ልዘዝ?ጥቁር ቡና ልዘዝ?ለምን ሰው አላዝም
?መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ ሞቱን ባንገት ቀብሮ ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል


ከሰለሞን_ሳህሌ

የቀረውን በ ቪዲዮ ጨርሱት

🖤💔❤️

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

11 Oct, 03:24


ቅናሽና የመጽሐፍ ስጦታው እንደቀጠለ ነው

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 የሚቆይ የመጻሕፍት ቅናሽና ሽልማት

እነሆ መጻሕፍት ብቅ ብላችሁ ሁለት መጻሕፍት ከሸመታችሁ አንድ ተጨማሪ የሥጦታ መጽሐፍ ይጠብቃችኋል።

አድራሻ፦ 4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

10 Oct, 09:04


👨🏾‍💻

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

08 Oct, 18:11


"ያልፋል ይለኛል ሰው"
(አስቱ)

ያልፋል.... ያልፋል ....ያልፋል
..
ያለወቅቱ መሽቶ ጨልሞበት ቀኑ
ለልቤ ምኑ ነው ተስፋ ማቀንቀኑ
አስማት የለኝ ፀጋ ጥበብ የለኝ መክሊት
እንዴት ልሸውደው ይህን ክፉ ለሊት

"ያልፋል... ያልፋል..... ያልፋል"

ሁሉም ጦሩን ስሎ ጋሻውን አንግቦ
ቁርስ ምሳ ራቱን ንዴት ተመግቦ
ሲሸልል ለግዳይ ሲፎክር ለበቀል
አይመክተው ሼሁ አይበግረው መስቀል

ከቀን እስካመሻሽ ከሌት እስከ ንጋት
እሰከመቼ ልግፋው ኑሮዬን በስጋት

ያልፋል.. ያልፋል... ያልፋል

"የሞተው ወንድምሽ የገደለው ባልሽ"
የሚባለው ተረት
መች ቀረ በወርት

ምን ጆሮ ተገኝቶ ምክር የሚሰማ
ዘውትር ለጦርነት ነጋሪት ጉሰማ
በለው ነው
ግፋ ነው
ግዝቱ ስብከቱ ልብ አያልፈሰፍስ
ያልፋል ያላችሁት ይህ ዘመን ባያልፍስ!?


@astawesegnregasa
@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

07 Oct, 04:24


ሶስት ነው አደራ

(ረድኤት አሰፋ) (Red-8)

የማላውቀው፡ መንገድ ጠራኝ
ልሄድ ነበር ... ግን አስፈራኝ...
ተነስቼ ልራመድ ስል
ጥቅም ያለው የማይመስል
አስጨነቀኝ ተራ ያልኩት
ለሶስት ነፍስ ያስለመድኩት
አሳሰበኝ ግዴታዬ።
ከኔ ሳይጎል የምቸረው
እኔ ብቀር የሚቀረው
ትዝ ቢለኝ ልቤ ፈራ
እባካችሁ እንኩ አደራ...

አደራ...ባካችሁ!

ገና ከሩቅ ሰው ሲያይ፡ ጭራ የሚቆላ
ከቤቴ ከፍ ብሎ፡ ካያችሁ ቡችላ
ባታበሉት እንኳ፡ እንዳትሉት ችላ...
ዳብሱልኝ እራሱን ፡ ኮርኩሩልኝ ሆዱን
እንደ ቁራሽ ዳቦ፡ እንዳትነሱት ልምዱን

አደራ... ባካችሁ...
የሚቀመስ ቢያጡ፡ የሚላስ ቢጠፋ
አጫዋች ካገኙ፡ ይቀጥላል ተስፋ።

ደግሞም ሁለተኛ... አደራ በሰማይ
ጥቂት ስትጓዙ ፡ ከኔ ቤት ወደላይ
በሁለት ክራንች ፡ የቆመች ተዛንፋ
ካያችሁ አንድ ህፃን፡ ምላሰ ኮልታፋ
አብሮ አደግ ጓደኞች፡ አይኖሯትምና
አደራ በሰማይ፡ ተጠግታችሁ ጎኗ
ትርጉም የሌላቸው፡ መድፊያቸው የጠፋ
ቀልዶች እያመጣች፡ ልታስቅ ስትለፋ
እያደመጣችሁ
አደራ ሁላችሁ
ባይገባችሁ እንኳ፡ ስቃችሁ እለፏት
እግር አያስራትም፡ ጆሮ ከደገፋት።

ደግሞም ለሶስተኛ...ባካችሁ... አደራ...
አደራ በምድር ፡  በጠዋት ስትነቁ
ልጆቿ በርሃብ፡ በጠኔ ያለቁ
አንዲት አረጋዊት፡ ከገጠመቻችሁ
አደራ ሁላችሁ
ቁጢጥ ብላ ፀሐይ፡ ስትሞቅ ስታገኟት
አደራ ቆማችሁ፡ እንዴት አደርሽ? በሏት
አይኖቿ ደካክመው፡ ዝለው ጆሮዎቿ
እንዴት ነሽ የሚሏት፡ መስለዋት ልጆቿ
አቅፋ ስትመርቅ ነው ፡ የኖረች እስካሁን
አደራ በምድር...ያገኛት ሰው ሁሉ፡ ላፍታ ልጇ ይሁን...

አይደለም የእጆቹን፡
አይደለም ልጆቹን
አይደለም ተስፋውን፡ ፍሬውን ያጣ እለት
ማጣቱን ሲያውቅ ነው ፡ ሰው የሚያበቃለት።

ስለዚህ... ድንገት...
ወደማላውቀው፡ መንገድ ስጠራ
ችዬ እንድራመድ፡ ልቤ እንዳይፈራ...
አርፌ እንድሄድ...ሶስቱን አደራ


@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

23 Sep, 07:02


ተማጽኖ
(በእውቀቱ ስዩም)

አቤቱ
የጠፈር ባለቤቱ
በየብስ ነህ፥ በባህር፥ በምድር ነህ በሰማይ?
በቅጡ ለማናውቅህ ፥ በድንግዝግዝ ለምናይ

አቤቱ የፍጥረት  አባት
ከሰማኸኝ ምናልባት
ኮረብታውን ሜዳ አድርገው ፤ ኮረኮንቹን አለስልሰው
የፎይታየን አድራሻ፥ ርቀቱን ቀንሰው
አልልህም !

ጽናት ስጠኝ ፤ ብርቱ አድርገኝ! በየርምጃው እንዳይደክመኝ
ከቀንበሮች ሁሉ መርጠህ፥ ምችለውን አሸክመኝ

አቤቱ! የጠፈሮች ሁሉ መስራች
አፈራርቀህ የምትሰጥ፥ መርዶና የምስራች !
ተወስነህ የማትገኝ ፤ በጊዜና በቦታ
ወሰን የሌለህ ዝምታ
እኔ ልጅህ-ሲመቸኝ ፤ ሲመቸኝ አማኝ
ባይመችህም ስማኝ
 
ካደፈጠው እዳ ሁሉ፥ በየበስ፥ ባየር በቀላይ
ከአውሎ ነፋስም በላይ
ከመሬት መራድም ይልቅ
ሰው ነው ሰውን ሚያሳቅቅ
ሰው ነው የሰው አደጋ
ደግሞ በሌላ ገጹ፥ ሰው ነው ለሰው ልጅ ጸጋ
ከስጦታው አካፍለኝ ፥ ካደጋው አስመልጠኝ
አልሳሳት አልልህም፥ የሚታረም ስህተት ስጠኝ !



@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

19 Sep, 18:03


እኔና አንቺ!
( በረከት በላይነህ).

በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
  
@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

29 Aug, 04:08


በረከት በላይነህ

ጎዳናው ሳይጠበን፣ አመል
እያጋፋን
አካሄዱ ቀርቶ፣ አቋቋሙም
ጠፋን፡፡
................



@astawesegnregasa

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

18 Aug, 04:43


በዕውቀቱ ስዩም



@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

2,962

subscribers

93

photos

68

videos