የኢትዮጵያው ከፍተኛ ባለስልጣን #ፌስቡክ መረጃዬን አሳልፎ ሰጠብኝ አሉ።
ዛሬ ምሽት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋ/ዳሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ''ሀክ ተደረጉ'' ከሚል ጹሑፍ ጋር ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተለጥፈው ነበር።
ይህ ከሆነ ከደቂቃዎች በኃላ ዳሬክተሩ፥ ''ለግንዛቤያችሁ'' ብለው ባሰፈሩት መልዕከት ይፋዊ የፌስቡክ አካውንታቸው ''በውጭ አካላት ሃክ አልተደረገም'' ብለዋል።
የተለቀቀው ቪዲዮም ከ1 ዓመት በፊት ፌስቡክ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ (Messenger) አማካኝነት ከጓደኞቻቸው ጋር ያወሩት እንደሆነ ገልጸዋል።
ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ''ፌስቡክ መዝግቦ ያስቀመጠውን መረጃ (Password, Username) እንዴት አሳልፎ እንደሰጠና በዚህም ግለሰብንና ሀገርን ለማሳጣት የተደረገውን የቴክኖሎጂ ውንብድና በህግ አግባብ እንሄድበታለን'' ሲሉ በጹሑፋቸው ገልጸዋል።
በገጻቸው ላይ ለተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስልም ፌስቡክን መረጃዬን አሳልፎ በመስጠቱ ነው ሲሉም አስረድተዋል።
''የኛ Username እና password እነርሱ ጋር ስለሚገኝ ይህንን ማድረግ ተገቢ አይደለም። ጠላትነታችን እዚህ የደረሰ አልመሠለኝም ነበር'' ይላል አጭር ያሰፈሩት ጹሑፍ።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዳይሬክተሩ ለጓደኞቻቸው በፊት ለፊት ካሜራ ቀርጸው የላኩት ''አታስቀኑኝ በርሬ መጣለው'' የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን በገጻቸው ላይ በተደጋጋሚ ''ሹመቴ ግዛው ሀክ ተደረገ'' የሚል የሥላቅ መልዕክት ታክሎበት በገጹ ለደቂቃዎች ተለጥፎ ነበር።
አሁን ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ ከገጹ የጠፉ ሲሆን ሂደቱን በህግ እንደሚከታተሉም ዶ/ር ሹመቴ አስታውቀዋል።
ዶ/ር ሹመቴ ከ2012 ጀምሮ የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
@ethioaddiszena