Islamic Media @sadatkemalabumeryemm Channel on Telegram

Islamic Media

@sadatkemalabumeryemm


Islamic Media (English)

Islamic Media is a Telegram channel dedicated to providing a platform for sharing and discussing various forms of media related to Islam. From informative videos and articles to inspiring podcasts and music, this channel aims to create a space for individuals interested in learning more about Islamic culture, traditions, and beliefs. Whether you are a practicing Muslim seeking to deepen your faith or a non-Muslim curious about Islam, Islamic Media offers a diverse range of content to educate and enlighten its audience. The channel is curated by @sadatkemalabumeryemm, an experienced educator and Islamic scholar, who ensures that all content shared is accurate, respectful, and informative. Join Islamic Media today to explore the beauty and richness of Islamic media and engage in meaningful discussions with like-minded individuals from around the world.

Islamic Media

04 Sep, 19:36


#BREAKING_ALERT - ኢትዮጵያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ወደ ሶማሊያ ድንበር አስጠግታለች!

T.me/TheNewsReports

Islamic Media

19 Aug, 18:50


#NOW - ብሊንከን በቴልአቪቭ: "እስራኤልን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል"

@TheNewsReports

Islamic Media

17 Aug, 18:18


በሀገራችን በኢትዮጵያ እየተሰሙ እና በሚዲያው እየተንሸራሸሩ የሚገኙት ዜናዎች እንኳን ለመስማት ለማጋራት ራሱ እጅጉን ሰቅጣጭ ሆነዋል።

ሰይጣናዊ ድርጊቶችን መስማት ቀላል እየሆነ መጥቷል። ፍርዶች እየተዛቡ ነው። በፊት በፊት እንዲህ ያሉ ነገሮች ከስንት አንዴ እንኳ ሲሰሙ እጅጉን ያስደነግጥ ነበር። አሁን አሁን ያ ሰዋዊ ባህሪ ጠፍቶብናል። 'ሰው'ነታችንን ጥለነው መጥተናል። ለእያንዳንዱ እንዲህ ያለ ድርጊት እያንዳንዱ ዜጋ ሐላፊነት ይውሰድ።

እንደ ሀገር ወድቀናል።

@TheNewsReports

Islamic Media

15 Aug, 04:09


#BREAKING_ALERT 🚨
የዓለም ጤና ድርጅት በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋን አውጇል።

@TheNewsReports

Islamic Media

14 Aug, 08:25


ዛቻ እና ፉከራ መገለጫዋ እየሆነ የመጣችው ኢራን እስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ካለች ይሄው ሁለት ሳምንታት ተቆጠሩ።

በትላንትናው እለት በሩሲያ ኤግዚቢሽን ላይ ያለ የሌላትን የረጅም ርቀት ድሮኖቿን ስታሳይ እና አቅሜን እዩ እያለች የነበረችው ኢራን በነዚህ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጠላት ግዛት አንድም የረባ ጥቃት ለማድረስ እንደማትሞክር ራሷ ታውቃለች። የኢራን ፉከራ "ፍልስጤምን መደገፍ" በሚለው መስመር በመካከላኛው ምስራቅ ከሚገኙ አረብ ሀገራት በላይ ብቅ ብላ ለመታየት ብቻ ያለመ ይመስላል፤ ልክ እንደ ቱርክ!

ቱርክ የጦር ሃይሏን እጅጉን እያዘመነች ብትመጣም በጦርነቱ ፍልስጤማውያንን ለመርዳት የሚያስችል በቂ ድፍረት የላትም፤ የኔቶ አባል ነችና! ነገር ግን ባትሆን ኖሮም አሁን ከምታደርገው ነገር የዘለለ ምንም እንደማትፈይድ እርግጥ ነው። ሳውዲና ጆርዳን ነገሩን በዝምታ ማየታቸው ብዙሃኑን እያስጮኸ የነበረ ቢሆንም አሁን ያለውን ሁኔታ ያየ ሰው ሀገራቱ በትክክል ምን እየሰሩ እንደነበር መረዳት ይችላል።

አንድ እውነታን መረዳት አለብን። አሜሪካ በተቃራኒ በኩል ያለችበት ነገር ላይ ማንም ምንም ሊፈይድ አይችልም፤ ተዓምር ካልተፈጠረ በስተቀር። ዩክሬንን፣ እስራኤልን እና ታይዋንን በአንድ ግዜ አንድላይ የመደገፍ እና የመርዳት አቅም ያላት አሜሪካ ብቻ ናት!

@TheNewsReports

Islamic Media

11 Aug, 08:01


ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ የተጀመረው የፀረ-ስደተኞች እና የፀረ-ኢስላም ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሀገራችን ሚዲያዎች ብዙም እየተወራለት ባይሆንም ተቃውሞው በዝምታ የሚታለፍ አይደለም። በቤልፋስት፣ በርሚንግሃም፣ ካርዲፍ፣ ግላስጎው፣ ለንደን እና በሌሎችም የእንግሊዝ ከተሞች የተስፋፋው ይህ ተቃውሞ ሙስሊሞችን ለማጥቃት እና መስጂዶችን ለመውረር ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል።

በሀገሪቱ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችም በቀላሉ የሚቀመሱ ሆነው አልተገኙም። ህብረት እና አንድነታቸውን ያሳዩት ሙስሊሞች እና ጥቁር ስደተኞች ከተቃዋሚዎቹ በበለጠ መልኩ ሃይላቸውን አጠናክረዋል።

በነገራችን ላይ አንዳንድ ጥናቶችን እንዳየሁት እስልምና ምዕራባውያን ዘንድ እጅግ ፍጥነት ባለው መልኩ እየተስፋፋ ያለ ሐይማኖት ነው። ይህ ተቃውሞ ጊዜያዊ ቀውስ ከመፍጠር በዘለለ እዚህ ግባ የሚባል ቁምነገር የሚያመጣ አይመስልም።

ለተቃውሞ እጅጉን ረፍዷል!

Share | T.me/TheNewsReports

Islamic Media

07 Aug, 19:38


#ALERT ⚠️ - በአለም ላይ ላሉ የሲቪል አቪዬሽን ኩባንያዎች ከኢራን ባለስልጣናት በተላለፈ ማስታወቂያ መሰረት፣ በወታደራዊ ልምምድ ምክንያት በኢራን የአየር ክልል ላይ መብረርን አስወግዱ ብላለች።

- Al Qahera News

@TheNewsReports

Islamic Media

07 Aug, 15:49


#ቴህራን እና ሒጃብ | (Latest News)

ምስሉ ፖሊሶች ሂጃብ በመባል የሚታወቀውን የራስ መሸፈኛ ያልለበሱ ልጃገረዶችን ሲደበድቡ፣ ሲያስሩ እና ጎትተው ወደ መኪናው ሲያስገቧቸው ያሳያል።

   ዛሬ በሚዲያው አለም መነጋገሪያ የነበረው ይህ የህግ አስከባሪ ሀይሎቹ ድርጊት አለምን አስቆጥቷል።
የ14 አመት ልጇ ተጎጂ የሆነችባት እናት ለኢንሳፍ ኒውስ ድረ-ገጽ እንደተናገሩት፤ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የልጇ ጭንቅላት በኤሌትሪክ ምሰሶ እንደተመታ እና ድብደባውም በመኪና ውስጥ እንደቀጠለ ትናገራለች። 

  የተጎጂዋ እናት በልጇ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ቅሬታ ብታቀርብም ወታደራዊ አቃቤ ህግ በሲሲቲቪ የተቀረፀው ምስል እንድታገኝ ቢፈቅድላትም ፍትህን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ብዙም አልተሳካም ትላለች።

እናትየው ከታሰሩ በኋላ የልጃቸውን ሁኔታ ሲገልጹ ታዳጊዋ ፊቷ፣ ከንፈሯ እና አንገቷ ላይ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን አለፍ ሲልም የመናገር ችግር እንዳጋጠማት ተናግራለች።

በዚህም በዛሬው እለት ምላሽ የሰጠው የቴህራን የፖሊስ ሃይል መረጃ ማእከል ቪዲዮው ከ2 ሳምንታት በፊት የተቀዳ ነው ብሏል። 

  ፖሊስ በመግለጫው ታዳጊዎቹ ተገቢ ያልሆነ ልብስ እንዳይለብሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር ሲል ገልጿል። 

ክስተቱ በኢራን ጥብቅ የአለባበስ ህግ እና የማስፈጸሚያ ዘዴዎቹ ላይ የነበረውን ክርክር አቀጣጥሏል ተብሏል።

ብዙ የፋርስ ቋንቋ ተናጋሪ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በታዳጊዎቹ አያያዝ ላይ ቁጣ እና ብስጭታቸውን ሲገልጹ አዲሱን የኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን እንዲ አይነት ነገሮችን እንዲያስቆሙ ብዙዎች ጠይቀዋል።

ፕሬዝዳንት መስዑድ በፕሬዝዳንትነት ዘመቻው ወቅት የግዴታ የሂጃብ ህግጋትን ባለማክበር የህግ አስከባሪ ፖሊሶች በኢራን ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ስላላላቸው አያያዝ በተደጋጋሚ ሲወቅስ ታይቷል። 
  
በመላው ኢራን የአለባበስ ደንብን ጥሰዋል በሚል ምክንያት ሴቶች መታሰራቸውን እና የኃይል እርምጃ እንደተወሰደባቸው በርካታ ሪፖርቶች ቀርበዋል።

  ይህም በበርካታ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞው እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል።

- AL ARABIYA , ENSAF

@TheNewsReports

Islamic Media

07 Aug, 08:31


#NEW - ጆርዳን፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ሰላም አስከባሪ ሃይል ለማሰማራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተሰምቷል።

ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጦር በማሰማራቱ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

አንድ የአረብ ባለስልጣን እንዳብራሩት፣ ከጦርነቱ በኋላ ጋዛ ውስጥ ሃይል ማሰማራት ለእስራኤል መከላከል ተደርጎ ስለሚታይ ጆርዳን፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ያን ማድረግ አይፈልጉም።

- Times of Israel

@TheNewsReports

Islamic Media

07 Aug, 08:00


#JUST_IN - ኒጀር ማሊን ተከትላ ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች።

ካለፈው አመት መፈንቅለ መንግስት በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው የሀገር ውስጥ ጥበቃ ብሄራዊ ምክር ቤት ኪይቭ አሸባሪ ቡድኖችን ትደግፋለች ሲል ከሰዋል።

@TheNewsReports

Islamic Media

07 Aug, 07:53


#RAPE - አንድ የደህንነት ካሜራ የእስራኤል ወታደሮች አንዲት ፍልስጤማዊትን እስረኛ አስገድደው ሲደፈሩ ቀርጿል።

ሌሎች አብረው የነበሩ ጠባቂዎችም መከላከያቸውን ተጠቅመው ካሜራውን ለመሸፈን ሲሞክሩ ይታያል።

እንስቷ በከባዱ የተጎዳች ስትሆን የፊን** መቀደድ፣ የአንጀት እና የሳንባ ጉዳት እና የጎድን አጥንት መሰበር አጋጥሟታል ተብሏል።

- N12

T.me/TheNewsReports

Islamic Media

06 Aug, 18:49


#BREAKING - ካናዳ ነገ ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል ልታስወጣ ነው።

@TheNewsReports

Islamic Media

06 Aug, 07:51


የዛሬ 79 ዓመት በዛሬዋ እለት፡ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 ዩናይትድ ስቴትስ በጃፓን ሂሮሺማ ላይ "Little boy" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠውን የዩራኒየም ቦምብ ጣለች።

- ቦምቡ ከ15,000 ቶን ቲአረንቲ (TNT) ጋር የሚመጣጠን ፈንጂ ምርት የነበረው ሲሆን ከተማዋን አውድሞ 70 በመቶ የሚሆነውን አቃጥሏል።

- በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ በሂሮሺማ የቦምብ ፍንዳታው 140,000 የሚገመቱ ሰዎች ተገድለዋል።

- ከሃይፖሴንተር በ1.2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙት መካከል 50% ያህሉ የሞቱት በዚያ ቀን ሲሆን በሉኪሚያ፣ ካንሰር እና ሌሎች በሽታዎችን ጨምሮ በጨረር መጋለጥ ምክንያት በሚቀጥሉት አመታት በርካቶች ሞተዋል።

ከላይ ምስሉ የሚያሳየው የሂሮሺማ ከተማ ከቦምብ ጥቃቱ በፊት እና በኋላ ነው።

@TheNewsReports

Islamic Media

06 Aug, 05:05


#JUST_IN - በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በደረሰ የሮኬት ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋል ሲል ምንጮች ለሮይተርስ ገልፀዋል።

@TheNewsReports

Islamic Media

05 Aug, 18:59


#BREAKING - ሁለት ሮኬቶች በኢራቅ የአሜሪካ ወታደሮች በሚገኙበት በአይን አል አሳድ የጦር ሰፈር ላይ ተተኩሷል። 

- REUTERS

@TheNewsReports

Islamic Media

05 Aug, 18:56


#JUST_IN - ዮርዳኖስ የአየር ክልሏን ለማንኛውም አካል እንዲጠቀሙ እንደማትፈቅድ ለአሜሪካ፣ ለእስራኤል እና ለኢራን አሳውቃለች።

- SKY NEWS ARABIA

@TheNewsReports

Islamic Media

05 Aug, 18:54


#BREAKING - ጀርመን ዜጎቿን ከሊባኖስ ለማስወጣት መዘጋጀቷን ስፒጌል የዜና ምንጭ ዘግቧል።

- Spiegel

@TheNewsReports

Islamic Media

05 Aug, 18:49


መካከለኛው ምስራቅን በተመለከቱ የተለያዩ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ፈጣን መረጃዎችን እናደርሳችኋለን፤ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

@TheNewsReports

Islamic Media

05 Aug, 12:05


አንድ ትልቅ የሚድያ ተቋም ስለ አንድ ፋውንቴን ዘገባ ሲሰራ

በግሌ እንደማስበው ህዝብ በእንደዚህ አይነት ዘገባዎች በእጅጉ ተሰላችቷል። አንድ፣ ሁለት፣ አምስት፣ አስር፣ ሀያ... ዘገባዎች ችግር ላይኖረው ይችላል።

ስንት በርካታ የሚነገሩ፣ ህዝብ የሚጮህባቸው እና መፍትሄ የሚፈልጉ ጉዳዮች እያሉ ሚድያው በሳምንት በመቶ የሚቆጠሩ ዘገባዎችን ስለ ኮሪደር ሲዘግብ መዋሉ ይባስ ህዝቡ ስለ ፕሮጀክቱ ሌላ አተያይ እንዲኖረው እያደረገው እንዳለ እየተገነዘብን ነው።

ዝም ተብሎ ቢሰራ ህዝብም "ድምፃቸውን አጥፍተው እየሰሩ ነው" ብሎ ያደንቃል። በዚህ መልኩ ህዝብን ማሰላቸት ተገቢ ነው ተብሎ ከታመነበት... አጠናክረህ ቀጥል፣ ብሎን ሲታሰር እና ጡብ ሲቀመጥም ዘግብ።

ግን ህዝብ ሰልችቶት ሀሳቡ ሁሉ የኑሮ ውድነት፣ የፀጥታ ስጋት እና የብልሹ አሰራር ማማረር ላይ ነው።

© Elias Meseret

@TheNewsReports