የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church @efgbc_ho Channel on Telegram

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

@efgbc_ho

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘልዓለምም ያው ነው። ዕብ 13:8
Jesus Christ is the same yesterday and today and forever. Heb 13:8

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church (Amharic)

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በየኤፍጂነሪኛ እንኳን መሰረት ይህ ገጽ ከተከፈተ በኋላ። ይህ መረጃዎች ያልተለመኑትን ኢትዮጵያ የአምልኮ እና የክርስቲያን መንፈሳዊ አቀናኝዎችን የምንወጪው መሆን ስላልነበረ፣ ሌላውን አገልግሎት አርብ። ስለዚህ EFGBC ቤተክርስቲያን (ሥርዓተ ኦፊሴም ወደዋ) ማንም እንዲጠቀሙ አስታወቁ። ዕብ 13:8 የኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘልዓለምም ያው ነው።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

18 Feb, 11:11

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ አካሄደ።
ከየካቲት 6-9/2017 በ ጉጄ ቆርቻ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ ተደርጓ 2243 ሰዎች ወንጌልን ሲሰሙ 38 ሰዎች ጌታን ተቀብለዋል ።
በወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ የተካፈሉ ወገኖች እንደተባረኩ ከአዘጋጆችሁ ለማወቅ ተችሎአል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

18 Feb, 07:59

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢ ክልል በኮንከን አጥቢያ የወንጌል ሥርጭት ኮንፈራንስ አካሄደ::         
        የካቲት 8 እና 9/ 2017 ዓ.ም በኮንከን አጥቢያ በተዘጋጀው የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ አእምሮና ጥሪ የተደረገላቸው ወገኖች ተገኝተዋል።
      ዘማሪ አማኑኤል ያደታ በዝማሬ ያገለገለ ሲሆን በእግዚአብሔር ቃልና  በፀሎት ወንጌላዊ አዲሱ አመኑ እና ወንጌላዊ ፋይና ቶሎሳ አገልግለዋል።
      በወንጌል ስርጭቱ ኮንፈረንስ 18 ሰዎች በንስሐ ወደ አምላክቸው መንግስት የተጨመሩ ሲሆን 60 ሰዎች ወደ ኋላ  የተመለሱ በንስሐ ታድሰው  ወደ ጌታ ቤት ተመልሰዋል።
     በቀጣይም  በተያዘው ዕቅድ መሰረት በሌሎች አጥቢያዎች የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ እንደሚያዘጋጅ ከክልሉ ፕሬዝደንት ከመጋቢ አእምሮ መልካሙ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

17 Feb, 05:58

#የወንጌል_ስርጭት_እና_የቤተክርስቲያን_ተከላ_ላይ_ስልጠና_ተካሄደ ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የጉሊሶ እና አካባቢው ክልል ከየካቲት 5 - 6/2017 ዓ.ም ድረስ ከግሬት ኮምሽን አጋልጋዮች ጋር በመተበበር ከ70 አጥቢያዎች ለተወጣጡ 185 አጋልጋዮች በወንጌል ስርጭት እና ቤተ ክርስቲያን ተካለ ላይ ስልጠና ተሰጥቶአል።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ወገኖች ጌታ መልካም ጊዜ እንደሰጣቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

14 Feb, 13:09

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ዜናዎች ይከታተሉ።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

13 Feb, 16:15

#የወንጌል_ስርጭት_ተካሄደ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል አስተባባሪነት በኤርቱ እና ቱሉ ኤርቱ እንዲሁም ቦሬ ገለን ሶስቱም የሙሉ ወንጌል አጥቢያዎች በጋራ በመቀናጀት የወንጌል ስርጭት ተካሄደ።
ሮዕብ የካቲት 5 እና 6 /2017ዓ.ም ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን የወንጌል ስርጭት  ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ አእምር መልካሙ እና የሶስቱም ክላስተር ተወካይ መሪዎች የተገኙ ሲሆን በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል።
   በአጠቃላይ በሁለቱ ቀን በነበረው የወንጌል ስርጭት ስራ ላይ ወንጌል አንድ ለአንድ በትራክት የሰሙ 5213 ወገኖች ጌታን የተቀበሉ የዳኑ 73 ወገኖች ቀጠሮ የሰጡ 11ሲሆን በአጠቃላይ ለ5000 ወገኖች የጀማ ስብከት ተካሄዷል።
አዘጋጆች እግዚአብሔር በብዙ መንገድ እንደረዳቸው በመግለጽ አመስግነዋል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

13 Feb, 06:09

የመጋቢ ሹመት ተካሄደ።
በ ኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል የመጋቢ ሹመት ተካሄደ።
እሁድ የካቲት 02/2017 ዓ.ም በሳንሱሲ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለወ/ም ሳሙኤል አሰፋ የመጋቢነት ሹመት የተካሄደ ሲሆን በዕለቱ መጋቢ ሽመልስ ጠጂ የክልሉን ፕሬዚዳንት ወክለው በመገኛት መልዕክት በማስተላለፍ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
መጋቢ ንፍታሌም የሹመት ስነ ስርዓቱን አስፈጽመዋል ።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

11 Feb, 11:57

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና ተካሄደ።
የካቲት 1 ቅዳሜ እና እሁድ 2/17 ዓ.ም በጎተራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በተካሄደው የወጣት መሪ ስልጠና ላይ 70 ወጣቶች ተገኝተዋል።
በወ/ም አማኑኤል መኮንን "የነፍሴ ጥያቄዎች በሚል ርዕስ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በመጋቢ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመናችን ቤተክርስቲያን እና ተሃድሶ በሚል ርዕስ ተሰጥቶአል።
ይህ የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና እየተሰጠ የሚገኘው ለ4ኛ ዙር መሆኑን ከአዘጋጆቹሁ ለማወቅ ተችሎአል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

10 Feb, 07:05

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል  በለቡ  ፉሪ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የአንድ መጋቢ ሹመት ላይ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተወከሉ መሪዎችና የክልሉ ፕሬዝዳንትመጋቢ አእምሮ መልካሙ በቦታው በመገኘት የእግዚአብሔር ቃል አካፍለው የሹመት ስርዓቱን ፈጽሟል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

10 Feb, 04:36

የተተኪ ወጣት መሪዎች ስልጠና ተጀመረ
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ እና አከባቢው ክልል የተተኪ ወጣት መሪዎች ስልጠና ተጀምሯል፡፡
በስልጠናው ከአጥቢያ የተወከሉ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑን ከክልሉ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

07 Feb, 13:57

የስልጠናና የምክክር ፕሮግራም ተጠናቀቀ!

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት ከጥር 28 - 30/2017 ዓ/ም በአዲስ አበባና አካባቢው ለሚገኙት ሶስቱ  ክልሎች  የስልጠናና የምክክር ፕሮግራም እየተካሄደ የቆየ ሲሆን በዛሬው ቀን ተጠናቋል።
በፕሮግራሙም ማብቂያ   የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ደቡብ አፍሪካ ከሚገኝው ፉል ጎስብል ቸርች ኦፍ ጋድ ጋር   በወንጌል ስርጭት፣ ቤተክርስቲያን ተከላና ስነ መለኮት ትምህርት አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

06 Feb, 11:30

ትናንትና የተጀመረው የስልጠናና የምክክር ፕሮግራም እንደቀጠለ ነው

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት ትናንትና የተጀመረው የስልጠናና የምክክር ፕሮግራም እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው ቀን ከደቡብ አፍሪካ ከእግዚአብሄር ሙሉ ወንጌል የመጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተው የህይወት ምስክርነት በመስጠት የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

04 Feb, 15:35

ትኩረቱን በልጆች አስተዳደግ ላይ  ያደረገ ስልጠና ተካሄደ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የልጆች ወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ከምስራቅ ክልል ጋር በመተባበር በሐረር ከተማ ሲሰጥ የነበረው አንደኛ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ከሐርር እና አከባቢው አጥቢያዎች  የተውጣጡ ሰልጣኞች ተካፋይ የነበሩ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት ነዋሪነታቸው በኖርዌ ያደረጉት ጋሽ ጋይም ክብረአብ እና ባለቤታቸው እህት አጥናፍ ብርሃኑ ናቸው፡፡  የስልጠናው ሁለተኛ ክፍል ከወር በኋላ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ተመሳሳይ ስልጠናዎች በሌሎች ክልሎች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን በሌሎች ክልሎችም ለመስጠት ዕቅድ እንደተያዘ ከአገልግሎት ክፍሉ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
Website | Youtube | Tiktok| Facebook |Telegram |Instagram | Threads | Linkedin | Twitter |Pinterest | Whatsapp | Imo

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

04 Feb, 06:07

በኢትጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የሀዋሳና ዲላ አካባቢ ክልል መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ተማሪዎችን አስመረቀ።
    ቅዳሜ ጥር በ24/2017  ዓ.ም ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጽ/ቤት የስነ መለኮት  ኮሌጆች ክትትል ክፍል ሀላፊ መጋቢ ታምራት አዉሎና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሴሚናሪየም ምክትል ፕሬዚዳንት መ/ር አዛሪያ ሹሚ በተገኙበት  13 ተማሪዎችን በዲፕሎማ 46 ተማሪዎችን  በድግሪ መርሃ ግብር በአጠቃላይ 59 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎችም በትምህርት ተቋሙ ባገኙት እውቀት እግዚአብሔርን ለመገልገል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

01 Feb, 11:17

የተተኪ ትውልድ ማስታጠቅ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል ከየአጥቢያ የተወከሉ 40 የሰንበት ልጆች አስተማሪዎች የተተኪ ትውልድን ማስታጠቅ ስልጠና ቅዳሜ ጥር 24/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ልማት ኮሚሽን በምክትል ኮሚሽነሪ በወ/ም እምሩ ሙላቱ በክልሉ ቢሮ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል ።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Jan, 11:48

በ ኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል ሁለተኛው ዙር የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና ተካሄደ።
ጥር 17 እና 18 /2017ዓ.ም በጉለሌ
ጰውሎስ አጥቢያ ቤተክርስቲያን በተካሄደው የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና ላይ ከ 60 አጥቢያ የተወጠጡ 70 የሚሆኑ ወጣቶች  የተሳተፉበት ሲሆን" በመሪነት ማደግ እና ወጣቶችን በመረዳት ማገልጋል/ Growing in leadership and Understanding youth ministry / በሚል ርዕስ በመጋቢ ኤርምያስ ገ/መድህን ስልጠና ተሰጥቶአል። ስልጠናው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል ። 
  በቀጣይ ወር በሌላ ርዕስ ስልጠናው እንደሚቀጥል ከአዘጋጆችሁ ለማወቅ ተችሎአል ።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Jan, 06:50

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሰሚነርየም በመቐለ ከተማ በስነ መለኮት በዲግሪ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 12 ተማሪዎችን አስመረቀ።
እሁድ ጥር18/2017 ዓ.ም በምርቃ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ሴሚናርየም ኘሬዝዳንት መምህር ኂሩይ አድማሱ እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ተማሪዎችም በነበራቻው የትምህርት ቆይታና ዝግጅት ለአገልግሎት እና ለመንፈሳዊ ሕይወት የሚጠቅሙ ብዙ መንፈሳዊ ግባቶችን እንዳገኙ ለማወቅ ተችሎአል።
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

30 Dec, 14:51

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል በጋብቻ ቤተሰብ ማማከር ላይ ስልጠና አካሄደ።
     ታህሳስ 19 እና 20/17 ዓ.ም  የጋብቻ ቤተሰብ የማማከር ስልጠና ላይ ከ40 አጥቢያዎች የተወጣጡ 44 ጥንዶች የተገኙ ሲሆን የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ አእምሮ መልካሙ " የስልጠናው አላማ በቤተሰብ እና በጋብቻ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ይበልጥ ትኩረት ሰጥታ መስራት እንዳለባት በመናገር ሰልጣኞችም የተሰጣቸውን ሀላፊነት በመወጣት አገልግሎት እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
     ስልጠናውንም የሰጡት ጋሽ ሰለሞን ረጋሳና ባለቤታቸው እንዲሁም ወ/ም በለጠ ዋቅቤካ ከባለቤታቸው ጋር በመሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ለበለጠ መረጃ
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

30 Dec, 13:32

የወጣት መሪዎች ስልጠና መጠናቀቁ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካበቢዉ ክልል ሲካሄድ የቆየው  የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና  መጠናቀቁ ታውቋል።
     ከ 45 አጥቢያዎች የተወጣጡ 61  ወጣቶች የተሳተፉበት የመጀመርያ ዙር ስልጠና እሁድ ታህሳስ 20/4/17 ዓ.ም በቤተል መካነ ኢየሱስ ጊቢ ተካሄዶአል።
     በቀጣይም በሁለተኛ ዙር ስልጠና ከ70 አጥቢያዎች 100 ወጣቶችን ለማሳተፍ እቅድ መያዙን ከአዛጋጆችሁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
    ለበለጠ መረጃ
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

29 Dec, 02:55

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካበቢዉ ክልል የተተኪ ወጣት መሪ ስልጠና ተካሄደ።
   የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ቅዳሜ ታህሳስ 19/17 ዓ.ም በጉለሌ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የተካሄደ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚዳንት መጋቢ ሰለሞን ባንቲ  በፕሮግራሙ ላይ በመገኝት የእንኳን ደና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
  በመቀጠልም በመጋቢ ሽመልስ ጠጂ 
ጴንጤቆስጤአዊ የወጣት መሪ /pentecostal youth leaders/ በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጥቷል ።
በስልጠናውም የተሳተፉ ወጣቶች እንደተጠቀሙ ለማወቅ ተችሎአል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

28 Dec, 14:05

#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

28 Dec, 10:19

#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት !!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Dec, 19:32

#አስቸኳይ_የማሳሰቢያ_መልዕክት!!
   በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያንና በፓስተር ዮናታን አክሊሉ በትብብር የሚሰራ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ እንዳለ ተደርጎ እየተሠራጨ ያለው ማስታወቂያ ፍፁም ሀሰትና ማጭበርበር ስለሆነ ቅዱሳን ከዚህ የማታለል ድርጊት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን በነገው እለት ቤተክርስቲያኗ ማብራሪያ የምትሰጥ መሆኑን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።
  👉ለሁሉም እንዲደርስ በአስቸኳይ share share ይደረግ!!
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Dec, 10:42

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
"የእግዚአብሔር ታላቅ ስጦታ ኢየሱስ" በሚል መሪ ቃል ለ10 ቀናት የሚቆይ የዲጂታል ወንጌል ስርጭት ዘመቻን ይቀላቀሉ:: በዚሁ አገልግሎት ፕሮፋይል በመቀየር በተለያዩ ፕላትፎርሞች ላይ ፖስት የሚደረገውን በማጋራት አብረን በዚህ የወንጌል ስራ እንድንጠመድ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
Website | Youtube | Tiktok| Facebook |Telegram |Instagram | Threads | Linkedin | Twitter |Pinterest | Whatsapp | Imo

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

26 Dec, 18:44

#የወንጌል_ስርጭት_ተካሄደ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ ክልል አዘጋጅነት  የወንጌል ስርጭት ኮንፈረንስ በልደታ ሙሉ ወንጌል  መካሄድ ተጀምሯል።
     ሀሙስ ታህሳስ17/04/2017 ዓ.ም በመጀመሪያው ቀን በነበረው  የወንጌል ስርጭት  ወንጌል አንድ ለአንድና በትራክት የሰሙ 8707 ወገኖች ሲሆኑ ጌታን በማግኘት የዳኑ 31 መሆናቸው እና ቀጠሮ የሰጡ 18 ወገኖች መሆናቸው ታውቋል።
      ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ይህ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት አርብ እንሚቀጥል ተገልጾአል ።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

24 Dec, 17:58

#ትላንት_ዛሬ_ነገ በሚል ርዕስ መነሻ ጹህፍ ቀረበ!!
      በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የምስራቅ ክልል  ጽህፈት ቤት ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም በክልሉ ስር የሚገኙ ከ27 አጥቢያዎች፣ የተወከሉ  መሪዎች፣ የኮሌጁ የቦርድ አባላት እና የኮሌጁ ዳይሬክተር በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል፡፡
       የምስራቅ ክልል ሙሉ ወንጌል ሥነ መለኮት ኮሌጅ መምህር  በሆኑት በሃይሉ እምቢበል ትላንት-ዛሬ-ነገ” በሚል ርዕስ መነሻ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ጽሁፍ የኮሌጁን ታካሪዊ ጅማሮ፣ ሂደታዊ እድገት፣ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች፣ አሁን ያለበትን ደረጃና እንዲሁም ወደፊት ምን ለማድረግ እንደታሰበም ጭምር ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
      የክልሉ ጠቅላላ ጉባኤም፣ ኮሌጁ አሁን ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ በመገምገም፣ ትምህርት ቤቱ በክልሉ እያበረከተ ያለውን አዎንታዊ አስተዋጽኦፆ ወደፊት በተሻለ መንገድና አቅም መፈጽም በሚያሰችለው ሁኔታ ላይ በመምከር፣ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እና አንዳንድ ውሳኔዎችን በመወሰን  ስብሰባው ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

24 Dec, 10:46

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት ሰሚነርየም በኦንላይን የ MA መርሐግብር በ ሚሽን ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን እየመዘገበ ይገኛል ስለሆነም የተመዘገቡ ተማሪዎች ስላሉ ከአንድ ሳምንት በኃላ ትምህርቱን ይጀመራል የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በኦንላይ እየላካቹህ እንድትመዘገቡ እናበረታታለን። የመግብያው ፈተና በእንላይን የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን። ለተጨማሪ መረጃ በ 0913124075 አና 0911094987 በመደወል ያነጋግሩን።
https://forms.gle/ZgmmWA3hqjaBDcZb6
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

20 Dec, 11:29

የሰሜን ምስራቅ ካውንስል ጽ/ቤት ተቋቋመ!
       የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የሰሜን ምስራቅ ጽ/ቤት ታህሳስ 01/2017 ዓ.ም በደሴ ከተማ ተቋቋመ ! !
         በዕለቱ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ
ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃድቁ አብዶ፣የካውንስሉ የጽ/ቤት ኋላፊ መጋቢ ጌቱ ለማ እንዲሁም ከ39 ከተሞች የተገኙ 200 የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል።
መርሃ ግብሩ  በተያዘለት  መሰረት የሥራ አስፈፃሚና የቦርድ አባላት ምርጫ
ያካሄደ ሲሆን በዚሁ መሰረት:-
1.መጋቢ ቴዎድሮስ ጌታቸው - ሰብሳቢ ከሙሉ ወንጌል  ቤተክርስቲያን
2.መጋቢ ሰለሞን አበጋዝ - ም/ሰብሳቢ ከሕይወት ብርሀን ቤተክርስቲያን
3..ቄስ ዋኘው አንዳርጌ - ፀሐፊ ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን
4.መጋቢ  ተሾመ ደምሴ መንፈሳዊ ዘርፍ
ከወአክኅ
5.ወ/ም ሞላ ምስራች - ሒሳብ ሹም
ከመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
6.ወ/ም አያሌው እብሬ - ገንዘብ ያዥ ከቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
7.ወ/ም ዳዊት አህመድ - አባል ከገነት ቤተክርስቲያን  የተመረጡ ሲሆን ጉባዔው  በፀለትና ቡራኬ አድርጎ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

20 Dec, 08:05

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምስራቅ ክልል ስነ መለኮት ኮሌጅ 30 ተማሪዎችን በዲግሪ አስመረቀ።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

15 Dec, 15:28

#በኢትዮጵያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተክርስቲያን_በአዲስ_አበባና_አካባቢው_ክልል_አዘጋጅነት_ሲካሄድ_የነበረው_የጀማ_ወንጌል_ስብከት_መርሐ_ግብር_ተጠናቀቀ።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

15 Dec, 15:03

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
ታላቅ የወንጌል ጀማ ስብከት ወንጌል በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀጥታ ስርጭት
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

01 Dec, 08:50

Day 7

አንድ የጠፋብህ ውድ እቃ ላንተ እጅግ ዋጋ እንዳለው ሁሉ የጠፋ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። ምክንያቱም የሰው ባበቤቱ እርሱ እግዚአብሔር ነውና። ዛሬም የአንተ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አንተን ሊፈልግህ መጥቷል:: ደግሞም ይህ ደግ እግዚአብሔር አንተ ወደ እርሱ እስክትመጣ ድረስ እንኳን አልጠበቀም። የጠፋኸውን አንተን፣ ከእግዚአብሔር የራቅከውን አንተን፤ ፈልጎ በልጁ ሊያገኝህ መጥቶ ድነትን አዘጋጅቶልህ።  ከራሱ ጋር በማስታረቅ የዘላለም ህይወትን አቅርቦልሀል:: ከመቅበዝበዝ ህይወት ተርፈህ  ወደሚፈልግህ አባት ልትመጣ ትወዳለህ? ዛሬ ቀኑ ነው::

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ|ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

30 Nov, 09:04

Day 6

ይህ የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  ታላቅ ጥሪ እውነተኛ እረፍት እና እፎይታ የሚገኝበት  ነው። በአካል፣ በስሜት ፣ በሀጢያት ወይም በመንፈሳዊ  ህይወትህ ደክመሀል? ኢየሱስ እኔ ዕረፍት እሰጥሃለሁ ይልሀል::  እርሱ የሚሰጥህ እረፍት:  ከጥፋተኝነትና ከበድለኝነት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት  ነፃ የሚያወጣ እረፍት ደግሞም እርሱ የሚሰጠው እረፍት ግዜያዊ ብቻ ያልሆነ የዘላለም ዕረፍት እና ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት ነው። ወደዚህ እረፍት ኢየሱስ ይጠራሀል!

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ | ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር  | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

29 Nov, 13:39

#የኢትዮዽያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተክርስቲያ_ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል_በሚል_መሪ_ቃል_በአዲስ_አበባ_ስታዲየሚ_የሚካሄደውን_ኮንፍራስ_በማስመልከት_ህዳር_20_ቀን_2017_ዓ/ም_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ተሰጠ።
         በመግለጫው ከታህሳስ 4 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2017ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ኢየሱስ ሰውን ሁሉ ይወዳል በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንፍራንሱ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ የተሰባሰቡ 206 የሚሆኑ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ኮንፍራንሱን በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልፃል።
      በጀማ ስብከቱ  #15ሺህ ሰዎች ወደ ጌታ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለ3 ቀናት የሚካሄደው የምስጋና እና የወንጌል ስርጭት፡ ጀማ ስብከት ሙሉ ወጪው በአጥቢያዎቹ የሚሸፈን ይሆናል። አጥቢያዎቹ በእነዚህ ቀናት ዝግ ሆነው ይቆያሉ።
       የጀማ ስብከቱ  በተመለከተ የቤተ ክርስቲያኗ ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፡ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ መጋቢ አበራ በላይ አዋሬ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል።
    የጀማ ስብከቱ  የአዲስ አበባ እና ሸገር ክልል አጥቢያዎች ናቸው በጋራ ያዘጋጁት። ያለፉትን 10 ወራት የወንጌል ስርጭት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ለ20 ቀናት የሚቆይ በወጣቶች የሚመራ የማህበራዊ ሚድያ የወንጌል ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።
       ከጀማ ሰብከቱ ጋር በተያያዘ በዳለቲ፡ ቂሊንጦ እና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለታራሚዎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
ለ230 ወጣቶች ከሱስ፡ መጤ ባህል እና ጎጂ ልማዶችን በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል። ታህሳስ 2 እና 3 በቂርቆስ ጤና ጥቅቢያ የነጻ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።
         ቤተ እምነቷ ከ3800 በላይ የሚሆኑ አጥቢያዎቿ እና ከሃገር ውጪ በጅቡቲ፡ ሶማሊያ፡ ደቡብ ሱዳን፡ ደቡብ አፍሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የወንጌል ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

29 Nov, 08:59

Day 5

እግዚአብሔር እንዳየ፣ እንደሰማ የሚፈርድ አይደለም:: እርሱ ምሕረት የተሞላ፣ ርህሩህ እና ይቅር ባይ ነው:: እግዚአብሔር ታጋሽ ነው በችኮላም አይቆጣም። ርህሩህ የሆነው እግዚአብሔር ወደ እርሱ እስክትመጣ በብዙ ምህረቱ ይጠብቅሀል::
ታጋሽ፣ ባለ ብዙ ምህረት ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ልትቀርብ ትወዳለህ? ልንረዳህ ዝግጁነን::

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
#ደካማ_ብሆንም_ይወደኛል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

28 Nov, 15:53

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

28 Nov, 08:59

Day_4

ከብዙ ስህተት እና ማባከን በኃላ ቁጣን እየጠበቀ ለተመለሰ ልጅ፣ አባቱ ግን በደስታ እና በርህራሄ ተቀበለው። ምክንያቱም አባት የልጁን መመለስ በጉጉት ይጠባበቅ ነበርና:: እግዚአብሔርም ላንተ ያለው ፍቅር እንደዚሁ ነው:: ወደ እርሱ ብትመለስ የሚቀበል ፍቅር፡ የቱንም ያህል ብትርቅ የሚያቅፍ ፍቅር ሊቀብልህ እጆቹን ዘርግቶ ይጠብቅሀል:: ዛሬ የተያዝክበት ሀጢአት ምንድነው? ዛሬ ከእርሱ እንድትርቅ ያደደገህ ነገር ምንድነው? አባት የሆነው እግዚአብሔር: ወዳጅ የሆነው እግዚአብሔር ና ልጄ ይልሀል:: ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ካለህብት የሀጢአት ክስ ሊያሳርፍ ወደእረፍት ለሚጠራህ አምላክ ምላሽ ዛሬ ልትሰጥ ትወዳለህ? ያሉብህን የትኛውንም አይነት ጥያቄ ልንመልስልህ በዚ አለን!

#የራቅኩ_ብሆንም_ይወደኛል
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል!

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ | ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር  | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Nov, 15:54

ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

27 Nov, 08:59

Day_3

ኃጢአተኛ ፣በደለኛ እንኳን ሆነህ እርሱ በፍፁም ፍቅሩ ወዶሀል:: ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጥቶሀል። ከበዛ እና ከተትረፈረፈ ምህረቱ የተነሳ ኢየሱስ የአንተን ሞት ሞቶልህ ሕይወቱንም ስለአንተ አሳልፎ በመስጠት መውደዱን፣ፍቅሩን በቀራኒዮ ገልጦልሀል:: በምህረቱ ባለጠጋ ወደሆነው ውደ እግዚአብሔር ልትቀርብ ትወዳለህ?

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

26 Nov, 09:21

#Day_2
ሀጢአተኛ እና በደለኛ ሆነህ እንኳን እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ ፍቅሩ ገለጦልሀል:: የእርሱ ፍቅር አንተ እርሱን እንደወደድከው ሳይሆን እርሱ እንዴት አንተን እንደወደደህ ነው:: የእርሱ ፍቅር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ፣ የማይቀያየር፣ ዘላለማዊ ነው:: ዛሬ እርሱን ሳታውቅ ያለህበት ሁኔታ ላይ እንኳን ብትሆን፣ እርሱን ያልተከተልክ እንኳ ብትሆን እርሱ አንተን አውቆህ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ዘላለማዊ የሆነ ፍቅሩን ገልጦልሀል:: ላይጠላህ ወዶህል! አንተን ለመውደድ ሀጢአትህ እና በደልህ ያላገደውን እንዲሁ የወደደህን አባት ልትከተል ትወዳለህ?

1 ዮሐንስ 4:10፤ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

25 Nov, 16:32

ሃጥያተኛ ብትሆን እንኳን እንዲሁ የሚወድህ፣ ሃጥያተኛ የሆነ ሁሉ ደግሞ ምህረት የሚያገኝበት አዲሱ ኪዳን የዓለም ሁሉ መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህም የምህረት ኪዳን ላይሻር፣ ላይጠፋ በደሙ ታትሟል። በኃጢአትህ ሙት ለነበርክ ላንተ፤ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ በሰራልህ ስራ እግዚአብሔር ላንተ ያለውን አስደናቂ ፍቅር አስረድቶሀል:: በዚህም በልጁ ስራ በማመን ደግሞ ከኃጢያት መዳን እንድትችል መንገድ ሆኖልሀል። በደለኛ እንኳን ብትሆን የሞተልህ ኢየሱስ እንዲሁ ስለወደደህ በፍቅሩም ዘላለም እረፍት ወደሆነው ወደ አባቱ መንግስት ይጠራሀል:: ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደተደረገልህ ጥሪ ልትመጣ ትወዳለህ? ካጎበጠህ የሀጢአት ሸክም ልታርፍ ትወዳለህ? ና ወደ ኢየሱስ እርሱ ከሸክም ሁሉ ይገላግልሀል!
ያሉብህን ጥያቄዎች ልንመልስልህ፣ ልንረዳህ በዚህ አለን::

#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

25 Nov, 16:01

ኢየሱስ ሰው ሁሉ ይወዳል በሚል መሪ ቃል  ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን እና ከግሬት ኮሚሽን ሚንስትሪ ጋር የተዘጋጀ የዲጂታል ወንጌል ስርጭት ዘመቻን  ይቀላቀሉ::
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት|ዩትዩብ|ፌስቡክ|ቴሌግራም|ኢንስታግራም|ሊንክድኢን|ትዊተር |ፓይንተረስት|ዋትስአፕ|ቲክቶክ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

25 Nov, 13:40

ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ለ20 ቀናት የሚቆይ የዲጂታል ሚሽን የወንጌል ዘመቻ ስለጀመርን እናንተም በዚሁ አገልግሎት ፕሮፋይል በመቀየር በተለያዩ ፕላትፎርሞች ላይ ፖስት የሚደረገውን በማጋራት አብረን በዚህ የወንጌል ስራ እንድንጠመድ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ:
በዌብ ሳይት፡ https://etfullgospel.com/
ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/efgbc_official_account/
ሊንክድኢን፡ https://www.linkedin.com/company/ethopian-full-gospel-believers-church/
ትዊተር፡ https://twitter.com/church43162
ፓይንተረስት፡ https://www.pinterest.com/EFGBC_HO/
ዋትስአፕ: https://whatsapp.com/channel/0029VaIRFHfLNSa6YKW7t01E
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/@efgbchurch/ ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

25 Nov, 12:53

#ዞር_ብዬ_ሳየው_ያለፍኩባቸው_ዝቅታዎች እና #ከፍታዎች_የተሰኘው_በዶ/ር_ንጉሴ_ተፈራ_ተጽፎ_የተዘጋጀው_መጽሐፍ_በድምቀት_ተመረቀ።
        እሁድ ሕዳር 15/17 ዓ.ም በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ "ዞር ብዬ ሳየው" ያለፍኩባቸው ዝቅታዎች እና ከፍታዎች የተሰኘው መጽሐፍ ሲመረቅ ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ የቅርብ የአገልግሎት ባለንጀሮቻቸው ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
      በመጋቢ ተመስገን ብርሃኑ የመክፈቻ ጸሎት ተደርጎ በሙሉ ወንጌል ሀ መዘምራን ቡድን ዝማሬ በማቅረብ  ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል።
      በዶ/ር ማሙሻ ፈንታ " 2 ጢሞ 3 -14 ህያው ምስክሮች ያስፈልጉናል በሚል ሀሳብ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አካፍለዋል።
     በመቀጠልም የቀድሞ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳን የነበሩት ወ/ም  ጌታቸው በለጠ "ዞር ብዬ ሳየው" መጽሐፍ  ተገምግሞአል።
   ስለ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ለቤተክርስቲያን ለሃገራቸው የከፈሉትን መስዋት እና ያበረከቱትን መልካም አስተዋጽኦ አጽንኦት በመስጠት አውስተዋል።
      መጋቢ ላኮ በዳሶ "ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ተንቀሳቃሻ ቤተ መጻሕፍት ናቸው ትውልድ ከእሳቸው ብዙ ይማራል ዛሬ ደሞ በመጽሐፍ ሕይወታቸው በመከተብ ለቀጣይ ትውልድ ተምሳሌነታቸውን አሳይተዋል ብለዋል"።
        የዶ/ር ንጉሴ ተፈራ ወዳጆች የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አለም፣መጋቢ መርዕድ ለማ፣ መጋቢ ሚናስ ብሩክ ሌሎችም ስለ መልካም ስብዕናቸው፣ እንግዳ ተቀባይነታቸው፣የአመራር ችሎታቸው፣ አንደበተ ርዑተነታቸው፣ስለ መልካም አስተማሪነታቸው፣ስለ ጸሎት ሕይወታቸው፣ ስለማህበራዊ ንቁ ተሳትፎአቸው ፤ስለ ስራ ችሎታቸው በአድናቆት በመናገር ፍቅራቸውን ገልጸውላቸዋል።
      ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ መጽሐፉን ሲጽፍ የረዳቸውን እግዚአብሔርን፣ በአጸደ ስጋ ያሌሉትንትን ወላጅ እናታቸውን አመሰግናዋል።
ባለቤታቸውና መላው ወዳጆቻቸውን አክብረዋል።
       በመጨረሻም   ዞር ብዬ ሳያው ያለፍኩባቸው ዝቅታዎችና ከፍታዎች መጽሐፍ  በድምቀት በጸሎት ተመርቆ ለአንባቢያን ቀርቦአል።
     መጽሐፉ 438 ገጾች ያሉት እና 31 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 21/17 ዓ.ም በተወዳጅ  ሚድያ አዘጋጅነት በድጋሚ በብሔራዊ ቲያትር ከፍተኛ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የስራ አጋሮቻቸው ባሉበት በደመቀ ሁኔታ በድጋሚ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሎአል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

23 Nov, 12:42

የማህበራዊ ሚድያ ፕሮፋይላችሁ በዚህ በመቀየር ዘመቻውን ይቀላቀሉ!

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

21 Nov, 14:47

ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

21 Nov, 05:19

#የኢትዮጵያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተክርስቲያን_ሴሚናሪዎችን እና #ኮሌጆችን_ሰብስቦ_በክላስተር_ደረጃ_ማደራጀቱ_ተገለጸ።
          ህዳር 10/3/17 ዓ.ም በመልካ አዳማ ሆቴል በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ የክልል እና የሴሚናሪየም ፕሬዝዳንቶች፣የስነ መለኮት ትምህርት ቤት ዲኖች አስተማሪዎች ተገኝተዋል።
           በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ያሉ በርካታ ስነ መለኮት ትምህርት ቤቶች አደረጃጀት ላይ ስብሰባ ተደርጓል ።
   ስብሰባው በዋናነት አቅም የተበታተነ እንዳይሆን በክላስተር በተለያዩ ቦታ ያሉ ጂኦግራፊ አቀማመጣቸው የሚቀራረብ የስነ መለኮት ተቋማት በአንድነት ተደራጅተው የሰው ሀይላቸውን አደራጅተው እና የፋይናንስ አቅማቸውን አዳብረው በተሻለ ሁኔታ የስነ መለኮት ትምህርት እንዲሰጡ እና የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እንዲሰለጥኑ ለማደረግ መሆኑን ተገልጾአል።
       የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የስነ መለኮት ሴሚነሪየም ፕሬዝዳንትና መምህር የሆኑት ሂሩይ አድማሱ " የተማሩ አገልጋዮችን ለማፍራት ፣ቤተ መጻህፍትን የስነ መለኮት ተቋማትን ከቁጥራቸውን በመቀነስ አንድ ላይ በማደራጀት ከዋናው ሴሚናሪየም ጋር በኳሊክረም ተያይዘው ቤተክርስቲያን የሚደግፉ መሪዎችን ለማፍራት ሲሆን ይህም ውጤታማ ያደርገናል" ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸውልናል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

12 Nov, 09:37

ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።ኋኀ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

12 Nov, 07:29

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል ከአዳጊ ቤተክርስቲያን ወደ አጥቢያነት ለመጡ መሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ  ተሰጠ።
      ጥቅምት 30/2/17 ዓ.ም በአዋሬ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፋሲል ተክሉ የልጆች እና የወጣቶች ሀላፊ መጋቢ ኤልያስ አየለ ከ12 አጥቢያዎች የመጡ 61 መሪዎች ተገኝተዋል።
      መጋቢ ፋሲል ተክሉ የሙሉ ወንጌል መተዳደርያ ደንብ  እና መመርያን ለመሪዎች አብራርተዋል።
      በመቀጠልም በመጋቢ አፈወርቅ ብርሃኔ ስለ እቅድ  እና ፋይናንስ ዝግጅት ስልጠና ሰጥተዋል።
መጋቢ ኤልያስ አየለ "የልጆች ታዳጊዎች ወጣቶች ዲፓርትመንቱን አስመልክቶ የግዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቶአል።
     በቤተ እምነቱ አማካኝነት  ታህሳስ ወር ላይ የሚካሄደው ታላቅ የጀማ ስብከት ወንጌል አስመልክቶ ዝግጅቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀላፊነት ለመሪዎች ተሰጥቶአል።
      ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።ኋኀ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

11 Nov, 07:52

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የመጋቢነት ሹመት መርሃ ግብር አካሄደ።
      እሁድ ሕዳር 1/3/17 ዓ.ም በከራቡ ሙሉ ወንጌል አጥብያ በተካሄደው የመጋቢ ሹመት መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ አእምሮ መልካሙ፣ሐዋርያው ገርቦሌ ሂርጳ ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች የቤተክርስቲያኗ ምዕመን ተገኝተዋል።
         ሐዋርያው ገርቦሌ ሂርጳ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር በሰጣት አገልጋዮች በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
     በመቀጠልም በመጋቢ አእምሮ መልካሙ "አትርሳ" በሚል መሪ ቃል ጌታ በሕይወታችን ላደረገው መልካም ነገር  መርሳት የለብንም ሲሉ በትንቢተ ኤርሚያስ 2:1-5 ያለው ላይ ቃል በመመስረት የእግዚአብሔር ቃል ለጉባኤው አካፍለዋል።
      የከራቡ ሙሉ ወንጌል አገልጋይ የሆኑት ወ/ም ገመቹ ቶሌራ በመጋቢነት የተሾሙ ሲሆን የሹሐት ስርዓቱን የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ አእምሮ መልካሙ አስፈጽመዋል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

08 Nov, 12:33

#ለታላቁ_የጀማ_ስብከት_ወንጌል_በአዲስ_አበባ_ስታድየም_ለሚካሄደው_መርሃግብር_ልዩ_የጸሎትና_የተሃድሶ_ኮንፈረን_ተካሄደ።
     የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባና አካባቢው የሚገኙ ሶስቱም ክልሎች አጥቢያ ቤተከርስቲያን ያዘጋጁት ጥቅምት 25 እስከ አርብ 29/2/17 ዓ.ም በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥብያ  የጸሎትና የተሃድሶ ኮንፈረንስ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሶስት ሺህ በላይ የጸሎት እና የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ተገኝተዋል።
     መጋቢ ምህረት ከበደ፣ነብይ ዳዊት በቀለ፣መጋቢ አበራ በላይ፣ነብይ ብርሃኑ፣ ነብይ ገዛህኝ ሎሎችም የጸሎት አገልጋዮች እና የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ሀ እና ለ መዘምራን ቡድን አገልግለዋል።
       የአምስት ቀኑ የጸሎትና የተሃድሶ ኮንፈረንስ አስመልክቶ አጠቃላይ ምን ይመስል እንደነበረ የጸሎት ግብረ ሀይሉ አስተባባሪ የሆኑት ወንጌላዊ ፍሬዎት ጉዲሳ " የጸሎት ኮንፈረንሱ ትልቅ መነቃቃት የታየበት፣ለሙሉ ወንጌል እና ለሀገርም ዳግም ትንሳኤ የሚሆኑበት መሆኑንና፣አንድነት የታየበት፣ታላቅ ማስታወሻ ሊሆን የሚችል  እግዚአብሔር በቃሉ እና በነብያቱ አማካኝነት ድልን እንደሚሰጥ የተናገረበት መሆኑን  ጌታ እጅግ መልካም ጊዜ እንደሰጣቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸውልናል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

04 Nov, 08:02

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል በቱሉ ቦሎ እና በሌመን አካባቢ ላሉ አጥብያዎች ስልጠና ሰጠ።
        ጥቅምት16 /02/ 2017 ዓ.ም ከአሥራ አንድ አጥቢያ ለተወጣጡ ለመሪዎች ጉባዔ ስብሳብና ለአቃቤ ነዋይ በሂሳብ አያያዝ  ዙሪያ ሥልጠና  በቱሉ በሎ አጥብያ ተሰጥቶአል።
    ሰልጣኞችም እጅግ አንደተጠቀሙ ገልጸዋል።
      በተያያዘም በሌመን አካባቢ  በጥቅምት 23 /0 2 /2017 ዓ.ም ከአስራ አንድ አጥቢያ የመጡ የመሪዎች ጉባዔ ስብሰቢ እና አቃቤ ነዋይ ለኦዲት ኮሚቴዎች በሂሳብ አያያዝ ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዚህ ሥልጠና አስፈሊጊ የሆነ የሂሳብ ፎርሞችንና ባህረ መዝገብ ተዘጋጅቶ ለአሥሩም የአጥቢያ መሪዎች መረከባቸው ተገልጾአል ።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

03 Nov, 14:56

#ዞር_ብዬ_ሳየው_ሊመረቅ_ነው።
          ዶ/ር ንጉሤ ተፈራ በአገራችን የጋዜጠኝነት ታሪክ ከብሥራተ ወንጌል ሬድዮ ጣቢያ ጀምሮ እስከ የኢትዮጵያ ሬድዮ በአገር መሪዎች ሳይቀር የተደመጡ እና የተወደዱፕሮግራሞችን አዘጋጅ ነበሩ። ከዚያም በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣንነት እስከ የሚኒስትር ማእረግ ድረስ በማደግ አገራቸውን በመስኩ በከፍተኛ ደረጃ ያገለገሉ አንጋፋ የአገር ባለውለታ ናቸው። በመንፈሳዊ ሕይወታቸውም ከቀደምቶቹ የወንጌል አማኞች አንዱ እና የሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን መስራች አገልጋይ ትውልድ መካከል የነበሩ ለበርካታ የወንጌል አገልጋዮችም (ለፓ/ር ዳንኤል መኮንን፣ ለፓ/ር መርእድ፣ ለፓ/ር ምክሩ በቀለ፣ … ) ተምሳሌት እና የአገልግሎት አጋር የነበሩ ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኝ አብያተ ክርስቲያናትን በፍቅር እና በትህትና በማገልገል ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አርበኛ ናቸው።
እነሆ የዶ/ር ንጉሤ ግለታሪክ መጽሐፍ ዝግጅት ተጠናቆ ሊቀርብልን ነውና ሁላችን በምረቃው ላይ ተገኝተን ጌታን እናመስግን መጽሐፉንም በማንበብ እግዚአብሔር በባሪያው ሕይወት የሠራውን ድንቅ ምስክርነት እንካፈል።
👉ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል !!
#እሁድ_ኅዳር_15_2017
#በቀጠና_ሁለት_ሙሉ_ወንጌል
#ከቀኑ_8_ሰአት_ጀምሮ
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

02 Nov, 17:06

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተከርስቲያን ለሶስት ቀናት የቆየ ስልጠና ተከናወነ
ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 22 ድረስ ለሶስት ቀናት በጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከEvery Home for Christ Ethiopia ሚኒስቲሪ ጋር የተዘጋጀው የheart Seminar ተጠናቀቀ። በቄስ ዶ/ር ሃንክ ካንተርስ የተሰጠው ስልጠና በዋናንት ያተኮረው ውስጣዊ ፈውስ ላይ ሲሆን ስለ ሰው ልጆች ልብ፣ ስለ ልብ ጉዳቶች እና የጉዳቶች ምንጭ፣ ከልብ ስለሆነ ይቅርታ እና ከተለያዩ ስሜታዊ ጉዳቶች ነፃ የመውውጣት አገልግሎት መፅሃፍ ቅዱሳዊ እና ተግባራዊ ትምህርቶች ተሰጥተዋል። በስልጠናው ብዙ ክርስቲያኖች እና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በተለያዩ የህይወታቸው አጋጣሚዎች ባገጠሟቸው ክስተቶች፣ የአስተዳደግ ሁኔታ፣ መገፋቶች እና በደሎች ምክንያት በብዙ ህመም ውስጥ እንደሚኖሩ እና ህይወታቸው እንዲሁም አገልግሎታቸው በብዙ መልኩ እየተጎዳ እና እግዚአብሔ በእነርሱ ሊሰራ ያለውን ነገር እንዳይሰራ እንደሚያደርገው መፅሃፍ ቅዱሳዊ ክፍሎች በመጥቀስ እና ከ40 አመት በላይ የቆየ የአገልግሎት ልምዳቸውን በማካፈል ለማሰተማር ሞክረዋል። እነዚህንም ችግሮች ለመፍታት ፍፁም የሆነን ይቅርታ ማድረግ፣ በፍቅር መመላለስ እና በእግዚአብሔር ፅድቅ ላይ ተደግፎ መኖር ቁልፍ የህይወት ስርዓቶች በመሆናቸው በጥልቀት በሶስቱም ጉዳዮች ላይ ትምህርት ተሰጥቷል። በስልጠናው ላይ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከጅቡቲ፣ ከሱማሊያ ሃርጌሳ፣ ከኤርትራ የመጡ አማኞች እና አገልጋዮች የተሳተፉ ሲሆን ከአገር ውስጥም ከትግራይ፣ ከጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ዝዋይ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ህብረት ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ አጥቢያዎች የመጡ አጋልጋዮች እና የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተለያዩ የዘርፍ አገልጋዮች ተሳታፊ ሆነዋል። ከተለያዩ የአፍሪካ አካባቢዎች ለመጡትም አገልጋዮች እና ሃገሮች ልመና እና ምልጃ የቀረበ ሲሆን በሃገራቱ ውስጥም ስላለው የወንጌል እንቅስቃሴ መልካም እድሎች እና እያጋጠሙ ስላሉ ስደቶች ምስክርነት እና ገለፃ ተደርጓል። ይህን ስልጠና ከአጥቢያ ቤተክርስቲያኒቱ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የ Every Home for Christ Ethiopia ሚኒስትሪ አገልጋዮችን በተለይም ደግሞ የሚኒስትሪውን የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ቀንድ ዳይሪክተር የሆነውን ቄስ ዶ/ር ሳሙኤል በቀለን እግዚአብሔር ይባርክ።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

30 Oct, 13:20

#ድጓበር_አልባው_ዘማሪ

ወንድም አዲሱ ወርቁ

          በሕዝብ ተወዳጁ ዘማሪ አዲሱ ወርቁ፤ “ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ በሚለው መዝሙራቸውና እንዲሁም ከዶ/ር ለገሰ ወትሮ ጋር በጣምራ ባቀናበሩት “ከሞትም ያድነዋል” በተሰኘ ዝማሬያቸውና በሌሎችም መዝሙሮቻቸው በምድሪቱ ላይ ይታወቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የዘማሪ አዲሱ ወርቁን መዝሙሮች በብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ካዳመጡ በኋላ ወደ ቤተ መንግሥት እንዲመጡ አድርገዋቸው፣ የሕይወት ምስክርነታቸውን አድምጠው እንዳበረታቱዋቸው ታሪካቸው ያወሳል፡፡ ዘማሪ አዲሱ ወርቁ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለይ በመዝሙር አገልግሎት ውስጥ ከፍ ያለ ድርሻ የነበራቸው ሲሆኑ፤ ዝማሬዎቻቸው በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለሕዝብ በረከትና ለወንጌሉ አገልግሎትም ዛሬም ድረስ እየዋለ ይገኛል፡፡
"ምስጋና ለኢየሱስ ምስጋና..."
“የአግዚአብሔር በግ...”
“ትዝ ይለኛል ያ መድሕኔ..."
“ጌታየን አከብራለሁ...” የሚሉትና ሌሎችም በርካታ መዝሙሮቻቸው የአማኙን መንፈሳዊ ሕይወት አንጸዋል፡፡ የዱሮው አውሮፕላን ማረፊያ - ውልደታቸውና እድገታቸው አዲሱ ወርቁ ከአባታቸው ከሻለቃ ወርቁ መርዕድና ከእናታቸው ወ/ሮ አረጋሽ ኪዳነማርያም በአዲስ አበባ ከተማ የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ተወለዱ፡፡ ካደጉ በኋላም በናዝሬት (አዳማ)ና በአዲስ አበባ የድሮው አውሮፕላን ማረፊያና፣ በመስከረም ማዞሪያ አካባቢም ኖረዋል፡፡
     ትምህርታቸውንም በአዲስ አበባ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በሒሳብ መዝገብ አያያዝ ካጠናቀቀቁ በኋላ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲም መማር ጀምረው በ1966 ዓ.ም ወደ አሜሪካ በማቅናት በአራል ሮበርትስ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን፣ ሁለተኛ ድግሪያቸውን በፋይናንስ አስተዳደር አጠናቅቀው በመቀጠልም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲና በኦክላሆማ ስቴት ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሦስተኛ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡
           የሥራው ዓለም
     አዲሱ ወርቁ በሥራው ዓለም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 1963 ዓ.ም እስከ 1966 ዓ.ም ያገለገሉ ሲሆን፤ ወደ ውጪ አገር ከሄዱ በኋላም በካሊፎርኒያ የፐብሊከ አካውንቲንግ ፎረም፣ በኦሬንጅ ካውንቲ ካሊፎርኒያ የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የበጀት ማናጀር በመሆን፣ በንግድ ልማት ውስጥ በጥናት፣ በኦዲተርና ዋና ማናጀር በመሆንም አገልግለዋል፡፡ በግል የንግድ ድርጅት በ “ፓሲፊከ ዩናይትድ” የቦርድ ሊቀ መንበርና ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን፣ እንደዚሁም “ፓን ሜር ኢንተርፕራይዝ" (Pan Mer Enterprise) ተቋም ውስጥ መሥራችና ዋና የሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሠርተዋል፡፡
አገልግሎት
         መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በሚመለከት ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩበት ወቅት በንግድ ሥራ ኮሌጅ (ኮሜርስ) ውስጥ የክርስቲያን ተማሪዎች ኅብረትን ከወንድም አዳሙ አባተ ጋር በመሆን አቋቁመው፣ የትምህርት ቤት ኳየር በማደራጀትና የሙሉ ወንጌል መዘምራን ከመቋቋሙ በፊት በድሮ አውሮፕላን ማረፊያ በነበረው የሙሉ ወንጌል አማኞች ጸሎት ቤት በኅብረት መዝሙር በማገልገል አሳልፈዋል፡፡ በሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን የመዝሙር አገልግሎትም የኳየሩ መሪ እስከ መሆን ተሳትፈዋል፡፡
በሰሜን አሜሪካ በሚገኘው የወንጌላውያን አብያተ ከርስቲያናት ኅብረት (Ethiopian Evangelical Churches Fellowship) ውስጥም ለምሥረታው ተባባሪ ከመሆን በተጨማሪ ለብዙ ዓመታት የፋይናንስ ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በሎስ አንጀለስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኅብረት ቤተ ከርስቲያንን (Ethiopian Christian Fellowship Church, Los Angeles) ለመመሥረት ጌታ ከተጠቀመባቸው ወገኖች መካከል አንዱ ሲሆኑ በሽማግሌዎች ቦርድ ሊቀ መንበርነትና በሒሳብ ኃላፊነት ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በሚገኘው የሙሉ ወንጌል አማኞች ኔትወርh (Mulu Wongel Believers' Fellowship Network) የተባለውን የእርዳታ ድርጅት ከመሠረቱት አንዱ ሲሆኑ የኔትወርኩ ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም ማህሌት የአምልኮና የሙዚቃ አገልግሎት (Mahlete Institute of Worship and Music) የተባለውን የአምልኮና የሙዚቃ ኅብረት ከፕሮፌሰር ጥላሁን አደራና ከመጋቢ መላኩ ይገዙ ጋር አብረው የመሠረቱ ሲሆን፤ የሒሳብ ኃላፊ በመሆንም አገልግለዋል፡፡
         አዲሱ ወርቁ ጌታን የተቀበሉት ታህሳስ 26 ቀን 1961 ዓ.ም ሲሆን የውሃ ጥምቀት የወሰዱት ሰኔ 2 ቀን 1961 ዒ.ም ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ደግሞ ነሐሴ 1961 ዓ.ም ነው፡፡ ለአዲሱ ወንጌልን የመሰከሩላቸው አቶ ሳምሶን እሸቴ የተባሉ ወንድም ናችው፡፡..........#ይቀጥላል!

👉መጽሐፍ ፦ "ቀደምቶችሁ"
👉ገጽ፦ 193/195
        ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

30 Oct, 08:01

ቦታው: ቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

29 Oct, 07:59

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነመለኮት ሴሚናሪ የሚከተሉትን ፕሮግራሞች ከ ጥቅምት  መጨረሻ ጀምሮ በሚከተሉት ፕሮግራሞ ማለትም :-
1. የልጆችና የወጣቶች አገልግሎት
2. በክርስቲያናዊ ማማከር አገልግልት
3. የሚስዮናዊነት

በ1ኛ ዲግሪ ለመሥጠት ዝግጅቱን አጠናቀዋል ስለሆነም መማር የምትፈልጉ ሁሉ በሚከተሉት መሥፈርቶች መሠረት መመዝገብ ትችላላችሁ።

1. እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲግሪ ያለው ሰው 54 ክሬዲት ይያዝለታል
2. በቲኦሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ሰው ደግሞ ቲኦሎጂካል ኮርሶች በሙሉ ይያዝለታል።
3. በቲኦሎጂ ዲፕሎማ ያለው ሰው ደግሞ 10 ኮርሶች ይያዙለታል
4. ምንም የሌለው ግን የመግቢያ መሰፈርቶችን አሟልቶ መማር ይችላል።

እነዚህ መመዘኛዎች አዳዲስ የሚከፈቱ ፕሮግራሞችን ሁሉ ይመለከታል።

+251913124075
+251968001933
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

24 Oct, 15:47

#የአገልጋዮች_ሹመት_ስነስርዓት_ተካሄደ።
   በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል የቱሉ ዲምቱ ፈጩ  ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የአገልጋዮችን ሹመት ስነ ስርዓት አካሄዳለች።
     እሁድ ጥቅምት 10/2/17 ዓ.ም የቱሉ ዲምቱ ፈጩ  ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው የአገልጋዮች ሹመት ስነ ስርዓት ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፋሲል ተክሉ እና ጥሪ የደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
     መርሃግብሩ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን የቤተክርስቲያኗ የህብረት መዘምራን በዝማሬ አገልግለዋል።
         በመቀጠልም በቤተክርስቲያኗ ዋና መጋቢ ለሚ ሆርሳ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማቅረብ በዚህ አስቸጋሪና ሰው ሁሉ ወደራሱ ባዘነበለበት ጊዜ በጣም ትሁት ቅኖች እግዚአብሔር የሚፈሩና ታዛዥ የሆኑ  አገልጋዮች ጌታ ስለሰጠን እናመሰግናለን ብለዋል።
     መጋቢ ፋሲል ተክሉ "የቀረልንን ዘመን በስኬት እንድንጨርስ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?? በሚል ርዕስ  2ኛዜና 26:1-5 ባለው ቃል በመመስረት የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት አቅርበዋል።
       የአገልግሎት ሹመት የተሰጠቸው አገልጋዮች  መጋቢ አዲስ ቢራ፣ወንጌላዊ ደበላ አደሬ፣ወንጌላዊ ትርንጎ ቦቤ፣ወንጌላዊ ዳንኤል ሞቲ ሲሆኑ የክልሉ ፕሬዝዳንት በሆኑት በመጋቢ ፋሲል ተክሉ የአገልግሎት ሹመት ስነ ስርዓት ተፈጽሞአል።
     በመጨረሻም ከቤተክርስቲያኒቱ አባላት ጋር በጋራ  አብሮ ማዕድ በመቁረስ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

19 Oct, 12:04

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ስነመለኮት ሴሚናሪ የሰነ አመራር ትምህርት በዲግሪ መርሀግብር እየሰጠ እንደ ሆነ ይታወቃል። የ2017 ፕሮግራም የሚጀምረው ሕዳር 2 ስለሆነ አዲስ ተመዝግባችሁ መማር የምትፈልጉ ሁሉ  ዶክመንታችሁን በ telegram በመላክና ክፍያ በመፈጸም መመዝገብ ትችላላችሁ። ለተጨማሪ መረጃ በ ስ.ቁ 0968001933 ወይም 0913124075  ደውላችሁ አነጋግሩን።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡  https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

19 Oct, 07:28

የወጣት መሪዎች ስልጠና ተከናወነ።
        በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአምቦ እና አከባቢው ክልል የወጣት መሪዎች ስልጠና ተካሄደ፡፡
     ከጥቅምት 7- 9/ 2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት  በተካሄደው ስልጠና ላይ ከ 70 አጥቢያዎች  የተውጣጡ 70 ሰልጣኞች ተገኝተዋል።
     ስልጠናውን  እና  የቤተ ዕምነቱ የልጆች ወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ሃላፊ  መጋቢ ኤርሚያስ ገብረ መድኅን እና የክልሉ ፕሬዝደንት መጋቢ ይበልጣል  ስለሺ  ሰጥተዋል።
    ስልጠናው በዋናነት የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ ያማከለ የወጣቶች አገልግሎት መገንባት ላይ ያተኮረ ሲሆን የወጣቶች አገልግሎት አብይ ዓላማ  የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በወጣቶች መፈፀም መሆኑን ተገልጿል ።
    ሰልጣኞች የሰለጠኑትን በአጥቢያዎቻቸው እንዲተገብሩ  የአደራ መልዕክት ተላልፏል ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን Ethiopian Full Gospel Believers' Church

18 Oct, 15:52

የመሪዎች ስልጠና ተካሄደ።
    በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያ የደቡብ ኦሞ እና የጋሞ ጎፋ
አካባቢ ክልል ለቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ስልጠና አካሄደ።
      ስልጠናው የተከናወነው ጥቅምት 7 እና 8 /2/17 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ሲሆን የቤተ እምነቱ  የወንጌል ተልእኮ እና የእረኝነት መምሪያ ዳይሬክተር የሆኑት መጋቢ ታረቀኝ ኡመታ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ሣሙኤል ተገኝ እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ካሉ ከ119 አጥቢያዎች የተወጣጡ 120 አገልጋዮች ተገኝተዋል።
       ስልጠናውን  ዘማሪ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ "ምስባኮቻችን" በሚል ርዕስ ሰጥተዋል።
  የስልጠናው መርሃ ግብር በዋናነት ዓላማው በጋራ  የምናካሄዳቸው መንፈሳዊ ኘሮግራሞች እግዚአብሔርን የሚያከብር ፣ቤተክርስቲያንን የሚያንጽና ሌሎችን የሚባርክ እንዲሆን ታስቦ መሆኑን ታውቋል።
    በስልጠናው የተገኙት መሪዎችና አገልጋዮች ስልጠናው  እጅግ እንደጠቀማቸው፣ መንፈሳዊ መረዳት እንደጨመረላቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸውልናል ።
     ስልጠናው የተዘጋጀው በዋናው ጽ/ቤት እና በክልሉ አማካኝነት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።