የቤተ ክርስቲያን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜያቸው ይሳሳቱ ነበርን?
አሳቤን እንደሚከተለው አቀርባለሁ:-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” በማለት መጸለዩን ወንጌላት ይናገራሉ። ለመሆኑ ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር (አብ) ጌታ ኢየሱስን ለብቻው ትቶት ነበርን?
አንዳንዶቹ አባቶች የክርስቶስ መለኮትነት የክርስቶስን ሰው-ነት (ትስብዕት) ትቶ ከመሄዱ የተነሣ ሰው-ነቱ መለኮትነቱን “ለምን ተውከኝ?” በማለት የተናገረበት አድርገው አቅርበውታል።
ኢጲፋንዮስ (Epiphanius):
... while these things were happening, these words were addressed in the name of his human nature to the divine nature united to it. (PG 15, 1929)
አምብሮስ (Ambrose):
“Jesus cried in a loud voice: ‘My God, my God, look at me; why have you abandoned me?’ Near death, the man raises a cry because of his separation from the divinity.” (Patrologia Latina( PL) 15, 1929).
Hilary of Poitiers:
The cry to God in truth is the voice of a body departing, having declared the separation of the Word of God from itself. (SC 258.254 On Matthew 33.6)
የእነዚህ አባቶች ትርጓሜ “ተዋሕዶ”ን የሚያፈርስ አይደል? ከዚህስ በላይ ንስጥሮሳዊነት አለ?
በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት ለእኛ መዳን እንዴት እንዳስገኘ ለማስረዳት ከሚያቀርቡት የስርየት ሞዴል ዋነኛው የቤዝዎት (ransom) ሞዴል ነው። ይህን ሞዴል በማስረዳት ሂደት ውስጥ ግን “ቤዝዎቱ የተከፈለው ለማን ነው?” የሚለው ጥያቄ ለማብራራት ሲሞክሩ አንዳንድ መልካም አባቶች ስሕተት ውስጥ ገብተዋል።
ለምሳሌ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (Gregory of Nyssa) ክርስቶስ ኢየሱስ በቤዛነት ለዲያብሎስ መሰጠቱን (መከፈሉን) አስተምሯል። ሰይጣን የተሻለውን ሰው (ኢየሱስ ሰው ብቻ መስሎት) በቤዛነት ክፍያ መረጠ፤ ተከፈለው።
"The Enemy, therefore, beholding in Him such power, saw also in Him an opportunity for an advance, in the exchange, upon the value of what he held. For this reason he chooses Him as a ransom1999 for those who were shut up in the prison of death." (Or. Catech. 22 (NPNF 205 ገጽ 923-24).
ከዚያም እግዚአብሔር ሰይጣንን ሸውዶ (አታልሎ) አሸነፈው። “that it was by means of a certain amount of deceit that God carried out this scheme on our behalf.” (Or. Catech 26 (NPNF 205 ገጽ 928).
እግዚአብሔር ሰይጣንን ያታለለው ለመልካም ነው፤ መድኃኒትን በምግብ ውስጥ እንደሚደብቅ ሐኪም። ይህም ጥቅምና ትርፍ ያስገኘው ለታገትነው (ለጠፋነው) ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለጥቃት አድራሹ ጭምር መሆኑን ይጠቁማል። (ሰይጣንም የመዳን ተስፋ አለው እንዴ?)
He Who is at once the just, and good, and wise one, used His device, in which there was deception, for the salvation of him who had perished, and thus not only conferred benefit on the lost one, but on him, too, who had wrought our ruin. (NPNF 207 ገጽ 928-29.)
ይህ መልካም አስተማሪ በዚህ ረገድ እንደ ሳተ ከሌሎች አባቶች ጽሑፍ እንገነዘባለን።
የጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ወዳጅ የነበረው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ (Gregory of Nazianzus) ግን ይህን አምርሮ ተቃውሟል። ይህንም ሲያደርግ ወዳጅነቱ አልገደበውም።
“Now, since a ransom belongs only to him who holds the bondage, I ask to whom was this offered, and for what cause? If to the Evil One, fie upon outrage! If the robber receives ransom, not only from God, but a ransom which consists of God himself, and has such an illustrious payment for his tyranny, a payment for whose sake it would have been right for him to have left us alone altogether.”
በዚህም አላበቃም። ቤዝዎቱ ለአብ ተከፈለ የሚሉትንም ይቃወማል፤ እግዚአብሔር የይስሐቅን መሥዋዕትነት እንኳን አልተቀበለምና።
But if to the Father, I ask first how? For it was not by Him that we were being oppressed; and next, On what principle did the Blood of His Only begotten Son delight the Father, Who would not receive even Isaac, when he was being offered by his Father, but changed the sacrifice, putting a ram in the place of the human victim? (Or. Bas 45.22 (NPNF 207 ገጽ 847)
ከሐዋርያውያን አበው አንዱ የሆነው ሄሬኔዎስም (Ireanaeus) ቤዝዎት በጦርነት ከማሸነፍ ጋር አያይዞ ነው የሚያስረዳው እንጂ ለሰይጣን ከመከፈልና ከማታለል ጋር አያይዞ አይደለም። (Haer. 5.21.3)
በሌላ በኩል ደግሞ ቀሌመንጦስ ዘእስክድርያም (Clement of Alexandria) ጌታችን ወደ ሲኦል ወርዶ ለኀጥአን ወንጌልን እንደ ሰበከና ኀጥአንም ያን ሰምተው ከሲኦል እንደ ዳኑ አስተምሯል።
… following the Lord, preached the Gospel to those in Hades. … He should bring to repentance those belonging to the Hebrews, and the Gentiles; that is, those who had lived in righteousness according to the Law and Philosophy, who had ended life not perfectly, but sinfully. (Strom 6.6) ANF 102 ገጽ 1044-45።
እንዲህ ዐይነቱን አስተምህሮ ቅዱስ አውግስጢኖስ (Augustine) ኑ-ፋ-ቄ ይለዋል፤ “another heresy holds that, when Christ descended into hell, those who had not believed came to believe and were all delivered from there. (Haer. 79)
ከቀሌመንጦስ ሌላ እንዲህ ዐይነት አስተሳሰብ የነበረው አርጌንስ ብቻ ነበር። ይህን አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያንም በኋላ አውግዛዋለች።