Ethiopian Lecturers Voice @euasas Channel on Telegram

Ethiopian Lecturers Voice

@euasas


Ethiopian Lecturers Voice (English)

Are you interested in staying updated with the latest news and insights from Ethiopian lecturers? Look no further than the 'Ethiopian Lecturers Voice' Telegram channel! This channel, with the username @euasas, is dedicated to providing a platform for Ethiopian lecturers to share their thoughts, research, and experiences with a wider audience

The 'Ethiopian Lecturers Voice' channel serves as a hub for intellectual discussions, debates, and collaborations among lecturers in Ethiopia. Whether you are an academician, student, or simply curious about the educational landscape in Ethiopia, this channel offers a unique perspective and valuable information

Who is it? The 'Ethiopian Lecturers Voice' channel is created by a group of passionate Ethiopian lecturers who believe in the power of knowledge sharing and community building. They are committed to promoting academic excellence, critical thinking, and diversity of thought within the Ethiopian educational system

What is it? It is a platform where Ethiopian lecturers can voice their opinions, share their research findings, and engage in meaningful discussions with like-minded individuals. From lectures and tutorials to research papers and conference announcements, this channel covers a wide range of topics related to academia and higher education in Ethiopia

Join the 'Ethiopian Lecturers Voice' Telegram channel today and be part of a vibrant community of intellectuals, scholars, and learners. Stay informed, educated, and inspired by the voices of Ethiopian lecturers who are shaping the future of education in Ethiopia and beyond.

Ethiopian Lecturers Voice

06 Dec, 08:51


ከብልፅግና ፓርቲ እንዲህ የህዝብን ስቃይ የሚረዱ እና የሚያስረዱ ቢኖሩ ሀገራችን ሰላም ነበረች። የመንግስት ሰራተኛው ትክክለኛ ክፍያ ቢከፈላቸው ሀገራችን የት በደረሰች።



@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

28 Nov, 15:58


1.ለአህመድ ሽቧር 831 ለአጠናው
2. ለሙት መኩሪያው ሀይሌ ሲ ሰ ኮ
3. የት/ት ቀለም በመስኮት ላለፈባቸው እና ለፊርማ ለተቀመጡ ለተገዘፉ ሚ/ር ም/ቤቶች ደረሰ

Ethiopian Lecturers Voice

28 Nov, 09:08


የት ደረሰ ?
👂🏾

Ethiopian Lecturers Voice

06 Nov, 02:27


ወዴት ???ወዴት???

በደሳለኝ እና በመሰለኝ የሚመራው


በቁም መቃብር ውስጥ የገባው ኢመማ በመንፈስ ፣ በደሳለኝ እና በመሰለኝ የሚጎርፈው ወራጅ ውሃ ምንድን ነው የፃፈው?

1. የበረሃ አበል ብሎ የፃፈው 46ቱንም ዩኒቨርሲቲዎች አካታች ነው ወይ?

በ2014 ዓ ም የ3ቱ ዩኒቨርስቲዎች ጥያቄ መሆኑን እናውቃለን?

የብዙሃን ዩኒቨርስቲዎች መ/ራን አድረው የከረሙት የጋራ የሚያደርጉ  ጥያቄዎቻችንስ ምን ምላሽ ተሰጥቷቸው ነው ተራ ነገር የቀደመው?

2.ጥር 16/2015 ጠ/ሚ/ር ከ3ተኛ ወገን ነፃ የሆነ ለመ/ራን መኖሪያ ሠፈር ቦታ የሚሆንና
ለተነሺው አርሶ አደር የካሳ ተመን መንግስት
ሸፍኖ እንዲያስረክብ ዮሐንስ ባንቴ የአጥኚ ቡድን ሰብሰቢ አርጎ የተወከለው የቁም ሀውልት
ምን ውጤት አመጣ?

እናንተ አስመሳይ መ/ራን ወኪል ባይ ባንዳዎች አፈፃፀሙን ገመገማችሁ ተጨባጩን ውጤት ወከለን ለምትሉት መ//ራን አሳወቃችሁ?ዘላቂ መፍትሔስ ----????

3. የቱ መቅደም እንዳለበት እንኳን በልኩ ያላወቀ መም/ማ ተብሎ ስም መሰጠቱ ይነረንረናል።

እናንተ የፎቶ ሾፕ ንጉሶች የመ/ራን ድምፅ ነን ባዮች እና እነኚያዎቹ መነሻና--መዳረሻ የማታውቁ
የቱ ነው የሚቀድመው--??????
?????

አለምን በእጅጉ እያነጋገረ ያለ ትኩስና ወቅታዊ የመ/ራን የዕለት ጉርስ እና የአመት ልብስ በማጣት ተማሪ ጋር ተሰልፎ ማዕድ እየተመገበ እያለ እራሱን መቀለብ የሚያስችለውን

#ደመወዝ ጭማሪን ከመጠየቅ አልፎ በስታንዳርድ ካልተከፈለን መ/ራንን ተቃውሞ እንጠራለን ያላልከው ኮስሞቲክስ የመ/ራን ወኪል ተብየዎች ፣

# በ2013 የተጠናውን በመተው የሻይ መግዣ የማይሆን ብር ብሎ የሚ/ሮች ም/ቤት ከአህመድ ሺዴ ተቀብሎ ሲያፀድቅ

# አሜን ተስማምተናል ብለህ የመምህር ድምፅ ሁነህ ተቀብለህ የመጣህ የባንዳዎች ስብስብ ሁሉ አስረግጠን የምነግራችሁ ከግራንድ በካንሰር በሽታ ታሞ አልድን ያለውን የደመወዝ ጭማሪን
በመቃወም ለሶሻል ሚዲያ መግለጫ በጋራ

ተፈራርማችሁ ከመስጠት አልፎ ለመቃወም መ/ራን የትጥቅ ትግል አስታጥቃችሁ ፊት ባለመምራታችሁ ታሪክ ይቅር አይላችሁም።


ጊዜ ለሁሉም

Ethiopian Lecturers Voice

02 Nov, 04:35


ለእነዚያዎች!
እኛ የማንም ጥገኛ አይደለንም
እናንተ ህዳር 26-30/2015 ከአሳያችሁት በላይ
ጥቅምት 22/2017 ታሪክ ሠርተን እናሳያለን ያሉት
ጥቅምት ለመድረስ ስንት ወራት ቀራቸው ይሆን???

Ethiopian Lecturers Voice

26 Oct, 18:39


🔈#የመምህራንድምጽ

" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - ቃላቸውን የሰጡ መምህራን

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

የማህበሩ ስብሰባ ላይ ፦

መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣

ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣

ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣

የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል።

ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።

ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።

" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Ethiopian Lecturers Voice

26 Oct, 15:48


ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ!

@EliasMeseret

Ethiopian Lecturers Voice

23 Oct, 22:30


በዚህ ፔጅ ይህ ሿሿ የሆነ አሳብ መለጠፉ እጅግ በጣም ይደብራል። ሿሿዎች የ30 አመት ስልጣንን የጉልት ገበያ አድርጎ ከተቀመጠው ጉዑዝ ዮሐንስ ባንቴ ጋር ፎቶ መነሳቱ የመ/ራን ደመወዝ ጭማሪ ምላሽ ነውን?
ጥር 30/2012 የተጠየቁትን 18 ጥያቄዎችን ፣ ህዳር 26-30/2015 የስራ አድማ የተደረገባቸውን ጉዳዮችን አዲስ አርጎ እንዲህ ብለው ጠየቁ ተብሎ እዚህ ፔጅ መለጠፍ ታሪካዊ ስህተት ነው። አስረግጠን የምነግራችሁ ዳቦ በማያስገዙ በሿሿ አሮጌ አስተሳሰቦችን የሚያራምድ ተላላኪ መ/ራ ወኪሎች የሉንም። ስብስቦቹ የጊዜዎች ናቸው።
ም/ት ኢመማ መ/ራን ድምፅ አለመሆኑን ያወቀው የአማራ ክልል መ/ማ ፣ መ/ራን ኮሌጆች ከተገነጠሉ 4 አመታትን አስቆጥረዋል።
በሚገርም ሁኔታ የዩኒቨርስቲ መ/ራን ለመጉዳት ተሰልቶ በሲሰኮ፣ በገ/ሚ/ር ተጠንቶ በሙሴዎቹ ፀድቆ ጥቅምት ወር ጀምሮ ይተገበራል የተባለውን የደመወዝ ጭማሪ ተብሎ ስያሜ የተሰጠውን እንደ መ/ራን ወኪልነታቸን የማንቀበለው መሆኑን እናሳውቃለን ብለው መግለጫ ተፈራርመው  አውጥተው በማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ ስላረጉ ዕውቅና ለመስጠት ነው የተለጠፉት?
ስለዚህ የፎቶ ሾፕ ስብስብ ውጤቱ ምንድን ነው? ጊዜ ጀግናነው ጊዜ ይፈታው።

Ethiopian Lecturers Voice

23 Oct, 18:31


የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር /ኢዩመማ/ ፕሬዚዳንቶች የዓለም የመምህራን ቀንን በድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም የኢዩመማ ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ በ37ኛ የኢመማ መደበኛ ምክር ቤት ጉባኤ አዳማ ከተማ ላይ በመሳተፍ በመድረኩ ለተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴታ ለአቶ ኮራ ጡሹኔ በርካታ ጥያቄዎችን አንስቷል። ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ በከፊል
1. በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነት ያሉ አካላት የሚገቡትን ቃል አለመፈጸም
2. የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ግዴታ ቢወጡም እስከ ኮሌጅ ለሚያስተምሩ መምህራን የቤት መስሪያ ቦታ ሲፈቀድ የዩኒቨርሲቲን መምህራንን ያለማካተት
3. ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚከፈለው የደመወዝ፣ የቤት ኪራይ አናሳ መሆን
4.  ለመምህራን በትርፍ ጊዜ የሚሰሯቸው ስራዎች እና የቤት ኪራይ ታክስ መደረግ
5. ለphd ተማሪዎች የሚከፈላቸው የምርምር ክፍያ በቂ አለመሆኑ
6. በስራ ምክኒያት ህይወታቸው ያጡ መምህራን የህይወት ኢንሹራንስ አለመኖር ለምሳሌ የመደወላቡ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራን
7. በሀገራችን ያለው የሰላም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው
8. የትምህርት ጥራትን በተመለከተ
9. የዩኒቨርስቲ መማ ፍልሰት እንዲጠና
10. የትምህርት ተቋሙ ከሲቪል ሰርቨስ እንዲወጣ
11. ለዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው በጀት አነስተኛ መሆን

Ethiopian Lecturers Voice

21 Oct, 18:51


👏

Ethiopian Lecturers Voice

19 Oct, 19:30


አዲሱን ደመወዝ ጭማሪ ለመቃወም ከጥቅምት 22/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ የሚደረገው የስራ ማቆም አድማ በመላ ሀገሪቱ እንዲተገበር የመምህራን ኔትወርክ ቤተሰቦች ገለፁ።

#ሼር
https://www.facebook.com/100059826090948/posts/pfbid0bdGooanDiZaCGiiXtjsdyS5Q6DtHsQBuj9oGn5rAHD74Vn2yyrJnVzEATrqQUPuFl/

Ethiopian Lecturers Voice

18 Oct, 17:04


ሰላም ዉድ የ አሶሳ university መምህራን አርዳታችሁ ያስፈልገኛል አኔ ንግስት የ አሶሳ university መምህርት ምግብ አና ቡና ስለጀምርኩ መታችሁ ጎብኙኝ ሲል አጠይቃለሁ
አድራሻ ሳርበቶች ቶቶ ጎን
Please come and visit us

Ethiopian Lecturers Voice

06 Oct, 20:25


INBOX #2

ተማራዎች ከመግባታቸው በፊት በመምህራን ማህበር በኩል በየጊቢው  ሰብሰብ ብሎ መመካከር ጥሩ ይመስለኛል። ሀሳብ የሚወለደው በመድረክ ወይም በመነጋገር ነው። አንድ ጊዜ ከተጀመረ ግለቱ እየጨመረ ይሄዳል።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የተዘጋብንን የምንከፍትበት ዋናው ቁልፍ አንድ መሆን ነው።
አንድ መሆን ማለት ስርዓቱ  በተለየ መንገድ የተማረውን ማህበረሰብ intentionally ወደሗላ እየጎተተ እና እያዳከመ ሸምተን እንዳንበላ ከገበያ ውጪ እያደረገን መሆኑን መቀበል ነው። ይህን አልቀበልም የሚል ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር Quickly መሬት ላይ ያለውን Review ማድረግ ነው። ከዚህ ውጪ አውቆ የሚያላግጠውን በሌሎቻችን ላይ የደረሰብን ችግርና መሳቀቅ እግዚአብሔር  ይስጥህ ብሎ በመርገም ጥሎ ማለፍ ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በችግራችን ረግጠኞች ከሆንን በሗላ የመፈትሔ አማራጮችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥና ለመተግበር ቆራጥ መሆን ነው። እዚህ ላይ ፍርሃትና መንቀጥቀጥ አያስፈልግም ምክንያቱም ሀሉም በአንድነት የመፍትሔ አማራጮችን ወደመተግበር እንጂ ፊቱን ወደሗላ የሚያዞርና የሚከዳ አይኖርምና።
ተጠየቅ ከመጣም ያው ሀሉም መጠ፞የ፞ቅ ነው ተለይቶ የሚጠ፞የ፞ቅ የለም።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ስርዓቱ ትምህርትን Strategically እየገደለው ነው። ትምህርት ሲሞት ተውልድ ይሞታል። ተውልድ ከሞተ አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ከምናየው እጅግ የከፈፋና እንደዱር አራዊት ሰው የሰውን ስጋ እየበላ ወደመኖር ያድጋል። ይህ ግነት አይደለም አይናችን እያየው ያለ ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
Saintific law ብቻውን ይመራናል ብለን ይኼው ከጉረኗቸው እንደተበተኑ በጎች ተለያይተን ያገኘን ሁሉ በጉረሯችን ላይ ቆመብን።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መፍትሄው በእጃችን ነው። መጠቀምና አለመጠቀም ምርጫው የራሳችን ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እያላዘኑ መኖር ደባሪ ነው!!‼️

Ethiopian Lecturers Voice

06 Oct, 20:23


Inbox

መምህር  ጠንካራ አንድነት የለውም  ከገቢዎች እና ጉምሩክ መማር ይጠበቅብናል  መንንግስት ጨመርኩ ካለው ውጭ የቤት 18500 በር፣ የሙያ 8000 ብር ፣ የመሸጋገሪያ 3000 ብር  እና የነዳጅ እና የስልክ የሚል 4000ብር እንደምረው አዳሜ መምህር  ደሞዝ እንዳይመስልህ ከዲፖሎማ እስከ  ዲግሪ ደሞዙ ብቻ ከ17000_35000 ከነሐሴ ወር 2016 ጀምሮ  በድምሩ ትንሹ የዲፖሎማ ደሞዝ 17,000 ብር ሲሆን ዲግሪው ደግሞ እስከ 60,000 ብር ድረስ በየደረጃው  እንደሚከፈላቸው ደብዳቤ ደርሷቸዋል  ወይኔ የዩኒቨርስቲ አስተማሪ  ለምን ሰቃይ ጎበዝ ሆንን የሚያሰኝ ነው  ፕሮፌሰር ያልተጣራ 20,000 ብር   ያገኛሉ   መምህሩን  ያንተ ሙህርነት ጉብዝና ምን ያደርጋል ኑሯችሁ ከእኛ በ300% ያነሰ  ማለት ጀምረዋል ጎበዝ ሆነህ አንተ አንች የዩኒቨረስቲ አስተማሪ ከሆናችሁት እኛ ዲግሪና ዲፕሎማ የገዛነው እንሻላለን  ሲሉ ተሳልቀዋል ባስቸኳይ የስራ ማቆም አድማ ካልተጠራ ..
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

05 Oct, 18:03


ምን ታስባላችሁ ?
1. https://www.facebook.com/HakimEthio
2. https://www.facebook.com/Teachersnetwork1
3. https://www.facebook.com/profile.php?id=100077487704652

እነዚህ በጣም ብዙ ተከታይ ያልቸው የሰራተኞች ድምጽ ናቸው። በቴሌግራም እኛ ከምናደርገው ትግል የእነሱ አንድ ፖስት ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ ይሆናል። ምናልባት ሌሎች ብዙ ተከታይ ያላቸው የሰራተኞች ገጾችን ማስተባበር እና አጀንዳወች በጋራ ተቀርጸው የመብት ትግል ቢደረግ ለዉጥ ይመጣል።

ምን ታስባላችሁ?
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

30 Sep, 08:46


“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”

ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
!

አስተማሪን? በጫማው ትለየዋለሁ እኮ። አንድን ጫማ ለብዙ ዓመታት ነው የምንጫማው። ብዙ ሲረገጥ የአቀማመጥ ሚዛኑን ያጣል።“እኛ ግቢ ብትመጣ ትደነግጣለህ። የብዙ መመህር ጫማ ተንሻፎ ነው ያለው። ድምጽ አውጥቶ ‘ጣሉኝ!’ ነው እያለ ያለው። እንዴት ትጥለዋለህ? ግማሽ ደመወዝህ ደህና ጫማ እንደማይገዛ እያወቅክ? “ታች ግቢ ለምሳሌ ኮመን ኮርስ የምንሰጣቸው የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች አሉ። 5 ዓመት ገደማ ዩኒቨርስቲ ይቆያሉ። እና ሸፋፋዋን ጫማህን ያውቋታል። ጃኬትህን ያውቋታል። ገደድ- ሸፈፍ እያልክ ስትመጣ ከርቀት ይለዩሃል። በጫማህ ባይለዩህ፣ በጃኬትህ ይለዩሃል። ደግሞ ይቀልዱብሃል። ባይቀልዱብህም እንደሚቀልዱብህ ታስባለህ። በአጠገባቸው ስታልፍ ትሸማቀቃለህ። ይህ ነገር ስሜትህን ይጎዳዋል።

“አስበው! አንድ የኢንጂነሪንግ ተማሪ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በኬሚካልም ይሁን በመካኒካል ኢንዱስትሪ እስኪመረቅ ድረስ አንተ መምህሩ ጫማ መቀየር አለመቻልህ...አያምም?
“በአጭሩ ቅድም ‘ኑሯችን ጫማችንን ነው የሚመስለው’ ያልኩህ ለዚያ ነው።”

አንዳንድ የሰቆቃ እና የሰቀቀን ታሪኮች

ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሠሩ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ መምህራን ለቅሷቸው የእናቱን ሞት ያረዱት ሰው ያህል ነው። “በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተነሳ እየቀነጨርን ነው” ብለው ያማርራሉ።

ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ ኑሮ በአምስት መምህራን ታሪክ ውስጥ ጨምቆ ማስቀመጡ የተሻለ መንገድ ሆኖ አግኝቶታል። ‘ዕጩ ዶክተሮቹ’ የሰቆቃ ሕይወታቸው በቤተሰባቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ሐፍረት ለማስቀረት፣ በተማሪዎቻቸውም ላይ አሉታዊ ስሜት ለማስወገድ ማንነታቸው በፊደል ተወክሏል።

“ቀንም ማታም ቀጭን ሽሮ ነው የምበላው”

“ልጆቼንና ባለቤቴን ገጠር ትቻቸው ነው የመጣሁት።አዲስ አበባ ባመጣቸው የት ያድራሉ? ምንስ ይበላሉ? እኔ ራሴ የማድረው ዶርም ውስጥ ለአራት ተዳብዬ ነው። በስተርጅና እንዲህ እኖራለሁ አላልኩም ነበር። ለዚህ 1500 ብር እከፍላለሁ። ሦስት ልጆች አሉኝ። በየወሩ ለቤተሰብ 7ሺህ እልክላቸዋለሁ። እጄ ላይ ስንት ቀረ? 1ሺህ ቀረችኝ። አንድ ሰው በ1ሺህ ብር አንድ ወር እንዴት ነፍሱን ያቆያል? ሌላም ወጪ አለብኝ። የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ። 2ሺህ ብር ነው። ከየት አምጥቼ ልክፈል? ከዚያም ከዚህም ተበዳድሬ እከፍላለሁ። የሚያቃዠኝ ልጆቼ ቢታመሙስ የሚለው ነው። እንቅልፌን አጣለሁ። እግዜር ረድቶን እስከዛሬ አልታመሙም። በቃ በየወሩ ጸሎቴ ልጆቼ እንዳይታመሙ ብቻ ነው። ምን ይውጠኛል? በምኔ አሳክማቸዋለሁ?
አንዳንዴ ችግር ሲጠናብኝ ወንድሜ አለ፤ በወር በወር እንዲደጉመኝ እለምነዋለሁ። አይጨክንብኝም። በወር 4ሺህ ብር አካባቢ ይቆርጥልኛል። እሱ ባይኖር ምን ይውጠኛል? ይህን ሁሉ ዓመት ተምሬ ራሴን አለመቻሌ ግን የእግር እሳት ይሆንብኛል።

ስለ ልጆቼ ልንገርህ?

የአስተማሪ ልጅ መዝናናት አያውቅም። ልብስ አይቀይርም። ልጆቼ ልብሳቸው ሰውነታቸው ላይ ያልቃል። ባደጉ ቁጥር እደነግጣለሁ። ሱሪው ያጥራቸዋላ። ልብስ መግዛት ሊኖርብኝ ነው። አባት ልጁ ሲያድግ መደንገጥ አለበት? እኔ ግን እደነግጣለሁ። ምንም ማድረግ አልችልም። ከየት አምጥቼ ነው ልብስ የምገዛላቸው? አስተማሪ ነኝ። ሙስና አልሠራ። እዚህ አገር ሙስና ካልሠራህ መኖር ትችላለህ እንዴ? ተወኝ በናትህ። ፒኤችዲ በአብዛኛው 4 ዓመት ነው የሚወስደው። በ6 ዓመት ያልጨረሱ አሉ። አእምሯቸው የተነካ አሉ። ‘ያበዱ’ መአት ልጆች አውቃለሁ። እንዴት ትማራለህ በዚህ ጭንቅ? ከአራት ኪሎ - 6ኪሎ ዞር ዞር በል። ብቻውን የሚያወራ ሰው አታጣም። የፒኤችዲ ተማሪ ነው።”

“ጓደኞቼን ካየሁ መንገድ እቀይራለሁ”

“ስለ ጓደኞቼ ልንገርህ? ድሮ አብረውኝ የተማሩ ጓደኞቼ ብዙዎቹ ባንክ ይሠራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ናቸው። ይናፍቁኛል - እናፍቃቸዋለሁ። ግን በፍጹም አላገኛቸውም። ከርቀት ካየኋቸው ራሱ መንገድ እቀይራለሁ። ለምን በለኛ? ልጋብዝህ ሲሉኝ ይሰማኛል። ግብዣውን ብፈልገውም ወደ ኋላ መቅረቴ ያንገበግበኛል። አሁን አንድ ጓደኛዬ አለ። የውጭ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሠራው። 2500 ዶላር ገደማ ያገኛል። ኑሮው ያስቀናኛል። ከአንዳንዶቹ ጋር መንገድ ካገናኘን፣ ‘ተው እንጂ! አትራቀን፤ እናግዝሃለን’ ይሉኛል። እሸማቀቃለሁ። ‘ምነው አሞህ ነበር እንዴ?’ ይሉኛል። ‘ራስህንማ እንደዚህ አትጣል’ ይሉኛል። ብዙ ሰው ጀዝቦ ቀርቷል እኮ። እኔ እግዜር ረድቶኝ እጅ አልሰጥ ብዬ እንጂ ብዙ ልጆች እኮ አእምሯቸው ተነክቶ መንገድ ወድቀዋል። ቀልዴን መሰለህ? ይሄ ይገርምሃል እንዴ? ፍቺ የፈጸሙ አሉ። ትዳራቸው የፈረሰ አውቃለሁ፤ በጭንቅ። ሱስ ውስጥ የወደቁ አሉ። ያበደ አስተማሪ 2 እና 3 በየዩኒቨርሰቲው አታጣም። ቀልዴን መሰለህ? እኔ ራሴ አንዳንዴ እያበድኩ ይመስለኛል። ቤተሰቤ ይደውላሉ። ባለቤቴ በጣም ስትቸገር ትደውላለች። ‘እስከመቼ ነው በዚህ ድህነት የምታኖረን? ለምንድን ነው ትምህርቱን ትተህ ሥራ የማትፈልግ?’ ትለኛለች። እኔም ነገሩን አስቤበት ነበር። ነገር ግን በማስተማር ላይ ነው ዕድሜዬን የፈጀሁት። እንዴት ነው አሁን ድንገት ልምድ ሳይኖረኝ ኤንጂኦ እና ባንክ የሚቀጥረኝ? ማን አስተማሪን ይቀጥራል ደግሞ? የመረጥነው መንገድ በጣም ጎዳን - ወንድሜ። ከዜሮ መነሳት ይከብዳል።
እንደነገርኩህ ጓደኞቼ አሉ። በጥሩ ጊዜ ኤንጂኦ የገቡ። በትምህርት ብዙም ያልገፉ። ጂፕላስ- 2 ቤት የገነቡ። እኔ በዚህ ዕድሜዬ ፒኤችዲ እየሠራሁ ዶርም ውስጥ ከ4 ሰው ጋር ተዳብዬ እኖራለሁ።

“እናቴ ደውላ አለቀሰች”
“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”
“ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ“ባለቤቴ ናት ሱሪ የገዛችልኝ”
“የድሃ ድሃ ነን”

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ - አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም - አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

“አእምሮዬ ልክ አይደለም”
“የፒኤችዲ ትምህርቱ ያን ያህል ከባድ አይደለም። ግን ቀልባችን ተበተነ። በትምህርቴ ላይ ማተኮር ተቸገርኩ። በዚህ የተነሳ መቀጠል አልቻልኩም።
እንዴት አይሰማኝም ታዲያ?”
#ቢቢሲ #BBC

@EUASAS
https://t.me/EUASAs/1576 [Special thanks to excellent members. https://t.me/EUASAs/1576]

Don't afraid to share it!
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpv2k0d714ro

Ethiopian Lecturers Voice

29 Sep, 12:50


ከ22 ብር ወደ 100 ብር - የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል። "ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡ የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡


@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

24 Sep, 11:58


MoE? Where are you?

Ethiopian Lecturers Voice

24 Sep, 11:58


MoE? Where are you?

Ethiopian Lecturers Voice

20 Sep, 14:24


መምህርነት የሙያዎች ሁሉ አባት!!
****
መምህራን ትውልዱን ከአለማወቅ ወደ ማወቅ ከጨለማ ወደ ብርሐን የሚመሩ የእውቀት አባቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ  መምህራን የአለም የእውቀት ብርሐን ሲባሉ እናዳምጣለን!! እውነትም መምህራን የአለም የእውቀት ብርሐን ናቸው፡፡
ዛሬ በሳይንስና ቴክኖሎጅ የበለጸጉት ሀገራት የእድገት ሚስጢር ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው መስራታቸው እንደሆነ ታወቆ ያደረ ሀቅ ነው፡፡ ትምህርት ማለት የሰው ሀብትን ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማልማት ነው፡፡ በሰው ሀብት ልማት ሂደቱ ዋናው ተዋናይ ደግሞ መምህራን ናቸው፡፡  መምህራን  በትምህርት ስርዓት ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ቁልፍ ተዋናዮች ናቸው፡፡ የተማሪዎችን ትምህርት እና እድገት ላይ በተለያዩ  መንገዶች  ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡ በዓለምም ሆነ በአገራችን ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱ ተመራማሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣….በትምህርት ዓለም ያለፉ በሙሉ በመምህራን ተኮትኩተው ያደጉና የተመከሩ ሳይንስን ከተግባር ጋር አዋህደው እንዲያውቁ የታገዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም መምህርነት የተከበረና የተወደደ ሙያ እንደመሆኑ መጠን ለሙያዉና ለሙያ አባቶች ክብርና ድጋፍ ማድረግ የሁሉም አካል እንዲሆን ሁላችንም መስራት ይጠይቀናል፡፡ ምክንያቱም፡-
* መምህራን የመማር አመቻቾች ናቸው፡፡ መምህራን አሳታፊ እና interactive ትምህርቶችን በመፍጠር የተማሪዎችን  የመማር ሂደት የሚመሩ ናቸው። መምህራን ተማሪዎች ውስብስብ ፅንሰ ሀሳቦችን እንዲረዱ እና ሂሳዊ አስተሳሰብን(Critical thinking)እንዲያዳብሩ  ያበረታቷቸዋል፤ ይረዷቸዋል።
* መምህራን አማካሪዎች እና አርአያዎች ናቸው፡- መምህራን እንደ አማካሪ ሆነው ለተማሪዎች ድጋፍ ያደርጋሉ ፡፡ ለተማሪዎች ማበረታቻ ይሰጣሉ፡፡ተማሪዎች ሊከተሏቸው የሚገቧቸውን  ባህሪያትን፣ አመለካከቶችን እና እሴቶችን ሞዴል ሆነው ያሳያሉ ይመክራሉ፡፡
* መምህራን የሂደት ገምጋሚዎች ናቸው፡፡ መምህራን የተማሪውን ግንዛቤ በግምገማ ይለያሉ፤ በዚህም ተማሪዎች እንዲሻሻሉ የሚያግዝ አስተያየት ይሰጣሉ። መምህራን የግለሰቦችን ፍላጎቶች ለማሟላት ለውጥ ተኮር መመሪያዎችን ይከተላሉ፡፡ በሂደቱ የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ይቀርፋሉ፡፡ ሁልጊዜም ለለውጥ ይዘጋጃሉ፡፡
* መምህራን የስርዓተ ትምህርት ዲዛይነሮች ናቸው፡፡ መምህራን ብዙውን ጊዜ ሥርዓተ ትምህርቱን በመንደፍ፣ ቁሳቁሶችን በመምረጥ እና የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይዘቶችን መርጠው ለተማሪዎች በሚመጥን መንገድ ያቀርባሉ
*መምህራን ለተማሪዎቻቸው ተሟጋቾች ናቸው፡፡ መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት በትምህርታዊም ሆነ በግል ለማሟላት ያለእረፍት ይሰራሉ። ሁሉም ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድና አካባቢ ለመፍጠር ይተጋሉ። አማራጭ መፍትሔዎችንም ይፈልጋሉ፡፡
*መምህራን ለተማሪዎች መማር ተባባሪዎች ናቸው፡፡ መምህራን የትምህርት ስራን ለማጎልበት ከስራ ባልደረቦቻቸው ፣ ከወላጆች እና ማህበረሰቡ ጋር በቅርበት ይሰራሉ። ይህም በመሆኑ ትምህርት ቤቱን ከማህበረሰቡ ጋር በማቆራኘት ለመማር ማስተማሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
*መምህራን የዕድሜ ልክ ተማሪዎች ናቸው፡፡ መምህራን ችሎታቸውን እና እውቀታቸውን ያለማቋረጥ ለማዘመን አንባቢዎች ናቸው፡፡ ይህ ባህሪያቸው ተማሪዎቻቸው  ከክፍል ትምህርት በዘለለ  ለትምህርት ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጡ ያነሳሳቸዋል።
በአጠቃላይ መምህራን የትምህርትን ገጽታ በመቅረጽ ረገድ አጋዥ ናቸው። የመምህራን  ተጽእኖ ከአካዳሚክ ስኬት በላይ የተማሪዎችን  የግል እድገት በማጎልበት እና ተማሪዎችን ለወደፊት ፈተናዎች በማዘጋጀት ረገድ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ለትውልዱ መማር ያላቸውን ሚና ተረድተን ሁላችንም መምህራንን ማክበርና መንከባከብ ይገባናል፡፡

                                
ለመምህራን ክብር እንስጥ!!
AEB
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

19 Sep, 07:40


https://addisfortune.news/wage-reform-fails-to-soothe-the-civil-service/

Ethiopian Lecturers Voice

13 Sep, 18:00


ከምሁራዊ ፁሑፍና ሀሳብ ወርቅና ሰም በማለያየት  እየኖርክ ያለኸው   መ/ር    የማይታማን ሰበር  ዜና  ስሙ
የንግድ ባንክ ታይቶና ተሰምቶ  የማይታወቅ  ከዚህ ፊት  ሐምሌ 1/2011 ቀጥሎ  በ2013 ከተደረገው  ደመወዝ ጭማሪ አሁን ላይ በአይነትና በመጠን ለየት ባለ መልኩ  ለ3ኛ  ጊዜያት  ተሰርቶ በቦርድ   ፅድቆ   ለዩኒቨርስቲ መ/ራን ጠል አህመድ ሸዴ ቀርቧለት   የገነነ   ነው ይስተካከል በማለት ክርክር ላይ ይገኛሉ ።

ይህ ጭማሪ በተደጋጋሚ አንዴም ለእኛው ሳይደረግ የተለቀቀው ዋናው ም/ት-

1. ከሙት የምሁር  ካንሰር ከሆነው ከሲቪል  ሰርቢስ ኮሚሽን ተገንጥለው ተቋማቸውን በቦርድ ስለተዳደሩ

2. ሠራተኛቹ የተናበበ በጥቅማቸው ላይ አተኩረው በጋራ በመታገላቸው

3. እኛ በፍራቻ ባህር ዋና ውስጥ በመሆናችን እየተደቆስን እንገኛለን ።

4. መ/ራን ከአንድነት ይልቅ መለያየትን መሠረት በማድረግ ፣  በሰፈር፣ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በእምነት  የተከፋፈለ በመሆኑ የምድርን የኑሮ ምፃዕትና ሰቆቃ እየኖረ ይገኛል።

አይን የሚያየውን፣ ልቦና የሚያስበውን ፣ ህሊና የሚናፍቀውን ሳያሟላ ኑሮውን እየኖረ ይገኛል።

መፍትሔው


ደመወዝን ማስጨመር ብቻ ዘላቂ መፍትሔ ሳይሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥገኝነት በመውጣት የመ/ራን ኮሚሽን ማቋቋም  መቻል ነው።

Ethiopian Lecturers Voice

10 Sep, 07:27


Our 2017, please .......

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 20:21


https://t.me/EUASAs/1659

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 19:53


ይህ የደሞዝ አማራጭ በሚንስትሮች ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል። ያኛውን አንቀበለዉም።

ይሄን ለመጠየቅ አትፍራ ! ሁሉም ካድሬ ይህን ደሞዝ ማግኘት ይፈልጋል። የሰራተኛዉን ትግል ይደግፋል። ይህ ደሞዝ እስኬል በሁሉም ዘንድ መስረጽ ይኖርበታል። ሼር

ሃሳብ ስጡበት

https://t.me/boost/EUASAs
https://t.me/boost/EUASAs
https://t.me/boost/EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 19:52


Live stream finished (1 hour)

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 17:58


Open Meeting, አወያይ ሆኖ መምራት ትችላላችሁ። መምህር የመምራት አቅም በማንኛዉም ሁኔታ አለው። inbox @MessageELAbot to lead

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 17:56


Live stream started

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 17:55


ሀ/ ተጨመረ ሳይሆን ልብና ኩላሊትን ሳይማር እውር ዘርፎ ወሰደ ተብሎ በደመወዝ ጭማሪ ለጭማሪ ለተተረከልን መሆን የሚገባው
1. አካታች ስራ ማቆም
2. ዩኒቨርስቲ አካ/ስተፍና አስተዳደር ሠራተኛች
3.. ኮሌጆችና ቴ/ሙያዎች
4. ሁሉም መ/ራን በየደረጃው ያሉት
5. ሁሉም የሀገሪቱ መንግስት ሠራተኛች
6. ሁሉም የቀን ውዝ አደሮች
7. ሁሉም ተጎጂ የማ/ሰብ ክፍሎች
8. ፀጥታ ክፍሎች
9. በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች
10. ሀኪሞች
11. መሀንዲሶች
12. የተለያዪ ያልተጠቀሱ አጋር አካላቶች
ለ. በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያጯጩኹ
1. ፌስ ቡክ --- በዋናነት
2. እውነት አንፀባራቂ ጋዜጠኛች
3. ዩቱበሮች
4. ቲዊተሮች
5. ኢንስታግራሞች
6. ቴክባ ወዘተ ያለፍራቻ መጠቀም ለሴኮንድ የለም ወደኋላ

ሐ. ከእኛ ምን ይጠበቃል??? እዚያ ያለኸው

የተደራጀ ና ሳይንሳዊ መረጃ ማዘጋጀት

የስርዐቱን ወራዳነትና ዝቅጠት በምሁራዊ ቋንቋ ተንትነህ አሳየው
ከንቱ ሲ ሰ ኮ አወራርደው
እኛው ለእኛው የሚመጥን መምህራን ኮሚሽን(ድርጅት እናቋቁማለን የሚለው አስነፍጠህ ንገረው ፈፅመው

መ/ራን ዝቅ አድርጎ ለወራት መኖር የሚችል ፖለቲከኛና መሪ መኖር እንደማይችል ጥሬ ሳይንሱን አስረግጠህ አሳየው።

ሀሳብ ሲሰጥ ማሽሞንሞን እንደማያስፈልግ ተረድተን የዕውቅት ውጊያ በግልፅ ማሳየት

በድሮ ጊዜ እነ መለስ ሰባት ሆነው ያም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሆነው ጨቋኝ ስርዓትን ገርስሰው ለመጣል ተነስተው ደምስሶ እንደጣሉ እኛም የዚ ዘመን የታሪክ ሻጮጭ ከ-ዚያ-ከኛ እያለን በፉራፉሬ መጫወት የጀርባ አጥንት

ከመላላጥ በመውጣት ለእኛ፣ ለእናቴ፣ ለእህቴ፣ ለሚስቴ፣ ለልጄ ወዘተ በማለት በእውነት ቁመህ ለእውነት ለመታገል ተነስ!

አንተው እራስን ችለህ ለመታገል ቀበቶህን አጥብቅ ፣ዝቅ የማይል ሱሪንም ልበስ። ተነስ ሁሉም ወረቀትህንና ደረጃህን ስምህን አስከበር።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ እራሱን ችሎ ያልታገለ የአስመሳይ የምሁር ካንሰር ነገ ታግለን ሌቦችን አስወግደን እናገኛዋለን ያኔ ስሙን እንጠይቃቸዋለን።
ታገዮች ተነሱ ለነገ በሚል ሰበበ አስባብ የምታደርግ ዜጎች ካላችሁ በጋራ የቆምነው ሙያችን ሰይፍ ሆኖ ይብላን።
የ50 ዪኒቨርስቲ መ/ራን ተነሱ መብታችን በክንዳችን እናስከብር።

ሲፒኦ የግል ኮሌጅ ለተማሩ የሚገዛ ምሁር አይኖርም።

10,717

subscribers

301

photos

14

videos