National ID Program - Ethiopia @idethiopia Channel on Telegram

National ID Program - Ethiopia

@idethiopia


Identity is the new collateral!
መታወቅ ለመተማመን።
ለማንኛውም ጥያቄ:- id.et/help

National ID Program - Ethiopia (English)

Introducing the National ID Program - Ethiopia Telegram channel! Are you curious about how identity is evolving and becoming the new collateral in our digital world? Look no further than this channel, where you can stay up to date on all the latest developments in Ethiopia's national identification program. From news and updates to informative articles and resources, the 'idethiopia' channel is your go-to source for all things related to identity. Whether you're a citizen of Ethiopia or simply interested in the intersection of identity and technology, this channel has something for everyone. Join us today and be part of the conversation! Remember, your identity is valuable - learn more at id.et/help.

National ID Program - Ethiopia

15 Feb, 14:45


“ፋይዳ ታማኝነትን የሚዘረጋ፣ የማንነት ማረጋገጫ፣ የተቋማትን ስራ የሚያቀናጅ፣ በግለሰቦች ደረጃም የራስን መብት የሚያስጠብቅ ነው።” ራሔል አብርሀም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ

ባሳለፍነው ሳምንት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት የመጀመሪያ የሆነው የፋይዳ ፓናል ውይይት ተካሒዷል። በውይይቱም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በፕሮግራሙ ሀላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
የፓናል ውይይቱን በዚህ ሊንክ https://youtu.be/iyXDQp7-2lc?si=5b5KFAJgTKD9SEoZ ገብተው ይመልክቱ።

ምስል ፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

National ID Program - Ethiopia

13 Feb, 09:25


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን አጠቃሎ የያዘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ!

ነዋሪዎች የዘመነ እና ቀላል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ በቀጣይም ከፋይዳ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎትን እንዲያገኙ ለማስችል ታልሞ ነው።

መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp እንዲሁም ከአፕ ስቶር https://apps.apple.com/app/fayda-id/id6740314990 ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ፣ የፋይዳ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳ #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

13 Feb, 05:59


የውይይት ጥሪ

አርብ የካቲት 7 ቀን ከቀኑ 8:30 - 10:30 ሰዓት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ ደንብ ዙሪያ የሚደረገው የኦንላይን ውይይት መድረክ ላይ በዚህ ሊንክ https://zoom.us/j/97756301001?pwd=OTaPJHjNcT0Oo2aUILhC0ZDpGLgGP5.1 በመግባት ይሳተፉ።

#ፋይዳ #ፋይዳመታወቂያ #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

10 Feb, 14:49


ፋይዳ ከየት ወዴት?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እሳቤ ምንድነው? እንዴትስ ተጀመረ? እንዲሁም በፕሮጀክቱ አተገባበር ዙሪያ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም ነገ ማክሰኞ ምሽት 3፡00 ላይ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ይጠብቁን።

National ID Program - Ethiopia

08 Feb, 13:37


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ይህም በሀገር ውስጥ የሚገኙ የውጪ ሀገር ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያጠቃልል ቢሆንም ፣ በአካል አገር ውስጥ የሌሉ የውጭ ዜጎች ሆነ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደ unite.et ያሉ አማራጮችን ተጠቅመው ፋይዳን ሳይጠቀሙ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተፈቀደ መሆኑን እንገልጻለን።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #ፋይዳ #financialinclusion

National ID Program - Ethiopia

05 Feb, 10:38


Call for Bid!

The National ID Program is looking for a service provider who provides event management & documentation services. Do you think you are the right fit?

Use this link to apply: https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00336960

#DigitalID #Fayda #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ

National ID Program - Ethiopia

03 Feb, 15:31


ለፋይዳ መመዝገብ መብት ወይስ.....?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አኳያ ምን ይላል?

#ፋይዳ #ፋይዳምዝገባ #DigitalID #Fayda

National ID Program - Ethiopia

29 Jan, 16:40


በፋይዳ ምዝገባ ወቅት የመረጃ ስህተት ካጋጠሞት በዚህ ቅደም ተከተል መሰረት ማስተካከል ይችላሉ።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

27 Jan, 08:26


"በሀገሪቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ከማምጣት ፣ ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ እንዲሁም ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ትራንፎርሜሽን ለምታደርገው ጉዞ ላይ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትልቅ ፋይዳ አለው። እስካሁን ድረስ 11.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት የሆኑ ሲሆን በቀጣይም በክልል ከተማ እና አስተዳደር ሁሉም ነዋሪዎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንዲመዘገቡ የክልል እና ፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ልዩ ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ለማሳሰብ እወዳለው።"

ክቡር ም/ጠ/ሚኒስቴር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዲጂታል ኢትዮጵያ "የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ" የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ከተናገሩት

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #ዲጂታልኢትዮዽያ

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

24 Jan, 13:32


ፋይዳ መታወቂያዎን በምን መልኩ መያዝ ይሻሉ?

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

21 Jan, 07:19


ፋይዳን የት ልመዝገብ ብለው እያሰቡ ነው?

በአቅራቢያ የሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ id.gov.et/locations ላይ በማየት ሔደው ይመዝገቡ።

#ፋይዳ #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

17 Jan, 10:24


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ በዓል እና ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

መታወቅ ለመተማመን!
ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም

#ፋይዳ #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

14 Jan, 14:47


የፋይዳን ካርድ ከፈለጉ ፤ ካሉ የማዘዣ አማራጮች ውስጥ አንዱ በ "ቴሌብር" በኩል መሆኑን ያውቃሉ?

የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሐዋሳ፣ አዳማና ወላይታ ሶዶ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ላይ ‘’NID (Fayda) Printing’’ በሚለው መተግበሪያ ተጠቅመው የካርድ ህትመትዎን በቀላሉ ይዘዙ!

እንደምርጫዎ በ6 የሥራ ሰዓታት፣ በ2 ቀናት ወይም በ7 ቀናት ውስጥ በመረጡት የመረከቢያ ቀንና ቦታ ይረከቡ፡፡

🔗 በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/40efSUZ

National ID Program - Ethiopia

13 Jan, 14:40


ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ የሚያገኟቸው የቁጥር አይነቶች…

#ፋይዳ #መታወቅ #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

09 Jan, 08:00


Call for Proposals

The National ID Program, is seeking for eligible proposers for:

1️⃣ Lot I: Design, supply, installation, operation and maintenance service, network, compute, storage and security infrastructure
2️⃣ Lot II: Data center facility infrastructure design, deployment and commission

Get details: https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00331841

#DigitalID #Fayda #ፋይዳለኢትዮጵያ

National ID Program - Ethiopia

06 Jan, 07:00


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መታወቅ ለመተማመን!
ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #Fayda #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

03 Jan, 13:12


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ነጻ ነው!

ለፋይዳ ተመዝግበው ልዩ ቁጥር እስከሚደርስዎ ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግዎትም። መታወቂያዎን በዲጂታል መልኩ ከቴሌብር እንዲሁም ከድረገጽ በወረቀት አትመው መያዝ ይችላሉ።

ነገር ግን ፋይዳ መታወቂያዬ በካርድ መልክ መያዝ ያስፈልገኛል ካሉ id.gov.et/card ላይ በህትመት አጋሮች ኢትዮቴሌኮም እና ኢትዮፖስት አማራጮች በማዘዝ ክፍያዎትን አጠናቀው መውሰድ ይችላሉ።

በኤሌክትሮኒክም ሆነ በካርድ መልክ የሚያዙ የፋይዳ መታወቂያ አይነቶች በህግ ፊት እኩል ተቀባይነት አላቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

01 Jan, 07:11


ያስተውሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከዛሬ ታህሳስ 23 , 2017 ዓ.ም (Jan 1st 2025) ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ሆኗል።

በፋይዳ ይታወቁ!

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

31 Dec, 13:16


የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ አካላት የፋይዳ ምዝገባ እንዲያደርጉ እና በዘርፉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ “የተማሪዎችን የትምህርት መረጃ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተሳሰረ እና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ይህም የተዛባ የትምህርት መረጃን ከመቀነስ ፣ ከድግግሞሽ የፀዳ አሰራር እንዲኖር እና የተማሪን መረጃ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ "ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በጋራ መስራት ለማህበረሰቡ አቅም ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለስራው ስኬታማነት ጉልበት እንደሚሆን ተናግረው በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የፋይዳ መታወቂያ የተማሪዎች ቅበላ የምዘገባ ቅድመ ሁኔታ ይሆናል" ብለዋል።

የአ.አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስራዉን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ለግል ትምህርት ተቋማት በቀጣይ የሚቀርበዉን የኢ-ስኩል ትግበራን ለማሳካት የፋይዳ ምዝገባ ማከናወን ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረው በመንግስት ት/ቤቶች የፋይዳ ምዝገባ ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው የግል ት/ ቤቶችም ምዝገባ ለማካሔድ ተቋማቱ ተገቢዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመድረኩ የፋይዳ መታወቂያን አስመልክቶ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም የየተቋሙ ሀላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

National ID Program - Ethiopia

27 Dec, 12:20


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "ፋይዳን ለባንክ አገልግሎት አስገዳጅነት" ትዕዛዝ ወደ ትግበራ መግባት ተከትሎ የተለያዩ ባንኮች የማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ሀላፊዎች ያሳተፈ በጥምረት ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በትላንትናው እለት በይፋ ተጀምሯል።

በውይይቱም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም National ID Ethiopia አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ባንኮች በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ልክ እንደ አንድ የባንክ አገልግሎት አጽንዖት ሰጥተውበት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በመድረኩም የተለያዩ የባንክ ተሳታፊዎች ከግንዛቤ እጥረት የሚነሱ ችግሮችን ጠቅሰው ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች አስተያየት ሰጥተው የወደፊት አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

26 Dec, 08:10


Channel photo updated

National ID Program - Ethiopia

25 Dec, 14:37


Invitation to Bid

The National ID Ethiopia invites service providers to serve as super-agents for Fayda ID registration and update of biometric and demographic data across all regions and city administrations in Ethiopia.

Interested in bidding? Find details here: https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00330127

#fayda #DigitalID #ፋይዳምዝገባ #ፋይዳለኢትዮጵያ

National ID Program - Ethiopia

20 Dec, 11:04


ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የዲጂታል መታወቂያ የግል መረጃ ማሻሻል ረቂቅ መመሪያ እና የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ረቂቅ መመሪያን አዘጋጅቶ የባለድርሻ አካላት እንዲሁም የህዝብ ውይይት መድረኮችን ማካሒዱ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ በነዚህ ረቂቅ መመሪያዎች ዙሪያ ከህብረተሰቡ ግብዓት ለመሰባሰብ ይረዳ ዘንድ (በዚህ ሊንክ id.et/law ላይ በሚያገኟቸው) ሰነዶች ላይ ማንኛውም አካል በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ ይህን ቅጽ በመጠቀም
(https://shorturl.at/aU3Z6) በመመሪያዎቹ ላይ ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት በጽሁፍ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

#ፋይዳምዝገባ #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

18 Dec, 13:14


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቀልጣፋ የምዝገባ ሒደት እና የነዋሪዎች አስተያየት

https://www.youtube.com/watch?v=alKrTOBMH4M

#ፋይዳምዝገባ #ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

17 Dec, 09:40


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ የነዋሪዎችን ሰብዓዊ መብቶች ለማስከበር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እየተካሄደ ባለው መድረክ ተገልጿል።

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተሳተፉበት በዚህ መድረክ፣ ፋይዳ መታወቂያ ነዋሪነት መሰረት ያደረገ፣ ለእንግልት የማይዳርግ የምዝገባ ስርዓት በመዘርጋቱ አካታችነቱ የተረጋገጠ የመታወቂያ ስርዓት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፋይዳ መታወቂያ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለስደተኞች፣ ለፍልሰተኞች እና መሰል ተጋላጭ ወገኖች ያለውን ተደራሽነት በማስፋት ሰዎች አገልግሎት ለማግኘት ማንነታቸውን ማረጋገጥ የሚችሉበትን የመታወቂያ ስርዓት መሆኑ ተነስቷል።

በተቋሙ እየተተገበሩ ያሉ የሙከራ ትግበራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው፤ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ አካላት የግንዛቤ አድማስን በማስፋት እና ክፍተቶችን በመሙላት የተተገበሩ ጅማሮዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

#ፋይዳ #አካታች #ፋይዳለኢትዮጵያ #Fayda #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

05 Dec, 07:57


Call for Bid 📢

The National ID Program is looking for eligible suppliers for 3,000 sets of biometric registration kits with accessories along with ensured delivery within the specified timeframe.

Ready to bid?

Read https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00326299 for details.

#Fadya #DigitalID #BiometricKit #Inclusive

Follow us on our social media platforms ፡ Facebook | X | LinkedIn | Telegram | YouTube | TikTok | Website

National ID Program - Ethiopia

02 Dec, 16:55


ለፋይዳ መመዝገብ መብት ወይስ.....?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አኳያ ምን ይላል?

#ፋይዳ #ፋይዳምዝገባ #DigitalID #Fayda

National ID Program - Ethiopia

28 Nov, 12:34


It was a pleasure to host Dr. Hassen Hussien, CEO of the Entrepreneurship Development Institute (EDI) - Ethiopia, for a visit to our office and register for Fayda.

Fayda Digital ID empowers start-ups and entrepreneurs by simplifying access to funding, enhancing digital security, and unlocking new opportunities for growth and innovation.

#DigitalID #Entrepreneur #Startups #Fayda

National ID Program - Ethiopia

27 Nov, 10:01


ሁሉን አቀፍ እና አካታች ለሆነው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል? እንግዲያውስ ይህን ያስተውሉ።

#ፋይዳ #ፋይዳለኢትዮጵያ #fayda #DigitalID

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

26 Nov, 08:18


በአሁኑ ሰዓት በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ለሀይማኖት ተቋማት በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ላይ ሼህ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት እና የሀይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ ፣ ፓስተር ታደሰ አዱኛ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት እና የጉባኤው ጠባቂ ፣ ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ፣ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የጉባኤው ጠቅላይ ፀሀፊ ፣ የተከበሩ ቸሩጌታ ገነነ በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፣ አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፕሮጀክት አስተባባሪ ፣ አቶ ዮናስ አለማየሁ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ፣ እና ከፍተኛ የሀይማኖት ተቋማት አመራሮች እና አባቶች በተገኙበት እየተካሔደ ይገኛል።

National ID Program - Ethiopia

25 Nov, 10:31


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው
"ብሔራዊ መታወቂያ እንደ ሀገር ተግባራዊ ስናደርግ ወዲያውኑ 7% የኢትዮጵያ ጂዲፒ ይጨምራል።" ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

ተመዝጋቢዎችስ ስለ ፋይዳ ምን ይላሉ?

https://youtu.be/brxsESnB9V4?si=nQZ5VcBvJr8N4RcS

#ፋይዳ #መታወቅ #Fayda #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

22 Nov, 11:53


Today, UNICEF Ethiopia handed over 100 biometric registration kits to the National ID Ethiopia, as part of the crucial step towards building an inclusive digital identity.

Part of these kits will be deployed to key Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency centers, in addition to our ongoing centers throughout the country accelerating birth registrations and improving access to identification.

UNICEF's support comes as part of the ongoing efforts, towards tackling the challenges of aid diversion through establishing strong social registry based on unique identification platforms, ensuring that every child’s right to legal recognition and support is upheld. We thank UNICEF for their continued support.

#DigitalID #Inclusion #ፋይዳ #መታወቅ

National ID Program - Ethiopia

21 Nov, 14:40


የፋይዳ ፋይዳው ምንድነው?

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር የተደረገ ቆይታ

https://www.youtube.com/watch?v=rgleR3JdcFw

#ፋይዳ #መታወቅ #DigitalID #Fayda

National ID Program - Ethiopia

18 Nov, 17:58


በፋይዳ ይታወቁ ፣ በፋይዳ ይገልገሉ ፣ በፋይዳ ይዘምኑ!!!

ፋይዳ ለኢትዮዺያ

National ID Program - Ethiopia

16 Nov, 17:55


በዛሬው እለት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፕሮጀክት አስተባባሪን ጨምሮ የኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ እና አባላት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በመገኘት የስራ ሂደት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ አብረን ልንሰራባቸው በምንችላቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገው የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

#ፋይዳ #መታወቅ #Fayda #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

15 Nov, 09:18


Fayda ID unlocking doors for access to essential services tackling gender and socio-economic barriers.

From education to finance, marginalized communities now have a path to opportunity and recognition. A brighter, more inclusive future starts here.

Read the full article here: id.et/news

Follow us on our social media platforms ፡ Facebook | X | LinkedIn | Telegram | YouTube | TikTok | Website

National ID Program - Ethiopia

14 Nov, 18:17


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ከፕሮግራሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ጋር በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገው የወደፊት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

#Fayda #ፋይዳ #DigitalID #media

National ID Program - Ethiopia

13 Nov, 12:04


ፋይዳን ለተማሪዎች

ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ Addis Ababa Education Bureau እና ኢትዮ ቴሌኮም @Ethio_telecom ጋር በመተባበር የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ እያስቻለ ነው።

ተማሪዎች "ስለ ፋይዳ ምን ይላሉ?" የሚለውን ከዚህ በታች በቀረበው ዘገባ ይመልከቱ።

#ፋይዳምዝገባ #studentID #CRRSA #telecom

ቪዲዮ፡ ፋና ብሮድካስቲንግ

National ID Program - Ethiopia

11 Nov, 09:55


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ "ፋይዳ" ብሔራዊ ድጂታል መታወቂያ ጋር በዛሬው እለት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ አርቴፊሽያል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ፋይዳን መሰረት ተደርጎ በሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ ተጠናክሮ በሚቀጥለው የምዝገባ ዘመቻ እንዲሁም የሲስተም ብልፀጋ እና ትስስር ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል ፣ ይህም ሀገሪቷ ለምታደርገው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ ላይ ትልቅ እምርታ እንደሚኖረው ይታመናል።

#ፋይዳ #Fayda #DigitalID #DigitalEthiopia

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

06 Nov, 16:53


በአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለሚሰጡ አገልግሎቶች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አስገዳጅነት ለምን አስፈለገ?

በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ id.et/locations ይጎብኙ።

https://www.youtube.com/watch?v=txk3oCM3CAw

#ፋይዳ #DigitalID #CRRSS #ፋይዳመታወቂያ

National ID Program - Ethiopia

05 Nov, 17:03


የፋይዳ ጥቅም ከህዳሴ ግድቡ የማይተናነሰው በምንድነው?

ሌሎች ሀገራት ዲጂታል መታወቂያን ተግባራዊ በማድረጋቸው ኢኮኖሚያቸው ላይ ያመጡት ለውጥ ምን እንደሚመስል ከቴክኖሎጂ ባለሞያ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ አና ከብሔራዊ መታወቂያ ከፍተኛ አማካሪ ኦላና አበበ ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/f2aOWEs3T0s?si=yA97L2eocpZGg42-

ቪዲዮ፡ Ethiopian Broadcasting Corporation

#ፋይዳ #fayda #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

04 Nov, 17:09


በዛፍ ጥላ ስርም የ "ፋይዳ" ምዝገባ፡፡

በጋምቤላ አቦቦ መንደር 11 እና 12 በኢትዮቴሌኮም @Ethio_telecom የብሔራዊ ዲጂታል ምዝገባ ንቅናቄ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ ምዝገባ ጣቢያ በ https://id.et/locations ላይ

#Fayda #DigitalID #ፋይዳ #ፋይዳመታወቂያ

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

04 Nov, 08:10


ለሁሉም ግብር ከፋዮች በሙሉ ከፋይዳ መታወቂያ እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር በተያያዘ የወጣ ማስታወቂያ

#Fayda #DigitalID #ፋይዳ #ፋይዳመታወቂያ

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

01 Nov, 18:14


ብጹዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅና የባህርዳርና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በመገኘት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያም ተመዝግበዋል።

#ፋይዳ #Fayda #DigitalID #EOTC

National ID Program - Ethiopia

31 Oct, 09:56


ስልክዎ ጠፍቶ ወይም በተለያየ ምክንያት የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎ ከስልክዎ ላይ ጠፍቶብዎታል?

እንግዲያውስ ያለ ምንም ኢንተርኔት ወደ *9779# በመደወል በቀላሉ የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎን ወዲያውኑ መልሰው የሚያገኙበትን አማራጭ ይጠቀሙ።

እንዴት? ከዚህ በታች የቀረበውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

#fayda #DigitalID #ፋይዳ #ፋይዳመታወቂያ

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

30 Oct, 09:10


Request for Proposal (RFP)

The National ID Ethiopia invites sealed Bids from eligible Proposers for the following:
1. The Supply, Implementation, and Commissioning of a Unified Endpoint Management Solution and Supply and Integration of 7,000 GPS Devices, and
2. For the supply of 2 Perimeter Firewall hardware and software

Visit https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00318933 for details on the RFP document.

#Fayda #RFP #WorldBank

Follow us on our social media platforms ፡ Facebook | X | LinkedIn | Telegram | YouTube | TikTok | Website

National ID Program - Ethiopia

29 Oct, 18:07


የውይይት ጥሪ

ሀሙስ ጥቅምት 21 ቀን ከቀኑ 10 - 11 ሰዓት “በፋይዳ መታወቂያ የግል መረጃ ለውጥ ረቂቅ መምሪያ” ዙሪያ የሚደረገው የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ በዚህ ሊንክ ይግቡ።

https://zoom.us/meeting/register/tJModeuvqjwtG9Q5HSJGNc6RgMr2epk4SYmg

#ፋይዳ #Fayda #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

29 Oct, 15:20


ነዋሪዎች የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

#Fayda #ፋይዳመታወቂያ #FaydaforService

ምስል፡ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የተወሰደ

National ID Program - Ethiopia

29 Oct, 10:04


ፋይዳን ለሀገር ውስጥ በረራ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ @ethiopian_airlines ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር ስርዓቶችን በማስተሳሰር ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሰነድነት መጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

አየር መንገዱ በፋይዳ የመንገደኞች አገልግሎት ማለትም ምዝገባ ከማስያዝ (Booking) ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያሉትን ባዮሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ እና የተሻለ ለማድረግ አቅዷል።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ id.gov.et/locations ላይ በመግባት ይመልከቱ።

#ፋይዳ #ፋይዳመታወቂያ #TravelSmart #FlyEthiopian

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

28 Oct, 13:04


ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች አካታች የሆነውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል?

እንግዲያውስ በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአ.አ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የክፍለ ከተማ እና ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ በዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም በኢትዮ ቴሌኮም ቅርንጫፎች በመሄድ ዛሬውኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎን በእጆ ያስገቡ!

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት ለማግኘት id.et/locations ወይም aacrrsa.gov.et/subcities ይጎብኙ።

#ፋይዳ #CRRSA #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

28 Oct, 08:25


በሀገር አቀፍ የፋይዳ ምዝገባ ንቅናቄ ዙሪያ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አመራሮች የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከታች በቀረበው ቪዲዮ ይመልከቱ።

https://www.youtube.com/watch?v=kZK2PjRtuFs

#Fayda #CRRSA #ፋይዳ #ፋይዳምዝገባ

በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ  X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ |

National ID Program - Ethiopia

24 Oct, 13:03


ID4Africa now comes to the Land of Origins.

Ethiopia is set to host the highly anticipated ID4Africa 2025 Global Conference in Addis Ababa, from May 20-24, 2025! This prestigious event will bring together government leaders, industry experts, and stakeholders from across the African continent to discuss cutting-edge developments in digital identity system.

Get the details: https://id.et/updates/Events/Ethiopia-Set-to-Host-ID4Africa-2025-Global-Conference-in-Addis-Ababa

#Fayda #ID4Africa #DigitalID #Ethiopia2025

National ID Program - Ethiopia

23 Oct, 07:06


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ የዕድሜ መነሻ አለው? የፋይዳ ቁጥሬ ካልደረሰኝ ወይም ከጠፋብኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?

የእነዚህን ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኝት ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።

#ፋይዳ #CRRS #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

18 Oct, 10:10


ይህን ያዉቃሉ?

በመንግስት ግዥ (eGP) ላይ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመሳተፍ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መያዝ ይኖርባቸዋል!

እርስዎም የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት በአቅራቢያዎ id.et/locations ላይ በሚያገኙአቸው የምዝገባ ማዕከላት በመሄድ የፋይዳ መታወቂያዎን ዛሬውኑ ይያዙ።

#ፋይዳ #eGP #Fayda

National ID Program - Ethiopia

17 Oct, 14:18


የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ህብረተሰቡም በስፋት ወጥቶ እየተመዘገበ ነው፡፡

እርስዎስ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል?

ሙሉ የፋና 90 ዘገባ https://www.youtube.com/watch?v=Aipss7C6vlA ይመልከቱ፡፡

National ID Program - Ethiopia

16 Oct, 10:43


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ እንደተጀመረ ያውቃሉ?

በአቅራቢያዎ በሚገኙ የአ.አ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የክፍለ ከተማ እና ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት በመሄድ ዛሬውኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ይሁኑ!

በአቅራቢያዎ የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት ለማግኘት id.et/locations ወይም aacrrsa.gov.et/subcities ይጎብኙ።

ምዝገባ በነጻ ነው! ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ አያስፈልጎትም!

#ፋይዳ #CRRSA #DigitalID

National ID Program - Ethiopia

15 Oct, 07:24


National ID Program held a successful consultation with the justice sector comprised of Presidents, over 350 judges of the Federal courts, and 350 administrative staff in line with the Federal Supreme Court, the Federal High Court, and Federal First Instance Court of Ethiopia.

An opening remark was made by H.E. Abeba Embiale, Vice President of the Federal Supreme Court in the presence of our Executive Director, Yodahe Zemichael who also delivered a keynote on the integration of Fayda with this important sector. NIDP legal and stakeholder engagement experts provided in-depth insights into the National ID Program’s legal and policy frameworks as well as the objectives and strategies of the Program and emphasized integrating #Fayda into the justice sector will help streamline effective management of identity justice and identity-relate crimes. Closing remarks was made by H.E. Tewodros Mihrete, President of the Federal Supreme Court of Ethiopia.

National ID Program - Ethiopia

14 Oct, 10:44


H.E. Belete Molla Getahun, Minister of Ministry of Innovation And Technology- Ethiopia, H.E. Worku Gachena Negera, Director General of the Ethiopian Artificial Intelligence Institute, and H.E. Yodahe Zemichael leading the Fayda program met with former British Prime Minster, Sir Tony Blair, Executive Director of Tony Blair Institute for Global Change and his delegation, to discuss on the broader work and successes achieved in the integrated effort of the Digital Transformation project.

The discussions included Fayda Digital ID implementation which now stands at almost 10 million digital IDs issued and 4 million eKYC authentications so far, contributing towards inclusion and access to key services.

#Fayda #DigitalID #DPI

National ID Program - Ethiopia

11 Oct, 15:20


የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የጋራ መርሃ ግብር ማስጀመርን ተከትሎ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በጋራ ለ454 አስተባባሪዎች እና የምዝገባ ኦፊሰሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡


በዚህ ስልጠና መክፈቻም ላይ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች አቶ ዮናስ አለማየሁ እና አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ተገኝተው አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ ስለ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፣ የምዝገባ ሂደት፣ ህዘብ ግንኙነት ፣ የደንበኞች አያያዝ እና የሚጠበቅባቸውን ሚና አስመልክቶ የግማሽ ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን 261 የምዝገባ ሰራተኞች የቴክኒካል ፣ ህጋዊ ጉዳዮች፣ የሳይበር ደህንነት እና የመረጃ ጥራት ላይ ያተኮረ የሶስት ቀን ስልጠና ወስደዋል።

#Fayda #CRRSA #DigitalID