አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን @ayatmekaneyesus Channel on Telegram

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

@ayatmekaneyesus


ፕሮግራሞች
👉🏽እሁድ ከ 3 - 5 ሰዐት የፀሎትና የአምልኮ ኘሮግራም።
👉🏽ማክሰኞ ከ 4 - 8 ሰዐት ፆም አና ፀሎት።
👉🏽እሮብ 12:00 - 1:30ተከታታይ ትምህርት።
👉🏽ቅዳሜ ከ 9 -11 ሰዐት የአዳጊ ወጣቶች ፕሮግራም
👉🏽ቅዳሜ ከ 9 - 12 ሰዐት የወጣቶች ፕሮግራም።

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን (Amharic)

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ለገንዘብ አንድ ሰው እና በዚህ ሰው እንዳለው ኢየሱስ እንዳልነበረለት በሚል ለተጠናቀቁ ሰዎች ብርሃን መሰረት እንደሚገኝ ጠይቁን። በዚህ ገንዘብ ላይ ሞቁትና እንደሚገኝ የሚለው አጭር ፕሮግራሞችን ይመልከቱ። በእውነት ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሰዓቱን እንዲጠብቁ ሁሉንም ኀብረተኛ የክርስቲያን ትምህርት ይመልከቱ። አይኮት እንደሚገኝ በዓይኖችዎችና መጻሕፍት በመሸጥ ምንም ማለፈን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በመደበኛ ሰአት ላይ አዳዲሞቹን እና ብክርስቲያንን ጠንቀቁ። ይሄ ቢሆንም እንኳ።

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

23 Jan, 13:20


የረቡዕ ጥር 14 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የ ማለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

23 Jan, 13:19


የረቡዕ ጥር 14 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የ ማለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

22 Jan, 08:48


ረቡዕ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የትምህርት ጊዜ በዶ/ር አብርሃም ተ/ማርያም
ይቀርባል። በትምህርቱ ጊዜ ላይ ሁላችሁም በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችዋል፡፡
አድራሻ :
አያት ጣፎ መብራት ኅይል
ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን የጎግል ካርታ ሊንክ በመጫን ቦታውን ማግኘት ይችላሉ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

16 Jan, 06:52


የረቡዕ ጥር 7 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የ ማለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

16 Jan, 06:50


የረቡዕ ጥር 7 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የ ማለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Jan, 11:34


ታህሳስ/28/17
(January/6/25)
የመልዕክት አቅራቢ: ጋሽ ንጉሴ ቡልቻ
የመልዕክት ክፍል: (ሉቃ 1: 67-79)
ርዕስ: ምን አይነት አምላክ ነው?
መግቢያ: በዚህ ክፍል ካህኑ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የተናገረውን ቃል እናገኛለን። ስለ ልጁ ዮሐንስ ከተናገረው ይልቅ ስለ ኢየሱስ የተናገረው ይበልጣል።

አምላካችን ምን አይነት አምላክ ነው?

1) የሚጎበኝ የፍቅር አምላክ ነው: እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኘ ፈፅሞም የማይረሳ አምላክ ነው። እግዚአብሔር የመጀመሪያው ጎብኚ ነበር። አምላካችን የትም ብንገባ፣ በየትኛውም ኃጥያት ውስጥ ብንሆን ይጎበኘናል።
*አዳምና ሔዋን ሀጥያትን ሰርተው አዳም በዛፎች መሀል በተደበቀ ጊዜ እግዚአብሔር እንደፈለገው፣ እንደጠራው፣ እንደፈለገው ቃሉ ይነግረናል።
*ኖኅ እና ቤተሰቡ አርባ ቀን ውሃ ምድሩን ሁሉ ከድኖ ሳለ እግዚአብሔር እንዳሰባቸው ቃሉ ይነግረናል።
2) ኪዳን አክባሪ ታማኝ አምላክ ነው: እግዚአብሔር በነብያት አፍ የተናገረውን ሁሉ ፈፅሟል። የክርስቶስ ልደት የትንቢት ፍፃሜ ነው። እግዚአብሔር ቃሉን የሚያከብር አምላክ እንደሆነ ይህ ማሳያ ነው።
3) አዳኝ አምላክ ነው: የመዳን ቀንድ አስነሳልን። የሚያድን ሐይል ለእኛ ሰጠን። የኢየሱስ ልደት የመዳን ልደት ነው። እግዚአብሔር ከዳዊት ቤት የመዳንን ቀንድ፣ ንጉስ የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን ላከልን። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ከሚጠሉን እጅ አዳነን።
     ኢየሱስ ከምን ከምን አዳነን?
** ከዓለም
*(ኤፌ 2:1-2) እኛ ሁላችን በምድራዊ ኑሮ አዙሪት የምንገዛ ነበርን። ጌታ እኛን ሳያገኘን በፊት ሰው እንደሚኖረው ሁሉ ነበር ኑሮኣችን።
**በአየር ላይ ስልጣን ካለው አለቃ
*(ኤፌ 2:1-2)ለሰይጣን የምንገዛ ነበርን። እርሱ በእኛ ላይ ስልጣን ነበረው።
** ከስጋችን አዳነን
*(ኤፌ 2:3) ስጋችን የሚያዘንን ሁሉ እናደርግ ነበር። ከምንገብርለት ስጋ ሁሉ ኢየሱስ ነፃ አወጣን።
**ካዳነን በኋላ ለራሳችን አሳልፎ አልሰጠንም
*(ሉቃ 1:74-75)ጌታ ኢየሱስ ነፃ ያወጣን እንድናገለግለው ነው።
       እና ጌታ ኢየሱስን ለምን እናመስግነው?
-የሚጎበኝ ግድ የሚለው አምላክ ስለሆነ፣ ኪዳን አክባሪ ስለሆነ፣ አዳኝ አምላክ ስለሆነ፣ ካዳነን በኋላ ለራሳችን አሳልፎ የማይሰጥ አምላክ ስለሆነ በሙሉ ልባችን እናመሰግዋለን።
                      ማጠቃለያ
ፈፅሞ ስላልተወን፣ ስለወደደን፣ ካለንበት አዙሪት ስላወጣን፣ ከጠላት ድንፋታ ስለገላገለን ክብር ለስሙ ይሁን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Jan, 11:33


የገና ዋዜማ ታህሳስ 28 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የፎቶ ምልከታ 👇 የማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Jan, 11:31


የገና ዋዜማ ታህሳስ 28 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የፎቶ ምልከታ 👇 የማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

02 Jan, 08:57


https://youtu.be/o8ymitWCA24

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

02 Jan, 06:34


ታህሳስ/22/17
(January/1/25)
የመልዕክት አቅራቢ: ቄስ ፀጋዬ አበበ
የመልዕክት ክፍል:(ዮሐ 8:1-11)፣ (1ኛ ዮሐ 2:1-2)
ርዕስ: ኢየሱስ የሚረታ ጠበቃችን
መግቢያ: በዚህ ክፍል የምናያቸው ነገሮች አሉ። ይህ ክፍል የችሎት ሀሳብን ይይዛል። ተከሳሽ አለ እርሷም አመንዝራ ሴት ናት፣ ከሳሽ አለ እነርሱም ፃፎች እና ፈሪሳውያን ሲሆኑ ዳኛው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። ይህን ክፍል ለየት የሚያደርገው ደግሞ ዳኛው ኢየሱስ አብሮ ተከሳሽ መሆናቸው ነው። እርሱንም በሚሰጠው ፍርድ ለመክሰስ ፈሪሳውያን ተዘጋጅተው ነበረና ኢየሱስ ተከሳሽ ነበር።
           ኢየሱስ የረታው ችሎት ምንድነው?
1) ብርቱ ከሳሾችን ነው የረታው:
* (ዮሐ 8:3) ላይ እንደምናየው ከሳሾች ፃፎች፣ ፈሪሳውያን ናቸው። እነዚህ ሰዎች ብርቱ ሰዎች ናቸው። አንዲትን ሴት ለመውገር የወጡት ብዙዎች ነበሩ። ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞች ነበሩ። የህግም አዋቂዎች ነበሩ። በቀላሉ የሚበገሩ አልነበሩም።
*ኢየሱስ የእኛን ክስ ያሸነፈው እንዲህ ነው። አዋቂዎች፣ አደገኛ ሰዎች ያቀረቡብንን ጉዳይ እርሱ አሸነፈ፣ ቆመልን፣ የከበቡንን ከሳሾች በተነልን።
2) ያለቀለትን ጉዳይ ነው የረታው:
(ዮሐ 8:5)-የሙሴ ህግ የተከሳሿን ነገር ቋጭቶት ነበር።የታያዘችው እጅ ከፍንጅ ስለሆነ ከመውገር ውጪ ሌላ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ነበር። ህጉ የማይሻሻል፣ የማይቀልም ነበር። ኢየሱስ ግን ፈፅሞ ደመሰሰው።
*የእኛን ያለቀለት ጉዳይ ያየልን ጌታ አምላክ፣ ለክርክር የማይቀርብን ጉዳይ እርሱ ረታልን። ማንም ባልቆመልን ጊዜ የቆመልን ኢየሱስ ብቻ ነው። ክሳችንንም አስወገደልን።
2) ቅጣቱ ሞት የሆነን ትዕዛዝ ነው የረታው:
(ዮሐ 8:3)-ላይ ቅጣቱ ሞት ነው። በብሉይ ኪዳን ላይ ብንመለከት አንድ ሰው ሲወገር ነፍሱ እስኪወጣ ነው በድንጋይ የሚመታው፣ ጉድጓድም አይቆፈርም። የተወረወረበት ድንጋይ ነበር እንደመቃብር የሚያገለግለው። ከእንዲህ አይነቱ አሰቃቂ ሞት ነበር ኢየሱስ ነፃ ያወጣት።
*እኛንም ከአሰቃቂው የዘላለም ሞት ነው የታደገን፣ ሞትን የከለከለልን።
3) ከሳሾች ያልሰሙትን ውሳኔ በመስጠት ነው:
(ዮሐ 8:5-8) ላይ ኃጥያት የሌለበት እንዲወግራት ሲናገር ማለት የፈለገው ማንም ኃጥያት እንደሌለበት ነው። የኢየሱስን ባህርይ አላወቁም ነበር፣ እርሱ ፍፁም ሰው ፍፁምም አምላክ ነው። ክሱ የተዘጋው በዚህ ቃል ነበር። የሞት ፍርድ የተዘጋው በአንድ ቀን ነበር። ከሳሾቿም በዚህ ቃል ህሊናቸው ተወቅሶ ቀስ በቀስ ዘወር አሉ፣ ወጡም። የመጨረሻውን ፍርድ እነዚህ ፈሪሳውያን አልሰሙም ነበር።
*የእኛን ውሳኔ ኢየሲስ የሰጠው ከሳሾቻችን በሌሉበት ነው። አስጨናቂዎቻችንን ከረታ በኋላ ዕዳችንን ደመሰሰው።
                 ውሳኔው ምንድን ነበር?
1) (ዮሐ 8:11)-ነፃነት ነበር። ከሞት ፍርድ ወደ ነፃነት ነበር።
*ኢየሱስ "በነፃ ሂድ/ሂጂ" የሚል አምላክ ነው።
2) (ዮሐ 8:11)- ደግመን ኃጥያትን እንዳትረሳ አሳስቦ ነበር ።
*ኢየሱስ የዋለልንን ውለታ እያሰብን ደግመን በዚያ ኃጥያት እንዳንገኝ ይፈልጋል።

*ኢየሱስ በማለዳ ነበር ወደ መቅደስ የሄደው። እያስተማረ እያለ ነበር በማለዳ ሰው ለመግደል ፈሪሳውያን ያቋረጡት።
*ኢየሱስም (ዮሐ 8:12) ላይ የተቋረጠውን ትምህርት ቀጠለ። እርሱ የዓለም ብርሃን እንደሆነ መስበክ ቀጠለ።
                 ኢየሱስ ምን ይለናል?
* "ልጄ ሆይ ደሜን ላንተ አፍስሼያለሁ፣ በአብ ፊት ቆሜ ስላንተ ተከራክሬያለሁ፣ ነፍሴንም ስላንተ ሰጥቻለሁ፣ ዕዳህን ሁሉ እኔ ከፍያለሁ፣ ከሳሾችህን እኔ በትኛለሁ፣ እባክህ ደግመህ ኃጥያትን አትስራ!  መስቀል ላይ ደግሞ ሁሉ ተፈፅሟልና አይዞህ! ከሳሾችህ የሉም! ነፍስህን የሚፈልጉ የሉምና በርታ! እኔ አለሁልህ" ይለናል።
                        ማጠቃለያ
ጌታ ኢየሱስ ይወደናልና ወደ እርሱ መቅረብ ይሁንልን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

01 Jan, 09:00


አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን pinned Deleted message

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

31 Dec, 17:07


New Year Challenge!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

30 Dec, 14:15


ታህሳስ/20/17
(December/29/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ዶ/ር ለማ ደገፋ
የመልዕክት ክፍል: (1ኛ ሳሙ 17:1-58)
ርዕስ: ሁለንተናዊ እድገት
መግቢያ: ይህን ክፍል ስንዳስሰው የእስራኤል ሰራዊት ፍልስጤማውያንን ለመግጠም በኤላ ሸለቆ እንደሰፈሩ እና ጎልያድ የተባለው የጌት ሰው ሲዝት እንደነበር እንመለከታለን። ዳዊት የተባለ ታናሽ ብላቴናም በእግዚአብሔር ሀይል ተሞልቶ እንደገጠመውና እንዳሸነፈው ሙሉ ምዕራፍ ይነግረናል።
*የእስራኤል ሕዝብ በፍርሃት ተውጦ ስለ ነበር ዳዊት ለወንድሞቹ መብልን እንዲያደርስ አባቱ እሰይ ላከው። ዳዊት የቤቱ ታናሽ፣ የከብቶች እረኛ ነበር። የስራ ድርሻው ምግብ ማድረስ ነበር። ሌላ ስራ አልተሰጠውም። ነገር ግን ከተሰጠው ስራ ውጪ ወንድሞቹን፣ ሰራዊቱን ስለተፈጠረባቸው ግርግር ሲጠይቅ እናያለን።
*ወንድሙ ኤልያብ ተናዶ ሲያባርረው፣ ሲጮህበት፣ ሲቆጣው እናያለን። ዳዊት ግን ሳያቋርጥ መጠየቁን ቀጠለና ነገሩ ንጉስ ሳኦል ጋር ደረሰ። እሱም የእርሱ ስራ እንዳልሆነ ሊያስረዳው ሞከረ።
          ዳዊት ምን አይነት ሰው ነበር?
1) ክብርን የማይፈልግ: ሳኦል የጦር ልብሱን ሲያስሞክረው ሞክሮ አወለቀው እንጂ በተሰጠው የክብር ልብስ የራሱን ክብር አልፈለገም።
2) በእግዚአብሔር ይታመናል: ጦርነቱ በዳዊት ጀግንነት እንዲጠናቀቅ ሳይሆን አለም ሁሉ እግዚአብሔር እንዳለ ያውቅ ዘንድ ነበር ጎልያድን የተጋጠመው። በእግዚአብሔር ታላቅ እምነት ነበረው። በሚያየው ነገር አልተናወጠም ነበር። እግዚአብሔርን መሳሪያው አድርጎ ያለ ምንም ትግል፣ ሰይፍ ነበር ተጋጥሞት ያሸነፈው።
    ሌላስ ምን አይነት የሕይወት ጥራት ነበረው?
1) ጤናማ ማህበራዊ ህይወት ነበረው: ህዝቡ በጭንቀት ላይ ሳለ ምግብ ብቻ አቀብሎ አልተመለሰም። ነገር ግን ቀረብ ብሎ ጭንቀታቸውን ለመካፈል ሲጥር እናያለን።
2) ልብ ነበረው: ዳዊት ተነሳሽነት ያለው ሰው ነበር። ለእግዚአብሔር ስራ የቀና፣ ችግር ለመፍታት የሚጓጓ ሰው ነበር። ስለጦርነቱ ጠይቆ ብቻ ዳዊት አልተመለሰም። ጠየቀ፣ ተዘጋጀ(ፀለየ)፣ ገባበት፣ አሸነፈ፣ እስራኤል ሁሉ አረፈ።
3) ግንዛቤ/እውቀት ነበረው: ዳዊት ጦርነቱ የህዝቦች ጦርነት ብቻ እንዳልነበር ያውቃል። በእግዚአብሔር መነፅር ሲያየው ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነበር። ይህን ዳዊት ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። ትኩረቱ ሁሉ እግዚአብሔር ላይ ነበር።
4) ክህሎት ነበረው: ዳዊት ፉከራ ብቻ አልነበረውም ፣ ልምድ ነበረው፣ ጠጠር ነበረው፣ ወንጭፍ ነበረው። እንደሚያሸንፈው በሚገርም ድፍረት ተናግሮ ነበር። እንደተናገረው ግን አደረገው እንጂ በወሬ ብቻ አልቀረም። ኢላማን ጠብቆ የመወንጨፍ ብቃት ነበረው። ጎልያድን በሙከራ አልበረም፤ አንድ ጊዜ ወነጨፈ፣ መታው፣ ሞተም።
5) ትጋት ነበረው: ዳዊት በግ ይጠብቃል፣ ምግብ ያደርሳል፣ መዝሙር ይዘምራል። ዳዊት ትጉህ ሰራተኛ ነበር። በጎቹን አንበሳ ሲነጥቅበት ተከታትሎ ያስጥላል እንጂ በስንፍና አይተውም ነበር።
6) አቋም ነበረው: ዳዊት የአቋም ሰው ነበረ። ሰው ተው፣ አይሆንም ቢለውም በራሱ አቋም የፀና ነበር።
7) ትህትና ነበረው: ዳዊት በነገር ሁሉ ትሁት ነበር። የራሱን ጀብዱ ሲያወራ አናገኘውም፣ ስሙን እያገነነ "እንዲህ አደረኩ" ሲል አናየውም። ዳዊት እጅግ ትሁት ነበር።
          ከዚህ ምን እንማራለን?
-የእግዚአብሔር ፀጋ ብቻውን በቂ እንደሆነ ማወቅ አለብን።
-በህይወታችን ላለብን ተግዳሮቶች መፍትሄ መሆን እንዳለብን ዛሬ መረዳት አለብን።
-ራሳችን ላይ መስራት አለብን። እንደ ዳዊት ቅን ልብ፣ ትጋት፣አቋም እና የመሳሰሉትን የሕይወት ጥራቶች ማዳበር አለብን።
ማጠቃለያ
ጌታ ኢየሱስ እርሱ ይርዳን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

30 Dec, 14:15


የእሑድ አምልኮ ታህሳስ 20 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

30 Dec, 14:13


የእሑድ አምልኮ ታህሳስ 20 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Dec, 06:46


https://youtu.be/bqNN1pw9D00

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

23 Dec, 12:52


ታህሳስ/13/17
(Decemeber/22/24)
የመልዕክት አቅራቢ: መምህር ዮናታን መንግስቱ
የመልዕክት ክፍል: (1ኛ ጢሞ 3:8-13)
ርዕስ: ዲቁና እና የምሳሌነት ሕይወት
መግቢያ: ይህ ክፍል አንድ ዲያቆን ምን አይነት ሕይወት ሊኖረው እንደሚገባ ይናገራል።
                   ዲቁና ምንድነው?
1) ዲያቆንያ ማለት አገልጋይ ማለት ነው: አገልጋይ ስንል ደግሞ ጌታን የሚያከብር ማንኛውም አይነት አገልግሎት ማለት ነው።
*(ፊሊ 1:1)- በፊሊጲስዮስ ካሉ ዲያቆናት ጋር ያገለግል እንደነበረ ይህ ክፍል ያሳያል።
2) ከቤ/ክርስቲያን ውጪ ያሉ ስራዎች አገልግሎት ናቸው
*(ሮሜ 13:4)-ከ ቤ/ክርስቲያን ውጪ በመንግስት ስራ ላይ ያሉ ሰዎች አገልጋይ እንደሆኑ ጳውሎስ ይናገራል።
3) በቤ/ክርስቲያን ውስጥ ራሱን የቻለ የአገልግሎት ክፍል ነው: ሁሉም የክርስቶስ አገልጋይ ዲያቆን ቢሆንም ዲቁና ተብሎ ደግሞ የራሱ መስፈርት የወጣለት፣ የሕይወት ጥራትን የሚጠይቅ የዲቁና አገልግሎት ክፍል እንዳለ (1ኛ ጢሞ 3:8) ጀምሮ ቃሉ ይነግረናል።
   አንድ ዲያቆን ምን አይነት ሕይወት ሊኖረው ይገባል?
1) በባህሪ የበቁ:
(1ኛ ጢሞ 3:8-9 ፣ ቁ 11)- ዲያቆናት በባህሪያቸው ጭምቶች፣ ቁጥቦች፣ የተረጋጉ፣ ልከኞች ሊሆኑ ይገባል።
-ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ: ወይን ጠጅ የማይቆጣጠራቸው፣ ሱስን ለማስታገስ የማይጥሩ ሊሆኑ ይገባል።
-(1ኛ ጴጥ 5:2-3)- ነውረኛ ረብ የማይወዱ ሊሆኑ ይገባል። ገንዘብን የማያጭበረብሩ ሊሆኑ ይገባል።
-የቤ/ክርስቲያንንም ምስጢር መጠበቅ አለባቸው።
-ሴቶች ዲያቆናትም የማያሙ፣ ጭምቶች፣ በሁለት ቃል የማይናገሩ፣ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል።
2) በእምነት የተመሰከራለቸው:የሐይማኖትን ምስጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባል: የክርስቶስን ብቸኛ አዳኝ መሆኑ የሚቀበሉ እና የሚጠብቁ መሆን አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዲያቆናት ብዙ ሰዎችን ስለሚጎበኙ፣ ስለሚያፅናኑ የሰዎችን ምስጢር መጠበቅ አለባቸው።
3) ተፈትነው የታዩ:ስለ ቅድስና ሕይወታቸው የተፈተነ፣ ነውር የሌለባቸው እንደሆኑ ተፈትነው መታየት አለባቸው። ምክንያቱም የቤ/ክርስቲያን ተወካዮች ስለሆኑ የ ክርስቶስን ባህሪ ሊያሳዩ ይገባል።
4) በቤተሰብ ሕይወት የተመሰከረላቸው:
(1ኛ ጢሞ 3:4-5)-የ አንድ ዲያቆን አገልግሎት ከቤቱ ይጀምራል። ቤተሰቡን በአግባቡ የሚመሩ ከሆነ፣ ልጆቹን በመልካም አስተዳደግ የሚያሳድግ ከሆነ፣ ሚስቱን የሚያገልግል ከሆነ የቤ/ክርስቲያንን ሰዎች ማገልገል የሚችሉ ይሆናሉ። በቤት የተመሰከረ ማንነት ውጪ ደግሞ ሌላ ባህሪ ሊኖራቸው ይገባል።
            እንዲህ ከሆኑ ምን ያገኛሉ?
1) ትልቅ ማዕረግ: (1ኛ ጢሞ 3:13) ላይ በዲቁና ስራ በመልካም ስራ የሚያገለግሉ ትልቅ ማዕረግን ያገኛሉ። ማን?
እግዚአብሔር ራሱ ከፍ ያደርጋቸዋል።
2) ብዙ ድፍረት: (1ኛ ጢሞ 3:13) ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት ደግሞ ብዙ ድፍረት ያገኛሉ።
                        ማጠቃለያ
እንዲህ የምናገለግል፣ ሀይላችንን፣ ዕድሜያችንን ሁሉ ለጌታ የሰዋን፣ የሰጠን ሁሉ በማያልፈው ዘመን ታላቅ ሽልማት አለን። በመልካም አገልግሎት መትጋት ይሁንልን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

23 Dec, 12:51


የእሑድ አምልኮ ታህሳስ 13 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

23 Dec, 12:47


የእሑድ አምልኮ ታህሳስ 13 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

09 Dec, 15:53


https://youtu.be/xaHWVkYTMUE

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

09 Dec, 12:02


ትምሕርት-6 | የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት| የመንፈስቅዱስ መውረድ አካሉን ለማነፅ | በቄስ ትዕግስቱ ሞገስ|Kes Tigistu Moges

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

09 Dec, 11:54


ህዳር/29/17
(December/8/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ዶ/ር አብርሃም ተ/ማርያም
የመልዕክት ክፍል: (ሐዋ 18:1-11)
ርዕስ: የቤ/ክርስቲያን ተከላ እንዲህ ነው
መግቢያ: ይህ ክፍል ሲጀምር "ከዚህም በኋላ" ብሎ ነው። በምዕራፍ አስራ ሰባት ወደ ግሪክ፣ አቴንስ ይወስደናል። ጳውሎስ ወንጌልን በብዙ ተቃውሞ ይሰብክ ነበር። ቤ/ክርስቲያንም ተተክላ ነበር። ከዚያም ወደ ምዕራፍ አስራ ስምንት ስንመጣ አቂላ ከሚባል የጳንጦስ ሰው አግኝቶ ስራቸው አንድ ነበርና አንድ ላይ ከእርሱ ጋር መስራት ጀመረ። እርሱም ድንኳን ስራ ነበር።
* ይህ ሰው ከባለቤቱ ጵርስቅላ ጋር ወደ ቆሮንቶስ የመጣው የሮም ከተማ ክርስቲያኖችን አባራ ስለነበር ነው።
       ቤ/ክርስቲያን እንዴት ይተከላል?

1) በተባረሩ፣ በተጨነቁ ሰዎች ቤ/ክርስቲያን ይሰራል። ጳውሎስ እና እነዚህ ባልና ሚስት ለቆሮንቶስ እንግዳ ነበሩ። ሁለቱም ተባረው፣ ተገፍተው ነው በቆሮንጦስ የተገናኙት። እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ቤ/ክርስቲያን ተከላን ሊሰራ ችሏል።
*ጳውሎስ እና አቂላ እንደ አጋጣሚ ስራቸው አንድ ነበር። ሙያቸው ድንኳን መስራት ነበር። እግዚአብሔር ይህን አደረገ። ለምን? ገና ይህ ህብረት አልፀናም፣ ገቢም የላቸውም። ስለዚህ ለመኖር እና ቤ/ክርስቲያን እንድትፀና ድንኳን መስፋት ግድ ነበር። የቆሮንቶስ ቤ/ክርስቲያን የጀመረችው እንዲህ ነው። ትንሽ በሚመስል፣ በተገፉ ሶስት ሰዎች ነው የተጀመረው።
*በስራ ቀን ድንኳን እየሰፋ በሰንበት ቀን ግን ወንጌልን በምኩራብ ይሰብክ ነበር።
2) እግዚአብሔር ሰዎችን በፉጨት ይጠራል። እግዚአብሔር ትክክለኛ ሰዎችን ለወንጌል ስራ በራሱ ይጠራል። ጳውሎስ ለ ሶስት ሳምንት ያክል ድንኳን እየሰፋ ወንጌልን ይሰብክ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ሲላስንና ጢሞቴዎስን ላከለት። እነርሱ ከፊልጲስዩስ ቤ/ክርስቲያን የተላከን ገንዘብ አመጡለት። አይሁድም ሲያባርሩት ወደ አህዛብ እንደሚሄድ ነግሯቸው አንድ ኢዮስጦስ ወደሚባል ሰው ቤት ሄደ። ይህ ሰው ክርስቲያን ነበር። ሌላ የምኩራብ አለቃ ቀርስጶስ ከነ ቤተሰቦቹ በጌታ አመነ። ከዚህ ምን እንማራለን?
*እነዚያ ሶስት ሰዎች አሁን ሰባት ደርሰዋል። ከዚያም አልፎ ብዙ ሰው ወደ ጌታ ተጨመሩ። እነዚህ ሁሉ ከተለያየ ስፍራ ነው የተሰባሰቡት፣ አልተቀጣጠሩምም። የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲህ ነው ቀስ በቀስ የሚበዛው።
3) እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል። እግዚአብሔር እንደ አስፈላጊነቱ በራዕይ ተገልጦ ድምፁን ይልካል። አንዴ ለሁሉ የተናገረው ቃል ቢኖርም፣ እንዲሄዱ የላካቸው ሐዋርያትም እርሱ ቢሆንም ድምፁን በሌሊት  አሰማው፣ አበረታው፣ ከእርሱ ጋር እንደሆነም ነገረው። ይህን ድምፅ እግዚአብሔር ያመጣለት ጳውሎስ ስለፈራ ነበር። እየሰራ ባለው የእግዚአብሔር ስራ ላይ እየታከተ፣ እየፈራ ስለነበር ነው ክፉ እንደማይነካው የነገረው።
*ስራንም ሰጠው። ምን? ይህ ሰው ለመመስከር፣ ለመናገር የተጠራ ሰው ነበርና ክፉ የለም ማለት ሰላም ነው ማለት አይደለም። ቆሮንቶስ የገባው ጳውሎስ ወንጌልን እንዲሰብክ ስለሆነ ዝም እንዳይል እግዚአብሔር ያሳስበዋል ። ዝም እንዲል የሚገፋፉ ብዙ ነገሮች ስለነበሩ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያ ከተማ ብዙ ህዝብ ነበረው። ስለዚህ ጳውሎስ ዝም ማለት የለበትም። ወንጌልን መስበክ መቀጠል ነበረበት። ለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን በራዕይ አሳወቀው። ለምን? ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር የቆሮንቶስን ከተማ ለራሱ ሊዋጅ፣ ሊወስዳት ፈልጎ ስለነበር ነው።
       ታድያ የእኛስ ድርሻ ምንድነው?
- እንደነ አቂላ እና ጵርስቅላ ባለትዳር የሆንን የጌታን ወንጌልን መስበክ አለብን።
-እንደነ ጢሞቴዎስ ደግሞ በቤ/ክርስቲያን ተከላ የተሰማሩትን ሰዎች በገንዘብ መደገፍ መቻል አለብን።
-እንደ ክርስቲያን በዙሪያችን ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር አለው። ስለዚህ በወንጌል ስርጭት መትጋት አለብን።
                     ማጠቃለያ
ድርሻችንን አውቀን፣ ያለንበትን ጊዜ በመመርመር እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ዝም ሳንል ወንጌሉን ማሰራጨት እንድንችል ጌታ ይርዳን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

09 Dec, 10:23


የእሑድ አምልኮ ህዳር 29 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

09 Dec, 10:22


የእሑድ አምልኮ ህዳር 29 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

06 Dec, 05:42


https://youtu.be/C0glKwmZOe8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

06 Dec, 05:39


ትምሕርት-5 | የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት| በመንፈስ ቅዱስ ህልውና ውስጥ የገባ ሰው 4 ምልክቶች | በቄስ ትዕግስቱ ሞገስ|Kes Tigistu Moges

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Dec, 14:20


ህዳር/25/17
(December/4/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ
የመልዕክት ክፍል:(ሐዋ 2:40-47; ሐዋ 3:1-11)
ርዕስ: እግዚአብሔር ከሞገሱ የሚያጠግበው ማንን ነው?
መግቢያ: (ክፍል-7)
በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ ሁለት የመጨረሻውን ቁጥር ብንመለከት ሐዋርያት በሰው ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ሞገስን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። ብዙ ሰዎች ግን ሞገስን ለማግኘት ብዙ ሲጥሩ እናያለን። በቀደመችው ቤ/ክርስቲያን ቃሉን የሚቀበሉ፣ እንጀራን በጋራ የሚቆርሱ፣ በአንድ ልብ በፀሎት የሚተጉ ስለነበሩ ነበር ጌታ ኢየሱስ በሁሉ ፊት ለሐዋርያት ሞገስን የሰጣቸው።
*ወደ ምዕራፍ ሶስት ስንገባ አንድ ሰው እናገኛለን። ይህ ሰው በመቅደስ ደጅ የሚለምን፣ ከማህፀንም ጀምሮ አንካሳ ነበር።
     እግዚአብሔር ከሞገሱ የሚያጠግበው ማንን ነው?
1) ለሰው በቅንነት ለሚኖር ሰውን
- እግዚአብሔር እንደሚያይ ለሚያዩ ለእነርሱ እግዚአብሔር ሞገስን ያጠግባል። ጴጥሮስ አስተሳሰቡ በክርስቶስ ስለተቃኘ ለአንድ ደሃ ፤ምፅዋትንም ለሚጠይቅ ሰው ተገኝቶ ነበር። ጴጥሮስ በአገልግሎቱ የታወቀ፣ ለድሆች ጊዜ የሌለው ቢሆንም ይህን ሰው በእጁ እንኳን ለመጨበጥ አልተፀየፈም ነበር። ጴጥሮስ ለዚህ አርባ አመት ሽባ ቆመለት። እጁንም ይዞ አስነሳው፣ አብሮት ወደ መቅደስ ገባ። ለምን? ለሰው ልጆች አክብሮት ነበረው። ይህን ከክርስቶስ ጋር በመዋል የወሰደው ነገር ነው።
*አንድ መቶ አለቃ ለባርያው እንዴት እንደራራ ማየት እንችላለን። የታመመበት ባርያው ሆኖ ሳለ ብላቴናዬ ታሟል ብሎ ወደ ኢየሱስ በፍጥነት ወጣ። ጌታ ኢየሱስ ቃልንም ቢናገር እንደሚፈወስ አምኖ እንደ ቃሉ እንደሆነለት  እናውቃለን። ለምን እንዲህ ያለ ዋጋ ለባሪያው ከፈለለት? ሰው በመሆኑ ስለሚያከብረው ነው። እግዚአብሔር ስለፈጠረው ስለዚህ ሰው ግድ ይለው ነበር። ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ እንኳን በእምነቱ የተገረመው።
2) ለወንጌል በትጋት የሚያገለግል:
(ሐዋ 3:11-12) በዚህ ክፍል ጴጥሮስ ሽባው በተፈወሰ ጊዜ ራሱን ለመግለጥ አልሞከረም ነበር። ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ወንጌልን ለመስበክ ሲጠቀምበት እናያለን። የተዓምራቱ ምንጭ ኢየሱስ እንደሆነ በብዙ ቃል በመናገር አከበረው። ብዙ ሰዎችም ጌታ ኢየሱስን ተቀበሉ። እንዲህ ለወንጌል ትልቅ ልብ ስለነበረው ሞገስን ይጠግብ ነበር። ሰማያት በአንፃሩ ተከፍቶ ነበር፣ ልብሱ እንኳን በሽተኞችን ይፈውስ ነበር።
                       ማጠቃለያ
ጌታ ሞገሱን እንዲያጠግበን ለሰዎች ግድ ይበለን፣ ወንጌልንም ባገኘነው አጋጣሚ ለመስበክ እንትጋ!  በፀጋው ብርታት እንድናደርገው ደግሞ ጌታ ይርዳን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Dec, 14:17


የረቡዕ ህዳር 25 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Dec, 14:09


የረቡዕ ህዳር 25 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

28 Nov, 12:43


https://youtu.be/5y_mygzLcj0

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

28 Nov, 12:22


ትምሕርት-5| የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት|በመንፈስ ቅዱስ ህልውና ውስጥ የገባ ሰው 4 ምልክቶች
|በቄስ ትዕግስቱ ሞገስ| Kes Tigistu Moges
ሐዋ,2፥1-28

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

28 Nov, 06:23


የረቡዕ ህዳር 18 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርትየሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

28 Nov, 06:21


የረቡዕ ህዳር 18 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርትየሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

21 Nov, 21:48


የረቡዕ ህዳር 11 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርትየሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

21 Nov, 21:46


የረቡዕ ህዳር 11 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

18 Nov, 09:16


ህዳር/8/17
(November/17/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ
የመልዕክት ክፍል:(መዝ 73:1-28)
ርዕስ: ከተሸናፊነት ሕይወት ወደ አሸናፊነት ሕይወት የሚያወጣን ምንድነው?
መግቢያ: አሳፍ በንጉስ ዳዊት ዘመን የነበረ የተወደደ ሰው ነበር። ይህ ሰው መንገዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው ቸርነት እንደሚሆንለት በብዙ መዝሙሮች  ዘምሯል። ነገርግን ይህ እውነት እያደር ሲሄድ ተጋጨበት፣ ተፀፀተም። በሰበከው እና በኖረለት ጌታ ማዘን ጀመረ። ለምን? መንገዳቸው ከእግዚአብሔር ጋር ያልሆኑ ሰዎች ሲበረቱ በእነርሱ መቅናት ጀምሮ ነበር።
  ከተሸናፊነት ወደ አሸናፊነት ሕይወት የሚያወጣን ምንድነው?

1) የእግዚአብሔርን ቃል ያለጥርጥር ስናምን: አንዳንዴ አሁን ባለንበት ዓውድ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ልንመዝን እንሞክራለን። ሕይወት ሲከብድብን እግዚአብሔርን ለምን ይህ ሆነብኝ እንላለን። የተናገረን ቃል በቶሎ ባይፈፀም፣ ባልፈለግነው መንገድ ለመሄድ ብንገደድም የእግዚአብሔር ቃል የታመነ እና የሚፈፀም መሆኑን ማወቅ አለብን።
*እዮብን ብንመለከት ባላሰበው መንገድ ውስጥ ቢያልፍም አምላኩን አልተጠራጠረም ነበር። እስኪጎበኘው ድረስ ይጠብቅ ነበር። አሳፍ ግን በክፉ ሰዎች ቀንቶ ነበር። ከሰው ጋርም ራሱን ማስተያየት ጀምሮ ነበር።
*አብርሃምም ቃል ተልኮለት ነበር። ልጁን ሰዋልኝ በተባለ ጊዜ እግዚአብሔርን አመነ። የእግዚአብሔር ቃሎች የታመኑ መሆናቸውን ተረድቶ ነበረና ልጁን ለማረድ አልሰሰተም ነበር።
-ስለዚህ ቃሉ የታመነ፣ እውነተኛ እንደሆነ ብናምን ከተሸናፊነት ወደ አሸናፊነት ሕይወት እንወጣለን።
2) እውነተኛ ንስሃ: በእውነተኛ ንስሃ በእግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ ጌታ ደስ ይለዋል። ድካማችንን ለእግዚአብሔር ስንገልጥ የሚያስፈልገንን ፀጋ ይሰጠናል። የምትጤስን ጧፍ እንደማያጠፋ ቃሉ ይናገራል። በእውነተኛነት በፊቱ ብንቀርብ የማይፈርድ አምላክ ነው ያለን። ይህን ሁሌ ማወቅ አለብን።
*ዳዊት ቤርሳቤህን ተመኝቶ ኦርዮንን በገደለ ጊዜ "አጥፍቻለሁ" ብሎ ወደ ንስሃ ፊቱን አዞረ እንጂ አልታበየም። እግዚአብሔር ለምህረት የሚቸኩል አምላክ መሆኑን ማወቅ አለብን።
*ሶምሶንም ፀጋውን ካስወሰደ በኋላ አይኖቹ ጠፍቶ ወፍጮ ይፈጭ እንደነበር እናውቃለን። ነገርግን አንድ ጊዜ "አስበኝ " ባለው ጊዜ አሰበው። ለምን? በእውነተኛ ልብ ስለለመነው ነበር።
*ከኢየሱስ ጋር የተሰቀለው ወንበዴ አደገኛ ሰው ቢሆንም፣ ብዙ ጥፋት ቢያጠፋም በመስቀል ላይ "አስበኝ" ባለው ጊዜ "የዘራኸውን እጨድ" አላለውም ነበር። "ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ" አለው። አምላካችን እንዲህ ነው።
-አሳፍም ሊወድቅ እንደሆነ ነገረው። እግዚአብሔርም አላኮረፈውም ነገርግን መጨረሻቸውን ይናገረው ነበር።
3) የፅሞና ጊዜ ስንወስድ: አሳፍ ይህ ነገር ሲያሳስበው ወደ ማንም አልሄደም። ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ። እግዚአብሔርም ተገለጠለት።
(መዝ 73:16-17) ወደ ህልውናው በገባ ጊዜ የእነዚያን ሰዎች መጨረሻ ማወቅ ቻለ። እግዚአብሔርም እጁን እንደያዘው ገለጠለት። እነዚያ በክፉ መንገድ የሚሄዱት የያዛቸው ክንድ እንደሌለም አወቀ።
-እኛም በሀጥያተኞች መቅናት የለብንም። ለምን? እጃችንን የያዘ አምላክ ስላለን ድጥ ላይ በሚራመዱት መቅናት የለብንም።
                      ማጠቃለያ
የእግዚአብሔር ቃል የታመነ ነውና መበርታት ፣ መፅናት፣ ማመን ይሁንልን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

18 Nov, 08:32


የእሑድ አምልኮ ህዳር 8 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

18 Nov, 08:26


የእሑድ አምልኮ ህዳር 8 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

14 Nov, 16:34


https://youtu.be/jYgmrF9wouw

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

14 Nov, 11:56


የጸጋ መተላለፊያ 3 ስነ ምግባሮች ትምሕርት ሶስት ሐዋ,1፥12-14 የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምሕርት

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

14 Nov, 11:14


የረቡዕ ህዳር 04 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

14 Nov, 11:12


የረቡዕ ህዳር 04 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ 👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

08 Nov, 15:01


የአዲሱ የማምለኪያ ስፍራ የመክፈቻ ፕሮግራም

🗓 2 ቀናት ብቻ ቀሩት! ሕዳር 1, 2017 ዓ.ም 🗓

👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Nov, 20:55


ጥቅምት 26/17
(November 6/24)
የመልዕክት ክፍል: የሐዋሪያት ስራ 1:12-14;
የመልዕክት ክፍል አቅራቢ : ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ
ርዕስ: ጸጋው እንዲተላለፍብን ሶስት ስነምግባሮች እንትጋ
መግቢያ
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከማረጉ በፊት ''ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፣ ሀይልን ሳትቀበሉ ከኢየሩሳሌም እንዳትወጡ'' ብሏቸው  ነበር።
እነዚያ አደገኛ ሊቀ ካህናት እነ ቀያፋ፣ ጲላጦስ ወዳሉበት ኢየሱስን በብዙ ወዳሰቃዩት፣ ወደ ሰቀሉት ነበር ተመለሱ ያላቸው።

የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲተላለፍብን ምቹ ስነምግባር የሚባሉት ምንድናቸው?
1.መታዘዝ ያስፈልጋል
መታዘዝ ውጤቱ የገባንን እና የቀለንን ማድረግ አይደለም - እሱ መስማማት ነው።
መታዘዝ አምላክ ከሆነ የተናገረው፣ እንደ ቃሉ ከሆነ መስዋዕታዊ ዋጋ ከፍሎ እሺ ብሎ ማድረግ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ሀይልም፣ ቅባትም፣ ንፋስም አይደለም ፣ አምላክ ነዉ። እኛን እርሱ  ይቆጣጠራል እንጂ እኛ አንቆጣጠረውም።
ሀዋሪያት ታዘዙት እና ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። - ኢየሱስ በሽተኞችን ፈውሶ ለማንም አትናገሩ ሲላቸው ፣ ሄደው ለሁሉ ሲያወሩ ትቷቸው ወደ ምድረ በዳ ይሄድ ነበር ፣ አላማዉ የመንግሥቱ ወንጌል ስለነበር። ስለዚህ በኢየሩሳሌም ጠብቁ ሲላቸው ለምን እንደሆነ ባያውቁም ታዘዙት፣ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ በየቋንቋቸው ከተለያዩ አገሮች የመጡ ሰዎችም ወንጌልን ሰሙ።
- ለአብርሃም እግዚአብሔር ይስሐቅን ሰዋልኝ ሲለው የሶስት ቀን መንገድ ተጉዟል፣ ለምን እንደራቀ ባይገባውም ታዟል።
-ዮሴፍ  ወንድሞቹን ወሬ ለማቀበል ታዞ ሲወጣ የግብፅ መንገድ ተከፈተ፣ ብዙ ምድረ በዳ ቢያሳልፍም እግዚአብሔር አልተለየውም።  -ሙሴ አለቱን ተናገረው ሲለው መቶት ውሀ በማፍለቁ/በዚያች አለመታዘዝ ከነዓንን የመውረስ እድል አጥቷል; ሙሉውን ምድር እግዚአብሔር ቢያሰየውም።
-ሳዖል ፈጽሞ ባለመታዘዙ እግዚአብሔር ከርሱ ርቋል።
-ንዕማን ሰባት ጊዜ ውሃ ወስጥ ብቅ ጥልቅ ብሎ ተፈውሷል፣ መንገዱ ባይገባውም። -ህዝቅኤል አጥንቱን በአፋ ቃል  ሰራዊት ያረገው ታዞ እንጂ ተመራምሮ አይደለም።
**ለመጣላቸው ቃል አሜን ብለው የታዘዙት እነርሱ ብጹአን ናቸው - እንደ ድንግል ማሪያም እና ዮሴፍ።
-ፊሊጶስ መልአክ ታዞ ወደ ምድረ በዳ በመሄዱ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ወንጌል ሰምቶ ማዳን ምክንያት ሆነ።
*መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል፣ በጥቂት የሚታዘዙ በብዙ ይሾማሉ።*

2. ለ ባለስልጣን መገዛት ያስፈልጋል
-ለጴጥሮስ ይሄ መርህ ገብቶታል። ወዲያው የመሪነት ቦታውን ወሰደ፣ እነርሱም ለሀሳቡ ተገዙለት።
ምንም ያህል ባለስልጣኑን ብንወደው ባይመቸን መገዛት አለብን።
-ሩት ለኑሀሚን እንደ ልጅ ተገዝታለች። ምንም በራሷ ጉዳዩን  መጨረስ ብትችልም ስለ ቦዔዝ አድርጊ ያለቻትን ሰማች፣ ሄዳ ግርጌው ላይ ተኛች ፣ ወደ ሌላ አትሂጂ ፣ ጠብቂው ስትላት' ጠበቀች፣ በረከትን አገኘች ።
-ሀናም ለኤሊ ምንም ያህል ቢዘባርቅ እና ጸሎቷን እንደ ሰካራም ቢቆጥራትም ስለ  ክህነቱ ተገዝታለች፣ 'የጠየቅሽውን ይስጥሽ' ብሏት በረከትን ተቀብላለች። ልጇም ሳሙኤል ከእግዚአብሔር ድምጽ  ተቀብሎ ለኤሊ ቤት በፍርሃት ፍርድን ከነገረው በኋላ ኤሊን በፍጹም መገዛት ያገለግል ነበር።
-እጅግ የተወደደ የተባለ ዳንኤል ንጉስ ዳሪዮስ አንበሳ ጉድጓድ ውሰጥ አስጥሎት በነጋታው ሲመጣ 'ንጉስ ሆይ፣ ሺህ አመት ንጉስ' አለው፣ ድለላ አይደለም ፣ አክብሮቱን ያሳያል።
-ዳዊትም ሳዖልን ተኝቶ አግኝቶ ''እግዚአብሔር የቀባው ላይ እጄን አላነሳም'' ብሏል።
- አባት እና እናትን ማክበር በረከት ያለው ትዕዛዝ ነዉ።
-ያለ ጥበብ ፓትሪያርክ አባቱን ያሳዘነ እና በህይወቱ ሁሉ ዋጋ የከፈለ ሰው አንዱ ሮቤል ነዉ። የአባቱን ያዕቆብን እቁባት ወሰደ፣ እርግማን በላዩ ኖረ።
-ቃየን እግዚአብሔርን በመናቁ በዘመኑ ሁሉ ተንከራታች ሆነ። ምድሩንም ፣ ልጁንም ሄኖህ አለው ፣ ተንከራታች ማለት ነው።
- እንዲሁም ማሪያም እና አሮን እግ/ር በሾመው መሪ ወንድማቸው ሙሴ ላይ ሲያጉረመርሙ ሜሪያም በለምጽ እንደተመታች እናያለን።
-(መክብብ 10:20)ላይ እንደሚናገር  ''በሐሳብህም እንኳ ንጉሥን አትንቀፍ፤ በመኝታ ክፍልህም ባለጠጋን አትርገም፤...''
-በአዲስ ኪዳን ጳውሎስ መሪዎችን ሲያከብር እናያለን። በሸንጎ ፊት በጥፊ ሲመታ ተሳድቦ ሊቀ ካህን መሆኑን ሲያውቅ በአደባባይ ይቅርታ ጠይቋል።
(2 ጴጥሮስ  2:10,18) ላይ ከንቱ ቃል እየደረደሩ ከሚኖሩት መሃከል እንዳንሆን ይነግረናል። እንዲሁም (ይሁዳ 1:12) ''እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋር ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው። '' ይላል።
- ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ። ስልጣንን አለማክበር ከአምላክ ጋር ያጣላል።  ባለስልጣናት  ቢያጠፋ በትህትና መምከር እና መገሰጽ ያስፈልጋል። ካልተመለሱ እየጸለዩ  ለእግ/ር መተው ይሻላል።

3. የመንፈስ አንድነትን መጠበቅ
- መንፈስ  ቅዱስ ከመውረዱ በፊት መቶ ሃያ ደቀመዛሙርት በአንድ ልብ ነበሩ። ተከፋፍሎ አይሆንም።
- ሁለት ሰው ተስማምቶ በጌታ ስም ማናቸውንም ነገር  ቢጠይቅ እንደሚሆን መጽሀፍ ቅዱሳችን ይነግረናል። 
-ለክፋት እንኳን የባቢሎንን ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ ለመስራት ሰዎቹ በአንድ ልብ ሆነው እግዚአብሔር ሲያይ ቋንቋቸውን የደበላለቀው አንድ ሀሳብ መሆናቸውን ስለሚያውቅ ነዉ። ዮናታን እና ጋሻ ጃግሬው በአንድ ልብ ተስማምተው በእግዚአብሔር ሀይል አስራ ሶስት ሺህ ሰራዊት ጦር አሸንፈዋል።
              ውጤቱ ምን ሆነ?
ጴጥሮስ በመገለጥ ቃል ተናገረ። በመዝሙር መጽሐፍ፣
‘መኖሪያው ባዶ ትሁን፤ የሚኖርባትም ሰው አይገኝ’ ደግሞም፣ 'ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፎአል።' በማለት ስለ ይሁዳ አስቀድሞ የተጻፈውን ትንቢት ገለጠ። በይሁዳ ላይ መሻር  ሞት ሲሆን በእነጴጥሮስ ላይ ሀይል እና ቅባት ሆነ።
                           ማጠቃለያ
ሀዋርያት ስለ ታዘዙ፣ ስለ ተገዙ የመንፈስ አንድነትን ስለ ጠበቁ እግዚአብሔር መንፈሱን በመስጠት  አከበራቸው። እኛም በዚህ ዘመን ለጌታ ታዛዦች እንድንሆን ፣ በቅንነት እንድንገዛ ፣ የመንፈስ አንድነትን እንድንጠብቅ  እና ለቅባቱ የተዘጋጀ ህይወት እንዲኖረን ጌታ ይርዳን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Nov, 15:23


https://youtu.be/-VWCGOhxeeU

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Nov, 15:00


የአዲሱ የማምለኪያ ስፍራ የመክፈቻ ፕሮግራም

🗓 3 ቀናት ብቻ ቀሩት! ሕዳር 1, 2017 ዓ.ም 🗓

👇የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Nov, 13:53


የረቡዕ ጥቅምት 27 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

07 Nov, 13:52


የረቡዕ ጥቅምት 27 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Nov, 16:35


አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን pinned «https://youtu.be/fjsMPd00r7A»

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Nov, 15:01


የአዲሱ የማምለኪያ ስፍራ የመክፈቻ ፕሮግራም

🗓 5 ቀናት ብቻ ቀሩት! ሕዳር 1/2017 ዓ,ም 🗓

የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ /
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Nov, 13:26


ረቡዕ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምህርት በቄስ ትዕግስቱ ሞገስ ይቀርባል። በትምህርቱ ጊዜ ላይ ሁላችሁም በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችዋል፡፡

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

05 Nov, 12:49


https://youtu.be/fjsMPd00r7A

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

04 Nov, 15:00


የአዲሱ የማምለኪያ ስፍራ የመክፈቻ ፕሮግራም

6 ቀናት ብቻ ቀሩት!

ሕዳር 1, 2017 ዓ.ም

👇 የአዲሱ ማምለኪያ ስፍራ አድራሻ 👇
https://maps.app.goo.gl/H4Wc2TxN7W3KjBLn8

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

04 Nov, 13:27


ኢየሱስ የመልካም ፍጻሜ ምሳሌ ትምሕርት ሁለት ሐዋ,1፥6-11 የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምሕርት

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

04 Nov, 10:36


ጥቅምት/24/17
(November/3/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ወ/ት መሠረት መብራቴ
የመልዕክት ክፍል:(ዘፍ 34:1-7)
ርዕስ: እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አለመመላለስ የሚያስከትለው መዘዝ
መግቢያ: በዚህ ክፍል እንደምናየው ዲና የምትባል ያዕቆብ ከራሄል የወለዳት ብቸኛ ሴት ልጅ ነበረች። እግዚአብሔር ለያዕቆብ ወደ ቤቴል እንዲሄድ በፈለገበት ጊዜ ነበር ዲና ድንገት ብድግ ብላ ያለ እግዚአብሔር ሀሳብ ማንንም ሳታማክር ተነስታ ወጣች።
   እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አለመመላለስ የሚያስከትለው መዘዝ ምንድነው?
1) የኤሞር ልጅ ሴኬም ባገኛት ጊዜ ወስዶ አስነወራት። ያለጊዜው ክብሯን ጣለች። ቤተሰቦቿ የጠበቁላትን ነገር በድንገት ወጥታ አጣችው። መመታትም ሆነ። ይህ ሴኬም ያደረገው ነገር ነውር ሆኖ ሳለ ነገሩ ከሆነ በኋላ አባቷን እርሷን ለመውሰድ ሲፈቅድለት እናያለን።
**እኛም እግዚአብሔር በሰጠን በያለንበት ነገር በቅድስና እንድንመላለስ ጌታ ይፈልጋል። ለምን? ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በሄደበት ስፍራ ከባድ ነገር ወደ ቤቱ መጣበት። ሰይፍ መማዘዝ ሆነ፣ ጦርነት ሆነ።ከዚህ መማር መቻል አለብን። በድንገት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ዘወር ማለት አይሁንብን። መዘዝም ከሚያመጣ ነገር ጌታ እንድንርቅ ይፈልጋል።
2) ርብቃን ብናይ እጅግ አስተዋይ ሴት ነበረች። በወጣትነቷ ከወላጆቿ ስር በስርዓት ያደገች ልጅ ነበረች። አካሄዷም እንደ እግዚአብሔር ቃል ነበር።
**አካሄድን ማስተካከል ፍፃሜን ያሳምራል።
3) የጠፋውን ልጅ ታሪክ ሉቃስ ላይ ብንመለከት ይህ ትንሽ ልጅ ድንገት ተነስቶ ውርስ ስጠኝ ብሎ አባቱን ሲጠይቅ እናያለን። ዲና እንዳደረገችው ወደ ውጭ ወጣ፣ ገንዘብ ስለነበረው ብዙ ወዳጆችን አፈራ። ሁሉ ባለቀበትም ጊዜ በባዶነት፣ በርሃብ፣ በመራቆት ተመታ።
**እኛንም ከአባታችን ቤት አውጥቶ ሊያዋርደን ያለ መንፈስ ላይ መንቃት አለብን።
4) ሶምሶንን ብናይ በጠላቶቹ ላይ እንዲሰለጥን ሀይልን የተሞላ ይህ ሰው በብዙዎች ይታወቅ እና ይፈራ ነበር። አካሄዱ ግን ተበላሽቶ ነበር። ደሊላ ግን በንዝነዛ ሀይሉን በመውሰድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውን ሀይል አሳጣችው።
**እኛም ላይ ያለውን ታላቅ ቅባት፣ የእግዚአብሔር ሀይል እና ሞገስ አይቶ ተራ ሊያደርገን የወጣውን ቅናተኛ መንፈስ ጌታ ይገስፀው! አመፅ ላይ ጌታ ያንቃን!
5) የሙሴን እናት ብንመለከት ወንድ ልጅ ይገደል በተባለበት ዘመን በእምነት ሙሴን ሸሽጋ አቆየችው። መሸሸግ ባልቻለችም ጊዜ ወስዳ አልጣለችውም። እንዳይሞት የአቅሟን በጥንቃቄ ወንዝ ላይ ለቀቀችው። እግዚአብሔርም ቤተ-መንግስትን በእርሱ አንቀሳቀሰ።
**እኛም ጊዜ ሰጥተን፣ እየፀለይን፣ የአቅማችንን አድርገን ለእርሱ በተውነው ነገር እርሱ ከህግ በላይ ሆኖ ነገራችንን፣ የጣልነውን ነገር ያነሳልናል።
           ታድና ምን እናድርግ?
እንደ ግለሰብ እንዲሁም እንደ ቤ/ክርስቲያን እግዚአብሔር ዕድልን እየሰጠን ነው። እንድንዘጋጅ፣ እንድንወጣ እየተናገረን ነው። የተጣላን በእርቅ ወደ አባታችን እንመለስ፣ ነገሮችን መተው ያቃተን በእርሱ ፀጋ ትተን ወደ ጌታ እንቅርብ፣ ያልነቃን አሁን ነቅተን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ።
**የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ ሲመለስ አባቱ ገና ሩቅ ሳለ ሄዶ እንዳቀፈው አባታችን ኢየሱስ የእኛን መመለስ ይጠባበቃል። ሰው ሲጎሳቆል መልኩ መጥፋቱ የታወቀ ቢሆንም ይህ አባት ልጁን አውቆት ነበር። አባታችንም ምንም ውስጥ ብንገባ ያውቀናል፣ ይፈልገናል። ወደቤቱም ወስዶ ከተትረፈረፈው ነገር እያነሳ ለልጁ ሰጠ፣ ደስታ፣ ዝማሬ ሆነ።
**በቤቱ የተተከልን ደግሞ እንደ ፈቃዱ የማያሳፍር ሕይወት እንኑርለት። ጌታ ፊት ለፊት ስንቆም በጎ ታማኝ ባሪያ መባል ይሁንልን!
                     ማጠቃለያ
ጊዜያችንን ከሚበላ፣ ከአባታችን ከኢየሱስ ከሚለየን፣ መዘዝን ከሚያመጣብን ነገር ጌታ ይጠብቀን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

04 Nov, 10:10


የእሑድ አምልኮ ጥቅምት 24 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

04 Nov, 10:06


የእሑድ አምልኮ ጥቅምት 24 - 2017 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የእሑድ መደበኛ አምልኮ ፕሮግራም የፎቶ ምልከታ

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

25 Oct, 12:14


አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን pinned «https://youtu.be/Iw86S7knTXk»

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

25 Oct, 12:14


https://youtu.be/Iw86S7knTXk

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

25 Oct, 06:19


አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን pinned «https://youtu.be/SvRdwu9VAdc»

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Oct, 19:01


አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን pinned «https://youtu.be/SvRdwu9VAdc»

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Oct, 15:25


https://youtu.be/SvRdwu9VAdc

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Oct, 10:18


ጥቅምት/13/17
(October/23/24)
የመልዕክት አቅራቢ: ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ
የመልዕክት ክፍል:(ሐዋ 1:1-4)
ርዕስ: የመጠባበቅ ወራት
መግቢያ: ይህ ሐዋርያት ስራ መፅሃፍ የተፃፈው በሉቃስ ሲሆን የተፃፈው ለቴዎፍሎስ ነው። በዚህ ክፍልም እንደምናየው ሐዋርያት መንፈስቅዱስን በቅርብ እንደሚቀበሉ እስከ ቁጥር አራት ባለው ክፍል ውስጥ ለ ቴዎፍሎስ ይነግረዋል። ከቅባት በፊትም ዝግጅት እንዲያደርግ ይነግረዋል።
ከቅባት በፊት ዝግጅት ያስፈልጋል
1) ለራስ ክብር መሞት: ቴዎፍሎስ በሉቃስ ወንጌል ላይ የከበረ ሰው መሆኑ ተገልጿል። በሐዋሪያት ስራ ላይ ግን ቴዎፍሎስ ሆይ ብሎ ነው የተፃፈው። ለምን? ክብሩን ሁሉ ትቶ ጌታን ስለመረጠ ነው።
2) የእግዚአብሔር ጥማት : ለእግዚአብሔር ቃል ጥማት የሌለው ሰው ሐይልን ለመቀበል ሩቅ ነው። ቴዎፍሎስ በእግዚአብሔር ቃል የተሞላ እና የተጠማ ሰው እንደነበር ታሪክ ይናገራል።
የቅባቱ ባህሪ በኢየሱስ ምሳሌነት
1) ኢየሱስ በድርጊት ታማኝ ነበር: ሉቃስ ለቴዎፍሎስ ታማኝ እንዲሆን ይመክረዋል። ለምን? ጌታ ኢየሱስ በስራው እና በኑሮው ታማኝ ስለነበር ነው።
-እነ ዳንኤልም በዘመናቸው ታማኝ ነበሩ። ዓለምን ንቀው ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር ተገዝቸው ነበር። እኛም በኑሮአችን ታማኝ መሆን አለብን። ቅባት ለጌታ ክብር እንጂ ለሰው ክብር መሆን የለበትም።
2) ኢየሱስ ለቃሉ ታማኝ ነበር: ኢየሱስ ለቃሉ ታማኝ ነበር። ሰዎች በሚሰጡት ምላሽ ላይ የተመሠረተ አልነበረም። በመልካም ዕድሎች ለመሸቃቀጥ አልሞከረም ነገርግን ለቃሉ ታማኝ ነበር። እኛም ቃሉን ስንሰብክ በታማኝነት ሊሆን ይገባል።
3) ኢየሱስ የጀመረውን ፈፅሞ ነበር: ኢየሱስ እስኪያርግ ድረስ ቃሉን ይሰብክ ነበር።(ሞትና ትንሳኤውን)፣ ወንጌልንም ያዳርስ ነበር። ቴዎፍሎስንም እንዲህ ይመክረዋል። እኛም የጀመርነውን የጀመርነውን እስከመጨረሻው እንድንጨርስ ይህ ቃል ይሞግተናል። ወንጌል የመጀመር ሳይሆን የመጨረስ አገልግሎት ነው።
4) ኢየሱስ ተተኪን ያበዛ ነበር: ጌታ አስራ ሁለቱን ደቀ-መዝሙር ሲጠራ ተከታይ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን እርሱን አንዲመስሉ እና እንዲተኩ፣ የጀመረውን የወንጌል ስራ እንዲያስቀጥሉ ነው። እኛም ተተኪን ማዘጋጀት እንዳለብን ጌታ ያስተምረናል። ጌታ ኢየሱስ አይቀናም ነበር። ከእርሱ በላይ ክብር እንዲገለጥ በአገልግሎታቸው ይረዳቸው ነበር። ተራ የነበሩትን ሰዎች ከሰሩ አስቀምጦ ሀያላን አድርጓቸው ነበር። ሉቃስ ቴዎፍሎስን እንዲህ እንዲያደርግ ይመክረው ነበር።
* በዚህ ከተቃኘን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሐይልን እንቀበላለን።
ማጠቃለያ
ጌታን እንድንመስል ሁላችን የተማርነውን ማስተማር ይሁንልን! አሜን!

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Oct, 10:16


የረቡዕ ጥቅምት 13 - 201 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምሕርት መክፈቻ የፎቶ ምልከታ

አያት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

24 Oct, 10:13


የረቡዕ ጥቅምት 13 - 201 ዓ.ም የአያት መካነ ኢየሱስ ማ/ም የረቡዕ መደበኛ ትምሕርት ፕሮግራም የሐዋርያት ሥራ ተከታታይ ትምሕርት መክፈቻ የፎቶ ምልከታ