BU Student's Union @bongausuchannel Channel on Telegram

BU Student's Union

@bongausuchannel


ይህ የቦ/ዩ/ተ/ህ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።በዚህ ቻናል ውስጥ የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የሚመለከት ትምህርታዊና ጠቃሚ መረጃዎች ይለቀቃሉ።
This is the official telegram channel of BUSU. In this channel educational & useful info about Bonga University students will be released.
MORE INFO @Bonga2010bot

BU Student's Union (Amharic)

ዓለም አቀፍ የበአለም ዩኒቨርስቲ ምክር ቤት (BUSU) ተማሪዎችን ለመመለስ እና ጠቃሚ መረጃዎችን እንዴት ማሳየት እርዳም። ይህ የቦ/ዩ/ተ/ህ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ውስጥ የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የሚመለከት ትምህርታዊና ጠቃሚ መረጃዎች ይለቀቃሉ። የቦ/ዩ/ተ/ህ ቻናልን በመረጃ ላይ መልዕክት ማስጠበቅ እና ከዚህ ሆነ በታላቅ ቻናል ተጨማሪ መረጃ መረጃ ላይ ባለው ቦታ @Bonga2010bot ተመልከቱ።

BU Student's Union

08 Feb, 09:19


የቦንጋ ዩንቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ /Remedial/ ተማሪዎችን ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል. . .
======የካቲት 01/2017 ዓ.ም.======
ለ2017ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደቦንጋ ዩንቨርሲቲ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ /Remedial/ ተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል. . .
ምዝገባው ከየካቲት 01 - 02/2017ዓ.ም. የሚቀጥል ሲሆን በዘንድሮው የት/ት ዘመን ከ2974  ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመድበዋል::
በጋራ እንችላለን!!

BU Student's Union

21 Jan, 19:09


በ2017 ዓ.ም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በማሻሻያ (remedial) ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ!!!

በ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የማሻሻያ (remedial) ትምህርታችሁን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የካትቲ 1 እና 2/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን ዋና ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፦
1ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ፤ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቃችሁበትን ትራንስክርፕት እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፤ 6 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶግራፎችን እንዲሁም በግል የምትጠቀሙባቸውን ብርድልብስ፤ አንሶላ፤ የትራስ ልብስ፤ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ፤

2ኛ. ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ካደረገባቸው ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
በጋራ እንችላለን!

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

BU Student's Union

15 Jan, 10:30


ቀን 7/2017ዓ/ም
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ደም ልገሳ ተካሄደ፡፡
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በርካታ የማህበረሰብ ድጋፎችን በማድረግ ለወገን አልኝታነቱን በተለያዩ ጊዜያት እያሳየ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ ድጋፎች መካከል አንዱ ደግሞ በደም አጦት የሚሞቱ ወገኖች ህይወት መታደግ በመሆኑ ከደም ባንክ የሚቀርብለትን ጥያቄ በመመለስ ከተቋሙ ፕሬዚዳንት ጀምሮ በፈቃደኝነት በየጊዜው ደም በመለገስ የወገኞቹን ህይወት በመታደግ ላይ ይገኛል፡፡
በጋራ እንችላለን

BU Student's Union

07 Jan, 08:56


እንኳን አደረሳችሁ

BU Student's Union

29 Nov, 08:19


የዛሬ ኅዳር 20/2017 ዓም የአዲስ ተማሪዎች አቀባበል።

በጋራ እንችላለን!

BU Student's Union

12 Nov, 05:12


https://online.atingi.org/course/view.php?id=5069

BU Student's Union

12 Nov, 05:12


ከዚህ በተጨማሪ በዚህ Link ተዘጋጅቶ የቀረበውን የእሰመኮ ትምህርት ተከታትሎ ለጨረሰ ተመረ ድርጅቱ certificate አዘጋጅተዋል ።

BU Student's Union

12 Nov, 05:12


የ ኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጅማ ከተማ ለተማሪ ህብረትና ሰላም ፎረም አባላት ስልጠና ሰጠ
ቦንጋ ዩኒቨርስቲ ጨምሮ ከአምስት ዩኒቨርስቲዎች ለተወጣጡ የተማሪ ህብረትና ና የሰላም ፎረም አባላት ለተከታታይ አምስት ቀናት የቆየ ስልጠና ከ youth Awareness and Mindset Growth (YAMG) ጋር በመተባበር  በኢትዮጲያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) አማካኝነት ሲሰጥ ቆይቷል።

በስልጠናውም የተሳተፉት የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፣የወራቤ ዩኒቨርስቲ ፣የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፣ ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ና የጅማ ዩኒቨርስቲ  የተማሪዎች ህብረት ና የሰላም ፎረም ተወካዮች ነበሩ።

የ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወረ መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ ሰዎች መብታቸውን እንዲያውቁና የመብት ጥሰት ሲያጋጥማቸው እንዲጠይቁ በማገዝ ላይ ነው።

ይህ ኮሚሽን የሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ እውነትን እያጣራ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ሰዎች የደረሰባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትም ወደዚህ ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ ወደ ሆነ ኮሚሽን በመምጣት የተፈፀመባቸውን በደል በማሳወቅ ፍትህ ማግኘት ይችላሉ።

በቀጣይ ጊዜያት ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ቦንጋ ዩኒቨርስቲው ህብረትና ሰላም ፎረም

ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

BU Student's Union

31 Oct, 16:05


  ቀን 21/02/2017 ዓም
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ፓሪላማ አባላት ለተማሪ ፕሬዝዳንት እና ለሥራ አስፈፃሚ ኃላፍነት ቦታዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች የፅሁፍ ፈተና ስወስዱ
🙏🙏🙏🙏🙏

BU Student's Union

23 Sep, 03:44


እንኳን ለካፊቾ ብሔር ዘመን መለወጫ ማሽቃሬ ባሮ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን !

በካፋ ዞን የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች የካፊቾ የዘመን መለወጫ /ማሽቃሬ ባሮ/ በዓል በየዓመቱ በተለያዩ ፕሮግራሞች ሲከበር ቆይቷል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም የብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶች በማልማት ፣የአካባቢውን ባህልና ሀብት የሚያሳዩ የቅርስ ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት ፣የአካባቢው ን ባህልና እሴት በምርምርና በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል ።

የዩኒቨርስቲው የመማር ማስ/ቴ/ሽግግርና የማህ/አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከለለው አዲሱ እንደገለፁት የዘንድሮውን ዘመን መለወጫ ማሽቃሬ ባሮ ከማህበረሰቡ ጋር ስናከብር በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

1ኛው በካፋ ብሔር አሮጌውን ዓመት አሳልፈን ወደ አዲሱ ዓመት በብሩህ ተስፋ በአንድነት የምንሸጋገርበት የዘመን መለወጫ የቤኔ ሻዲዬ ባሮን የምናከብርበት ፤

2ኛው ብሔራዊው የቡና ሙዚየም እድሳትና ጥገና ሥራዎች ያካሄደበት በመሆኑ ለየት ያደርገዋል።ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ፤

1,ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ከት/ት ሚኒስቴር ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ከ140 በላይ የሥራ መደቦችን ማስፈቀድ ተችሏል ።

2, ደረጃውን የጠበቀ የአጥር ሥራ፣ የቢሮ ቁሳቁስ ማሟላት ሥራ፤
የቡና እና ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞች ተከላ እና የግቢ ውበት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጿል ።

በቀጣይም ለብሔራዊ ሙዚየሙ አስፈላጊውን ግብዓት በሟሟላት ከቡና ጋር የተያያዙ ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ የቡና ምርምር ፣የቡና ቱሪዝም ፣የቡና ግብይትና የቡና ታርክ ሥራዎችን አጠናክሮ በመሥራት ከአካባቢው አልፎ ለሀገር ጥቅም እንዲያበረክት በትኩረት እንደምሰራ ገልጿል።
በመጨረሻም በዚህ ጅምር ሥራና ጥረታችን ከጎናችን በመቆም ለተባበራችሁንና ላበረታታችሁን አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
በጋራ እንችላለን!

BU Student's Union

10 Sep, 07:00


For all current students of Bonga University

We would like to inform you that the entry date of the current students for the 2017 academic year is September 7 and 8, 2017.

Together we can!

BU Student's Union

10 Sep, 06:59


ለቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

የ2017 ትም/ዘመን የነባር ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በጋራ እንችላለን!

BU Student's Union

03 Sep, 22:39


ለNGAT ተፈታኞች በሙሉ፡
==================
በቦንጋ ዩኒቨርስቲ የ2017 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች በነገዉ ዕለት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ICT ዳይሬክቶሬት በመቅረብ username እና password እየወሰዳችሁ ለፈተናዉ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን።
በጋራ እንችላለን!

BU Student's Union

29 Aug, 10:48


ማስታወቂያ

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን ስለማሳወቅ

በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸሁ እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑንን እየገለጽን በየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከ ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር

BU Student's Union

06 Aug, 14:47


ቀን 30/11/2016 ዓ/ም

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ሞዲዮ ጎምበራ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 714,500.00 /ሰባት መቶ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በሚያወጣ ገንዘብ ለመጠለያ አገልግሎት መስሪያ የሚሆን 100 ቆርቆሮ እና ሶስት ፓኮ ሚስማር፣ ለመኝታ አገልግሎት የሚውል 40 የስፖንጅ ፍራሽ፣ ለመጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ አገልግሎት የሚውል ባለ2ሺህ ሊትር ሮቶ፣ በቁጥር 100 የውሃ መጠጫ ኩባያ፣ 100ሊትር የንፅህና መጠበቂያ ፈሳሽ ሳሙና፣ እና ለ120 ወንድና ሴት የሚሆን የተለያዩ አልባሳቶችን እቦታው ድረስ በመውሰድ ለግሷል፡፡

ይህንንም ቁሳቁስ የወሰዱት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ወይንሸት ኃይሌ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ ሀ/ማርያም “ይህን መሰል አደጋ የተከሰተው በዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ተከስቶ የበርካታ ሰዎችን ህይወት እና ንብረት አውድሟል፤ ከነበሩበትም መንደር አፈናቅሏቸዋልና ተስፋ አትቁረጡ፤ እዚህም ሆናችሁ ይህን መሰል ድንገተኛ አደጋ በአካባቢያችንና ብሎም በሀገራችን ዳግም እንዳይከሰት በዚህ ይበቃን እያላችሁ በየእምነታችሁ ፀሎት በማድረግ ፈጣሪያችሁን ለምኑ፤ አይዟችሁ በርቱ፤ ጠንክሩ፤ ፈጣሪ ይረዳናል፤ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ እኛም ከጎናችሁ ነን“ በማለት በዩኒቨርሲቲው የተበረከተላቸውን ድጋፍ ተፈናቃዮቹ ባሉበት በስፍራው ለሚገኙ የወረዳው ተወካዮች እና ለቀበሌው አስተዳደር አስረክበዋል፡፡

በመጨረሻም የወረዳው የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የቀበሌው አስተዳደር እንዲሁም ተፈናቃይ ወገኖቻችን ዩኒቨርሲቲው ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በጋራ እንችላለን!

4,888

subscribers

1,369

photos

20

videos