አሁን የተዘጋጀው አፕሊኬሽን መጻሕፍትን ከማንበብም በላይ ነው ። በውስጡ።
1. ለትምህርት
2. ለአገልግሎት
3. ለስብከተ ወንጌል
4. ትውልድን ለማነጽ
5. ለቅጸላ (ከመደበኛ የአብነት ትምህርት እስከ አቋቋም)
የሚጠቅሙ features ተካተውበታል ።
በአጠቃላይ የትኛውም ክርስቲያን፣ አፕሊኬሽኑን ሲከፍተው #ዛሬ ምን ላንብብ ፣ ምን ልጸልይ ፣ የዛሬዎቹ የቤተ ክርስቲያኗ ምንባባትና አገልግሎቶች (ከቅዳሴ እስከ አቋቋም፣ ስንክሳሩና ሌሎችንም ጨምሮ) ምንድናቸው ወዘተርፈ.... የመሳሰሉትን ብሎ ማስላት ሳይጠበቅበት አፑ በተቀመጠለት የራሱ ቀመር መሠረት ያቀርብልዎታል ። እያንዳንዱ ነገር በቤተ ክርስቲያኗ #የቀናት_ቀመር_መሠረት በዓላትን (በተውሳክ የሚገኙትን እንዲሁም ቋሚ በዓላት)፣ አጽዋማትን (በተውሳክ የሚገኙ እና ቋሚ አጽዋማትን) እንዲሁም የአዘቦት ቀናትን መሠረት አድርገው የተዘጋጁ ናቸው ።
እርስዎ ከፍተው ማንበብ ብቻ ነው ።
ለጊዜው ፍንጭ የሰጠኋችሁ ይመስለኛል ።