Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) @gracecom Channel on Telegram

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

@gracecom


ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ በክርስቶስ የሚለምን አገልግሎት ነው! (2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20)

***
➥ጥያቄና አስተያየት ሲኖርዎ 👉 @Talkinggrace2023
➥የአገልጋዮች ገጽ_ https://t.me/+b--iG0U0LfM4ZGM0
➥የመጻሕፍት ክምችት 👉 https://t.me/gracel2017

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) (Amharic)

ጸጋ ተልዕኮ (Grace Commission) ከእግዚአብሔር የሚደረግ እና በክርስቶስ ምሳሌ የሚለምን አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ ከአገልጋዮችና ሌላ ሰውን እንደሚበሉ ለሚያበላቸውም ታሪክ እና ማስጠበቅን ስለመሆኑ ለመቀየር የሚጠቀሙ የክረምቱን ገጽና የመጻሕፍት ክምችትን ይዞታል። ከዚህ ስለሆነ, በተከታዩ ጠቃሚ ከሆነ ወይም የክለቡ ምንድን ነው እና ምንም እውነታው ከተሰጠለት ስለታወቁ መሰረታዊ መረጃ ድጋፍ እንደሚሆን እና መንግሥት ክረምቱን ለማስጠበቅ የምንጠቀሙበትን ወርሃዊ በመጠቀም የምንጠቀምበትን እናቴም ልማትና የሰዉን እምነት ያድምማል። አገልግሎትን መልኩ ራሷን መዝገበ በማሳጥ ከሚፈልገኝ አገልግሎቶች መታጠብ ከትክክለኛነቶቻችሁ መቀነስ እና ማንበር በማበር ማለፍ ናቸሁ።

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

15 Nov, 04:06


በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ስናልፍ ዓይኖቻችን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ እንዲቆዩ እንፍቀድ!!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

13 Nov, 16:59


ያለፈውን እንኳን ጉዳታችንን ድል እንኳን ቢሆን እየረሳን፣ አሁን የያዝነውን እንዳልያዝነው እየቆጠርን ... በፊታችን ያለውን ለመያዝ እንዘርጋ! በፊታችን ባሉት ነገሮች ላይ እናተኩር! በክብር ያለውን ኢየሱስን የሕይወታችን ግብ እናድርግ! የምናደርገውን ሁሉ ከርሱ አንፃር እናድርግ! ለኢየሱስ እንንቃ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

12 Nov, 08:29


<<ክርስቶስ እንዲከብርና እንዲመሰገን የሚፈልግ ሰው የሚከብርበትን መንገድ መምረጥ አይችልም።>> ምኒልክ አስፋው

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

11 Nov, 17:59


Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) pinned «<<ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥…»

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

11 Nov, 17:58


<<ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።>> 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥26_31

አንክሮ!?

ሞኝ ነገርን ማን ይመርጣል? ደካማን ነገር ማን ይመርጣል? ምናምንቴ ነገርን ማን ይመርጣል? እግዚአብሔር። ምርጫ ከሆነ የተሻለውን ነው። እግዚአብሔር ዋጋ የሌለውን መረጠ። ከርሱ በቀር ይህን ማድረግ የቻለ የለም!

ወገኖች ሆይ፣ መጠራታችሁን ተመልከቱ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

10 Nov, 19:35


ከኢየሱስ ጋራ ሩቅ ለመጓዝ ትልቁ መፍትሔ በርሱ መታመን እና መደገፍ ነው! እንደገፈው፣ ለሰማያዊ መንግሥቱ ይጠብቀናል! _ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥18

ተረፈ አበራ

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

10 Nov, 06:21


አንድ አማኝ ወደ ኋላ ሲያፈገፍግ፣ ከማናችንም በላይ የሚያዝነው እግዚአብሔር ነው! ከሁሉም በላይ የሚጎዳው ደግሞ ግለ-ሰቡ ነው!
👇
“... ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።” ዕብ. 10፥38

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

09 Nov, 20:31


Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) pinned «አንድ ሰው፣ #በኢየሱስ #ካመነ #በኋላ [ጸንቶ እንዲቀጥል] ምን ማድረግ ይኖርበታል? ሰሞኑን እህታችን ሐና መርዓዊ #በኒቆዲሞስ #ሾው ባደረገችው ቆይታ፣ ወደኋላ ስለተመለሱ አገልጋዮች እና ምእመናን ጥያቄ ቀርቦላት ነበረ። ምላሿን ደጋግሜ ሰማኹት። በውስጡ በርካታ መርሆች (Principles) እንዳሉት ተረዳኹ። ይጠቅማል ብዬ ስላመንኹ፣ በዚህ መልኩ አቅርቤዋለኹ። [የእህታችንን ዐሳብ፣ በትምህርተ ጥቅስ…»

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

07 Nov, 06:52


ድነት (ጽድቅ) በሰው ጥረት እና ጥሩነት እንደማይገኝ ተረድተናል!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

07 Nov, 05:47


https://youtu.be/z0jw0AXg8tY?si=__g1d79zSbjrxE8n

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

05 Nov, 16:57


https://youtu.be/NyIcLLRQauU?si=nSN25Mw_1aOjmO8M

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

05 Nov, 07:06


ይህ ዘመን የእውቀት ዘመን ይመስላል። ያሉትን የመጻሕፍት ክምችት እንኳን አንብበን ቆጥረን የማንጨርሳቸው ይመስለኛል። የተፈጠሩትን እይታዎች (School of thought) አጥንተንም ሆነ አስታርቀን አንጨርስም! እየገባኝ ያለው ኢየሱስን በማመን እና በማወቅ ላይ ማተኮር እንዳለብን ነው። ለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ መስጠት ያለብን መጽሐፍ ቅዱሱን ለማንበብ ነው። በሌሎች ነገሮች በመያዛችን ምክንያት ኢየሱስን መማር ባለብን መጠን እንዳልተማርነው አያለሁ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

01 Nov, 16:42


https://youtu.be/JXJ24EvPLGs?si=ZVYonH8gdjcSj1e7

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

31 Oct, 21:32


ሌሎችን ብዙ የሚያገለግሉ አገልጋዮች፣ ራሳቸውን ብዙ ያገለገሉ (ያዘጋጁ) አገልጋዮች ናቸው። Quality አገልግሎት ያላቸው፣ በጌታ እግር ሥር የቆዩ ናቸው። ሐዋርያት፣ ከጌታ ሥር ሆነው የተማሩት ከ3 ዓመታት በላይ ነው። ጳውሎስ፣ ከጌታ የተማረው ከ14 ዓመታት በላይ ነበረ። ለዚህ ነው፣ በቃልም በኑሮም ፍሬያማ የነበሩት።

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

31 Oct, 02:14


የአዳሹ (Reformer) የማርቲን ሉተር አንዳንድ አስተምህሮዎች ተሐድሶ እንደ ተደረገባቸው ያውቃሉ? የተሐድሶ ምንጭና መነሻ፣ ሂደት መሪና ተሰሚ ባለ ሥልጣን የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። አሁንም ለወንጌላውያንን ሥር ነቀል ተሐድሶ ያስፈልጋል!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

30 Oct, 04:35


ትምህርቶች፣ ስብከት፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎት፣ ዝማሬ፣ የሕይወት መርሕና ሥርዓት፣ አስተዳደር፣ ... የሚቀዱት ከአስተምህሮ (Doctrine) ነው!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

29 Oct, 04:22


ኢየሱስ የሚያስይዝህም የሚያስጥልህም ነገር አለ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

28 Oct, 03:45


ሉተር በቃሉ ታድሶ፣ አዳሽ ቢሆንም፣ የተሐድሶ መለኪያ (standard) አይደለም። የማያረጅ አዳሽ፣ የተሐድሶ ጠንሳሽና ቀያሽ፣ የተሐድሶ ሂደት ፊታውራሪና መሪ፣ የለውጡ መለኪያ እና መለወጫ መሣሪያ ራሱ ኢየሱስ ነው!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

27 Oct, 04:06


ሮሜና ገላትያ፣ አዳሾቹን (Reformers) ያደሱ (የሐዋርያው ጳውሎስ) ደብዳቤዎች ናቸው!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

26 Oct, 05:37


ኹለንተናዊ ተሐድሶ፣ ለኹሉም የክርስትና አብያተ እምነት ያስፈልጋል! ምክንያቱም ኢየሱስ እና እውነቱ፣ አንዳንዶቹ ጋራ ጠፍቷል፤ ሌሎቹ ጋራ ደግሞ ተቀይጧል ወይም ደብዝዟል!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

25 Oct, 19:59


Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) pinned «አሁን ሥራ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ጽድቅ ብቻ ነው። የሚገኘውም ኢየሱስን በማመን ብቻ ነው።»

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

25 Oct, 12:14


አሁን ሥራ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ጽድቅ ብቻ ነው። የሚገኘውም ኢየሱስን በማመን ብቻ ነው።

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

24 Oct, 13:48


Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) pinned «ተሐድሶ ወኔ አይደለም! ተሐድሶ፣ ቁጭ ብለን የእግዚአብሔርን ቃል በመመርመር፣ ሳናቋርጥ በመጸለይ፣ ርስ በርሳችን ያለንን ኅብረት በማጠንከር እና ለተረዳነው እውነት በመታዘዝ የሚመጣ #ሥር ነቀል #ለውጥ ነው!»

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

24 Oct, 12:35


ተሐድሶ ወኔ አይደለም!

ተሐድሶ፣ ቁጭ ብለን የእግዚአብሔርን ቃል በመመርመር፣ ሳናቋርጥ በመጸለይ፣ ርስ በርሳችን ያለንን ኅብረት በማጠንከር እና ለተረዳነው እውነት በመታዘዝ የሚመጣ #ሥር ነቀል #ለውጥ ነው!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

24 Oct, 02:31


ተሐድሶ ልባዊ እንጂ አፋዊ አይደለም!

መታደስ ውስጣዊ ነው! ተሐድሶ ከውስጥ ወደ ውጪ የሚገለጥ ለውጥ ነው! (ሮሜ 12፥2 ኤፌሶን 3፥16-17)

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

23 Oct, 08:46


ተሐድሶ ግላዊ ነው!

ተሐድሶ ለሌሎች የምንተወው ወይም ቀን የምንቀጥርለት ጉዳይ አይደለም! ተሐድሶ ለእያንዳንዳችን ያስፈልገናል! ስለዚህ ተሐድሶን ለራሳችን እናስበው! ተሐድሶን ከራሳችን እንጀምረው! ተሐድሶን ወይም መታደስን ለራሳችን ካላሰብነው ለሌሎች መታደስ እየሠራን እኛን መንፈሳዊ ርጅና ሊጫጫነን ይችላል! ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ መኖራችንን እንመርምር!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

21 Oct, 10:53


Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ) pinned «ሐሰተኞችን መቃወም ብቻውን በቂ አይደለም፤ እውነተኞችን መደገፍ ያስፈልጋል! የስህተትን አስተምህሮ ማጋለጥ ብቻውን በቂ አይደለም፤ እውነትን በፍቅር መግለጥ ያስፈልጋል!»

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

21 Oct, 08:22


ሐሰተኞችን መቃወም ብቻውን በቂ አይደለም፤ እውነተኞችን መደገፍ ያስፈልጋል! የስህተትን አስተምህሮ ማጋለጥ ብቻውን በቂ አይደለም፤ እውነትን በፍቅር መግለጥ ያስፈልጋል!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

21 Oct, 01:22


"የልጁን የኢየሱስን ሕይወት ማጥናት፣ ለእኔ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ ስጦታ ነው።"

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

20 Oct, 06:24


<<ለሕዝብህ እረኛ ልሆን እችላለሁ። ለአንተ ግን፣ አንተ ከምታሰማራቸው በጎች አንዱ ነኝ። ሕዝብህን ላስተምር እችላለሁ። ለአንተ ግን፣ ከምታስተምራቸው ደቀ መዛሙርት አንዱ ነኝ።>> "አቡነ" ሺኖዳ ሣልሳዊ

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

19 Oct, 05:49


እኔ_ነት በሕይወታችን በያዘው ስፍራ መጠን ተመርዘናል፤ እስረኞች ሆነናል። መገለጫው፣ ከራሳችን አልፈን የሌሎች ሕይወት "እኔ" ባይ መሆን ያምረናል!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

15 Oct, 06:49


<<መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ወሳኝ ግብ አለው፤ ርሱም #ድኅነት ነው።>> ጆን ስቶት

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

14 Oct, 18:58


"መሪዎች ስንሆን የእግዚአብሔር ሰዎች ነን እንጂ የሰዎች እግዚአብሔሮች አይደለንም" ለማ ደገፉ
👇
https://youtu.be/x8QDUGo3swA?si=QaJlsIhHoTq9aApU

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

14 Oct, 06:57


<<የክርስቶስ ማንነት ለሰው ልጆች ድኅነት ከሠራው ሥራ ተለይቶ እንዴት ይጠናል?>>  የድኅነት [የመስቀል] ሥራውስ እንዴት ከክርስቶስ ማንነት ተለይቶ ይጠናል?

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

13 Oct, 17:41


https://youtu.be/-bMg3QOyNZc?si=xG_tyGUNZHLJhKMw

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

11 Oct, 05:38


#ሉተር ስለ #ጽድቅ የነበረው አቋም፦

• ጽድቅ የሚገኘው በእምነት ብቻ ነው። (Justification by Faith)
• በእምነት የተገኘው ጽድቅ፣ ሂደታዊ ሳይሆን ቅጽበታዊ ነው።
• በእምነት የተገኘው ጽድቅ፣ በሥራ የምናሟላው አይደለም። በራሱ ሙሉ ወይም ፍጹም ነው።

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

10 Oct, 06:54


ዙሪያችሁን ኢየሱስን በሚወዱት ሰዎች እጠሩ! የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ በሚገዳቸው አገልጋዮች ተከበቡ! ለጥሪያቸውና ለመንፈሳዊ ነገር የነቃ መንፈስ፣ የጋለ ስሜት፣ የሰለጠነ አእምሮ ባላቸው ወገኖች ዙሪያ ኑሩ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

09 Oct, 12:44


ጅምር ቤትህ ነኝ፤ በጀመረኝ ጸጋህ ጨርሰኝ!

Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

07 Oct, 11:50


መዝሙር ማዘለል ብቻ ሳይሆን ማንበርከክ፣ ማስጮህ ብቻ ሳይሆን አርምሞ ማምጣት አለበት! የአስቴር አበበ መዝሙር ውስጥ ይህን የመዝሙር ውበት አግኝቻለሁ!