Ustaz yassin Nuru®™ @yasin_nuru_channel Channel on Telegram

Ustaz yassin Nuru®

@yasin_nuru_channel


ይህ ይፋዊ የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ተለግራም ገፅ ነዉ

Ustaz Yassin Nuru®™ (Amharic)

የአሜሪካን እንደገና የኢትዮጵያን ምስል ገለጻል! በመሆኑም ይህ ይፋዊ የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ተለግራም ገፅ በተወሰነ አገልግሎት የሚሰጡበት ቦታ ነው። ይህ ቦታ በዓለም ቆሞላ የበረታ መሰረትን በተጨማሪም ትምህርት በሚገኙበት እለት ይጠቀሙና የሚፈልግ ነው። በተጨማሪም ዘገባ እንኳን ወደ Ustaz Yassin Nuru®™ በጣም ሂደታ ሰጡ! የኡስታዝ ያሲን ኑሩ የሰለቸንም እናቶችን በእኛ ላይ ለምንድን እናማክራለን? ሌላው በመሆኑ እኛም ባህሪያት አገልግሎት ለመተናተን የምናመልጥበትን ማንኛውንም ትምህርት የሚገኘውን ታሪካቸውን በዘመን ከባህልና ምርመርት ለመቀየን ተጠቃሚ ነን። እናም በተጨማሪም በተደጋጋሚነት የUstaz Yassin Nuru®™ ገፅ በታሪኩ የሚሰጥለትን የአስተዳደር መረጃና ማግኘት እናም ከተያዙ አገልግሎታቸው በተጨማሪም በእርዳታ ይስጡ።

Ustaz yassin Nuru®

19 Aug, 21:25


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

Ustaz yassin Nuru®

08 Jan, 10:33


የታሰረ ተፈትቶ ከቤተሰቡ ጋር ሲቀላቀል ደስ ይላል።
ወንድሜ ጀውሐር፡ሀምዛ፡እስከንደር....ለሀገር በቃችሁ።
ስንክሳፘ ለበዛባት ሀገራችን አድስ ምዕራፍ ትሆኗትና ተራማጅ አጀንዳ ይዛችሁ ትመጡ ዘንድ ተስፋየ ነው።
ድሮም እስር ለሀሳብ ልዩነት መፍትሄ ሆኖ አያቅም።ጅምሩ አውንታዊ ውጤት ያመጣ ዘንድ ምኞቴ ነው።

አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!!

Ustaz yassin Nuru®

16 Dec, 14:30


ሚዛናዊ ህይዎትን ምራ

Ustaz yassin Nuru®

16 Aug, 20:11


ኢትዮጵያን በፆማችን እናስባት!!
—————-//————-
ፆመኛ እስከሚያፈጥር ድረስ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት አለው ነብዬ ሙሐመድ ( ሰላም በርሳቸው ይስፈን)!!
የአንድ ዓመት ውንጀል የሚያስምረው የአሹራ ፆም ከፊት-ለፊታችን ሲሆን ዘጠነኛውን ቀን መፆም ደግሞ የመልዕክተኛው ፈለግ( ሱና ) ነው::
ታድያ በነዚህ በተከበሩ ቀናት በዱዓ እንበረታ ዘንድ ማስታወስ ወደድኩ!!

Ustaz yassin Nuru®

19 Jul, 13:30


ለመላው ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አለን!
የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቀ::
አልሀምዱሊላህ

Ustaz yassin Nuru®

11 Jul, 04:14


Congratulations!! I know you deserve it.
መልካሙ ጎልብቶ: የተዛባው ተስተካክሎ የተሻለች ሀገር እንፈጥር ዘንድ
ምኞቴ ነው!!

Ustaz yassin Nuru®

12 May, 09:05


Eid Mubarak

Ustaz yassin Nuru®

11 May, 09:48


ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
ለአሕመዲን ጀበል፤ ለቤተሰቦቹና ለመላው ሙስሊም ማሕብረሰብ መጽናናትን እየተመኘን፤ አባታችንን አሏህ(ሱ.ወ) በጀነት እንዲያኖራቸው ዱዐችን ነው።
ﻟﻠﻪ ﻣﺎ ﺃﻋﻄﻰ ﻭﻟﻪ ﻣﺎﺃﺧﺬ ﻭﻛﻞ ﺷﻲﺀﻋﻨﺪﻩ ﺑﻤﻘﺪﺍﺭ ﺇﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺇﻧﺎ ﺇﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮ ﻥ
ﻏﻐﻔﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻪ ﻭﺃﺳﻜﻨﻪ ﻓﺴﻴﺢ ﺟﻨﺘﻪ ﻭﺭﺯﻕ ﺃﻫﻠﻪ ﺍﻟﺼﺒﺮ ﻭﺍﻟﺴﻠﻮﺍﻥ ﻭﺃﻣﺔﺍﻹﺳﻼﻣﻴﺔ

Ustaz yassin Nuru®

10 May, 10:47


ይቅርታ እጠይቃለሁ!
#Ethiopia | "ትላንት ለተፈጠረው ነገር በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ ።" - ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ረመዳን ከሪም!
ዉድ የከተማችን ሙስሊም ወገኖቻችን ፣ የኢትዮጵያ አደባባዮች የሁሉም ኢትዮጵያዊን ናቸው!
አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ ፤ አደባባይ "የኔ ፣ ያንተ" ብሎ አይጣላም፡፡
ትላንት በጎዳናዎች ላይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የአፍጥር ስነስርአት ተስተጓጉሏል።
ይህ የሆነው ወቅታዊ የደህንነት እና የጸጥታ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የቦታው ስፋት እና ርዝመት ዉስን እንዲሆን ባቀረብነው ሀሳብ አዘጋጅ ኮሚቴው ባለማመኑ ብቻ መሆኑ ግልጽ እንዲሆን እንፈልጋለን ።
የትላንት ምሽት ሁኔታ የሁላችንም ሰላም እና ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊ ጥንቃቄ ለማድረግ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ለማድረግ ብቻ የተንቀሳቀሱት እንጂ በፍፁም የአፍጥር ክልከላ አይደለም ። በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች የአፍጥር ስነስርዓት መካሄዱን አይተናል።
ይሁን እንጂ አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ይህን ጉዳይ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመዉሰድ በማህበራዊ ሚዲያ ሊያራግቡት ሞክረዋል።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰማውን ቅሬታ የገለጸበት መንገድ ጨዋነት የተሞላበት እና ሰላማዊ መሆኑ ሊደነቅ ይገባል።
ትላንት ለተፈጠረው ነገር በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ።
በድጋሜ ረመዳን ከሪም!
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ

Ustaz yassin Nuru®

10 May, 10:16


ሁሉም አንድ አይደሉም!!
በርካታ ክርስቲያ ወገኖቻችን ለአፍጥር ፕሮግራሙ ያሳያችሁትን ድጋፍ አደንቃለሁ።
በተለያዩ ከፍለ–ሀገራት የአፍጥር ማዕድ አብራችሁን ለተቋደሳችሁ የእምነቱ መምህራን ምስጋናየ የላቀ ነው።
እጅግ በጣም ጥቂቶች በሰሩት ስህተት ሁሉንም አንድ ቅርጫ ውስጥ እምንከት ኢ–ፍትሐዊ እንዳንሆን ቁርአን በአንክሮ ያዘናል ... "ለይሱ ሰዎአ" በማለት።
የእኒህን ፍቅር የሆኑ አባት አስተምህሮ ስታይ ለቁርአኑ መልዕክት እማኝ ታገኛለህ !!።
በአብሮነታችን ኢትዮጰያ ዳግም ትፈካለች!!

Ustaz yassin Nuru®

10 May, 05:03


አስር እጥፍ!!
የትናንትናው የአፍጥር ታዳሚ ቁጥር 100 ሽ እንደሚደርስ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ይህ ህዝብ ባሰበውና በታቀደው መልኩ በሰላም አፍጥሮ፣ ለሀገሩ ሰላም ፀልዮ ፣ ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር ማዕድ ተካፍሎ ቢጠናቀቅ ለኢትዮጰያ ደማቅ ታሪክ ይሆን ነበር።
ይህን ታሪካዊ ክስተት እንዲደናቀፍ እጅ የነበራቸው ሁሉ ተጠያቂ ሲሆኑ ማየት እንሻለን።
በ Hayat Regency በኩል ከነበረው በርካታ ምዕመናን ጋር አብረን አፍጥረን ከኔ ጋር ሰግደው በሰላም ተለያይተናል።
አዛኙ ጌታች ሀገራችንን ሰላም ያድርጋት!!

Ustaz yassin Nuru®

09 May, 15:08


እንዲህ እንደዋዛ...
ዛሬ ሮመዳን ከገባ 27 ቀን ሞላው?!! ጊዜው እንዴት ይሮጣል።
በወጉ ሳንጾመው፣ በአግባቡ ቁርዓኑን ሳንቀራው፣ ከታሀጁድ ሶላት ጋር በደምብ ሳንላመድ... እውነትም " አያመን መዕዱዳት– የተቆጠሩ ቀናት" ።
እነዚህ ቀናቶች መች ከሮመዳን ብቻ ከእድሜያችንም ነው አጉድለው የሄዱት።
የሰው ልጅ የቀናት ጥርቅም ነው ። በየቀኑ እየጉደለ ይሄዳል። ልክ battery full እንደሆነ ሞባይል በቀን የአገልግሎት ውሎው እየጎደለ እንደሚደሄው ሁሉ።
ጊዜ ህይዎት ነው ወርቅ አይደለም። ወርቅን በገንዘብ ልትገዛው ትችላለህ፣ የዓለምን ንብረት ሁሉ ኢንቨስት ብታደርግ ግን አንድን ቀን መግዛት አትችልም።
እዲህ እንደዎዛ ህይዎት ተጠንጥና ወደ ማይቀረው ጉዞ እንሄዳለን። አሰተዎይ ማለት ታድያ በሰው ልጆች ውስጥ ደማቅ አሻራ ትቶ ያለፈ ነው። የበጎ አሰተወፅኦ ፋናው አህጉራትን አቋርጦ ያበራለት ነው።ለማህበረሰቡ የመልካም ነገር ተምሳሎት ሆና ታሪክ ማህደር ላይ የሰፈረ ነው።
" His life is done, but his legacy is not" የተባለለት ነው።
ቀሪውን ቀናቶች አላህ ይባርክልን
# ረበና ተቀበል ሚንና ኢነከ አንተ ሰሚዑል ዐሊም።
ወቱብ ዐለይና ኢነከ አንተ ተዋቡ ረሒም♡

Ustaz yassin Nuru®

08 May, 11:40


እንዲህ እንደዋዛ...
ዛሬ ሮመዳን ከገባ 26 ቀን ሞላው?!! ጊዜው እንዴት ይሮጣል።
በወጉ ሳንጾመው፣ በአግባቡ ቁርዓኑን ሳንቀራው፣ ከታሀጁድ ሶላት ጋር በደምብ ሳንላመድ... እውነትም " አያመን መዕዱዳት– የተቆጠሩ ቀናት" ።
እነዚህ ቀናቶች መች ከሮመዳን ብቻ ከእድሜያችንም ነው አጉድለው የሄዱት።
የሰው ልጅ የቀናት ጥርቅም ነው ። በየቀኑ እየጉደለ ይሄዳል። ልክ battery full እንደሆነ ሞባይል በቀን የአገልግሎት ውሎው እየጎደለ እንደሚደሄው ሁሉ።
ጊዜ ህይዎት ነው ወርቅ አይደለም። ወርቅን በገንዘብ ልትገዛው ትችላለህ፣ የዓለምን ንብረት ሁሉ ኢንቨስት ብታደርግ ግን አንድን ቀን መግዛት አትችልም።
እዲህ እንደዎዛ ይህዎት ተጠንጥና ወደ ማይቀረው ጉዞ እንሄዳለን። አሰተዎይ ማለት ታድያ በሰው ልጆች ውስጥ ደማቅ አሻራ ትቶ ያለፈ ነው። የበጎ አሰተወፅኦ ፋናው አህጉራትን አቋርጦ ያበራለት ነው።ለማህበረሰቡ የመልካም ነገር ተምሳሎት ሆና ታሪክ ማህደር ላይ የሰፈረ ነው።
" His life is done, but his legacy is not" የተባለለት ነው።
ቀሪውን ቀናቶች አላህ ይባርክልን
# ረበና ተቀበል ሚንና ኢነከ አንተ ሰሚዑል ዐሊም።
ወቱብ ዐለይና ኢነከ አንተ ተዋቡ ረሒም♡

Ustaz yassin Nuru®

15 Jan, 10:41


የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!! የአላህ እዝነትና ሰላም በእርስዎ ላይ ይስፈን!!

Ustaz yassin Nuru®

11 Jan, 14:09


ስልጠናዎቻችን
ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትሮችና 65 ከሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሊደርሽፕ ፅንሰ ሀሳብ ዙርያ በኢሊሊ ሆቴል ቆይታ አድርገናል።
የወሰዷቸው ስልጠናዎች ተቋሙን በአዲስ መልክ ውጤታማ ለማድረግ የተጀመርውን የተሀድሶ ጉዞ ያሳልጣል ተብሎ የታሰባል!!
የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ አግኘቷል::
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት በ2013 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ትግባራት ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ኮሚቴ አባላት ጋር ገምግሟል፡፡
የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ገቢው የተገኘው ከ4112 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ፣26.97 ቶን ታንታለም፣1625 ኪሎግራም ጥሬ ኦፓል 37.8 ኪ.ግ እሴት የተጨመረበት ኦፓል እና 2123ኪ.ግ ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡ ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ማዕድናት 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡
በዘርፉ ለ48,785 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አቅጣጫዎች ተቀምጧል፡፡

2,012

subscribers

58

photos

5

videos